ለኢየሱስ
ሥፍራ ይኑረን
በአንድ ወቅት በአዲስ ከተማ ውስጥ
የተከሰተውን የአንድ አስገራሚ ሰርግ ሁኔታ በእንድ መጽሔት ላይ ተጽፎ አነበብን፡፡ ሰርጉን የደገሱ ሰዎች በሀብት የተባረኩ ስለነበረ
የልጃቸውን በተለየ ሁኔታ ደግሰው ነበር፡፡ለሠርጉ ከፍተኛ ዝግጅት አድርነው ነበር፡፡ በጊዜው ከ1500 በላይ ሰዎች ወደ ሠርጉ ተጋብው
ነበር፡ አራት ትላልቅ ድንኳኖችን ተክለዋል ሰናጋዎችን አርደዋል ፣
ምግብ በየዓይነቱ አሰናድተዋል፡፡ የታደሙትም ሰዎች ወደ ሰርግ ቤቱ
ከየአቅጣጫው ተምመዋል፡፡ ዘፈኑ ጭፈራው እልልታው ሲቀልጥ ግን የማታ ማታ አንድ ግራ የሚገባ ነገር ተከሰተ፡፡ ያውም በዚያ ሁሉ
ሁካታና ግርግ በፈጠረ ሠርግ ውስጥ ሙሽራው አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉን ያስደነደጠና ግራ ያጋባ ደስታውንና ጭፈራውን ሁሉ ወደ ድንጋጤ የለወጠ ነገር ነበር፡፡ ስለዚህ ሰዎች
ሁሉ ያንን ሙሽራ መፈለግ ነበረባቸውና ፍለጋውን ተያያዙት፡፡ በመጨረሻም ሙሽራው ተፈልጎ ተገኘና ለምን እንደጠፋባቸው ሲጠየቅ እኔን
አልፈለጋችሁኝም፣ ለራሳችሁ ብቻ ነው የምትጭፍሩት ፣ የምትደሰቱት፣ የምትበሉና የምትጠጡ እናንተ እኔን ዞር ብሎ ያየኝ ከእናንተ
ማንው;፡ ወጥቼ ሲሄድ እንኳ ወዴየት ነው አላላችሁኝም፡፡ ይህን ያህል ጊዜ ከመካካለችሁ ሳልኖር ሲቀር እንኳ አላስተዋላችሁም፡፡
እና ታዲያ ሠርጎ እናንተ ወይስ የእኔ ;አላቸው፡፡ ሙሽራው ሰይኖር ሰርግ ና ድግስ፣ ጭፈራና ስካር ያሳዝናል፡፡
ሙሽራ የሌለበት ሠርግ! በመሠረቱ ደስታው ሙሽራውን ለማስደሰት እንጂ
ሰዎች ለረሳቸው ብቻ እንዲደሰቱበት መሆን አልበረበትም፡፡ የሙሽራውን ደስታ ለራሳቸው ስለወሰዱበት ሙሽራ በዚ ሥፍራ አላገኙትም፡፡
ይህ እኛ ያለንትን ዘመን እና ሁኔታ
ግል አድርጎ የሚገልጽ ምሳሌ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ ባለንበት በዚህ ዘመን በየዓመቱ የሚከበሩ አለም አቀፍ የሆኑ በዓላት አሉ ፡፡
ከእነዚህ በዓላት አንዱ ጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ነው፡፡ በዓለም ዙሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች
ይህንን በዓልን ያከብሩታል፡፡ ይህ በዓል በክርስተትና እምነት ብቻ
ሳይሆን ክርስቲያን ባልሆኑትም ዘንድ በድምቀት ይከበራል ምክንያቱም
ለብዙዎች እንደ ብሔራዊ በዓል ስለሚታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ በሮማ
ውስጥ የኢየሱስ ልደት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በ354 ዓመት ነበር፡፡ እስከዚህ ዓመት ድረስ ቀድሞ በነበሩ ጊዜያቶቸ የጥበብ
ሰዎች ነበሩ ታስበው የሚውሉት፡፡ ይኸው ሁኔታ ዕለት የኋላ ኋላ ወደ
ጥር 6 ቀን መዛወሩ እንዳልቀረ ታሪኮች ይናገራሉ ፡፡ አንዳንድ የታሪክ ሰዎች በሮማ ቤተ-ክርስቲያን ይህንን ዕለት ሆነ ብለው የመረጡት
ድርጊት በ274ኛው ዓመት መከበር የጀመረውን በሀገሪቱ የማይሸነፍ ይባል የነበረውን የሮማውያን የፀሐይ ንጉስ ልደት ቀን ለማጉላት
እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባህላዊ የበኣል አከባሮችና የጌታ ልደት የሚከበርበት በዓል በአንድ
ወቅት እንዲውም በአንድ ቀን ስለሚደረግ የልደት በዓል አከባበሩ ለባህላዊ በዓል ጋር መቀላቀሉ ልማድ እየሆነ መጣ ማለት ነው፡፡
በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት የተለያዩ የቀን መቁጠሪያዎችን ካሌንደርስ በመጠቀም ገና በዓልን ያከብራሉ፡፡ ለምሳሌ የኢየሩሳሌም፣ የሩሲያ፣ የሰርቢያ፣
የፖላንድ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ የሶሎቫኪያ፣ የጆርጅያ፣ የኡክሪንያና አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም የኮኘቲክ ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያናትና አርሜኒያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የጁሊያንን የቀን መቁጠሪያ በመጠቀም የገናን በዓል ጥር 6
ቀን ያከብራሉ፡፡ የግሪክ፣ የኮንስቶትንኦኘል፣ የአሌክሳንደሪያ፣ የሩማኒያ፣ የቡልጋሪያ ፣ የሶሪያ አብያተክርስቲያናት በአንፃራቸው
የጎርጎሳዊያንን ካላንደር ይጠቀማሉ ፡፡ እነዚህ አገሮች ሁሉ የክርስቶስ
ልደት በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ የበዓል አከባበር ከጊዜ
ወደ ጊዜ ድምቀቱን እየጨመረ በመምጣቱ በየአመቱ በታላቅ ናፍቆት የሚጠበቅ በዓል ነው፡፡ ብዙ ግርግሮች የሚታዩበት፣ ብዙዎች ስጦታ
የሚለዋወጡበት፣ ቤተሰቦቻችውንና ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ከፍተኛ ወጪ አውጥተው ከቦታ ወደ ቦታ የሚጓዙበት በዓል ነው፡፡ በኣሉ የሚከበረው
ገና ዲሴምበር 25 ቢሆንም ከአሁኑኑ ከተማዎች መሸብረቅ ጀምረዋል፡፡ በዓሉ በእንዲህ ዓይነቱ በድምቀት ይከበር እንጂ የጌታ መገኘት የዚኑ ያህል
ትኩረት የመሰጠቱ ጉደይ ብም አይታይም፡፡ ጌታችን መወለዱን በተመለከተ በዓሉን እናከብራለን ግን በዓል ከማክበር ባለፈ ፣ ከመጠጣት፣
ከመብላት፣ እና ከመደሰት ባለፈ ጌታ ኢየሱስን እንደ ጌተነቱ የሚከብር ስንቱ ነው; ኢየሱስ የተወለደበትን ዓላማ በግልጠጽ ተረድቶ
ለዚህ ምላሽ የሚንሰጠው ስንቶቻችን ነን›
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም በተወለደባት እለት የቤተ ልሄም ከተማ ልክ እንደ አሁኑ
ያለወትሮዋ በሰዎች ብዛት የተጨናነቀችበት ጊዜ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ወደ ቤተልሔም የመጡበት ጊዜ ነበር፡፡ ምክንያቱም በንጉሡ አዋጅ
ምክንያት ለመመዝገብ( ለመቆጠር) ብዙዎች ወደ ክተማይቱ ስለመጡ ነው፡፡
በዚያን ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጸፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትዕዛዝ ወጣች፡፡ ቄሬኔዎስ በሶሪያ አገር
ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ ፡፡ ሁሉም እያንዳንዱ እንዲጸፍ ወደ ከተማው ሄደ( ሉቃስ 2፡2-3)፡፡
ንጉሡ እያንዳንዱ ሰው እንዲመዘገብ ወይም እንዲቆጠር በንጉሡ ስለታዘዙ ነው፡፡ የሕዝብ ቆጠራ
በጥንት ሰዎች ዘንድ በጣም ይታወቃል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናያቸው ታላላቅ የሕዝብ ቆጠራዎች አንዱ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ
ሁለት ላይ የምናየው ነው፡፡ ከዚያም በፊት በብሉ ኪዳን የተለያዩ ታላላቅ የሕብ ቆጠራዎች ተከናውነዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን በኦሪት
ዘኁልቁ 1-4 እና ምዕራፍ 26 ላይ የተደረጉ ታላላቅ የሕዝብ ቆጠራዎች
ነበሩ፡፡ ከዚያ ጊዜ አንስቶ የተለያቱ የሕብ ቆጠራዎች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ መንግሥታት ሕዝባቸው እንዲቆጠሩ ከሚያደርጉባቸው ምክንያቶች አራት ዋና ዋናዎቹ
ተጠቃሾች ናቸው፡፡ አንደኛው ለአገር ለአገር መከላከያ ( ለጦርነት የሚሆነው የሰው ኃይል ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ነው፡፡ ሁለተኛ
ለግብር ማለትም ታክስ ለመከፈል የሚችለውን የሕዝብ መጠን ለይቶ ለማወቅ ነው፡፡ ሶስተኛ ፍታዊ ሀብትና የመሬት ክፍፍል እንዲኖር ነው፡፡ አራተኛው በአገሪቱ ግዛት ውስጥ ያለው የሰው ቁጥር በውል ምን ያህል እንደሆነ ለመረዳት ነው፡፡ አውግስጦስ ቄሳርም ዓልም
ሁሉ እንዲጸፍ የሚውን አዋጅ ያወጣው በዚህ ዓላማ ምክንያ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ሁሉም
ሰው ወደዚያ ከተማው ሲሄድ ከዳዊት ወገን የሆኑት ሁሉ የዳዊት ከተማ ወደሆነችው ወደ ቤቴልሔም ተጓዙ፡፡ ስለዚህ ከተማይቱ በከፍተኛ
ሁኔታ በእግዶች ተጨናንቃች ማለት ይቻላል፡፡ እንግዲህ እንግዶች በሚገቡባቸው ጊዜ ከተሞች ላይ የሚታየው ደምቀት፣ ሽርጉድ፣ የአቀባበል
ዝግጅት፣ ሁሉ የተለየ መሆኑ ግድ ነው፡፡ ቤተልሄምም እንግዶችን በማስተናግድ በጣም የተጨናናቀችበት ጊዜ ነው፡፡
በወቅቱ ለመመዝገብ ወደ ቤተልሔም ከተጓዙት ታላላቅ እንግዶች ውስጥ ዮሴፍና ማርያም ይገኙበታል፡፡
እነርሱ ወደዚያ ከተማ ሲደርሱ ማርያም የማውለጀ ጊዜ ደርሶ ነበር፡፡ ምናልባት ዮሴፍና ማሪያም ወደዚያ ሥፍራ የመጡት እግዚአብሔር
አስቀድሞ በነቢያት አፍ ጌታ በቤተልሔም ከተማ እንደሚወለድ የተናረውን የትንቢት ቃል እያስተዋሉና ቀኑም መድረሱን አውቀው እንደሆነ
ወይም እንዳልሆነ አናውቅም፡፡ የሆነ ሆኖ ማርያም ልክ ወደ ከተማዋ
እንደገባች የበኩር ልጇን ጌታችንን ኢየሱስን ወለደች፡፡ የዓለም መድኃኒት የሆነውን፣ የዳዊት ዘር የተባለውን ንጉሥ፣ የነግሥታት
ንጉስ የሆነውን፣ ልዑል ጌታችን፣ የእስራኤል ተስፋ የሆነውን መሲህ ወለደች፡፡ ከወለደችም በኋላ በጨርቅ ጠቅልላ በግርግም ላይ አስተናችው
ይላል የእግዚአብሔር ቃል፡፡ ለምን; ለምንድነው በግርግም አስተናችው፡
ምክንያቱ አንድ ነው ያውም በእንግዶች ማረፊያ ለማርያምና ለየሴፍ በተለይም ደግሞ ለተወለደው ጌታ ለኢየሱስ ሥፍራ ስላልነበራቸው
ነው፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፡፡ በእግዶችም ማደሪያ ሥፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው ይላል፡፡ በቤተልሔም ከተማ ያሉ ሰዎች
ሁሉ እንግዶችን ይቀበላሉ ያስተናግዳሉ፣ ምናልባት የበሉና ይጠጡም ይሆናል፣ ይጨፍሩም ይሆናል፡፡ ይደሰቱበትም ይሆናል፡፡ ለመመዝገብ
መጥተው ስለ ታሪካቸው ፣ ስለ ዘራቸው፣ ስለትውልዳቸው ይዘክሩ ይሆናል ይህም ሊሆን ግድ ነውና፡፡ ሕዝብ ቆጠራውና ምዝገባው በባሕሪዩ
ይህ እንዲሆን ያስገድዳልና፡፡ ይሁን እንጂ ለኢየሱስ ሥፍራ አልበራቸውም፡፡ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ ይህም በመሆኑ ማርያምና ዮሴፍ የከብቶች በረት ውስጥ ገብተው ሕጻን ልጃቸውን
ከብቶች ምግብ በሚበሉበትና ውሃ በሚጠቱበት ገንዳ ላይ አስተኙት፡፡ እንግዲህ ማርያም ከዮሴፍ ጋር ወደ ቤተልሔም የመጣችሁ ገሊላ ከተባለው ከሌላ ቦታ ተጉዛ ነው፡፡ ማርያም ወደ
ቤተልሔም ስትመጣ ልትወለድ የደረሰች ነፍሰ ጡር ነበረች፡፡ እንደዚያ ሆና ወደ ቤተ ልሔም መጣች፡፡ ምናልባት በእግር ተጉዛ ይሁን ጋማ ከብት ላይ
ተቀምጣ ይሁን ስለ አመጣጣቸው አናውቅም ግን ነፍሰጡራን እንኳን ሳይቀሩ
ለመቆጠር እንዲመጡ ያደረገው የንጊሡ አዋጅ ምን ያህል ከውሃ የቀጠነ እንደሆነ ለመገመት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሌላው ቢቀር ለነፍሰ
ጡርነቷን እንኳ አይተው ሊራሩላት ይገባቸው ነበር፡፡ ግን ያንን ያደረገ አንድም ሰው በቤተ ልሔም ከተማ ውስጥ አልነበረም፡፡ ሕጻን
ከተወለደስ በኃላ አዲስ ለተወለደው ሕጻን ሲሉ ያያዙትን ቦታ እንኳን መልቀቅ ነበረባቸው ግን እንዲያ አይነት ልብ ያለው ሰው በቤተልሔም
ከተማ አልነበረም፡፡ ማርያምና ዮሴፍ ለጌታችን ለኢየሱስ የሚሆን ሥፍራፋ በእንግዶች ማረፊያ ውስጥ አላገኙም፡፡ ስለዚህ የዚህን ታሪክ
መንፈስ ስንረዳ ሰዎች በሚያድሩበትና በሚያርፉበት በእንግዶች ማረፊያ ሥፍራ ቦታ ስላጡ ወደ ከብቶች በረት የሄዱ ይመስላል፡፡ ማርያም
ኢየሱስን ስትወልድ ለኢየሱስም ሆነ ለዚያ ቤተሰብ የነበራቸው ብቸኛ ሥፍራ በከብቶች የመመገቢያ ገንዳዎች የተሞላ በረት ብቻ ነበረ
፡፡ አንዳንድ የሥነ-ጥበብና ተመራማሪዎችም የሥነ-መለኮት ምሁራንም እንደሚተነትኑት ያ ሥፍራ እንደዋሻ አይነት ሊሆን ይችላል ፡፡
ወይንም ደግሞ በአንድ ግቢ ውስጥ ለብቻዋ የቀረች ትንሽ ኦና ክፍል
ልትሆን ትችላለች ፡፡ ምን ዓይነት አሳዛኝ ነገር እንደሆነ መመልከት ቀላል ነው፡፡
ወገኖቼ ሆይ እሰቲ ልብ ብለን እንመልከት! እንደዚሁም በተልሔም ለሕዝብ ቆጠራ ታዘው በመጡ ዜጎች እንደተሞላችና ከተማዋ በከፍተኛ
ድምቀት ወስጥ ብትሆንም ጌታችንን ሊታስተናደው የምትችልበት የመረዳት
ብልጭታ እንኳን እልዳነበራት ሁሉ ዛሬ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝግጅት
እየተደረገ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመወለዱ መታሰቢያ የሆነው የልደት በዓል ወይም የገና በዓል በከፍተና ድምቀት እየተከበረ
ነው፡፡ አብየተ ክርስቲያናትም ሆነ ሌሎች ሕዝቦች በዓሉን ለማክበር እየተጣደፉ ናቸው፡፡ የስጦታ ልውውጦች እየተደረጉ ናቸው፡፡ ምብብና
የመጠቱ ዝግጅት ተጀምሮአል፡፡ የገና ዛፎች በየቦታው እየተተከሉ፣ የክርስትማስ መብራቶች በየዛፎች ላይ አያሸበረቁ ናቸው፡፡ ምክንያቱም
ጊዜው የክርስትማስ ጊዜ ነው፡፡ የመብላት የመጠጣት፣ የመደሰት ጊዜ ነው፡፡ ሳንታ ክላውስ ከተባለው ጋር ፎግራፍ የመነሳት ጊዜ ነው፡፡
ታዲያ በብዙ ቦታ የዚህ ሁሉ ደስታ ምክንያት የሆነው ጌታ ኢየሱስ ሥፍራ ሲሰጠው አይታይም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሚያደርጉት ዝግጅት ሁሉ
ውስጥ ለኢየሱስ ስፍራ የሌላቸው የእምነት ቤቶች በርካታ ናቸው፡፡ ይህም የምንነርበትን ዘመን ልክ ሙሽራ በሌለበት ሠርግ እንደሚጨፍሩ
ሰዎች ሕይወት እጅግ አሳዛኝ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡ የተወደዳቸወሁ ወገኖች ሆይ እኔና እናንተ ዛሬ በዚህ ዓለም ውስጥ ስንኖር
፣ አብረንም ይህን በዓል ስናከብር ለእየሱስ ያለን ሥፈራ ምን ይመስላል፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፣ ማንም
ድምፄን ቢሰማ በሩን ቢፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር ራት እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል( ራዕያ 3፡10)፡፡ ጌታ ኢየሱስ
ከቤተ ክርቲያናችን ውጭ ወጥቶ ከሆነ፣ በትዳራችንም ቢሆን እርሱ ማእከላዊ መሆን ሲገባው እርሱን አግልለነው ከፍተነው ወደ ውጭ አስወጥተነው
ከሆነ፣ በመድረካችንም እርሱ ሥፍራ አጥቶ ከሆነ ፣ ከሁሉም በቅድሚያ ደግሞ በልባችን ውስጥ እርሱ ሥፍራ አጥቶ ከሆነ እኛም ክልክለነው እንደሆነ ዛሬ
መልእክቱ እንዲህ ነው እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፣ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢጀፍትል ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱ ጋር ራት
እበላላሁ እርሱም ከእኔ ጋር እይበላል ይላል ጌታ፤፤
ሰዎች ዛሬ ለኢየሱስ ሥፍራ የማይኖራቸው ለምንድነው ብለን እንጠይቅ እስቲ፡፡ ካነበብነው የሉቃስ
ወንጌል ተነስተን ብንመለከት እነዚያ በቤተልሔም ከተማ የነበሩ ሰዎች
ከዚያ በፊት ስለ መሲሁ፣ ሊመጣ ስለነበረው ስለ ኢየሱስ የተነገረላቸውን የተስፋ ቃል ስለዘነጉት ይሆናል፡፡ ከእነርሱ
በፊት በነበሩ በሕግና በነቢያት ስለ መሲሁ ስለ ክስርቶስ ተነገሮአቸዋል፡፡ አባቶቻቸውም ይህንን ተስፋ ተቀብለው ነበር፡፡ የሙሴና
የነቢያት መልእክት ማእከላዊ አሳብ፣ የህጋቸውና የትንቢታቸውም ጭብጥ ሊገለጥ ስላለው መሲህ ስለ ክርስቶስ ነበር፡፡ በሙሴ በኩል
እግዚአብሔር ከእነርሱ መካከል እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ እንደሚያስነሳለቸውና
ሕዝቡም እርሱን እንደሚያዳምጡት በዘዳግም 18፡15-16 ላይ ተነገሮአቸዋል፡፡
እንደዚሁም ደግሞ ጌታ ነቢዩ በኩል በትንቢተ ሚክያስ ምዕራፍ 5፡ 2 ላይ አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ ከይሁዳ አእላፍ መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፡፡ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ
ጀምሮ ለዘላለም የሆነ በእስራኤል ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፡፡ ይህ ትንቢት ኢየሱስ ከመወደሉ ከ700 ዓመት በፊት የተነገረ ትንቢት ነው፡፡
ይህ ትንቢት ቤተልሔምን በተለየ ሁኔታ የሚመለከታት ስለሆነ ይህቺ
ከተማ ይህ ትንቢት የሚፈጸምበትን ጊዜና ሁኔታ በንቃት መጠበቅ ነበረባት፡፡ ቤተልሔም ማለት የዳቦ ቤት ማለት ሲሆን ቤተልሑም ኤፍራታ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ መካከል በጣም የመጨረሻዋና ደካማዋ ከተማ ነበረች፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር እሥራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ መሲህ ከእርሷ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር፡፡ ደካማና የናቀች ገረድና እግር አጣቢ
የሆነች ይህች ከተማ ከውስጧ የእሥራኤል መድኃኒት እንደሚወጣ የተነገረላትን ተስፋ በትጋትና በንቃት መጠበቅ ባለመቻሏ መሲሁ ኢየሱስ
በመካከሏ ተወልዶ እንኳን ልታውቀው አልቻለችም፡፡ ምናልባት በጊዜ የነበረው ግርግር፣ የንጉሡ አዋጅና እንግዶችን ለመቀበል የምታደርገው
ሩጫ ለሚወለደው መሲህ ልትሰጠው የሚገባትን ስፍራ ወስዶባት ይሆናል፡፡ በእኛም ዘመን አንዲሁ ወገኖቼ! ምናልባትም በእያንዳንዳችንም ሕይወት እንደዚህ
ይሆን ይሆናል፡፡ ጌታ የነገረንን የተስፋ ቃል ተግተን ባለመጠበቃችን
የተነሳ ልባችን በሌላ ጉዳይ ተይዞ ለእርሱ ሥራ አልሰጠነውም ይሆናል፡፡
የዛሬ የተለያዩ አብተክርስቲያናት እግጅ በጣም ማራኪ ሆኑ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃሉ፣ ስብሰባዎችን ያስተናግዳሉ፣ ነገር ግን ለጌታ ለኢየሱስ
ሥፍራ አይኖራቸውም ይሆናል፡፡ ኮንፍራንሶች ይዘጋጃሉ፣ የነቢያትና
፣ የሐዋሪያት፣ የመጋቢያን እና የመዘምራን ቁጥር እጅግ እየጨመረ ነው፡፡ ይህንን ስናይ የሁላችንም ልባችንም ልብ ይደነቃል፡፡ ነገር
ግን ቆም ብለን መጠየቅ የሚኖርብን አንድ መሠራታዊ ጥያቄ አለን ያውም ለኢየሱስ ሥፍራ አለን ወይ የሚለውን ነው፡፡ ለጌታ ስፋ አለን
ወይ; መድረኩን የሞላው ኢየሱስና የእርሱ ክር ነው ወይ ; ቤታችንን ትዳራችንን የሚስተዳድረው ኢየሱስና የእርሱ ቃል ነው ወይ;
ወይስ እርሱ ገለል ብሎ ሥፍራውንም ሁሉ ለእና ለቆ ሄዶ እኛ ባቻ የእታየን ነው የሚለውን መጠየቅና መልስ መስጠት ይኖርብባል፡፡
ብዙዎቻችን በምድሪቱ ካለው ድህነት ጋር እየታገልን ነው ያንን የኑሮ ውጣ ውረድ ለማሸነፍ ስንል ብዙ እንደክማለን እንጂ የተሰጠንን
የተስፋ ቃል አናስበውም፡፡. በበለጸጉና በአደጉ አገሮች ያለን ደግሞ ከቴክኖሎጂው ጋር ስንታገል ፣ ሲስተሙንም ለማሸነፍ ስነገላበጥ
ለጌታ ያለንን ሥፍራ ተወስዶብ ይሆን; ምናልባት ለአገራችን ያለን ፍቅር፣ ለምንታገልለት የፖለቲካ አቋም ያለን ፍቅር ለጌታ
ሥፍራ እንዳይረው አድርጎብ ይሁን› ለዘራችን ፣ ለቋንቋችን የምንለው ሁሉ ዘላማዊ የሆነው ጌታችን በእኛ ውስጥ ስፍራ እንዳገኝ አድርብን
ይሁን; ወስታችን በዙሪችን ያሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችን እንጂ ጌታ ለእኛ የተጠንን የተስፋ ቃል ለማሰብ ጊዜ እስከማያገኝ ድረስ ውስጣችን
ወደቆ ይሆንን;
ይህን አሳብ አንስተን በምንወያይበት ጊዜ ስለአንድ ነገር ልብ እንበል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ በሥጋ ከማርያም የተወለደበት ጊዜ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ባለንበት ዘመን መቼ እንደ ሆነ በማናውቀው ሰዓት ከመላእክቱ ጋራ ዳግመኛ የሚመጣበት (ድግም
ምዕአት) ጊዜ ከፍታችን አለ፡፡ እነዚህ ሁለት ክስተቶች ማለትም የኢየሱስ ልደትና ዳግም ምጽአቱ ተመሳሳይ ባሕሪይ አሉአቸው፡፡ ያውም
ሁለቱም በመጨረሻው ዘመን ክስተቶቸ መሆናቸው ነው፡፡ ጌታችን የተወለደው በመጨረሻ ዘመን ጅማሬ ላይ ሲሆን ተመልሶ የሚመጣው ደግሞ
በመጨረሻው ዘመን ፍጻሜ ላይ
ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት ዘመናት ውስጥ ያሉ ሰዎች የአኗኗር ሁናቴ ተመሳሳይ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በሥጋ የተወለደው በመጨረሻው
ዘመን ጅማሬ ላይ መሆኑን ለማሳየት ሐዋሪው ጳውሎስ በገላትያ 4፡4 እንዲህ አለ፡፡ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት
የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፣ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፣ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ እንዲህ አለ ከጥንት ጀምሮ
እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ
በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን( ዕብ 1፡1-2)፡፡
እንግዲሕ የጌታችን በሥጋ በተወለደበትም ሆነ ዳግመኛ በሚመጣበት ዘመን
ያሉ ሰዎች የአኗኗር ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ በሉቃስ ወንጌል እንዳነበብነው የኢየሱስ የመወለዱ ጊዜ ምንም እንኳ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር የተናገረው ተስፋ የተፈጸመበት አስደናቂ ክስተት ቢሆንም ሰዎች ለኢየሱስ ሥፍራ
እስከማሰይጡ ድረስ በግል አጀንዳቸው የተያዙበት ጊዜ ነበር፡፡
እኛ በአሁኑ ጊዜ ኡየሱስ ክርስቶስ ይወለዳል ብለን አንጠብቅም ፣ ልደቱን
እናከብራለን እንጂ፡፡ የእርሱን ዳግም መምጣት ግን እንጠብቃለን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ልክ
እንደ በፊቱ ስለሚመጣው ጌታ የማያስቡ በራሳቸው አጀንዳና መርሀ ግብር የታጠሩ መሆናቸውን የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል፡፡
በኖህ
ዘመን እንደነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናል፡፡ በዚያች ወራት ከጥፋት ውሃ በፊት ፣ ኖህ ወደ መርከብ እስክገባበት ድረስ
ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡ እንደነበሩ፣ የጥፋት ውሃም መጥቶ ሁሉን እስከወሰደ ድረስ እንዳላወቁ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ
ይሆናል(ማቴ 24፡38-39)፡፡ እንዲሁ በሉቃስ ወንጌል 21፡33-35 ላይ
ደግሞ ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም
በማሰብ እንዳይክብድ ፣ ያም ቀን በድንገት እንዳይ መጣባችሁ ለራሳችሁ
ተጠንቀቁ በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስጠንቅቋል፡፡
በዚህ ክፍል ትዳር ማለት የእያንዳዱን የሰው ልጅ የኑሮ ሂደት የሚመለክት ነው፡፡ ስለ ምግብና ስለ መጠጥ ማሰብ የመሠረታዊ ጉዳዮች
ናቸው፡፡ ይህንን የማያስብ የለም ነገር ግን ከመሠርታዊ ፍልጎት ባለፈ በመጠጣትና በመስከር እጅግም የመቀናጣትን ሕይወት እያሳደዱ ልባቸው በዚያ ብቻ ተይዞ የጌታን ቀን
ሳያስቡ እንዳይቀሩ ያስጠነቅቃቸዋል፡፡
እንግዲህ ከላይ ያየናቸው በቤተልሔም ከተማ የሚኖሩ ሕዝቦች በመካከላቸው
ለተወለደው ጌታ ሥፍራ ያልነበራቸው ስለሚመጣው መሲህ ተነገራቸውን የተስፋ ቃል ስለዘነጉ ነው፡፡
ሁለተኛ በቤተልሔምና ከቤተልሔም ውጭ የተገለጠውን የጌታ ክብር ለማየትና
የሚነገረውን የመላእክት መልእክት መስማት አለመቻላቸው ነው፡፡ የንጉሡን አዋጅ ሰምተው የመጡ ሕዝቦች በቤተልሔም ከተማ ሳሉ እንግዶች ሲቀበሉና ሲስናግዱ ሳለ የሚበላ ሲበላ የሚጠጣው ሲጠጣ ሳለ በከተማይቱ
ዳርቻ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ሁሉም ሊሰማው የተገባውን አስደናቂ አዋጅ ያውጅ ነበረ፡፡ በክፍሉ እንደምንመለከተው ኢየሱስ በቤተልሔም
ከተማ በተወለደበት ሰዓት የጌታ መልእክት በከተማይቱ ዳርቻ ላይ ለእረኞች
ሰማያዊ አዋጅ ተናገረ፡፡ ቃሉ በሉቃስ ወንጌል 2፡11 ላይ እንዲህ
ላል፡፡ በዚያ
ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ፡፡ እነሆ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ፡፡ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው
አበራ፡፡ በታላቅ ፍርሃትም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው፡ እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና
አትፍሩ፡፡ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶሰ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ እንግዲህ
የቤተልሔም ከተማ ይህን ታላቅ መልእክት መገንዘብ ነበረባት፡፡ እነርሱ ብቻም ሳይሆን ከዚያም በኋላ የነበሩ አብተ ክርስቲናትም ይህንን
የመላእክት ስብከት ማስተዋል ነበረባቸው፡፡ በአሁኑም ዘመን በተለያዩ ኣለም ማዕዘናት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል
የሚያከብሩ ሁሉ ዛሬ ይህንን መልእክት የምነሰማው እኛም ጭምር ይህን መልክት በጥልቀት በመረዳት ሌሎችም ልንመሰከር ይገባናል፡፡
መልእክቱ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፡፡ እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ በማለት ይጀምራል፡፡ ይህ መልእክት
የተነገረው ለእረኞች ነው፡፡ በዚያን ጊዜ እረኞቹ ሜዳ አዳሪዎች ነበሩ፡፡ እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ በቤተ ልሔም ከተማ ባለው የሕዝብ ምዝገባና ቖጠራ ሲደረግ እንደሌሎቹ
እነርሱ ሊመዘገቡ አልሄዱም፡፡ በሜዳ ነበር ያደሩት፡፡ ይህን ጊዜ አንድ አስደናቂ ነገር ሆነ፡፤ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ
ቀረበ፣ ከዚያም የተነሳ የጌታ ብርሃን በዙሪያቸው አበራ ይላል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ነገር ግን የቤተልሔም ከተማ አስቀድሞ
የተነገረላትን የተስፋ ቃል አለማሰብ ብቻ ሳይሆን አሁን ደግሞ የሚነገራትን መሠራታዊ መልእክት ልትሰማ የምትችልበት ጆሮና አቅም
አልነበራትም፡፡ ስለዚህ ይመስለኛል የጌታ መልአክ ከተማውን ትቶ ከዚያ ውጭ በሜዳ ላደሩ እረኞች የተገለጠው፡፡ ስለዚህ መላእከቱ
ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩበትን መልእክት ለእረኞቹ አስተላላፉ ይህንን መልእክት እንመለከታለን፡፡ ከሰማይ የመጡት የጌታ መላእክት ያስተላለፉት መልእክት የራሱ በህሪያት( character) አሉት፣ ሽፋንም(scope
) አለው‹ እንደገና ይዘትም(content) አለው፡፡
የመልእክቱን
ባሕሪይ content ስናየው ይህ መልእከት የምሥራች ነው፡፡ የምሥራች ማለት መልካም ዜና የምንለው ነው፡፡
በአንድ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ላለ ሰው ያ ጉዳይ መፍትሔ እንደተገኘለት ሲነገር የምሥራች ወይም መልካም ዜና ይሆናል ነው፡፡ ዌም ደግሞአንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነበር በመዘግየቱ ምክንያት
ልብ ወደቆ ባለበት ሰዓት የዚያን ጉዳይ መከናወን በድንገት ሲነገር የምስራች ይናል ማለት ነው፡፡ ይህን ለመረዳት እንዲህ አድርገን
እናስብ እስቲ! ልጃዋ ወደ ጦር ሜዳ ሄዶ በውጊያ ላይ እያለ በጠላት ወገን ጦር በወታደራዊ የበላይነት ተማርኮ የመወሰዱን ዜና የሰማች
እናት የልጇን መሞት ወይ በሕይወት መኖር ዜና መስማት በቀንና በሌሊት በልቧ ውስጥ ሳለ ምንም ሳትሰማ ዘመናት ስላለፉባት ተስፋ
ቆርጣ አልቅሳ አንብታ ወገቧን በጨርቅ ጥፍንግ አድርጋ አሥራ የእተከዘች ሳለ አንድ ሰው ወደ እርሷ ቀርቦ ስሟን ጠርቶ ያ በጠላት ወገን ተማርኮ የወሰደው ልጅሽ ፣ ገና በሕይወት አለ፣ እንዲያውም
ወደ አንቺ እየመጣ ነው ፣ እኔም አይቼዋለሁና ደስ ይበለስሽ ብላት ይህ ለዚች ሴት የምሥራች ወይም መልካም ዜና ነው ማለት ነው፡፡
እንዲያውም ለማን የሚስቸግር አስደሳች ዜና ይሆንላታል ማለት ነው፡፡
ልክ እንዲዚሁ የመላእክ የተናገሩት አሳብ በሮማውያን የአገዛዝ
ቀንበር ሥር ሆነው ለተጨነቁ ሕዝቦች ፣ በጨለማ ለኖሩ ለዓለም ሕዝቦች
ብርሃን መምጣቱና ያ ጨለማ በብርሃን ኃይል የሚለወጥበት አንድ ተአምር ስለ መፈጠሩ ሲሆን ይህም ለሰው ሁሉ መነገር ያለበት ታላቅ
ደስታ የምሥራች ነው፡፡ መልካም ዜናዎች ሁሉ አውራ ነው፡፡
የመልእክቱን ሽፋን ስናየው ለሰው ሁሉ የሚሆን ነው፡፡ (It is global )ኣለም አቀፋዊ ነው:: ምንም እንኳን መልእክቱን የተቀበሉት በሜዳ ላይ ያሉ እረኞች ቢሆኑም ይህ የምሥራች
ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ነው፡፡ ምክንያቱም በኃጢአት ቀንበር ውስጥ ያለው
ሰው ሁሉ ስለሆነ ነው፡፡ ሁሉም ኃጢአትን ስለሠራ የእግዚአብሔር ክብር በሁሉም ላይ ስለጎደለ ሁሉ የሞት እዳ አለበት፡፡
እዳ ደግሞ አስጨናቂ ነው፡፡ እዳ ያለበት ሰው አርፎ አያድርም እንቅልፍም አይወስደውም፡፡ ኃጢአተኛው ሕዝብ ደግሞ ተራ እዳ ሳይሆን
የሞት እዳ ያለበት ነው፡፡ ስለዚህ ኑሮው ሁሉ የጭንቅ ኑሮ ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳያስ በኢየሱስ መምጣት ምክንያት ሊገለጥ ስለለው ፍትሔ (
Resolution) ሲናገር እንዲህ አለ፡፡ ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም…..በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን
አየ፣ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ይላል (ኢሳ 9፡1-3)፡፡ ከዚህ በላይ የምሥራች የለም፡፡ በጨለማ
ውስጥ ለምንደፋደፉና የሕይወት ተስፋ ለማይታያቸው የሚደነቅ ብርሃን ስለመውጣቱ ከመናገር በላይ የተሻለ የምሥራች የለም፡፡ ይህ ምሥራች
ነው( This is the good news that must be told to all people, in every corner of the World)፡፡ የምሥራችነቱ ለእረኞቹ ብቻ አይደልም
፣ በቤተልሔም ከተማ ላሉ እንግዶችም ሁሉ ነው፡፡ ከዚያም በኃላ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ፣ ነገሥታት ሁሉ፣ ለአብያክርስቲያናት ሁሉ፣ በእኛም
ዘመን ላላነው ሁሉ ለሀያላን ሁሉ፣ ለመኳንንት ሁሉ ፣ ለጥቁሩ ለነጩ፣ ለሴት ለወንዱ ለሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች ነው፡፡
ወገኖቼ ሖይ የኢየሱስ መወለድ የምሥራች ( The good tiding, wonderful hearald) ነው፡፡ ይህ እንግዲህ መላአኩ
የሰበከው ስብከት ባሕሪይ ይህንን የሚመስል ነው፡፡
የመልእክቱ ይዘት (content) ምንድነው ብለን እንጠይቅ፡ አንዳንዴ ምንም ይዘት ይሌላቸውን ሰማይዊ ቁም ነገር ያላዘሉ
ስብከቶችን ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? በዚህ ሥፍራ የእግዚአብሔር መልአክ የሰበከው ስብከት አስደናቂ የሆነ ሰማያዊ ቁም ነገር ያለበት
ነው፡ ፡የጌታ መላእክት የተናገሩት መልእክት ይዘት እንዲህ የሚል ነው፡፡ ያ ሲጠበቅ የነበረው ወንድ ልጅ ተወልዶላችኋልና አትፍሩ፣
ብርሃን ተወልዶላችኋልና አትፍሩ ይላቸዋል ይህ የተወለደውን እንደሚከተለው ይገልጸዋል፡፡
መድኃኒት ተወልዶላችኋል የሚል ነው፡፡ የተወለደው ጌታ ኢየሱስ መድኃኒት
ነው፡፡ ይህ የነገር ሁሉ መቋጫ ነው፡፡ በእኛና በጌታ መካከል ላለው ግንኙነት እና ዝምድና ማዕከል ነው፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያስፈለገበት
ምክንያቱም ይህ ነው፡፡ በኃጢአት የተበከለው የሰው ልጅ ሁሉ ፣ ዓለም ሕዝብ መድኃኒት( አዳኝ) የሚሆነውን ይፈልግ ነበር፡፡ መላእክት ያሉትን ይህ አሳብ ልብ ብለን ያየን እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን መዳን
( Salvation) ከሚለው አሳብ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ እግዚአብሔርም
መልኣክ ለማርያም በተናገራት እንደምትጸንስና ወንድ ልጅንም እንደምትወልድ ስሙንም ኢየሱስ እንደምትለው ከተናገር በኋላ እርሱም
ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል አላት፡፡ ኢየሱስ ሲል አዳኝ ጌታ ማለት ነው፡፡ በዚም ክፍል እንደምናየው ጌታችን ኢየሱስ መድኃኒት
ነው፡፡ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ለኢየሱስ ከተሰጣቸው አስደናቂ ስሞች አንዱ መዳን ወይም መድኃኒት (Savior ) የሚል ነው፡፡
አንዳንድ ለዘብተኛ ሰዎች ይህ አሳብ የአዲስ ኪዳን አሳብ እንጂ ከብሉይ
ኪዳን ጋር ግንኙነት የለውም ምክንያም እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን ጨካኝ፣ የሚቀጣ፣ በእሳት የተመሰለ በቀለኛ ብቻ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክችን በብሉይ ኪዳንም ቢሆን
ለህዝቡ አዳኛቸው ነበረ፡፡ ረዳታቸው ነበረ፡፡ ከአንበሳው አፍ ሕዝቡን ያዳነው፣ ከእሳትና ከውሃ ያስመለጣቸው ፣ ባሕሩንም ከፍሎ
ሕዝቡን ካሸገረ በኋላ ከፈርዖን ሰይፍና ጦር ያዳነው እርሱ እግዚአብሔር ነበር፡፡ እንዲያው እግዚአብሔር አዳኝ ሴልቪሺን በሚለው
ቃል ከ180 ጊዜ በላይ በብሉይ ኪዳን ተጠቅሷል ፡፡ የእግዚአብሔርን አዳኝነት ትዕብተኞች የሆኑ የአህዛብ ነገሥታትም ጭምር እስክመሰክሩ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናቸው ነበር፡፡ በትንቢተ
ዳንኤል 3፡28-29 እንደምናበው ናቡካድናጾርም መልሶ መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ
እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፎ የሰጡትን የንጉሡን ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ
የስድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ…. እንደዚህ የሚያድን አምላክ የለምና (ዳን. 3፡28-28)፡፡ እንደ
ቤልና ናባው ያሉ የተፈሩ የባቢሎናውያን አማልት ነበሩ፡፡ ቤል ( በአል) ማለት ሎርድ ወይም ጌታ ማለት) ነው፡፡ ቤል ጌታ ይባል
እንጂ ሕዝቡን አያድንም፣ እግዚአብሔር ያህዌ ግን ያድናል፡፡ ቤል ጸሎት አይሰማም ፣ አምላዎቹ ሰውነታቸውን
በጭሬ እየቧጨሩና እያደሙ ከጠዋት አስከ ቀትር ድረስ ወደ እርሱ ቢጮኹም እርሱ አይሰማቸውም፡፡ የእሥራኤል አምላክ ያህዌ የተባለው ግን ጸሎትን ሰምቶ በእሳት ይመልሳል፡፡ ቤልና ናባው
በደካማ እንስሶች ጭነት ይሆናሉ እግዚአብሄር አዳኙ ግን ሕዝቡን እስከ ሽበት እስከ ሽምግልና ይሸከማል፣ እርሱ ያድናል፡፡ ስለዚህ
በብሉይ ኪዳን ዘመን እርሱ ለሕዝቡ የሚያደርገው አስደናቂ ሥራውና ሆነ እርሱ ራሱ ደግሞ መድኃኒት ተብሏል፡፡
ይህ ስም በአዲስ ኪዳን ኃጢአተኖችን ሁሉ ሊያድን ለተገለጠው ለጌታ
ለአየሱስ ተሰጥቶታል፡፡ ለምሳሌ ማርያም ስትዘመር ነፍሴ አምላኬን
መድኃኒቴን ታከብረዋለች( ሉቃስ 1፡47) አለች፡፡ ካህኑ ዘካሪያስም መጥመቁ ዮሐንስ በተወለደና ቤተሰቦቹም ወደ ቤተመቅደስ
ባመጡበት ወቅት ስለ ኢየሱስ ትንቢት ሲናገር እንዲህ አለ፡ ከጥንት ጀምሮ በነበሩት ቅዱሳት ነቢያት አፍ እንደተናገረ በብላቴናው በዳዊት
ቤት የመዳንን ቀንድ አስነስቶአልና፣ ማዳኑም ከወረደረኞቻችንና ከሚጠሉን እጅ ነው(ሉቃሰ 1፡68-71)፡፡ የዮሐንስ
ወንጌል 4፡42 እንደሚነግረን የሰማሪያ ሰዎች ኢየሱስ ያስተማረውን ሁሉ ሰምተው በእርሱ ካመኑ በኋላ ለሰማሪያዊቲቱ ሴት ሲናገሩ
እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን
አሉ ፡፡ ልክ መላእክት ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እንዳሉ ሁሉ የሰማሪያም ሰዎች ኢየሱስ የዓለም መድኃኒት ነው
አሉ፡፡
በአዲስ ኪዳን የመጠልን የተወለደለን ጌታ ኢየሱስ ነው፣ እርሱ መድኃኒት
ነው፡፡ መድኃኒት ሰጭ አይደለም፡፡ ራሱ መድኃኒት ነው፡፡ No expairation date ኤክፓየር የማያደርግ መድኃኒት ነው፡፡፣
ለዘመናት የኖር ግን በየእለቱ አዲስ የሆነ መድኃኒት ነው፡፡ እርሱ ብቻ ስለሚያድን መዳን በሌላ በማንም የለም ተባለ፡፡ በኢየሱስ
ዘመን ብዙ ባለ መድኃኒቶች ስለነበሩ ሕመምተኞቸ ወደ እነርሱ ይሄደ ነበር፡፡ ነገር ግን ያላቸውን ከስረው ሕመማቸውም ይብሰባቸውና
ጉዳም በላያቸው ጨምረው ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር፡፡ የባለመድኃኒቶች
መድኃኒት ለሕመምተኖች ሌላ ሕመም ይሆንባቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን የታመሙት ከሕመማቸው ይፈውሳቸው ነበር ይህም ብቻ ሳይሆን ፈውሱ በነጻ ያለ ዋጋ ነበረ፡፡ ያ ጌታ አየሱስ ዛሬም በጨለማ፣ በህመም በእንቆቅልሽ
ውስጥ ላሉት ሁሉ መድኃኒታቸው ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር የተሰጠው መድኃኒት ወይም አዳኝ የተለው ስም በኢየሱሰስ በኩል
ነው የተገለጠው፡፡ ኢየሱስ መድኃኒት ነነው፡፡ ስለዚህ ይህን የገታ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ብናከብርበት ጊዜ ኣመት በዓል
አይደለም እያከበርን ያለነው፡፡ ወይም አውደ ዓመት እያሳለፍን አይደለም ያለነው፡፡ ለእና ይህ የመብላት፣ ወይም የመጠጣት ወይም
በዓል ማድመቅ አይደለም፡፡ ከምንላውና ከምንጠጣው ሁሉ ባለፈ እጅግ በጣም የሚስደስተን ነገር የነፍሳችን መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ
መምጣቱ ነው፡፡ መድኃኒት ተፈልጣል፣ መዳን በሌላ በማንም አልተገኘም
የለምም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከሰማይ በታች የኢየሱሰስ ስም ብቻ ሆነ፡፡ ሃሌሉያ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ያድናል፣ ከመከራ ሁሉ ያድናል፣ በዓለም ካለው ጭንቅ ሁሉ ያድናል‹ ከጨለማ
ያወጣል፣ እርሱ መድሃኒት ነው፡፡ መድኀኒትነቱ ለሥጋ በሽታ ብቻ አይደለም፡፡
እርሱ ለምድር ፓለቲካ፣ ለሃማኖት ሁ ለምድር ምጣኔ ሀብት ሁሉ፣ ለዚህ ምድር ለአየሯ ፣ ለነፋሳት ሁሉ መድኃኒት ኢየሱስ ነው፡፡
ታዲያ ይህ ኢየሱሰስ የት ናው ያለው; የዓለም መንግሠታት ኢየሱሰስን ከፖፐቲካቸው አስወጥተውታል፣ አብያክርስቲያናትም ይህንን መድኃነኒት
ከቤታቸው አስወጥተው መድረኩን ብቻቸውን ሞልተውታል፡፡ ኢየሱስ በበርካታ ቦታዎቸ ላይ ዛሬ የለም፡፡ ነገርግን ኢየሱሰስን ወደ ውስጣቸው
ቢገብዙት፣ እንዲሰጥንባቸው ቢብዙት ኖር፣ ባለትዳሮች ከቤታቸው ያስወጡትን ጌታ ልሰው በቤታቸው ከመሾሙት አስደናቂ ፈውስ ይሆን ነበር፡፡
ለአሜሪካና ሌሌሎች የበለጸጉ አገሮች እድገትና ለልዕለ ኀያልነታቸው ምክንቱ የጥንት አባቶቻቸው ከእግዚአብሔር የነበራቸው መሰጠጥ
ነበር፡፡ ነገር ግን ይህች ምድር ሀታዋንና አምላኳን የሚገፋ ትውለድ ስለበዛ፣ ስለኢየሱስ ማሰብ ሞንነት ወይም ከዚያ አልፎ ወንጀል
እስከሚሆንበት ድረስ የሚየያስበ ትውልድና የፖለቲካ መሮዎች ስተበራከቱ ምድሪቱ የከፍተኛ የሞራልና መንፈሳዊ ውድቀት ውስጥ እተፈቀች
ትገኛለች፡፡ መድሃኒቱን ስለጣለት እርሷም አብራ እየወደቀች ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ይህንን መድኀኒት በሕይወታቸው ቢሾሙት ኖሮ ያድናቸው
ነበር ምድራቸውን ይፈውስላቸው ነበር፣ ትዳራቸውን ይፈውስላቸው ነበር፡፡ እነርሱ በአል ያደምቃሉ፡፡ የበኣሉን ጌታ ፣ በበአሉ ጊዜ
የደሰሱበሰት የደስታ ምክንያ ሖነውን ጌታ ከፍተው ዳር አስወጥተውታል፡፡ በአፋቸው ጌታን የሚያመልኩ ይመስላሉ ግን በልባቸው በፍጹም
ክደውታል እናዲያው ጦር ስለው ሳያሳድዱትም አይቀሩም፡፡ ሠይጣም የዚህ ዓለም ፈውስ ያለው በኢየሱስ እንደሆነ ስለሚውቅ የዓም መንግሥታት
ኢየሱስን እነዳያስጠጉት እና ፈውስም እንዳይኖራቸው ያለመታከት እየተዋጋ ነው፡፡ ትዳር ኢየሱስ ኖሮ ባልና ሚስት የተፈወሰ የትዳርን
ሕይወት እነዳጣታሙት መድኀኒት የሆነውን ጌታ ከትዳራቸው ከፍትረው እንዲያስጡ ያለው ዓላማው እየተሳካለት ነው፡፡ የዛሬ ዓለም
ሙሽራ በሌለበት ሠርግ ቤት እንደሚጨፍሩ ሰዎች ኢየሱስን ከሕይታቸው አውጥተው በዓል የሚደያምቁና የሚያከብሩ ሰዎች የበዛበት
ሀኗል፡፡ ወገኖች ሆይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታታ እንዳየነው እኛ ባለንባት በዚህ በአሜሪካን አገር ብዙ አብያተክርሰቲናት የክርስተማስ
በዓል በድንቅ ሁኔታ ያከበሩታል፡፡ ድራማው፣ ግጥም ንባቡ፣ እንዲያውም በአንዳንድ ቤተክርቲያናት የሚለኮሰው የገና መብራት የጉድ
የሚያሰኝ ነው፡፡ በአምና በአንድ ቤተክርሲያን አዳራሽ ብቻ 25000 መንራቶች ተለኩሰው ነበር፡፡ እንደዚህ የሚደርጉ ብዙ ጸሎት
ቤቶች ቢኖሩም ዪያኑ ህል የጌታ አዳኝነት ሲመሰከር አይታይም፡፡ ይህ አስደናቂ መልእክት በቤተ ልሔ ከተማ ዳርቻ ይሰበክ ነበር ያውም እግዚአብሔር ከሰማይ በላከው መልአክ
በኩል የተሰበከ ሲሆን ቤተልሔም ከተማ ግን ይህን መልእክት አልሰሙም ፡፡ የተወደዳችሁ ወገኖች ሆይ ፣ እህቶቼና ወንድሞቼ ዛሬ የጌታን ልደት ስናከብር
ደስ ይለናል፡፡ የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመን ደስ በሚያሰኙ ሁኔታዎች ሁሉ ይህንን ልደት በደማቅ ሁኔታ ልናከብረው እንችላለን ግን
ቁም ነገሩ ጌታ ኢየሱስ የተናገረውን ስለ እርሱን የተነገረንን እውነት እንሰማለንን; ለኣለምስ እንሰብካለንን፡ እርሱ መድኃኒታችን
እንደሆነ አውቀን ደስ ይልናልን፡ እግዚአብሔር የሰጠንን የተስፋ ቃል እየጠበቅነው ነው? ኢየሱሰስ በልባችን ሥፍራ ያለው ጌታ ነውን?
የቤልሔም ከተማ እንደፈለገችው ሆና አልፋለች፡፡ ቢህ ምድር ያሉው የጊው ሁኔታ እንምናየው ይሁን፡፡ እኔና እናንተስ ለእኛ ኢየሱስ
ማን ነው? በየትኛው ሥፍራ አስቀምጠነዋል? የእኛ ከሆኑት ነገሮቻችን ሁሉ አስወጥተነው እደጅ ነው ወይ እቤታችን በጓዳችን የነገሠ
የሰለጠነ ንጉሳችን ነው? እርሱ እንዲ ይላል እኔሆ በደጅ ቆሜ እንኳኳለሁ ምንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትል ወደ እርሱ እገባለሁ
ከእርሱም ጋር ራት እበላለሁ፣ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፡፡
ከመላእክቱ ትምህርት ውስጥ እጅግ በጣም አስደናቂው ነገር በመልእክቱ ውስጥ እረኞችን ያደረታቱበት መንገድ ያስደንቀኛልና እርሱን ተናግሬ እንጨርስ፡፡ የምስራች አምጥቼላችኋለሁና አትፍሩ የሚል መልእክት ሰጣቸው፡፡ አትፍሩ ምክንያምቱም አሁን ተወለደው መድኃኒት ስለሆነ ፣ አዳኝ ነውና ፣ ኢየሱስ ነውና አትፍሩ፡፡ በተለይም ደግሞ እረኞች የሚኖሩበትን ዓይነት ሕይወት ለሚኖሩት ሰዎች እንደዚህ ዓይነት የማጽናናት መልእክት ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ የሚያስፈራ ዘመን ነበረ፡፡ ምክንያቱም እረኝነት የከበረ ሥራ አልበረምና:: በኢየሱስ ዘመን በሮማውያን ዘንድ እረኝነት ዝቅ ተደርጎ የሚታይ ማንነት ከመሆኑም በላይ ሙያውም ያልከበረና ንጹህ እንደሆነም የማይተሰብ ነበር፡፡ ስለዚህም ሊሆን ይችላል እነዚያ እረኞች ሕዝብ ወደሚቆጠርበት ሥፍራ ከመሄድ ይልቅ በሜዳ መንጋዎቻቸውን ሲጠብቁ ማደርን የመረጡት፡፡ ይሁን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሆነው መልእክት ሲል በመጀመሪያ እነርሱን በማጽናናት ጀመረ፡፡ ስለዚህ እረኞችን መልአኩ እንዲህ አላቸው፡፡ አትፍሩ! የምትፈሩ አትፍሩ መድኃኒት ተገኝቶላችኋልና፡፡ ኢየሱስ ተወልዶአልና፡፡ አትፍሩ! አትፍሩ፡፡ የተነገረው መልእክት አስገራሚ የሆነው ደግሞ ጌታ የተወለደው ለእናንተ ነው፡፡ ይህንን በሁለት ቃላት ይገልጻል፡፡ የምስራች እነግራችኋለሁ፣ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህ በደንብ የሚገባን በእንግሊዝኛ ስናነበው ነው፡፡
ከመላእክቱ ትምህርት ውስጥ እጅግ በጣም አስደናቂው ነገር በመልእክቱ ውስጥ እረኞችን ያደረታቱበት መንገድ ያስደንቀኛልና እርሱን ተናግሬ እንጨርስ፡፡ የምስራች አምጥቼላችኋለሁና አትፍሩ የሚል መልእክት ሰጣቸው፡፡ አትፍሩ ምክንያምቱም አሁን ተወለደው መድኃኒት ስለሆነ ፣ አዳኝ ነውና ፣ ኢየሱስ ነውና አትፍሩ፡፡ በተለይም ደግሞ እረኞች የሚኖሩበትን ዓይነት ሕይወት ለሚኖሩት ሰዎች እንደዚህ ዓይነት የማጽናናት መልእክት ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ የሚያስፈራ ዘመን ነበረ፡፡ ምክንያቱም እረኝነት የከበረ ሥራ አልበረምና:: በኢየሱስ ዘመን በሮማውያን ዘንድ እረኝነት ዝቅ ተደርጎ የሚታይ ማንነት ከመሆኑም በላይ ሙያውም ያልከበረና ንጹህ እንደሆነም የማይተሰብ ነበር፡፡ ስለዚህም ሊሆን ይችላል እነዚያ እረኞች ሕዝብ ወደሚቆጠርበት ሥፍራ ከመሄድ ይልቅ በሜዳ መንጋዎቻቸውን ሲጠብቁ ማደርን የመረጡት፡፡ ይሁን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሆነው መልእክት ሲል በመጀመሪያ እነርሱን በማጽናናት ጀመረ፡፡ ስለዚህ እረኞችን መልአኩ እንዲህ አላቸው፡፡ አትፍሩ! የምትፈሩ አትፍሩ መድኃኒት ተገኝቶላችኋልና፡፡ ኢየሱስ ተወልዶአልና፡፡ አትፍሩ! አትፍሩ፡፡ የተነገረው መልእክት አስገራሚ የሆነው ደግሞ ጌታ የተወለደው ለእናንተ ነው፡፡ ይህንን በሁለት ቃላት ይገልጻል፡፡ የምስራች እነግራችኋለሁ፣ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህ በደንብ የሚገባን በእንግሊዝኛ ስናነበው ነው፡፡
And the angel said unto them, Fear not: for, behold, I
bring you good tidings of great joy, which shall be to all people. For unto
you is born this day in the city of David a Saviour, which is Christ the Lord.
በሕብረተሱ ውስጥ የክብር ሥፍራ
ያላገኙ እረኞች፣ ሜዳ አዳሪ የነበሩ፣ ዝምድናቸውና ዉሎአቸው ከከብት ጋር የነበረ እነዚህ ሰዎች አስደናቂ በሆነው የእግዚአብሔር ክብር ሲጎበኙ እጅግ ያስደንቃል፡፡ እረኞቹ
ለማመን ተቸግረው ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይም ደግሞ ይህ መድኃኒት የተወለደው ለእናንተ ነው ሲባሉ ያቺን ቀን እንዴት ባርከው ይሁን፡፡
በእግዚአብሔር የተጎበኙባት ያቺ ሌሊት እንዴት አስደናቂ ናት፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈልግሃል ሲሉን ለማመን እንቸገራለን፡፡ እኔን ፣ እኔን ደካማውን ደካማዋን፣ እኔን ሞኙን እኔን ኃጢአተኛውን
እንዴት ብሎ ነው ያልንባቸው ቀናት አሉ፡፡ እኔም ራሴ እገረማለሁ ኢየሱስ ለእኔ መምጣቱ፣ የእኔን ታሪክ መቀየሩ፣ ያስገርመኛል፡፡
አንዳንድ ጊዜ እኔን እግዚአብሔር ያየኛልን ብለን የምጠይቅበት ጊዜ እንዲያውም ብዙ ነው፡፡ አሁን ይህንን ፕሮግራም ለመካፈል ስትመጡ
እንኳን እግዚአብሔር እንደሚያያችሁና ጸሎታችሁን እንደሚሰማ ሳይመስላችሁ የምትቸገሩ ሁሉ አላችሁ፡፡ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ ሆኜ
እንግራችኋለሁ፣ ይህ መልእክት ለእናንተ ነው፡፡ የአንቺ ነው አትፈሪ፣ ወንድሜ ሆይ ይህ መልእክት የአንተ ነው አትፍራ ምክንያቱም
ኢየሱስ መድኃኒት ሆኖ የተወለደው ለንተ ነው፡፡ ተወለወዶልሃል ፣ እርሱ መድሃኒት ተገኝቶልሻል፡፡ ወገኖቼ ሆይ እባካችሁ ጌታን የራሳችሁ
አድርጉት፡፡ ሌሎች ሰዎች አምላክ አታድርጉት እነዚያ እርሱን የሚያመልኩና እናንተ ግን አጃቢዎች አድርጋችሁ አትውሰዱ፡፡ እርሱ የናንተም
ጌታ ነው፡ ለእናንተም መድሃኒት ነው፡፡ ኢየሱስ የበሽታ መድኃኒት ፣ የትዳርህ የትዳርሽ መድኃኒት የልጆቻችሁ መድሃኒት የእርሻችሁ የሥራችሁ
የጓዳችሁ መድኃኒት ነው፡፡ ስለዚህ አይአችሁ አትፍሩ፡፡ ይህ ለሕዝቦች ሁሉ ሊነገር የሚገባው ታላቅ የምሥራች ነው
ሃሌሉያ፡፡
የምሥራች ዛሬ መድሐኒት ክርስቶስ እርሱ ጌታ የሆነው የተወለደው ለእኛ ነው፡፡ ለእረኞች የታወጀው
መልካም ዜና መድሐኒት ተወልዷል ብቻ ሳይሆን ተወልዶላችኋል የሚል ነው፡፡ የኢየሱስ መወለድ የምሥራቹ በመጀመሪያ ለግላችን ነው ፡፡
ለእኔ ነው ብለን የምንቀበለው ነው ፡፡ ለእኔ ለኃጢያተኛው ተወለደ ፡፡ እኔን ከጥፋት ፈልጎ ሊያገኘኝ እርሱ ተወለደ፡፡ ለእናንተ
ተወልዶለችኋል፡፡ ይህ የተወለደው መድኃኒት የእኛ ነው፡፡ የእኛ ጌታ
ኢየሱስ የተወለደበት ቀን ያቺ ሌሊት ከቀኖች ሁሉ ልዩ ቀን ናት፡፡ በየእምነት ቤቱና ሥርዓቱ በተለያዩ ቀናት ቢታሰቡም ያቺ ልናያት
ያልቻልናት ግን ሁልጊዜ የምናስባት ቀን የከበረች ቀን ናት፡፡ እግዚአብሔር እኛን የጎበኘበት ቀን ያቺ ቀን ያቺ ሌሊት የተባረከች
ትሁን ፡፡ የምሥራቹን ቃል የሰማሁባት ቀን /ሌሊት መድኃኒቱ ኢየሱስ የተወለደልን ያቺ ቀን ያቺ የደስታ ምሽት ከቀኖች መካከል የተባረከች
ትሁን፡፡ እግዚአብሔር የሠራት በእርሷም ደስ የምንሰኝባት ያቺ ትታሰብ በጨለማ ለምንሄድ ታላቅ ብርሃን የበራልን ያቺ ቀን ትወደስ
ትባረክ፡፡ በቀኖች ሁሉ መካከል ከፍ ትበል ያቺ ቀን ኢየሱስ ሥጋ ለብሶ በበረት በግርግም ተኝቶ የተገኘባት ሌሊት ያቺ ሌሊት ውድናት
ዋጋዋ በብዙ አልማዝና እንቁም አይመዘንም የተባረከች ትሁን ስትታሰብ ትኑር ፡፡ አትረሳ ያቺ ቀን የምሥራቹን የሰማንበት ቀን አብረን
ደስ የምንሰኝባት ምሽት መልአኩ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ
የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፡፡ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ” አለን ፡፡ ዛሬ ለዓለም ሁሉ የምሥራች የምሥራች የምሥራች!!