Thursday, March 13, 2014

ጌታ በአጠገቤ ቆሞ …..፡፡

ጌታ በአጠገቤ ቆሞ..፡፡
                                                         ከፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ
እንግልዛዊው የነገረ መለኮት ሰው ጆፌሪ ኪንግ እግዚአብሔር አብንወልድና መንፈስ ቅዱስን  በሦስት ወፎች ይመስላቸዋል፡፡  እንደ ኪንግ አገላለጽ እግዚአብሔር አብ እንደ ንሥር ሲሆን እርሱ በንጉሥነቱ የእኛን ሕይወት ይመራዋል፣ካለንበት አስቸጋሪ ሁኔታም ነጥቆ ያወጣናል( ዘጸ.194፣ዘዳ.3211፣ኢሳያይስ 403)፡፡ እግዚአብሔር ወልድ በአዲስ ኪዳን በዶሮ የተመሰለ ሲሆን ይህም የሚያመለክተው ዶሮ ጫጩቶን በክንፎቿ እንደምትሰበስባቸው ጌታ ኢየሱስም እኛን ከማናቸውም የሰይጣን ጥቃት እንደሚጠብቀንና እንደሚከለክለን ነው( ማቴ. 2337)፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ የተመሰለ ሲሆን እርሱ ለአገልግሎት ኃይልን ፣ ለኑሮአችን ሰላምንና ለክርስትና ሕይወታችን ንጽሕናን ለመስጠት በእኛ ላይ እንደ ርግብ ይመጣል ይወርዳል፣ ከእኛም ጋር ለዘላለም ይኖራል(ማቴ. 316)፡፡ ጆፌሪ ኪንግ ስለ አሀዱ ስሉስ ያቀረበው ይህ አገላለጽ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ጥበቃና ጥንቃቄ ፍንትው አድርጎ ከሚያሳዩን ምሳሌያዊ ትምህርቶች አንዱ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ባሕሪያት ከሆኑት አንዱ እርሱ ለሕዝቡ ያለው ጥበቃና ጥንቃቄ ነው፡፡ ከአምላካችን ጋር በምንኖርበት ወቅት ልዩ የሆነ ዋስትና ይሰማናል ምክንያቱም ያለነው አምባችን በሆነው በእግዚአብሔር ውስጥ ነውና፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የእርሱን ክብርና ጥበቃ የምንፈልግ አምባችን የሆነውን እርሱን እንድንወድ አድርጎ ነው የፈጠረን፡፡ እርሱ ማምለጫቸችንና መሸሸጊያችን ሊሆን ወድዶ ወደ እኛ ተጠግቷል፡፡ እንደ ክርስቲያኖች እያንዳንዳችን የምንኖረው በዚህ ዓለም ስለሆነ በሕይወችን መከራንና ሀዘንን የምንጋፈጥ ብንሆንም እግዚአብሔር ግን ከማናቸውም ክፉ ሁኔታዎች ይጠብቀናል ፣ከጥቃትም ሁሉ ይከልለናል፡፡
ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም በዘመኑ ብቸኝነት፣ስድብ፣ ስደት፣ እሥራትና መደብደብ በደረሰበት ወቅት እግዚአብሔር ከዚያ ሁሉ ሲታደገው አይቶታል፡፡ ጳውሎስ እግዚአብሔር በመከራና በችግር ጊዜ ሰውን እንደሚረዳና ከክፉ ሁሉ እንደሚከልል ለአድማጮቹ ከሚያስተምራቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፈለ- ንባቦች አንዱ በ2 ጢሞቴዎስ 49-18 ድረስ ያለው ነው፡፡ ቃሉ እንዲህ ይነበባል፡
በቶሎ ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ ፤ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና ፣ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአልና፣ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፡፡ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው፡፡ ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ላክሁት፡፡ ስትመጣ በጢሮአዳ ከአግሪጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጸሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጣፉትን አምጠጣልኝ፡፡ የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ ፤ ጌታ እንደሥራው ይመልስለታል፡፡ አንተም ከእርሱ ተጠበቅ፤ የምናገረውን እጅግ ተቀውሞአልና፡፡ በፊተኛው ሙግቴ አንድ ስንኳ አልደደረሰልኝም፣ ሁሉም ተውኝ እንጂ፣ ይህንን አይቁጠርባቸው፡፡ ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዝብም ሁሉ እንዲሰሙት ፣ ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፤ከአንበሳም አፍ ዳንሁ፡፡ ጌታ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድናነል፡፡ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፡ ለእርሱ ከዘላላም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን አሜን፡፡

ይህ የንባብ ክፍል ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሕይወቱ መጨረሻ ላይ በወንጌል ለወለደው ልጁ ለጢሞቴዎስ የጸፈው የስንብት መልእክት ነው፡፡ ጊዜው ኔሮ የተባለ ንጉሥ በሮም ባሉ አማኞች ሁሉ ላይ ከባድ መከራና ስቃይ ያደረሰበትና ጳውሎስም እንደ አደገኛ ወንጀለኛ በሰንሰለት ታሥሮ በሮም እሥር ቤት ሆኖ ሞትን እየተጠባባቀ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ሐዋሪያው ከደረሰበት እንግልትና አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተነሳ እንደ እስጥፋኖስ ለወንጌል ሲል ሰማዕት ሊሆን ራሱን አዘጋጅቷል፡፡ ከዚህም የተነሳ ይህን ደብዳቤ ለጢሞቴዎስ እንደጻፈ ወዲያው ሊሞት እንደሚችል አድርጎ ራሱን እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት እግዚአብሔር በቀደሙት የአገልግሎቱ ጉዞዎች እንዴት እንዳዳነውና እንዴት እንዳበረታው በዝርዝር ይናገራል፡፡
እንግዲህ ይህ ሰው በአስቸጋሪ ሁኔታ ማለትም ሞት የመሰለ ነገር ወደ እርሱ እየመጣ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ነበረ፡፡ በእኛም ሕይወት በአንድም ሆነ በሌላ መከራና ችግር እንዲሁም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚገጥሙን ጊዜ አለ፡፡ ይሁን እንጂ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ጌታ ሳይተወን በአጠገባችን እንደሚቆምና እንደሚያበረታን ትልቅ መልእክት ያስተላልፍልናል፡፡ አማኞች ፣ አገልጋዮች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ እንዲሁም ለክርስቶስ እውነት እየኖርኩ ባለሁበት ዘመን ሁሉ የጌታ የኢየሱስን አዳኝነት ለዓለም ሁሉ አውጃለሁ፤ ለእርሱ ክብር እኖራለሁ የሚሉ ሁሉ እንደሚሰደዱ፤ ነገር ግን ጌታ ከሁለላችን ጎን በመቆም እንደሚያበረታን ይህ ክፍል ያስተምረናል፡፡ ባነበብነው ክፍል ሦስት ብርቱዎች ተጠቅሰዋል፡፡ አንደኛው አንበሳ ነው፡፡ አንበሳ በብርታቱ የሚታወቅ የአውሬ ዘር ነው፡፡ አንበሳ በብርታት ብቻ ሳይሆን በጭካኔውም የሚታወቅ መሆኑን ለመግለጽ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ሰይጣንን ከሚያገሳ አንበሳ ጋር አስመስሎታል(1 ጴጥ57-8)፡፡
ሁለተኛው ብርቱ ብርቱና ጨካኝ ከሆነ አንበሳ አፍ አምልጦ የሚወጣ አማኝ ነው፡፡ አማኞች የሚጋፈጡትና የሚታገሉት በአንበሳ ከሚመሰለው ብርቱና ጨካኝ ከሆነው ባለጋራችን ከዲያብሎስ ጋር እንዲሁም ከዚሁ ዓለም ክፉ አሠራር ጋር ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጌታው የሚበረታ አማኝ ሁል ጊዜ ያሸንፋል ፣የአንበሳውንም ራስ ይቀጠቅጣል እንጂ አይሸነፍም(መሳፍንት 145-6፣ ሉቃስ 10 17-19)፡፡ ሦስተኛው ብርቱ አማኞችን ከአንበሳው ይልቅ ብርቱ የሚያደርጋቸው ከብርቱዎች ሁሉ ብርቱ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ አማኞች የብርታታችን ምንጩ አንበሳ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ነው( ራዕይ 55)፡፡  
ስለዚህ ጳውሎስ ጌታ በአጠገቤ ቆሞ ብርቱና ጨካኝ ከሆነው አንበሳ አፍ እንድድን አበረታኝ ይላል፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ባለ ሁኔታ ውስጥ እንደሚያበረታን ከክፍሉ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
1. በሰዎች በተጣልንና በተገለልን ጊዜ ጌታ በአጠገባችን ቆ(.9-10)፡፡
መከራ ሲደርስብንና በችግር ስንጠቃ ሁኔታዎች ንደ ሰላሙ ጊዜ ሆነው አይቀጥሉም፡፡ ሰዎችን የምናጣው እጅግ በጣም አስፈላጊ በሚሆኑት ሰዓትና ደቂቃ ነው፡፡ ያም ጊዜ የመከራና የችግር ጊዜ ነው፡፡ እኛ አማኞች በተለይም አገልጋዮች ብዙውን ጊዜ በአገልግሎት አጋሮቻችንና በሌሎች ሰዎች ተስፋ የምደርግባቸው ጊዜያቶች አሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ታማኞች ሆነው በችግር ጊዜያቶች ከጎናችን ሆነው ሲያጽናኑን አይተናቸዋል፡፡ ኖም አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች ከእነርሱም አቅም ያልፍና ለእኛ አስፈላጊ በምንለው ሰዓት ልናገኛቸው ሳንችል እንቀራለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የቅርብ በሆኑ ወዳጆቻችንና የአገልግሎት አጋሮቻችን ስንገለል ማየት ከምንም በላይ የሚያም ነው፡፡ ለክርስቶስ ባለን መሰጠት ምክንያት ከቤተሰቦችን በኩል እንኳን መገለልና ውግዘት ሊደርስብን ይችላል፡፡ በኢትዮጵያ በነበረኝ 20 ዓመታት አገልግሎት ውስጥ ጌታ ኢየሱስን ለመከተል በመወሰናቸው ምክንያት ከቤተሰባቸው የተባረሩና የውርስ መብታቸውም የተነጠቀባቸው እንዳሉ ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡ እንደዚህ ዓይነት መገለል የደረሰባቸውን ወገኖች ማጽናናት ራሱ ከባድና የጌታን ልዩ ጥበብና ጸጋ የሚፈልግ እንደሆነ አይቻለሁ፡፡ በሚያስፈልገን ጊዜ ወደ ኋላ ቀርተን አቅም አንሶንና ጥንካሬአችንም ተዳክሞን ራሳችንን የምገኝባቸው ወራት ይኖራሉ፡፡ ብቸኝነት የጋሪዮሽ ችግራችንና ለሁላችንም አሳሳቢ ፈተና ነው፡፡ሓዋሪያው ጳውሎስ ከሚገለጥበት ጸጋ አንጻር ሲታይ ሰው ያጣል ማለት የሚቻል አልነበረም፡፡ ታላቁ የወንጌል ሐዋሪያ የነበረው ጳውሎስ አገልግሎት አጋሮቹ የሆኑት ሁሉ በተውት ጊዜ ርቆ ያለውን ጢሞቴዎስን ወደ ራሱ እንዲመጣ ጠየቀው፡፡ ጳውሎስ ስለ አስቸጋሪ ሁኔታዎቹ ሲያወሳ ዴማስ የተባለ አገልጋይ እንደተወው ይናራል፡፡ ዴማስ በቆላስይስ 414 ላይ እንደምናየው  ከጳውሎስ ጋር በአጋርነት የሚያገግል ነበር ግን አሁን የዚህን ዓለም ወደደና በአስቸጋሪ ሁኔታና ወቅት ደግሞ ትቶት ሄዷል፡፡  ሌሎች ደግሞ በአዎንታዊ ምክንያት ከጳውሎስ አጠገብ ሊገኙ ሳይችሉ ቀሩ፡፡ ቄርቂስ ወደ ገላትያ ሲሄድ ቲቶ ደግሞ ወደ ዲልማጥያ ሄደዋል፡፡ ጳውሎስ ራሱ ደግሞ ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኮታል፡፡ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ ብቻውን እንደሆነ ተሰማው፡፡ በሐዋሪያት ሥራ ምዕራፍ 19 እንደምንመለከተው ሰዎች ጨርቃቸውን እንኳ ወደ እርሱ ያመጡና ካለባቸው ደዌ ሁሉ እስክፈወሱ ድረስ ታላቅ ጸጋ የተገለጠበት ሰው ብቸኛ ይሆናል ብሎ ማሰብ የሚቻል አልነበረም፡፡ በእርሱ ላይ የተገለጠው የመፈወስ ፣ የማስተማርና የመግለጥ ስጦታ ያለበት ሰው በዘመናችን በብዙዎች ዘንድ የሚፈለግና በሺዎች የሚታጀብ እንጂ ሰው አጥቶ ሁሉም ተውኝ ይላል ብለን አናስብ ይሆናል፡፡ ጳውሎስ ግን ሁሉም ተውትና ብቻውን ሆነ፡፡ ዛሬም እኛ በአገልግሎት ወቅት የምንተማመንባቸው ሰዎች ትተውን ብቻችን ብንሆን፣በቤተሰባችንና በጎረቤታችን ያልጠበቅነው መገለልና መገፋት ቢደርስብን፣በመሥሪያ ቤታችንና በህብረተሰባችን ሁሉ ያላሰብነው የመጣል ሁኔታ ቢደቀንብን እንግዳ ነገር እንደደረሰብን ልንቆጥር አይገባንም፡፡ በተለይም የቅርብ የሆኑ ሰዎች በምንፈልጋቸው የብቸኝነታችን ሰዓት ሲተውን ማየት ልብን እጅግ የሚጎዳ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ በዚያን ሰዓት በአጠገባችን ቆሞ ያበረታናል፡፡ ኢየሱስ በሁሉም የተተወበትን ጊዜ ስለሚያውቅ በሰዎች የተጣሉትንና የተረሱትን ሁሉ ይረዳቸዋል፡፡ እርሱ ሁሉም በተዉት ጊዜ አባቴ ፣ አባቴ ስለን ተውከኝ ብሎ እንደቃተተ ያውቃልና፡፡ ስለዚህ ነው የዕብረውያን ጸሐፊ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም ያለው( ዕብ.415)፡፡
2. ባጣንና በነጣን ጊዜ ጌታ በአጠገባችን ቆ( .11-13)፡፡
ሁሉን ያጣና የነጣ ደሀ ማንም አይከተለውም፡ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ ወፎች መሳፈሪያ ቀበሮዎች ጉድጓድ አላቸው የሰው ልጅ ግን ራሱ የሚያስጠጋበት የለውም እያለ ሰዎች እንደተከተሉት እናውቃለን፡፡ ኢሱስ እንዲህ ይበል እንጂ የሚያስገርም ተአምር ያድርግ ስለ ነበር ከጥቅማቸው አንጸር ብዙዎች ተከትለውታል፡፡ ሓዋሪያው ቅዱሰ ጳውሎስ ሁሉም ትውት ብቻውን ከመሆኑም በላይ የሚያሳዝን ፈተናውን የሚናየው በጥሮአዳ ትቶት የመጣውን ንብረቶቹን እንዲያመለት ጢሞቴዎስን መጠየቁ ነው፡፡ ንብረቶቹ መጻሕፍቶቹ ሲሆኑ ምናልባት አብዛኛዎቹ እርሱ ራሱ የፋቸው ሊሆኑ ይችላሉ፤ የብሉይ ኪዳን መጸሕፍት እንደሚገኙበት ግን ጥርጥር የለንም፡፡ ከመጻሕፍቱ ሌላ ለጳውሎስ እጅግ በጣም አስፈጊ ሆ የተገኘው ንብረት በጢሮአዳ ትቶት የመጣው በርኖስ ነው፡፡ በርኖስ ምንድነው ለምንስ ይጠቅማል የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አስፈላጊ ነው፡፡ ጉይ ሆፕ ኪንግ የተባሉ የሥነ መለኮት አስተማሪ እንደሚገልጹት በርኖስ ከበጎች ፀጉር የሚሠራና በብርድ ጊዜ መላ ሰውነትን መሸፈን የሚችል እንደ ብርድ ልብስ ዓይነት የሆነ ራም ልብስ ነው፡፡ በጊዜው የነበሩ ሰዎች ይህንን ከበጎች ፀጉር ይሠሩና እግራቸው እስከ ጭንቅላታቸው ድረስ በመሸፈን ጭንቅታቸውንም ደግሞ ልክ በሞተር ብስክሌት የሚሄድ ሰው ራሱን በሄልሜት እንደሚሸፍን በበርኖስ ይከናንቡታል፡፡ ጳውሎስ በጢሮአዳ በነበረበት ወቅት ይህ ብርድ ልብስ ነበረው፡፡ ድንኳን የመስፋት ልምድ ያለው ሰው ስለሆነ ራሱ አዘጋጅቶትም ሊሆን ይችላል፡፡ ወደ ሮም በሚሄድበት ወቅት ለምን ትቶት እንደሄደ ታሪካዊ ማስረጃ የለንም ግን በሮም እስር ቤት እያለ ይህ ቡሉኮ በጣም አስፈልጎታል፡፡ ምክንያቱም በእሥር ቤት እያለ ከባድ የሆነ የብርድ ጊዜ እየመጣበት ስለሆነ ነው፡፡ ሐዋሪያው በአውሮጳ ሌላኛው ጫፍ የተወውን አሮጌና የነተበ ብርድልብስ ከሚያስመጣ ይልቅ በአካባቢው ከሚሠሩ ሰዎች አዲስ ቢገዛ አይሻለውም ነበር? የጌታ ባሪያ ጳውሎስ ያንን ማስመጣት እንጂ የተለውን የሚገዛበት የገንዘብ አቅም አልነበረውም፡፡ ይህ ሁኔታ ጳውሎስ ራሱና እርሱ የሚገለግለው ቤተ ክርስቲያን በምጣኔ ሀብት ዝቅጠት ውስጥ እንዳሉ የሚያመላክት ነው፡፡ ምንም በእሥር ቤት ውስጥ ቢሆንም እርሱን ለመጎብኘት የሚመጡ እንደነ ቲኪቆስ ያሉትን ሰዎች በአቅራቢያው ወዳለው የገበያ ቦታ ሄደው ሰውነቱን ከብርድ የሸፍንበትን ልብስ እንዲገዙለት ሊካቸው ያልቻለው የገንዘብ አማራጭ ስላልነበረው ነው፡፡ ጢሞቴዎስ ይህንን በርኖስ ያምጣው ረስቶት ሌሎችን ንብረቶች ብቻ ይዞ ይምጣ እርግጥኞች ልንሆን አንችልም ግን ምናልባት ይህ በርኖስ ቢረሳ የሐዋሪያው ምርጫ ምን ይሆናል? ከሮም ገበያ አዳራሾች አዲሱን ይገዛ ይሁን? በጭራሽ አይመስልም፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ ስንገባ ይህንን የመሰለ የንብረት እጦትና የገንዘብ እጥረት ውስጥ እንድንዘፈቅ የሚያደርገን ጊዜ አለ፡፡ በኢትዮጵያ ወንጌልን የሰበኩ የቀደሙት አባቶቻችን የአገልግሎት ታሪክ የሚያሳንም ይህንን የሚመስለውን ነው፡፡ የጌታን ወንጌል በሰበኩባቸው ጊዜያቶች ሁሉ በጊዜው የነበረው ሥርዓት ከፈጠረው ስደት በተጨማሪ ምግብ ፣ ውሃ፣ በቂ መጠለያና የመጓጓዣ እጥረት ደርሶባቸው እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል፡፡ አንዳንዶች ሥራ ሥር በልተዋል፣ የራሳቸው መጠለያ ስልነበራቸው እንደ አርቢቶ አደሮች ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ በመንቀሳቀስ ፣ ምሽቶቻቸውን በትላልቅ ዛፎች ላይ በማሳለፍ ሲነጋ ደግሞ የወንጌልን ቃል ይዘው እየተጓዙ እንደነበር እሙን ነው፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በአጠገባቸው ቆሞ እያበረታቸው የወንጌል ስብከቱን ሥራ ፈጽመዋል፡፡ ዛሬም ይህ ሁኔታ ሊገጥመን ይችል ይሆናል፡፡ ያለንበት የኢኮኖሚ ድቀት ሁላችንንም እየተፈታተነን  ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ጳውሎስ እንዳለ ጌታ በአጠገባችን ቆሞ ያበረታናል፡፡ እጦት ሰውን ሥፍራውን ሊያስለቅቅ የሚችል ብርቱ ተዋጊ ነው፡፡ በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን የሚያመልኩትና የሚያገልግሉት ጌታ ይጎብኛቸዋል፡፡ በዚህ ዓመት 15ኛ ዓመቷን ያከበረቺው ታላቅ ልጄ ገና የ4 ዓመት ልጅ ሆና እያለች የምትፈልጋቸውን ነገሮች እንድገዛላት ስትጥይቀኝ እኔም ልገዛላት ልቤ ጓጓም ከነበረኝ የገንዘብ እጦት ተነሳ ላደርግላት እንደማልችል እነግራት ነበር፡፡ በተደጋጋሚ በተለያዩ ጊዜያት ለምትጠይቀኝ ሁሉ ምላሼ ገንዘብ ስሌለለኝ ልገዛልሽ አልችልም የሚል ብቻ ሲሆንባት እኔን ተወችኝና እናቷን እንዲህ አለቻት፡፡ ማማ አንቺ ትክክል አልነበርሽም ምክንቱም አንቺ ይህን ባባን ባታገቢ ኖሮ እኔ ከእርሱ ባልተወለድኩና አባቴ ገንዘብ የሌለው ባልሆነ ነበርበልጅ አንደበቷ ይህን የመሰለ ቃል መናገሯ ልቤን እጅግ እንደሰበረ አስታውሳሁ፡፡ ከዚያ በኋላ አገልግሎቴ በገንዘብ እጥረት ምክንያት እንዳይሽመደመድ በእግዚአብሔር ፊት  ያነባውበትንና ያለቀስኩበትን ጌታ ያየኝ ወራት አስታውሳለሁ፣ አልረሳውምም፡፡  ጌታ እምባዬን አይቶ ብዙ ወንድሞችንና እህቶቼን በአጠገቤ አቆመና በኢትዮጵያ የነበረኝን አገልግሎት እስከማስረክብበት ቀን ድረስ እንደረዳኝ የሁል ጊዜ ምስክሩ ነኝ፡፡ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ! እግዚአብሔር የሚያስፈልገን በሚያስፈልገን ጊዜ ሁሉ የሚሰጠን ባለጠጋና ለጋስ አምላክ ስለሆነ በጉድለታችን ወቅት በአጠገባችን ቆሞ ያበረታናል እንጂ ለአንበሳ እንድንተኛለት አይፈቅድምና በፊቱ አንበርታ፡፡ ያለፈውን ወራት እያሰብን ጌታን የምናደንቅበት ዘመን ይመጣል፡፡ ቤት አይተው ቤት ለናፈቃቸው ቤት የሚሰጥ፣ ልብስ ለመልበስ የናፈቁትን የሚያለብስ፣ ምግብ የተራቡትን በእንጀራ የሚያጠግባቸው አምላክ በሰማይ አለ፣ በአጠገባችንም ቆሟልና ተስፋ አንቁረጥ፡፡
3. ባላንጣዎቻችን ክፉን በሚያደርጉብን ጊዜ ጌታ በአጠገባችን ቆ(.14-15)፡፡
የጠላቶቻችን ጥቃት አንዳንድ ጊዜ የምር እምነታችን የሚፈተሸበት መንገድ ነው፡፡ ክርስትና ሕይወትም ፈተና ያለበት ነው፡፡ እግዚአብሔርም የሚያጠቁንን ገለል ማድረግ እየቻለ በእኛ ዙሪያ እንዲሆኑ ይፈቅድላቸዋል፡፡ የመሳፍንትን መጽሐፋ ምዕራፍ 3 1-5 ድረስ ያለውን ክፍል ስንመለከት እግዚአብሔር ብዙ የእሥራኤል ሕዝብ ጠላቶችን ካጠፋቸው በኋላ  በጦረኝነታቸውና በጥንሬአቸው የሚታወቁትን አምስት ነገሥታትን ፍልስጥኤላውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ሲዶናውያንን፣ኤዊያውያንን የመሳለሱትን እንዳስቀራቸው እንመለከታን፡፡ ጌታ ይህን ሲያደርግ ዓላማ ነበረው፣ያም ዓላማ ስልፍ ያልለመዱ የእሥራኤልን ልጆች ውግያን ለማስተማርና እምነታቸውም በእነዚህ መንግሥታ ምክንያት ለመፈተን ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በብዙ መድረኮች ንደምንሰማው እኛ ክርስትናን ከምድራዊ በረከትና ስኬት ጋር እናያይዘዋለን፡፡ እግዚአብሔር በብዙ ባለጠግነት ሊባርከን ፈቃደኛ ቢሆንም በተለያዩ ሁኔታዎች ፈትነን እንደ ወርቅ እንድንወጣ ይሻል፡፡ አንዳንድ ወንድሞች ሲሰብኩ መከራችሁን አታስቡ፣ችግራችሁን አታስቡ፣ ድላችሁን ተመልከቱ ይሉናል፡፡ ይህኛውን እንደ እግዚአብሔር ቃል መውሰድ ካባድ ይሆናል ምክንያቱም በመከራ ወስጥ ያ አንድ ሰው ስለ መከራው ፣ ታማሚው ስለ ሕመሙ ማሰብ ግድ ነውና፡፡ እዚአብሔር የእኛ እምነት እንዲጠነክር ከሚጠቀምብን መንገዶች አንዱ  የባላንጣዎች ተቃውሞ ነው፡፡ ጳውሎስ ጌታን ባገለገለበት ወቅት እስክንድሮስ በተባለ አንጥረኛ በኩል ከፍተኛ እግልት ደርሶበታል፡፡ እስክንድሮስ በሮም ከተማ ውስጥ የታወቀ የብት አንጥረኛ ነው፡፡  በኤፌሶን ከተማ የነበረው ዲሜጥሮስ እንዳደረገው ለቤተ መቅደስ የጣት ምሥል እያነጠረ የሚያቀርብ ሊሆን ይችላል፡፡ እርሱ ጳውሎስ እንደዚያ የከፋበት ምክንያት የግሪክ ጣዖታትን ምሥል ቀርጾ እየሸጠ የሚያገኘው ጥቅም በውሎስ የወንጌል አገልግሎት ምክንስለተጎዳበት ሊሆን ይችላል፡፡ ጥቅም የተነካበት ሰው አጋጣሚን ሲያገኝ አቅሙ የቻለውንም ከአቅሙ በላይ ሆነው በቀል እንደሚገለጥ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ጳውሎስ ስለ እስክንድሮስ ሲናገር እጅግ ከፋብኝ ይላል፡፡ እንግዲህ ይህ ሰው ለክርስቲያኖች ሁሉ በጣም አደገኛ የሆነ ሰው ነው ማለት ነው ምክንያቱም ጳውሎስ ጢሞቴዎስም ቢሆን ከእርሱ እንዲጠነቀቅ ይመከረዋልና፡፡ ጳውሎስ በእስክንድሮስ ተቃውሞ ምክንያት የወንጌል ሥራውን አልተወውም ምክንያቱም ወንጌል ለእርሱ ከሁሉም ቀዳሚ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ የራሱን ምቾትና ደህንነት ወደ ጎን ትቶ ለወንጌል የሚከፈለውን ጋ ሁሉ ለመክፈል ራሱን ሰጠ፣ ጌታም በአጠገቡ ቆሞ አበረታው፡፡ ከባላንቻችን የሚሰነዘርብን ተቃዉሞ የምንሰብከውን ወንጌል ሊገው አይልም፡፡ ቃዋሚዎቻችን እጅግ እየከፉብንና እየተቃወሙን በሄዱ ቁጥር ወንጌላችን በበለጠ እየተስፋፋና እኛም የአምላካችንን የማዳ እጁን እየተለማመድን እንሄዳን፡፡ ከጎናችን የሚቆመው ጌታችን ከሚያሳየን አስደናቂ ህልውናው የተነሳ ራዕያችን እያደገና እየሰፋ ይሄዳል እንጂ ለሞት አንተኛም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ብዙ አገልጋዮቻችን ከተቃዋሚዎቻቸው ከሚደርስባቸው ብርቱ ጥቃት በአእምሮም፣ በአካልም በምጣኔ ሀብትም እየተጎዱ ናቸው፡፡ በእምነታቸው ምክንያት ብቻ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ፣ ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ፣ አልፎ ተርፎም ከመኖሪያ ሥፍራቸው የተሰደዱ በርካታዎች ናቸው፡፡ ይህንን የሚመስለው ሁኔታ በዚህ ምድር ላይ እያለን መከሰቱ አይቀሬ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ ከዚህም ሁኔታ ሊያድነን በአጠገባችን ቆሟል፡፡
4. በሙግታችን ጊዜ ጌታ በአጠገባችን ቆሞ(.16)፡፡
ዋሪያው ጳውሎስ እምነቱን ባቀበ ጊዜ የሮም ፍርድ ቤት እጅግ በጣም አስጊ ሥፍራ ነበር፡፡ በፍርድ ዳኘ ፊት የሚቀርብ ሰው ከሌላ ከማንም ምንም ዓይነት እገዛ ሊያገኘው የማይችልበት አደገኛ ሥፍራ ነበር፡፡ የፍድ ቤት ችሎት በሕሪይው ብዙ ሰው የሚገኝበት ቢሆንም ማንም በተከበረው ዳኛ ፊት የቆመውን ተከሳ በአሳብም ሆነ በሌላ ሊያግዝ አይፈቀድለትም፡፡ ጳውሎስ በሮም ፍርድ ቤት ዳኛ ፊት በቀረበበት ወቅት አንድም የአገልግሎት አጋር ከእርሱ ጋር ወደ ፍርድ ቤቱ የመጣ ስላልነበረ ሙግቱና ማንንቱ ለእርሱ ብቻ ተተወ፡፡ ያ ጊዜ ለጳውሎስ ምን ያህል አስቸጋሪ ሊሆንበት እንደምንችል እናስብ! ጳውሎስ ወደ ፍርድ ቤት እንደ ቀ ምናልባት ያ ጊዜ ለእርሱ የሕይወቱ መጨረሻ ሊሆንበት እንደሚችል አስቀድሞ በመንፈስ ተረድቷል፡፡ በዚህን ወቅት በቁጥር 17-18 እንደምንመለከተው በሙግቴ ማን አልደረሰልኝም ይላል፡፡ ያንን ካሰበ በኃላ ግን ጌታ በአጠገቡ እንቆመና ንዳበረታው ይመሰክራል፡፡ ጌታ ኢሱስ ይህንን በመስል አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን በአጠገባችን ቆሞ ያበረታናል፡፡ በምድር ላይ ስንኖር በክርስትና ሕይወታችን እጅግ መራራ ነገር ቢኖር ብቸኝነት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ አብረውን የሚሆኑ ሰዎችን የምንናፍቅበት ከናፍቆት ሁሉ የጠለቀ ነው፡፡ ከጌታ ከኢየሱስ ጋር እየተራመድን ባለንበት ሰዓት እንኳን በዚህ ዓለም ላይ ስላለን ብቻችን የሆንን የሚመስለን ጊዜ አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የሚደርስንብንን ሁኔታ አይተው የሀዘኔታ ስሜት እያሳዩ ሲያጽናኑንም ንኳ በውስጣችን የብቸኝነት ስሜት ስለሚሰማን ሰዎች የሚሉትን ትተን የራሳችንን ውሳኔ መወሰን እንገደዳለን፡፡ ሸክማችንን ለማቅለል የግል ሕይወታችንን ጦርነት ራሳችን የመዋጋት ግዴታም አለብን፡፡ የሚገጥምንን የሕይወት ጥያቄ እኛው ራሳችን ብቻ የመመለስ ግዴታም ይጠብቀናል፡፡ በሕይወታችን የሚገጥምንን ፈተና ምንጋፈጠው እኛው ራሳችን ብቻ ነን፡፡ ተሟጋቻቾቻችን የሚያቀርቡልንን የሙግት የምንሟገተው እኛው ብቻ እንሆናለን፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ በዚህ ሁሉ ጊዜ በታማኝነት በአጠገባችን ቆሞ ያበረታናል እንጂ ብቻችን አይተወንም፡፡ ሌሎች ረዳቶቻችንና ጓደኞቻቸችን ምንፈልገው ሰዓት ሳይገኙልን ሲቀሩ ጌታ ግን በቅረርባችን ቆሞ ይረዳናል፡፡ ሌሎች ፊታቸውን ቢያጠቁሩብን ጌታ ዓይኖች ሁል ጊዜ በፍቅር እንዳበሩልን የክብሩ ጸዳል በእኛ ላይ እንደወረደ ይቀጥላል፡፡ እምነታችንን ስንከላከል የሮም ፍርድ ቤት በሚመስል ሥጋት የሰፈነበት ቦታ ብቻችን ብንቆም እንኳ እግዚአብር በታማኝነት በአጠገባችን ቆሞ ያበረታናል፡፡
ከጌታ ከኢየሱስ ሕይወትም የምንማረው ይህንን ነው፡፡ እርሱ በአስቸጋሪና አሥጊ ቀናት ውስጥ ለብቻው ተተወ፡፡ የሮማውያን ወታደሮች ሊይዙት በመጡበት ወቅት ሌላው ቢቀር የቅርብ ደቀመዛሙርት ከነበሩት ውስጥ እንኳ አንድ ሰው በአጠገቡ አልነበረም፡፡ ጌታችን እንጀራ ያበላቸው፣ ከበሽታ የፈወሳቸው፣በምድረ በዳ ያገለገላቸው ሁሉ እርሱ መስቀል ተሸክሞ ሲንገላታ ከአጠገቡ ሊገኙ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም ሁሉ በተውት ሰዓት ኤሎሄ፣ኤሎሄ ላማ ሳበቅታኒ ብሎ ወደ አባቱ ጮኸ፡፡ ዛሬ እኛ የምንጋፈጣቸው መከራዎችና ችግሮች ሁሉ በጌታችን በኢየሱስም ሕይወት ተከስተው ነበር፡፡ በአገልግሎታችንና በክርስትናችን ወቅት መከራና ሙግት ሲደርስብን አሉን የምንላቸው ሰዎች ከእይታችን ቢሰወሩብን በእኛ ላይ ብቻ የተከሰተ አድርገን አንቁጠር ምክንያቱም በኢየሱስና በጰውሎስም ሕይወት ይህ ሆኖአልና፡፡
በፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ውስጥ ከሳሽ ይቀርባል፣ተከሳሽም የእምነት የክሂደት ቃሉን ለመስጠት ይቀርባል፣ ዳኛው የከሳሹንና የተከሳሹን የክስና የመልስ ቃል ሰምቶ ብያኔ ለመስጠት በፍርድ ወንበር ላይ ይቀመጣል፣ ችሎቱን የሚካፈሉትም ሰዎች ምናልባትም የተከሳሽ ወዳጆችና ቤተሰቦች ሊሆኑ ይችላሉ እነርሱም የፍርዱን ሂደት እየተከታተሉ በሥፍራው ይገኛሉ፡፡ ይህ ሁሉ በሚሆንበት ወቅት ከማም በላይ ለተከሳሹ ወሳኝ ሰው በፍርድ ዳኛ ፊት ተከሳሹን ወክሎ የሚናገር ጠበቃ የተባለ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው ስለ የአገሪቱ ሕግ በቂ እውቀት እንዳለው ተረጋግጦ ፈቃድ የተሰጠውነና የመናገር መብትም ያለው ነው፡፡ ብቃት ያለው ጠበቃ ተከሳሹን ለሞት ከሚያበቃው ወንጀል እንኳ ነጻ ሊያሰለቅቅ ይችላል፡፡ ጳወሎስን ያሳዘነው በሮም ፍርድ ቤት ችሎት ከወዳጆቹ አንድም ሰው ሳይገኝ መቅረቱ እንጂ ብቃት ያለው ጠበቃ እንዳለውማ በደንብ ይታየው ነበር፡፡ ያውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህንን ስለተረዳ በፊተኛው ሙግቴ ማንም አልደረሰልኝም…..ጌታ ግን በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ ከአንሳም አፍ ዳንሁ አለ፡፡ እኔና የዚህ መልእክት አንባቢዎች አንድ ልዩ ጠበቃ አለን፡፡ እርሱም ስለ እኛ ሐጢአት ሞቶ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሕፈት የደመሰሰልን ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ እርሱ በአጠገባችን ቆሞ ስለ እኛ ይሟገትልናል፣ ከሳሻችንንም አሸንፎልናል፡፡ እርሱ ብቻ በአጠገባችን ቆሞ!
5. ዓላማው በእኛ እንዲፈጸም ጌታ በአጠገባችን ቆሞ( .17-18)፡፡
እግዚአብሔር ያለ ዓላማ ከእኛ ጋር አይሠራም፡፡ እርሱ የዓላማና የግብ አምላክ ነው፡፡ የእርሱ ዘላለማዊ ዓላማው በእኛ ሕይወት ይፈጸም ዘንድ በችግርና በመከራ ሰዓት ሁሉ በአጠገባችን ቆሞ ያበረታናል፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ በሕይወቱ ችግርና ስደትን ተለማምዷል፡፡ እንዲያውም በልዩ ፍርድ ቤት ምናልባትም በንጉሥ ኔሮ ፊትም ቆሟል፡፡ ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው ሥፍራው በሰው የተጨናነቀ ቢሆንም ጳውሎስ መከራን በሚጋፈጥበት ወቅት ማንም አልረዳውም፣ ከጎኑም የቆመ አንድ አልነበረም፡፡ ዳሩ ግን ጌታ በኃይሉ እንዳበረታው ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ የሚያበረታን ለምን እንደሆነም ከጳውሎስ እንማራለን፡፡
የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ዓላማ የወንጌል ስብከቱ ሥራ በእኛ እንዲፈጸም ነው፡፡ የክርስቶስን ወንጌል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በእግዚአብሔር ኃይል ታግዞ ከመስበክ የበለጠ የምናደናንቀው ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ በዚህን ጊዜ ከማንም ሰው ይልቅ በታማኝነት ከእኛ ጋር የቆም እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በእኛ ላይ ያለው የእርሱ ዓላማ እንዲሰናከልብን ጌታ በፍጹም አይፈቅድም፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ በአገልጋየዮች የወንጌል እወጃ አማካይነት ወረሳል፡፡ አምላካችን እግዚብሔር በእኛ ያስቀመጠው ዓላማ እስክፈጸም ድረስ በስደት፣ በመከራ፣ በባላንታዎቻችን ክፉ ጥቃት ምክንት አንሞትም፡፡  የምሠራው ነገር ካለቀብን በምድር የከንቱ ኑሮ ከመኖር ከክርስቶስ ጋር ለመኖር መሄድ እጅግ የሚሻል ነው(ፊልጵ. 123)፡፡ ጳውሎስ ወንጌል በሮማ ግዛት በተለያየ የሕወት ደረጃ ላሉ ሰዎች ማለትም ለነገሥታትና ለተርታው ሕዝብ ለመስበክ ምቹ አጋጣሚውን ያገኘው  በደረሰበት መከራ ምክንያት ከቦታ ወደ ቦታ ሲሰደድና ወደ እሥር ቤት ሲወሰድ ነው፡፡ ስደትና መከራው በርካታ ቁጥር ባሉባቸው ታላላቅ የሮማ ከተማዎችና በአሕዛብ ዋና ዋና አካባቢዎች የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብክበትን በር ወገግ አድርጎ ከፍቶለታል፡፡ በሕይወታችን የሚናከናውናቸው ተግባራት ሁሉም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ወንጌልን መስበክና የእግዚአብሔር አሳብ ማገልገል ግን ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነው፡፡ ሥራው በእኛ እንድፈጸም ጌታ በሁሉም ጊዜ እያበረታን ከአጠገባችን ይቆማል፡፡
ጌታን ባገለገልኩበት 20 ዓመታት የእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ የተለማመድኩት ይህንን ነው፡፡ በ20 ዓመት ውስጥ 1040 እሁዶች አሉ፡፡ እንደ ህመም፣የገንዘብ እጦት፣የቅርብ ዘመዶቼን በሞት መነጠቅ፣የትረንስፖርት እጥረት ሁሉ ቢያጋጥመኝም አንዱንም እሁድ አይደለም መቅረት ሰዓት እንኳ እንዳላረፍድ ጌታ ረድቶኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ታምሜ አውቃለሁ ግን ይህ አንድም ቀን ከእግዚአብሔር ጉባኤ ወደ ኋላ አላስቀረኝም፡፡ አባትና እናቴን በ9 ወራት ልዩነት ውስጥ ማጣቴ የስብከት አገልግሎቴን አላስቆመኝም፡፡ እናቴ ወደ ጌታ መጠራቷን ሰምቸቼ ወደ አገር ቤት ስሄድ ታላቅ ወንድሜ በልቅሶው ላይ እንድሰብክ አደረገኝ፡፡ በዕለቱ ያካፈልኩት ቃል ሁል ጊዜ የማውቀውና በሁሉም ዘንድ የተለመደ ዓይነት ስብከት ቢሆንም ከነበረው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በጣም ኃይል የተላበሰ ሆነ፡፡ እንደሚታወቀው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የነበረው የትራንስፖርት ችግር ለአገልጋይ ከአቅም በላይ የሆነ ፈተና ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በሚያስገርም ሁኔታ እግዚአብሔር በአገልግሎት መስክ እንገኝ አድርጎኛል፡፡ ይህንን የምለው የእኔን የአገልግሎት ውጤታማነት ለማሳየት ሳይሆን እግዚአብሔር እንዴት እንደሚደግፍና በእኛ ላይ ያለው ዓላማ ይፈጸም ዘንድ እንዴት አድርጎ እንደሚያበረታን ለማሳየት ነው፡፡ ዋሪያው ጳውሎስ የደረሰበትን ችግርና መከራ፣ ስደትና ብቸኝነት ሁሉ ከአንበሳ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህ አገላለጽ ሁኔታዎች ጥጉን የያዙ አደገኞች እንደነበሩ የሚያሳይ ምሳሌ ነው፡፡ ንባብ ክፍላችን አውድ መሠረት ጳውሎስ ለሞት አልፎ እንደሚሰጥ በእግዚአብሔር የታቀደ ቢሆንም በእርሱ እንዲሠራ እግዚአብሔር የወሰነው ሥራ ሳይጠናቀቅ የትኛውም ሁኔታ ሕይወቱን እንዲያጠፋ አልተፈቀደለትም፡፡ ጳውሎስ ሞት እንደሚጠብቀው አስቀድሞ እንተረዳ በቁ.6 እና 18 ላይ አስረድቷል፡፡ ይሁን እንጂ ያ ጊዜ አስክደርስ ድረስ እርሱ የተጠራለት ፣ የክርስቶስን የማዳን ወንጌል ለአሕዛብ የመስበክ ዓላማ እንዲፈጸም ጳውሎስን የአንበሳው ጥቃት እንዳያሸንፈው ጌታ በአጠገቡ ቆሞ ከአንበሳው ይልቅ አበረታው፡፡
 እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ሌላው ዓላማ የሰዎች መዳን ነው፡፡ ጳውሎስ ወንጌልን ለአሕዛብ መስበክ የተሰጠ ማንነት ያለው ሐዋሪያ ነበር፡፡ እነርሱን በወንጌል ለመድረስ ጥልቅ ፍላጎትና ሸክም ነበረው፡፡ እግዚአብሔር ከደረሰበት ፈታኝና አስጊ ሁኔታዎች ታደገው ይህንን ወንጌል እዲያዳርስ እንደሆነም በእርግጠኝነት እየተናገረ ነው፡፡ የእርሱ ስብከት ከፑልፒት ጀርባ ብቻ ሳይሆን በምኩራብ፣ በቤት፣ በፍርድ ቤት ፣ በገበያ ቦታዎች፣ሕዝብ በሚበዛባቸው ታላላቅ ጎዳናዎች እንዴት አድርጎ ወንጌልን እንደሰበከ ስናይ እንገረማለን፡፡በስብከቱ አገልግሎት ወቅትም ለአሕዘብ፣ ለአገረ ገዥዉም፣ እርሱ ወደ እርሱ ካልመጣ የወንጌል መልእክት የመስማት እድል ለሌላቸው ታዋቂ ለሆኑም፣ እጅግ ለተገለሉም ሁሉ የእግዚአብሔርን አደራ ይዞ ተሰማራ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርም ከአንበሳ አፍ አድኖታል፡፡ ያ አንበሳ ኔሮ ራሱ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ  ለኔሮና ከእርሱ ጋር ላሉ ባለሥልጣናትም ጭምር ወንጌል የሚሰብክበት መልካም አጋጣሚዎችን የሚፈጥርለት ነበር፡፡ እውነተኛ አገልጋይ ትርጉም ያለውን ሕይወት ኖሬአለሁ የሚለው ሰዎችን በጠቀመበትና ከእግዚአብሔር ጋር ባስታረቀበት ሥራው እንጂ በግዙፍ ጉባኤ ፊት ቆሞ በመስበኩ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርም የሚጠይቀን በስንት ሰዎች ፊት ቆመህ አገለገልክ ሳይሆን በምፈልግህ ቦታ ላይ ቆመህልኛል ወይ ብሎ ነው፡፡ ምን ያህል አገለገልክ ሳይሆን ያዘዝኩህን አድርገህልኛልን ብሎ ይጠይቀናል፡፡ ጳውሎስ በእምነቱ ምክንያት ሞት እንደሚፈረድበት እርግጠኛ ነው፡፡ አገልግሎቱን እስክያጠናቅቅና ሩጫውን እስክጨርስ የረዳውን ጌታ በደስታ ያመሰግነዋል እንጂ የሐዘንና የመቆጨት ቃል  ከአፉ አልወጣም፡፡ እንዲያውም የደረሰበትህ ሁሉ ወደ ጎን ትቶ እግዚአብሔርን ሲያመልክና ሲያመሰግን እናያለን፡፡ እግዚአብሀየር በእርሱ ሕይወት ያለው የወደፊት ሁኔታም ይታየዋል፡፡ የቀረቺውን ዘመን ቢሆን አሁንም ጭምሮ ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል ይላል፡፡ይህ ለእኛ ትልቅ መልእክት ያለው ቃል ነው፡፡ ጌታን እናገለግለዋለን እንላለን እንጂ የምናገለገልው እኮ ሰዎችን ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰባኪ ስለሚሰብክ ጌታን እያገለገልኩ ነኝ ይላል፡፡ የሚሰብከው ግን ጌታን ሳይሆን ሰዎችን ነው፡፡ አስተማሪውም በማስተማሩ ጌታን አገለግላለሁ ማለቱ ትክክል ቢሆንም ቂሉ የሚያስተምረው ግን እግዚአብሔርን ሳይሆን ሰዎችን ነው፡፡ እግዚአብሐሔርም ሰዎችን የማዳኑን ሥራ የሚፈጥመው በሰዎች ነው፡፡ ይህም በምድር ላይ የመኖራችን ምክንያትና የእግዚአብሔር ዓላማ ነው፡፡ ይህንን ዓላማ እንዲናስፈጽምለት ዛሬም ይፈልገናል፣ አንበሳውም አንዳይበላን ያስመልጠናል፡፡ ስለዚህ በዚህ የታነመ ጌታ ላይ ራሳችንን እንጣል፡፡ በሰዎች የተተዋችሁ፣ መሠረታዊ ፍላጎታችሁ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ልታገኙ ያልቻላችሁ፣ከማትችሉት ጋር የመሟገት ግዴታ የሚገጥማችሁ፣እና በሌሎች አስጊና አስጨናቂ መንገዶችና የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፋችሁ ያላችሁ በክርስቶስ ወንድሞቼና እህቶቼ ሁላችሁንም በጌታ መንፈስ ሆኜ የማረበታታችሁ ነገር ይህ ነው፣ጌታ ከአንበሳው አፍ ያድናችኃል፡፡ ጌታ በአጠገባችሁ ቆሞ!