መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ይቅርታ (
part two)
በመጋቢ ሳሙኤል ሾንጋ
በተለያየ
ዘመናት የነበሩ መንግስታት ከወንጀል ጋር
በተያያዘ በወህኒ ለታሰሩ እስረኞች ይቅርታ
አድርገው ይለቅቋቸዋል፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር
በሮማውያን ዘንድ የተለመደና በየዓመቱ
የሚከናወን ስለነበረ ኢየሱስ በምድር በነበረበት
በአገልግሎቱ መጨረሻ አካባቢ በሰዎች እጅ
አሳልፎ ተሰጥቶባለበት ወቅት ከእርሱ ወይም
በረባን ከተባለ ሌባ ከሁለት አንዳቸውን
ለመፍታት ሙግት የተነሳው ከዚህ ጋር በተያያዘ
ነበር ፡፡ በእርግጥ እንዲህ አይነቱ ይቅርታ
የሚሰጠው የሕዝብ በዓላት በሚከበሩበት ወቅት
ነው፡፡
በአገራችንም
የሕዝብ ታላላቅ በዓላት በሚከበርባቸው ወቅቶች
በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞች ከወህኒ ቤት ተለቀው
የወጡበት ሁኔዎች እንደነበሩ ትዝ ይለናል፡፡
መንግስት ቀለል ያለ ወንጀል የሰሩና በትምህርትና
በምክር ሊታረሙ የሚችሉ ናቸሙ ብሎ የሚያምንባቸውን
ወንጀለኞች ይቅርታ አድርጎ ሲፈታቸው ተመልሰው
ከሕብረተሰቡ ጋር ሰላማዊ ኑሮ እንደሚኖሩ
በማዘጋጀትና ይህንኑ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
እነዚህ ሰዎች ተመልሰው እንደገና እኩይ
ተግባራትን ቢፈጽሙ በቀጣዩ የሚጠብቃቸው
ቅጣት ከፍተኛ ይሆናል፡፡ በፊት የነበረው
ሪከርድ ተጠቅሶ የፍርድ ሂደቱን ሊያከብድባቸው
ይችላል፡፡
በጌታ
ኢየሱስ የምድር ዘመን በጣም የሚታወቁ የአይሁድ
ሕዝብ አካል የሆኑት የኩምራን ሕብረተሰብ
ናቸው፡፡ ኩምራን ግዙፍ ሃይማኖታዊ ሕብረተሰብ
ሲሆኑ የራሳው የሆነ የማህበረሰብ ሕግና ደንብ
ነበራቸው፡፡ ወጋቸው መሠረት የሚያደርገው
የሙሴን ሕግ ፍፁም በማክበር ላይ ሲሆን አንድ
ሰው ሆነ ብሎ ወንጀል ቢሰራ ከማህበረሰቡ
እስከመጨረሻው እንደሚገለል መመሪያቸው
ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ ሰነድ ውስጥ ደግሞ
እግዝአብሔር ትልቅ በሆነው በጎነቱ የሰውን
በደል ይቅር እንደሚል ተስፋ ይሰጣል፡፡
በተለያዩ
የእምነት ክፍሎች ይቅርታ ትርጉም አለው፡፡
በዓለም ዙሪያ ብዙ የእምነት ዓይነቶች መኖራቸው
የሚታወስ ሲሆን አንዱ የሚያምንበት
ቅዱስ መጽሐፍ ከሌላው
መጽሐፍ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ የክርስትና
እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል
የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለይቅርታ
የሚያስተምረው ሰዎች በዓለማዊ ልማድ ከመሰረቱት
ይቅርታ እጅግ የሚለይ ነው፡፡ ስለ ይቅርታ
ከቃሉ የምንማረው እውነት በሥራ ላይ ለማዋል
የውስጥ ጥንካሬንና መንፈሳዊ ቁርጠኝነንም
ይጠይቃል፡፡
እስልምና
ደግሞ በቁርዓን
ላይ ሲያምን የተመሠረተ ነው፡፡
ታዋቂዎቹ የእምነት ክፍሎች እነዚህ ቢሆኑም
ቡድሃ፣ ሕንዱ ጃይኒዝም፣ የአይሁድ ሃይማኖት
ደግሞ የየራሳቸው የእምነት አቋም ያላቸው
ናቸው፡፡ እነዚህ እያንዳንዳቸው ስለይቅርታ
የሚሎት አላቸው፡፡
ለምሳሌ
አንድ ጥፋት ሰርቶ እንደሆነ ይቅርታን መጠየቅ
የሂንዱ እምነት ልምምዶች ከሆኑት ውስጥ አንዱ
ነው፡፡ በእስልምና እምነት መሠረትም ቢሆን
አምላክ/አላህ/
የይቅርታ
ሁሉ ምንጭና ይቅር ባይ ነው፡፡ ይቅርታን
የሚፈልግ ሰው ንስሐ ሊገባ ያስፈልገዋል፡፡
ሰዎች ንስሐ ሲገቡ ከአላህ ዘንድ በቀጥታ
ይቅርታ ይደረግላቸዋል፡፡ ከእግዚአብሔር
/ከአላህ/
ይቅርታን
ለመቀበል ሶስት ነገሮች ማሟላት አለባቸው
አንደኛው የሰሩትን በደል ማወቅና በእግዝአብሔር
ፊት ማቅረብ ሁለተኛው ያንኑ በደል ደግመው
ላለመስራት መወሰን ሲሆን ሶስተኛው ከእግዚአብሔር
ይቅርታን መጠየቅ ነው፡፡
በጃይኖች
እምነት መሠረት ደግሞ አንድ ሰው ይቅርታን
ለማግኘት ከተለያዩ ፍጥረታት ደጋጋሞ ይቅርታ
ከትንንሽ ፍጥረታትና እጽዋት ሁሉ ይቅርታን
መጠየቅ ይጠበቅበታል፡፡ ይቅርታ የዚህ እምነት
ተከታይ መሆን የፈልግ ሰው ከሚከተላቸው አብይት
ተግባራት አንዱ ነው፡፡ በአይሁድ እምነት
መሠረት አንድ ሰው በሌላው ላይ በደል አድርሶበት
ከሆነ ወደ ተበደለው ወገን ሄዶ ይቅርታ መጠየቅ
አለበት፡፡ የራሱን ግዴታ ለመወጣት ስለ ሠራው
በደል ሶስት ጊዜ ይቅርታን መለማመን ይኖርበታል፡፡
እነዚህ ለምሳሌ ያህል የምንመለከታቸው ሲሆኑ
ይቅርታ በሁሉም አንፃር እንዴት የከበረና
በጥብቅ የሚፈለግ ሃይማኖታዊ ማህበራዊ እይታን
የሚስብ እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡
ማንኛውም ይሁን ለሰው የሚደረግ ይቅርታ
የሚሰማውን ሁሉ ያስደስታል፡፡
የእግዚአብሔር
ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለ ይቅርታ
የሚያስተምረው ሰዎች በዓለማዊ ልማድ የመሰረቱት
ይቅርታ እጅግ የሚለይ ነው፡፡ ስለይቅርታ
ከቃሉ የምንማረው እውነት በሥራ ላይ ለማዋል
የውስጥ ጥንካሬንና መንፈሳዊ ቆራጥነትንም
ይጠይቃል፡፡ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት አንባቢያን
የነበሩ አይሁዶች ስለይቅርታ ጥልቀት ያለውን
ግምት የሚሰጡ ሲሆን በእነርሱ አተረጎጎም
መሠረት ይቅርታ ማለት መሸከም፣ መታገስ ወልወል
አድርጎ ማጽዳት፣መሸፈን ማለት ነው፡፡ የብሉይ
ኪዳንን መጽሐፍት ወደ ግሪክ ቋንቋ የተተረጎመ
ሴኘቱኤጀንት ተብሎ የሚታወቀው የሰባ ሊቃውንት
ጉባኤ በተረጎመው መሠረት ከሆነ አፒ.ኤሚ፣ዴኮማይ፣ኢፖሪዮ፣
ሄሊዩስ ፣አይናዳ፣ ኤክስልዮስኮማይ የሚባሉና
ከእነዚህ ጋር ተቀራራቢነት ያላቸው የተለያዩ
ቃላት ስለይቅርታ በጥልቀት ያስረዳሉ፡፡ ምን
ማለት እንደሆነ ተብሎ ሲጠየቅ ይቅርታ ማለት፣
ማስወገድ፣ መማር፣ ማጽዳት፣ በአድናቆት
የመቀበል ግንዛቤ ማሳየት የሚለውን የሚያሳዩ
ናቸው፡፡
በአዲስ
ኪዳን ይቅርታ ጥልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን
በእግዚአብሔር ቃል እንደምናምን ክርስቲያኖች
እንደሚተለው የተቀመጡትን ሐሳቦችን መተርጎም
ይገባናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይቅርታ፡፡
በእግዚአብሔር
ባህሪይ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
እግዚአብሔር
በባህሪው ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ ነው፡፡
የመረጣቸውና የጠራቸው የእስራኤል ሕዝቦች
ደጋግመው ሲበድሉ ይቅርታ ሊላቸው አልሰለቸውም፡፡
በአባትነት ምክር ቢገስፃቸውም ተመለሰው
ምህረት ሲለምኑት ከጠላታቸው እያዳናቸው ቃል
ኪዳኑን ሳይረሳ ይቅርታውንና ምህረቱን ለሺህ
ትውልድ የሚጠብቅ አምላክ መሆኑን አሳይቷል፡፡
ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆላስይስ ቤ/ክ
አማኞች በተፃፈው መልዕክት እርስ በእርሳቸው
ይቅርታ እንዲባባሉ ይመክራቸዋል፡፡ ይህንን
ማድረግ የሚችሉት ክርስቶስ ያደረገላቸን
ሲያስቡ ብቻ ነው፡፡ "
ማንም
ባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው ይቅርታ
ተባባሉ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም
ደግም ይቅርታ ተባባሉ"
ቆላ
3፡13፡፡
ከእግዚአብሔር የምንማረው ባህሪያቱን ነው፡፡
እርሱ ፍቅር እንደሆነ ፍቅርን እንድንለማመድ
እንደሚጠበቅብን ሁሉ የቅርታንም ከእርሱ
እንማራለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ክርስቲያናዊ
ይቅርታ በክርስቶስ ባህሪይ በሆነ የይቅርታ
ሥራ ላይ የቆመ ነው፡፡ ያለዚያ እውነተኛ
ይቀርታ የለም፡፡ የእግዚአብሔርን ይቅርታ
የምንቀበልበት መንገድ ነው፡፡ የክርስቶስ
ፍቅር ከሁሉም በላይ በመሆኑም የበደሉንን
ይቅር ከማለት አልፎ በፍቅር መቀበል የእውነተኛ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይቅርታ መገለጫ ነው፡፡ ይቅር
ብያለሁ ማለት ብቻውን አይበቃም፡፡ መቀባበልና
መውደድ ይቅርታን እውነት ያደርገዋል፡፡
ማቴ 6፡14
የምንኖረው
ከሰዎች ጋር ሲሆን እያንዳንዱ ሰው ደግሞ
ኃጢአተኛ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡
ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር እንድንል ታዘናል፡፡
ይቅር የምንለው ኃጢአተኛው የቱ ነው?
የውርስ
ኃጢአታቸው ወይስ የድርፍረት ኃጥአታቸው ?
እንዲህ
አይነቱን ይቅር ማለት የሚችል ከእግዚአብሔር
ሌላ አይኖርም፡፡ ታዲያ ይቅር እንድንላቸው
የተጠየቅነው ከእኛ ጋር በተያያዘ ያስቀየሙንንና
ያሳዘኑንን በደላቸውን ከውስጣቸው አውጥተን
ስለመጣል እንጂ፡፡ ከሚወዱት ሰው መጎዳት
በሚያውቁት ሰው መጠቃት ልብን ያሳዝናል፡፡
እንደዚህ ባለ ወቅት በደልና ኃጢአት መልሰን
ከመቁጠር ይልቅ ምህረት እንድናደርግ ታዘናለ፡፡
ይህንን የሚመስል ልምምድ ሲኖር ከእግዚአብሔር
ይቅርታን እናገኛን፡፡ ሰዎች ይበድሉናል
እኛም ደግሞ በራሳችን አቅጣጫ እግዚአብሔርን
እንበድለዋለን፡፡ ምህረት ካልተደረገልን
የሚጠብቀን የእርሱ ቁጣ ነው፡፡ እርሱ ይቅርታ
እንዲለን የምንፈልግ ከሆነ መንገዱ ለሌሎችን
ይቅርታ ማለት ብቻ ነው፡፡
በኃጢአታችን
ጊዜ ምህረትን በህመማችን ወቅት ፈውስን
በችግራችን ጊዜ እርዳታን ከጌታ እንጠብቃለን፡፡
የምንፈልገውን ስናገኝ አብዝተን ደስ እንሰኛለን፡፡
ጌታም የምንፈልጋቸውን ሁሉ የሚያደርግልን
መልካምነታችን ማርኮት ሳይሆን ብዙ በሆነው
ምህረቱና ይቅርታው ምክንያት ነው፡፡ እኛም
የበደሉንን ሰዎች በደል ከልባችን በማውጣት
ኃጢአታቸውን በማስወገድ ልባችንን በማንፃት
እነርሱን ፈጽመን ለመቀበል ዝግጁ መሆን
ይጠብቅብናል፡፡ በባህሪያችን መስጠት እንጂ
መቀበል አያቅተንም፡፡ ምህረትና ይቅርታን
ስንቀበል እንደሰታለን ጨምረንም እንመኘዋለን፡፡
ለሌሎች ይቅርታን ለማድረግ ግን ይከብደናል፡፡
ስለዚህ ነው ይቅርታን በማድረግ ወቅት ስሜታችንን
የጎዱንን ይቅር ብለን መባረክ መንፈሳዊ
አቅምንና የውስጥ ቆራጥነትን የሚጠይቅ ነው
ያልኩት፡፡ በየትኛውም መንገድ ቢሆን ከእግዚአብሔር
ይቅርታን የመንቀበለው የሰዎችን በደል ይቅር
ስንል ብቻ መሆኑን ቃሉ በግልጽ ያስተምረናል፡፡
በደለኛውን
በምህረትና በፍቅር መቀበል ነው፡፡
ይቅር
ብሎ መተው ብቻ ሳይሆን በፍፁም ምህረትና
በይቅርታ መንፈስ የራስ አድርጎ በፍቅር መቀበል
ነው፡፡ መቀበል የሚለው ቃል እንዲሰመርልኝ
እፈልጋለሁ፡፡ እንዲህ አይነቱ አባበልን
ዕብራውያን/Dechomai/
ዴኮማይ
ብለው እንደሚጠሩት አዲሱ የሥነ-መለኮት
መዝገብ ቃላት /the
new dictionary of biblical theology/ ይነግረናል፡፡
የበደሉንን ሰዎች ኃጢአትና በደል ይቅር ማለት
ብዙም ላይከብደን ይችላል፡፡ ነገር ግን
እነርሱን እንደ አካላችን አድርገን መቀበል
አቅምን የሚፈታተን ነው፡፡ የቱም ቢሆን
የእግዚአብሔር ሐሳብ ይኸው ነውና ማድረግ
ይኖርብናል፡፡
ጊዜው
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1992
ዓ.ም.
ገደማ
ነው፡፡ የተወሰኑ አይሁዳዊያን ለጉብኝት ወደ
አገራችን መጥተው ነበር፡፡ ቁጥራቸውም ወደ
ሃያ የሚጠጋ ሲሆን ወንዶችም ሴቶችም በዕድሜአቸው
የገፋም ደግሞ ወጣቶችም ይገኙበታል፡፡ እነዚህ
ሰዎች እኔ በማገለግልበት ቤተክርስቲያን
በአንድ ምሽት ምስክርነት እየሰጡ ያጽናኑና
ያስደንቁ ነበር፡፡ የአንዲት ባልቴት ምስክርነት
ግን ምን ጊዜም ከልቤ ሊጠፋ አልቻለም፡፡
እንዲህ አሉ የናዚ ጀርመን አይሁዶችን በጨፈጨፈበት
ወቅት እኔ ቢበዛ የሶስት ዓመት ልጅ ነበርኩ፡፡
በአንድ ሥፍራ ከሴት አያቴ ጋር እያለን የናዚ
ወታደሮች መጡብን፡፡ ልጅ ስለነበርኩ ስለጉዳዩ
ምንም ግንዛቤ አልነበረኝም፡፡ ግን ወዲያው
አንድ አሰቃቂ ነገር ተፈጠረ ፡፡ ያውም አያቴን
በፊቴ ሰውነቷን እየቆራረጡ በታትነው ሥጋን
እንኳን መለየት እስከማይቻል ድረስ አበላሽተው
ከገደሏት በኋላ እኔ ምርር ብደ እያለቀስኩ
ብቻዬን ትተውኝ ሄዱ፡፡ የነበረው የአገዳደል
ሁኔታ በአህምሮዬ ተስሎ ያሰቃየኝ ጀመር፡፡
በኋላ ሰዎች አግኝተውኝ ወስደው አሳደጉኝ፡፡
ቤተሰቦቼ ሁሉ በተመሳሳይ ጭፍጨፋ አልቀው
ስለነበር ያለዘመድ አደግሁ፡፡ ካደጉህ በኋላ
ኢየሱስን አምኜ ከመጽሐፍ ቅዱስ የበደሉንን
ይቅር ማለት እንዳለብን የሚያስተምር ቃል
ሳነብ ማንንም ቢሆን ይቅር ማለት ይቻላል፡፡
ጀርመኖችን ግን እንዴት ይቅር ማለት እችላለሁ?
እንኳን
እኔ እግዚአብሔር እንዴት ይቅር ይላቸዋል?
ብዬ
እሟገት ጀመርኩ፡፡ በኋላ ግን ይህንን ካላደረኩ
እኔንም እግዚአብሔር ይቅር እንደማይል በቃሉ
ስለተናገረኝ በፍፁም ልቤ ይቅርታ አልኩ ብለው
መሰከሩ፡፡ እኚህ እናት በምስክርነታቸው
ከተናገሩት ከባድ ነገር ይቅር ብለው ማለፍ
የሚቻል ቢሆንም ጀርመኖችን መውደድስ ይቻላልን?
ማለታቸው
ነው፡፡ የክርስቶስ ፍቅር ከሁሉም በላይ በመሆኑ
የበደሉንን ይቅር ከማለት አልፎ በፍቅር መቀበል
የእውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይቅርታ መገለጫ
ነው፡፡ ይቅር ብያለሁ ማለት ብቻውን አይበቃም፡፡
መቀባበልና መውደድ ይቀርታውን እውነት
ያደርገዋል፡፡ ለዚህ ዋቢ የሚሆነን አንድ
ምሳሌ ማየት ይጠቅመናል፡፡
አንደኛው
በዘፍጥረት 50፡17
ላይ
የምንማረው ታሪክ ሲሆን በወንድሞቹ የተበደለ
ዮሴፍ እግዚአብሔር ታሪኩን ለውጦለት በዳዮቹን
በእጁ በጣለለት ወቅት ያዕቆብ ይቅር በላቸው
ብሎ መልዕክት ላከለት፡፡ እነርሱ ከፈተውብሃል፣
ግን የአባትህ አምላክ ባሪይዎች ናቸውና ይቅር
በላቸው ሲለው መልዕክቱን ሰምቶ አለቀሰ፡፡
የያዕቆብ
ልጆች ተባብረው ወንድማቸው በሆነው በታናሹ
ዮሴፍ ላይ እጅግ የሚያሳዝን በደል አድርሰውበታል፡፡
"እባክህ
የወንድሞችህን በደለ ኃጢአታቸውንም ይቅር
በል እነርሱ በአንተ ላይ ከፍተውብሃል የሚለውን
የአባታቸውን መልዕክት ተቀበለ፡፡ በሌላ
አባባል ወንድሞችህ ክፉ አድርገውብሃል ስለዚህ
ይቅር በላቸው የሚለው የአባቱ የይቅርታ ጥሪ
ዮሴፍ የተቀበለው በእምባ ነበር፡፡ ቃሉ አለቀሰ
ይለናል፡፡ ይህ ልቅሶ የቂም በቀለ ልቅሶ
ሳይሆን ወንድሞቹን ለመቀበል ያደረገው ልቅሶ
ነበር፡፡ ክፋት ያደረጉብንን ክፋም ሆነውብን
ስንለምናቸው እንኳን አንሰማ ብለው በጭካኔ
የልባቸውን ሐሳብ የፈፀሙብንን ሰዎች ቀናት
ተለዋውጠው ጊዜም መጥቶ በእጃችን ወድቀው
ብናያቸው ምን እናደርጋቸው ይሆን?
ከእምባና
ከለቅሶ ጋር ተቀብለን ምህረት እናድርግላቸው
ይሆን?
ወይስ
በውስጣችን የታመቀውን በቀልና የቂምን ትኩሳት
እናፈስባቸው ይሆን?
አንድ
ቀን እኛ አቅም አግኝተን እነርሱን ለመርገጥ
የምንችልበት አጋጣሚው ቢሰጠን እነርሱም
በእጃችን ቢወድቁ ማረን ብለው ቢለምኑን ብናይ
ዓይን ለዓይን እጅም ለእጅ ሳንል በክርስቶስ
በሆነው ምህረት አድርገን እንቀበላቸው ይሆን?
መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ይቅርታ የምንለው ይኸው ነው፡፡ እኛም
እውነተኛ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት የሚያሰኘን
መለያችን ይህ ነው፡፡ ወንድሞቹ በዮሴፍ ላይ
ያደረጉት ግፍ ከልብ የሚወጣ ከአህምሮም የሚፋቅ
አልነበረም፡፡ ያኔ በትንሽ አቅሙ ሲማጠን
አንሰማ ብለው ሊገድሉት ፈልገው በታላቅ
ወንድማቸው ጣልቃ ገብነት ሐሳባቸውን ቀይረው
ራቁቱን በጉድጎድ ውስጥ ጥለው ከዚያም አውጥተው
እንደ በግ ጠቦት በትንሽ ዋጋ ሸጠው ያንከራትቱት
ጨካኞች የእግዚአብሔር ቀን መጣና በእርሱ
እጅ ሲወድቁ በዓይኑ አየ፡፡ ብድራታቸውን
ለመክፍል አሁን ቀኑ ደርሷል፡፡ ለሰሩት ክፉ
ሥራ ሰባት እጥፍ የሚያስከፍልበት ምቹ ሁኔታ
ተፈጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ ክፋ አድርገውብሃልና
ይቅር በላቸው ሲባል ይቅር ማለት አልከበደውም፡፡
ያውም ከአምባ ጋር፡፡ ይህ እውነተኛ መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ይቅርታ ነው፡፡
በእርግጥ
ሕይወታችንን ስንመረምረው ከዚህ አንፃር ምን
ይመስላል?
እንዲያው
የበደለንን ሰው በፍቅር እንቀበለው ይሆን?
ይቅርታ
አድርጉልኝ ብሎ ሲመጣ አይተናል ከእምባ ጋር
እንቀበለው ይሆን?
አባካኙን
ተቀብሎ የሚሸከም ነው፡፡
በሉቃስ
ወንጌል ምዕራፍ 15
የምንመለከተው
የአባካኙ ልጅ አባት የሰራው ሥራ አስደናቂ
ነው፡፡ ልጁ እኮ ከአባቱ ሐብት ምንም ድርሻ
ላይፈልግ የሚገባውን ወስዷል፡፡ ካደረጋቸው
ከባድ በደሎች አንዳንዶቹ እንጥቀስ፡-
አባቱ
በሕይወት እያለ ድርሻ መጠየቁ በኢትዮጵያውያንም
ዘንድ ቢሆን በጣም አስነዋሪ ተግባር ሊባል
ይችላል፡፡ በአይሁዶችም ባህል ቢሆን እንዲህ
ዓይነቱ ልማድ የላቸውም፡፡ የራሱ ያልሆነውን
ግን የአባቱን ገንዘብ ወስዶ ወደ ሩቅ አገር
ሄዶ አባከነ፡፡ ያም ባለፋ እሪያዎች ከሚበሉት
አሰር ለመጥገብ ተመኘ፡፡ በእስራኤል ልጆች
አሳማ/እሪያ/
እንደ
እርኩስ የሚቆጠር እንስሳ ነው፡፡ ያንን የመሰለ
ሕይወት ለመኖር ራሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡
ገንዘቡን
ያባከነው ከጋለሞታዎች ጋር ነው፡፡ እነዚህ
ከበደለኝነትም ከባድ በደለኝነት ተደርጎ
ሊቆጥሩ ይችላሉ፡፡ እኛ አባት አብርሃም አለን
ብሎ ከሚመፃደቅ ማህበረሰብ መካከል የተወለደ
ልጅ እንደዚህ አይነት ሥራ መስራቱ ለወላጅ
አባቱ የልብ ስብራት ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም
ልጁ አባቱን ልጅህ ልሆን አይገባኝም፡፡
ከሞያተኞች እንደ አንዱ አድርገኝ ብሎ ለመለመን
ሲመጣ አባትየው ከሩቅ አይቶ አዝኖለት አቅፎ
በመሳም ምንም ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ ለእግሩ
ጫማ ለጣቱ ቀለበት እንዲያውም የሰባ ፍሪዳ
አርዶ አብረው ለመደሰት አልከበደውም፡፡
ከዚህ ለጅ አባት የምንማረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ይቅርታን ነው፡፡ አባካኙን የሚሸልም ነው፡፡
ለእግሩ ጫማ ለጣቱ ቀለበት የሚያመጣ ያውም
የሌሎችን ተቃውሞ ወደ ጎን ትቶ ፡፡
ቀጠሮ
የማይሰጥ ሉቃስ 23፡34
ይቅርታ
ለመስጠት ጊዜ መውሰድ አያስፈልግም፡፡ ብዙ
ጊዜ አማኞች ሕይወት የምናየው የቅዱስ ቃሉ
ከሚያስተምረን ውጭ ነው፡፡ በደልንና የልብን
ሐዘንን ተሸክመው አስታራቂ ይፈልጋሉ፡፡
በመሠረቱ አስታራቂ የሚያስፈልገው መግባባት
ሲያቅት ወይም ሁለት ወገኖች እርስ በእርሳቸው
እንደጠላት የተያዩ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ነገር ግን አስታራቂ እስኪመጣ ሳይጠብቁ
በደለኛውን ይቅርታ ማለት ይቻላል፡፡ ይቅርታውን
እውነተኛ መጽሐፍ ቅድሳዊ የሚያደርገው ይህ
ነው፡፡ ኢየሱስ ይቅር ያለን በእርሱና በእኛ
መካከል ምንም አስታራቂ ሳይፈልግ ነው፡፡
ጌታ በመስቀል ላይ የሰቀሉትን የሮማውያን
ወታደሮችን እዚያው ይቅርታ አድርጎላቸዋል፡፡
በመስቀል ከመስቀላቸው በፊት የገረፋትን፣
እንጨት አሸክመው እየገፈታተሩ ወደ ዳገት
ያራመዱትን የሮማውያን ወታደሮችን ከባዱ
የእንጨት መሸከም ሥር ሆኖ እየተንገዳገደና
እየተደናቀፈ ሲወድቅና ሲነሳ እያዩ ያልራሩለትን
በጥፊ እየመቱት ሕጋቸው ከሚፈቅደው በላይ
በደል ካደረሱበት በኋላ በመስቀል ላይ መስቀላቸው
ሳያንስ መራራ ውሃ ያጋቱትን የሮማውያን
ወታደሮችን ይቅርታ ለማለት ጊዜ አልፈጀበትም፡፡
አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር
በላቸው ያለው እዚያ በመስቀል ላይ ሆኖ ነው፡፡
ልብሱን ሲከፋፈሉ አይቶ፡፡
ሐዋሪያው
ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክቱ ውስጥ ተቆጡ.
. . በቁጣችሁ
ላይ ፀሐይ አይግባ፣ ለዲያቢሎስም ፈንታ
አትስጡ፡፡ ኤፌ 4፡26
ያለው
ስለዚህ ነው፡፡ ቂምና ቅሬታ ውሎ ማደር
የለበትም፡፡ ውሎ ቢያድር ተበዳዩም አይጠቀምበትም
በዳዩም አይጎዳበትም፡፡ ዲያቢሎስን ከማስደሰት
ሌላ የሚፈይደው ነገር አይኖረውም፡፡ መጽሐፍ
ቅድሳዊ ይቅርታን ከሌሎች የተለየ የሚያደርገው
ይህ ነው፡፡ ተበድያለሁ ተጎድቻለሁ የሚለው
ሰው ምንም ጊዜ ሳይሰጥ ባልንጀራውን ይቅር
ማለት ይኖርበታል፡፡ እየሰደበ፣ በጥፊ እየመታ
፣ ስብዕናችንን እየጎዳ በሞራላችን ላይ
እየተረማመደበት እያለ በዚያው ሰዓት ወንድማችን
ነውና ይቅር ማለት ይቻል ይሆን?
ኢየሱሱና
እስጢፋኖስ ያደረጉት ይህንን አይደል?
ኢየሱስ
ጎኑ በጦር እየተወጋ እያለ እስጢፋኖስ ተኝቶ
በድንጋይ እየተወገረ እያለ ስለጠላቶቻቸው
ሕይወት ከአብ ዘንድ ይቅርታን ለምነዋል፡፡
ዛሬ በቤተክርስቲያን የሚታየው ግን የዚህ
ተቃራኒ መሆኑ አሳዛኝ ነው፡፡ ታረቁ ብለው
የሚሰብኩ ታላላቅ የቤተክርስቲያን መሪዎች
ይቅርታ ለማድረግ ሁለትና ሶስት ዓመታት ከዚያም
በላይ ሸንጎ ካልተቀመጠ እሺ አይሉም፡፡
የአንዳንዶች ችግር የሚፈታው በይቅርታ መንገድ
ሳይሆን የውጭ አይላት ጣልቃ ሲገቡ ነው
አሳፊሪ!!፡፡
ይህ ለክርስትና ምን ያህል ሩቅ መሆናችንን
የሚያሳይ ነው፡፡ የብዙ ቤተክርስቲያን መሪዎች
መጽሐፍ ቅዱስ የሼልፋቸው ማዳመቂያ እንጂ
በእርግጥ የሚያምኑበት አይደለም፡፡ ለዚህ
ብዙ ማስረጃ መቁጠር ሳያስፈልግ ወንድማቸውን
ይቅር ማለት አቅቷቸው ልበ-ቅን
ምዕመናን የሚያስለቅሱበትና የሚጎድበት
ሕይወታቸው በቂ ነው፡፡
ቀጣይት
ያለው ነው ፡፡ ማቴ 18፡21-22
ለመሆኑ
እኔ ወንድሜን ይቅር ማለት ያለብኝ ስንት ጊዜ
ነው?
ከወህኒ
የተፈቱ ወንጀለኞች ያንኑ የቀድሞ ጥፋታቸውን
እንዳይደግሙት መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ በሌላ
ወንጀል ቢጠረጠሩ ወዮላቸው ሪከርድ አላቸውና
ቅጣታቸውም ሊከብድ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ግን ከዚህ ይለያል፡፡ ወንድማችን ደጋግሞ
ቢበድለን ደጋግመን ይቅር እንድንለው ቃሉ
አዞናል፡፡ ወንድሜ ሰባት ጊዜ ቢበድለኝ
ሰባቱንም ጊዜ ይቅር እላለሁ?
ብሎ
ጴጥሮስ ለጠየቀው ጥያቄ ኢየሱስ የመለሰው
መልስ አስፈሪ ነው፡፡ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ
ሰባት ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ ለመሆኑ አንድ
ሰው ያንኑ ያህል ይበድለኛል?
አይመስለኝም፡፡
ጌታ እንዲህ ያለውን ምን ጊዜም ቢሆን ደጋግሞ
ይቅር ማለት እንደሚገባን ለማመልከት ነው፡፡
እንደክርስቲያን ባለፈው ይቅር ያልነው በደል
አሁን አይታሰብም፡፡ የዛሬው ጉዳይ ዛሬ ብቻ
መታየት ይገባዋል፡፡ ዛሬ ተበድሎ ትናንት
ይቅር ያለውን በደል የሚቆጥር ሰው ከልቡ ይቅር
አላለም ነበር ማለት ነው፡፡
መጽሐፍ
ቅዱስን መሠረት ያደረገ ይቅርታ ወዳጃችንን
ሁልጊዜ ይቅር ማለት ነው፡፡ እባካችሁ ይህንን
ጽሑፍ የምታነቡ ወገኖች ሁላችሁም ለባልንጀራችሁ
ይቅርታ ያደረጋችሁላቸውን ጊዜያቶች አትቁጠሩ፡፡
በልባችሁም እርሱን መዝግባችሁ አትያዙ፡፡
ባልንጀራችሁ በየትኛውም ጊዜ ይቅርታ አድርጉልኝ
ቢላችሁ ደስ እያላችሁ ይቅር በሉት፡፡
መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ይቅርታ በዙሪያው በጣም ብዙ እንቅፋቶችና
ግልጽ ያልሆኑ ጥያቄዎች አሉት፡፡ የጌታ ፍቃድ
ቢሆን እነዚህን አንድ በአንድ እያነሳን
እንመለከታለን፡፡
ይሸፍናል፡፡
ስለዚህ ዓለማዊውን ሰው ቢሆን ይቅር ማለት
ይኖርብናል፡፡
በክፋ
ፋታ ክፋን አትመለስም ሮሜ 12፡17
በጎችና
ውሾች በጣም የተለያዩ ፍጥረቶች /እንስሳት/
ናቸው፡፡
ውሾች መጥፎዎች አንዳንዴም ተንኮለኞች ናቸው፡፡
ከዱር አውሬ የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ
ውሾች አሉ፡፡
ውሻ
የሚፈራ በጣም ብዙ ሰው አለ፡፡ በጎች ደግሞ
ተንክል የሌላቸው በየዋህነታቸው የሚታወቁ
የቤት እንስሳት ናቸው፡፡ ውሾችና በጎች በአንድ
አካባቢ የሚኖሩ ቢሆንም ውሾች በበጎች ላይ
ይጮሃሉ፡፡ የቱንም ያህለ ቢጮሁ በጎች መልሰው
ውሾች በጮሁበት አጯጯህና ድምጽ ውሾች ላይ
አይጭሁባቸውም፡፡ ምክንያቱም የተሰጣቸው
ባህሪይ ስለማይፍቅድ እንዲሁም ሁሉ ከክርስቶስ
የተማርነውና የተቀበልነው መልካም ማንነታችን
ክፋን በክፋ መመለስ አያስችለንምና፡፡ ለማንም
ስለክፋ ፋንታ ክፋ አትመለሱ ይላል፡፡ ለማንም
ሲል ምን ማለቱ ነው?
ዓለማዊው
ያላመነው ሰው ክፋ ቢያደርግብን እኛ ክፋን
ለእርሱ መመለስ አይኖርብንም፡፡ አማኝ
ወንድማችንን ክፋ ቢያደርግብንም በክፋ ፋንታ
ክፋ አትመልሱ ብሎ አያበቃም፡፡ በሰው ሁሉ
ፊት /ባመኑም
ባላመኑም/
ፊት
መልካም የሆነውን እንድናስብ ይጠየቀናል፡፡
የክፋ ሥራ መነሻ የሚሆነው ክፋ ሐሳብ እንደሆነ
አያራጥርም፡፡ በመልካም ሐሳብ የተሞላ ሰው
ድርጊቱ መልካምና በጎ ይሆናል፡፡ ይህም በመሆኑ
አለማዊውን ሰው ይቅር ብለን ምህረት እንድናደርግ
የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው፡፡
እናንተ
አትበቀሉ፡፡ ሮሜ 12፡18-19
አማኞች
እንዳንበቀል የሚያደርጉ ሁለት ታላላቅ
ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛው ተወዳጅነታቸው
ነው፡፡ ለአማኞች ከተሰጣቸው ደማቅ ስሞች
አንዱ ይህ ነው፡፡ ተወዳጅነታችን በእግዚአብሔርም
በሰውም ፊት ከሆነ ማንንም ለመቀበል ጉልበት
እናገኛለን፡፡
ሁለተኛው
የበደሉን ሁሉ ብድራታውን ይቀበላሉ በቀልም
የጌታ ነው፡፡ በቀል ቢያስፈልግም ጌታ እንዲቀበልና
ብድራቱን እርሱ እንዲመልስ ዕድል ፈንታ ለጌታ
እንድንሰጥ ጳውሎስ ጠይቆናል፡፡ የበቀሉን
ጉዳይ ለጌታ መተው ይሻላል፡፡ እግዚአብሔር
እናንተ አትበቀሉ እኔ ግን እበቀላለሁ ይላል
ተብሎ እንደተፃፈው የሚያስታውስ ሲሆን በቀል
ማለት በሌላ አገላለጽ ቅጣት ማለት ነው፡፡
መቼም ቢሆን ጌታ ሳይበቀልልን አይተውም፡፡
ዘመናት ይረዝሙ ይሆናል ወይም እርሱ የረሳን
አድርገን እንቆጥር ይሆናል እንጂ ለእያንዳንዱ
ብድራቱን ሳይመልስ አይቀርም፡፡ የሰው ልጅ
ከመላዕክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንደ
አለውና ያን ጊዜ ለሁሉም እንደሥራው ያስረክበዋል፡፡
ማቴ 16፡27
ክፋን
ያደረገ ብድራቱን መቀበል እንዳለበት በእርግጠኝነት
እናምናለን፡፡ መጽሐፍ
ቅዱሳችንም ቢሆን
ክፋ አድራጊው በዚያው ድርጊቱ እንዲቀጥል
ተፈቅዶለታል እያለ አይደለም፡፡ እያንዳንዱ
የሥራውን ዋጋ ይቀበላል ይለናል፡፡ ይሁን
እንጂ ክፋ ላደረጉብን ሰዎች ከሥራቸው ጋር
የተመጣጠነ ምላሽ መስጠት የእግዚአብሔር
ጉዳይ ነው እንጂ የእኛ አለመሆኑን ያስገነዝበናል፡፡
ጠላቶቻችሁን
አገልግሉ፡፡ ሮሜ 12፡20
"ጠላት
ቢራብ አብላው ቢጠማም አጠጣው"
በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ብዙ የተስፋ ቃሎች፣ ምክሮች
ተግሳፆች እና ትህዛዞች አሉ፡፡ ሁሉንም የእኛ
እንድናደርጋቸው ይፈልጉብናል፡፡ በተለይም
ደግሞ የተስፋ ሐሳብ ያሉባቸውን ክፍሎች ስናነብ
ወዲያው ተቀብለን እንደሰትባቸዋለን፡፡ ወደ
ግሳፄ ሐሳቦች ስንመጣ ግን የልባችን መነቃቃት
እንደ እዚያኛው አይሆንም፡፡ በተለይ የሮሜ
መልዕክት 12፡20
በጣም
የሚፈታተነን ትህዘዝ ነው፡፡ ለአንባቢያን
በእርግጠኝነት የምለው አለኝ፡፡
ይህ
ክፍል ባነበብኩ በመጀመሪያው ወራት መልዕክቱ
ለእኔ አይደለም፡፡ የተፃፈው ብዬአለው፡፡
እርሱ ለሮሜ ቤ/ክ
ሰዎች እንጂ ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም
ብዬ ነበር፡፡ ይህንን ያልኩበት ምክንያት
ጠላቴ ሲራብ አይቼ የጣፈጠ ምግብ ሲጠማም ሳይ
ቀዝቃዛ ውሃ አቅርቤለት ሥጋውን መደገፈ
የመችልበት አቅሙ ስለሌለኝ ማምለጫ እንዲሆነኝ
ብዬ እንጂ ቃሉስ በደንብ ይመለከተኛል፡፡
እንደ እኔ አይነት የሆነ ክርስቲያን ወንድሞችና
እህቶች አይኖሩም ብዬ አላምንም፡፡ አንዳንድ
ጠንከር ያሉ ክፍሎች ሲነበብላቸው ይሄማ
ለቀድሞዎቹ ሰዎች የፃፈ ነው ይላሉ፡፡ በአንድ
ሥፍራ ቃሉን በጋራ እያነበብን "
ሴት
ለባሏ ትገዛ"
በሚለው
ሐሳብ ዙሪያ ስንወያይ አንዳንድ ሰዎች ይህ
እኮ በኤፌሶን ላሉ ሰዎች ነው የተፃፈው፡፡
ለእኛ አይደለም ብለው ያርፋቡትን ቀን
አልረሳውም፡፡ የማያወላዳ እውነት ግን ሁሉም
ሐሳቦች በመጀመሪያ የተፃፋት ለእኛ አይደሉም፡፡
በጊዜው የነበሩ ፀሐፊዎች በዚህ ዘመን እንበልና
በኢትዮጵናያ ያለነውን የአሁኖቹን አማኞች
በጭራሽ አያውቁም ነበር፡፡ ቃሉን እንዲጽፉ
ለእነርሱ የሰጣቸው ያኔ ከእነርሱ ጋር ሲሰራ
የነበረው መንፈስ ቅዱስ ግን ዛሬም ቃሉን
ሳይለውጥ ስላለ እኛን አይመለከተንም ለማለት
አንችልም፡፡ ስለዚህ ከማንነታችን ጋር
የማይመስል ቢሆንም ከቃሉ አንድንም ሳናስቀር
እንኖርበታለን፡፡ እንገዛለትማለን፡፡
እንግዲህ ጠላትህ ቢራብ አብላው ቢጠማም አጠጣው
ማለት በአጭር ቃል የበደለህን ሰው የማያምን
አለማዊ እንኳን ቢሆን በመልካም ልብ ቀርበህ
አገልግለው ማለት ነው፡፡ እንደዚህ ከሆነ
አለማዊያን ቢበድሉንም እንኳን ይቅር ማለት
ይኖርብናል፡፡
ጠላታችን
ቢራብ የምናበላው ሲጠማስ የምናጠጣው ከሆነ
ውጤቱ መን ይሆናል?
ብለን
ባናልፈው ጥሩ ነው፡፡ "
ጳውሎስ
እንዲህ አለ ይህንን በማድረግ በራሱ ላይ
የእሳት ፍም ትከምራለህ"
ይለናል፡፡
በጠላታችን ራስ ላይ የእሳት ፍም መከመር ማለት
ምን ማለት ነው?
ለዚህ
መልስ እንዲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች
የሚያቀርቧቸው የተለያዩ አማራጭ ትርጉሞች
አሉ፡፡
አንደኛ-
በበደለኛው
ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት ጠንከር እንዲል
ማድረግ ነው፡፡ የእሳት ፍም የፍርድ ወይም
የቅጣት ምልክት ነው፡፡ ወጥመድ በኃጢአት
ላይ ይዘንባል፡፡ እሳትና ዲን አውሎ ነፋስም
የጽዋቸው ዕድል ፈንታ ነው፡፡ መዝ 11፡6
ሁለኛው
ደግሞ በደለ ያደረገብንንም ሰው ማሳፈር ነው፡፡
የእሳት ፍም በክፋ ፈንታ መልካም ስናደርግላቸው
በደለኞች የሚሰማቸው ሐፍረት ወይም የመሸማቀቅ
ምሳሌ ነው፡፡ እኔ ያንን ያህል ክፋ ነገር
እያደረኩበት እንደዚህ መልካም ያደርግልኛል
ብሎ በሠራው ሥራ እንዲፀፀት ማድረግ ነው፡፡
ሶስተኛው፡-
አማራጭ
ንስሐ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ በጥንት ዘመን
በግብፆች ልማድ መሠረት አንድ በደል የሰራ
ሰው ከሰራው በደል ንስሐ ሲገባ እሳት ፍም
በአናቱ ላይ ተሸክሞ እንዲሄድ ይደርጋል፡፡
ይህንን በሚያደርግበት ወቅት ንስሐ መግባቱንና
በኃጢአቱ መፀፀቱን ያሳያል፡፡ እንደዚሁ እኛ
የምንሰራው መልካም ሥራ በደለኛው በበደሉ
ተፀጽቶ ንስሐ እንዲገባ ያደርገዋል ማለት
ነው፡፡ መልካም ማድረግ የበደለኞችን ልብና
አህምሮ በንስሐ ወደ መመለስ ይመራዋል ማለት
ነው፡፡ ሶስቱን ሐሳቦች አከብራቸዋለሁ፡፡
ዓለማዊው ሰው ቢበድልህ ይቅር እላለሁ ወይ?
ለሚለው
ሐሳብ ከብዙ ነጥቦች ጥቂቶቹን ተወያያተንበታል፡፡
ለጊዜው በዚሁ ገና እናድርግና ወደሚቀጥለው
እንለፍ፡፡
አውቆ
የልቡን ከፈፀመ በኋላ ይቅርታ አድርግልኝ
ቢል ላድርግለት ወይ?
ሁላችንንም
የሚቸግረን ይህ ነው፡፡ የሚሰራው ሥራ ልክ
እንዳይደለ በትክክለ እያወቀ ጉዳት ካደረሰብኝ
በኋላ ይቅርታ የሚጠየቀንን ሰው እሺ ምህረት
ይሁንልህ ብዬ እግዚአብሔር ያስገድደኛልን?
ብለን
ራሳችን የፍርዱን ውሳኔ እንሰጣለን፡፡ በእርግጥ
የአንዳንድ ሰዎች ድርጊት ለይቅርታ ያለንን
መንፈስ ያበላሻል፡፡ የሚሰራው ሥራ በሌላው
ላይ በደል እያደረሰበት እንደሆነ የማያውቅ
የለም፡፡ አህምሮውን የለቀቀ ሰው ካልሆነ
ማንም ሰው ጥፋቱን ያውቃል፡፡ ቀለል ያለ
የአህምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንኳ አሉታዊ
ድርጊቶቻቸውን ያውቃሉ፡፡
ሳያውቁ
ኃጢአትን ቢያደርጉ በደል ቢፈጽሙ ልንኮንናቸው
በድለውናል ልንላቸው አንችልም፡፡ ለምሳሌ
ሕፃናት ሲሰድቡን ብንሰማ ያስቀናል እንደ
አያስቆጣንም፡፡ ምክንያቱም ጥፋት ማለት የቱ
እንደሆነ ወደሚለዩበት ደረጃ ገና ስላልደረሱ
አንቀየማዠውም፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአተኞች
ናቸው አይላቸውም፡፡
አማኞች
የእግዚአብሔርን ቃል እያነበቡ ኃጢአትንና
ጽድቅን እንዲለዩ ቃሉ በልባችንም በአህመሮአቸውም
ቀርቧል፡"
የእግዚአብሔር
ቃለ የሆነው ሕግ ለሌላቸው ደግሞ ህሊናዠውም
ራሱ ሕግ ነው፡፡ ሮሜ 2፡12-16
በወገኑ
ላይ በደል እያደረሰበት እንዳለ የማያውቅ
ማንመ የለም፡፡ ሁሉም ሰው የሚበድለው እያወቀ
ነው፡፡ ይቅርታ እንድናደርግ የምንጠይቅበት
ምክንያቱመ ይህ ነው፡፡ ልቦናው እያወቀ የልቡን
ስላደረሰብን የቅርታ እናደርጋለን፡፡ ሳያውቅ
ቢያደርግ ኖሮ ቅር ላይለን የችላል፡፡ ሰዎዡ
አንዲያውም ይህንን በደል ስላደረሰ ደስ የሰኙ
ይሆናል፡፡ አንዳነዶችም ጽድቅ እንደፈፀሙ
ሊቆጥሩ ይችላሉ፡፡ አንደንዶች ቀድመው የፈፀሙት
በደል ሳያንስ ሌላም ለመጨመር ሊጋበዙ ይችሉ
ይሆናል፡፡ በዚህ ወቅት ይቅርታ ለማድግ ኃይል
አናገኝም፡፡ ቢሆንም ፍቅር የኃጢአትን ብዛት
የሸፍናል፡፡ ስለተባለ ይቅርታ ማድረግ ግዴታችን
ነው፡፡ ወደዚህ ደጃ ለመድረስ የእውነተኛ
ደቀመዝሙርነት ሕይወት ወሳኝ መሆኑን ይ ሐሳብ
ይጠቁማል፡፡