እግዚአብሔር በተቀበለው ላይ ልትፈርድ አንተ ማን ነህ?
ሰሞኑን በአሜሪካን አገር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በመከታታል ላይ ያለ ወጣት ተማሪ አስቸጋሪ በሆነ አንድ ጉዳይ ጓደኞቹን ሲሞግታቸው ሰማሁ፡፡ ጉዳዩ ስለ ተመሳሳይ ጾታ መሳሳብ ሲሆን ወጣቱ ደግሞ እግዚአብሔር ግብረሰዶማውያንን ከተቀበላቸው እኛ ለምን እንኮንናቸዋለን እያለ ነበር ጓደኞቹን የሚሞግታቸው፡፡ ይህ ልጅ ብቻ ሳይሆን የአሜሪካን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ከፈቀደበት ወርሃ ነሐሴ 2015 ወዲህ የጉዳዩ አነጋጋሪነትና አወዛጋቢነት በሁሉም ዘንድ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ሕጉ በፍርድ ቤት እንደ ጸደቀ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ወዲያውኑ ለመላው አሜሪካን ሕዝብ ባሰሙት ንግግራቸው “የዛሬው ቀን ወደ እኩልነት ለምናደርገው ጉዞ ወሳኝ ነው፡፡ ግብረሰዶማውያንና ሌስቢያውያን እንደ ማንኛውም ሰው የመጋባት መብት ያገኙበት እለት ነው፡፡ ፍቅር ያሸንፋል” በማለት በተለይም የግብረሰዶማውያንን አንጀት አርሰዋል፣ የብዙዎቻችንንም ቆሽት ደግሞ አሳርረዋል ፡፡ የፍርድ ቤቱን ውሳኔና የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተከትለው ግብረሰዶማውያን የደስታ ድምጸቸውን ማሰማት ጀመሩ፣ወዲያውኑ ቀስተ ደመና መሰል ባንድራ በአንዳንድ ቤቶች ላይ መስቀል ተጀመረ( እዚህ ቤት የምንኖረው ግብረሰዶማውን እንደሆንን ይታወቅልን እንደማለት)፡፡ በመንገድ ሲሄዱም ይህ ባንድራ ያለበትን ወይም መሰል ልብሶችን እና፣ ወይን ጠጅ ቀለም ( ፔርፕል) የበዛበትን አልባሳትን በማድረግ የራሳቸውን ልዩ መለያ ለሕዝብ ሁሉ ማሳየት ጀመሩ፡፡ ለመጋባት የተጫጩ ጌዬዎች(ግብረሰዶማውያን) በአደባባይ መሳሳሙን ተያያዙት፡፡ ተደብቀው ሲያደርጉት የነበረውን የአገሪቱ ሕጉ ከፈቀደላቸው ዕለት ጀምሮ ይፋና አዋጅ አደረጉት፡፡ እንዲያውም “የእኛ ይሻላል ከሌላ” የሚሉ መሰሉ፡፡
በአንጻሩ ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እጅግ ያስደነገጣቸውና ያሰቆጣቸው ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ናቸው፡፡ አንዳንዶች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፣ በውሳኔው ላይ ምንም ለውጥ ማምጣት ባይችሉም እንኳ፡፡ የቢሊግሪሃም ወንጌል አገልግሎት ማህበር ፕሬዝዳንት ታዋቂው አሜሪካዊ ወንጌላዊ ፍራክሊን ግሪሃም ፣ ዶር ጆን ማካርተር ፣ ዶር ጆኤል አር ቢኪ እና ሌሎችም በርካታ ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎችም ግብረሰዶማዊው ጋብቻ ኃጢአት መሆኑንና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለምድሪቱ የእግዚአብሔርን ቅጣት የሚያስቸኩል መሆኑን በጉባኤያቸውም አስተምረዋል በአገሪቱ መገናኛ ብዙሐንና በማህበራዊ ገጾችም አውጀዋል፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን በግብረሰዶማዊው ጋብቻ ላይ ለዘብተኛ አቋም የያዙ ብቻ ሳይሆን ሌሎች በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያምናሉ ከምንላቸው አብያክርስቲያናትም ይህን ጋብቻ የሚፈቅዱ መበራከታቸው ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ለወንጌላውያን አማኞች የባሰ አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ ይህ እንደማንኛውም ጋብቻ ስለሆነ ተጋቢዎቹን የምትኮንኑት እናንተ እነማናችሁ፣ እኛስ ምን መብት አለን፣ መፍረድ የሚችለው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ፍቅር ነው እያሉ የሚሰብኩ እየተበራከቱ ናቸው፡፡ ወጣቱ ተማሪም ጓደኞቹን የተገዳደራቸው ይህንን ስብከት ስለማ እንደሆነ መጠራጠር አያስፈልግም፡፡ የግብረሰዶማውያንን ጋብቻ አልቀበልም፣ ለሠርጋቸውም ኬክ አልጋግርም፣አዳራሽም አላከራይም ያሉቱ ለእሥር መጋለጣቸው ታይቷል፡፡ የግብረሰዶማውያንን ጋብቻ በቤተክርስቲያኔ አላስፈጸምም፣ በጋብቻቸው ምስክር ወረቀትም ላይ ፈርሜ አልሰጣቸውም የሚሉ የቤተክርስቲያናት መጋቢዎች የኬንታኪው የሩዋን ክፍለ ከተማ ጸሐፊ ኪም ዴቪስ እጣ ሊደርስባቸው እንደሚችል ከወዲሁ ሁኔታው ያመላክት ነበር፡፡ የወጣቱን አቀራረብ ካየሁና ከሰማሁ በኋላ ወንድም ዘላለም መንግሥቱ ሊገጥመን ያለውን ፈታኝ ሁኔታ ሲገልጸው “ድጣማ ዳገት” ማለቱ ( ስንቶቻችን በልባችን እንዳኖርነው ባላውቅም) የበለጠ ገባኝ፡፡
ያ ወጣት ተማሪ እንዳደረገው የዛሬዋ እውነተኛ ቤተክርስቲያን ከምትጋፈጣቸው ከፍተኛ ጥያቄዎች አንዱ ግብረሰዶማውያንን እናጋባቸው ወይስ አናጋባቸው የሚለው ሲሆን ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውም መልስ ከወዲሁ ብዙ እያጋገረ ነው ፡፡ በግልጽ እንደምናየው የግብሰዶማዊነትን አኗኗር ዘይቤ ህጋዊ ነው ብሎ የማይቀበል ክርስቲያን እንደአጥፊ፣ ግልፍተኛ ወይም እንደ ጠላት ሊቆጠር ነው፡፡ ለዘብተኛ በሆኑ ቤተ እምነቶች ብቻ ሳይሆን ቫንጄሊካልና ፔንቴኮስታል በሆኑትም ዳግመኛ የተወለዱ ከሚባሉት መካከል በተመሳሳይ ጾታ የሚሳሳቡ እንዲያውም መጋባት የሚፈልጉ መኖራቸው የቤተ ክርስቲያንን ጭንቀት በጣም ያገዝፈዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በሚያምንና በሚያስተምር ቤተ ክርስቲያን ግብረሰዶምነት ፈቃድ አግኝቶ ማየት ለብዙዎች የልብ ስብራት ነው፡፡ ዶር ጆኤል አር ቢኪ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በሰሙበት ሳምንት ለጉባኤያቸው ሲያስተምሩ “የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ የሰማሁባትን ቀን እንደ ቀብር ቀን እቆጥራታለሁ፣ በህይወቴ አሳዛኝ ከምላቸው ቀናት አንዷ ናትና” ብለዋል፡፡ ዶር ቢኪ ለጉባኤታቸው ባዘነና በተሰበረ ልብ ሲናገሩ፡ “አሜሪካ ያደረገችው ነገር ምንም ጊዜ ሳይፈጅ በአዳጊ አገሮች ይተገበራል፣ የብልግና ፍልም፣ የአደንዛዥ እንክብልና ሌሎችን ለዓለም ሕዝብ አስተዋውቀናል፣ አሁን ደግሞ የግብረሰዶማውያንን ጋብቻ ፈቅደናል ስለዚህ ሌሎች የዓለም ሕዝቦች እኛን እየተከተሉ ያንን ሊያደርጉት ነው፡፡ ለልጆቻችን የምናስወርሰው መልካም ቁም ነገር እያጣን ነን” ብለዋል፡፡
ይህ እውነተኛ አባባል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ባለች አንዲት ቤተ ክርስቲያን ዳግመኛ ተወልደዋል ተብለው ከሚታሰቡ፣ የደህንነት ትምህርት ተምረው የውሃ ጥምቀት ከወሰዱ በኋላ በአገልግሎት ከተሰለፉት መካከል ሁለት ወንዶች የወደፊት ሕይወታችንን አብረን በጋራ ለመምራት እንድንችል በጋብቻ ለመጣመር ተስማምተን በእግዚአብሔር ፊት እየጸለይን ቆይተናልና ቤተ ክርስቲያናችን ለጋብቻችን እውቅና ትስጥ የሚል ጥያቄ ይዘው ቢመጡ የቤተ ክርሰቲያን መጋቢ ምላሽ ምን ይሆናል? መቼም ብስል ከጥሬ ከሆነው የአሜሪካን ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ልምምድና ከቴሌብዥን ስብከታቸው የማይቀዳ ጉድ የለምና ጠያቂዎቹ ይህ ሰብዓዊ መብታችን ነው፣ ደግሞም እግዚአብሔር የእኛን ጋብቻ አልከለከለም ብለው ቢሞግቱ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምን ልታደርግ ትላለች? ሰዎችን ከቤተ ክርስቲያን ታባርር ወይስ ትቀበላቸው? አንዳንዶች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ ስለዚህ በፍቅር እንቀበላቸው የሚለውን ስብከት በመስበክ በመጽሐፍ ቅዱስ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተወግዞም እንኳ ቢሆን መጽሐፉ በተጻፈበት ዘመን የነበረውን ባሕል ታሳቢ በማድረግ ሰለሆነ አሁን እኛን ከመጋባት አይከለክለንም እያሉ ቢፋለሙን ምን እናደርጋቸዋለን? እግዚአብሔር የተቀበላቸውን ልትኮንኑ እናንተ ማን ናችሁ የሚሉ ከዉጭ ሳይሆን ከውስጥ ያውም ከአገልጋዮች መካከል መነሳት ጉዳዩ ለቤተ ክርስቲያን እጅግ በጣም አደገኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ወንድም ዘለለም “ድጣማ ዳገት” ያለውን ይህንን ችግር እንዴት ትወጣዋለች?
የአሜሪካን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ሕጋዊነት ካጸደቀ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ደግም የውርጃን ሕጋዊነት ይፋ አድርጓል፡፡ ዜናውን ጃኑዋሪ 26 2016 ላይ ያወጀው የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማሪኛው ፕሮገራም በይፋ ሲያሰማን የድጣማው ዳገት ጉዳይ እንደገና መታሰብ እንዳለበት ሁሉም ያሰላሰለ ይመስለኛል፡፡ አሜሪካንም እኮ የለስቢያንና የጌዬዎችን ጋብቻ ሕጋዊ ወደምታደርግበት አሳዛኝ ሁኔታ የደረሰችው ውርጃና መሰል ነገሮችን ስትፈቅድ ቤተ ክርስቲያናትም ከሥሯ እየተከተሉ ስቀበሉአት ቆይታ ነው፡፡ የኃጢአት ትንሽና ትልቅ ባይኖርም እንደ ሰው አበባል ከትንሹ ወደ ትልቁ ወይም ከዲጡ ወደ ማጡ እያለች እዚህ ደርሳለች፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ውርጃን በመፍቀድ የአሜረካንን የክህደትንና የሕገ እግዚአብሔር ጥሰት ተግባር በምድሪቱ ለመገንባት አጥልቃ እየቆረች መሆኗን እያሳየች ነው፡፡ ለግብረሰዶማዊው ጋብቻ እደርስበታለሁ አሁን ከውርጃው ልጀምር የምትል ትመስላለች፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያናት ድንጋጤ የፈጠረ ይመስለኛል፡፡ በአሁኑ ዘመን ፖለቲከኞችና አንዳንድ እያዋዙ የሚወስዱ አጥቢ የቤተ ክርስቲያን ፓስተሮች በል ልበልህ፣ እከከኝ ልከክልህ የሚባባሉበት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን እያደከማት ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ነቢያትና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት የሚሹ ሀብታም ነጋዴዎች አንዱ በአፍ ሌላው በእጅ ሲባባሉ እውነት ሰሚ እያጣች ነው፡፡ ያውም በቤተ ክርስቲያን ! ይህንን በዓይኑ ያየ ለእውነት የሚቀና ማንም መንፈሳዊ መሪ ማረሩና መድበኑ አይቀርም፡፡ ውርጃ እኮ የትውልድ ማጥፊያ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንም ቀንደኛ ተግዳሮች ነው፡፡ የውርጃና የግብረሰደማውያን ጉዳይ ያን ያህል ወሽመጥ የሚቆርጥ የሆነበት ምክንያት በፖለቲካው አካባቢ ካሉ አማኞች መካከል አንዳንዶች ለጉዳዩ(ለውርጃና ለግብረሰዶማዊነት) ዘብ ስለሚቆሙላቸው ጭምር ነው፡፡ የትኛውም ይሁን የቱ ታዲያ የኢትዩጵያ ቤተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ እሴታቸውንና ዘመን ተሻጋሪ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከመጠበቅ አንጻር ምን እየሠሩ ነው? ምንስ ማድረግ ይገባቸው ነበር የሚለውን ለማንሳት ነው፡፡ እንመለስበታለን፡፡

No comments:
Post a Comment