ከተማችን ሲከበብ እግዚአብሔር ምን ይላል
ፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ
በብሉይ
ኪዳን ዘመን የዜማና የቅኔ ንጉሥ የነበረው ዳዊት
በመዝሙር መጽሐፉ 31፡21
ላይ
ሲዘምር በተከበበ ከተማ
የሚያስደንቅ ምህረቱን በእኔ የገለጠ እግዚአብሔር
ይመስገን ይላል፡፡ የዳዊትን
ዝማሬዎች ስንመለከታቸው ስለ እግዚአብሔር
ማንነትና ስለ ሥራው የሚያወሱ ናቸው፡፡
እውነተኛ ቅኔና ዜማ የሚመነጨው ከላይ
ከእግዚአብሔር ነው፡፡ የእግዚአብሔር
መንፈስ እየመራው ዘማሪው በሕይወቱ ካለፈበት
መንገድና በዚያ መንገድ እግዚአብሔር እንዴት
እንደረዳውና እንዳገዘው
የሚዘምርበት ጊዜም አለ፡፡ ዳዊት በሕይወቱ
የተገለጠውን የእግዚአብሔርን አስደናቂ
ርዳታን ከሚያሳይባቸው ዝማሬዎች አንዱና
አስገራሚው እንግዲህ ከፍ ብሎ የተገለጸው
ነው፡፡
ዳዊት
ስለተከበበ ከተማ ሲናገርና እኛ ስለተከበበ
ከተማ ስናወራ በመካከላችን ትልቅ ልዩነት
አለ፡፡ በእኛ ዘመን የከተማ መከበብ የሚባለው
ነገር ብዙም የተለመደ አይደለምና ይህ ክፍል
በደንብ ሊገባን አይችልም፡፡ ምናልባት ለአጭር
ጊዜ በሽምቅ ተዋጊዎች ምክንያት ዳር ዳራቸው
የሚታጠርባቸው አንዳንድ ከተሞች ሊኖሩ
ይችላሉ፡፡ ይህም ቢሆን ምናልባት በከተማው
በአንድ አቅጣጫ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ በሰሜን
በኩል ቢያዝ በደቡብ በኩል ክፍት ሊሆን ይችላል፣
የምዕራቡ አካባቢ ቢያዝ የምሥራቁ ነጻ ሊሆን
ይችላል፡፡
ዳዊት
በተከበበ ከተማ እግዚአብሔር የሚያስደንቅ
ምሕረት ስለማድረጉ ሲናገር አንድ አስደናቂ
ታሪክ እንዳለ ማወቅ እንችላለን፡፡ እርሱ በኖረበት ዘመን የነበሩ ከተሞች
እንደ ዛሬዎቹ የተለጠጠ ስፋት ያላቸው
አልነበሩም፡፡ የሥልጣኔአቸውም ሁኔታ እንደዚያ
ነበር ማለት እንችላለን፡፡
ሁሉም ከተሞች በመጠናቸው አነስ ያሉ በመሆናቸው
ዙሪያቸው በጠንካራ አጥር ይታጠራል፣ ጠንካራ
መዝጊያም ይገጠምባቸዋል፡፡ በከተማው ውስጥ
ያለው ሕዝብ እንደፈለገ መውጣትና መግባት
ሳይሆን በተዘጋጀለት መውጪያና መግቢያ በር
በኩል ይወጣል፣ ይገባልም ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የኢየሩሳሌም ከተማ በግንብ የታጠረች ሆና የተለያዩ 12 በሮች እንዳሉአት የሚናየው እንደፈለጉ የሚወጡበትና የሚገቡበት ሳይሆን የራሱ ደንብና ሥርዓት እንዳለው የሚያመላክት ነው፡፡ ይህ
የሚሆንበት ምክንያት በከተማው ውስጥ ያለውን
ሕዝብ ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕዝቡ በሚገባበትና በሚወጣበት በር አናት
ላይ በተዘጋጀው ማማ የጦር ቃፊሮች የጠላትን
መምጣት እየተመለከቱ በውስጥ ያለው ሕዝብ
የሚመጣበትን ጦር ለመመከት የሚያስችለውን
ዝግጅት እንዲያደርግ መለከት በመንፋት
ያነቃቃሉ፡፡ የአሕዛብ
ከተሞችም ተመሳሳይ የሆነ ልማድ ነበራቸው፡፡
የፍልጥኤማውያን ከተማ የሆነቺው ጋዛ በግንብ
የታጠረች ስለሆነች በግንቡ ላይ ትልቅ መዝጊያ
ተገጥሞበት እንደነበር በመሳፍንት 14፡1
ላይ
መመልከት እንችላለን፡፡ ይህንን የግንብ
አጥር ላይ ተገጠመውን መዝጊያ ከነመቃኑ
የነቃቀለባቸው እግዚአብሔር በእሥራኤል ላይ
አዳኝ መስፍን አድርጎ የቀባው ሰው ሳምሶን
እንደሆነ በቃሉ እንመለከታለን፡፡
ሳምሶን ይህንን ያደረገው የእግዚአብሔር
ሀይል በእርሱ ላይ ስለወረደበት እንጂ
በተራ ሰው ጉልበት እንደዚያ እንደማይሆን
በእግዚአብሔር ቃል በትረካ መልክ መቀመጡን
ስናይ የሁኔታዎች አሳሳቢነት ምን ያህል ከባድ
እንደሆኑ በግልጽ ለማወቅ ያስችለናል፡፡
እግዚአብሔር
ባሪያ የቅኔ ሰው ዳዊት በተከበበ ከተማ
የሚያስደንቅ ምህረቱን በእኔ አደረገ ሲል
የሚገባው ነገር ነበረው፡፡ ከተማ በግንብ
ብቻ አይከበብም፡፡ እጅግ በጣም የሚያስፈራው
በጠላት የመከበብ ሁኔታ ሲኖር ነው፡፡ አንድን
ከተማ የሚያጠቃ ጠላት ከመጣ የከተማዋን
የመውጫና የመግቢያ በሮችን ይይዝና በውስጥ
ያሉት እንዳይወጡና በውጭ ያሉትም ወደዚያ
ከተማ እንዳይገቡ በሩን ይዘጋል፡፡ ያን ጊዜ
በውስጥ ያለው ሕዝብ፣ ከነልጆቻቸውና
ከነእንስሶቻቸው ምግብና ውሃ በማጣት ይጠቃሉ
ማለት ነው፡፡ የተከበበች ከተማ በውስጧ ረሃብ፣
ጥማት፣ ሞት፣ እንግልት፣ ልቅሶና ሀዘን
አለባት፡፡ ዳዊት የሚነግረን እንዲህ ባለ
ሁኔታ የተከበበችውን ከተማ እግዚአብሔር
እንዴት አድርጎ ታላቅና አስደናቂ የሆነውን
ምሕረቱን ገልጦ እንደሚያድናት ነው፡፡
በጉልበተኞች የሚረገጡ ከተሞች ሁል ጊዜ
የሚገጥማቸው ዕጣ ፋንታ ይህ ነው፡፡ ይህ
በሚሆንበት ወቅት በከተማዋ ያለ አንድ ንጉሥ
ሕዝቡን ለማዳን የሚችልበት አቅም የለውም፡፡
የሠራዊትም ብዛት ከዚህ ሁኔታ ሊያስመልጥ
አይችልም፡፡ ከዚህ ሁኔታ ሊያስመልጥ የሚችለው
እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር በተከበበ
ከተማ ምሕረት አደረገ ሲል ምን ማለቱ ነው? ምሕረትን
በሁለት መልክ ልናየው እንችላለን፡፡ ኃጢአተኛው
ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቀርቦ በደሉን በመናዘዙ
ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ፍጹም ይቅርታ ምህረት
ይባላል፡፡ በሌላ አንጻር ደግሞ እግዚአብሔር
ለችግረኛ የሚደርገው ርዳታ ምሕረት ተብሎ
ሊወሰድ ይችላል፡፡ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ
ጋር ወደ ኢያእሪኮ ከተማ በመጣ ጊዜ የጤሜዎስ
ልጅ ዓይነ ሥውሩ ቤርጠሜዎስ በመንገድ ላይ
ተቀምጦ እየለመነ የኢየሱስን መምጣት ባወቀ
ጊዜ እየደጋገመ ከፍ ባለ ድምፅ የዳዊት
ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ ብሎ
እንደጮኸ እንመለከታለን(ማር.
10፡46-52)፡፡
ይህ ሰው ማረኝ ሲል ምን ማለቱ ነው?
በግልጽ
አባባል እርዳኝ ማለቱ ነው፡፡ ከእውርነቴ
ነፃ አውጣኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህንን በሌሎችም
የወንጌላት ክፍሎች ማየት እንችላለን፡፡
ዓይናቸው የማያይ ሌሎችም ይህንን የእርዳኝ
ጩኼት ሲጮኹ እናያለን(
ማቴ.20፡29-34፣ማቴ
2፡27-31)፡፡
እንግዲህ ከዚህ አሳብ ስንነሳ በተከበበ ከተማ
እግዚአብሔር የሚያስረንቅ ምሕረትን በእኔ
ገለጠ ሲል ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት
አያስቸግርም፡፡ እግዚአብሔር በተከበበ ሁኔታ
የሚያስደንቀውን ርዳታውን በእኔ በችግረኛውና
በተጠቃሁ ሰው ላይ አሳየ ማለት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ርዳታ አስደናቂ ነው፡፡ ሰው
ወዳጁን ሊረዳ ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር
እርዳታ ግን የሚያስገርምና የሚያስደንቅ
ነው፡፡
ከዳዊት
ሕይወትና
ከሌሎች
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመነሳት በጠላት
የተከበቡ ሁለት ከተማዎችን ሁኔታ መመልከት
እንችላለን፡፡ አንደኛዋ ጽቅላግ የተባለች
ከተማ ስትሆን ሁለተኛዋ ደግሞ ሰማሪያ የምትባል
ከተማ ናት፡፡ ጽቅላግ የተባለችው
ከተማ ዳዊትና ቤተሰቡ
የነበሩባት ከተማ ስትሆን አማሌቃውያን
ዳዊት ያልነበረበትን
አጋጣሚ ተጠቅመው ያችን ከተማ እንደከበቡአትና
የዳዊትንም ልጆች ፣ ሚስቶችና እንስሶቻቸውንም
ሁሉ ማርከው እንደወሰዱበትና በእሳትም
እንዳቃጠሉአት
በጌታ ቃል እንመለከታለን(1
ሳሙኤል
30፡
)፡፡
የሰማሪያንም ሁኔታ ስንመለከት የሶሪያ ንጉሥ
ወልዴ አደር ሰማሪያን እንደከበባት በ2ኛ
ነገሥት 6 ተጽፎ
እናገኛለን፡፡ ከተማዋ ከመከበቧ የተነሳ
በውስጧ ከፍተኛ
የምግብ ዕጦት ውስጥ ገብታለች፡፡ እንዲያውም
ቃሉ የሶሪያ ንጉሥ ወልዴ አደር ሠራዊቱን
ሁሉ ሰበሰበ፣ ወጥቶም ሰማሪያን ከበባት፡፡
በሰማሪያ ታላቅ ረብ ሆኖ ነበር ፣ እነሆም
የአህያ ራስ በአምሳ ብር የርግብ ኩስ የጎሞር
ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስክሸጥ
ድረስ ከበቡአት ይላል፡፡ እዚህ ላይ “ድረስ”
የምትል ቃል ልዩ ትርጉም የምትሰጥ ናት፣ ምክንያቱም
የሁኔታዎችን አሳሳብነትና በከተማው ውስጥ
የሚታየው ችግር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ
የምታመለክት
ቃል ናት፡፡
ይህቺ የሰማሪያ ከተማ ስለተከበበች
በውስጥዋ ያለው ችግር እጅግ መራራ ነው፡፡
በዚያ ከተማ እህል የሚባል ነገር አይታሰብም፡፡
ምን ያህል ጊዜ እንደተከበበች ባናውቅም ብቻ
ለረጅም ጊዜ ሊሆን እንደሚችል
የንባብ አውዱ ይጠቁማል፡፡
የሶሪያ
ንጉሥ ወልዴ አደር ሰማሪያን ስለከበበ
በከተማዋ ውስጥ የሚበላ ነገር የለም፡፡ አለ
ቢባልም ለምግብነት ውለው የማያውቁ ሦስት
ነገሮች ብቻ ለምግብነት አገልግለዋል፡፡
አንደኛው አህያ ራስ ነው፡፡ ሁለተኛው የርግብ
ኩስ ሲሆን እነዚህን የሚበሉት
ምናልባት ገንዘብ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡ በአንድ
አገር ብሔራዊ
ችግር ቢከሰት የብዙዎች ሕይወት አደጋ ላይ
እየወደቀ ባለበት ለራሳቸው
አጋጣሚውን ተጠቅመው የሚከብሩበት አንዳንድ
ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ይሆናሉ፡፡ በእዚህም ከተማ ነጋዴዎች የአህያ ጭንቅላትና የርግብ ኩስ ሰብስበው ለተራበው ሕዝብ እየቸበቸቡ ናቸው፡፡ አምሳ ብር
ያለው የአህያ
ራስ ይገዛለል ያልቻለው
ደግሞ አምስት ብር ይዞ የርግብ ኩስ ወደሚሸጥበት
ሥፍራ ሄዶ ይገዛና የእለት ምሳውን ወይም ራቱን
ይወጣዋል፡፡ ይህ ሁሉ ባይሆንስና ገንዘብ
የሌለው ምን ይሆናል የሚል ጥያቄ ቢነሳ ሦስተኛው
አማራጭ በከተማው ውስጥ ተከስቷል፡፡ ያውም
የወለዱትን ልጅ አርዶ መብላት ነው፡፡ በታሪኩ
እንደምንመለከተው በሰማሪያ ከተማ የሚኖሩ
ሁለት ሴቶች አንድ ወንድ ልጅ ቀቅለው እንደበሉ
በቁጥር 29 ላይ ተጽፏል፡፡ ልጅ የመሰለውን የሚያስበላ
ፈተና ገጠማቸው ማለት ነው፡፡ ታዲያ ይህን
ሁኔታ ስናይ ሰማሪያ ተስፋ ይኖራታል
ብሎ ማሰብ ይቻላል ወይ?
የዚህች
ከተማ ታሪክስ ሊለወጥ ይችላል ወይ?
በውስጧ ያሉ ሰዎችስ ከዚህ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ወጥተው
እንደሌሎች ሰዎች አግባብ ያለውን ምግብ
የሚበሉበት ሁኔታ ይመጣል ወይ?
የሰማሪያ
ሁኔታ ምንም
ተስፋ የሌለው ይመስላል፡፡ ምክንያቱም የሰማሪያ
ንጉሥ ራሱ ምንም ተስፋ አጥቷል፡፡ በከተማዋ
ምግብ አለመኖር ብቻ ሳይሆን
ሌላው ችግር ንጉሡ ጠላትን መመከትም ሆነ
የሕዝቡን ብሶት ሰምቶ ምላሽ መስጠት አለመቻሉ
አንዱ ፈታኝ ነገር ነው፡፡ ልጇ የተበላባት
ሴትዮ ንጉሥ ሆይ
ርዳኝ ብላ ወደ እርሱ
ስትጮኽ
የመለሰው ምላሽ አስደንጋጭ ነው፡፡ በዚህ
ከተማ ውስጥ ያሉ ሰዎች ፍትሕ ሲያስፈልጋቸው
የሚጮኹት
ወደ ንጉሡ ስለነበረ እንደተለመደውም
ያቺ ሴት እርዳኝ እያለች ወደ እርሱ ስትሮጥና
ስትጨኽ "እግዚአብሔር
ያልረዳሽን እኔ
በምን እረዳሻለሁ?” የሚል
ምላሽ ነበር የሰጣት፡፡ ታዲያ ይህች
ከተማ ተስፋ አላት?
በንጉሥ
የማይቻለው በእግዚአብሔር እንደሚቻል የሚያምነው
ሕዝብ እግዚአብሔርም እንደማይረዳው
ተደርጎ በንጉሡ በኩል ተነገረው፡:
ታዲያ
ሰማሪያና በውስጧ ያለው ሕዝብ እጣ ፋንታው
ምን ሊሆን ነው‹?ወይ
ንጉሡ እንዳለው
እግዚአብሔርም ይህቺን ከተማ ላይረዳ ነው?
ንጉሡ
ተስፋ አስቆራጭ በሆነ መልኩ እግዚአብሔር
ያልረዳሽን እኔ በምን እረዳሻለሁ ያለው ብዙ
ምክንያቶች ስላሉት ነው፡፡ አንደኛው የሶሪያ
ንጉሥ ወልዴ አደር ከእርሱ ይልቅ በወታራዊ
የበላይነት በልጦ አሸንፎታል፡፡ ሁለተኛው
የተቸገረውን ሕዝብ እንዳይረዳ አውድማና
መጥመቂያ ወይም ጎተራ የለውም፡፡ ስለዚህ
እግዚአብሔርም እርሱ ባለበት ተጽእኖ ሥር
የወደቀና የተሸነፈ መስሎት ነው፡፡ በሥጋ
ዓይን ለሚያይ ሰው ሰማሪያ ምንም ተስፋ
አይተይባትም፡፡ ምክንያቱም የተከበበችበት
መከበብ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ የሚገርመው
ግን እግዚአብሔር እንደዚህ ባለ ሁኔታ ውስጥ
ተገልጦ ይረዳል፡፡ እውነትም መጥመቂያና
አውድማ የለም፡፡ እንዴት ንጉሥ ሊረዳ ይችላል? እርሱም እኮ በከተማዋ ከተጋረጠው ችግር
ምክንያት የሚበላው የአህያ ጭንቅላት ሊሆን
ይችላል፡፡ መቼም ቢሆን ልጁን ላይበላ ይችላል፡፡
የእርግንም ኩስ ይበላል ብለን አናስብ ምክንያቱም
ንጉሥ ነውና መጠነኛ ገንዘብም ይኖረዋልና ለምሳና
ለራቱ የሚቀርብለት ሻል ያለው የአህያ ጭቅላት
ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ሕዝቡን የሚቀልብበት
ምንም የተከማች ነገር ስለለለ ከምኔ እረዳሻለሁ
አለ፡፡ ንጉሥ ከማጥመቂውና ከአውድማው ይረዳል
ያለዚያ ማንንም ሊረዳ አይችልም፡፡ እግዚአብሔር
ግን ከምንም ይረዳል፡፡ ንጉሥ በጎተራው ካለው
እህል ይረዳል፣ በባንክም ካለው ገንዘብ አውጥቶ
እህል ሊሸመት ይችላል፣ ካልሆነ ግን ምንም
ሊያደርግ አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ግን
እኛን የጠራን የንጉሡን ጎተራ ተስፋ አድርጎ
ሳይሆን በራሱ ተማምኖ ነው፡፡ ስለዚህ በተአምራቱ
ረድቶን ታሪካችንን ይለውጠዋል፡፡
በዳዊት
ዘመን ከተማ ይከበባል፣ እግዚአብሔርም በዚያ
በተከበበ ከተማ ውስጥ
ያለውን ችግረኛ ይረዳል፡፡ ዛሬ ከከተማ መከበብ
ይልቅ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር
ቢኖር የሰው ሕይወት መከበብ ነው፡፡ ለአንዳንዶቻችን
ትዳራችን ተከብቦ ይሆናል፡፡ ለአንዳንዶቻችን
ጤናችን ተከቦ ይሆናል፡፡ የቱንም
ያህል ብንከበብ እግዚአብሔር እንደዚያ
ባለው ሁኔታ ውስጥ ተገልጦ
የሚያስደንቅ ርዳታ ያደርጋል፡፡ የሥራው
ሁኔታ የተከበበበት፣ የትምህርቱ ሁኔታ
ተከብቦበት ግራ የተጋባና የተጨነቀ ሰው ቢኖር
ይህ ትልቅ መልእክት ይሆንለታል ምክንያቱም
ጌታ በተከበቡ ነገሮች ውስጥ ገብቶ ታላቅና
የሚያስደንቅ ርዳታ ያደርጋል፡፡ የተከበበ
ሰው በራሱ መውጣት እንደማይችል
ሁሉ ላካችሁበት
አስጨናቂ ሁኔታ መውጣት ያቃታችሁና እያለቀሳችሁ
ያላችሁ ዓይናችሁን ወደ እግዚአብሔር
አንሡ ፣እርሱ በተከበበ ከተማ ታላቅና የሚያስደንቅ
ምሕረት ወይም ርዳታ የሚደርግ አምላክ
ነው፡፡
ሰማሪያ
ምንም የተስፋ ፍንጭ የማይታይባት ከተማ ሆና
በላችበት እግዚአብሔር ረድቶአታል፡፡ የሕዝቡንም
ሕይወት ለውጧል፡፡ እግዚአብሔር
እኛን እንዴት እንደሚረዳን በ2
ነገሥት
6፡24-7፡20
ላይ
ከተጻፈው አስገራሚ
ታሪክ ውስጥ አራት መንገዶችን እንመለከታን፡፡
1.
እግዚአብሔር
በተከበበች ከተማ ለችግረኛው ቃሉን በመላክ ይረዳል(2
ነገ
7፡1-
2)፡፡
ሕዝቡ
በመከራ ውስጥ ስንደፋደፍ፣ ሞትም ሲያስፈራው
እግዚአብሔር አይቶ ከሚያደርጋቸው ጠቃሚ
ነገሮች አንዱና ቀዳሚው ቃል መስጠት ነው፡፡
የአሥራኤልን ሕዝብ ታሪክ ሁሉ ስንመለከት
በየትኛውም ሁኔታ ያሉትን ሰዎች በየጊዜው
ነቢያቶችን በመላክ ያጽናናቸው እንደነበር
ቃሉ ምስክር ነው፡፡ የሶሪያ ንጉሥ ወልደ
አደርም ሰማሪያን በሚያሳዝን መልኩ ቢከብበውና
ቢበድለውም እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚያጽናና
መልእክት በመረጠውና በቀባው ነቢይ ኤልሳዕ
በኩል ላከለት፡፡ ኤልሳዕም ለሕዝቡ
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ
አለ፡፡ ቃሉን መስማት መረጋጋትን ያመጣል፡፡
ለምንድነው ኤልሳእ ቃሉን ስሙ የሚለውን
መልእክት
ያስቀደመው? በመከራ
ውስጥ ያለ ሕዝብ በስብከት ብዛት መጽናናት
ያቅተዋል፡፡ በተለይም ደግሞ መረር ባለ ሁኔታ
ውስጥ የሚያልፍ ሰው ቶሎ ከዚያ ወጥቶና መንገዱን
ጨርሶ ድል ማድረግን ወይም አንድ ነገር እጁ
ውስጥ ገብቶለት እፎይ ማለት እንጂ ስብከት
ብዙ አይመቸውም፡፡ ይህ የሁላችንም ችግር
ነው፡፡ በሕይወት ጨለማ በተከበብንበት ሰዓት
የሚነበብልን ቃል ሁሉ የማባባያ እንጂ እውነት
አይመስለንም፡፡ ይሁን እንጂ የነቢያትን ቃል
መስማት ወደር የማይገኝለት መፍትሔ ነው፡፡
የሚነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይሠራል እንጂ
እላማውን እንደሳተ ፍላጻ ሆኖ አይቀርም፡፡
እኔና
ቤተሰቤ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ባለንበት
ወቅት በርካታ የእግዚአብሔር ሰዎች የተለያዩ
አጽናኝ መልእክቶችን በተለያዩ ጊዜያቶች
ቢያመጡልንም እንኳን እኛ ግን ያንን ቃል ሁሉ
ማመን ሲያቅተን አይቻለሁ፡፡
እንዲያውም ከትላንትና ዛሬ በሕይወታችን
የተከሰተው ጨለማ እየጨመረ ሲሄድ ሁሉ ይሰማን
ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር የሰማናቸውም ተስፋዎች
የሚፈጸሙባቸው መንገዶች ሁሉ ጠፍተው አልቀው
ሁሉም ነገር ዝግ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ
እግዚአብሔር የሚለውን
ለማመን አቅም አንሶን እያለ ጌታ
በትምህርትና በትዳር እጅግ የባረከው
ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር አንድ ቀን ከሕይወቱ
ተሞክሮ አንድ የሚያስገርም አሳብ አካፈልኝ፡፡
ፕሮፌሰሩ እግዚአብሔርን በጣም የሚወድና
በአምላኩ ፊት ራሱን በጣም ዝቅ የሚያደርግ
ሰው ነው፡፡ እርሱ አንድ ቀን ያየውን ሕልም
እንዲህ ሲል አካፈለኝ፡፡ በአንድ ትልቅ ጉባኤ
ውስጥ ይካፈል ነበር፡፡ በሕልሙ እንዳየው
በዚያ ትልቅ ጉባኤ የእግዚአብሔርን ቃል
የሚያካፍለው አንድ ኮሪያዊ ሰባኪ ነበር፡፡
ያ ሰባኪ ለእያንዳንዱ
ሰው በስም እየጠራ መልእክት ያስተላልፍ
ነበር፡፡ ሁሉንም ካደራሰው በኋላ በመጨረሻው
ላይ ወደ ፕሮፌሰሩ ዞር አለና በስሙ ጠርቶት
You are thick minded አለው፡፡
ይህን ካለም በኋላ በተደጋጋሚ አሁን እኔ
የምልህን ሁሉ ታደርጋለህን ብሎ እየጠየቀው እያለ ከእንቅልፉ
ነቃና ይህ thick minded ማለት
ምን ማለት ነው ብሎ
መመርመር ጀመረ፡፡
የዚያ ቃል ትርጉም ደደብ ማለት ነው፡፡
እንዴት አንድ ፕሮፌሰር ደደብ ተብሎ ያውም
በአንድ የእግዚአብሔር ሰው ይሰደባል?
ጌታ
ሆይ ይህ ለምን ሆነ ብሎ በጌታ ፊት አምርሮ
ጸለየና እግዚአብሔርም መረዳትም ሰጠው፡፡
ደደብ ማለት እኮ የተነገረውን ነገር ወደ ውስጡ
የማያስገባ ፣ የማይቀበል ፣ ስለሚነገረው
ነገር በአእምሮው ሥፍራ የለሌው ሰው ማለት
እንደሆነ እግዚአብሔር አስረዳው፡:
ይህ
በሚሆንበት ጊዜ እኔ ደግሞ ባለሁበት ሁኔታ
የሚመጣውን መልእክት ሁሉ መቀበል አቅቶኝ
በችግር ውስጥ ነበርኩ፡፡ እንዲያውም የተነገረኝ
ትንቢትና የተሰበከልኝ ቃል አንዱም ሳይፈጸም
የእኔና የቤተሰቤ ነገር ከጨለማም ወደ ድቅድቅ
ጨለማ ውስጥ እየገባ ሄደ፡፡ የምንጠብቀውም
ተስፋ አንዱም ሳይፈጸም የተስፋዎቹ ምንጭ
መድረቁ እየታየን መጣ፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር
ለእኔ ያንን ሁሉ ትንቢትና የቃል ብዛት መላኩ
ለምንድነው እያልኩ ራሴን ጠየቅሁና አሁንም
ሰዎች የሚያመጡልን
መልእክቶች ምንም አስፈላጊዎች አይደሉም
ወደሚለው ድምዳሜ ውስጥ ገባሁ፡፡ እንግዲህ
በዚህ ጊዜ ነበር ፕሮፌሰሩ የሕይወቱን ተሞክሮና
ያየውን ሕልም ያካፈለኝ፡፡ እርሱ እኔ ያለሁበትን
ሁኔታ ስለሚያውቅ ሊያጽናናኝ ደውሎ ይህንን
ይንገረኝ እንጂ እኔም እንደ እርሱ ቃሉን ማመን
አቅቶኝ እየተቸገርኩ እንዳለሁ ግን
አያውቅም ነበር፡፡ ያን ጊዜ
እኔ እንዲህ አልኩ፡፡ በእርግጥ በጣም ደደቡ
እኔ ነኝ አልኩ፡፡ ስንቶቻችን ነን
በእግዚአብሔር ቃል መጽናናት የሚያቅተን?
ከሚነገረን
ቃል ይልቅ በሕይወታችን
የተጋረጠው የጨለማ ብዛት ስለሚታየን ቃሉን
ማመን እጅግ ያቅተናል፡፡ ምንም ይሁን
ምን በከባባ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ ከምንም
አስቀድማችሁ እግዚአብሔር ለልባችሁ የሚለውን
ስሙ፡፡ ቃሉ ምድረ በዳውን ያናውጣል፡፡ ቃሉ
ይሠራል፣ ነገራችሁ ቢብሞትባችም እንኳ
እግዚአብሔር ከነገራችሁ ቃል የተነሳ ወደ
ሕይወት ይመጣል፡፡
አስቸጋሪ
ሁኔታዎች ውስጥ ስንገባና ዙሪያችን ሁሉ ጨለማ
ሲሆን እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል የውሸትም
ሊመስለን ይችላል፡፡ ንጉሡ ተደግፎበት የነበረ
አለቃ ኤልሳእ የሚነገረውን መልእክት ሰምቶ
እግዚአብሔር
በሰማይ መስኮት ቢያደርግ ይህ ነገር ይሆናልን
ያለው የመከራው ጥልቀትና የሚነገረው ነገር
አብሮ አልሄድ ስላው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ የማያደርገውን
ሳይሆን ሊያደርግ ያለውን ነበረና የተናገረው
ያውም ሆነ፡፡ በቁጥር 18
ላይ
የእግዚአብሔር ሰው ለንጉሡ፡-
ነገ
በዚህ ጊዜ በሰማሪያ በር ሁለት መስፈሪያ ገብስ
በአንድ ሰቅል፣አንድ መስፈሪያ መልም ዱቄት
በአንድ ሰቅል ይሸመታል ብሎ እንደተናገረው
ቃል እንዲሁ ሆነ ይላል፡፡ አዎን ሁኔታዎችን
ካየን ምንም የማይቻል ይመስላል፡፡ እግዚአብሔር
ከተነገረ ግን የማይቻል በሚመስል ሁኔታ ውስጥ
አስደናቂ ሥራውን ይሠራል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል እንስማ፡፡ እርሱም የተናገረውን ቃል በሕይወታችን ሲፈጽመው እናያለን፣ መከራችንንም እንረሳዋለን፡፡
2.
እግዚአብሔር
በተከበበች ከተማ ችግረኛውን ፈጥኖ ይረዳል(
2 ነገሥ
7፡1-2)
፡፡
ነቢዩ
ኤልያስ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በሚል ብቻ
አያበቃም፡፡ እግዚአብሔር ለዚያ በችግር
ውስጥ ላለው
ሕዝብ ሊያደርግ ያለው ነገር ምን
እንደሆነም
ጭምር ይናገራል ፡፡ በሰማሪያ በር አንድ
መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል፣ሁለት
መስፈሪያ ገብስ በሁለት ሰቅል ይሸመታል ማለትም
እግዚአብሔር የሚያደርገው ይህ ነው፡፡ በምዕራፍ
6 ፡
27 ላይ
እንደምንመለከተው
መጥመቂያም ሆነ አውድማ አልነበረም፡፡ ታዲያ
እንዴት ገብስና ዱቄቱ ሊሸመት ይችላል? ከየትስ መጥቶ? እግዚአብሔር
የሚረዳው ፈጥኖ ነው እንድንል
የሚያደርገን ይህ ነው፡፡
ይህ ሁሉ የሚሆነው በሚያስገርም ሁኔታ በ24 ሰዓት
ውስጥ ታሪክ ሁሉ ሲገለበጥ ነው፡፡ በዚህ ክፍል
ኤልሳዕ ነገ በዚህን
ሰዓት የሚል ቃል
ተጠቅሟል፡፡ ይህ ገብስና ዱቄት የሚሸመተው
በሰማሪያ በር መሆኑን መስማት በውስጥ ያለው
ሕዝብ እንዳያምን
ምክንያት
ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የሰማሪያ
በር እኮ በወልዴአደር ሠራዊት
ተከብቧል፡፡ እንዴት ተደርጎ
ነው በዚያ ቦታ እህል የሚሸመተው?
የእግዚአብሔር
ነገር ተአምር ነው የሚባለው ከሰው አእምሮና
አስተሳሰብ ያለፈ ነገር ስለሆነ ነው፡፡
በአንዲት
መጥመቂያና
አውድማ በለላት፣ ጎተራው በባዶ በሆነባትና
እርሻ ተስፋ በማይደረግባት ሁኔታ ውስጥ ባለች
ከተማ ስንዴ እንዲሸመት ከተፈለገ ሕዝቡ
አስቀድሞ ካለበት ሁኔታ መውጣትና እርሻውን
ማረስ ስንዴውንም መዝራትና ማጭድ ነበረበት፡፡
ይህ ደግሞ ቢያንስ ከሦስት እስከ አራት ወር
ያልህ ጊዜ ሊፈልግ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር
ግን ይህንን ቅድመ ሁኔታ ሳይጠብቅ ፣ እርሻና
ጎተራ ሳያሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ ገብስና
ዱቄት እንደሚሸምቱ አረጋገጠላቸው፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ታሪክ ተለውጦ ለእርግብ ኩስና ለአህያ ጭንቅላት የሚውለው በጀት ለገብስና ለዱቄት ይዞራል ማለት ነው፡፡ በነጻ
ምድር ለሚኖር ሕዝብ ጊዜውን ጠብቆ ቢሠራም
በጭንቅና በመከራ ውስጥ ለሚሰቃየው ሕዝብ
ሲል ፈጥኖ ይነሳል ፣ ፈጥኖም ይፈርድለታል፡፡
እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ያረገውን ምሳሌ ኢየሱስ ያስተማረን ለዚህ ነው(ቃሰ 18፡1-8)፡፡ ዳኛውና መበለቲቱ ሁለቱ በጣም ተቃራኒ ሰዎች ናቸው፡፡ ዳኛው ከሰውም ሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ሕብረት የተበለሸበት ፣ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውን የማያፍር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ህግ የቅንጣት ያህል የማይገደው ነው፡፡ ለፍትህና ለሌላው ጉዳያቸው ወደ እርሱ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ የተለየና ጨካኝ የሆነ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ሕግም ሆነ በሰው ምህበራዊ ጉዳይ ማንም ጥሶ ሊያልፈው እስከማይችለው ድረስ አስፈፈሪ የሆነና ለሁሉም ግድ የሌለው ሰው ነው፡፡ ለአምልኮ ቦታ አይሰጥም፡፡ በሐዘን ተጎድቶ የሚያለቅስ ሰው ካየም ምንም የማይሰማው ነው፡፡ ዳኛ የሚል ስም ይሰጠው እንጂ ኢየሱስ እንደተናገረው አመጸኛ ዳኛ ነው፡፡ የዚህ ሰው ዓመጽ ደግሞ በጣም መርዘኛ የሆነ አመጽ ነው፡፡ ዳኞች በብዛት ማሕበራዊ ፍርድ ቤት የሚሠሩ ናቸው፡፡ ኢየሩሳሌምን በሚመስሉ ከተሞች በየቦታው ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች መኖራቸው ያታወሳል፡፡ በእሥራኤል ሕዝብ መካከል በመንግሥታቸውም የሚቀመጠው የፍርድ ቤት ዳኛ ስለ ብሉይ ኪዳን ሕግ ጠንቅቆ የሚያውቅና ያንን የሚያስከብር መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ለሰውም ስሜትና ሀዘን ሪኅራኄ ያለው እንዲሆንም ይፈለግበታል፡፡ ይህ አማጸኛ ዳኛ ግን ከዚህ ሁሉ እውቀት ውጭ የሆነ ሰው ነው፡፡ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በሚገዛባቸው ቦታዎች ሁሉ ዳኞችን እንዳስቀጣቸውና መመሪያም እንደሰጣቸው እንመለከታለን፡፡ የሰጠውም መመሪያ እንዲህ የሚል ነው፡፡ በምድር ላይ በተመሸጉ የይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ፈራጆችን አኖረ፡፡ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱና ፣ እርሱም በፍርድ ነገር ከእናንተ ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ፡፡ አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና በሰው ፊት ማድላት መማለጃንም መውሰድ የለምና ሁሉንም ተጠንቅቃችሁ አድርጉ ኣላቸው( 2 ዜና 19፡)፡፡ በእሥራኤል ላይ የሚሾም ዳኛ ይህንን ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ኢየሱስ በምሳሌው ያቀረበው ያ ዳኛ ኢዮሳፍጥ ለእሥራኤል ዳኞች የሰጠው ይህ መመሪያ የማይገዛው ዓይነት ፍጹም አመጸኛና ጨካኝ የሆነ ዳኛ ነው፡፡ ከዚህ ዳኛ ፍትሕ ፈልጋ ወደ ፊቱ የምትመጣው ሴት ደግሞ መበለት ናት፡፡ ከባላጋራዬ ሕጋዊ ጥበቃ ስጠኝ እያለች ትመጣለች፡፡ ከዳኛው ጋር ሲነጸጸር የምታሳዝንና ሚስክን ሴት ነች፡፡ እቤቷ ሊያግዛት የሚችል ወንድ ማለትም አባት፣ ባል፣ ወንድ ልጅ፣ ወንድም፣ የልጅ ልጅ፣ የባል ወንድም ወዘተ የሌላት የመጨረሻ ሚስክንና አሳዛኝ ሴት ናት፡፡ ወደ ዳኛ ከመመላለስ ያለፈ የምታማከረው ሰው እቤቷ የሌላት ብቸኛ ና የተቸገረች ሴት ናት፡፡ ኢየሱስ በምድር በመካካለኛ ምሥራቅ የነበረው የፍርድ ቤት ሁኔታ ለዚህች ሴት እጅግ በጣም ፈታኝ ነው፡፡ በእነርሱ ባህልና ደንብ መሠረት ሴት ወደ ፍርድ ቤት አትቀርብም ፣ የሚቀርቡት ወንዶች ብቻ ናቸው፡፡ አቤቱታ ካላቸውም ከላይ በተጠቀሱት ወንድ ዘመዶቻቸው አማካይነት እንጂ ራሳቸውን ችለው ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው መሟገት አይችሉም ነበር፡፡ ፍርድ ቤት የሚፈቀደው ለወንዶች ብቻ ነው፡፡ አንዲት ሴት ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ የምትችለው እቤቷና በዘመዶችዋ መካካል ወንድ ሌላት ከሆነች ብቻ ነው፡፡ ታዲያ ይህች ሁሉን ያጣች መበለት በባሕሪው ዓመጸኛ ወደ ሆነው ዳኛ እንዴት ልትቀርብና መብትዋን ልታስከብር ትችላለች? ይህች ሴት አቅመ አልባ፣ ዘመደ-አልባና ብቸኛ ናት፡፡የህግ ከላላ ያጣች፣ የምንከባከባት የሌላት ፣ ማንም የማያስባት ሆና ይህ ሁሉ ሳያንስ ባላንጣ የጎዳት ናት፡፡ በዘዳግም 22፡22 ላይ የእግዚአብሔር ቃል መበለቱንና የደሀ ፍረዱላቸው ይላል፡፡ ሉቃስ በወንጌሉ ያቀረበልን መበለት ግን የተገፋች ናት፡፡ በአመጸኛ ዳኛና በእርሷ መካካል ያለው ልዩነት ይህን ያህል ከፍ ያለ ሆኖ እርሷ ግን ያለማቋረጥ ፍረድልኝ እያለች ትመጣ ነበር፡፡ ዳኛውም ከጭቅጭቋ ለመገላገል ሲል እንዳታውከኝ እፈርድላታሁ ብሎ ፈረደላት ይላል፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ይህንን ምሳሌ ሲያጠቃልል በፊቱ ለሚጮኹ ለሚታገሳቸውም ለምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል አለ፡፡ የእግዚአብሔር ፍርድ ፈጣን ነው፡፡ በመከራና በችግር ውስጥ ሆነው በፊቱ ለሚያለቅሱና ለሚጮኹ እግዚአብሔር አይዘገይም፡፡ የደሀውን መከራና፣ የችግረኛውን ጩሔት ያያል፣ በእርሱም ላይ ይነሳል ይላል ዳዊት በመዝሙሩ ላይ ምእራፍ 12፡5 እግዚአብሔር "አሁን" እነሳለሁ ይላል ብሎ ይነግረናል፡፡ እኛ ስንጮህ እርሱ አሁን አይመቸኝም የሚል ዳኛ አይደለም፡፡ ጠበቃችንም ኢየሱስ በጉዳዩ ላይ የማሰቢያ ጊዜ ይሰጠኝ ሳይል ዳኛውም ሌላ ምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል ሳይል ፈጥኖ ይፈርድልናል፡፡ ስለዚህ ነው በተከበበች ከተማ በሰማሪያ ያሉትን ሕዝብ ነቢዩ ኤለሳዕ እግዚአብሔር አምላክ በ24 ሰዓት ውስጥ ታሪካችሁን ይለውጠዋል ያለው፡፡ እግዚአብሔር የተጠቁትን ያያል ፣ የተራቡትን ያያል፣ የሚያለቅሱትንም ይመለከታል፡፡ የተጠቁትን እያየ ዝም አይልም ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፡፡
እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ያረገውን ምሳሌ ኢየሱስ ያስተማረን ለዚህ ነው(ቃሰ 18፡1-8)፡፡ ዳኛውና መበለቲቱ ሁለቱ በጣም ተቃራኒ ሰዎች ናቸው፡፡ ዳኛው ከሰውም ሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ሕብረት የተበለሸበት ፣ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውን የማያፍር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ህግ የቅንጣት ያህል የማይገደው ነው፡፡ ለፍትህና ለሌላው ጉዳያቸው ወደ እርሱ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ የተለየና ጨካኝ የሆነ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ሕግም ሆነ በሰው ምህበራዊ ጉዳይ ማንም ጥሶ ሊያልፈው እስከማይችለው ድረስ አስፈፈሪ የሆነና ለሁሉም ግድ የሌለው ሰው ነው፡፡ ለአምልኮ ቦታ አይሰጥም፡፡ በሐዘን ተጎድቶ የሚያለቅስ ሰው ካየም ምንም የማይሰማው ነው፡፡ ዳኛ የሚል ስም ይሰጠው እንጂ ኢየሱስ እንደተናገረው አመጸኛ ዳኛ ነው፡፡ የዚህ ሰው ዓመጽ ደግሞ በጣም መርዘኛ የሆነ አመጽ ነው፡፡ ዳኞች በብዛት ማሕበራዊ ፍርድ ቤት የሚሠሩ ናቸው፡፡ ኢየሩሳሌምን በሚመስሉ ከተሞች በየቦታው ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች መኖራቸው ያታወሳል፡፡ በእሥራኤል ሕዝብ መካከል በመንግሥታቸውም የሚቀመጠው የፍርድ ቤት ዳኛ ስለ ብሉይ ኪዳን ሕግ ጠንቅቆ የሚያውቅና ያንን የሚያስከብር መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ለሰውም ስሜትና ሀዘን ሪኅራኄ ያለው እንዲሆንም ይፈለግበታል፡፡ ይህ አማጸኛ ዳኛ ግን ከዚህ ሁሉ እውቀት ውጭ የሆነ ሰው ነው፡፡ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በሚገዛባቸው ቦታዎች ሁሉ ዳኞችን እንዳስቀጣቸውና መመሪያም እንደሰጣቸው እንመለከታለን፡፡ የሰጠውም መመሪያ እንዲህ የሚል ነው፡፡ በምድር ላይ በተመሸጉ የይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ፈራጆችን አኖረ፡፡ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱና ፣ እርሱም በፍርድ ነገር ከእናንተ ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ፡፡ አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና በሰው ፊት ማድላት መማለጃንም መውሰድ የለምና ሁሉንም ተጠንቅቃችሁ አድርጉ ኣላቸው( 2 ዜና 19፡)፡፡ በእሥራኤል ላይ የሚሾም ዳኛ ይህንን ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ኢየሱስ በምሳሌው ያቀረበው ያ ዳኛ ኢዮሳፍጥ ለእሥራኤል ዳኞች የሰጠው ይህ መመሪያ የማይገዛው ዓይነት ፍጹም አመጸኛና ጨካኝ የሆነ ዳኛ ነው፡፡ ከዚህ ዳኛ ፍትሕ ፈልጋ ወደ ፊቱ የምትመጣው ሴት ደግሞ መበለት ናት፡፡ ከባላጋራዬ ሕጋዊ ጥበቃ ስጠኝ እያለች ትመጣለች፡፡ ከዳኛው ጋር ሲነጸጸር የምታሳዝንና ሚስክን ሴት ነች፡፡ እቤቷ ሊያግዛት የሚችል ወንድ ማለትም አባት፣ ባል፣ ወንድ ልጅ፣ ወንድም፣ የልጅ ልጅ፣ የባል ወንድም ወዘተ የሌላት የመጨረሻ ሚስክንና አሳዛኝ ሴት ናት፡፡ ወደ ዳኛ ከመመላለስ ያለፈ የምታማከረው ሰው እቤቷ የሌላት ብቸኛ ና የተቸገረች ሴት ናት፡፡ ኢየሱስ በምድር በመካካለኛ ምሥራቅ የነበረው የፍርድ ቤት ሁኔታ ለዚህች ሴት እጅግ በጣም ፈታኝ ነው፡፡ በእነርሱ ባህልና ደንብ መሠረት ሴት ወደ ፍርድ ቤት አትቀርብም ፣ የሚቀርቡት ወንዶች ብቻ ናቸው፡፡ አቤቱታ ካላቸውም ከላይ በተጠቀሱት ወንድ ዘመዶቻቸው አማካይነት እንጂ ራሳቸውን ችለው ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው መሟገት አይችሉም ነበር፡፡ ፍርድ ቤት የሚፈቀደው ለወንዶች ብቻ ነው፡፡ አንዲት ሴት ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ የምትችለው እቤቷና በዘመዶችዋ መካካል ወንድ ሌላት ከሆነች ብቻ ነው፡፡ ታዲያ ይህች ሁሉን ያጣች መበለት በባሕሪው ዓመጸኛ ወደ ሆነው ዳኛ እንዴት ልትቀርብና መብትዋን ልታስከብር ትችላለች? ይህች ሴት አቅመ አልባ፣ ዘመደ-አልባና ብቸኛ ናት፡፡የህግ ከላላ ያጣች፣ የምንከባከባት የሌላት ፣ ማንም የማያስባት ሆና ይህ ሁሉ ሳያንስ ባላንጣ የጎዳት ናት፡፡ በዘዳግም 22፡22 ላይ የእግዚአብሔር ቃል መበለቱንና የደሀ ፍረዱላቸው ይላል፡፡ ሉቃስ በወንጌሉ ያቀረበልን መበለት ግን የተገፋች ናት፡፡ በአመጸኛ ዳኛና በእርሷ መካካል ያለው ልዩነት ይህን ያህል ከፍ ያለ ሆኖ እርሷ ግን ያለማቋረጥ ፍረድልኝ እያለች ትመጣ ነበር፡፡ ዳኛውም ከጭቅጭቋ ለመገላገል ሲል እንዳታውከኝ እፈርድላታሁ ብሎ ፈረደላት ይላል፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ይህንን ምሳሌ ሲያጠቃልል በፊቱ ለሚጮኹ ለሚታገሳቸውም ለምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል አለ፡፡ የእግዚአብሔር ፍርድ ፈጣን ነው፡፡ በመከራና በችግር ውስጥ ሆነው በፊቱ ለሚያለቅሱና ለሚጮኹ እግዚአብሔር አይዘገይም፡፡ የደሀውን መከራና፣ የችግረኛውን ጩሔት ያያል፣ በእርሱም ላይ ይነሳል ይላል ዳዊት በመዝሙሩ ላይ ምእራፍ 12፡5 እግዚአብሔር "አሁን" እነሳለሁ ይላል ብሎ ይነግረናል፡፡ እኛ ስንጮህ እርሱ አሁን አይመቸኝም የሚል ዳኛ አይደለም፡፡ ጠበቃችንም ኢየሱስ በጉዳዩ ላይ የማሰቢያ ጊዜ ይሰጠኝ ሳይል ዳኛውም ሌላ ምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል ሳይል ፈጥኖ ይፈርድልናል፡፡ ስለዚህ ነው በተከበበች ከተማ በሰማሪያ ያሉትን ሕዝብ ነቢዩ ኤለሳዕ እግዚአብሔር አምላክ በ24 ሰዓት ውስጥ ታሪካችሁን ይለውጠዋል ያለው፡፡ እግዚአብሔር የተጠቁትን ያያል ፣ የተራቡትን ያያል፣ የሚያለቅሱትንም ይመለከታል፡፡ የተጠቁትን እያየ ዝም አይልም ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፡፡
3. በተከበበ
ከተማ እግዚአብሔር ችግረኛውን
ባልተጠበቀ መንገድ ይረዳል(2
ነገሥ
6፡3-8)፡፡
እኛ የእግዚአብሔር ርዳታ የምንጠብቅበት የራሳችን
የሆነ መንገድ ይኖረናል፡፡ ያ መንገድ ግን
እኛው ራሳችን የቀየስነው የእኛው መንገድ እንጂ
እግዚአብሔር ያንን መንገድ
ላይጠቀምበት ይችላል፡፡ እኛ ያላየነው ሌላ
የእርሱ መንገድ አለውና፡፡ በሰማሪያ ከተማ
ውስጥ ከተከሰተው ረሀብ የተነሳ ልጇን ቀቅላ
የበላች ሴት ለፍትህ ፍለጋ የሄደችው ወደ ንጉሡ
ነበር ምክንያቱም በእርሷ ዓይን የሚታየው
እርሱ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ የመፍትሔዋ መንገድ
ያደረገችውም ይህንን ብቻ ነው፡፡ በዚያ
ከተማ ውሰጥ ሁለት ሥልጣናት ነበሩ፡፡ አንደኛው
ምድራዊ ሥልጣን ሲሆን ሁለተኛው መንፈሳዊ
ሥልጣን ነበር፡፡ የምድራዊ ሥልጣኑ ያለው
በንጉሡ እጅ ሲሆን እርሱ ለሕዝቡ መከራ መፍትሄ
ሊያመጣ እስከማይችል ድረስ ችግሩ ከአቅሙ
በላይ ሆኖበታል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር
ስላልረዳችሁ እኔም ልረዳችሁ አልችልም ብሎ
ደምድሟል፡፡ መንፈሳዊ ሥልጣን የምንለው
ደግሞ የእግዚአብሔር ሥልጣን ነው፡፡እግዚአብሔር
በኤልሳ በኩል እየሠራ ነው፡፡ ፍትሕ ፈላጊዎቹ
ግን ወደ ኤልሳእ ሳይሆን ወደ ንጉሡ ነበር
አስቀድመው የሄዱት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሕይወት
መከበብ ሲገጥመን ወደ ማን መሄድ እንዳለብን
እንኳ ይጠፋብናል፡፡ በአይናችን በሚታየው
ንጉሥ እጅ መላ ያለን ይመስለንና ወደ እግዚአብሔር
መጮኹን የምንረሳበት ሁኔታ ሊገጥመን ሁሉ
ይችላል፡፡እግዚአብሔር ግን
የራሱ የሆነ ለእኛ ያዘጋጀልን ሌላ የመላ መንገድ አለው፡፡
በዚህ ንባብ ክፍል እንደምንመለከተው እግዚአብሔር
በበር ላይ የተቀመጡ አራት ለምጸሞችን ተጠቅሞ
የከተማውን ታሪክ ቀየረ፡፡ ቃሉን ልብ ብለን
የተመለከትን እንደሆነ አራቱ ለምጻሞቹ ያሉት
በከተማው በር ላይ ነው፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው
በሰማሪያ በር የሶሪያ ወታደሮች ስላሉ ማንም
የከተማ ሰው እዚያ አካባቢ ሊቀርብ
አይችልም፡፡ ታዲያ እነዚህ አራት ለምጻሞች
እንዴት እዚያጋ እንደተገኙ
ያስደንቃል፡፡ በከተማው ውስጥ
እንዳይኖሩ ተፈጥሮአቸው
አልፈቀደላቸውም ምክንያቱም ለምጻሞች ናቸው፡፡
ለምፅ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ የእግዚአብሔር
ቅጣትና የርኩሰት ምሳሌ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
የለምጻምና የለምጽ ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ ከ40
ጊዜ
በላይ ተጠቅሷል፡፡ የሙሴ ሕግም ለምጻሞችን በሚመለከት ለእሥራኤል ልጆች
ግልጽ የሆነ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ማንም
በሰውነቱ ላይ ይህ በሽታ እንዳለበት በጠረጥር
ራሱን በካህን ያስመረምርና በሽታው መኖሩ
ከተረጋገጠ ከሰው ሁሉ ተለይቶ ለብቻ እንዲቀመጥ
በሕግ ታዟል(ዘሌ.
13፡2-3፣45-46)፡፡
እንዲህ ዓይነት ምልክት በሰውነቱ ያለበት
ሰው ከከተማ ውጭ ካምፕ ሰርቶ እዚያ መቀመጥ
እንዳለበት በሕግ ተቀምጧል፡፡ ምክንያቱም
ለምጽ በፍጹም አካላዊና መንፈረሳዊ ርኩሰት
ተደርጎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ ብዙዎች እግዚአብሔር
ሰው ኃጢአት ሲሠራ ሊድን በማይችል ለምጽ
ስለሚመታ ይህ የኃጢአት ውጤት ነው ብለው ያምኑ
ነበር፡፡ በዘኁልቁ 5፡2
ላይ
እንደምንመለከተው እንዲህ ዓይነት ችግር
ያለበት ሰው
ከራሱ ሕብረተሰብ
ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር አይፈቀድለትም ነበር፡፡
እንዲያውም በጥንት አይሁዶች ሕግ መሠረት
ለምጽ ያለበት ሰው ወደ ቤተሰቡም ሆነ ወደሌላ
ሰው ከስድስት ጫማ በበለጠ ርቀት እንጂ ከዚያ
ያህል አልፎ መቅረብ እንደለለበት ይደነግጋል፡፡
በጊዜው የነበሩ ሰዎች ለምጽን
እንደ ዘግናኝ ነገር ስለሚቆጥሩ ነፋስ በሚነፍስበት
ወቅት ሕመምተኛው ከሌላው ሕዝብ 150
ጫማ
ያህል ራቅ
ብለው መቆም ይጠበቅበት ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ
የተነሳ የሰማሪያ ለምጻሞች በህብረተሰቡ
መካካል መኖር ስለማይችሉ ከከተማው ተሰድደው
ወደ ዳር የወጡ ገለልተኞች ነበሩ፡፡ ወደ
ሌላውም ሕዝብ ሳይሄዱ እዚያው በበሩ አካባቢ
ድንኳን ሠርተው ተቀመጡ፡፡ የሚያስገርመው
ግን እግዚአብሔር የሕዝቡን ጩኼት ሰምቶ ለማዳን
እነዚህን የተናቁትን ተጠቀመ፡፡ ንጉሡን
እንዳይጠቀም ንጉሡ ነፍሱን ለማዳን ሲል በከተማ
ውስጥ መሽጓል፡፡ ሌሎችን እንዳይጠቀም ሁሉም
እግዚአብሔር የሚረዳ አልመሰላቸውም፡፡ ነገር
ግን እግዚአብሔር የኃይሉን ታላቅነት ለማሳየት
የተናቁትን ተጠቀመ፡፡ የእግዚአብሔር
ጊዜ ስለደረሰ
እነዚህ አራቱ ለምጻሞች እርስ በእርሳቸው
መመካከር ጀመሩ፡፡ እስክንሞት
ድረስ በዚህ
ለምን እንቀመጣለን ወደ ከተማ እንገባ
ዘንድ
ብንወድድ ረሀብ በዚያ አለ በዚያም እንሞታለን
በዚህም ብንቀመጥ እንሞታለን ፡፡ እንግዲህ
ኑ ወደ ሶሪውያን ሠፈር እንሽሽ፣ በሕይወት
ቢያኖሩን እንኖራለን፣ ብገድሉንም እንሞታለን
ተባባሉ፡፡ እግዚአብሐሔር
የተጠቀመበት መንገድ ይህ ነው፡፡ ይህ እጅግ
በጣም አስደናቂና አስገራሚ
አሠራር ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶችን ሰዎች እግዚአብሔር ለሥራው ይመርጣቸዋል ብሎ ማን ያስበል? በአንድ ከተማ ውስጥ እንደሌላው ሰው የመኖር
ነጻነት አጥቶ የተገፋና የተገለለ ወገን ንጉሥን
ያቃተው መከራ ለመለወጥ መፍትሄ የሚመጣበት
መንገድ ይሆናል
ብሎ ማንም ሊያስብ አይችልም፡፡ በተለይም
ሰማሪያውያን ይህንን የሚቀበሉበት አቅም አይኖራቸውም፡፡
እግዚአብሔር ልኮናል ብለው ለምጻሞቹ አስቀድሞ
ቢመጡ እንኳን እግዚአብሔር በለምጻም
የሚያድነን ሰው አጥቶ ነው ወይ ሁላ ሊሉ ይችላሉ፡፡ የብዙ የእግዚአብሔር ሕዝቦች
ችግር ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔር
እንደሚያይ
ማየት ስለሚሳነን እግዚአብሔር
የመረጠውን መንገድ መቀበል እንቸገራለን፡፡
በሕይወታችን ችግርና መከራ ሲገጥመን ከዚያ
ለመውጣት አይናችንን የሚናነሳው
ወደ ትልቅ ተራራ፣ ወደ ሀብታም፣ ወደ ጉልበተኛ
ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን የኃያላንን ኃይል
ለማዋረድ ደካማውን መሣሪያው አድርጎ
ይጠቀምበታል፡፡ ለመፍቴአችን መንገዱን ከግራ
ብንጠብቅ እግዚአብሔር መላውን ከቀኝ በኩል
ሊያመጣልን
ይችላል፡፡ ከቀኝም
ስንጠብቅ የእግዚአብሔር ማዳን ከግራ
በኩል ሊመጣ ይችላል፡፡ ወዳጃችንን
ተስፋ ስናደርግ ጠላታችንን የትግራችን መፍትሔ
ሊያድርግልን ይችላል፡፡ ይህ እግዚአብሔርንና
የእርሱን ሥራ አስደናቂ ያድርገዋል፡፡
እግዚአብሔር
አብቅቷል ማለት እችልም፡፡ እርሱ እኛ አቅቶን
ስንተው አዲስ አድርጎ ይጀምራል፡፡ ነገራችን
ሳይሞት እንዲደርስና እንዲፈውስልን ስንጠብቅ
ሁሉም ነገር ሞቶ ከተቀበረ በኃላ ይደርሳል፡፡ ይህንን የሚያደርገው ወደ እኛ የሚመጣበት መንገዱ ስለረዘመበት አይደለም፡፡ የእርሱ ክብር ያለው እኛ በምንጠብቀው ሁኔታ
ሳይሆን በጭራሽ በልባችንም በአእምሮአችን
ባላሰብነው ሁኔታ በመሥራቱ ነው፡፡ ስለዚህ
በተከበበ ሕይወት ውስጥ ያለን፣ በበሸታ
የተጎዳን፣ በችግርና በመከራ የተጠቃን ፣
ነገር ሁሉ የተዘጋብን ፣ እግዚአብሔርም
የሚያየን ያልመሰለን ሁሉ የእግዚአብሔር
መንገድና አሠራር ከእኛ ፍጹም የተለየ ስለሆነ
በእርሱ ላይ እንረፍ፣ እንታመንበት፣
እንጠብቀውም፡፡ እርሱ እኛ ባልጠበቅነው
መንገድ መጥቶ ታሪካችንን ይለውጠዋል፡፡
4.
እግዚአብሔር
በተከበበች ከተማ ችግረኛውን ለመረዳት ለጠላት
አስደናጋጭ ድምጽ ያሰማል(2
ነገሥ.
7፡6-7
)፡፡
በሰማሪያ
በር ያሉ ለምጸሞች ወደ ከተማ ገብተው በረሀብ
ከሚሞቱ ይልቅ የመኖርና ያለመኖር
ተስፋ ይዘው ወደ ሶሪያውያን ሰፈር መዝለቃቸውን
ከፍ ብሎ
ተመልክተነዋል፡፡ ቢያንስ በሶሪያውን ሰፈር
ምግብ አለ፡፡ ሶሪያውያን ካልገደሉአቸው
ለምጸሞቹ መኖር የሚችሉባቸው እድሎች የተረጋገጠ
ሲሆን ይህም ደግሞ በከተማው ውስጥ ካለው ሕዝብ
ይልቅ የተሸለ ሕይወት እንዲለማመዱ
ያስችላቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ የአህያ
ጭንቅላት፣ እርግብ ኩስ በገንዘብ ገዝቶ
፣ ገንዘብ የሌለው ደግሞ የገዛ ልጁን አርዶ
በሚበላበት መራራ ሕይወት
ውስጥ ሲዘፈቅ እግዚአብሔርን የማያውቅና
የማያመልክ ሕዝብ ደግሞ እህል
ተርፎት ማየት የሰውን ሕይወት ተገላቢጦሽ
ያደርገዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ግን እንደዚሁ ሊቀጥል
አይችልም፡፡ የሰማሪያ ለማጸሞች ማንም
ሳይልካቸው ነፍሳቸውን ከረሀብ ለማዳን ወደ
ሶሪያውያን መንደር ሲገቡ እግዚአብሔር
ሶሪያውያን የሰረገላና የፈረስ የብዙም ጭፍራ
ድምጽ አሰምቶ ነበር፡፡ እርስ በርሳቸውም
፡- እነሆ
የእሥራኤል ንጉሥ የኬጢያውንና የግብጻውያንን
ንገሥት ቀጥሮ አምጥቶብናል
ይባባሉ ነበር፡፡ ስለዚህ ተነስተው በጨለማ
ሸሹ( ቁ.6)፡፡
ካነበብነው
ምዕራፍ ስድስትና ምዕራፍ ሰባት
እንደምንረዳው እግዚአብሔር
ሁለት ዓይነት
ድምፆችን ያሰማል፡፡ አንደኛው ሕዝቡን
የሚያጽናናበት ድምጹ ነው፡፡ በቁጥር አንድ
ላይ በነቢዩ ኤልሳዕ አማካይነት የእግዚአብሔርን
ቃል ስሙ ነገ በዚህን
ጊዜ በሰማሪያ በር አንድ መስፈሪያ መልካም
ዱቄት በአንድ ሰቅል ሁለት መስፈሪያ ገብስ
በአንድ ሰቅል
ይሸመታል
የሚል የሚያጽናና
መልእክት ላከላቸው፡፡ ይህ መልእክት ለሰማሪያ
ሕዝብ እንጂ ለሶሪያውያን አይገባቸውም፡አልሰሙትምም፡፡
እግዚአብሔር
አምላክ ሕዝቡን በመከራቸው ጊዜ ያለ ተስፋ
እንደማይተዋቸውና ዝም እንደማይላቸው የተረጋገጠ
ነው፡፡ ሁለተኛው ድምፅ ደግሞ እግዚአብሔር
ለሕዝቡ ጠላቶች የሚያሰማው
ድምጽ ሲሆን ይህንን በቁጥር 6
ላይ
የምናነበው ነው፡፡ በዚህን ጊዜ የእሥራኤል
ሕዝብ ጠላት ሶሪያውያንና የሶሪያውን ንጉሥ
ናቸው፡፡ እውነት እንነጋገር ካልን በሶሪያውያንና
በእሥራኤላውያን መካከል ምንም ዓይነት ፈረስም
ሆነ ሠረገላ አልነበረም፡፡ የእግዚአብሔር
ሕዝብ ጠላቶች ምንም ፈረስ በሌለበት የፈረስን
ድምጽ የሚሰሙ ፣ሠረገላም
በሌለበት የጦር ሠረገላ ሲሰግር ዓይነት ግርርግ
ሰምቶአቸው ያሉበትን ቀዬ ጥለው የሚኮበልሉ
ዓይነት ናቸው፡፡ ይህንን ድምጽ እግዚአብሔር
ለሶሪያውያን እንዳሰማቸው ሰማሪያው በፍጹም
አያውቁም ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በሰረገላና
የፈረስ ድምጽ አሰምቼአቸው አራወጥኩአቸው
ብሎ ለእሥራኤል ሕዝብ
አልነገራቸውም፣ የመንገርም ግዴታ አልነበረበትም፡፡
እግዚአብሔር
እኔን አያየኝም፣ በጠላቴ ስረገጥ ዝም ብሎኛል፣ የምንልባቸው
ጊዜያቶች ብዙ ናቸው፡፡ ይህንን የምንለው
እግዚአብሔር
ስለ እኛ እየሠራ ያለውን ሥራ ስለማናውቀው
ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛ በማናየውና በማንሰማው
ሁኔታ ስለእኛ
እየተዋጋና እየተሟገተ ነው፡፡ ያዕቆብ በላባ
ቤት 20 ዓመት
ከተገዛበት ሁኔታ ወጥቶ እግዚአብሔር
ወደሚያሳየው በቦታ ሲሄድ ጉልበቱን
መበዝበዝ የለመደው ላባ እንደገና በባሪነት
ሊይዘው እንደተከተለውና እግዚአብሔር
ጣልቃ ገብቶ ባሪያዬን ያእቆብን በክፉ
እንዳትናገረው
ተጠንቀቅ እንዳለው
እንመለከታለን፡፡ ይህ ሲሆን ያዕቆብ አላወቀም
ነበር፡፡ እግዚአብሔርና ላባ ብቻ ናቸው
የተገናኙት፡፡ ዛሬም እንደዚሁ ነው ፡፡
የእሥራኤል ሕዝብ በሰማሪያ
ከተማ ውስጥ
ተከበው እያሉ እግዚአብሔር ለሶሪያውያን
የፈረስና የሰረገላ ድምፅ ያሰማቸው እነርሱን
ነፃ ለማውጣት ሲል ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ
አስደናቂ የእግዚአብሔር ሥራ ነው፡፡ እኛ
ግን ይህን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ
ስለማናውቀውና
ስለማይታየን ጌታ ረስቶናል ብለን እናጉረመርም
ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ሁል ጊዜም በሥራ
ላይ ነው፡፡ እኛ ስንደክም ስናዝንና ስንጎዳ
እርሱ የረሳን ይምሰለን እንጂ አምላካችን
አሁንም በሥራ ላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር
የተጠቃውን ሕዝብ ሥራ እየሠራ ለመሆኑ የሰማሪያ
ሰዎች እግዚአብሔር እንደተናገረው ቃል
በተባለውም ሰዓት ገብስና ዱቄት መሸመታቸው
ራሱ ምስክር ነው፡፡ በሰማሪያ በር የተሸመተውን
ዱቄት የፈጨው ማን ነው ብለን እንጠይቅ ፡፡
ገብሱንስ የወቃው ማን ነው የሚለውን እናክልበት
እስቲ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነገረን
አራቱ ለምጻሞች
ወደ ሶሪያውያን
ሰፈር ሲገቡ እግዚአብሔርም የፈረስና የሠረገላ
ድምጽ ስላሰማቸው ሶሪያውያን ድንኳኖቸቸውን
ጥለው እንደሸሹና ሁሉም ነገር በሜዳ ላይ
እንደተበተነ
እንመለከታለን፡፡ ከዚያም እነዚያ ለምጸሞች
የሚችሉትን ያህል
ከበሉ በኃላ ወደ ከተማው መጥተው የምሥራች
ተናገሩ፡፡ ይህን ጊዜ ሕዝቡ መጥቶ የሶሪያውያንን
መንደር በዝብዞ ሲመለስ ያንን ገብስና ዱቄት
ሁሉ ሸመተ ማለት ነው፡፡
ሶሪያውያን
የእግዚአብሔርን ሕዝብ መርገጣቸውንና
ማስቀለሳቸውን እንጂ እግዚአብሔር ምን
እያሠራቸው እንደሆነ ገና አላወቁም፡፡ ምናልባት
የሰማሪያን ሕዝብ ከነንጉሣቸው የርግብ ኩስ
አብልተነዋል ብለው የኩራት ኩራት ተሰምቶአቸው ሊሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ግን የሕዝቡን
የቤት ሥራ እያሠራቸው እንደነበር አልተረዱም
ነበር፡፡ የሰማሪያ ሴቶች ከማሕፀናቸው
ወለዱአቸውን ልጆች አርደው ለመብላት ሲበቁ
ሶሪያውያንና ንጉሥ ወልዴአደር ልዩ
ጀብደኝነት ተሰምቶአቸው ይሆናል፡፡ ይሁን
እንጂ እግዚአብሔር የሕዝቡን ታሪክ መለወጥ
፣ ረሀባቸውንም በጥጋብ ለመቀየር ስላቀደ
የሕዝቡን እህል እያስፈጫቸው ነበር፡፡
ሶሪያውያን ሳያውቁ ለሰማሪያውያን ዱቄት
ፈጩ፣ ገብስንም ወቁ፡፡ እግዚአብሔር ከፈለገ
የጠላታችንን እንጀራ ሊያበላን ይችላል፡፡
ሰማሪያውያንም
እግዚአብሔር በሶሪያውያን እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል
በሚል አጉረምርመው ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ
አምላካቸው ኃይሉን በጠላታቸው ላይ በማሳየት
ዱቄት ያስጭላቸው እንደነበር አልተረዱም፡፡
ስለ እግዚአብሔር ሥራ ሳንረዳ ስንቀር በእርሱ
መታመንና የሚገባውን ምሥጋና መስጠት ያቅተናል፡፡
እኛ አንረዳው እንጂ እግዚአሔር ሥራችንን
እየሠራ ነው፡፡ እርሱ በመንበሩ፣ በዙፋኑ ፣
በከፍታው ላይ ነው፡፡
ከላይ
በዝርዝር እንደተመለከትነው ሁሉ በተከበበ
ከተማ እግዚአብሔር ለእኛ ምሕረትን ያደርጋል፡፡
ርዳታን ያደርጋል፡፡ ማነው ዛሬ በእንቆቅልሽ
ውስጥ ያለ? መከራው
ስለ በረታበት ከዚያ ውስጥ መውጣት ያቃተው
ማን ነው? ተስፋ
የማይታውና ያለቀሰው ማን ነው?
መላ
ሕይወቱ ስለተከበበችበት በሀዘንና በልቅሶ
ውስጥ ያለ እርሱ ማን ሰው ነው?
የእግዚአብሔር
ቃል እንዲህ ይላል፡፡ በተከበበ ከተማ እግዚአብሔር
የሚያስደንቅ ምሕረቱን በችግረኛው ላይ
ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔርም ይረዳችኋል፡፡
የማይለወጠውምን እውነተኛ ቃሉን በመላክ፣
እንደ ጭካኝና አመጸኛ ዳኛ ሳይሆን እንደ
እውነተኛ ዳኛ ሆኖ በፍጥነት ይፈርድላችኋል፡፡ እናንተ
በጠበቃችሁበት መንገድ ሳይሆን በራሱ መንገድ
በመምጣት ያስደንቃችኋል፡፡ አምላካችን
እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፣ ለነፍሳችሁም
ይሟገትላታልና ዝም አለኝ አትበሉ፡፡ እርሱ
ትላንትና እነዳዊትን በረዳበት ኃይሉና ማንነቱ
ዛሬ እኛንም ይረዳናል፣ያድነናልም፡፡ ክብርና
ምሥጋና ሁሉ ለእርሱ ይሁን፡፡ በተከበበ ከተማ
የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ ያደረገ እግዚአብሔር
ይመስገን(መዝ.31፡21)፡፡
አሜን፡፡