እግዚአብሔር የተቀበለውን ልትፈርድበት አንተ ማን ነህ?
ባለፈው ሳምንት የግብረሰዶማውያንና የሌስቢያንን ጋብቻ አስመልክቶ ሰዎች እግዚአብሔር በተቀበለው ላይ ልንፈርድ እኛ ማን ነን በማለት እንደሚከራከሩና ወደፊትም ክርክራቸውን አጠናክረው እንደሚገፉበት ተነጋግረን ነበር ያቆምነው፡፡ መነሻውን ከአሜሪካ ያደረገው የግብረሰዶማዊትና የውርጃ ሕጋዊነት ቀስ በቀስ ወደ አዳጊ አገሮችም እየተዛመተ በመሆኑ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚገጥማትን ተግዳሮት ለመመከትምን ልታደርግ ይገባታል በሚል አሳባችንን በእንልጥልጥል እንደተውነው ይታወሳል፡፡ ወደ ተነሳንበት አሳብ እንመለስና ውይይታችንን እንቀጥል፡፡ እግዚአብሔር ግብረሰዶማውያንን ከተቀበለ እኛ ለምን እንፈርድባቸዋለን የሚለው አባባል አንድ ነገር አስታወሰኝ፡፡ አንድ ክርስቲያን በሠርጉ ላይ ሰዎች መንፈሳዊ መዝሙር ሲዘምሩ አብሮአቸው ሲዘምር ቆየና ከዘመዶቹ መካከል የክርስቲና ተቃዋሚ የሆኑት ስለሚበዙ መዝሙሩ ጋብ ባለበት ሰዓት ብድግ ይሉና ሠርግ ቤቱን በዘፈን ያናውጡታል፡፡ ያን ጊዜ ክርስቲያን የሆነው ሙሽራም ከእነርሱ ጋር ጭፈራውን ያነስካዋል፡፡ ያነ እነዚያ ዘፋኞች ኃይላቸውን ጨምረው በአንዴ ድንኳኑንና አካባቢውን በመቆጣጠር ሳያቋርጡ በመዝፈን የሚዘምሩ ክርስትያን ወገኖችን ጸጥ አሰኙአቸው፡፡ በሁኔታው የተደናገረ አንድ ወንድም በሠርጉ ማግሥት ሙሽራውን አንተ ክርስቲያን ስትሆን በሠርግህ ላይ እንዴት ዘፈን እየዘፈንክ ዓለማዊ ጭፈራ ትጨፍራለህ ብሎ ጠየቀው፡፡ ሙሽራውም ሲመልስ እግዚአብሔር ይክበርበት እንጂ አይደለም ዘፈን ሌላም በተገኘና ባደረግኩት ፡፡ እንዲያው አንተ እንዴት እግዚአብሔር እንደከበረና ክብርንም እንደገለጠ አላየህም እንዲዬ አለው፡፡
እግዚአብሔር ግብረሰዶማውያንን ከተቀበለ እኛ ለምን እንፈርድባቸዋለን የሚለው ጥያቄ ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ በጣም መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡ እግዚአብሔር የተቀበለውን ማን ሊፈርድበት ይችላል? ቃሉስ የሚለው ይህ አይደል? እግዚአብሔር ያጸደቃቸውን ማን ይከሳቸዋል? ይህንን ጥያቄ ይዤ ስለ ግብረሰዶማዊነት የቅዱሳት መጻሕፍትና የሥልታዊ ነገረ መለኮት ጥናት ምን ይላሉ የሚለውን ማሰብ ጀመርኩ፡፡ የክርስቲያን ፈላስፋዎች ከሆኑት ዊሊያም ኤል ግሬይግ እና ሌሎች የሚሉት አሳብ ግን መሠረታዊ ነው፡፡ እንደ ክሬይግ አባባል እግዚአብሔር የተቀበለውን ልንፈርድበት እኛ ማን ነን የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ሌላ ወሳኝ ጥያቄ መመለስ ይኖርብናል፡፡ ልክ የሆነና የተሳሳተ (right and wrong) የምንላቸው ነገሮች ስለ መኖር አለመኖራቸው አስቀድመን እንጠይቅና መልስ ልናገኝላቸው ይገባል፡፡ ይህ ልክ ነው ፣ ያ ደግሞ የተሳሳተ ነው ብለን ከመወሰናችን በፊት ልክ( right) የሆነውና ስህተት (wrong) የሆነው የትኛው እንደሆነ ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ አንድን ነገር ልክ ነው ወይም ስህተት ነው የምንለው ምንን መሠረት በማድረግ ነው? ልክ በሆነውና በተሳሳተው መካካል ያለው ልዩነትስ ምንድነው? በተለምዶም ቢሆን እንደሚነገረው የግብረገባዊ እሴት ( moral values) መሠረቱ እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር በባሕሪዩ ቅዱስ ነው፣ መልካም ነው፡፡ እርሱ ጻድቅ፣ አፍቃሪ ፣ታጋሽ፣መኃሪና ቸር ሲሆን መልካም ነገር ሁሉ ከእርሱ የሚገኝ በመሆኑ የእርሱ ባሕሪያት ነጸብራቅ ነው፡፡ ፍጹም መልካም የሆነው የእግዚአብሔር ባሕሪይ እኛም መልካምን እንድናደርግ ያዘናል፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ቃሉ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም አሳብህ ውደድ፣ ባልንጀራህንም እንደራስህ ውደድ፣ አትግደል ፣ አትስረቅ አታመንዝር የሚሉና ሌሎች ትዕዛዞችን ይሰጠናል፡፡ እነዚህ ትዕዛዞች እንዲያው ዝም ብለው ግምድል አሳቦች ሳይሆኑ ፍጹም ከእግዚአብሔር ከራሱ ባሕሪይ የሚመነጩ ትእዛዞች በመሆናቸው አንድ ነገር ልክነው ወይም የተሳሳተ ነው የምንለው እግዚአብሔር በሰጠው ትዕዛዛት ላይ በመመሥረት መሆን አለበት፡፡ ክርስቲያኖች ልክ የሆነውንና የተሳሳተውን ነገር የምንረዳው በዚህ መንገድ ነው፡፡ ዓለማትን ሁሉ የፈጠረና ራሱን ለእኛ የገለጠ ታላቅ አምላክ አለ፡፡ ይህ አምላክ እኛ አንዳንድ ነገሮችን እንድናደርጋቸውና ሌሎችን ደግሞ እንዳናደርጋቸው አዝዞናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የሰጠንን ትዕዛዝ ሁሉ እንድናከብረው ግረገባዊ ግዴታ moral obligation አለብን፡፡ ትዕዛዙን የተላለፍን እንደሆነ ደግሞ ጥፋተኞች ስለምንሆን በፊቱ ይቅርታ መጠየቅና ምህረት እንድናገኝ ያስፈልጋል፡፡
እኛ ጥፋተኞች የምንሆነው የጥፋተኝነት ስሜት ሲሰማን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ህግ ተላልፈን ስንገኝ ነው፡፡ ሕጉን ከጣስን በኋላ የጥፋተኝነት ስሜት ባይሰማንም እንኳ ጥፋተኞች ነን፡፡ ምክንያቱም ጥፋተኝነት ወይም ጥፋተኛ አለመሆን የሚወሰነው እግዚአብሔር በሰጠን ሕግ መሠረት እንጂ በሚሰማን ስሜት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ዊልያም ኤል ክሬግ ይህንን አሳብ በምሳሌ ሲገልጸው እንዲህ አለ፡፡ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጊዜ ድል የቀናቸው ናዚዎች ከአሳባቸው ጋር የማይሰማሙትን አስተሳሰብ የማሰለወጥ ካልሆነ እንደዚያ ያለውን ጨርሶ በማጥፋት ሁሉም ሰው በአይሁዶች ላይ የተረደገው ጭፍጨፋ ( Holocaust) መልካም እንደሆነ እንዲያስብ የሚደርጉት ተግባር ተሳካላቸው፡፡ ይሁን እንጂ ድርጊቱ አሁንም ቢሆን ስህተት ነው ምክንያቱም ሰው እንዴትም ቢያስብ እግዚአብሔር ግን ስህተት ብሎታልና”፡፡ ግብረገባዊነት የሚደላደለው በእግዚአብሔር ስለሆነ አንድ ልክ የሆነ ነገር ልክ መሆኑና ስህተትም ስህተት መሆኑ በሰዎች አስተሳሰብ ምክንያት ሊቀየር አይችልም፡፡
ኪሬይግ በጉዳዩ ላይ ይህንን ዓይነት አጽንኦት የሚሰጥበት ምክንያት በማህበረሰባችን መካከል አብዛኛዎች ሰዎች ትክክል( right) ወይም ስህተት ( wrong ) ስለሆነው ነገር የሚያስቡትና የሚበይኑት ከእውነት አንጻር ሳይሆን ከልምዳቸው ወይም ከሚሰማቸው ስሜት አንጸር ስለሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ በዘፈን እግዚአብሔር እንደሚከብርና ክብሩንም እንደሚገልጥ ሙሽራው የተረዳው እንዴት ነው? በአብዛኛው አንድ ነገር ሞቅ ደመቅ ሲል የእግዚአብሔር ክብር ወረደ እንላለን፡፡ ይህ የራሳችን ልምምድ አንጂ በሞቀና በደመቀ ነገር ሁሉ ውስጥ የእዚአብሔር ክብር ስለመገለጡ እርግጠኖች ሆነን አይደለም፡፡ ሙሽራውም እግዚአብሔር ደስ መሰኘቱንና ክብሩን መግለጡ የሚታወቀው መዝሙሩ፣ ጭብጨባው እና እልልታው ሽብሽባውም ምድሩን ሲያናውጥ እንደሆነ የለመደው ነገር ነበረው፡፡ አሁን ግን ሲያየው ከመዝሙሩ ይልቅ በጣም ያየለው ዘፈኑ ሲሆንበት እዚያ ውስጥ ነው እንግዲህ እግዚአብሔር የሚከብርበት ብሎ ደመደመ ማለት ነው፡፡ ግብረሰዶማውያንንስ እግዚአብሔር እንደተቀበላቸው በምን እርግጠኞች እንሆናለን? ፍርድ ቤቱ ስለፈቀደና እነርሱም በጣም ሞቅ ብሎአቸውና ነካ አድርጎአቸው መንገድ ላይ ወጥተው ስለጨፈሩ እንዲሁም በጣም ሀብታሞች ስለሆኑ እግዚአብሔር ተቀብሎአቸዋል ማለት ነው? ይህም ቢሆን የሰዎች ስሜት ወይም ልምምድ የወለደው መሳሳት እንጂ እውነቱ ይህ ሆኖ አይደለም፡፡
ስለዚህ የአንድ ነገር ትክክለኛነት ወይም ትክክለኛ አለመሆንን ለመበየን መለኪያ ያስፈልጋል ፡፡ ያለዚያ ብያኔው አንጻራዊ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ጎመን ለሁሉም ሰው ሊጣፍጥ አይችልም፡፡ ለአንዳንድ ሰው በጣም ይጣፍጠዋል ለሌላው ደግሞ አይጠፍጠውም፡፡ አንዲት ሴት የሠራችው ጎመን ለእኔ በጣም ሲጣፍጠኝ ጓደኛዬ ደግሞ ጭራሽ እንደሚያስጠላው ሁሉ ሰዎች የግብረገባዊ ሕጉን እንደዚሀው ያዩታል፡፡ አንድ ነገር ለአንዱ ልክ ሆኖ ያው አንዱ ነገር ደግሞ ለሌላው ሰው የተሳሳተ ከሆነ እውን የሆነ ልክ የሚባል ወይም እውን የሆነ ስህተት የሚባለ ነገር የለም ማለት ነው ምክንያንቱ ብያኔው አንጻራዊ ስለሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ ግብረሰዶምነት ምንም ችግር የለበትም፣ ውርጃም ኃጢአት አይደለም የሚሉ በጣም ብዙ ሲሆኑ የውርጃን ወይም የግብረሰዶምነት ትክክለኛነት የሚመዝነበት መለኪያ ( standard) ኖሮአቸው ሳይሆን ከሚሰማቸው ስሜት በመነሳት ብቻ ነው፡፡ ለሌሎቻችን ደግሞ ያ ነገር ፍጹም ኃጢአት ነው አልፎም ርኩሰትም ሰይጣናዊነትም ነው፡፡ በዚህ መካከል የሚዳኘን ኃይልና እርሱ የሚሰጠን መለኪያ ያስፈልጋል፣ ያውም የእግዚአብሔር መኖርና ዘመን ተሻጋሪ የሆነው የእርሱ ሕግ ናቸው፡፡
እንግዲህ ለሰው ልጆች ሕግን የሰጠው እግዚአብሔር ባይኖር ሁሉም ነገር አንጻራዊ ነው ማለት ነው፡፡ በተለያየ ባህልና ህብረተሰብ መካከል የአንድ ነገር ትክክለኛነቱ ወይም ስህተት የመሆኑ ጉዳይ አንጻራዊ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሌለ ፍጹም የሆነ ሕግ የለም ማለትነው፣ ስህተት ወይም ትክክል የምንለው አንድም ነገር አይኖርም ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ የሚያደርገው ነገር እንደየራሱ አንጸራዊ ነው ማለት ነው፡፡ ያለ እግዚአብሔር ሕግ የአንድ ነገር ፈይዳው ልክ ነው ወይም የተሳሳተ ነው የሚል የለም፡፡ ልክ ወይም ስህተት የምንላቸው ነገሮች ራሳቸው የመጡት ከየት ነው? ልክን ልክ ወይ ስህተትን ስህተት የሚደርገው እግዚአብሔር የሰጠን መለኪያ (standard) ነው፡፡ ያው የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ማመን አለማመን፣ ለእርሱ መገዛት አለመገዛት ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኃጢአት ያለው ምን ጊዜም ኃጢአት ነው፡፡ ጽድቅ ነው ያለውም እንደዛው ጽድቅ ነው፡፡
ታዲያ ከዚህ አንጻር ይህ መለኪያ ( ስታንዳርድ) ስለ ግብረሰዶማዊነት ምን ይላል? ስለውርጃስ? እንመለስበታለን፡፡