ይህንን ጽኹፍ ለማዘጋጀት ከመጀመሪያው ዕቅድ አልነበረኝም፡፡ ነገር ግን በየ15 ቀኑ እየጓዝኩ በሚሰብክባት የሰውዝፍልድ ሚቺጋን ኢትዮጵያ ወንጌጌላዊት ቤክ አባልና አገልጋይ የሆነች እህት በራዕይ መጽሐፍ 11 ፡ 4 ላይ ስለሚገኙ ስለ ሁለት ወይራዎች ምስጥራት እንድነግራት ስለጠየቀችኝ ለእርሷ ምላሽ እንዲሆን ብዬ ያዘጋጀሁትን ምላሽ ነው አሁን የማቀርብላችሁ፡፡ መቼም በመድረክ ማገልገል በተለይም ቃሉን እየተረጎምን የምናስተምር ከሆነ ከአገልግሎት በመልስ ሌሎች ክፍሎችንም እንድናብራራላቸው የሚጠይቁ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ደግሞ በጣም የሚያስደስት ነገር ነው፡፡ ይህንን ክፍል እንዳብራራላት የጠየቀቺኝን እህት እያሰገንኩ እኔም አሳቡን ለመመልከት ችያለሁ፡፡ ጭንቀቴ እንደ ፓስተሯ ለምታየኝ ቅንና የቃሉ ወዳድ ለሆነቺው እህቴ የተሳሳተ ነገር እንዳልናገር ነበር፡፡ እንግዲህ አሳቡን፡ካየሁና ለእርሷም ምላሽ ከሰጠሁ በኋላ ለራሴም ትልቅ መልእክት ስለሆነኝ ጓደኞቼም እንዲያነቡት ባደርግስ ብዬ ስላሰብኩ ይኸውና ከነማብራሪያ ከዚህ እንደሚከተለው ስላስቀመጥኩ ተቋደሱት፡፡
የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ ለመተርጎም ከባድ ከምንላቸው መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መጽሐፉ አቡቀለም ሲስ ተብሎ ከሚጠሩት መጽሓፍት ጋር የሚመደብ ስለሆነ ነው፡፡ እንደዚህ ባሉት መጽሓፍት አንዳንድ አሳቦች ከተለመደው ውጭ በሆኑ ቋንቋዎች ወይም የአገላለጽ ዘይቤዎች ስለተነገሩ ትርጉሙን በቀላሉ ማግኘት አዳጋች ይሆናል፡፡ አቡቀለም ሲስ ማለት መገለጥ ወይም ራዕይ እንደማለት ነው፡፡
በምዕራፍ 11 ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሱ ሁለቱ ወይራዎች እነማን ናቸው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ወደ ምንባብ ክፍል መሄድ ያስፈልጋል፡፡ በታላቁ መከራ ጊዜ በምድር ላይ ሊነሱ ስላሉት ሁለት ምስክሮች ፣ ሁለቱ ወይራዎች ወይም ሁለቱ መቅረዞች የሚናገር ሲሆን የክፍሉን ሙሉ አሳብ ለማግኘት ከቁጥር 1-13 ሙሉን ማበብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ የንባብ ክፍል በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙ ሰባት ወዮዎች በሁለተኛው ውስጥ ያለ ነው፡፡ በተለይም ስለ ሁለቱ ምስክሮች ሦስት መሠረታዊ አሳቦችን እናገኛለን፡፡ 1. ስለ ሁለቱ ምስሮች አገልግሎት (3-6)፣ 2. ስለ ሁለቱ ምስክሮች አሟሟት( 7-10) እና 3. ስለ ሁለቱም ምስክሮች ትንሳኤ ( 11-13) እናያለን፡፡
ታዲያ እነዚህ ማናቸው የሚለውን ለመመለስ የሞከሩ ብዙ የስነ መለኮት አስተማሪዎችና ተማሪዎች አሉ፡፡ በዚህ ላይ የእግዚአብሔር ሰዎች በመከራው ጊዜ ስለ እምነታቸው ቢሰደዱም እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ የሚሆን መልእክት መስጠትን አልተወም፡፡ እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች በታላቁ መከራ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሕዝብ እጅግ በጣም አስፈላጊዎች ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ክፍል ውስጥ እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች እነማን እንደሆኑ አልገለጻም፡፡ ስለዚህ ነው የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች የተለያዩ ትርጉሞችን መስጠት የቻሉት፡፡ እነዚህን የተለያዩ ትርጎሞቹን እንደሚከተለው አስቀምጬዋለሁ፡፡1. ሙሴና ኤልያስ ናቸው፡፡ ይህንን ትርጉም የሚከተሉ ሰዎች በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 11 ላይ ያሉ ምስክሮች ሙሴና ኤልያስ በብሉይ ኪዳን ጊዜ ያደርጉ የነበሩትን አይነት ተአምራት ማድረጋቸው ስለተጠቀሰ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የሆኑት ሙሴና ኤልያስ እንደገና ወደ ሕይወት ተመልሰው ይመጡ ይሆናል ብለው ነው የሚተረጉት፡፡
2. ሄኖክና ኤልያስ ይሆናሉ፡፡ በዚህ ትርጉም መሰረት እግዚአብሔር ሄኖክንና ሙሴን ሳይሞቱ ወደ ሰማይ እንደወሰዳቸው በብሉይ ኪዳን ስለተጸፋና አሁንም እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች ከሞት ከተነሡ በኋላ ሳይሞቱ መወሰዳቸው በምንባብ ክፍል ስለተጠቀሰ እነርሱ ይሆናሉ፡፡
3. ኤልያስና ሚልክያስ ይሆናሉ፡፡ መሲሁ ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት ኤልያስ ይመጣል ብሎ ሚልክያስ ስለተነበየ ኤልያስና ትንቢቱን የተናገረው ሚልክያስ ራሱ ይሆናል ብለው ያስተምራሉ፡፡
4. ያዕቆብና ጴጥሮስ ናቸው፡፡ እዚህ ሁለቱ ሮማውያን የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያንን ባሳደዱበት ጊዜ የተገደሉና ለከፍተኛ እሥራትና ግርፋት ከዚያም ለሞት የተሰጡ በመሆናቸው በዚህ መከራ ጊዜ ከሙታን ተነስተው የሚያገለግሉ እነርሱ ይሆናሉ በሚል ነው፡፡
5. ቅዱሳን በሙሉ ናቸው፡፡ ይህንን አሳብ የሚሰጡ ሰዎች እንደሚናገሩት ሁለቱ ምስክሮች የተባሉት ሁለት ግለሰቦች ሳይሆኑ ሁለቱን የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ይዘው በመከራ ውስጥ ላሉት ሁሉ የሚመሰክሩ ቅዱሳን ወገኖች ናቸው፡፡
እንግዲህ የምንባብ ክፍሉ ስለ ሰዎቹ ማንነት በግልጽ ባይነግረንም እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መልእክት በጊዜው ላሉ አማኞች የሚተነብዩ ወንጌሉን የምስራች የሚሰብኩ መሆናቸው ግን እሙን ነው፡፡ አገልግሎታቸውም በትንቢተ ዳንኤል 12፡11 ላይ እንደተጠቀሰው ዓይነት ለ 1260 ቀናት ወይም 42 ወራት ነው፡፡ ያ ማለት ለሶስት ዓመት ተኩል ያገለግላሉ ማለት ነው፡፡ የዮሐንስን ራእይ በምናጠናበት ወቅት የትንቢተ ዳንኤልንም መጽሐፍን አንድ ላይ ማጥናት ያለብን ለዚህም ጭምር ነው፡፡ የትንቢተ ዳንኤልም መጽሐፍ እንደ ዮሐንስ ራዕይ ዓይነት የአቡቀለም ሲስ የሆኑ መልእክቶች አሉበት ፡፡ ስለዚህ ከዚህ ክፍል ያሉትን አሳቦች በሦስት ከፍለን እንይ፡፡
1. የሁለቱ ምስክሮች አገልግሎት
ሁለቱ ምስክሮች በሚገለግሉበት ወቅት ማቅ ለብሰው እንደሚሆን ዮሐንስ ይነግረናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ በሙላት በሚሰበክበትና የእግዚአብሔር ክብር በምንቀሳቀስበት ወቅት በአንጻሩ ደግሞ ሰዎች ኃጢአትን ሲለማመዱ ሲያዩ ነቢያትና ነገሥታት ካህናትም ማቅን መልበሳቸው የእግዚአብሔር ፍርድ ስላለ ንስሐ መግባት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ለዚህም ኢሳ 12፡22፣ ኤር.4፡8፣ኤር 6፡26፣ ዮናስ3፡5፣6፣8፣ ማቴ 11፡21ን መመልከት ይቻላል፡፡
የሁለቱ ምስክሮች አገልግሎት ከምርኮው ወደ እሥራኤል አገር ከተመለሱ በኃላ ወደ ተሐዲሶ ለማምጣት ያገለገሉ የዜሩባበልና የካህኑ የኢያሱን አገልግሎት ይመስላል( ዘካርያስ 4፡2-3፣11-14)፡፡ ምክንያቱም እነዚህ መቅረዞች ተብለዋል፡፡ በዘካርያስ መጽሐፍ አንድ
መቅረዝ ያለ ሲሆን በዮሐንስ ራዕይ ግን ሁለት መቅረዞች ተጠቅሰዋል፡፡ በዮሐንስ ራዕይ በራሱ ደግሞ መቅረዝ የክርስቶስን ቤተ ክርሰቲያን የሚወክል መሆኑን ደግሞ በመዕራፍ አንድ ላይ መመልከት ይቻላል( 1፡12-13)፡፡ በዘካሪስ ላይ ያለው መቅረዝ መንፈስ ቅዱስን የሚያመለክት ሲሆን በታላቁ መከራ ጊዜ የሚነሡ ሁለቱ ምስክሮች ( ሁለቱ መቅረዞች) የአገልግሎታቸውን ኃይል የሚቀበሉት ከመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ይህን ኃይል ከመንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኋላ በመቅደሱ ሆነው ልክ እንደ መቅረዝ የጌታን ብርሃን የሚሳዩ የእግዚአብሔር እውነተኛ ምስክሮች ይሆናሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተደግፈው ዓለምን ሁሉ ለሚቆጣጠረው እግዚአብሔር ምስክሮች ይሆናሉ፡፡
ሁለቱ ምስክሮች ነቢዩ ኤልያስ በ2ኛ ነገስት 1፡10-14 እንዳደረገው ሊጎዱአቸው በሚመጡ ጠላቶቻቸው ላይ እሳትን ከሰማይ በመጥራት ራሳቸውን ለመከላከል የሚችሉበት እግዚአብሔር ኃይል እንደሚሰጣቸው እንመለከታለን፡፡ ከእነዚህ ምስከሮች አፍ እሳት እንደሚወጣ መናገሩ ቀጥተኛ ትርጉም ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ተአምራትን እንዲያደርጉ በኃይል እንደሚሞላቸው ከክፍሉ እናገኛለን፡፡ ልክ ሙሴና ኤልያስ ሲያደርጉ እንደነበረው ሁሉ ውሃን የመለወጥና መቅሰፍትን በምድር ላይ የማምጣትና ዝናብ እንዳይወርድ የመከልከል ሥልጣን እንደሚሰጣቸው እንመለከታለን( ዘጸአት 7፡17-21፣ 9፡14፣ 11፡10፣ 1ሳሙ.4፡8፣ ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሚዎች ሁለቱ ምስክሮች ( ሁለቱ ወይራዎች) ኤልያስና ሙሴ ናቸው ያሉበት ምክንያትም ይህ ነው፡፡

2. የሁለቱ ምስክሮች ሞት
አገልጋዮች በታላቅ ኃይልና ጸጋ ሲያገለግሉ ሁል ጊዜ አድፍጦ የሚጠብቃቸው ጠላት እንዳለ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ አውሬው እነዚህን ሰዎች ሊገድላቸው የሚችለው ግን እነርሱ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን አገልግሎት ከጨረሱና እግዚአብሔርም የፈቀደለት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ምስክሮቹ ከትክክለኛ ጊዜአቸው በፊት ሊሞቱ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ጊዜ ሲደርስና እነርሱም አገልግሎታቸውን ሲያጠናቅቁ እንዲገድላቸው ተፈቀደለት፡፡ ይህ አውሬ ሐሰተኛው ክርስቶስ ነው፡፡ አውሬው የሁለቱ ምስክሮች ሬሳ በመንገድ ላይ ተኝቶ ሁሉም እንዲያያቸው ማድረጉ እነርሱን ማዋረዱ ሲሆን ይህም በቀድሞ የእግዚአብሔር ቃል በተነገረባቸው ዘመናት ተከናውኗል( መዝ 79፡2,3)፡፡ ጠላት አጋጣሚውን ካገኘ በሙሉ ኃይሉ በመጠቀም የእግዚአብሔር የሆኑትን አገልጋዮች ያዋርዳል፡፡ እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች የሞቱባትና የተዋረዱባት ከተማ ከሰዶምና ከገሞራ ጋር ተመሳሳይነት ያላት፣ በከፍተኛ ሁኔታ በደል፣ የምግባር ውድቀት፣ እግዚአብሔርን አለመውደድና ሕዝብን የመጭቆን ሁኔታ የሚታይባት ናት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ የተሰቀለባት ከተማም ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ያላት ናት፡፡ ምክንያቱም ሐሰተኛው ክርስቶስ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደረ ስለሆነ ነው፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው አገልግሎታቸው በታላቅ ተአምራት ሲታጀብ የነበረ ሁለቱ ወይራዎች አሁን ተገድለው ሬሣቸው በመንገድ ላይ ተጥሎ ሁሉም እየመጣ ያየው ጀመር፡፡ ጠላት የእግዚአብሔርን አገልጋዮች ሲያዋርድ እንደዚህ ነው፡፡
የእነዚህ ሰዎች ሬሳ የወደቀው በአንድ ከተማ ሲሆን ቃሉ ግን ከነገድ ከቋንቋ አህዛብ የሆኑ ሁሉ በመንገድ ላይ የወደቀውን የሁለቱ ምስክሮችን ሬሣ ለሶስት ቀን ያዩታል፡፡ እንዴት አድርገው በሁሉም ቦታ ያሉ ሰዎች ይህንን ሊያዩ ይችላሉ፡ እንግዲህ በጊዜ ከፍተኛ ስልጣኔ ስለሚሆን ምናልባት ሁሉም በያለበት ሆነው በቴሌቭዥን ወይም በሌላ የመገናኛ መንገድ ሊመለከቱት ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ ሕዝቦች ከተለያዩ ወገኖች ተውጣጥተው በወቅቱ እነዚህን ሰዎች ለማየት ሲሉ በኢየሩሳሌም የሚገኙበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በታላቁ መከራ ጊዜ ሰው ሁሉ የተደሰተበትን ሁኔታ የሚያሳይ ብቸኛው ታሪክ ይህ ነው፡፡ የምድር ወገኖች በእነዚህ ምስክሮች ሞት ምክንያት በጣም ይደሰታሉ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔርን የማዳን ወንጌል ስለማይሰሙ ነው፡፡ ልብ እንበል የወንጌል ሰባኪዎች፣ አስተማሪዎች ቅዱሳም ምስክሮች ሲወድቁና ሲዋረዱ ወንጌልን የመስበኩ ሥራ የሚቋረጥ ስለመሰለው አውሬውና ተከታዮቹ አጅግ አድርገው ይደሰታሉ፡፡ ይህኛው በምድር ላይ የመጨረሻው የሰው ልጆች ፈንጠዚያ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ሌላ ደስታ የሚባል በምድር ላይ አይሆንም ወይም ያበቃል ማለት ነው፡፡ ይህ የሚገርም ነው፡፡

3. የሁለቱ ምስክሮች ትንሳኤ
በዚህ ክፍል የሚያስደንቀው ነገር ሁለቱ ምስክሮች ሞተዋል ተብለው ከነገድ ከቋንቋ እና ከየአገሩ ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ደስታቸውን ከገለጹ በኋላ እንደገና ተነስተው፣ ወደ ሕይወት ተመልሰው መታየታቸው ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወጣው ሕይወት መንፈስ ለሞተው ሰውነታቸው ሕይወትን እንደሰጠ እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለሞተው ሕይወትን በመስጠት የሚታወቅ አምላክ ነው( ሕዝ 37፡5፣10፣ሮሜ 4፡17)፡፡ የሞቱ ምስክሮች በድን ሰውነታቸው በሰዎች ፊት በእግር መቆሙ በሞታቸው ለተደሰቱት ጠላቶቻቸው ሁሉ ድንጋጤ ሊፈጥር የሚችል ነው፡፡ የእግዚአብሔርንም ሆነ የሰውን የሆኑ ጠላቶችን እግዚአብሔር የሚያዋርደውና የሚስደነግጠው እንደዚህ ዓይነት ተአምራቶችን በማሳየት ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በዓይናቸው ከሚያዩት ድንቅ በተጨማሪ ከሰማይ የመጣው ድምጽ የበለጠ አስደንጋጭ የሚሆን ነበር፡፡ እንዲህ ነው የሚለው “ወዲዚህ ውጡ”፡፡ ከዚያም እነርሱም ለጣላቶቻቸው እየተመለከቱአቸው በደመና ወጡ፡፡ አውሬ ሐሰተኛው ወይም ሰይጣን መግደል ይችላል፣ ሬሳንም ማዋረድ ይችላል፣ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚመጣውን ትንሳኤና በክብር መውጣትን ሊከለክል አይችልም፡፡ ተገድለው ሬሳቸው እንኳ እንዳይቀበር ተደርገው የተዋረዱና በውርደታቸው ጠላቶቻቸው የተደሰቱበት እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች ወደ ሰማይ የወጡት በእግዚአብሔር ድምጽ ነው፡፡ ይህ ድምጽ የጌታቸው የኢየሱስ ድምጽ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ለባሪያዎቹ ይገለጥና ይናገራቸው የነበረው የሞትንና የስዖልን መክፈቻ ቁልፍ የያዘውና በሰባቱ ወርቅ መቅሮች መካከል ይመላለስ የነበረው ኢየሱስ ነውና፡፡ ዛሬ በተለያዩ ሁኔታዎችና ምክንያ የተዋረዳችሁ ካላችሁ፣ የተሰበራችሁና የወደቃችሁ ካላችሁ፣ ከጠላቶቻችሁም ሲፈነጥዙባችሁ እያያችሁ ቅስማችሁ የተሰበረ ልባችሁ የወረደባችሁ ወገኖቼ ዛሬ ለእናንተ የምሥረች አለኝ፡፡ የሞትና የሲዖል መክፈቻ ቁልፍ ያለው ጌታ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል ፣ ውርደታችሁንም በክብር ይለውጥ ዘንድ አለ፡፡
እነዚህ ሁለቱ ምስክሮች ወደ ሰማይ የወጡት በደመና ሲሆን ይህም “ሸክና ግሎሪ” ተብሎ የሚጠራውን የእግዚአብሔርን ክብር የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ደመና የእግዚአብሔር ክብር ምሳሌ ነው፡፡ እነርሱ ወደ ሰማይ የወጡበት ሁኔታ ከጌታ ከኢየሱስ አወጣጥ ጋር ይመሳሰላል፡፡ አንደኛ ሰዎች እያዩ፣ ሁለተኛ በደመና ነው የተወሰዱት( ሐዋ 1፡9)፡፡ ይህ የክብር መነጠቅ በብሉይ ኪዳን ከኤልያስ
መነጠቅ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው(2ኛ ነገሥት 2፡11)፡፡ እንደዚሁም ደግሞ አማኞች በደመና እንደምንነጠቅ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል( 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡17)፡፡ በሞታቸው የተደሰቱ ፣ በውርደታቸውም የፈነጠዙና የቧረቁ ጠላቶቻቸው ዓይናቸው እያየ ፣ ጆሮአቸውም እየሰማ ሲነጠቁ ደግሞ ምንም ማለት አልተቻላቸውም፡፡ ቁጥር 13ን በምንመለከትበት ጊዜ የምድር መናወጥ 7000 ሰዎችን ሲገድል ሐሰተኛው ክርስቶስ ሊያድናቸው እንዳልቻለና በዚህ ያሉት ደግሞ ለእግዚአብሔር ክብር እንደሰጡ እንመለከታለን፡፡ ሰይጣን ለጊዜው ኃይል ያገኘ እና ያሸነፈ ይምሰል እንጂ እግዚአብሔር ግን ክብሩን ሳይወስድና ባሪዎቹንም ሳያከብር በፍጹም አይተውም፡፡ እንግዲህ ከሰባቱ ወዮዎች የሁለተኝ ወዮ የተጠናቀቀው አገልጋዮች ሞት በሕይወት፣ ውርደታቸውንም በክብር ለውጦ ራሱም ከጠላቶቹ ሁሉ ክብርን በወሰደበት አስደናቂ ክንውን ነው፡፡ ሃሌሉያ