Sunday, August 12, 2018
ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥረን፣ በቁጣውም እንደ መብረቅ ሊመታን፡፡
( ለወላይታና ለሲዳማ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች)
ላለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በአገራችን የሚታየው የፖለቲካ ግለት የአንዳንዶቻችንን ልብ ደስ ሲያሰኘው የአንዳንዶቻችንን ደግሞ በሀዘንና በትካዜ መምታቱ አልቀረም፡፡ ብዙዎች የፖለቲካ ነጻነት ሲያገኙ ፣ ከእሥራትም ሲፈቱ ፣ የሞት ቅጣት ፍርድ ሲሻርላቸው አንዳንዶች ደግሞ መራር ሀዝን ወደ ቤታቸው መግባት ግድ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ እሥረኞቹ ከግዞት ቤት በሚለቀቁበት ወቅት ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በታላቅ ደስታ ሲቧርቁ በተቃራኒው ደግሞ ከቀለሱት ቀዬ ፣ ከኖሩበትም እልፍኝ ተፈንቅለው ሜዳ ላይ የተጣሉ መኖራቸው ልብን የሚሰብር ፣ አጥንትን የሚያደቅቅ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ሰላማውያን ሰዎችም መዘረፋቸውና አንዳንዶችም እንደ ከብት ተጋድመው መታረዳቸው ያላስለቀሰው መኖሩ ያጠራጠራል፡፡ በብዙ የአገራችን ክፍሎች ግዲያና ልቅሶ የመበራከቱ ምክንያት ምንድነው? ቢባል ሁላችንም የየራሳችንን መልስ እንሰጥበት ይሆናል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበት ቀጣና የአፍሪካ ቀንድ ሲሆን ይህ አካባቢ ግጭት ከሚያይልባቸው የዓለማችን ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ አገሮች በብዙ አሥርት ዓመታትና ከዚያም በላይ ጊዜያቶች የግፍ ግዲያ፣ የከባድ መሣሪያ ሩምታ ፣ የስደትና የከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ውድመት የሚስተዋልበት ቀጣና ሲሆን የቀጣናው ነዋሪዎችም ተረጋግተው የተቀመጡበት ፣ በሰላም የኖሩበት ዓመት አለ ለማለት ድፍረት አልተገኘም፡፡የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ከውጭ የሚመጣ ጠላት ሳይሆን ወንደም በወንድሙ ላይ እንዲነሳ በሚያደርግ የዘረኝነት ፖለቲካ መርዝ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝባችን አርፎ በሰላም መኖር እየፈለገ እንዳያርፍ ሆኗል፡፡
ባለፉት ወራት በወንድማማች
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment