የእግዚአብሔር ጥያቄዎች
ትምህርት ቤት ከመሄድ ይልቅ አስቸጋሪውና ልዩ ትኩረት የሚሻው የፈተና ጥያቄዎችን መመለስ ነው፡፡ ተማሪዎች በፈተና አመርቂ ውጤት ለማምጣት እንዲችሉ ቀንና ሌሊት መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለዚህ የፈተናቸው ቀን ሲደርስ ያጠኑትን ለማስታወስ ሲሉ በቡድን በቡድናቸው ሆነው እርስ በርሳቸው ይወያያሉ፣ ይጽፋሉ፣ በዶርም ውስጥ ያሉት ደግሞ የእንቅልፍ ጊዜአቸውንም እንኳን በጥናት ላይ ያሳልፋሉ፡፡ በተለይም ደግሞ የፈተና ዋዜማ ለአንዳንዶች አስጨናቂ ይሆንባቸዋል፡፡ በፈተና መውደቅን ከመፍራታቸው የተነሳ ሳያስቡት የጠርሙስ ውሃ የሚያልቅባቸውም አሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ከባድ ፈተና በማምጣት የሚታወቁ አስተማሪዎች ፈተና በሚሆንበት ዕለት የአብዛኛው ተማሪ ልብ በፍርሃት ይናወጣል፡፡ ይህ ፍርሃት በምሁራን ዘንድ እዛሚኔሺን ፎቢያ ይባላል፡፡ ትርጓሜውም የአእምሮ ፍርሀት ማለት ነው፡፡
የክርስትና ሕይወት በትምህርት ሂደት ውስጥ እንዳለ ተማሪ ሕይወት ነው፡፡ በሕይወታችን አስተማሪው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን እርሱ ከእኛጋር ላደረገው ሕብረት እና ከእርሱ ለተረከብናቸው እውነቶች ሁሉ ምላሽ እንድንሰጥ የሚያቀርብልን ጥያቄዎች አሉ፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን መልስ የምንሰጥበት የሕይወት ጥያቄዎችን ሲያቀርብልን እንደ ታታሪና ጎበዝ ተማሪ ትክክለኛና ተገቢ መልስ መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ ተማሪው በፈተና ወደቀ የሚባለው ለተጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛ መልስ መስጠት ሳይችል ሲቀር አይደል? የመልሱ ትክክኛነት የሚወሰነው አስተማሪው በሚፈልገው መልኩ የመለሰ እንደሆነ ብቻ እንጂ ተማሪው ለራሱ የመሰለውን የሰጠው መልስ ከአስተማሪው ፍላጎት ጋር ካልተጣጣመ እንደማያሳልፈው ሁሉ እግዚአብሔርም በሕይወታችን ለእኛ የሚያቀርብልን የሕይወት ጥያቄዎች እርሱ በሚፈልገው መልኩ መመለስ መመለስ እንዳለብን አንዘንጋ። አስተማሪያችን እግዚአብሔር አስቸጋሪ አስተማሪ አይደለም፡፡ የእርሱ ጥያቄዎች አድካሚ ጥናት አይሹም፣ ወረቀት እንድናገላብጥ፣ እንቅልፍ አጥተን እንድንጨነቅ፣ ሌሎች ሥራዎችን ሁሉ ትተን በዚያው ላይ ብቻ እንድንመሰጥ አይጠበቅብንም፡፡ በጣም ቀላል ናቸው ግን ብዙዎች ይወድቁባቸዋል፡፡ በቀላል ፈተና የሚወድቅ ተማሪ በአስተማሪ ብቻ ሳይሆን በጓደኞቹ ሁሉ እንደሚናቅና የወደፊት ግቡም እንደሚበላሽበት ሁሉ በሕይወታችን እግዚአብሔር የሚያቀርብልን ጥያቄዎች ሁሉም በጣም ቀላል ሆነው ሳለ እያወቅንም ትክክለኛውን መልስ ትተን የማይፈለገውን መልስ ስለምንሰጥ ለዘመናት ዋጋ እንከፍልበታለን፡፡ ትውልዳችንም በእኛ ጥፋት ያልተበደረውን እዳ እንዲከፍል እናደርገዋለን፡፡ ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ የመለስን እንደሆነ ደግሞ ከእኛ አልፎ ለትውልዳችን ሁሉ የሚሆን በረከት እናገኝበታለን፡፡ ታዲያ እርሱ የሚጠይቀን ከእኛ ሊማር ፈልጎ ሳይሆን ያለንበት የሕይወት ጥራታችን ምን ያህል እንደሆነ እንድንገነዘብ ፣ ከእኛ መልስ የተነሳ ከሚመጣው በረከትም ሆነ ቅጣት ሌሎች እንዲማሩበት ፈልጎ ነው፡፡ ቀላሎቹ የእግዚአብሔር ጥያቄዎች የትኞቹ ናቸው?
እነዚህን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛቸዋለን፡፡ ጌታ ለእያንዳንዳችን ከሚያቀርብልን በርካታ ጥያቄዎች ለዛሬው የሚከተሉትን ብቻ እንመልከታቸውና መልስ እንስጥባቸው፡፡
የእግዚአብሔር ጥያቄ አንድ ፡ አንተ ወዴት ነህ ?
እግዚአብሔርም አዳምን ጠርቶ፡- ወዴት ነህ? አለው፡፡ እርሱም አለ፡- በገነት ድምፅህን ስለሰማሁ ራቁቴንም ስለሆንሁ ፈራሁ፣ ተሸሸግሁም( ዘፍጥረት 3፡10)፡፡ ይህ እግዚአብሔር ሰውን ሲጠይቅ የምናየው፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ የመጀመሪያው ጥያቄ ሲሆነ ሰው ያለበትን ሁኔታ ( Position and Condition) የማመልት እንደሆን ተደርጎ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ አዳም እግዚአብሔር ባስቀመጠው ሥፍራ ስላልተገኘና የተሰጠውንም ኃላፊነት በተገቢ ሁኔታ ስላልተወጣ እግዚአብሔር ወደ እርሱ መጣና አዳም ሆይ ወዴት ነህ የሚለውን ጥያቄ እንዳቀረበለት እንመለከታለን፡፡ ይህ በጣም ቀላል የሆነ ጥያቄ ቢሆንም በፍጹም በጥንቃቄ መመለስ የሚገባው ነበር፡፡
እግዚአብሔር አዳምን ወዴት ነህ? አለው፡፡ አዳም ግን ራቁቴን ስለሆነኩኝ ድምጽህን ስለሰማሁ ተሸሸግሁ የሚል መልስ ሰጠ፡፡ አዳም እዚህ ላይ የተነገዘበው አንደኛው ራቁትነቱን ሲሆን ሁለተኛ በገነት ውስጥ የሚሰማው የእግዚአብሔር ድምጽ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር ካስቀመጠው ሥፍራና ከእግዚአብሔር ፊት ተሸሸገ፡፡ እንደ በፊቱ በመተማመን ሊቆም አልቻለም፡፡ ምክንያቱም የወደቀበት ውድቀት ሁሉም ነገሩ ከእርሱ እንዲርቅ አደርጎታል፡፡ ባለጋራችን ዲያብሎስ እኛን ከእግዚአብሔር ለማራቅና ካለንበት ሥፍራ ለማፈናቀል ተደብቆ የሚገባበትና የሚወጣበት ብዙ የስርቆሽ በሮች አሉት፡፡ ወደ አዳምም በዚህ በር በኩል በመግባት ክፉኛ እንዳሳሳተው ከዘፍጥረት ምዕራፈ -ሳሊስ በመጀመሪያዎቹ አሥር ቁጥሮች እናነባለን፡፡ ወደ እኛ እንዳይመጣ እነዚያ በሮች ሙሉ በሙሉ የተዘጉ መስሎን እንዳንታለል፡፡ በክርስቶስ ካልተሰወርን በቀር ለሰይጣን ክፍት የሆኑ ብዙ በሮች አሁንም አሉ፡፡ሰይጣን አዳምን አሳስቶ ከጣለው በኃላ እርቃኑ ሲታይ ራሱን የሚሸሽግበት መግቢያ እንዲያጣ አደረገው፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ በሰይጣን ፈተና ተጠላልፎ የወደቀውን ምስክን ሰው እንደወደቀ ሊተወው ስላልፈለገ ከውድቀቱ ሊያነሳ ባሪያው ወዳለት ሥፍራ መጣ፡፡
እግዚአብሔር አዳምን በገነት ውስጥ ያስቀመጠበትን ዓላማ ቃሉ ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡ እግዚአብሔርም አምላክ ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በኤደን ገነት አኖረው(ዘፍ.2፡5)፡፡ አዳም ምድርን ማበጀትና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ፍጥረታትና እንስሳት ሁሉ ላይም አሳዳሪ ሆኖ ተሹሞ ነበር፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር እንዳስቀመጠው ሁኔታ ገነትን እያበጃትና እየጠበቃት አልነበረም፡፡ስለዚህ ነው እግዚአብሔር ወዴት ነህ ያለው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ መንፈስ ቅዱስ ቢጠይቀን እኛ ምን ዓይነት መልስ እንሰጥ ይሁን? አንድ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲ.ኤም. ሲ. ወደሚባለው መንደር ሄጄ ወደ ቤቴ እየተመለስኩ ወደ መገናኛ ደርሼ እስከ ስታዲየም መሄድ ስላለብኝ ክፍቷን ያለች ሀይገር አገኘሁና ወንበር ይዤ ተቀመጥኩኝ፡፡ ከሌሎች ትሳፋሪዎች ጋርም የሐይገሯን መንቀሳቀስ እየተጠባባቅን እያለ በአጠገቤ ተቀምጦ የነበረ ሰው የእጅ ስልኩ ደወለ፡፡ ስልኩን አንስቶ ምላሽ ሲሰጥ "እዚያው 7ኛ ሆነህ ጠብቀኝ አሁን እኔ ሜክሲኮ ደርሻለሁ "አለው፡፡ ይህንን ስንሰማ በእርሱ ዙሪያ ያለን ሰዎች በሁሉ ሳቅንና እንደ ቀላል አለፍነው፡፡ እንግዲህ እርሱ ያለው መገናኛ በሚባለው አካባቢ ሆኖ እያለ ለጓደኛው ሜክሲኮ ነኝ ሲለው ጓደኛው እውነት ብሎ ሊቀበለው ይችል ይሆናል፡፡ በአጠገቡ ላለን ግን አስቂኝ የሆነ የማታለያ በመሆኑ ሳቅን፣ የሰውዬውም ማንነት ( personality) ጥያቄ ውስጥ ገባ፡፡ እግዚአብሔርም እኛን የት ነህ ሲለን ኃጢአት ውስጥ እያለን በቅድስና እየኖርኩ ነኝ እንል ይሆናል፡፡ በድካምም ውስጥ እያለን በጣም እየበረታን እንደሆነ አድርገን ፣ በየትም አላስፈላጊ ሁኔታ ውስጥ ተው ባይ እንደሌለው እየተመላለስን በእግዚአብሔር ቤት በመኖሬ ታዲያለሁ ፣ ለመበየን የሚያስቸግር ነቀል ተከል የሆነ የዘላን ኑሮ እየኖርን በጌታ ሥራ ተጠምጄአለሁ ወዘተ እያለን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ምላሽ ሰው ለሚጠይቀን ጥያቄ ቢመቸውም እግዚአብሔር ከሚያቀርብልን ጥያቄ ጋር ስለማይገጥም ፈተናውን አናልፈውም፡፡
አዳም እግዚአብሔር ባስቀመጠው ሥፍራ ሊገኝ ባለመቻሉ ራሱን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ ሞከረ፡፡ እርሱና ሚስቱ በሠሩት ኃጢአት ምክንያት በእግዚአብሔር ሕልውና ፊት ላለመገኘት ራሳቸውን በኤደን ገነት ውስጥ ባሉ ዛፎች መካካል መሰወር ብቸኛ አማራጭ መሰላቸው፡፡ ሰማይናንና ምድርን እንዲሁም ግዑዝ ዓለማትን ከሠራውና ሁሉን ከሚያየው እግዚአብሔር ፊት መሰወር የማይቻል መሆኑን አልተረዱትም ፡፡ በአንድ መንገድ ይሁን በሌላ ሐጢአት ሰውን በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም እንዳይችል አቅም ታሳጣዋለች፡፡ ይህ የሰው ውድቀት ውጤት ነው፡፡ በዘመናችንም ሰዎች በኃጢአታቸው ንስሐ ከሚገቡ ይልቅ ከእግዚአብሔር ፊት መኮብለል የሚያዋጣቸው ይመስላቸዋል፡፡ ከሀዲዎች እግዚአብሔርም ኃጢአትም የለም በሚል ማምለጥ ይሞክራሉ፡፡ በድካም ውስጥ የወደቁ ደግሞ እግዚአብሔር የእኔን ጸሎት ስለማይሰማና እኔንም ስለረሳኝ እርሱን መከተል አያዋጣኝም በሚል ከፊቱ ለመኮብለል ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዴ ብዙዎች በቅዱስ ቃሉ የሚነገረውን ትተው የራሳቸውን ትምህርት በማደራጀት ከእግዚአብሔር ፊት ካለው ተጠያቂነት ለማምለጥ ብዙ ድንጋዮችን ይነክሳሉ፡፡ ርቃናቸውንም ለመሸፈን በማለዳ ጸሐይ የሚጠወልግ ቅጠል ይሰፋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ጥረት የሰውን ማንነት ለይቶ ከሚያውቀው እግዚአብሔር ፊት ለመኮብለል አያስችልም ከተጠያቂነትም አያስመልጠንም፡፡ የወደቀና በኃጢአት የተበከለ ሰው ራሱን እግዚአብሔር በሠራው ዓለም ውስጥ ገብቶ ያውም ከእግዚአብሔር ፊት ለመኮብለል መሞከር እንዴት ያለ ሞኝነት ነው!
በክርስትና ሕይወታችን እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች ይቀርቡልናል፡፡ የሰውን አስመስለን እናልፈው ይሆናል ፣መንፈስ ቅዱስን ግን ለማታለል እንችልም፡፡ ምን ይሁን ምን እግዚአብሔር ግን በስማችን እየጠራ አዳምን በጠየቀበት ሁኔታ ወዴት ነህ/ሽ ቢል መልሳችን እንዴት ዓይነት ይሆን? እግዚአብሔር ዛሬም ይጠይቀናል፡፡ ባስቀመጥኩህ ቦታ አለህን? ይለናል፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ቀላል ጥያቄ ሲሆን መልሱን ደግሞ የማያውቅ ሰው የለም፡፡ መገናኛ አካባቢ በሀይገር አውቶቡስ ውስጥ የተቀመጠ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወዴት እንደሆነ ጓደኛው ለጠየቀው በጣም ቀላል ለሆነ ጥያቄ መልሱን ያውቀዋል ግን ሲመልስ የተሳሳተ መልስ ሰጠ፡፡ የትምህርት ቤት ተማሪዎች በፈተና የሚወድቁት ጥያቄው አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው ነው፡፡ ነገር ግን በእንዲህ ዓይነት እግዚአብሔር በሚጠይቀው ቀላል ፈተና የሚወድቁት ደግሞ በእነርሱና በጠያቂው መካከል ስላለው ግንኙነት ደንታ ቢሶች ስለሚሆኑ ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱሳችን የመጨረሻ መጽሐፍ በሆነው በዮሐንስ ራዕይም እግዚአብሔር የሚያሳስበን እንደዚህ ባለ ሁኔታ ነው፡፡ እንግዲህ ከወዴት እንደወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ፣ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ ያለዚያ እመጣብሃለሁ፣ መቅረዝህንም ከሥፍራው እወስዳለሁ( ራዕ 2፡5)፡፡ ዛሬም እግዚአብሔር ወዴት ነህ/ነሽ ይለናል። ያለንበትን ትክክለኛ ሁኔታ እንንገረው። እግዚአብሔር ሰው አይደለም፡፡ ሁሉንም ያውቃል፡፡ ውድቀታችንን በግልጽ እናሳየው፣ይህንን ስናደርግ የእርሱን ርዳታ መፈለጋችን፣ ተሀዲሶንም መሻታችን እንደሆነ ይገባናል፡፡ እርሱ በፊቱ እውነተኞችና ንስሐ ፈላጊዎች እንድንሆን ይፈልግብናል፡፡
የእግዚአብሔር ጥያቄ ሁለት፡ ወንድምህ ወዴት ነው ? ምን አደረግህ?
እግዚአብሔር እኛን የሚጠይቀን ሁለተኛው ጥያቄ ስለ ወንድማችን ነው። እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፡- ወንድምህ አበል ወዴት ነው ፡ እርሱም አለ፡- አላውቅም የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን( ዘፍ.4፡9)፡፡ ይህንን ጥያቄ የተጠየቀው ደግሞ የአዳም ልጅ የነበረው ቃየን ነው፡፡ ቃየን የተጠየቀው ስለራሱ ሳይሆን ስለ ወንድሙ ስለ አበል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ቃየን ለመመለስ የማይችለው፣ የሚያስቸግርና በጣም ውስብስ ጥያቄ አይደለም፡፡ እንዲያውም የመጨረሻ ቀላል ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄውን ቀላል የሚያደርጉ ሦስት አሳቦች በጥያቄው ውስጥ ተካተዋል፡፡ አንደኛው የአቤል ስም ሲሆን ሁለተኛው በአበልና በቃየን መካከል ያለው ዝምድና ነው፡፡ አቤል ለቃየን ወንድሙ ነው፡፡ ሕጋዊ ወንድሙ ሳይሆን፣ ከዘር ግንድ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የተገኘ ወንድሙ ሳይሆን ከእናቱ ሆድ የወጣ እውነተኛ ወንድሙ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ወንድምህ አቤል ያለው ለዚህ ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ቃየን በአቤል ላይ የፈጸመው ተግባር ነው፣ "ምን አደረግህ?”(ዘፍ.3፡ቁ.10)፡፡ በጌታ በኢየሱስ ያመንን ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን ወንድማማቾች ነን፡፡ አዲስ ኪዳን በበርካታ ቦታዎች አማኞችን ወንድሞች ብሎ የሚጠራን ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ወንድማችን ምን እንደሆና የት እንዳለ በደንብ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ምን እንዳደረግንበትም ስለምናውቀው ሳንሸሽግ ለእግዚአብሔር መመለስ ይጠበቅብናል፡፡ ቃየን እነዚህን ለማወቅ ምንም ጥናት አያስፈልገውም፡፡ ለአፍታም እንኳ ማሰብ አይኖርበትም፡፡ ሁሉም ለእርሱ ግልጽ ነውና፡፡ ከስሙም ይልቅ የዝምድናውና የተፈጸመው ነገር ጉዳይ የማይደበቅና የማይረሳ ነው፡፡ ሰው ከአንድ ሆድ የወጣውን፣ በአንድ ቤትም አብሮት የሚኖረውን የእናት የአባቱን ልጅ ወንድሙን አላውቀውም ካለ በጣም ምንጡቅ ውሸታም ነው፣ ወይ ደንደሳም ከሀዲ ነው ካልሆነም የአእምሮ ችግር ያለበት ሰው መሆን አለበት፡፡ ይህንን ጥያቄ እግዘአብሔር አዳምን ጠይቆት ቢሆን ኖሮ ለአዳም ከባድ ሊሆንበት ይችላል ምክንያቱም አበል የሆነውን ሁኔታ የሚያውቀው ከአዳም ይልቅ ቃየን ነውና፡፡ ሔዋንስ ብትጠየቅ ኖሮ ብለን እናስብ! ለእርሷም ቢሆን ጥያቄው ከባድ ሊሆንባት ይችላል፡፡ እርሷም አበል ያለበትን ትክክለኛ ሁኔታ አታውቅምና፡፡ ለቃየን ግን የአበል ሁኔታ ስውር ሳይሆን በጣም ግልጽ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ወንድምህ አበል ወዴት ነው ያለውም ስለዚህ ነው፡፡ የት እንደሆነ ቃየንም በግልጽ ያውቅ ነበር፡፡ ነገር ግን ቃየን ለእግዚአብሔር ሲመልስ አላውቅም በማለት የተሳሳተ ምላሽ ሰጠው፡፡ የሚገርመው አላውቅም ማለቱ ሳይሆን የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን? ማለቱ ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ ማመጹን የሚያሳይ ነው፡፡ ወንድምህ ወዴት ነው የሚለው ጥያቄ ለቃየን ብቻ የሚቀርብ ሳይሆን ለእኛም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚቀርብልን ጥያቄ ነው፡፡ በጌታ በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን ሁላችን ስለ ወንድማችን በእግዚአብሔር ፊት መጠየቃችን አይቀርምነና ምን ምላሽ አለን?
በምዕራፉ እንደምንመለከተው ቃየንምና አቤል ሁለቱም በየተራቸው ለእግዚአብሔርር መስዋዕት ሲያቀርቡ እንመለከታለን፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የቃየንን መስዋዕት ሳይቀበል ወደ አቤል መስዋዕት መመልከቱና ወደ ቃየንን አስቆጣው። አቤል እግዚአብሔርን ለማምለክ በፊቱ የቀረበበትን ንጹህ ልቡን እግዚአብሔር ተመልክቶ መስዋዕቱንም ተቀበለ፡፡ የቃየን ልብ ለእግዚአብሔር ፍጹምና ቅን አልነበረም፡፡ አምልኮውም እግዚአብሔርን አላስደሰተውም፡፡ ስለዚህ ቃየን ተቆጣ ፣ በወንድሙም ላይ ተነሳበት፡፡ ስለዚህ ነው ይሁዳ በመልእክቱ ላይ ወዮላቸው በቃየን መንገድ ሄደዋልና ስለደመወዝም በበለዓም ስህተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፣በቆረም መቃውም ጠፍተዋል፡፡ እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ እንደ እድፍ ናቸው፡፡ እንደ እረኞች ያለ ሃፍርት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፡፡ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች ፣ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሰራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፣ የገዛ ነውራቸው አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባህር ማዕበል፣ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው ያለው(ይሁዳ 11-13)፡፡ እነዚህ ሰዎች የሀይማኖት መልክ ያላቸው ግን የሚያደርጉት እውነተኛ ያልሆነ ውሸታሞች ናቸው፡፡ ቃየን ከእነዚህ ሰዎች ጎራ የተመደበው እውነተኛ በሆነ ማንነትና በተሰበረ ልብ ወደ እግአብሔር መቅረብ ስላልቻለ ነው፡፡ ግብዞችና ዓመጸኞች እንዲሁም ውሸታሞች በእውነተኞች ላይ ይቆጣሉ፣እውነተኞችንም ያሳድዳሉ፡፡ ሲቻላቸው ሁሉ ይገድላሉ፡፡ በቁጥር 5 ላይ እንደምንመለከተው ቃየን ተቆጣ፡፡ ከመቆጣቱም ተነሳ ፊቱ መጥቆሩ ለእግዚአብሔር ታየው፡፡ ከእግዚአብሔርም ፊት ወጣና ሄደ፡፡ ወንድሙንም ወደ ሜዳ አውጥቶ ገደለው፡፡ ይህን ጊዜ እግዚአብሔር ወደ ቃየን መጥቶ ስለ ወንድሙ ጠየቀው፡፡ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? ይህ ጥያቄ በቃየን ሕይወት ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ እግዚአብሔርም የማያወቀውን ነገር አይደለም እየጠየቀ ያለው፡፡ በዚህን ጊዜ ስለ አቤል ቃየን መረጃ እንዲሰጠውም አይደለም የፈለገው፡፡ የቃየንን ልብ ነበር የፈለገው፡፡ ቃየን ስለ ወንድሙም ሆነ ስለ እግዚአብሔር ያለው የገዛ ልቡ ምን እንደሚመስል እንዲረዳና እግዚአብሔርም ያንን ልብ እንደሚያወቀው ለቃየን ለማስረዳት፣ የአመጸኝነቱንም ልብ እንዲቀይር ለመርዳት ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለቃየን ሕይወቱን እንዲያስተካክል እድል እየሰጠወው ነበር( ቁ.7) መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚያበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅህ ታደባለች አለው፡፡ ይህ ማለት እንግዲህ መልካምን እንድታደርግ አሁንም እድሉ አለህ ፣ በኃጢአት ላይ ለመሰልጠን አሁንም ሰፊ እድል አለህ እያለው እንደሆነ ቃየን አላወቀም፡፡ ቃየን ወደ እግዚአብሔር አሳብ ከሚመለስ ይልቅ በወንድሙ ላይ እንደተቆጣ ቀጠለ፡፡ ወንደሙንም ከገደለው በኃላ እግዚአብሔር ለሚጠይቀው ጥያቄ ያቀረበው ምላሽ ቀጣዩን ቅጣትና መርገም አስከተለበት፡፡ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው ሲለው ሲመልስ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እኔ ወንድሜን ገደልኩት፣ ትልቅም ኃጢአት ሠርቻለሁ፣ በዚህ አጥፍቻሁ ቢልስ ኖሮ እግዚአብሔር ምሕረቱን በእርሱ ላይ ይገልጽ ዘንድ ይችል ነበር ብለን ማሰብ የሚከብድ አይደለም፡፡ ነገር ግን ቃየን እኔ አላውቅም ብቻ ሳይሆን እኔ የወንድሜ ጠባቂው ነኝን? ብሎ የክፉ ምንነት መግለጫ የሆነውን መልሱን ሰጠ፡፡ ራሱንም ከሠራው ኃጢአት ለመሸሸግ ፣ እግዚአብሔርንም ለማታለል ሞከረ፡፡ እንዲያውም እንደመቆጣትም አደረገው፡፡ ወንድሜን የመጠበቅ ግዴታ አለብኝ? አለ፡፡ የእርሱ ጉዳይ እኔን ያገባኛልን? የሚል አቋም ይዞ ተገኘ፡፡ ቃየን በራሱ ቤት እንግዲህ እግዚአብሔር የጠየቀው ጥያቄ መጠየቅ የማይገባ ወቅቱንም ቦታውንም ያልጠበቀ ዓይነት ጥያቄ ለማስመሰልም የቃጣው ዓይነት ስሜት ተሰምቶታል፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ የሚጠይቀው ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ ነበር፡፡ ያውም "ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” "ምንስ አደረግክበት?” የሚል፡፡
እስቲ ሁላችንም ይህንን ጥያቄ ራሳችንን እንጠይቅ! እግዚአብሔር አምላክ ቃየንን በጠየቀበት ሁኔታ እኛንም ወንድምህ ወዴት ነው? እህትህ ወዴት ናት? ወንድምሽ ወይም እህትሽ ወዴት ናቸው የሚል ጥያቄ ዛሬ ቢጠይቀን እንዴት ብለን እንመልስ ይሆን? ለነገሩ እግዚአብሔር አሁን እንደዚህ እየጠየቀን ነው፡፡ ምን ብለን እየመለስን ነው? አላውቅም ነው የምንለው ወይስ ወንድሜን ገድዬዋለሁ፣ ዛሬ ከምድር ላይ ወደ አንተ ከሚጮኸው ደሙ በደምህ አንጻኝ ብለን በፊቱ እንወድቅ ይሆን? አብሮህ ሲያገለግል የነበረው ወንድምህን ምን አደረግከው? የእግዚአብሔርን መንጋ እንድታገለግሉ ጌታ እግዚአብሔር ሁለታችሁንም መርጦና ቀብቶ ሳለ አንተ በወንድምህ ላይ ያደረስክበት ወይም ያደረግክበት ምንድነው? በክርስቶስ ሞት የተገኘው የጌታም ክቡር ደም የፈሰሰለት ያ የጌታ ልጅ ወዴት ነው? ምን አደረግህበት? ምናልባት ብዙዎች የወንድም እገሌና እህት እጌሌ ነገር እኔን አይመለከተኝም እንል ይሆናል፡፡ በበቀልና በቁጣ ሆነን የገደልነው ወንድማችን ደሙ ከምድር ላይ ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፡፡ መንፈሱን ሰብረንበት ከጸጋው ያንከባለልነው ወንድማችን ያለቀሰው እምባ ወደ እግዚአብሔር ደርሷል፡፡
ይህ ቃየን ወንድሙን አቤልን የገደለበት ታሪክ ነው እንጂ እኛን አይመለተንም የሚሉ አያሌ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ እስከ አሁን ድረስ የማንንም ሕይወት አጥፍተን ተጠይቀን አናውቅም እንል ይሆናል፡፡ አብሮ የሚያመልከውንና የሚያገለግለውን ምዕመን ወንድሙን ገድሎ በመንግሥት ወታደር የተያዘና ዘብጥያ የወረደ አገልጋይ ወይም ምዕመን አለመኖሩ እርግጥ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው ይላል(1 ዮሐ.3፡15)፡፡ ቃየንም እኮ ወንድሙን የገደለወው ስለጠላው ነው፡፡ ዛሬ ከወንድምህ ጋር ተጣልተህ እርቅን እምቢ ያልክ ግን መድረኩን ሁሉ የሞላህ አገልጋይ፣ ፓስተር ፣ ዘማሪ፣ የጸሎት አገልጋይ፣ ሽማግሌ ፣ አስተማሪ የሆንከው ሆይ የእግዚአብሔር ቃል እኮ አንተን ነፍሰ ገዳይ ነህ ይልሃል፡፡ ወንድምህ ወዴት ነው እያለ በህልናህ ውስጥ ይጮሃል፡፡ መንፈስ ቅዱስን የምትሰማበትና በእርሱ የምትወቀስበት ህሊናህ ከሞተብህ ብቻ ነው ምላሹን የማትሰጠው፡፡ ሕያው ማንነት ካለህ ግን ወንድምህን በመግደልህ በደለኛ መሆንህን በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ምላሽ ልትሰጥ ይጠበቅብሃል፡፡ ወንድምህ ወዴት ነው ? ህልናቸው የታመመባቸውና ህልናቸውን የጣሉት በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረውን ሰው ሲሳደቡ፣ ሲያሳዝኑ፣ ሲበድሉ፣ ሲያስለቅሱት፣ እና ሌላውንም ሲያደርጉበት የቅንጣት ያህል አያሳዝናቸውም፣ ትንሽም ቢሆን አይጸጽታቸውም ግን ያገለግላሉ፣ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያንንም ሊመሩ ይሆናል፡፡ አንባቢ ግን እንዴት ራስህን/ሺን አይተሃል/ሻል?
ብዙዎችችን የምንጨነቀው ለምናገለግለው አገልግሎት ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን በመጀመሪያ የሚጠይቀን ወንድምህን እንዴት እያነጽክ ነው የሚለውን ጥያቄ እንጂ እንዴት ያለ ደማቅ ስብከት ሰብከህ፣ እንዴት ተሳካልህ አይለንም( ማቴ 5፡24-26)፡፡ እኛ በአገልግሎታችንና በሩጫችን ብዛት እግዚአብሔርን ልናሰደስት እንጣደፈፋለን፣ እግዚአብሔር የሚደሰተው ግን ሰው ሲድን ነው፡፡ እኛ ደግሞ የዳነውን በጥላቻችን እየገደልን ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይለናል፡፡ ወንድምህ ……ወዴት ነው? ወንድምህ ወዴት ነው? ምንስ አደረግክበት?
እኔ የወንድሜ ጠባቂው ነኝን የሚለው ዛሬም በብዙ አገልጋዮችና መሪዎቸች ዘንድ የሚወራ የቃል ርክፍካፎ ነው፡፡ ይህ አደገኛ አቋም ወደ ምዕመናንም እየተዛመተ ስለሆነ ብዙዎች እኔ ሰለ ሰው አይመለከተኝም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ልቁምና እንደ እግዚአብሔር ሰው ፣ እንደ አገልጋይ በነቢይነት መንፈስ ልናገር! የእግዚአብሔርን ክቡር መድረክ ሰዎችን ከደልናቸው በኋላ አንርገጥ! የወንድምቻችንና የእህቶቻችንን እምባ ህልናችን እያየው፣ መንፈስ ቅዱስም እነርሱንም የጠላንበትም ነፍሰ-ገዳይነታችንን እያሳየን ስለ እግዚአብሔር ምሕረት በተመረጡ ቃላት አናውጅ! ይልቁንም ምሕረት እናድርግ ፣ ምሕረትም እንቀበል አንጂ! የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በተለይም ፓስተሮች በጥላቻ መያዛችንን ምዕመናን ያያሉ፡፡ የሚያሳዝነው ግን እኛ በድፍረት ባስተማርንና ባገለገልን ቁጥር የምናፈራቸው ነፍሰ ገዳይ ቀመዛሙርት መበራከታቸው ነው፡፡ የሚማሩት እኮ ከመድረኩ ሰዎች ከሆንነው ከእኛ ነው፡፡ ለምዕመናን እያስወረስን ያለው እኮ ይህንን ነው፡፡ በምዕመናን ሕይወት ለውጥ የሚያመጣው ከአፋችን ከሚወጣው ቃል ይልቅ በፊታቸው የምናሳየው ተግባር ነው፡፡ በአፋችን ከምንናገረው በፍቅር መመላለስ ትተው የምናደርገውን ያንን የእርስ በርስ መጠላላትን የሚለማመዱት፡፡ እንዲያው እነርሱ ምን ጥፋት አለባቸው ብንል በእርግጥ በሚሠሩት ሥራ ተጠያቂዎች መሆናቸው ባይቀርም እጥፍ ድርብ ተጠያቂነት ደግሞ በእኛ ላይ ነው፡፡ ወንድምህ ወዴት ነው?
የእግዚአብሔር ጥያቄ ሦስት፡ አንተ ማን ነህ?
ያዕቆብ ግን ብቻውን ቀረ፣ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገው ነበር፡፡ እንዳላሸነፈውም ባየው ጊዜ ይጭኑን ሹልዳ ነካው፣የያዕቆብ የጭኑ ሹልዳ ጻገላ ደነዘዘ፡፡ እንዲህም አለው፡- ሊነጋ አቅላቷልና ልቀቀኝ፡፡ እርሱም ፡- ካልባረክከኝ አልለቅቅህም አለው ፣ እንዲህም አለው‹፣ ስምህ ማን ነው? (ዘፍ. 24-26)፡፡
የፈተና ወረቀት እንዳይጠፋ ተማሪው ጥቄዎችን ከመሥራቱ በፊት በወረቀቱ በላይኛው አናት በተዘጋጀው ሥፍራ ስሙን የመጸፍ ግዴታ አለበት፡፡ ቢሆንም ስምህ ማን ነው የሚል፣ ነጥብ የሚያስገኝ የፈተና ጥያቄ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ የለም፡፡ ቢኖርም ለመዝናኛ ካልሆነ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ የተማሪን እውቀት ለመለካት ለሚደረገው የመመዘኛ ፈተና አያገለግልም፡፡ በእግዚአብሔር ትምህርት ቤት ግን ውጤት የሚያስገኝ ወሳኙ ጥያቄ ነው፡፡ "ስምህ ማነው?” አንተ ማን ነህ? የሚለው ጥያቄ! የእግዚአብሔር ጥያቄ በጣም ቀላል ነው የምንለው ለዚህ ነው፡፡ በእርግጥም ቀላል ይመስላል፡፡ ዛሬም እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ ይጠይቀናል። ጥያቄው ስለ ሌላ ሰው የምንጠየቅበት ሳይሆን ስለ ራሳችን ወይም ስለ ግል ሕይወታችን የምንጠየቅበት ነው፡፡ ከፍ ብሎ እንደተቀመጠው ስምህ ማን ነው የሚለውን ጥያቄ የተጠየቀው የእሥራኤል ሕዝብ አባት የሆነው ያዕቆብ ነው፡፡ ያዕቆብ ይህንን ጥያቄ ሲጠየቅ ይህ ለሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡ አንድ ጊዜ በአባቱ በይስሐቅ ሲሆን አሁን ደግም በአምላኩ በእግዚአብሔር ተጠየቀ፡፡ አባቱ ሲጠይቀው ያዕቆብ ሆኖ ሳለ እኔ ኤሳው ነኝ አለ፡፡ ምክንያቱም የይስሐቅ ዓይኖች ከማየት ፈዝዘው ነበርና፡፡ ይስሐቅም ለኤሳው ያዘጋጀለትን በረከት ለያዕቆብ ሰጠው፡፡ ያዕቆብ እግዚአብሔር ስምህ ማን ነው ብሎ ሲጠይቀው የጥያቄውን መቅለል ሳይሆን ማየት ያለበት ለጥያቄው እርሱ ከሚሰጠው መልስ ተነስቶ በሕይወቱ ሊመጣ የሚችለውን ለውጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጥያቄዎች በጣም ቀላል ቢመስሉን ከዚህ አንጻር ደግሞ ከባዶች ናቸው፡፡ የጥያቄዎቹ መልሶች በአእምሮአችን በግልጽ ይታዩናል፡፡ የአእምሮ ችግር ያለበት ሰው ካልሆነ ስሙን ተጠይቆ ሌላ የሚሰጥ የለም፡፡ ከዚያ ውጭ ከባድ ወንጀል ለመሥራት ያቀዱ ሰዎች ለማምለጥ ሲሉ ራሳቸው ያልሆነውን ስም ይናገራሉ። በዚህ መንገድ በልቡ ክፋት ቋጠረ ሰው ካልሆነ ስሙን አሳስቶ የሚናገር ሰው አይኖርም፡፡ ያዕቆብ ይስሐቅ ሲጠይቀው እኔ ኤሳው ነኝ ያለው በልቡ ተንኮል አባቱን አታልሎ በረከትን የመቀበል ጥማት ስላደረበት ነበር፡፡ የአባቱ ዓይን ስለማያይ ተሳክቶለት የፈለገውን በረከት ወሰደ፡፡ የሚያታልሉና የሚስመስሉ ሰዎች ተሳክቶላቸው የምናየው በዚህ መንገድ እያለፉ ፣ስማቸወውንም ስለሚቀያይሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ወንጀልን የሚደብቁት በእንዲህ መንገድ ነው፡፡ በመዋሸትና ያለ የሌለ ሁሉ በማውራት ብዙዎችን አታልለው የተሳካላቸው ወንድሞችም ሆነ እህቶች ጥቂት ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚያዩት የዛሬውን ስኬትና ጊዜያዊ ደስታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን አንድ ቀን እነርሱንም “አንተ ማን ነህ?” ማለቱ አይቅርም፡፡ እግዚአብሔር ስማችንን በደንብ ያውቀዋል ግን እኛው ራሳችን ስለ ማንነታችን እንድንናገር መፈለጉ በጣም አስገራሚ ነገር ነው፡፡ ሰዎች እንደመሆናችን መጠን ባልንጀሮቻችንን ስንዋሻቸውና ስናታልላቸው ስለኖርን ያ አብሮን የበቀለው ባሕሪያችን በእግዚአብሔርም ፊት ዋሽተንና አጭበርብረን እንድናልፍና በዚያውም መንገድ በረከትን መቀበል የምንችል ያስመስልብናል፡፡ ያልሞተና ፍጥረታዊ ማንነት ያላቸው አገልጋዮች ዛሬም በሕያው እግዚአብሔር ቤት በእግዚአብሔርም ስም የሚያደርጉት ይህንን ነው፡፡ በእውነት፣ በቅንነትና እንዲሁም በጽድቅ አገልግለው ከሚኖሩ ይልቅ አታላይ አገልጋዮች ሲሳካላቸው ማየት ብዙዎችን ይፈትናቸዋል፡፡
ያዕቆብ እግዚአብሔር ሲጠይቀው እንደልማዱ እኔ ኤሳው ነኝ ይል ይሆን? ያዕቆብ ግን በዚህ ጊዜ የመለሰው ምላሽ ትክለኛና እውነተኛ ነበር፡፡ እርሱ የፈለገው በረከት ሲሆን እንዴት ሊያገኘው እንደሚችልም በደንብ ያውቅ ነበር፡፡ በየትኛው ቦታ ምን የሚል ምላሽ መስጠት እንዳለበትም ጠንቅቆ ያውቃልና በያቦቅ ወንዝ አጠገብ የተገኘለትን በጎ አጋጣሚ ሊያጣው አልፈለገም፡፡ ካልባረክከኝ አልለቅህም የተባለው አካል ስምህ ማን ነው ስለው ኤሳው ነኝ ቢል ሌላ መርገም በላዩ ላይ ሊያስከትለው እንደሚችል ያውቃል፡፡ ከዓመታት በፊት እናቱ ስትመክረው ኤሳው ነኝ ብል በራሴ ላይ ከበረከት ይልቅ መርገምን አመጣለሁ በማለት ተጨማሪ መፍትሔ እንዲፈለግ አደረገ እንጂ እንደተመከረ ዝም ብሎ አልሄደም፡፡ እግዚአብሔር ሲጠይቀውም በለመደው መንገድ የሚያታልል መልስ ሊሰጥ አልፈለገም፡፡ እውነተኛ ማንነነቱን ሳይደብቅ እኔ ያዕቆብ ነኝ አለ፡፡ ይህንን በማድረጉ ቀደም ሲል የሠራቸው ስህተቶች ሁሉ አልታሰቡም፡፡ የፈለገውን በረከት ከማግኘት የሚከለክል ምንም እቅፋት ሳይገጠመው ወደሚቀጥለው የበረከት ርከን ተሻገረ፡፡ አባቱን ዋሽቶና አታልሎ የተቀበለው በረከት ዓይነት ሳይሆን በጣም የተለየ በረከት ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበለ፡፡ የአታላይነት ስሙ ተቀየረለት፣ እግዚአብሔርም የሚፈልገውንም በረከት ሳይሰስት ሰጠው፡፡
ያዕቆብ አባቱን በማታለል የወሰደው ለወንድሙ ለኤሳው የተዘጋጀለት በረከት እረፍትና እርካታ አልሰጠውም ነበር፡፡ እንዲያውም በዚያ ምክንያት ተሰዳጅና ኮብላይ ነው የሆነው፡፡ በላባ ቤት 20ዓመት እንዲገዛ፣ የቀን ሐሩር የሌሊት ቁር እንዲበላው ፣ ደመወዙም አሥር ጊዜ እንዲለዋወጥበት ምክንያት የሆነው እኮ በማታለል የተገኘው በረከት ነው፡፡ ኤሳው ሊገድለው እንደሚያስብ እናታቸው ስላወቀች ያዕቆብን በሞት እንዳታጣው በሁለት ወንዞች መካከል ወዳሉ ወንድሞቿ በመሄድ ከወንድሙ ሰይፍ እንዲያመልጥ ስለመከረቺው ወደ ላባ ሄደ፡፡ እዚያ ሆኖ መክፈል የሚገባውን ዋጋ ሁሉ ከፈለ፡፡ እንግዲህ በጽድቅ ሳይሆን በማታለል የተገኘ በረከት አያረካም ፣ አያረጋጋምም፣እንዲያውም ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ዛሬም በእግዚአብሔር ቤት በብዙ መንገድ የሚሽለከለኩ አገልጋዮች ምድራዊ በረከትን ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል፣ ያ በረከት ግን ሙሉ እርካታ አይሰጣቸውም፡፡ በእግዚአብሔር ፊት እውነተኛ ማነትን ይዞ በመቅረብ የሚገኘው በረከት ግን ለነፍስም ሆነ ለሥጋ ሙሉ ደስታን ይሰጣል ፣ ምንም ጸጸት የለበትም፣ እስከ ወዲያኛውም ጊዜ ድረስ አብሮ ይዘልቃል፡፡ ኦየእግዚአብሔር በረከት ይሻላል፡፡
ያዕቆብ እውነተኛ ማንነቱን ለእግዚአብሔር ከተናገረ በኋላ በሕይወቱ የታየው ለውጥ አስገራሚ ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚያ ሥፍራ የአጭር ጊዜም ሆነ የረጅም ጊዜ ለውጥ አደረገለት፡፡ አንደኛ ስሙን ያቆብ እንዳይባል እሥራኤል አለው፡፡ ሁለተኛ ሰውነቱም ተፈወሰችለት፡፡ በክፍሉ እንደምንመለከተውሲታገል የጭኑ ሹልዳ ተነክቶበት እንደሚያነክስ ቃሉ ይናገራል ግን ያዕቆብ ሰውነቴ ዳነ እያለ ነበር፡፡ እንዴት ሰውነቴ ድና ቀረች ሊል ቻለ? እያነከሰ አይደለም ወይ? ያገኘው ፈውስ ውሰጣዊ ፈውስ ነው፡፡ የማንነቱ ፈውስ ነው፡፤ ከያዕቆብነት ወደ እሥራኤልነት የተሸጋገረበት አስደናቂ የሆነ መንፈሳዊ ፈውስ ነበር የሆነለት፡፡ ምክንያቱም ለአምላኩ ማንነቱን ለመደበቅ አልፈለገምና አምላኩም እንደፈለገውና ከዚያም በላይ ባረከው፡፡
ውድ አንባቢያን ሆይ! ሁላችንም በረከትን እንፈልጋለን፡፡ ደግሞም ያስፈልገናል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር እኮ የበረከት አምላክ ነው፡፡ እርሱ እኛን ሊባረከን ወዶ ወደ እኛ ስለመጣ ደስ ይበለን፡፡ የእግዚአብሔርን ጥያቄ ከምንነታችን የተነሳ ውስስብና ከባድ ሳናደርጋቸው በትከከል እንመልሳቸው። ስለ ትክክለኛ ማንነታችን ሥፍራ እንስጥ፡፡ እውነተኛ ማንነታችንን ይዘን ወደ ፊቱ እንቅረብ፡፡

የእግዚአብሔር ጥያቄ አራት፡ እግዚአብሔርን ማን ትለዋለህ?( እኔን ማን ትሉኛላችሁ?)
ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣሪያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀመዛሙርቱን፡- ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ፡፡ እነርሱም ፡- አንዱ መጥመቁ ዮሐንስ ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉ፡፡ እርሱም እናንተስ እኔም ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ?አላቸው( ማቴ.16 ፡13-15)፡፡
ጌታ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በነበረው ቆይታ ብዙ ነገሮችን እንዳስተማራቸው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ለረጅም ጊዜያት ከእነርሱ ጋር ሲቆይ ስለ መንግሥቱ አስተምሮአቸዋል፡፡ ወንጌልን እንዲሰብኩና አጋንንትን እንዲያስወጡ እንዲሁም ደግሞ ድዉያንንም እንዲፈውሱ ሥልጣንን ሁሉ ሰጥቶአቸዋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሁሉ ከእርሱ ብዙ ሲማሩ ቆይተዋል፡፡ አሁን ግን የመጨረሻ ፈተና ወደሚፈተኑበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ በትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች በትምህርት ሂደት በትንሽ በትንሹ የቅምሻ ፈተናዎችን እየወሰዱ ወደ ዓመቱ ወይም ወደ ሰሚስቴሩ ፍጸሜ ሲደርሱ የማጠቃያ ፈተና ይፈተናሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የኢየሱስ ተማሪዎች የሆኑ12 ደቀመዛሙርትም በቂሣሪያ ተቀመጡ፡፡ የሚፈትናቸውም ሲያስተምራቸው የቆየው መልካሙ መምህር ኢየሱስ ነበር፡፡ በዚህ ፈተና ጌታ ለደቀ መዛሙርት ያቀረበው የፈተና ጥያቄዎች ሁለት ሲሆኑ ቀደም ብለን እንደተመለከትናቸው ሁሉ በጣም ቀላል ነበሩ፡፡ ጥያቄ አንድ፡ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል? ጥያቄ ሁለት ፡ እናንተስ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ? ደቀ መዛሙርቱ የመጀመሪውን ጥያቄ በጥሩ መልሰዋል፡፡ ይህ ጥያቄ ሌሎች ሰዎች ስለ ኢየሱስ ካላቸው ግንዛቤ ተነስተው የሚያወሩትን ደቀመዛሙርትም የሰሙትን እንዲህና እንዲያ ይላሉ ብሎ መናገር ብቻ ነው፡፡ እዚህ ጋ የተሳሳተ መልስ ሊኖር አይችልም ምክንያቱም ሰው እንደመሰለው እየተናረ ያለውንና እነርሱም እንደሰሙት እንደዚያው ለኢየሱስ መመለስ ብቻ ነው፡፡
ነገር ግን ሁለተኛ ጥያቄ ከመጀመሪው ይልቅ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ እናንተስ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ? በዚህኛው ላይ መሳሳት አይኖርባቸውም፡፡ ሦስት ዓመት ተኩል ከእርሱ ጋር በብዙ ሁኔታ ሲያሳልፉ የእርሱን ማንነት ካላወቁ እጅግ የሚያሳስብ ይሆናል፡፡ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ያቀረበው ይህ ጥያቄ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥያቄ ነው፡፡ ለደቀ መዛሙርት ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ የሚገኝ እያንዳንዱ አማኝ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ/ለአንቺ ማን ነው? ይህ የብሉይ ኪዳንም ትንቢትም ሆነ የአዲስ ኪዳን የወንጌልና የመልዕክታት ሁሉ ድምድማት ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ በትክክል ለመመለስ ካልቻልን የክርስትና ሕይወት ትርጉም አልገባንም፣ በአሸዋ ላይም ተመሥርተናል ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ በተመላለሰባቸው ሥፍራዎች ሁሉ የኖሩ ሰዎች ስለ እርሱ የነበራቸው አስተያየት የአንዱ ከሌላው የተለየ ነበር፡፡ አንዳንዶች ንጉሥ ይሁንልን ብለዋል፡፡ በጊዜው ከተፈጠረው ሁኔታ የተነሳ የፖለቲካ መሪ ሊያደርጉት በመሞከር ይንገሥልን ብለዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የአጋንንት አለቃ ነው አጋንንትን ያወጣል ብለዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ የጠራቢ ልጅ ነው ብለዋል፡፡ እንደነሰዱቃውያንና እንደፈሪሳውያን ያሉት ደግሞ አሳች ነው ፣ ኃጢአተኛ ነው ብለዋል እንጂ ቀደ መዛሙርቱ እንዳሉት ብቻ አልነበረም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በአገልግሎታቸው ምክንያት በሕዝቡ መካካል በተመላላሱባቸው ጊዜያት የሰሙአቸው እነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ ሌሎች አሉታዊ አስተሳሰቦችንም የሰነዘሩ ነበሩ፡፡ ሰዎች ያሉትን ቢሉ ደቀ መዛሙርት ግን ሰለ ኢየሱስ ትክክለኛ እውቀት ሊኖራቸው ይገባቸዋል፡፡ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?
ወንጌላዊው ማቴዎስ ይህን መልእክት ሲያቀርብ ገና በቁጥር 13 ላይ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ፊልጶስ ቂሣሪያ እንደ መጣ ይናገራል፡፡ ይህ መልከአ-ምድራዊ አውድ በዚህ የንባብ ክፍል ውስጥ መጠቀሱ የራሱ የሆነ ሥነ መለኮታዊና ታሪካዊ እንድምታ ያለው ነው፡፡ በክፍሉ እንደምንመለከተው ጌታ ከደቀ መዛሙርት ጋር የነበረውን የአገልግሎት ጊዜውን በገሊላ ባሕር ዙሪያ ባሉ የሰሜኑና የምሥራቁ አካባቢዎች ነው፡፡ በአካባቢው ሁለት የቂሣሪያ ከተሞች የነበሩ ሲሆን አንደኛው በኢየሩሳሌም ከተማ በስተ ምዕራባዊ ዳሪቻ አካባቢ የሚገኝ ከተማ ነው፡፡ ሁለተኛው ቂሣሪያ ደግሞ በፍልስጥኤም ምድር በሰሜንና በምዕራቡ ጫፍ ላይ የሚገኝ አካባቢ ሲሆን ለዳን የተሰጠና በጣም ታሪካዊ ሆነ ሥፍራ ነው፡፡ ደቡብ ቂሣሪያ ደግሞ ለቤርሳቤህ የተሰጠ መሬት ሆኖ የዮርዳኖስ ወንዝ መነሻ አካባቢ ነው፡፡ በአካባቢው ፓን በሚባል የግሪክ ጣዖት ስም የተሰየመ ፓንያስ የሚባል አነስተኛ ከተማም እንደነበር ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በዚያ አካባቢ ከፍታው 9232 ጫማ የሆነ የሄርሞን ተራራ ስለሚገኝበት አካባቢው በጣም ታዋቂ ነበር፡፡
እንግዲህ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የተለየ የአምልኮ ሥርዓት ወዳለበትና በጣም ታሪካዊ ወደሆነው ወደዚህ አካባቢ ደረሰ፡፡ በወቅቱ ፓን የተባችው የግሪክ አምልኮ በአካባቢው ባሉ የአህዛብ ሕዝቦች ላይ ተጽዕኖ አሳድረውባቸው ስለነበር ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ በግሪክ ሥርዓትና አምልኮ ተጽእኖ ሥር ወድቆ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያ አካባቢ የሶሪያ ግዛት ሆኗል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ወደ ፍልጶስ ቂሣሪያ ከደቀ መዛሙርት ጋር የመጣበት ታሪክ በጣም ወሳኝ በመሆኑ ሦስቱም ወንጌላውያን ማለትም ማቴዎስ ማርቆስና ሉቃስም እንደየተነሱበት ዓላማ አንጻር ተርከዋል፡፡ ማርቆስ ኢየሱስ ወደዚያ የመጣው ከጸሎት መልስ መሆኑን ይነግረናል፡፡ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በእነዚያ መንደሮች ሲመላለስና በግሪክ ሕዝቦች መካከል ሲያልፍ በራሱና በቀደ መዛሙርቱ መካከል ባለው ግንኙነት ውስጥ ወሳኝ የሆነውን ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲያሰለጥናቸውና ሲያስተምራቸው እንዲሁም ደግሞ ብዙ ተአምራትን ሲያለማምዳቸው ቆይቶ የመጨሻ ፈተና እየሰጣቸው ያለ ይመስላል፡፡ ምናልባት አህዛቦች ወይም ግሪኮች ፓን ለተባለችው ጣዖታቸው የሚሰጡትን ክብር ጥንቃቄና አክብሮት በመንደሮች መካከል ሲያልፉ ገምግመው ይሆናል፡፡ ሰዎች ሁሉ ስለ አምላካቸው የሚሉት አላቸው፡፡ ስለ ኢየሱስም የሚሰጡት የተለያየ ስያሜ ነበራቸው፡፡ ሌሎች ስለ እርሱ የፈለጉትንና የመሰላቸውን ይበሉ፡፡ በስሙ የተጠሩ ደቀ መዛሙርት ግን ጌታቸውን የተረዱት እንዴት እንደሆነ መግለጽ ስላለባቸው "እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው፡፡
አሕዛቦች ለማያውቁት አምላክ ይሰግዳሉ ያመልኩታልም( ሐዋ.17፡23)፡፡ የሚያውቁአቸውም ቢሆኑ የሚያድኑአቸው አይደሉም፡፡ የእሥራኤል አምላክ ግን ራሱን ለሕዝቡ የገለጠ፣ የሚታወቅ፣ ያዳናቸውና የሚያድናቸው አምላክ ነው፡፡ የአርሱ አዳኝነት በእሥራኤል ብቻ ሳይሆን በአህዛብና በነገሥታቶቻቸውም ሁሉ የታወቀ በመሆኑ ናቡካድናጾር የተባለ የባቢሎን ንጉሥ ሲመሰክር፡ እንደዚህ የሚያድን አምላክ የለም ብሏል(ዳንኤል 3፡ 29)፡፡ እግዚአብሔርም ራሱ ከማናቸውም የአሕዛብ አማልክት ጋር እንደማይመሳሰል ሲያረጋግጥ እኔን ከማን ጋር ታመሳስሉኛላችሁ ከማንስ ጋር ታስተያዩኛላችሁ እያለ የእሥራኤልን ሕዝብ ይጠይቃቸዋል( ኢሳ 46፡1-10)፡፡ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚያቀርብላቸው ጥያቄ እርሱን ከማንም ጋር ማወዳደር እንደማይቻልና ከአማልክት ሁሉ የላቀ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ያቀረበው እኔን ማን ትሉኛላችሁ የሚለው ጥያቄ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለ ጌታ ኢየሱስ ምን ያህል እንደተረዱ ለማሳሰብ የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ብቻ ሳይሆኑ ዛሬ በዚህን ዘመን ያለንም አማኞች ሁላችንም ስለ ኢየሱስ ምን ያህል ገብቶናል? ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ስለ ኢየሱስ ምን ትላለች? የያዝነው ነገረ መለኮት ከሚያስረዳው ሌላ በሕይወታችን የምንመሰክረው ኢየሱስን ምን ብለነው ነው? በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ስናልፍ የምናምነው ጌታ ኢየሱስ ለእኛ ማን ነው? አገልጋዮች በመድረክ ላይ ስንወጣ ጌታ ኢየሱስን የሚያሳይ ማንነት አለንን? ኢየሱስን ማን አንለዋለን? እኔ ለእናንተ ማን ነኝ? ይህንን ጥያቄ በትክክል መመለስ ይኖርብናል ምክንያቱም ዘላለማዊው መድረሻችንን የሚወሰነው ለዚህ ጥያቄ በምንሰጠው ምላሽና በምላሹ ላይ ተመሥርተን በምንኖርበት ሕይወት ነውና፡፡
በዚህ የመጨረሻ ፈተና የጌታ ደቀ መዛሙርት ሳይወድቁ አልፈዋል፡፡ እንደ ሌሎች የሚያጠራጠር መልስ አልሰጡም፡፡ የጌታን ማንነት በሚገባ ገልጸዋል፡፡ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መለሰ፡፡ አንተ ክርሰቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለው፡፡ ይህን ምላሽ ዘርዘር አድርገን የተመለከትን እንደሆነ አጭር የሚመስል ግን ትልቅ ቁም ነገር ያለበት ነው፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስን አንተ ክርስቶስ ነህ አለው፡፡ ይህ አስደናቂ አገላለጽ ነው፡፡ ክርስቶስ ነህ ሲል ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ ሲጠበቅ የነበረ የተቀባው መሲህ ነህ ማለቱ ነው፡፡ አይሁዶች ጌታ ኢየሱስን ስለ እርሱ ነቢያት የተነበዩለት ሕዝቡን ሁሉ ያድናቸው ዘንድ ይመጣል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው እርሱ ነው ብለው ሊቀበሉ ባይችሉም ሐዋሪያት ለጌታ ምስክር ሆነው ራሳቸውን ገለጡ፡፡ አንተ ክርስቶስ ነህ አሉ፡፡ አንተ ክርስቶስ፣ በእግዚአብሔር የተቀባህ፣ ነቢያት ስለአንተ የተነበዩልን፣ ልትመጣ እንደሆነ ተስፋ የተገበህልን፣ የዘላላም ንጉሥ፣ ለዘላለም የምታድነን ነህ፡ ሊቀ ካህናችን ነህ ማለቱ ነው፡፡ የጌታ ሓዋሪያት ገና ጌታን ሲቀበሉ የተነገራቸው ነቢያት ስለ እርሱ የመሰከሩለትን የናዝሬቱ ኢየሱስን መሲሁን አግኝተነዋል ተብለው ነው(ዮሐ.1) ዛሬም ከ3 ዓት ተኩል አገልግሎት ቆይታ በኋላ ጌታ ስለራሱ ሲጠይቃቸው ያስተማራቸው መሲህ ፣ ተአምር ያደረገላቸው መሲህ፣ ከሁሉም የአይሁድ መምህራን የሚበልጥ ፣ የብዙዎችን እንቆቅልሽ የፈታ፣ ደውያንን የፈወሰ፣ ሙታንንም ያስነሳ አጋንንትና ማዕበል ሁሉ ሲገዙለት ያዩት መሲህ የተቀባ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ባደረጋቸው ሁሉ ባዩትም ሁሉ አምነውበታል፡፡ ስለዚህ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አሉት፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ኢየሱስን አንተ ለእኔ ክርስቶስ ነህ፣ ከአንተ ወደ ማንም ልሄድ አልችልም ምክንያቱም አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ ልንል ይገባናል፡፡ ጌታን አውቀነው ስንከተለውና ስናመልከው አምልኮአችንና አገልግሎተታችን ትርጉም ይኖረዋል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ለእኛ በእግዚአብሔር የተቀባልን መሲሀያችን፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ የዘላለም የሕይወት ቃል አለው፡፡ ሁሉን ትተን ብንከተለው ያዋጣናል፡፡ ሁሉ ብጎድልና ብያንስብን የእርሱ እጅ ግን አይጎድልበትም፡፡ ይህን እንመስክር !
ለመጠቅለል ያህል፣ የእግዚአብሔር ቃል ለእኛ ተገልጦአል፡፡ እግዚአብሔርም በልቤ ያስቀመጠውንን ቀለል ባለ ሁኔታ ላቀርብ ሞክሬአለሁ፡፡ ጌታም ብዙ እንደሚያስተምራችሁ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ምንም ይሁን ግን እግዚአብሔር እኛን ለሚጠይቀን ቀላል ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንስጥ፡፡ የት ነህ ብለን የለንበትን ሥፍራ በግልጽ እንናገር፡፡ ስለ ወንድማችን ቢጠይቀን ወንድማችን የት እንዳለና ምን እንዳደገረግንበት ምንም ሳንሳሳት እንንገረው፡፡ ስለ ማንንታችን ቢጠይቀን ደግሞ ትክክለኛ ስማችንን እንንገረው፡፡ ስለ እግዚአብሔር አውቀን አንጭርስም ቢሆንም የጌታችን እውነተኞች ምስክሮች እንሁን! ኢየሱስ ጌታ፣ ኢየሱስ ንጉሥ፣ ኢየሱስ መድሓኒት፣ ሁልጊዜ ኢየሱስ!ክብሩን ሁሉ እርሱ ብቻ ይውስድ! አሜን፡፡

No comments:
Post a Comment