Sunday, February 16, 2014

ምድራችሁን እፈውሳለሁ ( ክፍል ሁለት)


ከፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ
ባለፈው እግዚአብሔር አምላክ ምድራችንን እንደባረካትና ምድሪቱም እግዚአብሔር የሰጣትን በረከት በአግባቡ መጠቀም እንድትችል ከጌ ዘንድ ፈውስ እንደሚያስፈልጋት ብዙ ተነጋገረንበታል፡፡ አሁን ደግሞ ምድራችን ፈውስን እንድታገኝ ልናደርግ የሚገባንን መሠረታዊ ነገሮች በዚህኛው የጽሑፍ ክፍል እንመለከታለን፡፡ ከዚያ በፊት ግን ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እናነባቸው ዘንድ እጋብዛችኋለሁ(2ኛ ነገሥት 2 19- 22 እና 2 ዜና 711-14 )  
ቃሉ እንዲህ ይላል፡
የከተማይቱም ሰዎች ኤልሳዕን ፡- እነሆ ጌታችን እንደምታይ የዚህች ከተማ ኑሮ መልካም ነው ፣ውሃው ክፉ ነው፣ ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች አሉት፡፡ እርሱም፡- አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ ጨውም ጭምሩበት አለ፣ ያንን አመጡለት፡፡ ውሃውም ወዳለበት ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና ፡ እግዚአብሔር እዲህ ይላል፡- ይህንን ውሃ ፈውሼዋለሁ፣ ከዚህም በኃላ ሞትጭንገፋ አይሆንበትም አለ፡፡ ኤልሳም እንደተናገረው ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል፡፡ 2 ነገ.219-22
ሰለሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት ረሰ፣ በእግዚአብሔር ቤትና በራሱ ቤት ይሠራው ዘንድ በልቡ ሰበውን ሁሉ አከናወነ፡፡ እግዚአብሔርም ለሰለሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው፡- ጸሎትህን ሰምታለሁ፣ይህንንም ሥፍራ ለራሴ ለመሥዋእት ቤት መርጫለሁ፡፡ ዝናብ እዳይወርድ ሰማያቱን ዘጋ፣ወይም ምድሪቱን የበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው፣ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድድ ፣ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢፀልዩ ፣ ፊቴን ቢፈልጉ፣ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ ፣ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፣ ኃጢአታቸው ይቅር እላለሁ፣ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ፡፡ 2 ዜና 714-
እነዚህን ሁለት መለኮታዊ ፈውስ የሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ይዘን እግዚአብሔር አምላክ እንዴት አድርጎ ምድርን እንደሚፈውስና እኛም እንደ አማኞች ልናደርገው የሚገቡ ቁልፍ አሳቦችን ከዚህ አንማራለን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለእኛ የሚሰጠን የሥጋ ፈውስ ብቻ ሳይሆን የምድርንም ፈውስ ጭምር ነው፡፡ እርሱ በመለኮታዊ ሥልጣኑ ምድርን ይፈውሳል፣ አየርን ይፈውሳል፣ ውሃን ይፈውሳል፣ የሰውን ሥጋ ይፈውሳል፣ ሁሉም ፈውስ በእርሱ እጅ ነው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ ባገለገለበት ጊዜ የኢያሪኮ ከተማ ለኑሮ እጅግ የምትመች እንደሆነች ነዋሪዎቿ ይመሰክሩ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር መልካምና የተሻለ ቢሆንም ከውሃው ጨዋማነት የተነሳ የምድሪቱ ፍሬ መጨንገፉ ደግሞ መልካሙን ነገር ሁሉ አበላሸ፡፡ ፈሬዋ ይጨነግፋል ሲባል ምን ማለት ነው፡፡ የተዘራው ይበቅላል ግን ካበበ በኋላ ይረግፋል ፣ ፍሬን ሊበሉ ሲሉ ይጠወልጋል፤ ሕዝቡ የሮማኑን፣ የወይራውን፣ የወይኑን እንዲሁም የሌሎችንም ፍሬ ለመብላት ናፍቆ ባለበት ወቅት እየደረሰ ያለው ፍሬ ይጠወልግና ውጤት አልባ ይሆንባቸዋል ማለት ነው፡፡ መጨንገፍ ማለት ደግሞ የተፀነሰው ሳይወለድ ሞተ ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በሕዝብ ላይ የወደቀ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሆነ ከፍተኛ ፈተና ነው፡፡ የዚህ መፍትሔ ያለው በእግዚአብሔር እጅ እንጂ በሰው ዘንድ አይደለም፡፡ የሰለጠኑ ታላላቅ መንግሥታት ለዚህ መፍትሔ ሊያመጡ አይችሉም፡፡ ጭንገፋን ከምድር ላይ ሊያስወግድ የሚችል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
2ኛ ዜና 711-14 ለውን ክፍ ስንመለከት እግዚአብሔር ምድርን ለመፈወስ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እንግዲህ እግዚአብር በቀጥታ ምንም ቅደመ ሁኔታ ሳይፈልግ የሚያደርጋቸው የእርሱ ሥራዎች ቢኖሩም አንድ ነገር ለማድረግ የሕዝቡን ወደ እርሱ የመመለስ ሁኔታና ከእርሱ ጋር መጣበቅን የሚፈልግባቸው ብዙ መንገዶች መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ እርሱ እኛን ተደግፎ የሚሠራ አምላክ አይደለም፡፡ ለብቻው የወደደውን መሥራት ይችላል፡፡ አሁን ግን ታመመቺውን ምድር ለመፈወስ የሕዝቡን ሁኔታ ለማየት ፈለገ፡፡ ካነበብነው ክፍል የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት
1. በምድር ላይ ደዌ አለ(ምድር ታማለች)፡፡
ይህ ደዌ የሰው አካል የታመምበት ሳይሆን ምድር የምትታመምበት ነው፡፡ ምድር በብዙ መንገድ ትታመማለች፡፡ ከመታመሟ የተነሳ ፍሬ ይጨነግፋል በውስጧ ለሚነኖረው ተንቀሳቃሽ ሁሉ የሚሆን ፍሬ ከማፍራት ጋር እሾኽና ሜኬላ ታበቅላለች፡፡ እግዚአብሔር እፈውሳታለሁ የሚለው መታመሟን ስለ አየ ነው፡፡ የእግዚአብርን ቃል በዘፍጥረት 69-12 ባለው ክፍል ምድር መበላሸቷን ይገራል፡፡ ይህ ማለት እንግዲህ ቀደም ሲል መልካም የነበረች በኋላ ግን መልኳን ያጣች ሆነች ማለት ነው፡፡ ይህቺ ምድር በአንድ ወቅት እግዚአብሔር ሲያያት መልካምና ውብ ነበረች፡፡ እግዚአብሔር በፈጠራቸው ጊዜ ሰማይና ምድር በፊቱ ያማሩ ነበሩ(ዘፍ. 14101218212531)፡፡ በዘፍጥረት ምዕራፍ ስድስት ላይ ስናነብ  እግዚአብሔር ምድርን እንደ ገና ሲያያት እንደ ቀድሞው በፊቱ መልካም ሆና አላገኛትም፡፡በምዕራፍ አንድ እንደምናየውና መልካምም ሆና እንደተገኘችበት ሁኔታ አልቀጠለችም፡፡ ቃሉ እንደሚናገር እግዚአብሔር ምድርን አየ፣እነሆ ተበላሸች ይላል፡፡ ሰማይንና ምድርን ፣ በውስጣቸው ያለውንም ሁላ በራሱ እቅድ የሠራው እግዚአብሔር የምድርቱን መበላሸት በሚይበት ወቅት ምን ያህል እንዳዘነ ለመገመት ያስቸገራል፡፡ ምድር ለምን ተበላሸች ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሰው መንገዱን በምድር ላይ ስላበላሸ ነው፡፡ እግዚአብሔር በራሱ መልክና አምሳል የፈጠረው ሰው ላይ አኗኗሩን ፣ ሕይወቱንና፣ ምግባሩን ስላበላሸ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ምድር ተበላች፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፣ ምድር በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸች፣ምድር ግፍን ተሞላች፣እግዚአብሔርም ምድርን አየ፣ እነሆ ተበላሸች፣ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበረና፡፡ 

ቅዱሳን ሁላችን እስቲ ቆም እንበልና አንድ ነገር እናስብ፡፡ እግዚአብር ሰውን ሲፈጥር እኮ ከሰው አንድ የጠበቀው ነገር ነበር፡፡ ያውም ምድርን እንዲያበጃትና እንዲጠብቃት ነው፡፡  አምላክ ለሰው ይህቺን ምድር የመንከባከብ፣ ዋስትና የመስጠት፣ መልኳም እንዳይበላሽ የመጠበቅ ኃላፊነት ሰጥቶት ነበር፡፡ ይህ ለሰው ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትልቅ ኃላፊነት ነው፣ አደራም ጭምር ነው፡፡ ይህንን ኃላፊነት ከእግዚአብሔር የተቀበለው ሰው ግን ምድርን ከሚያበጃት ይልቅ አበላሽቶ ተገኘ፡፡ ለምን ቢባል ሰው ራሱ ስለ ተባላሸና መንገዱን ስላበላሸ ምድርንም ማበላሸት እንጂ ማሳመርና ማበጀት አልቻለምና አበላሻት፡፡
ዛሬ ምድር ብቻ አይደለችም የተበላሸቺው፣ ይልቁንም በምድር ላይ ጨውና ብርሃን እንድትሆን እግዚአብሔር ያስቀመጣት ቤተ ክርስቲያንም  እየተበላሸች ናት፡፡ ይህንን ስል ብዙዎችን ሊስቆጣ እንደሚችል ሳልጠራጠር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እየተበላሸት ናት ሲባል ሕንጻዋ አርጅቷል ማለታችን እንዳይደለ በጣም ግልጽ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ቅድስና፣ የአምልኮ ሥርዓት፣ የምዕመናን መንፈሳዊ ሕይወት፣ በአማኞች መካካል ያለው የእርስ በርስ አንድነትና ፍቅር፣ ክርስትያናዊ ጋብቻና የቤተሰብ ሕይወት፣ ሁሉ መጽፍ ቅዱሳዊ መልኩን እስክለቅ ድረስ መበላሸቱን ሊክድ የሚችል ማን ነው? ቤቱን እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከሾማቸው እረኞች አንዳንዶቹ አካሄዳቸውን ስላበላሹ ምእመናንም የእነርሱን መንገድ ተከተሉ፣ ቤቱ እየተበላሸ ሄደ፡፡ ፊቺን የሚቃወም ጠፋ፡፡ ይባስ ብሎ ፈት ዘማሪያንና መጋቢያን፣ ፈት የሆኑ ሐዋሪያት ተብየዎችም አሉን፡፡ መቼም ቢሆን ትዳርን የፈታ ከእግዚአብሔር ቤት ይውጣና ይጥፋ የሚል ትምህርት የለም፡፡ ማንም በኃጢአቱ  ቢናዘዝና ወደ እግዚአብሔር ቢመለስ ይቅርታን ያገኛል፡፡ አገልጋይነትና መሪነት ግን ምሳሌነትን የሚጠይቅ ስለሆነ በተቻለ መጠን ራሳቸውን በቅድስና የጠበቁ  መሀሆነን ይጠበቅባቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ ፣ ከነገድ፣ ከቋንቋ ከዘር ዋጅቶ የአባቱ መንግሥት ካህናት እንዳደረገ ለመስበክ በተጠራች ቤተ ክርስቲያን ዘረኝትና ጎሰኝነት ንግሶባታል፡፡ ይህቺን ቤተ ክርስቲን ያበላሻት ማነው? ሰይጣን ይሆንን? ምናልባትም እርሱ ነው ይባል ይሆናል፡፡ ግን ሰይጣን ብቻ አይደለም ፣ መሪዎች ካልናቸው መካከል ብዙዎቹ ለዚህ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሳ በምድር ላይ ፈውስ ንድታመጣ የምትጠበቅ ቤተ ክርስቲያን ራሷ በዓለም ገመድ ተጠላልፋ እየወደቀች ናት፡፡ ሰው ራሱ ተበላሽቶ ምድርንም እንዳበላሻት ቤተ ክርሰቲያንም ራሷ ስለ ተላሸች ለተበላሸው ዓለም ፈውስን ልመጣታ አልቻለችም፡፡ እባካችሁ ወገኖች ሆይ እግዚአብሔር እየሠራ አይደለም ? ነፍሳት እየዳኑ አይደለም ወይ?፣ተአምራት እየሆነ አይደለም ሆይ? እኛም እኮ በኑሮአችን እየተባረክን ነው፣ ቤተክርስቲያናችን ምንም ችግር የለባትም አትበሉኝ፡፡ ጌታ ስለ ስሙ ሲል መዳን የሚገባቸውን እየጠራ ነው፡፡ በጨለማው ዓለም ያሉ ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ጌታ ጥቂት ሰዎችን እየተጠቀመባቸው ስለሆነ ነፍሳት እየዳኑ ናቸው፡፡ ይህ የሚገርም የመንፈስ ቅዱስ አሠራር ነው፡፡ እንደ እኛ ቢሆንማ ኖሮ የሰዎች ነጻ መውጣት በፍጹም ባልታሰበ ነበር፡፡ ሁላችንም እንደምናየውና ምስክር ልንሆን እንደምንችል በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ ጌታ እየመጡ ነው፣ አስደናቂ ተአምራቶችም እየሆኑ ናቸው፡፡ ነፍሳት ዳኑ፣ ጌታም ተጠቀመብን ማለት እግዚአብሔር በእኛ በከብሮብናል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ሲከብርብንና ሲጠቀምብን ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ካልንስ ልዩ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት የሚያሻው ችግር አለብን እንጂ፡፡ ቤቱ የጸሎት ቤት ሆኖ ሳለ ነጋዴዎች የንግድ ማዕከል አደረጉት፣ የወንደቤዎች ዋሻ አስመሰሉት፡፡ ጌታ ይህንን ሲያይ ለጊዜው ጽዋው እስከሞላ ድረስ ይታገሥ እንደሆነ እንጂ ጅራፍ ማንሳቱ ይቀራል ብዬ አላስብም፡፡ የእግዚአብሔር ቤት የጸሎትና የአምልኮ ሥፍራ ብቻ ንጂ የንግድ ቤት አይደለም ነበር፣ ክርቶስ ቤተ ክርስቲያኑን የሠራው ለብዙዎች ማምለጫ፣ መጽናኛና ማምለኪያ ቦታ እንድትሆን እንጂ የነጋዴዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር እንድትሆን አልነበረም፡፡ ዛሬ ግን እኛ የጌታን ቤተ ክርስቲያን በራሳችንና በልጆቻችን ስም እየሰየምናት የባለቤትነቱን ሥፍራ እየወሰድን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በግለሰቦች ስም የሚጠሩ ቤተክርስቲያናት በርካታዎች ናቸው፡፡ የሚኪ ቤተክርሰቲያን፣ የዳንኤል ቤተ ክርስቲያን፣ የዳዊት ቤተክርስቲያን፣ ወዘተ እየተባለ ነው፡፡ ይህ ሲባል የቤተ ክርስቲያኑ ባለቤቶች ደግሞ ሞቅ ይላቸዋል መሰለኝ እባካችሁ ቤተ ክርስቲያኑ የእኔ አይደለም የጌታ ነው፣ እኔ በጌታ ቤተ ክርስቲያን ላገለግል የተጠራሁ አገልጋይ ነኝ ፣ የቤተ ክርስቲያን ባለቤት ክርስቶስ ነው ፣ ዓይናችሁን ከእኔ ላይ አንሱና ክርስቶስን እዩ ያለ አንድም አልተሰማም፡፡ እኛ ፓተሮች ሰዎችን ለምን ወደ ክርስቶስ ማመልከት አቃተን? ብዬ ራሴን ጠየቅሁና ሁለት ነገሮች ትዝ አሉኝ፡፡ አንደኛው አሁን ሕዝባችን የሚያደርገው ዓይነት አጅብ ያጋጠመው አንድ አስደናቂ አገልጋይ ነበር፡፡ እርሱም መጥመቁ ዮሐንስ ይባላል፡፡ ይህ ሰው የብሉይ ኪዳን የመጨረሻ፣ የአዲስ ኪዳንም የመጀመሪያ ነቢይ ነበር፡፡ እርሱ አገልገሎቱን በጀመረ ጊዜ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ እየመጡ ስለ ማንነቱ ጠየቁት፡፡ አንተ ማን ነህ? መሲሁ ነህ?፣ ኤሊያስ ነህ?፣ ኤርምያስ ነህ?፣ ክርስቶስ ነህ ነቢዩ ነህ ወይ? እያሉ ጠየቁት፡፡ ዮሐንስ ግን ለሁሉም አይደለሁም የሚል መልስ ነበር የጣቸው፡፡ ሲያገለግሉ ሞቅ ያለ ጭብጨባ የሚያስደስታቸው የአሁኖቹ ፓስተሮችና ሐዋሪያት ክርሰቶስ ነህ መባል ይቅርና አገልግሎትህ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዓይነት ነው ቢባሉ እንዲያው ተኝተው የሚያድሩ እንኳ አይመስለኝም፡፡ መጥመቁ ዮሐንስ ግን ይህ ሁሉ ቢባልለትም እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል በማለት ወደ ክርስቶስ አመለከተ እንጂ በተደረገው አጅብ ተፈትኖ ለጌታው የሚገባውን ክብር ለራሱ አልወሰደም፡፡ መጋቢያንና ሐዋሪያት ራሳቸውን እላይ የሰቀሉት የመጥመቁ ዮሐንስ ዓይነት ልብ ስሌለላቸው ለመሆኑ ሥራቸው ምስክር ነው፡፡ እስቲ በጌታ ስም ልጠይቃችሁ! ለመሆኑ ሰባኪያን ከመስበካቸው በፊት ወደ መድረክ ሲወጡ በሕዝብ ጭብጨባ መታጀብን የለመዱት ለምንድነው? ሕዝቡ ሲያጨበጭብ ጭብጫውን በሞቀ ልብ ይቀበሉና ሃሌ ሉያ ያ ያ ያ….እያሉ ማንረቅ እንጂ ዝግ ባለ መንፈስ ወገኖቼ ሆይ ክብርና ጭብጨባ የሚገባው ሌላ አለ እርሱም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፣ልጁም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው መንፈስ ቅዱስም ነው ከእኔ ይልቅ እርሱ ሊከብርና ሊጨበጨብለት ይገባዋል ብለው ሕዝቡን የሚመክ ሐዋሪያ ፣ፓሮችና ዘማሪያን እነማን ናቸ? ከአሁን በኃላ ቢያደርጉልን ዕድለኞች ነን፡፡ እስከ አሁኑ ግን ሲጨበጨብላቸው እዚህ ደርሰዋል፣ ደርሰናል ልበል እንጂ እኔም ፓስተር ስለሆንኩኝ፡፡ ጉዳዩ እኔንም ይመለከተኛልና፡፡ ሌላው አሳቤ ምሳሌያዊ አገልለፅ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ አንድ ብዙ ተወዳጅነት ያተረፈ ንጉሥ ነበር፡፡ በሌላ አገር የሚኖሩ ሕዝቦች ከአገሬው ሕዝብ ይልቅ በበለጠ ከማድነቃቸው የተነሳ አምላክ ነው አሉና ያመልኩት ጀመሩ፡፡ ይህን ጊዜ ሌሎች የንጉሡ ወዳጆች ወደ ንጉሡ መጥተው ንጉሥ ሆይ እነዚያ ሰዎች እኮ አምላካችን ነው እያሉህ ነው ለምን ይህንን ተው አትላቸውም? ብለው ጠየቁት ፡፡ የንጉሡ ሲመልስ ግን ሰው ለምን ተወደደ ይባላል ኤንዲዬ አለ፡፡ መቼም ንጉሥ ነውና ከዚያ በላይ ገፍቶ መናገር ሌላ ጣጣ ስለሚያስከትል ጉዳዩ በዛው ተደመደመ ይባላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መጋቢዎቻችንና ሐዋሪያዎቻችን ለምን ይህንን ነገር መልክ አታስይዙትም ቢባሉ በእኛ ላይ የተገለጠውን ጸጋና የፈሰሰብንን ሞገስ አይተው ያደረጉት ነውና ጌታ ይክበርበት እንደሚሉ አይጠረጠርም፡፡ አሁን አሁን መደማመጥ ያልቻልንበት ያልንበት፣አንገት እያስደፋን ያለው የቤተ ክርስቲያናት መከፈት ነው፡፡ እገሌ ቤተ ክርስቲያን ከፈተ ማለት አንድ ድርጅት አቋቋመ የማለት ያህል ሆነ፡፡ በእርግጥም ደግሞ ግብር የማይከፈልበት ዳጎስ ያለ ገቢ የማግኛ መንገድ ቤተ ክርስቲያን መክፈት ነው፡፡ ስለዚህ የተጠራውም ያልተጠራውም አንድ አዳራሽ እንደ ምንም ይከራይና በየቦታው ፖስተር መለጠፍ በቂ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን መክፈት እንጂ መትከል የሚለውን ደግሞ አይሞክሩትም ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያን ተከላ የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍ ያለ ነውና፡፡ ሌሎች የለፉበትን፣ አልቅሰውና አምጠው አስተምረው ደቀ መዝሙር ያደረጉትን በምንም ይሁን በምን አማልለው ወደ ራሳቸው መጥራትን ብቻ ይመርጣሉ፡፡ በዚህን ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መንፈሰዊ ገጽታዋ ጠፍቶ የንግድ ተቋም እየመሰለች መጣች፡፡  ይሁን እንጂ ይህንን ሁሉ አልፎ ይፈውሰን ዘንድ የእርሱ ቅሬታዎች አሉን፡፡ በእርግጥ ከጌታ ጥሪ የተቀበሉና በእውነትና በጽድቅ የወንጌልን አደራ እየተወጡ ያሉ ብዙ አገልጋዮች አሉ፡፡ ታማኝ የጌታ ባሪያዎች ባሉበት ሐኬተኞችም ደግሞ እንደማይጠፉ የታመነ ቢሆንም ለጽድቅ የቆሙ የመከሩ ሠራተኞች ለመንግሥቱ መስፋፋት የሚጠቅም ሥራ የሚሠሩ እነርሱ ናቸው፡፡ ጌታም በእነርሱ ምክንያት ምድሪቱን ይፈውሳል፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ምድር ይፈውስ ዘንድ አቅም ያለው አምላክ ነው፡፡ የእኛን ዝግጅት ግን ይፈልጋል፡፡

2. በምድር ላይ ፈውስ እንዲመጣ ቤተክርስቲያን ትፈለጋለች፡፡

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው ፍቅርና አክብሮት እንዴት ታላቅ ይቅርታውም እንዴት የላቀ ነው! ሕዝቡ የቱንም ያህል ቢበላሽ እርሱን ከማያምኑት ይልቅ ሕዝቡን የፈውስ መሣሪያ ማድረጉና አብሮ ለመሥራት መፈለጉ እጅግ የሚያስደንቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ምድር እንደ ተበላሸእንድትኖር አይፈልግም ቤቱም እንደቆሸሸና ጓዳው እንደተዝረከረከ እንዲቀጥል አይፈቅድም፡፡ ይልቁን ፈውስ ሊያመጣ ይሻል፡፡ ለዚህም መሣሪያው አድርጎ የሚጠቀምበት አሁንም ሕዝቡ ነው፡፡ ሕዝቡን እንደ መሣሪያ ተጠቅሞ ሪቱንና ቤቱን ካበት በሽታ ለማላቀቅ መፍቀዱ ለሕዝቡ ትልቅ ክብር ነው ፡፡ ጌታ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ የሚለው አሳብ እርሱ ለሕዝቡ የሚሰጠው ዋጋ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የሕዝቡ ቅድስና ፣ፈርሀ እግዚአብሔር የተሞላበት ሕይወት ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚደረግ ጸሎት ፣ በምድሪቱ ላይ ፈውስን ያመጣል፡፡ የ 2ኛ ዜና 714 መልእክት የሕዝቤን ትክክለኛ ማንነት ተጠቅሜ ምድራችን እፈውሳለሁ የሚል ነው፡፡ ምድር ስትታመም በምድሩ ላይ የሚኖሩ ያመኑም ያላመኑም፣ እንስሳትና አራዊት ሁሉ ይጎዳሉ፡፡ ቢሆንም እግዚአብሔር ለምድሩ የሚሰጠው ፈውስ በዓለም ባሉ ኃያላን በኩል ሳይሆን በስሙ በተጠሩ ልጆቹ እጅ እንደሆነ ቃሉ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያን ምዕመናንና አገልጋችዮች ከዚህ ቀጥሎ ያሉ ለፈውስ የሚሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን እንመልከት፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ አምላካቸው እንደሚላቸው ሆነው ቢገኙ የእግዚአብሔር ቅጣት ከምድር ላይ እንዲከለከል ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
እግዚአብሔር ኃጢአኞችን ሲቀጣ ፣ ተፈጥሮን ያዛል፣ ከባድና የማይፈወስ በሽታ ይልካል፣ ሥጋ ለባሽንና እፅዋትን ሁሉ የሚያወድም ጨካኝ አራዊትን ይልካል፣ ወይም ደግሞ ጨካኝ ነገሥታትን ያስነሳል ወዘተ፡፡ በ2ኛ ዜና 711-14 የምናየው ይህንን ነው፡፡ በክፍሉ ከማንም ዘንድ ፈውስ የማይገኝባቸው የእግዚአብሔር ቅጣቶች ተጠቅሰዋል፡፡ ለምሳሌ
ተፈጥሮን ማዛባት፡
ዝና እንዳይወርድ ሰማትን ብዘጋ ሲል እንመለከታለን፡፡ ዝናብ ማጣት ለምድር ትልቅ ትዳሮት ነው፡፡ የዝናብ እጦት ሚሊዮኖችን ሕይወት ለሞት ሊዳርግ የሚችል ከባድ የእግዚአብሔር ቅጣ ነው፡፡ ሰማይን በመዝጋት ዝናብ የመከልከል አሊያም ሰማይን በመክፈት ዝናብን በመስጠት ምድርን ማረስረስ፣ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ የማድረግ ሙሉ ስልጣን ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ሰማይ ቢዘጋ እንኳ ከእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ አለ፡፡ 
ሥጋ የለበሰ ሁሉ መንገዱን በእግዚአብሔር ፊት ስላበላሸ እግዚአብሔር አዘነ፡፡ ሰውንም በኃጢአቱ ምክንያት ቀጣ፡፡ ሥጋ ለባሹንም ከምድር ላይ ለማጥፋት ተፈጥሮን አዛባ፣ ያውም ሰውን ጨምሮ ሌላውን ፍጥረት ሁሉ የሚያጠፋ ውሃ በመልቀቅ ነበር፡፡ ቀላያት ተነደሉ፣ 150 ቀን ያለ ማቋረጥ ከሰማይ ዝናብ ወረደ፣ በምድር ላይ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ በውሃው ምክንያት ጠፋ(ዘፍጥ.7)፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ታላቅ እንደ ሆነ እናስብ፡፤ ኢያሱ ከነገሥታት ጋራ በተዋጋ ጊዜ እግዚአብሔር ስለ እሥራኤል ሕዝብ ተዋግቶ እንደ ነበርና እሥራኤልም እንዳሸነፈ እናነባለን፡፡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የተዋጋው የበረዶ ድንጋይ በጠላት ወገን ላይ በማዝነብ ነው፡፡ ይህም ተፈጥሮን እንዳዛባ ያሳየናል( ኢያሱ 101-11)፡፡ እግዚአብሔር የተፈጥሮ ሁኔታ በእጁ ያዘ አምላክ ስለሆነ ተፈጥሮን ለሰው ልጆች ጥቅም መኖ ይሰጣል፣ ሊቀጣም ሲፈልግ የተፈጥሮን ሥርዓት ያዛባዋል፡፡ ሁሉ ከእርሱ ሥልጣን ሥር በመሆኑ የወደደውን በወደደው ሰዓት ሊፈጽም የሚችል አምላክ ነው፡፡
ጨካኝ አውሬዎችን መላክ፡፡
ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው የሚለው ቃል ይህንን ያመለክተናል፡፡ እግዚአብሔር ከተቆጣና ሊቀጣም ከተነሳ ከቅማል እስከ እባብ፣ ከአንበጣ እስከ ድብ ድረስ የእርሱ አልጋዮች መሆን ይጀምራሉ፡፡ አምላክ ፈርዖንን ከቀጣባቸው መንዶች አንዱ ቅማልና ጓጉንቸር መላክ ነበር፡፡ የእሥራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ በበደሉት ጊዜ እባብን በመላክ ቀጣቸው፡፡ ነቢዩ ኤልሳን የሰደቡት ልጆች የተሰበሩት በድብ ነው፡፡ ይህ ማለት እንግዲህ ተፈጥሮና አራዊት እግዚአብሔር ሲቆጣ የመቅጫ በትሮቹ ይሆናሉ ማለት አይለምን? እግዚአብሔር የተቆጣው ንጉሥ በቅማል ሲሸነፍ አምላኩን የታመነ ሚስኪን ስደተኛ በእንበሶች ጉድጓድ የሰላም እንቅልፍ ተኝቶ ያድራል፡፡ ልዩነቱ ያለው ለእግዚአብሔር በመኖርና ባለመኖር መካከል ባለው ማንነት ነው፡፡
በሽታን መላክ ነው፡፡
በሕዝቤ ላይ ቸነፈር፣ ረሀብ ብሰድድ የሚለው አሳብ ደግሞ በሽታን ወይም ወረሪሽን የሚያሳይ ነው፡፡ ፈውስ የሌላቸው በሽታዎች በምድር ላይ ቢከሰቱ መድኃኒት ያለው በእግዚአብሔር ሕዝብ ዘንድ እንደሆነ ጌታ ነግሮናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ከሰው አቅምና ችሎታ በላይ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ የበላይና የመፍትሔ አምላክ ነው፡፡
የምድሪቱ ፈውስ እንዲፋጠን በእግዚአብሔር ስም የተጠሩ ሕዝቦች የማያወላዳ ሚና መጫወት እንደሚኖርባቸው የንባብ ክፍላችን ያሳስበናል፡፡ እግዚአብሔር ተመለሱ የሚለው አሁንም ቢሆን የራሱን ሕዝብ እንጂ እርሱን የማያውቁትን አሬማውያንን አይደለም፡፡ እንዲህስ ከሆነ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምን ያድርግ? ቀጥሎ ከእግዚአብሔር ዘንድ የቀረቡልንን ጥሪዎች እንመልከት፡፡ እግዚአብሔርን የምናመልክ ሰዎች በእግዚአብሔር ስም የተጠራን መሆናችንን እንንዘብ፡፡ ታዲያ ልናደርግ የተገባን ምንድነው?
1. የንስሐ ጸሎት ማድረግ ፡
በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ የሚለው አንዱ መሥፈርት ነው፡፡ ይህ እጅግ መሠረታዊ ጥሪ ነው፡፡ በብሔራዊ ደረጃ ከመሪው እስከ ምዕመናን ያለ ምንም ልዩነት በንስሐ በእግዚአብሔር ፊት መውደቅ ሰውን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኘውን ፈውስ እንዲቀበል ያደርገዋል፡፡ ጸሎት መጸለይ አንድ ነገር ሆኖ፣ እግዚአብሔር ግን በፊቱ ራሳችንን አዋርደን እንድንጸልይ ይሻል፡፡ መከራና ችግር በነገሠበት ምድርና ትውልድ ሁሉ በሚጎሳቆልበት ዘመን እውነተኛ መፍትሔ እንድናመጣ በፍጹም መዋረድ ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ ይገባናል፡፡ እግዚአብሔር ልቀጣችሁ ነው ብሎ ነቢያትን የላከባቸው ሕዝቦች ከንጉሳቸው ጀምሮ እስከ ተራው ሕዝብ ድረስ ማቅ ለብሰው፣ በአንዳንድ ጊዜ በራሳቸውም ላይ አመድ ነስንሰው፣ ከምግብና ከውሃ ተለይተው የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ ሲጀምሩ እግዚአብሔርም ሊያደርግ ካለው ጥፋት ይመለሳል ማለት ነው፡፡ ለዚህ በትንቢተ ዮናስ 31-10 ናየው የነነዌ ሕዝብ ሕይወት ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት መንፈስ ቢኖርብን የእግዚአብሔር ፈውስ ይፈጥናል ማለት ነው፡፡ ዛሬ ያጣነው ግን ይህንን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ቤት ናት፡፡ የምንጸልየው ጸሎት ምን ያህል ራሳችንን በማዋረድ የሚደረግ ነው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ዛሬ መተላለፍ እንጂ መጸጸት፣ ድፍረት እንጂ ፈርሃ እግዚአብር የጠፋበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ቅርብ ጊዜ አንድ አሳፋሪና አሳዛኝ ነገር ታዝበን ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጋቢያንና የሐዋሪያትን ሹመት በተመለከተ መላው የጠፋበት ግርግር እንደ ነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ሐዋሪያ እንሾማለን ብለው የተነሱ ታላላቅ የተባሉ መሪዎች ትልቁን የእግዚአብሔርን ሕግ ሲጥሱና የእግዚአብሔርን ክቡር ስም ለሰው ሲሰጡ ተስተውለዋል፡፡ መቼም ቢሆን ከዚህ የሚበልጥ ስህተት የለም፡፡ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ከማድረግ የበለጠ ሰይጣናዊ ትምህርትና አሠራር የለም፡፡ ፍጡር የሆነውን ሰውን እንደ እግዚአብሔር ለማድረግ ከመሞከር የበለጠ ክህደት የለም፡፡ ከመጀመሪያውም ቢሆን ሰይጣን ሰውን ያሳተው በዚህ መንገድ ነው( ከዛፉ ፍሬ ብትበሉ እንደ እግዚአብሔር ትሆናለችሁ) በማለት ሔዋንን አሳታት፡፡ የሐዋሪያት ሹመት እንሰጣለን ብለው ከባህር ማዶ ወደ ኢትዮጵያ የሄዱ ታላላቆቻችን ያደረጉት ይህን የሚመስል ትርጉም የሌለው ርካሽ ነገር ነው፡፡ ይህንን ያየ ሁሉ በቃልም በጽሑፍም ተሳስታችኋል ብላቸውም ራሳቸውን ዝቅ የማድረግና የመመለስ  ልብ አላየንባቸውም፡፡ አንዳንዴ መጠኑን ያለፈና ከልኩ የዘለለ ሙቀት ሲሰማቸው ቀድመው የሚሳሳቱት ትላልቅ የተባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ በተለይም ሰዎች የሚያደናንቃቸው መሪዎች እነርሱ ያሉት ነገር ሁሉ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በጊዜው ሞቅ ስላላቸው የሠሩት ስህተት ነው እንዳንል ሙቀቱ ሲበርድላቸውና ወደ አእምሮአቸውም ሲመለሱ በጌታ ፊት ንሰሐ እንግባ፣ ሕዝባችንንም ይቅርታ እንጠይቅ አላሉም፡፡ አንተ መልከፀዴቅ ነህ ያሉትም ሰው በአደባባይ ሌባ ነው ተለ፡፡ ዘራፊ ነው አመንዝራ ነው ተባለ፡፡ መልኬፀደቅ ነህ ብለው ሲያሞካሹት የነበሩ ሌባ አይደለም መልኬጸዴቅ ነው፤ አመንዝራ አይደለም ሐዋሪያ ነው ለማለት ሳይችሉ ቀርተው ከነጭራሹ የውሃ ሽታ ሆኑ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ወደ አደባባይ ይዘን እየወጣን ያለነው አሳፋሪና አስነዋሪ ገጽታችን፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ለንስሐ ወደ ስታዲየም እንሰብሰብ ይሉናል፡፡ እነርሱ ግን የንስሐ ልብም ሕይወትም የላቸውም፡፡ ታረቁ ይሉናል እንጂ በአሜሪካን አገር የመከፋፈልና የእርስ በርስ መሰደድ ምክንያቶችና ምሳሌዎች እነዚህዎቹ የኢትዮጵያን ቅን ሕዝብ ካልታረቃችሁ እያሉ ከቤቱ እያወጡ በአደባባይ የሚያሰጡ ሰዎች ናቸው፡፡ የኢትየጵያ ኮሚኒቲ በሚበዛባቸው የአሜሪካን ከተሞች የሚያለግሉ ፓስተሮች እርስ በርሳቸው የሚያደርጉት ጦርነት እንዴት እንደሚዘገንን ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ በተለይም በዋሽንግተን ዲሲና በቨርጂኒያ አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን መጋቢዎች ምዕመናንን በመነጣጠቅ ምክንያት የሚያሳዩት ጥላቻና መቃቃር አሳፋሪና አንገት የሚያስደፋ ነው፡፡ ለክፋቱ ደግሞ ጌታ ጠራኝ የሚል ሁሉ ወንጌል ለመስበክ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ለመክፍት የሚሄደው ወደ እነዚህ ከተሞች ነው፡፡ እውነቱ ተገልብጦ የተጠራሁት ወንጌል ለመስበክ ነው መባሉ ቀርቶ እዚህ የመጣሁት ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ነው ሆነ፡፡ ትንቢት ሲነገር ወዲያና ወዲህ ሊል የሚችል በርካታ ኢትዮጵያዊ በብዛት ያለው እዚያ አካባቢ ነውና፡፡ ወንጌል መስበክ የመጀመሪያ ዓላማ ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን መክፈት ሳይሆን መትከልም ቢሆን ተከታይ ነገር መሆን ነበረበት፡፡ አሁን ግን ወንጌልን መስበክ ቤተ ክርስቲያንን መክፈት እየተከተለ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚከፈተው ደግሞ በምንም ይሁን በምን ከጎረቤት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን በማፍለስ እንጂ ሌላ መንገድ የለውም፡፡ ይህ ደግሞ የመጋቢዎችን ጥቅም እየነካ ስለሆነ ጦርነቱ እየተባባሰ ነው፡፡ ዛሬ የንስሐና የእርቅ ሐዋሪያ ነኝ እያሉ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ብቻ የንስሐና  የእርቅ ነገር የሚታያቸውን መሪዎቻችንን በጌታ ፍቅር ራሴን ዝቅ በማድረግ አንድ ነገር ለምናቸው እፈልጋለሁ፡፡ ያውም በአጠገባቸው ሆነው አንዳቸው በሌላው ጦር የሚመዝዙትን በአሜሪካን ያሉ ኢትዮጵያውያን መጋቢዎችን እንዲያስታርቁ ነው፡፡ እርሳቸውም ከሌሎች ጋር እንዲታረቁ ፣ በአንድነት መንፈስ እንዲያምኑ ነው፡፡ እኔ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ያሉ የወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት የሚያገለግሉ መሪዎችም ይህንን ጥሪ እንዲያሰሙአቸው እለምናለሁ፡፡ ምናልባት እኩያዎቻቸውን ይሰሙ ይሆናልና፡፡ የመጣ ሁሉ ወደ ፈለገው እንዲጎትት ሕዝቡን አሳልፈው ከመስጠት በፊት እንግዳውን ሰው አንተ እንዴት ነህ?፣ የምትለውንስ ራስህ ኖረህበታል ወይ ማለት ይኖርባችኋል ብዬ እጠይቃቸዋለሁ ፡፡ ከውጭ የሚመጡ ሰዎች የሚያቀርቡላቸውን ገንዘብ ሳይሆን እውነቱ የቱጋ እንዳለ መፈተሽ ይገባቸዋል፡፡ በአሜሪካን አገር ያለንን መጋቢዎች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያም ያሉ ሁሉ በእውነተኛ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጌታ እግዚአብሔር በእኛ ምን ያል ተደስቶብናል? መጠኑን እየጨመረ የመጣውን የአማኞችን ፊቺ ስናይ ልባችን ምን ይሰማዋል? ምንዝርና ፣ ዘረኝነት፣ ወገንተኝነት እያየለ መሄዱን ስናይ ምን ይሰማናል? በእርግጥ እንነጋገር ካልን አሁን የሚከፈቱ ቤተ እምነቶች ምን ለውጥ አመ? በእውነት የምንከፍታቸው ቤተ ክርስቲያና በትክክለኛ የወንጌል ራዕይ ተመስርቶ ነው? የሐሰትን ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል የተቃወሙ ነቢያትና ሐዋሪያ እነማን ናቸው? እንዲያውም ነቢያት ተብዮችን  እየጋዝን ሕዝቡ ለስህተት እንዲጋለጥ ያደረግነው እኛ ፓስተሮች አይደለምን? በቤተ ክርስቲያናትን የገነጣጠልነው እኛ መጋቢያን እንጂ ምዕመናን አይደሉም፡፡ ይህንን ስል ራሴን ከዚህ ነጻ አድርጌ ሳይሆን ሁላችንም ስህተት ሠርተናል እያልኩ ነው፡፡
እስቲ ንገሩኝ፣ የእግዚአብሔር ቅድስና ከማስከበር አንጻር ትንቢት የተናገረ ብሔራዊ ነቢይ ማን ነው? ነቢይ አገሌና እገሊት የሚባሉ ብዙ ቢኖሩንም የአብዛኛዎቹ ነቢይነት ብሔራዊ አይደለም፡፡ እንዲያው የሚበዙት የሀብታም ነጋዴዎች አሽከሮች ናቸው፡፡ ነጋዴዎቹን የሚያስደስት እንጂ በጽድቅ እንዲኖሩ የሚያስችል ትንቢት ቢናገሩ የተገጠመላቸው ጉሉኮስ እንዳይነቀልባቸው ስለ ፈሩ መልካም መልካሙን ብቻ መረርጠወው በጥንቃቄ ይተነብያሉ፡፡ በየመድረኩ ድምጻቸው ከፍ ብሎ የሚሰማው አብዛኛዎቹ እንደነዚህ ዓይነቶች ከመሆናቸው የተነሳ የወንጌል ትርጉም እየጠፋ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉ ንስሐ መግባት የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ድርሻ ነው፡፡ ራሳችንን በማዋረድ ፣ በእምባና በልብ ስብራት ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፡፡
እስከ አሁን ድረስ በየቦታው ጸሎት እየተደረገ ነው፡፡ ብዙ ወገኖቻችን በየጓዳቸው እያማጡ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በርካታ ማላጆች በቅዱስ እግዚአብሔር ፊት እየቃተቱ ናቸው፡፡ ይህ እጅግ በጣም የሚያስደስትና ተስፋንም የሚያሳየን ነው፡፡ ስለ እነዚህም ጌታን እናመሰግናለን፡፡ በተጨማሪም መላ ምዕመናንን ወደ ስታዲየም ጠርተን የንስሐ ጸሎት አድርገናል የሚሉ እንደሚኖሩ አልጠራጠርም ምክንያቱም ሲያደርጉት አይተናልና፡፡ በእርግጥ የማንሸሽገው እውነት አለ፡፡ ያውም እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ቤተ እምነቶች ውስጥ ያሉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማኞችና መሪዎችን አንድ ላይ እንዲያመልኩና አደባባይን ሞልተው እንዲታዩ አድርገዋል፡፡ ለዚህም ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ መስዋዕት አድርገወው ከፍለዋል፡፡ በአደባባይ ለእርቅ ሲሉ እንደ ሕጻን ልጅ አልቅሰዋል፡፡ ያለ መሰላቸትም ወደ ኢትዮጵያ በመመላላስ መሪዎችንና ምእመናንን ለንስሐ ጎትጉተዋል፡፡ ችግሩ ያለው እነርሱ ራሳቸው በእርቅና በአንድነት በንስሐም ሳምኑበት ሌለውን ንስሐ ግቡ በማለታቸው፣ ራሳቸው ለንስሐ የተዘጋጀ ልብም ሆነ የተሰበረ መንፈስ ሳይኖራቸው ይህንን ሁሉ በማድረጋቸው ነው፡፡ ይህንን ስናይ ሰዎቹ ምን ነካቸው ያለ ስታዲየምስ የማይታያቸው ለምንድነው? በንስሐና በእርቅ ስም ለራሳቸው ዝና ላይ ዝና ፈልገው ወይም ገንዘ ለማሰባሰብ ይሆናል ወደሚል ድምዳሜ እንድናዘነብል አያይገድደንምን? ምናልባት በየቤታችን እውነተኛ ንስሐ ብንገባ? እግዚአብሔር ወደ አደባባይ ወጡልኝ መቼ  አለ? በአደባባያችን እኛና የመሪዎቻችን አሳፋሪ ሽኩቻ እንጂ ጌታ ኢየሱስስ መቼ ታየ? በተከፈቱስ ቤተ እምነቶች ሐዋሪያቶቻችንና የቤተ ክርስቲኖች ባለ ቤቶችና ቤተሰባቸው እንጂ ለጌታ ኢየሱስ ማን ቦታ ሰጥቶት!
ምእመናን ስለ ቅድስና ተሰብከው አያውቁም፡፡ ሰባኪው ራሱ ከቅድስና ክልል ውጭ መሆኑን ካዩ ቅድስና ማለት ተራ ተረት ይሆንባቸዋል፡፡ ጉቦ ሰጪዎችና ተቀባዮች እነ ማናቸው? አማኞችስ አሉበት አይደለምን? ጉቦ የሚሰጥ ሽማግሌ ጉቦ የሚሰጠውን ምዕመን ለመገሰጽ እንዴት ሥልጣን ይኖረዋል? ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን ያገባ ፓስተር ጋብቻ እስከ ሞት ድረስ ነው እግዚአብሔር መፋታትን ይጠላል ብሎ ለማስተማር ምን አፍ አለው? አብረው የሚያገለግሉትን በቅምና በጥላቻ የሚያሳድደው ስለ ይቅርታና ስለ ፍቅር ቢሰብክና ቢያስተምር እንዴት ሊያምርበት ይችላል? እውነት እንነጋገር ካልን ገጠርና ከተማውን ሁሉ ያጥለቀለቀው የነቢይ ብዛት በእውነት ከእግዚአብሔር የተላከ ነው? ነቢያት ከሆኑ ከእግዚአብሔርም መልእክት ተቀብለው ከሆነ ወደ የሰው ቤት እየገቡ መተንበይ እውነት ከቃሉ የተገኘ ትምህርት ነው? ሐሰተኛ ነቢያት ያሉት እኮ በቤታችንና በየመድረኮቻችን ነው፡፡ ሕዝባችን የእግዚአብሔርን ቃል  ሰምተው ትክክለኛ ኑሮ እንዳይኖሩ የትንቢቱ ግርግር እንቅፋት ሆኖ የለምን? ነቢይ ነን ከሚሉት የሚበልጡቱ ትንቢት በመናገር የነቢይነት ማዕረግ የማግኘት ተስፋ ሰንቀው ነው:: ምክንያቱም ይህም ከኪስ ጋር የተያያዘ ነገር አለውና፡፡የኪስ ራዕይ የወለደው ነቢይና ሱቅ ያነቃቃው ዘማሪ የሐሰት ትምህርት ማስተላለፊያ መንገድ የእየሆነ ሕዝባችን ተንከራትቷል፣ከእውነትም ወጥቷል፡፡ በእውነት እላችኋለሁ ሁላችንም በአንድነት ተሳስተናል፡፡ ክቡር ወንጌላችን ኃይል አጥቷል፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት እንውደቅና እንመለስ፡፡ ንስሀም እንግባ! በአንድነት እንዋረድ! መቅረዙ ከስፍራው ሳይወሰድ ቶሎ ብለን እንንቃ ፣ እንቅና፣ ንሐም እንግባ! እግዚአብሔር ይፈውሰናል፡፡
2. ከከፉ መንገድ መመለስ፡፡
በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፣ የሚለውን እንቀበል ብንል ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ የሚለው እኛን ይመለከተናልን እንል ይሆናል፡፡ እኛ አማኞች ነን እንጂ ምን ክፉ ነገር አለብን ማለታችን አይቀርም፡፡ ጌታ ብትምለሱ ምድራችሁን እፈውሳለሁ ያለው እኮ እኛ ክፉ ነገር እንዳለብን አይቶ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ በክፉ መንገድ በመሄድ የሚታወቅ ነው፡፡ የእሥራኤል ሕዝብ ከግብጽ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በመንገዱ ክፉን በመሥራት አምላኩን ያስቆጣ አንደ ነበር በቃሉ የምናየው ነው፡፡ የመሳፍንትን መጽሐፍ ስናነብ የእሥራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ የሚለውን አሳብ በተደጋጋሚ ተጽፎ እናያለን፡፡ የነገስታትንም ታሪክ ስናነብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ያደረጉ ብዙ ነበሩ፡፡እግዚአብሔር ለሕዝቡ በሰጠው መመሪያም  ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ( መዝ 11 ) የሚለን ሰዎች እንደመሆናችን ክፋት ስለ ተገኘብን ነው፡፡ በነቢያትም በኩል ደግሞ ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛ አሳቡን ይተው ፣ ወደ እግዚአብሔር ይመለስ እርሱም ይምረዋል ይቅርታውም ብዙ ነውና( ኢሳ. 556) የሚለው ምክር የተሰጠው በሕዝቡ ዘንድ በደልና ክፋት ስለ ተገኘ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጴጥሮስም ለአማኞቹ ሲጽፍላቸው ክፋትምን ሁሉ ፣ ተንኮልንም ሁሉ ግብዝነትንም ሁሉ አስወግዱ ይላቸዋል(1 ጴጥ.21)፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ከመጀመሪያውም ክፋት ተገኝቶባቸዋልና፡፡ እኛም ብንሆን ከእነዚህ የተለየን አይደለንም፡፡ እንዲያውም የዘመኑ ፍጻሜ እየቀረበ ሲመጣ የሰዎች ክፋት እንደሚጨምር በቃሉ በግጽል ተቀምጧል( 2 ጢሞ.31)፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን(ቃሉ በተጻፈበት ጊዜ ማለቴ ነው) ካሉ ይልቅ የእኛ ክፋት የባሰ ስለ መሆኑ ጳውሎስ ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እየሳቱና እያሳቱ በክፋትም እየባሱ ይሄዳሉ በማለት በ 2 ጢሞ 313 ላይ ነግሮናል፡፡ በእርግጥም አሁን በዘመናችን  የምናየው ይህንን ነው፡፡ ተንኮልና ክፉ ሥራ የሚታይብን እኛ አማኞችና መንፈሳውያን የተባልን አይደለንምን? 
ክፋት ማለት የመልካም ተግባር ተቃራኒ አይደለምን?ዛሬ ከመልካም ይልቅ ክፋትን፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን ፣ ከምሕረት ይልቅ በቀልን የምናየው በእግዚአብሔር ቤት ነው፡፡ አማኞችን ከማያምኑት ልዩ የሚያደርገን በእግዚአብሔርና በሰው ፊት የሚታይ መልካም ሥራ እንጂ የመዝሙራችን ብዛት አይደለም( ማቴ 516)፡፡ መልካም ስንሠራ ሰዎች ያያሉ፡፡ ክፉንም ስንሠራ ያያሉ፡፡ መልካሙን ስንሠራ እግዚአብሔርን ያከብራሉ፣ ክፉ ስናድርግ ቢያገኙን ደግሞ ፈጣሪያቸውን ባይንቁትም  አያመልኩትም፣ ምክንያቱም የእኛ ሕይወት እነርሱን ወደ ጌታ ሊያመለክት አልቻለምና፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ጌታ ስንመሰክርላቸው የሚሉን ይህ ነው፡፡ በእናንተና በእኛ መካካል ምን ልዩነት አለ? ያው እናንተም እንደ እኛ ትዋሻላችሁ፣ ትሠርቃላችሁ፣ትጣላላችሁ፤ እንዲያውም በአንዳንድ ነገር እኛ እንበልጣችኋለን ይሉናል፡፡
ወደ ተነሳንበት አሳብ ስንመለስ ዛሬ የምድራችንን ፈውስ የምንናፍቅ ከሆነ እግዚአብሔር የሚለን ይህ ነው፡፡ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፡፡ በዚህም ደግሞ መሪዎች ምሳሌዎች በመሆን ሕዝባችንን ወደ እውነተኛ ንስሐ መምራት ይኖርብናል፡፡ ክፉ መንገድ ማለት በአጭር ቃል የኃጢአት መንገድ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ የቃል እንጂ የአሳብ ልዩነት የለበትም ፡፡ መሠረታዊ አሳቡ ከኃጢአታችሁ ተመለሱ የሚል ትዕዛዝ ነው፡፡ አማኞች ሁላችን፣ አገልጋዮች፣ ወንዶችና ሴቶች፣ መጋቢያን ወንጌላውያን ፣ ዲያቆናት መዘምራን ሁላችንም በአንድነት ወደ እግዚአብሔር መመለስ ይገባናል፡፡ በእውነት ስራችን ክፉ እየሆነ መጥቷል፡፡ ወንድሞቻችንን እያሳደድናቸው ነው፡፡ ሚስክኖችን እየገፋናቸው ነው፡፡ ክርስትናችን በገንዘብ ፈተና እየወደቀ ነው፡፡ ክርስትናችን ዘረኝነትን ማሽነፍ አልቻለም፡፡ አገልጋይነታችን በውጭ ባሉት ዘንድ ይቅርና የትም የክርስቶስን ክብር ሊያሳይ አልቻለም፡፡ አሁንም በስህተት እንዳትረዱኝ አደራ፣ ለእግዚአብሔር ራሳቸውን የለዩ ለጌታም የተሰጡ ታማኝና ልባም ልጆቹ በብዛት አሉ፡፡ እነርሱማ ስለ ሁላችንም ከእግዚአብሔር ይቅርታን እየለመኑ ናቸው፡፡ የሚሳዝነው ግን እነዚህ በጽድቅ የሚኖሩ ሰዎች በአደባባይ አይታዩም፡፡ ከእውነተኞች ነቢያት ይልቅ ሐሰተኛ ትንቢት ተናጋሪዎች ይደመጣሉ፡፡ ከትክክለኞቹ የወንጌል ሰባኪዎች ይልቅ የሐሰት ትምህርት አስተማሪዎች ብዙ አድማጮች አሉአቸው፡፡
በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያለን ሁላችንም ወደ በደልነው ጌታ እንመለስና ንስሐ እንግባ፡፡ ያሳትነውንም ሕዝብ ይቅርታ እንጠይቅ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልሆነውን ትንቢት በመናገር የሕዝቡን ሕይወት ያቀጨጫችሁ ነቢያቶች ፣ ሚስኪኑን ሕዝብ የበዘበዛችሁ ፓስተሮች፣ ቄሳውስት፣ ዋሪያት እባካችሁ ሁላችንም ወደ ጌታ እንመለስ፡፡ ሁላችንም በድለናል፡፡ በተለይም በአሜሪካን አገር ያላችሁ ትላልቅ ስም የያዛችሁ ፓስተሮች ሆይ እባካችሁ ራሳችሁን ከሰቀላችሁበት ኮረብታ ውረዱና በእግዚአብሔር ጸጋ ፊት ውደቁ ፣ ያኔ እግዚአብሔር ማንም ወደማያውረዳችሁበት ከፍታ ያወጣችኋል፡፡ እባካችሁ ገንዘብ ለመስብሰብ ካሆነ በቀር ስልጠና ለመስጠትም ሆነ ኮንፍራንስ ለማካሄድ በሚል ወደ ኢትዮጵያ አትሂዱ፡፡ በፈጠረንና ስለ ሁላችንም በተሰቀለልን ጌታ ይህንን ድርጊታችሁን ተው፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ያለውን ሕዝብ እናንተ አትመጥኑም፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያቲያን ያለባት የኮንፍራንስ ችግር አይደለም፣ ኮንፍራንስ ሰልችቶታል፡፡ ሥልጠና መስጠትም ከሆነ ምን ዓይነት ሥልጠና እንደሚያስፈልጋቸው የሚያውቁት ከሕዝቡ ጋር ያሉ እረኞች ናቸው፡፡ ሥልጠና ካስፈለገም በሕይወትም በቃልም የተመሰከረላቸው ቃሉን በእውቀትና በኑሮ መግለጥ የሚችሉ ብዙ የጌታ ልጆች አሉና ሥራውን ለእነርሱ ተውላቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ እያስከተላችሁት ያለው አደጋ ይብቃ! እባካችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እናንተ በአሜሪካን ምን አይነት ሕይወት እንደምትኖሩ አያውቅና እባካችሁ በእግዚአብሔርና በወንጌል ስም ያንን የዋህ ሕዝብ አታታልሉ፡፡ በሞተልን ጌታ ስም እለምናችኃለሁ፡፡ እስከ አሁን ድረስ የተታለለው ይብቃና ተወት አድርጉት፡፡ እናንተ ኢትዮጵያ መሄድ ከጀመረችሁበት ጊዜ አንስቶ መለያየቱ፣ ዘረኝነቱ ፣ መከፋፈሉ ባሰ እንጂ ለውጥ አላየንበትም፤የቤተ ክርስቲያናት ሽኩቻ አየለ፣አንድነታቸውም ሻከረ፣ ቤተቸን ባለቤት እንደሌለውና እንደተፈታ ማንም እየተነሳ በፊቱ የመሰለውን የሚያደርግበት ሆነ፡፡ ዛሬ በምድሪቱ የሚከፈቱ ጸሎት ቤቶች በጤናማ ዓላማና በእርስ በርስ መመካከር ቢሆን እኛም በተደሰትን ነገር ግን ባለ መቀባበል ምክንያት ስሀሆነ ብዙ ጥፋቶች አሉ፡፡ እናንተ ደግሞ (እኛ ልበልና) ይህንን አበረታታነው እንጂ አላስተካከልነውም፡፡  ምክንያቱም በአደባባይ ስለ ንስሐና ስለ እርቅ ትሰብካላችሁ፣ ከዚያ ስትምለሱ ኑሮአችሁ ሌላ ነው፡፡ ከሕዝባችን መካከል የምትኖሩትን ኑሮና የምትሰብኩትን ቃል ለማነጻጸር እንዲችሉ ብቃታቸውን ያሳደገጉ ብዙዎች አሉ፡፡ ይህንን ብቃት ያገኙት ደግሞ በእናንተ ባቀመሳችኋቸው በዓመት የ3 ቀን ስብከት  ሳይን አብረው ያሉ ምስኪም መጋቢዎቻቸውና አስተማሪዎቻቸው ባስታጠቁት የእውነት ቃል ነው፣ በጸለዩላቸውም የጸሎት ጉልበት ነው፡፡ ስለዚህ ለብዙዎቻች ያልተመቸውን ድርጊታችሁን ተውና እስከ አሁን ድረስ የበደላችሁትን ሕዝብና የከፋፈላችሁትን አብያክርስትያናትን ይቅርታ በመጠየቅ ከክፉ መንገዳችመለስ በሉ፡፡ በእናንተ ምክንያት ብዙ ነገችን ፈራርሷለል፡፡ አሁን ግን እየመጣችሁ ሕዝባችንን በፈፍርስራሽ ላይ አታስጨፍሩት፡፡ ይልቁንም የፈረሰውን ለመጠገን ለእኛና ለሕዝባችን ፋታ ስጡን፡፡ ኢትዮጵያን ሕዝብ ማገልገል ካስፈለገም ደግሞ ሌሎች ሕዝቡን ሚመጥኑ አሉና አሁን ደግሞ ተራውን ለእነርሱ ስጡና ከሕይወታቸውም እውቀታቸውም ይትረፉልን፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ይግቡና ቤታቸውን ይገንቡ፡፡ እንደ ተባለውም ብዙ አበላሽታችኋል፡፡ የቀረውን ሳታወድሙ እባካቸሁ ለሌሎች እነተኞች ለሆኑትም እድሉን ስጡአቸው፡፡ በአገር ቤትም ቢሆን እግዚአብሔር የቀባቸው አገልጋዮች በየቤተ እምነቱ አሉ፡፡ በአመራር ጥበብ የተሞሉ ድንቅ መሪዎችን ጌታ አስቀምጧል፡፡ ስለዚያ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ በእርግጥ እንደ እናንተ ከፍተኛ ገንዘብ የማሳየት አቅም የላቸውም፡፡ ይሁን እንጂ የጌታ ጸጋ በኃይል ይገለጥባቸዋል፡፡ድሮውንም ቢሆን እነርሱ የገነቡትን ነው እየመጣችሁ የምታፈራርሱት፣በነፍሳቸውም ተወራርደው የጠበቁትን መንጋ እየበተናችሁባቸው ነው፡፡
እኔ ደፋር ሰው አይደለሁም ፡፡ አባቶችን በማክበር ያደግኩ ፣ በእነርሱ ሕይወት የተቀረጽኩ ሰው ነኝ፡፡ እናንተንም እግዚአብሔር እንደ ቀባችሁ ሙሉ በሙሉ አምናለሁ፡፡ እናንተን አብዝቼ የምወድበት ፍቅሬ አሁንም የጸና ነው፡፡ ስትሳሳቱ የምነግራችሁ ሰው ግን ያስፈልጋችኃልና እኔ ካልተናገርኩማ ሌላው እንደማይገደድበት ለእናንተም ግልጽ ነው፡፡ እናንተም ደግሞ እኔን ታናሻችሁን ሰው በውስጤ ባለው የእግዚአብሔርር መንፈስ ምክንያት ተቀብላችሁ ባትሰሙኝ ታላላቆችንስ ብትሰሙአቸው ምን ምሥጋና ይኖራችኋል? ደግሜ እላለሁ በቀጣዩ ጊ ወደ ኢትዮጵያ ስትሄዱ ያፈረሳችሁትን ቤት እየዞራችሁ ካልጠገናችሁ እግዚአብሔር ያንባችኋል፡፡ ከአብያ ርስቲያናት መሪዎች ቀዳሚዎች የሆኑቱ ብዙዎች ዝምታን የመረጡ ይመስላል፡፡ ያ ደግሞ ለእናንተ መልእክት ስለሆነ እባካችሁ፡ የፈረሰውን ቤት፣ የሻከረውን አንድነት ፣ የተሰበረውንም የመሪዎች ልብ ጠግኑ፡፡ ከሰማችሁንምህ አሜሪካን አገር በአጠገባችሁ በጣም ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች አሉ፡፡ እናንተ እንደምታደርጉት አደባባይ ውጡልኝ ሳይሆን ወደ ሕዝቡ ወርደው፣ ጸሎት ቤቶችን በመሥራት የወንጌል ሥርጭቱንም አገልግሎት ለማፋጠን ድጋፍ አድርገው የሚመለሱ ታማኝና እውነተኞች አሉና ልምድም ከእነርሱ መውሰድ ያስፈልጋችኋል፡፡ እንደ እናንተ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመላልሰው የሚያገለግሉ ግን ዋጋ የሚያስከፍለውን አገልግሎት ለመስጠት ወደ ገጠሩ ክፍል ዘልቀው በመግባት የማይመቸውን የትራንስፖርት፣ የምግብና የመኝታ ሁኔታ ተቋቁመው ካገለገሉ በኋላ ወደ አሜሪካው አገልግሎታቸው የሚመለሱ የተሰጡ የኢትዮጵያ በቤተ ክርስቲያን ልጆች አሉና እስቲ ከእነርሱም ጋር ተመካከሩ፡፡ እናንተም ብትሆኑ በአገር ቤት በነበራችሁ ጊዜ በጣም ታማኖች እንደ ነበራችሁ እናውቃለን:: አሁን ግን ያ ማንነታችሁ በገንዘብና በዝና ተፈትኖ ወደቀ፡፡ ከአደባባዩ በዓላዊ ስብ(Religious Celebration ) ይልቅ እነዚህ ሰዎች ወደ ሕዝቡ ወርደው የሚያደርጉት ድጋፍና የሚሰጡት ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በእናንተ ኮንፍራሶች ተጠቅመንበታል ፣ ስም ተሰኝተንበታል፡፡ ብዙ የተሰሩ ሥራዎች ንደ ነበሩ እናውቃለን፡፡ አን ግን ጊዜ የኮንፍረንስ አይደለም፡ የአንድ ለአንድ የግል ወንጌል ሥርጭት ፣በየጓዳው የማስታጠቅ እንጂ፡፡ ወደ አደባባይ የወጣውን ወደ ቤት ተመለስ የሚል መንፈስ ይውደቅ እንደማታስብሉብኝ ተስፋ አደደርጋለሁ፡፡ አደራ!! ይህም አንዱ የማሳሳት መንገድ ነውና!  ጊዜው የኮንፈራንስይሆንበት ምክንያቱ የአደባባይ ስብሰባ ሐይማኖታዊ ንጂ መንፈሳዊና ሕይወት ያለበት መሆኑ እየቀረ ስለ መጣ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሐማኖት ስብሰባ አለ ለመባል ትቋ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምታደርገው ብቻ በቂ ነው፡፡ ሁላችን በአንድነት ከክፉ መንገዳችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ የፈረሰውን የእግዚአብሔርን ቤት እንጠግን፡፡ ያሳትናቸውን ወደ እውነተኛው መንገድ እንመልስ፡፡ ሕዝባችንን ይዘን በየጸሎት ቤታችን በእግዚአብሔር ፊት እናልቅስ! እግዚአብሔር የሚናገረኝ ይህንን ነው፡፡ ይህንን የምናደርግ ከሆነ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ምድር ይፈውሳል፡፡ ይቀጥላል፡፡



No comments:

Post a Comment