የኢየሱስ
ማኅተም
( የማንነታችን
ምልክት )
በፓስተር
ሳሙኤል ሾንጋ
በኢትዮጵያ
ዘመን አቆጣጠር በ1992
ዓ.ም.ገዳማ
በምዕራቡ በአገራችን ክፍል አንድ በዓይነቱ
የተለየ ወፍ ተገኘና መንግስት ልዩ ትኩረት
ሰጥቶት እንደተንከባከበው
ይታወቃል፡፡ ይህንን ወፍ ልዩ የሚያደርገው
ነገር መልኩ ብቻ ሳይሆን በአንገቱ ላይ
ያንጠለጠለው
ታግ ወይም ምንነቱን የሚያሳይ ጽሑፍና ቁጥር
ያለበት ካርድ መኖሩ ነው፡፡ የአካከቢ
ጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማሩት ሰዎች ይህንን
በሚያዩበት
ወቅት ይህ ወፍ ከየት አካባቢ እንደመጣና
እንዴትስ
እንደመጣ
ጥናት ማድረግ
ነበረባቸውና ሲጠና በታጉ ላይ የተቀመጠው
ጽሑፍ በዴች ቋንቋ የተጻፈ በመሆኑ ወፉ ከሆላንድ
አገር መምጣቱ
ታወቀና የኢትዮጵያ መንግሥት ከሆላንድ መንግሥት
ጋር ግንኙነት በማድረግ ያንን ወፍ በአውሮፕላን
አሳፍሮ ወደ አገሩ መመለሱ በኢትዮጵያ ዜና
መነገሩን እናስታውሳለን፡፡
ይህ ወፍ በአገራችን ካሉ በብዙ ሚሊዮን ከሚቆጠሩ
ወፎች እንዲያውም በሌሎች በአገሮች የማይገኙ
ከተባለትና አገራችንን የቱሪዝም
መገኛ እንድትባል
ካደረጉ ብርቅዬ ወፎች ሁሉ ተለይቶ የሁሉን
ትኩረት የሳበበት ምክንያት ምንድነው ብለን
መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ይህ
ወፍ በአንገቱ ላይ የተንጠለጠለው ታግ ባይኖረውስ
ኖሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ግምት ሰጥቶ
ወደ ሆላንድ አገር ይመልሰዋል ማለት እንችል
ይሆን፣ ምናልባት በዓይነቱ የተለየ ወፍ
በአገራችን ተገኘ ተብሎ ከመወራት ያለፈ ነገር
ሊደረግለት ባልቻለ ነበር፡፡ በተሸከመው
ምልክት ምክንያት ያ ሁሉ እንክብካቤ ተደርጎለት
ክብርም አግኝቶ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡
ይህ
ለእኛ ለጌታ አገልጋዮችና ምዕመናን ሁሉ ልዩ
ትምህርት ሊሰጥ የሚችል ምሳሌ ነው፡፡ የማንነታችን
ማረጋገጫ ፣ ከሌላው የዓለም ሕዝብ የምንለይበት
መለያ ምልክት ምንድነው፡፡ የጌታ የኢየሱስ
መሆናችን ተለይቶ የሚታወቀው በምንድነው፡፡
የሚያዩ ሁሉ የሚማረኩበት ኢየሱስን በእኛ
የሚያዩት ስለ እኛ የሚመሰክሩበት ምልክታችን
ምንድነው? ስብከታችን
ወይስ ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትረን
መሄዳችን? በጉባኤ
መገኘታችን ወይስ ብዙ መማራችን?
ይህ
ሁሉ አስፈላጊና መልካም ነው፡፡ ሰዎች ማን
እንደሆኑና ከየት እንደሆኑ በምን ዓይነት
ልምምድ ውስጥ እንዳሉ በሰውነታቸው
የሚታዩና የሚለጠፉ ነገሮች፣ የተለበሱ
ልብሶች ለይተው ያሳዩአቸዋል፡፡ ካህናት
በሚብሱት ልብስ፣ ናዝራውያን በጸጉራቸው፣
ዜማውያን በልብሳቸው፣ የመንግስት ታማኝ
ወታደሮች
በትከሻቸው ላይ ባለው የማዕሬግ ምልክቶቻቸው፣
ተለይተው
ይታወቃሉ፡፡ ህንጸዎችም እንደዚሁ፣ ለምሳሌ
ትምህርት
ቤቶች፣ መስጊዶች፣ ቤተክርስቲያናት ፣ የጦር
ካምፖች፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና
ኬላዎች፣ ሆቴሎች በላያቸው
በተተከለው ምልክት ምክንያት ምንነታቸውና
ባለቤትነታቸው ተለይቶ ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም
ሁሉ እኛ የኢየሱስ ክርስቶስና ለእርሱ አገልግሎት
ራሳችንን የሰጠን መሆናችን የሚታወቅበት
ምልክታችን ምንድነው?
ሓዋሪያው
ቅዱስ ጳውሎስ በሥጋችን ስለ ምንሸከመውና
ተለይተን ስለምንታወቅበት መለያችን በገላትያ
6፡17፣
ሐዋ 9 ፡10
-16፣ እና 2ቆሮ
4፡11-16
ባሉ ክፍሎች
እንዲህ ይላል፡፡ አነባለሁ
የጌታችንን ቃል፡፡
ከጳውሎስ አጠቃላይ
ትምህርቶች በአጭሩ የተወሰኑ ነጥችን
እንመለከታለን፡፡
1.
በሥጋችን
የምንሸከመው የኢየሱስ ማህተም ነው፡፡
እኔ
የኢሱስን ማህተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና
ከእንግዲህ
ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ፡፡
ይህ
አንድ ዓረፍተ ነገር ነው ፣ ነገር ግን ትልቅ
መንፈሳዊ ምሥጥር ያዘለ መልእክት ነው፡፡
አጭር አሳብ ነው ግን የጳውሎስን ሕይወት
ከደህንነቱ እሰከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ያለውን
ዓላማ ሁሉ ተቅልሎ በውስጡ የያዘ አሳብ ነው፡፡
የጳውሎስ ብቻ ሳይሆን የእኛን የሁላችንንም
ሕይወት፣ አገልግሎት፣ ትምህርት ፣ ስብከት
፣ በምድር ላይ የምንኖርበትን የኑሮ ዓላማ
ሁሉ የሚያሳየን አሳብ ነው፡፡ ያውም በሰውነታችን
የምንሸከመው የማንነታችን መለያ ፡፡
ሐዋሪያው
ጳውሎስ በገላትያ አውራጃዎች የጌታን ወንጌል
ሰብኮ ቤተ ክርስቲያናትን ከተከለ በኋላ ሌሎች
ሌላ ወንጌል የሚሰብኩ ሐሰተኛ አስተማሪዎች
ተነስተው ጳውሎስ እውነተኛ ሐዋሪያ ስላይደለ
የሚሰብከው ስብከት ትክክል አልነበረም ብለው
አስተማሩ:: ደህንነት
የሚገኘው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን
በጸጋው ብቻ መሆኑን ያስተማረውን የጳውሎስን
ስብከት በማጣጣል ደህንንት የሚገኘው ሕግን
በመጠበቅ፣ በመገረዝና በመልካም ሥራ ነው
በማለት ምዕመናንን ከእውነተኛው ትምህርት
ዘውር አድርገዋል፡፡ ይህንን የነፋቄ ትምህርት
ሲሞግት ከቆየ በኋላ የገላትያን መጽሐፍ
ሲያጠቃልል እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ
ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ ማንም
አያድክመኝ በማለት ይናገራል፡፡
ለኢየሱስ
ክርስቶስ ታማኝ ሓዋሪያ የመሆን፣ እውነተኛ
ለመሆኔ ምንም ጥርጥር የሌለው በሥጋዬ የተሽከምኩት
ምልክት አለኝ፡፡ ይህ ምልክት ሌሎች የኑፋቄ
አስተማሪዎች የሌላቸው ምልክት ነው፡፡ ይህን
ምልክት ጳውሎስ ማኀተም ብሎታል፡፡ ጳውሎስ
ይህ ምልክት የኖረበት ምክንያት ምንድነው
ለሚለው የተለያዩ ምክንያቶች
ይኖራሉ፡፡ አንደኛው በልስጥራና በደርቤ
ወንጌልን በሰበከበት ወቅት ተቃዋሚዎቹ ክፉኛ
ከደበደቡት በኋላ ከከተማው ውጭ ጎትተው
እንደጣሉት የገላትያ ሰዎቸ ራሳቸው ያውቃሉ፡፡
ጳውሎስ እንደዚያ የተደበደበው የወንጌል
ስብከት ሥራውን በተቃውሞ ውስጥ በመስበክ
ለኢየሱስ ያለውን ታማኝነት በመግለጹ ምክንያት
የተደረሰበት ስለሆነ በድብደባው ምክንያት
በሰውነቱ ላይ የተፈጠረውን ጠባሳ ማኅተም
ብሏል፡፡ እንዲያውም እርሱ አይሁድ አንድ
ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ
( 2 ቆሮ
12 ) እንዳለው
ይህ ድርጊት በተፈጸመበት ወቅት በሰውነቱ
ላይ ከግርፋቱ የተነሳ የከሰተው ጠባሳ ለሁሉም
ሰው የሚታይ ሲሆን ያ ደግሞ ለጌታ ኢየሱስና
ለወንጌል አገልግሎት ባለው መሰጠት ምክንያት
የመጣበት ነው፡፡ ይህንን በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና
ማንም አያድክመኝ ይላል፡፡ እኛ የጌታ ታማኝ
መሆናችንን ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁልን
በዚህ ዘመን የግድ የግርፋትን ጠባሳና ገጣባ
ለሰው ሁሉ በሚታይ የሰውነት ክፍላችን መኖር
አይኖርብንም፡፡ ነገር ግን
ማኅተም የሚለው ሌላ ቁልፍ አሳብ አለ፡፡
እርሱም ከማንም ጋር ድርድር የማናደርግበት
የድንነታችን ጉዳይ ነው፡፡ በጌታ ያለንን
ደህነንትና ሕይወት ማንም ይሁን የማንም
ትምህርት እንዲያጎድፍብን አንፈቅድለትም፡፡
ይህ ማሕተም የጌታ የመሆናችን ማረጋገጫ ነው፡፡
ይህንን በኤፌሶን 1፡13-14
እንመለከታለን፡፡
ከምንም በላይ የደህንንታችንና ስለ
ደህንነታችን የሚሰጠው ትምህርት
፣ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በምንም የሚለካና
ከምንም ጋር የምናወዳድረው አይደለም፡፡
ስለዚህ ነው
ጳውሎስ የጌታ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ
ተሸክምአለሁና ማንም አያድክመኝ የሚለው፡፡
ማኅተም
የባቤትነት ማረጋገጫ ነው፡፡ የማን እንደሆንን
እና ለየትኛው ዜጋ እንደሆንን የማያዩን
ሰዎች የሚለዩን በያዝነው
መታወቂያ ወይም በታታመበት ማሕተም ነው፡፡
የበግ ነጋዴዎች በጅላ ካጫኑቸው በጎች ውስጥ
የየራሳቸውን በጎች ለይተው የሚያውቁት በበጎቹ
ጀርባ ላይ በቀቡት የቀለም ማሕተም ነው፡፡
ለእኛ ደግሞ ለእግዚአብሔርና
ለመንግሥቱ የተለየን መሆናችን የሚታወቅበት
ትልቁ ማኅተማችን በሥጋችን የተሸከምነው
የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው፡፡
2.
የጌታችን
የኢየሱስን ስም ነው(ሐዋ
9፡10-16)
በደማስቆ
ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀመዝሙር ነበር፣
ጌታም በራዕይ ሓናኒያ ሆይ አለው፡፡ እርሱም
ጌታ ሆይ እነሆኝ አለ፡፡ ጌታም ተነስተህ ቅን
ወደሚባለው መንገድ ሂድ በይሁዳም ቤት ሳውል
የሚባል አንድ የጤርሴስ ሰው ፈልግ፡፡ እነሆ
እርሱ ይጸልያልና ሓናንያ የሚሉት ሰው ገብቶ
ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቷል
አለው፡፡ ሐናንያ መልሶ ፣ ጌታ ሆይ በኢየሩሳሌም
በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ
ሰው ከብዙዎች ሰምቻለሁ ፣ በዚህም ስምህን
የሚጠሩትን ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን
አለው አለ፡፡ ጌታም ይህ በአሕዛብም ፣
በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን
ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፣
ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው
እኔ አመለክተዋለሁ አለው፡፡
ጌታ
ኢየሱስ ከጳውሎስ ምን ፈልጎ እንደጠራው ይህ
አሳብ ይነግረናል፡፡ ጳውሎስ በአህዛብ አገሮች
ቤተ ክርስቲያናትን ተክሏል፡፡ ብዙ ሰዎችን
የጌታን ቃል አስተምሯል፡፡ እንደነ
ጢሞቴዎስ ያሉት ደመዛሙርትና የቤተ ክርስቲያን
መጋቢያንን አፍርቷል፡፡ እንደምናየው ዛሬም
ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት የሚሆኑ
13 የሚያህሉ
መልእክቶችን ጽፎ አል፡፡ በተዘዋወረባቸው
አገሮችና መንደሮች ሁሉ
ተአምራቶችን ሁሉ አድርጓል፡፡ እነዚህ ሁሉ
ሥራዎቹ የተጠቃለሉት በአህዛብም በነገሥታም፣
በእሥራኤልም ልጆች ፊት የጌታን ስም በመሸከም
ውስጥ ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ ልናደርጋቸው የተገባን ቢሆንም
ከሁሉም በላይ የጌታን ስም የምንሸከምለት
ዕቃው እንድንሆን
ይፈለግብናል፡፡ ዛሬ አማኞች በምንኖርበት
የክርስትና ሕይወታችን የጌታ የኢየሱስ ስም
ከፍ ብሎ ይውለበለባል ወይስ ይሰደባል?
መቅረዝ
የሚባል ዕቃ አለ፡፡ ይህ መቅረዝ
የሚባው ዕቃ በአንድ
ቤት ውስጥ መብራትን ከፍ አድርጎ የሚሻከም
ነው፡፡ መቅረዙ መብራቱን ከፍ አድርጎ ሲሸከም
መብራቱ ሲታይ
እርሱም አብሮ ይታያል፡፡ መብራቱ ካልታየ
ግን መቅረዙ
ምንም ክብር ሊኖረው እንደማይችል
ሁሉ እኛም የኢየሱስን ስም ካልተሸከምን
ከክርስቶስ የሚመጣውን
ክብር ልናይ አንችልም፡፡ ወገኖቼ ሆይ ዛሬ
ራሳችንን የጌታ ዕቃ አድርገን አቅርበናል
ወይ? ክቡር
ስሙን ለመሸከም የተመረጥን ዕቃዎች መሆናችንን
አውቀን ስሙን እየተሸከምን
ነው ወይስ ራሳችንን እያወጅን ነው?
በየቤተ
ክርስቲያናችን መድረክ ኢየሱስ ይሰበካል?
ከመድረክ
ስንወርሰድ ሰዎች ኢየሱስን እንዲመለከቱ
ስሙን እንዲጠሩ ፣ በስሙ እንዲታመኑ ፣ የኢየሱስ
ብቻ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ ስሙን ከፍ እያወጅን
ነው ወይስ የእኛ ስም እያወጅን ነው?
ተሸካሚ
ዕቃ ለራሱ አይኖርንም ለተሸከመለት ጉዳይ
ይኖራል ምክንያቱም ዕቃ ነውና፡፡ የሚታየው
እርሱ አይደለም ያ የተሸከመው እንጂ፡፡
ተሸካሚው ምንጊዜም
ከታች እንጂ ከላይ ሊሆን አይችልም፡፡ እኛ
ከታች ሆነን የጌታ ስም በእኛ ላይ ሆኖ ሰዎች
ሁሉ ይህንን ስም በሰውነታችን፣ በሕይወታችን
፣ በአካሄዳችን አኗኗራችን ያዩታል ወይ?
3.
የክርስቶስን
ሞትና ትንሳኤ ነው(
2 ቆሮ.
4
፡7-16)
የኃይሉ
ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን
ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፡፡፡
በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፣ እናመነታለን
እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፣ እንሰደዳለን እንጂ
አንጣልም፣ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፡፡የኢየሱስ
ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁል
ጊዜ የኢየሱስን ሞት በሥጋችን ተሸክምን
እንዞራለን፡፡
ይህን
አሳብ ለመግለጸው ሐዋሪያው ጳውሎስ ከቀጥር
7 ጀምሮ
በጣም አስደናቂ ነገር ይናገራል፡፡ በእኛ
እግዚአብሔር የሚሠራው ሥራ የሚያስገርም
መሆኑን ሲያመለክት እንዲሁም ደግሞ አንድንም
ነገር በራሳችን ብርታት እንዳላደረግነው
እንድናውቅ ያሳስበናል፡፡
የኃይሉ ታላቅነት ከእኛ እንዳይደለ እንድናውቅ
ያሳስበናል፡፡ በዓለም ላይ
ብርቱዎች የተባሉ ብዙዎቸ እያሉ እግዚአብሔር
አምላክ የክብር መዝገቡን ሸክላ በሆንንው
በእኛ ውስጥ እንዳስቀመጠ ይናገራል፡፡ ሸክላ
ምንም ክብር የሌለው ነገር ነው፡፡ በጣም ደካማ
ነገር ነው፡፡ አንዴ ወድቆ ከተሰበረ መልሶ
መጠገን የማይችል በጣም አሳዛኝ የሆነ ዕቃ
ነው፡፡ ሸክላ ከአፈር
የሚሠራ ነው፡፡ ሸክላ ደካማና አቅመ ብስ
ነው፡፡ ሸክላ ብዙ ክብርም የሚሰጠው ነገር
አይደለም እንዲያም
የሸክላ ዕቃ የሚሠሩ ሰዎችም ጭምር በሌሎች
ዘንድ ክብር የማያገኙባቸው ብዙ ሁኔታዎች
አሉ፡፡ ግን የሚገርመው ነገር
ቢኖር ይህ ደካማ የሆነ ተሰባሪ ዕቃ ውድ የሆነውን
ነገር ለመሸከምና በውስጡ ለመጠበቅ መመረጡ
ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በሸክላ ዕቃ ውስጥ ወርቃቸውን
ይኖሩታል፣ ብራቸውን ያስቀምጡበታል፣ ጌጣቸውንም
ይደብቁበታል፡፡ ሽካላ ዕቃ ተሰባሪና የተናቀ
ደካማ ነው ግን በጣም ውድ ለሆነ አገልግሎት
ይውላል፡፡ በጥንት ጊዜ የእግዚአብሔር ሰዎች
በጣም አስፈላጊ የሆነ የብራና ጽሑፋቸውን
መሸሸግ ባስፈለጋቸው ወቅት በእንሥራ (
በሸክላ
ዕቃ) ውስጥ
አድርገው በዋሻ ስለሸሸጉት ሰነዱ ሳይጠፋ
ለዘመናት እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ዕቃው ሸክላ
ነው ግን ለክቡር አገልግሎት ተፈለገ፡፡
ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በኩል ባለው በረሀማ
አካባቢ የኖሩ ኩምራን ሶሳይቲስ የተባሉ
በሚኖሩበት ኩምራን ዋሻ ውስጥ የተገኘው
የሙት ባህር ጥቅል የተባለው ብራና የተገኘው
በዋሻ ውስጥ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ታሽጎ ነበር፡፡
ይህ የሙት ባህር ጥቅል የተሰኘው ብራና ትክክለኛ
የሆኑ ብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በውስጡ የያዘ
የጥንት ጽሑፍ ሲሆን ለበርካታ ዘመናት
ተደብቆ የቆየውና ከመቃጠልና ከመውደም የተረፈው
በሽክላ ዕቃ ውስጥ ነበር፡፡ በጊዜው የነበሩ
ሰዎች ያንን ስክሮል ለመሸሸግ ለምን የሸክላ
ዕቃ እንደመረጡት ባይገባኝም ግን ታሪኩ በጣም
ያስደንቀኛል፡፡ ወገኖቼ ሆይ እግዚአብሔር
አሁንም እያደረገ ያለው ይህን ነው፡፡ የእርሱን
ታላቅ ሥራ በሚያምኑትና በማያምኑት ሁሉ ዘንድ
ለማስፈጸም እኛን ደካሞችን፣ ሸክላዎችን፣
ተሰባሪዎችን መረጠና ክቡር መዝገቡን በእኛ
ውስጥ አኖረው፡፡ ለምን?
የእርሱ
ሥራ በሰው ኃይል እንደማይከናወን እንዲታወቅ
ነው፡፡ ኃይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ
እንዳይደለ እንዲታወቅ ነው፡፡ በዓለም ስንኖር
ይህ የክብር መዝገብ እያለ በሁሉ እንገፋን፣
እናመነታለን፣ እንሰደዳለን፣ እንወድቃለን
ይላል፡፡ ይሁን
እንጂ አንጨነቅም፣ ተስፋ አንቆርጥም፣ አንጠፋም
ይለናል፡፡ ምክንያቱም ጌታ በውስጣችን
ላስቀመጠው መዝገቡ ስለሚጠነቀቅ ነው፡፡
ጳውሎስ
ይህንን አስደናቂ ነገር ከተነናገረ በኋላ
አሁንም በሥጋችን ስለምንሸከመው ጉዳይ
ይናገራል፡፡ እንዲያው በሥጋችን
የኢሱስን ሞትና ሕይወት ተሸክምን እንዞራለን፡፡
የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን
እንዲገለጥ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን
ተሸክመን እንዞራለን ይላል፡፡
ወንጌልን በመስበካችን ምክንያት የተለያዩ
መከራዎች ቢደርሱብንም እንደሚደርሱብን
መከራዎች ብዛት መጠን አንጠፋም ምክንያቱም
ለደካማው የሸክላ ዕቃ የእግዚአብሔር ርዳታ
ስለማይለየው ነው፡፡ ከዚህም በላይ በመገፋት
፣ በማመንታት፣ እና በስደት ውስጥ በምናልፍበት
ጊዜ ሁሉ እኛን በሚያዩን ሁሉ ፊት የኢየሱስ
ሞት በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን፡፡
ይህንን የምናደርገው የኢየሱስ ትንሣኤ በሰዎች
ሁሉ ዘንድ
እንዲታወቅ ነው፡፡ በወንጌል አገልግሎታችን
ምክንያት ለሞት አልፈን የምንሰጥ ቢመስለንም
ግን የኢየሱስን ሞት በሥጋችን ተሸክመን
እንዞራለን ይላል፡፡ እንዞራለን ማለት ምን
ማለት ነው በሚያዩን ሁሉ ዘንድ ፣ የምንመላለሰው
የኢሱስን ሞትና ትንሣኤ እያወጅን
ነው፡፡ የቤተ ክርሰቲያን በምድር የመኖሯ
ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ
ለሁሉም ማወጅ ነው፡፡ እኛ
ይህንን እድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
የቤተ
ክርስቲያን ትልቁ ጥሪ የጌታችንን የኢየሱስን
ሞትና ትንሣኤ በዓለም ላይ ከፍ አድርጋ መሸከም
ነው፡፡ የክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ መስበክ
ከጳውሎስ በፊት ሆነ ከእርሱ በኋላ የነበሩ
ነቢያትና ሐዋሪያት ቁልፍ ተግባርና የተልዕኮአቸው
ማእከል እንደሆነ ቅዱሳት መጸሕፍትን
በምናነብበት ጊዜ
የምናገኘው ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው
ነቢይ የነበረው መጥመቁ ዮሐንስ ከኢየሱሰስ
በፊት የመጣ ነበር፡፡ እርሱ መንግሥተ ሰማይ
ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ እያለ ለንስሐ በውሃ
እያጠመቀ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ በሰበከበት
ወቅት አንድ ምቹ አጋጣሚ አግኝቶ ነበር፡፡
ያውም ሰዎች አንተ ማነህ ፣ መሲሁ ነህን?
ኤልያስ
ነህን፣ ኤርምያስ ነህን፣ ነቢዩ ነህ እያሉ
ሲጠይቁት ሁሉንም አይደለሁም ነው ያላቸው፡፡
ስለራሳችን ዝና፣ ክብርና ሞገስ እንደምንኖረው
የዛሬው ዘመን አገልጋዮች ቢሆን ኖሮ ስለ ራሱ
ብዙ መናገርና ብዙ ክብር ማግኘት ይችል ነበር፡፡
ግን አይለደለሁም አለ፡፡ ታዲያ ማን ነህ ሲሉት
እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፣ ከእኔ
በኋላ የሚመጣው አጎንብሼ የእግሩን ጠፍር
መፍታት የማይገባኝ ከእኔም የሚበረታ መንፈስ
ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቃችሁ ነው አለ፡፡
ኢየሱስ ሲመጣ ኣይቶ እነሆ የዓለምን ኃጢአት
የሚያወግድ የእግዚአብሔር በግ ብሎ ወደ ኢየሱስ
አመለከተ፣ እንዲያውን እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ
ይገባኛል ብሎ ክብርን ለኢየሱስ ሰጠ እንጂ
ከራሱ ባገኘው አጋጣሚ ክብርን ሙገሳን
አልወሰደም፡፡ ስለዚህ ከሴቶች ከሚወለዱት
መጥመቁ ዮሀንስን የሚበልጥ የለም ተባለለት፡፡
ጌታ ሲከብር እርሱም አብሮ ከበረ፡፡
ሐዋሪያው
ጳውሎስም አንደዚሁ ነው፡፡
የኢየሱስን
መኅጸም በሥጋዬ ተሸክሜአሁ፣
ግሪኮች
ጥበብን ይሻሉ፣አይሁዶች ምልክትን ይፈልጋለሉ
እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እሰብካለን፡፡
ለእኔ
ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነው
ለእኔ
ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት
ቆጥሬዋለሁ …. እርሱንና
የትንሳኤውን ኃይል አውቅ ዘንድ ቢሆንልኝ
በሞቱ እንኳ እመስለው ዘንድ እነፍቃለሁ
ከጌታችን
ከኢየሱስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ
ራቅ አለ፡:
እኔ
ክርስቶስን እንደሚመስል እናንተ ደግሞ እኔን
ምሰሉ
በቆላስይስ
መልእክት ብቻ ከ18ጊዜ
በላይ የክርስቶስን
የበላይነት ጠቅሷል፡፡
አንዳንድ
ሕይወታቸው
ለጌታ ያልታመኑ ሰዎችን
ሲገልጽ ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉ የክርስቶስ
ኢየሱስን ግን አይደለም፡፡ ፊል 2፡21
በ18ኛው
ክፍለ ዘመን የፑሪታን አባት ተብለው የሚጠሩ
ዊሊያም ፔርክንስ
የተባሉ የሥነ መለኮት ሰው የትምህራቸውና
የሕይወታቸው
መፈክር ለክርስቶስ፣
በክርስቶሰ፣ ስለ ክርሰቶስ
የሚል ነበር፡፡ በቅርቡ
ከሁለት ዓመት በፊት ገዳማ ወደ ጌታ
የተጠሩት የእግዚአብሔር ሰው ጆን ሰቶትም
ክርስቶስ ካልተሰበከ
ስብከቱ አልተሰበከም፡፡ ክርስቶስ
ካልተዘመረ
ዘማሪው መዝሙሩን አልዘመረውም፣ ክርስቶስና
ስሙ ካልታከሉበት
ፀሎቱም
አልተጸለየም ብለዋል፡፡
4.
የጌታ
የኢየሱስን መስቀል መሸከም፡፡ ማቴ.
16፡
24-28፣
ሉቃስ 9 23-24
ሰዎች
ጌታን እንደተቀበሉ መጀመሪያ የሚሰጣቸው
ትምህርት የደቀመዝሙርነት ትምህርት ነው፡፡
ጌታ ማንም እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር መስቀሌን
ይሸከም ያለውን ትምህርት አማኞች የው ጥምቅ
እስክ ወስዱ ድረስ ብቻ ብቻ እናስተምራቸዋለን፡፡
ከዚያ በኋላ ላለው የክርስትን ሕይወት ዕድገት
ደረጃዎች ውስጥ እንደማያስፈልገን አድርገን
እንመለከተዋለን፡፡
ይሀን
እንጂ የጌታን መስቀል መሸከም እስከ ሕይወታችን
ፍጻሜ ድረስ የምንተገብረውና የማናቋርጠው
ጉዳይ ነው፡፡ ክርስትና ደስ የሚል የሕይወት
ጉዞ ቢሆን መስቀል የመሸከም ግዴታ ያለበት
መሆኑ ደግሞ ሌላው ገጽታው ነው፡፡ በክርስትና
ሕይወት ጦርነት ድል፣ ያለ መስዋዕትነት ክብር
፣ ያለመሰጠት በረከት የለበትም፡፡ ስለዚህ
ክርስትና እንዴት ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚፈልግ
እንደሆነ እንመለከታለን፡፡ ኢየሱስ በዚህ
ሥፍራ ምንም እኔን ለመከተል
የሚወድ የሚወድ ቢኖር
የሚል ቃል ተጠቅሞአል፡፡ በሌላ ሥፍራ ደግሞ
ከኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር አለ፡፡ ይህ ማለት
ምን ማለት ነው; ማንም
ክርስቲያን ሊሆን የሚፈልግ ማለቱ ነው፡፡
ምክንያቱም ክርስትና የጥንት ስሙ መከተል
ወይም መንገድ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በአንጾኪያ
ክርስትና ከመባለቸወው በፊት ክርስትና መንገድ
በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አማኞችም ደግሞ
የመንገዱ ሰዎች ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ ስለዚህ
ኢየሱስ እኔን መከተል የሚወድ ወይን ከኋላዬ
ሊመጣ የሚወድሲል ክርስትያን መሆን የሚወድ
ወይም የሚፈልግ ማለቱ ነው፡፡ ክርስትና መሆን
ደግሞ የአንድ ጊዜ ሞቅታ የሚያመጣው ሳይሆን
ሁል ጊዜ የምንተገብረው ነው፡፡ የኢየሱስ
ተከታይ መሆን ፣ የእርሱ ተማሪ መሆን
የክትትል ትምህርት ጨርሰን ወደ አገልግሎት
መሥመር እስክንገባ ድረስ ብቻ የሚሆን ነገር
አይደለም፡፡ ኢየሱስን የምንከተው ፣ በመንገዱም
የምንራመደው በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ነው፡፡
እህግዲህ
ይህ አሰብና እውነት ዛሬ ተረስቷል፡፡ አንዳንድ
ጊዜ ወደ አገልግሎት ደረጃ ከደረስን ምንም
ከክርስትና አኗኗር እንደተመረቅን ይሰማናል፡፡
ግን የእግዚአብሔር ቃል መስቀሉን መሸከም
ያለብን በየዕለቱ እንደሆነ ይነገረናል፡፡
በየዕለቱ እንምንዘምረውና እንደምናገልግለው
ሁሉ በየዕለቱ የጌታን መስቀል እንሽከማለን
ማለት ነው፡፡ መስቀሉን ሳይሸከሙ በኢየሱሰስም
ንገድ ሳይሄዱበት የሚያገልገልሉት አገልግሎት
ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም ለምዕመናንም
አይጠቅምም፡፡ በኢየሱስ መንገድ ሳይሄዱበት
የሚደረገው አገልግት፣ ዘማሪነት፣ ሰባኪነት፣
አስተማሪነት፣ መሪነት ሁሉ ለቤተከርስቲን
እጅግ በጣም ጠንቅ ነው፡፡ የዛሬዋ ቤተክርስቲያን
ትለቁ ችግር የአገልጋዮችና የመሪዎች ችግር
ሳሆን በሕይወታቸው ጌታን የማይከተሉ አገልጋዮችና
መሪዎች የተበራከቱ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ለመሆኑ በሕይወታቸው ኢየሱስን የማይተሉ
መሪዎችና አገልጋዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ
እናውቃለንን;
የኢየሱስ
መሆናችንና በመንገዱ የመሄዳችን ትልቁ መሥፈርት
አንዱ ራስን መካድ ነው፡፡
ራሳችን ካልካድን የእርሱን መንገድ መምረጥ
እንችልም፡፡ ሰው ወደ ጌታ ሲመጣ ራሱን ሲክድ
ብቻ ነው ኢየሱስ በልቡ የሚነግሰው፡፡ ሰዎች
ክርስትያኖች አንዲሆኑ እናስተምራቸውና
ራሳቸውን እንዲክዱ ስላላገዝናቸው ማነታቸውና
እነርሱነታቸው በውስጣቸው ይኖራል ፣ ሲያድጉም
ያ እኔነታቸው አብሮ እያደገ እየጎመሰ ይሄድና
የክርስቶስን ቦታ ይይዝባቸዋል፡ ከዚህ የተነሳ
በሕይወታቸው ጌታን ሌለሎች ማሳየት ያቅታዋል፡፡
ምክንያቱም በልባቸው ዙፋን ላይ ፣ በሕይወታቸው
የውስጠኛው ክፍ ላይ ቦታውን የያዘውና የሞላው
ጌታ ኢየሱስ ሳይሆን እኔነቻው ነው፡፡ እኔን
አወድሱኝ የሚሉ መጋቢዎች ገጥሞአችሁ አያውቁም;
እኔ
ነኝና ባለመፍትሔው እኔን ብቻ የሚሉ አገልጋዮች
ገጥሞአችሁ አያውቁም;
እነዚህ
ራስን ያለመካድ ችግር ተጠቂዎች ናቸው
ማለት ነው፡፡ ራሳችንን በካድን ጊዜ እኛ
ሳንሆን እገዚአብሔር ብቻ ሕይወታችንን ሊያድን
እንደሚችል አውቀን ራሳችንን በእርሱ እጅ
ላይ ወደምንጥልበት የአቅም ደረጃ እናድጋለን
ማለት ነው፡፡ ስላራችንን ያለንን የተሳሳተ
ግምት ትተን ፣ ሰይጣንም የሚሰጠንን ፍቅር
ሁሉ ወደ ጎን በመተው በክርስቶስ ፍቅር
ወደምንታሰርበት ካፓሲቲ እያደግን እንሄዳን
ማለት ነው፡፡ በአንጸሩመ ደግሞ ራሳችንን
ወደ ማገሱና መሸሙ ደረጃ በደረሽን ቁጥር ጌታን
ከልባችን ዙፋንና የክብር ሥፍራ ወደ ማውረዱ
ደረጃ እየተሸጋርን እሄዳለን ማለት ነው፡፡
ሰዎች የእግዚአብሔር ነገር እንደተወሰደባቸው
ከሚታወቅበት መንገድ አንዱ እኔ እኔ እኔ ሲሉ
ነው፡፡ በእኔነት የተሞላው ሰው ጌታ ኢየሱስን
ለሌሎች ማሳየት አይችልም ምክንያቱም ሰው
በውስጡ ከሞላው ነገር ያፈሳልና፡፡
ሁለተኛው
መሥፈርት ፈቃደኝነት
ነው፡፡ የሚወድ ቢኖር (
የሚፈልግ
ቢኖር) የሚለው
አሳብ በጣም አስፈላጊ ቃል ነው፡፡ ሁሉም ነገር
በራስ ውሳኔ በፈቀደኝነትና በፍቅር ነው፡፡
ይህ ማኛውንም ነገርለማድረግ የሚያስችለን
ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔርም ሆነ ሰይጣንም
የራሳቸውን መንገድ እንድንከተለ የሚያደርጉን
በፍቅር ነው፡፡ ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ የእርሱ
ተለታች የሚየደርገን በፍቅር ነው፡፡ ሰጣን
ደግሞ የራሱ ተከታዮች የሚያደርገን ፍቅርን
በማሳየት ነው፡፡ ሰይጣን ፍቅርን የገለጠበት
መንገድ ኢየሱሰስ ፍቅርን ከገለጠበት መንገድ
ይለያል፡፡ ይህንን ነው አማኞች መለየትና
መንቃት ያቃተን፡፡ ኢየሱስ ምክንያታዊ ባልሆነ
ፍጹም ፍቅር ወደደን፡፡ እኛን አብልጦ ከመውደዱ
የተነሳ ክቡር ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ክቡር
ደሙንም ስለ እኛ አፈሰሰልን፡፡ ሰይጣን ደግሞ
ፍቅር የገለጠው ሰዎች ብቻ አፍቃሪዎች
እንዲሆኑ በማድረግ ነው፡፡ የገንዘብ አፍቃሪዎች፣
የክብር አፍቃሪዎች፣ የዝሙት አፍቃሪዎች፣
የዚህ ዓለም አፍቃሪዎች ፣ የዘር የወገን
አፍቃሪዎች፣ የመጠጥ የሲጋራ የጫት ፣ ተድላ
ወዘተ አፍቃሪዎች እንዲሆን ያደርግና ጌታ
የሚያፈቅሩበትን አቅም ይወስድባቸዋል፡፡
እዚያ ውስጥ ግን ሳይታወቅ እየተወደደ ያለው
እርሱ እንደሆነ ማንም ላያስተውል ይችላል፡፡
ለሰዎች ደግሞ የሚያምራቸው መንገድ ሰይጣን
የገለጠው መንገድ ነው፡፡ ስዚህ መከራን ፣
ችግርን፣ ስዴትን ልፋትንና መንፈሳዊ ጦርነትን
እንዲሁም መስዋዕትነትን የሚጠይቀውን የኢሱስን
መንገድ ለጊዜውም ዞር አድርገው ይሕንን በጣም
ማራኪና ናፋቂ የሆነ ልፈትና እንግልት የሌለበትን
የፍቅረር መንገድ መከተል ይላቸዋል፡፡
ሌላው
እንግዲህ መስቀሉን መሸከም
ነው፡፡ ምንድነው መስቀሉ;
መስቀል
የመሸከም ጉዳይ ብዙ ጊዜ የማይገባን ምስጥር
ይሆንብናል፡፡ ሌላው ቀርቶ የኢየሱስ ደቀ
መዛሙርትም ቢሆኑ ግር ሳይላቸው አልቀረም
ምክንያቱም ኢየሱስ መስቀሉን ማይሰከም ለእኔ
ሊሆን አይችልም ሲል ገና በመስቀል አልተሰቀለም
ነበርና፡፡ ይሁን እንጂ በጊዜው ከኢየሱስ
በፊት በመስቀል ላይ የተሰቀሉ ብዙ ሰዎች
ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ ለመምጣቱ
ምናልባት 120 ዓመታት
በፊት ኢንተርተስታሜንት
ፒሬድ ተብሎ በሚታወቅው
ጊዜ አንቲክዮስ ኤፒፓኔስ በግሪክ መንግሥት
ሥልጣን ጊዜ በርካታ አይሁዶችን በእንጨት
ላይ ሰቅሎ ገድሎአቸዋል፡፡ ደግሞ የሮማውያን
ንጉሥ ታላቁ ሄሮዲስ 2000
አይሁዶችን
ሰቅሎአቸዋል፡፡ በኢየሱስ የምድር አገልግሎት
ጊዜ ሥቅላት በግሪክ፣ በሮማውያን፣
በመካካላኛው ምሥራቅ
በግብጾችም ዘንድ በጣም
የተለመደ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች
30.000 አይሁድ
በስቅላት ተገድለዋለል
የሚል ግምት አላቸው፡፡ ይህንን ደግሞ የኢየሱስ
ደቀ መዛሙርት ያውቃሉ፡፡ ቢሆንም ኢየሱስ
የሚለው ከባድ ሊሆንባቸዋል፡፡ እንዲህ ኢየሱስን
መከተል እና የክርስትና ሕይወት መኖር ምን
ዓይነት ከባድ እንደ ነበረ የሚያሳይ ነው፡፡
በቤተ ክርስቲያንም ብዙ ሰዎች የመስቀልን
ከቁሳዊ ገጽታ በላይ ባለፈ ማየት የሚሳነን
ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ ግን መስቀልን መሸከም
ስንል ምን ማለታችን ነው› የክርስትናችን
ምልክት ነው አይደለም;፡፡
በደረት ኪሳችን ላይ የምናስቀምጠው፣
በቤተክርስትያናችን ሕንጻ ላይ የምንተክለው፣
በአንገት ብላችን ላይ የምናሳትመው፣ ሌላ
ሌላም፡፡ አዎን ይህ
እውነት ነው
ግን በልባችን የሚሳውም እርሱ ሊሆን ይገባዋል፡፡
መስቀሉ ለእኛ ምን ያሳየናል;
ጌታ
ኢየሱስ በሄደባቸው መንገዶች ሁሉ ለመሄድ
ራሳችንን
የሰጠንበት ሕይወት ተሞክሮ አይደለምን ;
ክርስትና
እኮ ኢየሱስ
የኖረበትን ሕይወት ለመኖር በመወሰን ራሳችንን
የምንሰጥበት
መርህ ነው፡፡ ይህ መርህ ማቴ 10፡24
ላይ
እንደተቀመጠው ባሪያው እንደ ጌታው ደቀመዝሙሩ
እንደ መምህሩ የሚሆኑበት የሕይወት መርህ
ነው፡፡ እኛ ኢየሱስስን ለመከተል ስንል
ሕይወታችንንና እኛነታችንን ለእርሱ የምንሰጥበት
የሕይወት መርህ ነው፡፡
ከዚህም
በላይ ጌታ ኢየሱስ ስለ እኛ መከራን የተቀበለበትን፣
የተዋረደበትን፣ የተንገላታበትን የሚያሳይን
ነው፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ተወረዶ እኔን
ያስከበረበትን፣ የእኔን ነፍስ ሊያረካት
ተጠማሁ ያለበትን፣ የእኔን እጅና እግር ለክብሩ
ለመማረክ እጅና እግሩን የተቸነከረበትን፣
እኔን ከአብ ጋር ሊያስታርቀኝ እርሱ በአባቱ
የተራሳበትንና አባቴ አባቴ ሰልምን ተውከኝ
ያለበትን ፣ የእኔን ቁስል ለመፈወስ እርሱ
ጀርባው በሮማውያን መጥፎ ጅራፍ አለንገጋ
የተተለተከበትን ፣ እኔን የእግዚአብሔር፣
የሰውና የራሴ ጠላት የሆንኩትን ሰው የእርቅና
የሰላም ሰው ለማድረግ የሚያደርጉትን አየውቅምና
ይቅር በላቸው ብሎ የተማጠነበትንና ያማለደበትን
ያንን የክርስቶስን መስቀል በሥጋዬና በነፍሴ
ተሸክሜአለሁ፡፡ እንግዲህ ይህንን በሕይወታችን
በምንተግብርበት ጊዜ የማነታትችን መለያለሁሉም
ያወቃል ማለት ነው፡፡
5.
የጌታ
የኢየሱስ ቀንበር መሸከም(
ማቴ
11፡29-31)
እኛ
የኢየሱስ መሆናችን ከሚታወቅበት መንፈሳዊ
ገጽታዎቻችን አንዱ ቀንበር
መሸከም ነው፡፡ በጣም
የሚገርመው ነገር ብዙ ሰው በክርስትና ሕይወቱ
መስቀል ስለመሸከም ይሰማል ቀንበር መሸከም
የሚባል ነገር እንዳለ አያውቅም፡፡ ብዙዎቻችን
የመስቀል ምልክት አለን ግን የቀንበር ምልክት
የለንምምክንያቱም ቀንበርን ስለመሸከም ብዙም
ትኩረት ስላለሰጠን ነው፡፡ መስቀልምን መሸከም
ያልቻለ ነው ቀንበርንም መሸከም ሊከብድበት
ይችላልና፡፡ ምክንያቱም መስቀል ወደ ክርስትና
ሕየወታችን ከገባንበት ቀን ጀምሮ የምለማደው
ስለሆነ ቀንበር ወደምንሸከምበት ሁኔታ ስንደርስ
ቀላል ይሆናል፡፡ መስቀልን መሸከም ያልተለማመደ
ሰው ቀንቡም የዚያሀውኑ ያህል ሊከብደው
ይችላል፡፡ ግን መሸከም ማን ማለት ነው፡፡
አይሁዶች ቀንበር የሚለውን ቃል የሚወስዱት
በአንድ ነገር ውስጥ ለመግባት ራስን ከመስጠት
ጋር በማያያዝ ነው(
ሳሚሺን)
፡፡
በሐዋሪት ዘመን መሪዎቻቸው ሕዝቡ ሊሸከሙ
የማይወዱትን ቀንበር (
ግዴታ)
በትከሻው
ላይ ይጭኑባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡
ምክንያቱም የሮማውያን አገዛዝና ሥልጣን
በሕዝቡ የተወደደ ሳይሆን በግድ ተብሎ የተጫነ
ቀንበርና እሥራት ነበር፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ
ለሕዝቡ ቀንበሩን እሰብራሁ እያለ ተስፋ
ይሰጣቸው የነበረው፡፡ መጥፎ ቀንበር፣ የባርነት
ቀንበር፣ የጭቆና ቀንበር ተጭኖባቸው
ስለነበር ሕዘቡ ወደ እግዚአብሄር በጮኹ ጊዜ
እገዚአብሔር ቀንበሩን ከትከሻቸው እንሚሰብር
ተናረ፣ ያም ቀንበር ደግሞ በጌታ በኢየሱስ
ስም ተሰብሮልናል፡፡
ኢሱስ
በማጣ ጊዜ ወደ እርሱ የሚመጡትን ቀንበር
እንዲሸከሙ ጥሪ አድርጎላቸዋል፡፡ ይህንን
ያደረገው ግን በሕይወታቸው ያለውን ከባዱን
ቀንበር ሁሉ ከሰበረ በኋላ ነው፡፡ በነፍሳቸውም
ያለውን ቀንበርና ሸክም ሁሉ ካወረደላቸው
በኋላ ነው፡፡ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ
ሁሉ ወደ እኔ ኑ ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ ብሎ
ነው፡፡ የእናንተን መጥፎ ሸክም እኔ አነሳለሁ
እናንተ ግን የኔን ቀላልና እረፍት የሚሰጠውን
ሸክም የሆነውን ቀንበር በላያችሁ ተሸከሙ
ይለናል፡፡ ልክ እንደመስቀሉም ሁሉ ቀንርም
ከእንጨት የሚሠራ መሣሪያ ነው፡፡
ቀንበር
ለኃላፊነት የምንሰጥበት መንገድ ነው፡፡
ቀንበር የሚሠራውም በሰለጠኑ አናጢዎች
እንስሳውን በማይጎዳ መልክ ተለክቶ የሚሠራ
ነው፡፡ ከዚያ ቀንበር ሥር የሚሆነው በሬ
ሞፈሩን ለመጎተት፣ በገበሬውም ትልም ለመመራት፣
ትልሙንም የመቅደድ ኃላፊነቱን ለመቀበል
አቅመ ቢስ ከሆነው ገበሬ እጅ ሥር ራሱን አስገዝቶ
በቀንበሩ ላይ ባለው ማነቆ ይተሰራል፡፡
እንደዚሁም ሁሉ የጌታን ሥራ ለመስራት
የአገልግሎትንም ኃላፊነት ለመቀበል በፈቃዳችን
ራሳችንና ሁለንተናችንን ለጌታ ለኢየሱስ
መስጠታችንን የሚያመላት ነው፡፡ ቀንበሬን
በላያችሁ ተሸከሙ የሚለው ቃል፡፡
በኢየሱስ
ጊዜ ለቀንበር የሚሰጠው ሌላው ምሥል ደግሞ
መማር
ነው፡፡ ተማሪው ሁሉ ጊዜ በራሱ ውዴታ ከመምህሩ
ለመማር ይመጣል እንጂ ተማሪ አስገድዶ የሚያስተምር
አስተማሪ በፍጹም የለም፣ አይኖርምም፡፡
ስለዚህ አይዶች ቀንበርን ምን ይሉታል የህግ
ቀንበር፣ ቶራህ ቀንበር፣የትዕዛዝ (
ኮማድሜንት)ቀንበር፣
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የእግዚአብሔር ቀንበር
ብለው ይጠሩታል፡፡ ጌታ ኢየሱሰስም ያኑትን
የሚጠይቃቸው አንዱ ጥያቄ ይህ ነው፡፡ ቀንበሬን
በላያችሁ ተሸከሙ(
ከእኔ
ተማሩ ) ይላቸዋል፡፡
የእርሱን ቀንበር መሸከምና ከእርሱ መማር
ማለት ምን
ማለት ነው፡፡ ለእርሱ አመራር፣ ትምህርት
ሥልጣን ራሳችንን መስጠት ማለት ነው፡፡
ይህ መታዘዝን የሚያሳይ ቀንበር ነው፡፡ ይህ
ቀንበር በክርስትና ሕይወታችን ስንኖር
ይንጨነቅበትና የምንጠበብበት ሳይን እፎይ
የምንልበት ነው፡፡ ለጌታ መታዘዝና
ራሳችንን ለእርሱ መስጠት እረፍትን የሚሰጥ
ነው፡፡ ሸክማችሁን ወደ እኔ አምጡ እኔ
አሳርፋችኀዋለሁ ብሎ እንዳሳረፈ
ሁሉ ቀንበሩንም ስንሸከም
ነፍሳችንን ያሳርፋታል
ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ለነፍሳችሁ እረፍትን
ታገኛላችሁ
የሚለን::
ኢየሱስን
ቀንበር የመሸከም ሌላው ምስጥር ደግሞ ትብብር
ነው፡፡ ከእንዱ ከሌላው ጋር በሕብረት
መዋሄድን የሚያመለክት ነው፡፡ ቀንበር በአንድ
በሬ ትከሻ ብቻ አይጫንም፡፡ ሁለት በሬዎች
ናቸው የሚገትቱት፡፡ የበሬዎቹ ትክለ ቁና፣
እድመሜ ፣ ጉልበት፣ ልምድ፣ ባሕሪያ ወዘተ
የተለያየ ሊሆን ይችላ፡፡ እነዚህ የተለያዩ
በሬዎችን በአንድ ሥራ ላይ የሚያሰማረው ቀንበሩ
ነው፡፡ሁለቱ በቀንበር ሥራ ሆነው አንዳቸው
ለሌላው ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሲሰጡ በእነርሱ
ላይ ጌታ የሆነው የገነሬው ሥራ ወይም እርሻው
በተሳካ ሁኔታ ይታረሳል ማለት ነው፡፡ ነገር
ግን ከሁለቱ በሬዎች አንዱ እምቢ ያለ እንደሆነ
እርሻው ሳይታረስ ሊከርም ይችላል ከቀንበር
ምስጥር ይንማረው አንዱ ይህን ነው፡፡ ጌታ
ቀንበሬን በላይችሁ ተሸከሙ ሲለን በእግዚአሔር
እርሻ ላይ ለመሰማራት አንዳችን ለሌላችን
ራሳችን ዝቅ ማድረግን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ
ደግሞ በጣም ከባድ ሆኖብናል፡፡ ይሁን እንጂ
እግዚአብሔር አሁንም ይህንን እንድናደርግ
ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ወንድሞችና እህቶች ሆይ
ይህ ታላቅ ምስጥር ነው፡፡ ትልቅ በረከት
ያለበት ነው፡፡ ለወንጌላውያን አብያተክርስትያና
አገልጋዮች ዘንድ ትልቅ ፈተና የሆነብን ይህ
ነው፡፡ ሸክማችንን በኢየሱስ አጠገብ ላመስቀመጥና
ለማረፍ በጣ እንመኛለን ግን የእርሱን ቀንበር
በሸከም የሚገኘው የነፍስ እረፍት ለማወቅ
አልቻልንም፡፡ ሐዋሪው ጳውሎስ ማን ባልንጀራው
ከእርሱ እንዲሻል ይቁጠር የሚለው ለዚህ ነው፡፡
ኢየሱስም እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ ደቀመዛሙርቴ
እንደሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ ብሏል፡፡
ሰዎች እኛ የኢሱስ መሆናችንን የሚያቁብ መንገድ
ወይም መለያ ምልክታችን የእርስ በርስ ፍቅር
ነው
6.
የቅዱሳንን
ሸክም መሸከም (
ገላትያ
6፡2፣5)
የቅዱሳንን
ሸክም መሸከም ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ይህ
እንዲገባን ዕብራውያን 13፡1-3
፣
እና ሮሜ 12፡9-16
ያለውን
ማበቡ የተሸለ ነው፡፡ የታሠሩ ሰዎች ሲኖሩ
እናንተም ከእነርሱ ጋር በእሥር ቤት እንዳላችሁ
አድርጋችሁ ራሳችሁን ተመልከቱ፡፡ ከጌታ
ከኢየሱስ ትምህርትና ከመጀመሪያዋ የኢየሩሳሌም
ቤከርስቲያን ተግባራዊ አኗኗር የምንማረው
አስደናቂ ነገር ቢኖር አንዱ የከመንፈስ ቅዱስ
ሌላውን ሸክም መሸከም ነው፡፡ የሐዋሪያትን
ስራ 4ን
በምመለከትበት ወቅት በበዓለ ሃምሳ ቀን
የተከሰተውን የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ተከትሎ
በሕይወታቸወ ከታየው አስደናቂ ነገር አንዱ
የእርስ በርስ ሸክም መሸካካም ነበር፡፡ አንድም
ደሀ በመካላቸው አንዳይኖር ያላቸውን ሁሉ
እያመጡ በሐዋሪያት እግር ሥር ያስቀምጡ
ነበር፡፡ ለሁሉም እንሚያስፈልጋቸው ያካፍሉ
ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የአይሁድ እምነት ወይም
የሀይኖት መሪዎች የነበሩ ፈሪሳውያ ደሀዎችን
ቤት ፣ የመበለቶችን ቤቶስ ሲበዘብዙ ኣና
ሲበሉአቸው ደቀመዛሙርቱና የኢየሩሳኬም
ቤተክርስቲያን አማኞች ደግሞ ያቻውን ንብረትን
ጥሪት በመሸጥና ወደ ሐዋሪያት በማምጣት
ደሀዎችንኛ የተቸገሩትን ይደግፉአቸው ነበር፡፡
ይንን በማደረጋቸው በፈሪሳውያንኛ በመንደፍስ
ቅዱስ አማካይነት በሚደረገው እወውነተኛ
ርስትና መካካል የሚኖረውን ልዩነት በግልጽ
ለማሳየት ችለዋል፡፡ በመከራና በችግር ውስጥ
ላለችው ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ገንዘብ
አዋጥተው ይሰጡ ነበር፡፡ ይህን የሚያደርጉት
ደግሞ ስለ ተረፋቸው ሳይሆን ከድህነታቸው
ጥልቀት ሁሉ የኢየሱሰስን ቸር ላጋስነት
በተግባራቸው ይገልጡት ነበር፡፡ ይህ ዓይነት
ሕይወተወ ለሁላችንም የሚያስፈልግ ነው፡፡፡
ከዕብራውያ
ትምህርት እንደምንመለከተው በክርስቶስ
የሆነው ወንድማችን ቢታሠር ያ እሥራት የእኛም
ነው ማለት ይኖርባቸዋል፡ የታመመውን ሲያይ
ያንን ሕመም አብራችሁ ልትታመሙ ይገባቸዋል፡፡
ይህ የክርስቶስ የመሆናችን መለያ ነው፡፡
የጥንታቤተ ክርስቲያን የምትታወቀው በዚህ
ነው፡፡
በወንገጌው
ያን አብያተ ክርስቲናት ዘንድ ይህ እነደቀድሞዎቹ
ሕዝቦች መሆን እጅግ የተሳነን ጊዜ ቢሆን አሁን
ነው፡፡ ዛሬ አንገታቸው እየተቀላባቸው ወገኖች
ጉዳይ ፣ የቤተሰባቸው ልቅሶና ሰቆቃ እኛን
ለየገነበግብ ይገባናል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ
በየሰምንቱና በየቀኑ የሚቃጠሉ ቤተ ክርስቲያናት
የእኛ ናቸው ፣ እኔ የማመልክባት ቤተ ክርስቲያን
ነው የተቃጠለው ማለት ወደምንችልበት የአቅም
ደረጃ ከፍ ማለት ይኖርብናል፡፡ ስግብግብነት
በጣም አደገኛ እሥራት ነው፡፡ በመካከላችሁ
የተቸገሩትን ገልጋዮቻችሁን፣ እህቶቸችሁን
፣ የቤተከርስቲያን አባቶች ፣ የተራቡ በእሥራት
ያሉትን በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ
ሰዎች አንገታቸው በክርስትና ምክንያት እየተቀላ
ነው፡፡ እነዚያን ከብባችን ልናስብ ይገባናል፡፡
ብዙ ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ ነው፡፡ የእኔ
ቤተ ክርስትያን እደተቃተለ በማሰብ በእግብሔር
ፊት አብረን ልናለቅስ ይገባናለ ይህ ሁሉ
የክርስቶስ የመሆናችን ምልክት ስለሆን በዚህ
ልንተጋ ይገባናል፡፡
የክርስቶስ
የመሆናችን ምልክት.
የማነታችንና
የምነታችን መለያ ፡፡
No comments:
Post a Comment