Tuesday, January 21, 2014

ውርጃ የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ተግዳሮትና የትውልድ ማጥፊያ

ውርጃ፣ የዘመናችን ቤተ ክርሰቲያን ተግዳሮትና የትውልድ ማጥፊያ
ከፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ
E-mail satemefe@yahoo.com

አርጄንቲናዊው ሪቻርድ ቶሬ እ.. . ምቤር 11 ቀን 2013 ላይ ድል ባለ ድግስና በቃል ኪዳን ሥነ ሥርዓት በወንዝ ዳር ከቆመ ትልቅ ዛፍ ጋር የጋብቻ ሥነ ሥርቱን መፈሙን የሰማና ያየ ሁርሟል፡፡ ቶሬ የጋብቻ ሥነሥርዓቱን ሲፈጽም ብዙ ታዳሚች፣ ሚኒስክርት የለበሱ ሴቶች ሚዜዎችሚዜዎች፣ አበባ በታኝ ልጆች፣ ካሜራ ባለሙያዎችና ሌሎችም ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡ የሚያምር ነጭ ሙሉ ልብስና አሬንጓዴ ባርኔጣ አድጎ ከወደደው ንጨት ጋር ጋብቻውን የጸመው ቶሬ በአስፈጻሚዎቹ አማካይነት ከፍቅረው ዛፍ ጋር ጋብቻ ቃል ኪዳን ከፈጸመ ኃላ ቀለበትም አድርጓል፡፡ በእድምተኞቹ ፊት ፉን እወድሻማለት አቅፎመና ከላሰ በኃላ የተያዩ የምግ ዓይነቶችንም ጋዟል፡፡ ቶረ የጋብቻ ሥነሥርዓቱ በፈረንጅ አገር ሰው ለሰው ከሚደረገው ሠርጎች የሚበልጥ እጂ የሕዝብ የተገኘበት ነው፡፡ ይህንን ላና ለሰማ እውነተኛ ክርስያን ሁሉ ሰይጣን በረቀቀ መንገድ እየሠራ መሆኑ በደንብ ገባዋል፡፡ እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ክቡር ጋብቻ ምን ያህል እየረከሰ እንደሆነ ለመገመት አያስቸግርም፡፡ ከጋብቻ ጋር በተያያዘ የሻሮን ቴንዳሌ ጋብቻ ሌላው አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ 9 ዓመት በፊት ፣የ41ዓመቷ እንግሊዛዊቷ ቱጃር ሻሮን ቴበታህሳስ ወር 2005 ልፊን ጋር ጋብቻን የፈጸመችው የሚያምር ቬሎ አድርጋ የሙሽራውን ጉንጭ ደጋግማ በመሳም ነው፡፡ ከጋብቻዋ በፊት ለ15 ዓመታት ያህል ከዶልፊኑ ጋር የተቀራረበው ቴንዳሌ አንድ ቀን ያልጠበቀችው ነገር ገጠማት፡፡ ከፍቅረኛዋ ከዶልፊን ጋር ለመዋት ከገባችበት ባህር ውስጥ ሳትመለስ በዚያው ፍጸሜዋ ሆነ፡፡
የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና ዓላማ ስለ ጋብቻ ለማሳሰብ ሳይሆን ባለንበት ዘመን የሰው ልጅ በምን ዓይነት ውድቀት ውስጥ እንዳለ ለማሳየትና እንድንነቃ ለማድረግ ነው፡፡እንደነዚህ ዓይነቶች አሳፋሪና አሳየሆኑ፣ የሰው ልጆች ውድቀቶችን መስማት ተራ ነር እየሆነ ጥቷል፡፡ እንደነዚህ ዓነቶች ነገሮች ለቤተክርቲያን ትልቅ ተግዳሮት እንና የተጣለባትን ኃፊነት በእነት በቅንነት፣ በትጋትና ታማኝነትም እንትወጣ የሚያለክ፣ጌታም በደጅ ሆነ እንናስተውል የሚያደር የማቂያ ደወል ናቸው፡፡ የጋብቻ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዘመናችን ቤተክርስቲያን ሌላ ብዙ ፈተናዎች አሉባት፡፡
21ኛው ክፍለ ዘመን መንግሥታትንና ቤተክርቲያናትን ከሚፈታተኑት ጉዳዮች ሌላውና ዋንኛው ውርጃ ወይም አዲስ ከመጣው አጠራሩ መረት ጽንስ ማረጥ ነው፡ ጽንስ ማረጥ ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ሙግቶች ሲደመጡ ኖረዋል አሁንም እየሰማናቸው እንገኛለን፡፡ ከዚህ አንጻር ቤተክርቲያ ልትጫወት የሚገባ ሚና እጅግ በጣም ከፍመሆኑን ውርጃና ተለዋዋጭ ገጽታው፣ በዘርፉ የሚሰነዘሩ ሙግቶች እና ከፍተኛ ፍጥነት የታከለበት ዕድገቱ ይጠቁማሉ፡፡ ቤተክርስቲያ ከማንም በላይ ቀድማ ለፍትህ መቆም ሕይወትን ለመታደግና ለድምጽ አልባዎች የምትገት መሆን እንዳለባት ከጌታ የተቀበለችው ኃላፊነት ያስገድዳታል፡፡ የምንሰብከው የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሕገ መንግሥት ስለሆነ በሙላት ሊሰበክ የሚገባው ሲሆን ለዚህም ቀዳሚ ሚና ጫወት የሚበቅባት እግዚአብሔር በምድር ላይ የራሱ እንደራሴ አድርጎ ያስቀመጣት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ባደጉና ዴሞክራሲያዊ በሆኑ አገሮች የሕናትን መብት መጣስ፣ሕጻናትን ማጥቃት ( Child abuse ) ፣ሕጻናትን ለጦርነት መጠቀም ፣ ከአቅማቸው በላይ ሥራ ማሰራት እና ወዘተ ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትል አደገኛ ወንጀል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለዓለም ሁሉ በማስተጋባት ጉልህ ሚና የመጫወት ኃላፊነት የሚጠበቅባት ቤተክርቲያን ከዴሞክራት አገሮች በላይ ለዚህ ጉዳይ ልትቆም ይገባታል፡፡
ባለጋራችን ዲያብሎስ የእግዚአብሔር ዓላማ በሰዎች ሕይወት እንዳይከናወን ከሚያደርጋቸው ስልቶች አንዱ ሊወለዱ ያሉ ሕጻናትን ማስጨንገፍ ወይም ከተወለዱም በኃላ በጅምላ እንዲጨፈጨፉ ማድረግ ነው፡፡ የእሥራኤል ልጆች በምድረ ግብጽ እየበረከቱ ሲሄዱ ያየ ንጉሥ ይህንን ሕዝባዊ ዕድገታቸውን ለመግታት ያደረገው ሙከራ የዕብራውያን ሕጻናት ሳይወለዱ በሆድ ውስጥ እንዲጨነግፉ ማድረግ እንደነበር ኦሪት ዘጸት ምዕራፍ አንድ ላይ የምናገኘው ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ ንጉሥ ሆኖ መወለዱን በመስማቱ የደነገጠው ንጉሥ ሄሮዲስ በቤተልሔም አራጃ ያሉ ዕድሜአቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆናቸው ሕጻናትን እንዳስጨፈጨፋቸው ወንጌላዊው ማቴዎስ በስፋት ተርኮልናል( ማቴዎስ ወንጌል 2)፡፡ የሔሮዲስ ሰይፍ ሰዎችን ለማዳን ሲል በእግዚአብሔር እቅድና ፈቃድ የተወለደውን ጌታና የዘመናት ንጉሥ የሆነውን ኢየሱስን ማግኘት ባይችልም ብዙ ሕጻናትን ሕይወት ቀጥፏል፡፡
በዘመናችንም ደግሞ ሰይጣን መልኩንና አሠራሩን ቀይሮ በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጠፋቸው ልጆች ቁጥር አስደንጋጭ ነው፡፡ በክርቲያናዊ ትምህርትና በሥነ መለኮት በተለይም በስይስተማቲክ ቲዮሎጂ ቁልፍ ሰው የሆኑት ዶር ኢዩኤል አር ቢኪ ታላላቅ የዓለም ጦርነቶች ከጨረሱአቸው ሰዎች ይልቅ በውጃ ምክንያት የሚያልቁ ሕጻናት ቁር በእጥፍ ንደሚበልጥ ያትታሉ፡፡ እንደ ቢኪ ባባል እንደ አውሮፓውያን ቆጣር በ2005 ሆስፒታሎችና የጤና ጣቢዎች በሜሪካን 1.2 ሚሊዮን ውርጃ ሲያከናው በካናዳ ደግሞ ከ96 ሺህ በአከናውነዋል፡፡ በአሜሪካን ከ1973 .. ጀምሮ በካናዳ ደግሞ ከ1969 .ም ጀምሮ ከ53 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ሕጋዊ ውርጃ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በሁለቱም አገሮች ያለው የሕዝብ ብዛት 350 ሚሊዮን ሲሆን ካለው የሜሪ ሕዝብ ብዛት ጋር ሲነጻሕጋ ውርጃ የሚያቀው ቁጥር ከአጠቃላይ የሕዝቡ ቁጥር አንድ ሰባተኛ ጋር እኩል ነው፡፡ ይህም የሚሆነው እንግዲህ የሕጸናት መብት ቀዳሚ አጀንዳ በሆነባቸው ፣ የሰለጠኑና ዴሞክራት በሆኑ አሜሪካንና ካናዳን በሚመስሉ አገሮች ነው፡፡የታሪክ ምሁራንም እንደሚገምቱት የናዚ ጀርመን ጅምላ ጭፍጨፋ 6ሚሊዮን አይሁዶችን ጨምሮ ከ10-11 ሚሊዮን ነጻ ሰዎችን ፈጅቷል፡፡ ከእነዚያ መካከል አብዛዎቹ ሕጻናት ናቸው፡፡ የሚያሳዝነው ግን በውርጃ ምክንያት የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር ከዚህ ሁሉ በብዙ እጥፍ እየበለጠ መሆኑ ነው፡፡1
እንደ አሜሪካ ባሉ ሰለጠኑ አገሮች የጽንስን ሕይወት ማጥፋት ይም ጽንስ እንዲረጥ ማድግ እንደ ወንጀልም እንደ ነውርም አለመቆጠር ብቻ ሳይሆን እንደ ብት እየታሰበ ሲሆን ይህንን የሚያጎለብቱ ብዙ ሙግቶችና ጠንካራ ክርሮች እየተደመጡ መሆናቸው የጉዳዩ ተፋላሚዎች ከሆኑት ይልቅ የደጋፊዎችን መጠን እያሳደገ መጥቶአል፡፡ የምዕራባውሥርዓተ አልበኝነትን ኑሮ እንደ ሥልጣኔ የቆጠሩ አንዳንድ 3ኛው ዓለም ሕዝቦችም ይህንኑን መንገድ መከተላቸው ደግሞ በጣም አስገራሚም አሳሳቢም ነገር ነው፡፡ የምዕራቡም ሆነ ሌላው ሕዝብ በእንዲህ ዓይነት መሥመር በሳተ የልምምድ ማጥ ውስጥ እንዲዘፈቅ ያደረገው በየጊዜው የሚደመጠውና በውስጡ ክፋት የቋጠረው የምሁራንና የፈላስፋዎች አሳብ በተራው ሕዝብ አእምሮው ውስጥ ዝግ ባለ አኳኃን እየሰረጸ መምጣቱ ይሆናል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ ግዚአብሔር ቤት ቅናት ያላቸው ምሁራንና ፈላስፋዎች ንዳሉን ሁሉ መርዘኛ አስተሳብ የተሞሉም እዳሉ አካድምና፡፡
እንግዲህ ካታ ምሁራንና አጢኚዎች ባደጉት ዳሰሳ ውጃን ከግብረ ገባዊና ከህጋዊ አቅዎች /Moral and Legal aspects/ አንጻር ለመተንተን ሞረዋል፡፡ በትንተናቸውም በመንተራስ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ለመጠት ጥረዋል፡፡ ውርጃ የሕግ ተገቢነት ያለው ነውን?፣ ጽንሱ ንዳች ሕጋዊ ወይም ምግባራዊ መብት አለው ወይ?ጽንሱ ወይም ሽሉ ሰው ነው ተብሎ ከለላ ሊደረግት ይገባዋል ወይ? ሰው የመሆንስ መስፈርቱ ምንድነው? እና ርግዝናው በሥወት ሂደት ከሴት የንቁል ዘር ጀምሮ እስከ መወለድ ድ/ from Unicellular zygote to birth/የሚያሳየውን ጉልምስና እንዲረጥ የሚያስችል ንዳች ግብረ ገባዊ አግባነት አለ ወይ? የሚሉና ወዘተ ናቸው ፡፡ የብዙ ምሁራን ጥናታዊ ዳሰሳ ቀጥሎ ያሉ አስተቦችን በመተንተን የጥያቄዎችን መልስ እንድናገኝ በጥቂቱ ግዘናል፡፡
1 ውርጃ በሚመለከት ሦስት አመለካቶች
1.1 ፅንፈኛ ወግ አጥባቂ አመለካካት(Extreme conservative view) ይህንን አስተብ የሚያራምዱት ሙሉ በሙሉ የውጃ ተቃዋሚዎች ሆኑ የካቶክ ቤተክርስቲያን ግንባር ቀደም ናት፡፡ የዚህ አስተሳሰብ አራማጆች በያዙት ጠንካራ አቋም መሠረት ከሆነ ሰው ማለት በሴት ሆድ ከእቁላል ዘር ፈጠር ጊዜ ጀምሮ ያለው ማንነቱ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን አንድ ፅንስ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረ ሰው ስለሆነ (by virtue of Imago- Die) ውርጃ ሊደረግበት አይገባም ብለው ያምናሉ፡፡ የዚህ ትልቁ ጥቅም ወይም ብልጫው የሰውን ሰውነት ከሴት የእንቁላል ዘር ጀምሮ ያለ እንደሆነ አድርጎ ፊቺ የሚሰጥ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ውርጃን በፈጸም ሰውን መግደል ወይም ነፍስ ማጥፋት ነው፡፡
1.2 ጽንፈኛ ለዘበብተኘኛ አመለከካከተት(Extreme liberal view) የዚህ አመለካራማጆች ውጃን የሚደግፉ ናቸው፡፡ በእነርሱ አገላለጽ መሠረት ሰው ሰውነት የሚጀምረው ከማህፀን ከወጣ በኃላ ከዚያ ቂት ቆይቶ ነው፡፡ ስለህ ሰው ለማት ተገወቅት የውልደት ጊዜ ወይም ከዚያ በኃላ ለው አጭር ጊዜ ምናልባት እስከ አንድ ወር ድረስ ያለው ጊዜ ሲሆን ውርጃ ተገቢ መሆ አለመሆን የሚወስነው ከዚህ ንጻር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አመለካከት ችግር የተሸከመ ነው፡፡ ለምሳሌ ከመወለዱ 5 ደቂቃ በፊት በማህፀን ውስጥ ባለ ሕጻንና ከማሕጸን ከወጣ አንድ ደቂቃ በሆነው ሕጻን መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ በግልጽ ሊያስቀምጥ የሚችል አለመሆኑ ነው፡፡
1.3 መካከለኛ አመለካከት(Moderate view) ህ ከመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ይልቅ ለስላሳ የሆ አመለካከት ነው፡፡ በእህ አመለካከት መሠረት ጽንስ መ ያለበት ተገቢ ጊዜ በሥ ሕይወታዊ ዕድገት ሂደት ወቅት ነው፡፡ ይህ ጊዜ ደግሞ ከሴት እንቁላል ዘር ጀምሮ እስከ መወለድ ባለው ጊዜ ነው፡፡ ዚህ አሳብማጆች ጽንሱ ከእርግዝና ወደ ልጅነት ዝግ ባለ ሂደት ውስጥ የሚያልፍ ንድ ቁም ነገር ላይ ያለ ዘር ነው ሰው አይደለም ብለው ይሞግቱናል፡፡ እንግዲህ ይህ ማለት ከእርግዝና እስከ ልጅነት የተለያ የሰውነት(ብአዊነት) ደረጃዎች ይኖራሉ ማት ነው፡፡
ከላይ ከተመለከትናቸው በተጨማሪ ሌሎች የምናያቸው ሙግቶች ደግሞ አሉ፡: Internet Encyclopedia of Philosophy ሙግቶቹን በይከፍላቸዋል፡፡ መጀመሪያው ዋና ሥነ ሥርዓት ክርክር(Standard Argument ) ሲሆን ሁለተኛው ገላጭ የሥነ ሥርዓት ክርክር(Modifier Standard Argument) ይባል፡፡
ዋና የሥነ ርዓት ክርክር ሎገሲም Syllogism የተባለ ዝርዝር ትንበማቅረብ ውርጃን ይቃወማል፡፡
የሰውን ልጅ መግደል ክልክል ነው፡፡
ሽል የሰው ልጅ ነው፡፡
ሽልን መግደል ክልክል ነው፡፡
የሰውን ሕወት መግደል የተከለከለ ስለሆነ ሽልን መግደል በፍጹም የተከለከለ ነው የሚል አም ይዘዋል፡፡ ይህ አም ሙሉ በሙሉ ጽንፈኛ ወግ አጥባቂ ከሆነው አመለካት ጋር የሚዛመድ ነው፡፡ ኖርበርት ሆርስተር የተባሉ ውቅ የጀርመን ፈላስፋ "ሽል እንደ ማንኛውም ማለትም ደ ሌሎች ሁሉ ሙሉ ሰው ስሆነ ሽልን መግደል የተከለከለ ነው" ብለው ይከራራሉ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ሆርስተን የአእምሮ ህመምተኞችና የአካ ጉዳተኞችም እንደ ማንኛችንም ሰዎች ስለ ሆኑ ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡
ገላጭ ወይም አሻሻይ ዋና ሥነ ሥርዓት ክርክር የመጀመሪያው የሆነውን የዋና ሥነ ሥርዓት ክርክርን አሳብ በራሱ መንገድ በማሻሻል ወሰብሰብ ያለ መከራከሪያውን ያቀርባል፡፡ ሽልን በተመለከተ የሰው ልጅ Human ሚለው ቃል ፋንታ የሰው ሕይወት ዓይነት Human life formሚለውን ተክቶ ስለሚሟገት ክርክሩ የበለጠ ውስብስብ ሆነ፡፡ ይህንን አመለካከት የሚያራምዱ አካላት የሚያቀርቡት ዝርዝር ትንተና( syllogism ) እንደሚከተለው ነው፡፡
የሰውን ሕይወት ዓይነት መደል የተከለከለ ነው፡፡
ሽል የሰው ሕይት ዓይነት ነው፡፡
ሽልን መግደል ክልክል ነው፡፡
የሁለተኛው ክርክር አሳብ ውርጃን ለሚደግፉ ሁሉ ከመጀመሪያው ይልቅ የሚመች ነው፡፡ ምክንያቱም ሽል የሰውን ሕይወት የሚመስል እንጂ የሰው ልጅ አይደለምና ከለላና ጥበቃ ይደረግለት ለማለት የሚያስችል ምንም መሠረት የለንም ወደ ሚለው ድምዳሜ ያደርሳቸዋል፡፡ የዚህ ክርክር አራማጆች እንደ ያዙት አቋም ከሆነ ሰው ሰው የሚሆነው በሂደት እንጂ ከጽንስ ወቅት ጀምሮ አይደለም፡፡
ሌሎች ደግሞ ማለትም እንደነ ጃኔ እንግልሽ እና ማሪ አን የመሳሰሉት በክርክራቸው ወቅት ሰው የመሆን መስፈርት ናቸው ብለው የሚያቀርቡአቸው አሉ፡፡ መስፈርቶቹን በአምስት ምድብ የከፈሉአቸው ሲሆን እንደሚከተለው ያቀርቡአቸዋል፡ እነርሱም 1/ ስነ ሕይወታዊ የመስፈርት ምድብ ነው(Biological sector)፡፡ በዚህ መሥፈርት መሠረት አንድ ሰው ሰው ለመባል ሙሉ እጅና እግር ሊኖረው የሚገባ ሲሆን ይህም መብላትን ፣ መጠጣትንና መተኛትን ያካትታል፡፡ 2/ ሥነ ልቦናዊ የመሥፈርት ምድብ ( psychological sector) በዚህ ምድብ ውስጥ የሚጠበቀው ነገር ቢኖር የጠለቀ አስተሳሰብ፣ስሜት፣ ፍላጎት ፣ ምኞት፣ ከሌላው ጋር የመገናኘት ችሎታው Ability of communication)፣ መሣሪያን መጠቀም መቻል፣ራስን ማወቅን ሁሉ የሚያካትት ነው፡፡ በተጨማሪም በዚህ መሥፈርት ውስጥ መታወቅ ያለበት ደግሞ ሰው ሕመም ና ሥቃይ ሊሰማው ይችል እንደሆነም ጭምር ነው፡፡ 3/ ምክንያታዊ መሥፈርት ምድብ ነው ( Rational Sector)፡፡ ምክንያትን ማቅረብና ጠቅለል ያለ አሳብ መስጠት፣ማቀድና ከልምድ መማርን የሚያካትት ነው፡፡ 4 / ማህበራዊ ምድብ / social sector)፡ በማህበራዊ ምድብ ውስጥ የሚጠበቀው የአንድ ውስን ቡድንና የሌሎች ሕዝቦች አባል መሆንና እንዲሁ ሀዘንንና ፍቅርን መጋራት ናቸው፡፡ 5/ ሕጋዊ ምድብ /Legal sector/ ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚደረስ፣ውል የመፈጸም ችሎታ ና የአንድ አገር ዜጋ መሆን መቻልን ያካትታል፡፡2
እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩ አሳቦች ሰዎች የምናደርጋቸው ቢሆኑም ሰውን ሰው የሚያደርጉ ናቸው ብሎ ማመን ተገቢ የመሆኑ ጉዳይ በጣም አጠያያቂ ሆኖ ሰነበተ፡፡ ሰው እነዚህን አምስት ምድቦችን እሺ ብሎ ባይቀበልስ ሰው አይሆንም ወይ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሲሉ ሜሪ ዋሬን የተባሉ ሰው እንዲህ ብለዋል፡፡ አንድ ሰው ሰው ነኝ የሚለውን ጥያቄ በሚያነሳበት ወቅት ቢያንስ የሚከተሉትን ሁኔታዎችን ማላት አለበት፡፡ እነርሱም ንቁ መሆንንና ሕመምን የመስማት ብቃት፣ራስን የማነሳሳት እንቅስቃሴ፣እና የራስ ንድፈ አሳብ ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ ከማህፀን የወጡ ወይንም የተወለዱ ልጆች ወይም ሰዎች ሊያከናውኑት የሚችሉት ናቸው፡፡ ስለ ውርጃ በምንነጋገርበት ወቅት መታሰብ የሚገባው በሆድ ውስጥ ስላሉት እንጂ ስለ ተወለዱት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተወለዱትን ወይም ከማህፀን የወጡትን መግደል ውርጃ ሊባል ስለማይችል ነው፡፡ ያም ሆኖ አንድ ሽል ከተጸነሰ እስከ ስድስት ሳምንታት ውስጥ የአእምሮው እንቅስቃሴ እንደሚጀምር፣ ስቃይን መለየት እንደሚችል፣ድምጽ እንደሚሰማና ይህም ደግሞ በጥናት የተረጋገጠ መሆኑን ብዙዎች ያምኑበታል፡፡
ጠቅለል ስናደርገው፣ ውርጃን የሚቃወሙና የሚደግፉ የየራሳቸውን ጎራ አበጅተው የየበኩላቸውን ሙግት እየተሟገቱና የየግላቸውን መከራከሪያ እያቀረቡ መሆኑን እያየን እንገኛለን፡፡ እንደ እግዚአብሔር ሰዎች በጉዳዩ ላይ የራሳችንን አሳብ መስጠትነና የአማኞችስ እምነት ስለ ጉዳዩ ምን ይላል ? የሚለውንም ጥያቄ መመለስ ይኖርብናል፡፡ ወደዚያ ከመሄዳችን በፊት ውርጃ የተፈቀደ ነው የሚሉ ወገኖች የሚያቀርቡአቸውን መከራከሪያዎች በመገምገም ወደ ምንፈልገው አቅጣጫ እናምራ፡፡ ውርጃ ሕጋዊ ይሁን ፣ጽንስ ማቋረጥ ኃጢአት የለበትም የሚሉ የሚከተሉትን ውስን (specific ) ነጥቦችን መሠረት በማድረግ ይከራከራሉ፡፡ እስቲ እኛም ደግሞ እንገምግማቸው፡፡
  1. ሽሉ የሰው ሕይወት ( ነፍስ ) ስላይደለ መገደል/ መወረድ/ ይችላል፡፡
    በዚህ አባባል መሠረት ሽል በሂደት ሰው ወደ መሆን ደረጃ የሚደርስ እንጂ አሁን በሆድ ውስጥ እያለ ግን ሰው ወይም የሰው ነፍስ አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ዋንኛ ተሟጋች የሆኑት ጆይስ አርቶር ሲሆኑ በእሳቸው አቋም መሠረት ሽል በሰው ውስጥ ያለ የአካል ቁራጭ (ቲሹ) እንጂ የሰው ነፍስ ወደምንልበት ማንነት አልደረሰም ፡፡ ይሁን እንጂ እንደዚህ ዓይነቱ ክርክር በክርስቲያኖችና በቤተክርስቲያን አስተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ ለምሳሌ ሽልን የሚገልጹ Embryo እና Fetus የ ሚባሉ ቃላት ከግሪክና ከላቲን ቋንቋ የመጡ ሲሆን ትርጉሜውም ለጋ ( Young one ) ማለት ነው፡፡ ሳይንትስቶች ሽልን Embryo ወይም Fetus ሲሉ ስለ አንድ ሌላ ፍጥረት ለመናገር ፈልገው ሳይሆን የጽንሱን አጀማመርና ያለበትን የእድገት ደረጃ እንዲሁም የሚገኝበትን ሁኔታ ለማመልከት ነው፡፡ ለምሳሌ ሕጻን፣ ልጅ፣ አዳጊ ልጅ፣ ወጣት ፣ ጎረምሳ ፣ ጎልማሳ፣ አዋቂና አዛውንት እንደምንላቸው ሲሆን ሽሉም ቢሆን በአካላዊ ዕድገቱ ገና በጅማሬ ላይ ያለ ከመሆን በቀር እንደ ሌሎቹ ሰው እንዳይባል የሚያደርግ መሠረት የለም፡፡3 ጎልማሳውን ሰው በምንልበት መንፈስና አገላለጽ ሕጻኑንም ልጅ ሰው እንለዋለን፡፡ በሁለቱ መካከል የአካልና የእድሜ ልዩነት እንጂ የስብዕና ልዩነት የለም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከተረገዘበት /ከተፈጠረበት/ ጊዜ ጀምሮ ያለ አንድ ሽል ከተወለዱት ልጆች የሚለየው በአካል ቅርጹና በእድሜው ብቻ ነው፡፡የሰው ሰውነት የሚወሰነው በአካላዊ እድገቱ መሠረት ከሆነ ህጻን ልጅን ከጎልማሳ ጋር እኩል ሰው ለማለት አቅም ሊያንሰን ነው ማለት ነው፡፡
    ሽል ማለት በሆድ ውስጥ ያለ ግልገል ወይም ጨቅላ የሆነ ሰው ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን አንድ ሕጻን ከእርግዝናው ጀምሮ የራሱ የሆነ የዘመናዊ ሰው homo sapiens አካል ክፍል ያለው የሰው ዘር እንደ ሆነ በግልጽ የሚያሳይ የሥነ ባሕሪይ መለያ(generic code) አለው፡፡ የሕጻኑ ዲ.ኤን.. ከእናቱ የተለየ መለያ ( distinct code) ያለው ሲሆን ከእናቱ የተለየና በውስጧ በጊዜያዊነት የሚኖር ሰው መሆኑን ያመለክታል፡፡4 በሦስተኛም ደረጃ ዘመናዊ የሕክምና ዜዴ ሽሉ የሰውን ቅርጽ ይዞ እያደገ መሆኑን ያረጋግጥልናል፡፡ ለዚህም አልትራ ሳውንድ የተሰኘው መሣሪያ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ሽሉ በጣም ቀጫጫ ልጅ ቢሆንም የሆነ ጓል ወይም ጠብ ብሎ የተቀመጠ ፈሳሽ ነገር ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ የተወሳሰበና የረቀቀ ማንነት ያለው የሰው ልጅ ነው፡፡ የጥናት መረጀዎች እንደሚያመለክቱ ሽሉ ከተጸነሰ በ3 ሳምንታት ውስጥ የልብ ምቱ በመጀመር ወደ ሌሎች የሰውነት አካላቱ ደም መሠራጨት ይችላል፡፡ በ6 ሳምንታት ውስጥ የአእምሮው እንቅስቃሴ የሚጀምር ሲሆን እጁ፣እግሩ፣ክንዱ፣ቅልጥሙ በሚገባ ማደጋቸውን ከማሳየታቸውም በላይ የእግሮቹና የእጆቹ ጣቶች መሥራት የሚጀምሩት በተረገዘ በ8ኛ ሳምንት ውስጥ ነው፡፡ በመጀመሪያው የ3 ወር ጊዜ ውስጥ ሕጻኑ በሆድ ውስጥ መራገጥና መዝለል ፣ እጆቹን መጨበጥና መዘርጋት ይጀምራል፡፡ ሕጸኑ የሚያሳየው ይህን የሚመስል እንቅስቃሴ እነ ሜሪ ዋሬንነና ጃነኔ እንግሊሽ ሰው የመሆን መስፈርቶች ብለው ከሚያቀርቡአቸ በላይ አልፎ የሚታይ ነው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር አሠራርና አመራረር ላይ ካላመጽን በቀር በምንም መለኪያ ቢሆን ጽንስ ማቋረጥ የነፍሰ ግደያ ነው፡፡
  2. ሽሉ ሙሉ ሰው ሳይሆን የሌላ ጥገኛ ( dependent) ስለሆነ ውርጃን የሚከለክል አግባብ የለም፡፡
    ጆሲ አርቶር የተባሉ ተሟጋች ይህንን በጣም ለማመን በሚያስቸግር አገላለፅ እንዲህ በማለት ያቀርቡታል፡፡ ሸሉ በአንድ ሰው አካል ውስጥ ጥገኛ ሆኖ የሚኖር ቲሹ እንጂ የሰው ነፍስ የለውም፣ በጭንቅላታችን ላይ ያለ ፎፎር ቢፋቅና ብናየው በሰውነት ክፍላችን ላይ ተጠግቶ የሚኖር ቲሹ ነው እንጂ ነፍስ ያለው አይደለም፣ የሽሉም ሁኔታ ከዚህ የተለየ አይሆንም ይላሉ፡፡ የሥነ መለኮቱ ሰው ኢዩኤል ቢኪ ይህን አስተሳሰብ አጠንክረው ተፈታትነውታል፡፡ በእናትዮዋ የሆድ ከረጢት የምትኖረዋ የካንጋሮ ልጅ ካንጋሮ አይደለችም ማለት ነው? ይላሉ ዶር ቢኪ አርቶርን በመገዳደር፡፡ የሚኖሩበት ቦታና ሁኔታ ሽሉን ሰው ከመሆን አያግደውም የሚሉት ቢኪ የጆሲ አርቶር አሳብ በአደገኛ መሠረት ላይ የቆመ ነው ይላሉ፡፡ በእርግጥም የጆሲ አሳብ እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ አእምሮ ያለውንም ሰው ጭምር የሚያስቆጣና የሰውን አፈጣጠር የሚያቃልል አደገኛ አቀራረብ ነው፡፡ ሽል ከጥገኝነት ያለፈ ሌላ ማንነት ስሌለለለው በእናት ሆድ ውስጥ እያለ ሊገደል ወይም ህልውናው እንዲቋረጥ ማድረግ ይቻላል የሚል እምነት ያለው በመሆኑ እጅግ በጣም ክፉና ሰይጣናዊ አሳብ ነው፡፡ ጆሲ አርቶር የሚያቀርቡት አሳብ የሚመቻቸው በርካታ ሰዎች እንደሚኖሩ ጥርጥር የለኝም፡፡ ሽል የሌላ ሰው ጥገኛ መሆን ሰው የመሆን መብቱን ያሳጣዋል ብለን የምንደመድም ከሆነ አንድ ነገር እናስብ ዘንድ ይገባል፡፡ ሁለት ሴቶች ነፍሰ ጡር ናቸው እንበል፡፡ የአንደኛዋ ልጅ እድገቱን ሳይጨርስ ያለ ጊዜው ተወለደና ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ሙቀት ሊሰጥ በሚችል የህክምና መሣሪያ እየታገዘ ሕይወቱ እንዲቀጥል በሙቀት ክፍል ሲቀመጥ፣ የሌላይኛይቱ ልጅ ደግሞ ዘጠኝ ወሩን ቢያጠናቅቅም ገና አልተወለደም ወይም በእናቱ ማሕፀን ውስጥ ይገኛል እንበል፡፡ አንደኛው ልጅ ተወልዶአል ግን ያለ ጊዜው የተወለደ ስለሆነ በሰው ሠራሽ መሣሪያ ጥገኝነት ሥር ነው ያለው፡፡ አንደኛው ደግሞ ጊዜው ደርሶአል ግን ሳይወለድ በእናቱ ሆድ ውስጥ ያለ እድገቱን ያጠናቀቀ ልጅ ነው፡፡ የአርቶር አሳብ የትኛን ነው ሰው የሚለው​? ዕድገቱን ሳይጨርስ ተወልዶ በኢንኩበተር ውስጥ ያለውን ወይስ በእናቱ ማሕፀን ያለውን፡ እድገቱን ሳይጨርስ የተወለደውን፣ የመሣሪያ ጥገኘኛ የሆነውን መግደል ይቻለል ይሉ ይሁንን? አንዲት እናት እንዲህ ዓይነቱን ልጅ ብትገድልስ በህግ ይፈቀድላት ይሆንን? የእግዚአብሔርስ ሕግ እንዲህ ያለውን ይፈቀድ ይሆንን? ዘጠኝ ወራቱ ቢጠናቀቁም ሳይወለድ በእናቱ ማህጸን ያለው ልጅስ እንዲገደል የሚያደርግ የህግና የምግባር አግባብነት የቱ ነው? ልጁ ያለ ጊዜው የተወለደባት እናት ልጅዋን ለመግደል ጩቤ ይዛ ወደተኛበት ክፍል ብትገባስ ሐኪሞቹ ይፈቅዱላት ይሆን? በሙቀት ክፍል ያለውን ልጅ መግደል ሕገ- ወጥ ከተባለ በእናተቱ ሆድ ውስጥ ያለውን ጤናማ ልጅ መግደል እንዴት ይፈቀዳል? በትክክኛና በጤናማ ዓይን ካየነው ሁለቱም ጥገኖች ናቸው፣ ሁለቱም ልጆች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለሁለቱም ሕጋዊና መንፈሳዊ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል::
  3. ሴት በሰውነትዋ ላይ የፈለገችውን የማድረግ መብት አላት፡፡
    እንዲህ ዓይነቱ ደግሞ ሽሉን የተሸከመችው ሴት ስሆት ብትፈልግ መውለድ ፣ባትፈልግ ደግሞ የማስወረድ ሙሉ መብት የእሷ ነው የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ እስከ አሁን የምናወራው እኮ ይህንን ነው፡፡ ፅንስ እንዲቋረጥ የምታደርገው ሴቷ ናት፡፡ በእግዚአብሔር ሕግም በውርጃ ምክንያት የመጀመሪያ ተጠያቂ እናት ናት፡፡ ያገባች ልትሆን ትችላለች ያላገባች ፣ ማን ትሁን ማን እናት ናትና ቀዳሚ ተጠያቂ ናት፡፡ ሴት በሰውነቷ ላይ ሥልጣን አላት፡፡ ይሁን እንጂ ማንም በሰውነቱ ላይ ያለው ሥልጣን ግዱብ ነው፡፡ በሰውነታችን ላይ ሥልጣን ቢኖረንም ሰውነታችንን እንደፈለግነው መጉዳትና እስከ ሞት የሚያደርስ ነገር ልናደርግበት አይፈቀድልንም፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ራሱን ሊያጠፋ ሲያቅድ ብናየው ይቅርና ጥርጣሬ ቢያድርብን በሰውነቱ ላይ ሥልጣን አለው ብለን ልንተወው አንችልም፡፡ ሕግም አይፈቀድለትም፡፡ አትግደል የሚለው የአምላክ ቃል ሰው የራስንም ሕይወት እንዳያጠፋ የሚያስጠነቅቅ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ ሴት በሰውነትዋ ላይ ሥልጣን አላት ማለት ሽሉ የእናቱ ከሆነው የሰውነት አካል ክፍል አንዱ ነው ወደሚለው አሳብ የሚያመራ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሽሉ የትኛው የእናቱ አካል ክፍል ነው? ያልለተወለደው ሕፃን የልብ ምቱ የማን ነው? የእናቱ? የሽሉ የአእምሮው እንቅስቃሴ ብናይ ያ አእምሮ የማን ነው? የእናቱ? ሌላም ጥያቄ እንጠይቅ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማሪያም ወደ ኤልሳቤጥ በሄደችበት ወቅት በኤልሳበጥ ማሕፀን ያለው ፅንስ በደስታ እንደዘለለ በሉቃስ ወንጌል 144-45ላይ እናገኛለን፡፡ እዚህ ጋ በሕጻኑ /በሽሉ/ የታዩ ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛው ደስታ/ሐሴት / ሲሆን ሁለተኛው ዝላይ / ፍንደቃ/ ነው፡፡ ደስታውን የተደሰተው ማን ነው? የዘለለውስ ማን ነው? የስድስት ወር የሆነው ሽል እንጂ ኤልሳቤጥ ራስዋ አልነበረችም፡፡ እርስዋ ልጁ መደሰቱንና መፈንደቁን አረጋገጠችና ለማሪያም ነገረች እንጂ ደስታው የልጁ ነው፡፡ ኤልሳቤጥም ተደስታለች ግን የሽሉ ደስታና ፍንደቃ ከእርስዋ ደስታ የተለየ ነው፡፡ ታዲያ ጽንስ ማቋረጥ ነፍሰ ግድያ አይደለም ማለት እንችላለንን? እንግዲህ ማንኛዋም ነፍሰ-ጡር ሴት ሁለት ሰዎችን ታመለክተናለች፣ያውም ራሷንና ሽሉን፣ምክንያቱም ሽሉ ሰው ነውና፡፡
    ስለ ሰው መብት በምንነጋገርበት ወቅት ስለ አቅመ -ደካሞቹና ስለ ድምጸ- አልባዎቹም ጭምር መሆን እንዳለበት አንዘንጋ፡፡ እናት ልጅዋን የመከላከል፣ ከሞትም የመጠበቅ ኃላፊነት አለባት ፣እኛም ለአቅመ -ደካሞችና ለድምጸ- አልባዎች ዘብ የመቆምና እነርሱን የመከላከል ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንዳለብን አንዘንጋ፡፡ እናት ስለ ወለደቻቸው ብቻ በልጆችዋ ላይ የፈለገችውን ማንኛውንም ነገር የማድረግ መብት አላት ማለት ይቻላልን? ይልቁንም እናት ለልጆችዋ መስዋዕትነት የመክፈልና የመታደግ አደራ አለባት፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘው፣ ተራክቦና ተዋልዶ የግል ጉዳዮች ስለ ሆኑ ሌሎች ጣልቃ መግባት የለባቸውም የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ ይህ አባባል እውነትነት ያለው ነው፡፡ ሩካቤ ሥጋ በባልና በሚስት መካከል የሚደረግ የግል ሚስጢር መሆኑን ሁላችንም እናምናለን፡፡ በሩካቤ ስጋ ሁለት ተጋቢዎች ጥልቅ የሆነ የቅርብ ግንኙነትና ትውውቅን( deep intimacy) ይጋራሉ፡፡ ቢሆንም ሩካቤ ሥጋ ሕዝብ የሚያየውን ዋጋ ማስከተሉ ደግሞ አይቀርም፡፡ ስለዚህ ማንኛዋም ሴት በሰውነቷ ላይ ሥልጣን ቢኖራትም የሥልጣኗን ገደብ የማለፍ መብት የላትም፡፡ ሸሉን የማኖርና የመግደል ሥልጣን የእግዚአብሔር እንጂ በጭራሽ የእናቲቱ አይደለም፡፡ ሥልጣን አለኝና በብለላ ፅንሱን ብታስወርድ፣ብዙ ተጠያቂነት አለባት፡፡ አንደኛው ተጠያቂነት እግዚአብሔር የሰጣትን አደራ ያለመወጣት፣ሁለተኛ ነፍስ የመግደልና ሦስተኛው በእግዚአብሔር ሥልጣን ውስጥ እጇን የማስገባት ተጠያቂነት አለባት፡፡ እንደዚህ ያደረገች እናት በምድር ላይ የመንግሥት ሕግ ባይጠይቃትም የሥራዋን ብድራት እየተቀበለች በመጨረሻም አደራውን የሰጣት እግዚአብሔር ለሚጠይቃት ጥያቄ መልስ የምትሰጠው እርሷ ብቻ ትሆናለች፡፡ ያን ጊዜ የዛሬዎቹ አደነጋጋሪ ተከራካሪዎችን አታያቸውም፡፡ ብቻዋን በአምላክ ፊት ትቆማለች፡፡
  4. የማይፈለግ ልጅ ከመወለዱ በፊት ቢሞት ይሻላል፡፡  
    የማይፈለግ ልጅ የሚሉት ምናልባት ያልተሟላ አካል ይዞ የሚወለድ ሊሆን ይችላል፣ወይም እናቱ ስለ እርግዝና ሳታስብና ልጅ መውለድን በማትፈልግበት ወቅትና ሁኔታ ላይ እያለች የተረገዘ ልጅ ሊሆንም ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ልጅ ቢወለድ እናቱ ማሳደግ አትፈልግምና ተወልዶ ከሚሰቃይ ሳይወለድ በፊት እንዲወርድ ማድረግ የተሻለ ነው የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ወላጆች በጥልቅ ድህነት ውስጥ እያሉ ልጅ ተወልዶ ልጁም ወላጆቹም በገንዘብና በምግብ እጦት ከሚሰቃዩ ባይወለድ ለእርሱም ሆነ ለወላጆቹ ምንም ጭንቅ የለባቸውም ይላሉ፡፡ የዚህ አስተሳሰብ መሠረታዊ ችግሮች ብዙ ናቸው፡፡ አንደኛው፣ የአንድን ሰው የወደፊት እጣ ፈንታውን ሌላ ግለሰብ እንዲወስንለት ማድረግ በራሱ አደገኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሊወለድ ያለ ልጅ የሚፈለግና የማይፈለግ ብሎ ስለ ሌላው የመወሰን መብት ለማንም የለውም፡፡ ከሁሉም በላይ ሰዎች እንዲኖሩ ስላልፈለግን የመግደል መብት ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው እንዳልተሰጠን በውል ልንገነዘብ ይገባናል፡፡ ይህም የሰው መብት ጥበቃን መርህ የሚጋፋና የሚቃረን ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ እያደገ ከሄደ ዘር የማጥፋት ፍላጎት ሊጎለብት ይችላል፡፡ ሁለተኛው አሳብ ሽሉን ማንም አይፈልገውም የሚለው አስተሳሰብ በራሱ የተሳሳተ ነው፡፡ ምክንያቱም በሁሉ ሰው የሚጠላ ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ በአንዱ የተጠላው በሌላው ይፈለጋል፣አንዱ የሚፈለገውን ሌላው አይፈልገውም እንጂ በሁሉ የሚጠላ ወይም በሁሉ የሚወደድ ሊኖር አይችልም፡፡ ለምሳሌ ብዙ እናቶች ማርገዛቸውን ይጠሉና ልጅ ከተወለደ በኃላ ለልጁ ደጎች ይሆናሉ፡፡ ልጁ እንዲወለድ እናቱ አትፈልግም ማለት ደግሞ እናት ያንን ልጅ አታፈቅረውም ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ትንሰፈሰፍለታለች እንጂ፣ ካልሆነማ በውስጧ ሰብአዊነትም ሆነ ህሊና የለላተት የጌታም መንፈስ የማይገዛት ምናልባትም ነፍሰ ገዳይ የሆነው፣ የዚህ አለም አምላክ የተባለው የዲያብሎስ መንፈስ አድሮባት ሊሆን ይችላል፡፡ የሰውን የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ የሚወስነው የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት እንጂ የሰዎች የግል ምኞት ያፈለቀው ስሜት ሊሆን አይችልም፡፡ ሰዎች በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ውሳኔ ላይ እጃቸውን ማስገባት በእርሱ ላይ መድፈር ነው፡፡ እግዚአብሔር መኖርንና አለመኖርን፣ ሕይወትንና ሞትን፣መቻልንና አለመቻልን የሚወስን ሉዓላዊ አምላክና ንጉሥ ስለ ሆነ ውሳኔውን ለእርሱና ለእርሱ ብቻ እንተውለት ዘንድ ይገባናል፡፡
    በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ካሉ ትላልቅ ቤተክርስቲያናት አንዱ በሆነው የምታገለግል አንዲት ሴት በአንድ ወቅት ከአቅሟ በላይ የሆነ ነገር ገጠማት፡፡ ከባለቤቷ ጋር የተጋቡት ገና ታዳጊነታቸውን ጊዜ እንደጨረሱ ሲሆን አንድ ልጅ ብቻ እንደወለዱ ባለቤቷ ሞተ.፡፡ ልጁ ግን አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ባሕሪያት የሚታዩበት ነውና እናቱ በጣም ትቸገር ነበር፡፡ በሁኔታው እየተቸገረች ባለችበት ወቅት አንድ ቀን ምሽት ጎረምሳ ልጇ አስገድዶ ደፈራት፡፡ በጉዳዩ በጣም ልቧ ተሰብሮ እያለ ከአንድ ወር በኃላ ይባስ ብሎ ማርገዟ ይታወቃታል፡፡ በዚያን ጊዜ የምትሆነው ይጠፋትና ስታወጣ ስታወርድ፣ በእግዚአብሔርም ፊት ስታለቅስ ቆየችና ጭንቀቷን መሸከም ሲያቅታት ጉዳዩን ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዳ ለአገልጋዮች በግልጽ አጫውታ የፀሎትና የምክር ድጋፍ ማግኘት እንደለባት ተሰማትና ሄዳ ያለችበትን ሁኔታ በዝርዝር ነገረቻቸው፡፡ የልጇን መጥፎ ሁኔታ ሁሉም ስለሚያውቁ በጣም አዘኑ፣ሊያጽናኗትም ሞከሩ፡፡ ቀጥለውም እንደተሰማቸው መንፈሳዊ ምክር ለገሱላት፡፡ እንግደህ በእንደዚህ ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ላለ ሰው መንፈሳዊ ምክር መስጠት በጣም ከባድ ፈተና ነው፡፡ ለ20 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ባገለገልኳቸው ዘመናት ውስጥ ይህንን የሚያክል ከባድ ነገር ባይገጥኝም ለምክር የሚያስቸግሩ ጉዳያቸውን ይዘው እኔጋ የመጡ ብዙ ምክር ፈላጊዎች እንደነበሩና በእጅጉ የተቸገርኩባቸውን ሁኔታዎች በደንብ አስታውሳለሁ፡፡ ይህቺንም ሴትዮ እነዚያ አገልጋዮች እንዴት አድርገው እንደሚያማክሩአት ግራ ገብቶአቸው ሊሆን ይችላል፡፡ የሆነው እንዲህ ነው፡፡ የአገልጋዮቹ ምክር ለሁለት የተከፈለ ሲሆን ገምሶቹ ይህንን ኃጢአት ወደሽና ፈቅደሽ ያደረግሺው ስላልሆነ ከልጂሽ ወልደሽ ዕድሜ ልክሽን ከምታዚኚ ሕጸኑን ማስወረድ በእግዚአብሔር ዘንድ አያስጠይቂሽም ሲሉ፣ ገምሶቹ ደግሞ የለም፣  ተገድደሽ ስትደፈሪ ኃጢአቱ የአንቺ አልነበረም፣ሕጸኑን ብታስወሪጂ ግን በእግዚአብሔር ፊት በነፍሰ-ገዳይነት ትጠየቂያለሽ፡፡ ልጅሽ ሲደፍርሽና አንቺም ስታረጊዢ እግዚአብሔር ስላየ ፣ ይህንንም ሁኔታ ስለ ፈቀደ ፍርዱን ሉዓላዊ ለሆነው ለእርሱ ብቻ መተው ይኖርብናል እንጂ ጽንሱን እንዳታስወሪጂ ይሉአታል፡፡ ወጥነት ከሌለው የአገልገጋዮቹ ምክር የተነሳ ሴትዮዋ በበለጠ ጭንቅ ውስጥ ብትገባም ወደ ቤቷ ሄዳ በእግዚአብሔር ፊት በመራራ ልቅሶ አምላኳን ስትማጠን የጌታ መንፈስ ሕፃኑን እንዳታስወርድ ተናገራት፡፡ እንግዲህ ለምትወልደው ልጅ እናትም አያትም የመሆን ዕድል ሊገጥማት ነው፣ በሕብረተቡም ዘንድ ልትሳቀቅ ነው፡፡ ይህ እንዴትና ምን ያህል ከባድ እንደሚሆን መገመት ለማንም አያዳግትም፡፡ቢሆንም ሴትዮዋ ከመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ጋር ተስማማችና ሕጻኑን ወለደች፡፡.በህብረተሰቡ ዘንድ ያላትን ግምት ወደ ጎን ትታ፣የሚሰማትንም የበታችነት ስሜት ችላ ብላ ልጇና የልጅ ልጇ የሆነውን ፍጥረት ማሳደጉን ተያያዘችው፡፡ የሚገርመው ግን ያ ልጅ አድጎ እግዚአብሔር በኃይል የሚጠቀምበት አገልጋይ ሆነ፡፡ እንግዲህ ሁሉንም ልዑል ለሆነው እግዚአብሔር እንተውለት እንጂ የእርሱን ቦታ በመያዝ የራሳችንን ውሳኔ አንስጥ፡፡ እግዚአብሔር ከመጥፎና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ መልካም ነገርን ማፍለቅ ይችላልና፡፡ ውይይታችንን እዚህጋ ገታ እናድርግና ውርጃን በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱሳዊና ነገረ -መለኮታዊ ትንተና ይዘን በሚቀጥለው ክፍል እንመለስበታን፡፡

1Joel R. Beeke. Is Abortion Really so Bad?. Pasadena, California: Chapel Library,2011 pp.1-3
2Jane English. Abortion and the Concept of a Person.1984, p.153.
3Joel R Beeke , Is Abortion Really  So Bad?, p.4
4Ibid.,p.5

No comments:

Post a Comment