Friday, July 15, 2016

ለአሉታዊ ነገሮቻችን የምንሰጠው ምላሽ ምንድነው?


             2ኛ ነገሥት 5፡1-19

በዚህ ክፍል የምንመለተው ሰው ንዕማን የሚባል የሶሪያ ሠራዊት አለቃ ነው፡፡ ይህ በቀላሉ የሚታይ ማዕረግ አይደለም፡፡
·         ንዕማን በጣም የተሳካለት ሰው ነው፡፡ ባነበብነው ክፍል ብቻ ስለ እርሱ ብዙ የስብከት ሁኔታዎችን የሚያሳይ ነገር ይናገራል፡፡
·         እርሱ የሦሪያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ነው፡፡ ካፒቴን ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ሰው ወደዚህ ደረጃ ዝም ብሎ አልመጣም፡፡ በአገር ደረጃ ወደሚታወቅበት ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ የተለያዩ እርከኖች አልፎ መሆን አለበት፡፡ በእነዚያ እርከኖች ሁሉ ውጤታማነቱ እየተረጋገጠ ብቃቱም እየተመሰከረለት እንጂ በቀላሉ ሊደርስ የቻለው በቀላሉ አይደለም፡፡
·         እግዚአብሔርም በእርሱ ምክንያት ከአገሪቱ ድልን (ደህንነትን) ሰጥቷል፡፡ ሶሪያ ከእሥራኤል ጋር ነበራት ጦርነት  ወቅት እግዚአብሔር በምዕማን ምክንያት ለሕዝቡ አርነትን ወይም ድልን ሰጠ፡፡ ይህ ደግም እጅግ በጣም የሚያስደንቅ ነገር ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ በአገሪቱ ደረጃ በጣም የሚወደድ ሰው ሊሆን ቻለ፡፡
·         ንዕማን የተከበረ ሰው ነው መሆኑን ይህ ክፍል ይነግረናል፡ ይህ ክብር እንዲሁ ተራ የሆነ ክብር ሳይሆን በአገር ደረጃ በንጉሡም ዘንድ የሆነ ብክር ነው( በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበር) ፡፡ ንጉሡ አከበረው ማለት ምን ማለት እንደሆነ መገመት በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡ ንጉሥ ካከበረና ከወደደ ሌላ ከዚያ የሚሻል ነገር ያለ አይመስልም፡፡ ንጉስ እውቅና ሲሰጥ፣ ሽልማት ሲሰጥ፣ ንጉሥ ሹመት ሲሰጥ ፣ ቦታ ሲሰጥ፣ ማዕረግ ሲሰጥ፣ ንጉሥ ግብዣ አዘጋጅቶ አቤቱ ሲጋብዝ  
·         ይህ ብቻ ሳይሆን ጽኑና ኃያል የሆነ ሰው ነበር፡፡
·         በዘመኑ በሶሪያ አገር ከንጉሡ ይልቅ በጣም የሚታወቀው ንዕማን ነበር፡፡ በጊዜው የትኛው ንጉሥ እንደሆነ ባናቅም በአገሪቱ ሻይን አውት ያደረገው ንዕማ ነበር፡፡
·         እግዚአብሔርም አጅግ በጣም የረዳው ሰው ነው፡፡ በንጉሥ ዘንድ ከሚያገኘው ክብርና ሙገሳ ሁሉ ይልቅ እግዚአብሔር ያደረገለት ርዳታ እና ስኬት ደግሞ ልዩ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ ሶሪያ ከእሥራኤል ጋር በነበራት ጦርነት ወቅት እግአብሔር በንዕማን ምክንያት ለሶሪያውያን ድል ሰጥቶት ነበር፡፡ ይህ  ደግሞ በጣም  የንዕማንን ዝና እና በሕዝብ ፊት ያውን ሙገሳ ከፍ ያደረገለት በጣም አስደናቂ ነገር ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ሰው በጣም የተሰካለት ሰው ነው፡፡ ቢሆንም በሕይወቱ ትልቅ ጥያቄ ነበረበት፡፡        
·         ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ ግን አንድ በሕይወቱ ሰንካላ ነገር ነበረበት፡፡ ያለበትን ክብርና ሙገሳ ሁሉ አልፎ  እንዲቆዝም የሚያደርግ ነገር ነበረበት፡፡ አንድ የማያስፈልግ ጉድለት አለበት፡፡ እንቅፋት አለበት፡፡ የሆነ ደንቃራ  ነገር ገጠመው፡፡ ያውም የእግዚአብሔር ቃል ነገር ግን ብሎ ይነግረናል፡፡ ነገር ግን ለምጸም ነበረ፡፡ ይህ ከንጉሥ ያገኘው ክብርና ዝና ሁሉ ሊሸፍነው የሚያችለው አሳኝ የሆነ ገጠመኝ ነው፡፡ ችግሩ የእርሱ ብቻ ቢሆንም ግን ደግሞ ሊደብቀው የማይቻል በሰውነቱ ላይ የሚታይ ነገር ነው፡፡ ከዚይ የተነሳ ተሸማቆ ሊሆን ይችላል‹፣ ልቡ በየዕለቱ እዝን ትክዝ ይልበት ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ለምጽ በጣም አደገኛ ነገር ስለሆነ፡፡ ለምፅ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ የእግዚአብሔር ቅጣትና የርኩሰት ምሳሌ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ የለምጻምና የለምጽ ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 40 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ የሙሴ ሕግም ለምጻሞችን በሚመለከት ለእሥራኤል ልጆች ግልጽ  የሆነ መመሪያ ሰጥቷል፡፡  ማንም በሰውነቱ ላይ ይህ በሽታ እንዳለበት በጠረጥር ራሱን በካህን ያስመረምርና በሽታው መኖሩ ከተረጋገጠ ከሰው ሁሉ ተለይቶ ለብቻ እንዲቀመጥ በሕግ ታዟል(ዘሌ. 132-345-46)፡፡ እንዲህ ዓይነት ምልክት በሰውነቱ ያለበት ሰው ከከተማ ውጭ ካምፕ ሰርቶ እዚያ መቀመጥ እንዳለበት በሕግ ተቀምጧል፡፡ ምክንያቱም ለምጽ በፍጹም አካላዊና መንፈረሳዊ ርኩሰት ተደርጎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ ብዙዎች እግዚአብሔር ሰው ኃጢአት ሲሠራ ሊድን በማይችል ለምጽ ስለሚመታ ይህ የኃጢአት ውጤት ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በዘኁልቁ 52 ላይ እንደምንመለከተው እንዲህ ዓይነት ችግር ያለበት ሰው ከራሱ ሕብረተሰብ ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር አይፈቀድለትም ነበር፡፡ እንዲያውም በጥንት አይሁዶች ሕግ መሠረት ለምጽ ያለበት ሰው ወደ ቤተሰቡም ሆነ ወደሌላ ሰው ከስድስት ጫማ በበለጠ ርቀት እንጂ ከዚያ ያህል አልፎ መቅረብ እንደለለበት ይደነግጋል፡፡ በጊዜው የነበሩ ሰዎች ለምጽን እንደ ዘግናኝ ነገር ስለሚቆጥሩ ነፋስ በሚነፍስበት ወቅት ሕመምተኛው ከሌላው ሕዝብ 150 ጫማ ያህል ራቅ ብለው መቆም ይጠበቅበት ነበር፡፡ አንግዲህ ንዕማን የተባለውን ታላቅ የተከበረና በሁሉ የተሳካለትን ሰው የቀደመው እንደዚህ ዓይነት ተግዳሮት ነው፡፡
·         እግዚአብሔር ታላላቅ ድሎችን ከሰጠን በኋላ ፣ በአገልግሎት፣ በትምህርት፣ በኑሮ፣ በሌሎችም ሁሉ ጉዳዮች መከናወንና መሳካትን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብለን ስናበቃ ሌላ ደግሞ ከጎን ሆኖ የሚታይ ደንቀራ ነገር ገጥመናል፡፡ እንዲያው ልባችንን የሚያርድ ነገር የሚፈጠርበት ሁኔታ ይከሰታል፡፡ አገልግለን ከተባረክን በኀኋላ አንድ አሉታዊ የሆነ ኔጌቲቭ ፊታችን ድቅን ሲል ምለሻችን ምንድነው፡ በተለይም እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱ ነገር ፈተናቸው፣ መስቀላቸውና ቀንበራቸው ይሆንባቸዋል፡፡
·         እኛ የምንኖረው በተገለጠው  እና ሙሉ በሙሉ ባልተገለጠው( already and not yet kingdom of God) ውስጥ ስለምንኖር ደስታና ሀዘን ፣ ማግኘትና ማጣት፣ መክበርና መዋረድ ወዘተ ይፈራረቁብናል፡፡  ይህ ሲሆን የእኛ ምላሽ ምንድነው;
·         የብል ኦዶኖቫን ምሳሌ፡፡
·         እንዲህ ዓይነቱ ነገር በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአገርም ደረጃ ተከስቶ አይተናል፡፡ በምናነበው መጽሐፍ ምዕራፍ ሁለት ላይ ተመሳሳይ ነገር እናነባለን፡፡ ኤልሳዕ ወደ ኢያሪኮ በመጣ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ኤልሳን እነሆ ጌታችን እንደምታይ የዚህች ከተማ ኑሮ መልካም ነው፣ዉሃው ግን ክፉ ነው ምድሪቱ ፍሬዋን ትጨነግፋለች፡፡ እርሱም አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ ጨውም ጭምሩበት አለ ይህንን አመጡለት፡፡ ውሃው ወዳለበት ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ ከዚህ በኋላ ሞትና ጭንገፋ አይሆንም አለ፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰላም የሰፈነባት ለሰዎች ኑሮ በጣም የምትመች ከተማ ናት፡፡ ለሚገባውም ለሚገባው ሁሉ  ምንም ሥጋት የለበትም፡፡ ከዚያም አልፎ ለመብላትና ለመጠጣት ሁሉም ነገር የተመቻቸ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሌላ የጎንዮሽ ውጋት የሆነ ነገር አለባት፡፡ ያውም ውሃው መጥፎ ከመሆኑ የተነሳ የምድሪቱ ፍሬ ይጨነግፋል፡፡ ይህዓይነት ነገር በቤተከርስቲያናም በአገር ደረጃ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት የእኛ ምላሽ ምን ይሆን;
·         በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸውን የምናያቸው ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች ከአምላካቸው ታላቅ ክብር እያገኙ እያለ በዚያው ልክ ደግሞ ልባቸው የሚያንበት ደንቃራ ጉዳይ ሲገጥማቸው እንመለከታለን፡፡ የእግዚአብሔር ሰው አብርሃም ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ታማኝ ሰው በከመሆኑ እግአብሔር የብዙ አህዘዛብ አባት ያደረገው ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ቤቱ ሲገባ ሚስቱ መካን ከመሆንዋ የተነሳ መቶ አመት እስክሆነው ድረስ ልጅ አልነበረውም፡፡ ዳዊት የእግዚአብሔርን ጠርነት የተዋጋና የተሳካለት ሰው ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በብዙ የረዳው ሰው ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ቤቱ ሲመጣ ልጁ አቤሴሎም ጦር ይዞ ያሳድደው ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ በጣም አሳኝና ከባድ የሆነ ይይወት ተሞክሮ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስም አስደናቂ የእግዚአብሔር ክብር በአገልግሎቱ እየተገለጠለት እያለ ሥጋውን የሚዋጋ ሌላ ፈተነ በሕይወቱ ነበረበት፡፡ በእኛም ዘመን ቤተከርስቲያን መሪዎችን ሕይወት እንዲህ ዓይነት ካሉ ፈተናዎች  ያጋጠሙባቸው ጊዜቶች እና ምሳሌዎች በጣም ብዙ  ናቸው፡፡ በአደባባይ እግዚአብሔር ባርኮን የብዙዎችም እንቆቅልሽ በአገልግሎታችን ተፈቶ እኛ ወደ ቤታችን ስንመለስ ያልተፈታ የእኛ እንቆቅልሽ ምን ይሆን; እንዲህ ያሉ ፈተናዎች በፊታችን ሲደቀንብን እኛ ለእግዚዚአብሔር ያለን ምላሽ ምን ይሆን፡ እግዚአብሔር አምላካችን ያለብንን ችግርና ፈተና ሁሉ ሊፈታ የሚችል ኤልሻዳይ አምላክ ነው፡፡ ታዲያ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ እኛ ለእግአብሔር ያለን ምላሽ ሊሆን ይገባዋል፡፡
·         እያንዳንዳችን እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሊገጥሙን ምላሻችን ምንድነው፡ ካነበብነው ክፍል በጣም  ቀላል የሚስሉ ግን በጣም መሠረታዊ የሆኑ  ሦስት አሳቦችን እንመለከታለን፡፡
1.      እግዚአብሔርን መስማት ነው(ቁ.2-4)፡፡ እግዚአብሔር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር ባሕሪያት አንዱ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ሳይናገር አለመተው ነው፡፡ ግን አንዳንዴ እርሱ የሚናገርበት መንገድ ይህ እግዚአብሔር ተናገረ ብለው ሰዎች ለመቀበል በሚቸገሩበት መንገድ መሆኑ በመሆኑ  ብዙዎቻችን እንሰናከልበታለን፡፡ ለችግሮቻችንም መፍትሔውን  የሚያመጣው ካልተጠበቀ ሥፍራ መሆኑ እጅግ ያስደንቃል፡፡ብዙዎች ከእግዚአብሔር አሳብ ጋር የሚተላፉት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ለንዕማን እግዚአብሔር የተናረበት መንገድ በጣም የማይመስል ነው ፡፡ ያውም በአንዲት ሕጻን ልጅ አንዲያውም ምርኮኛ በሆነች ልጅ በኩል ተናገረው፡፡ አንደነዚ ዓይቶችን ሕጻናት እንደነንዕማን ዓይነት ከፍተኛ ሥፍራ ላይ ያሉ ሰዎች ስለሚንቁአቸው አይሰሙአቸውም፡፡ ጎሊያድ ዳዊትን የናቀው ለምንድን ነበር ልጅ ስለሆነ. አይሁዶች መሲህ ሆኖ የመጣውን ኢየሱስ ለመቀበል ይከብዳቸው ይነበረው ለምንድነው  ልጅ ስለነበረና በመካከላቸው ካለው ክዝቅተኛ ቤተሰብ ስለተወለደ ነው፡፡ የእሥራኤል ሕዝብ ልጆችን ከሰዎች ጋር እኩል አይቆጥሩአቸውም ፣ ሰለዚህ ነው ኢየሱሰስ ተአምር አድርጎ አምስቱን አንጀራና ሁለቱን ዓሣ ለ5 ሺህ ሰዎች በመገበ ጊዜ ልጆችና ሴቶች ሳይቆጥር የተባለው፡፡ ይህን የመሰለ ይህ የሰውሥራዓት ውስጥ ያለ አንድ ሰው አንዴት አድርጎ አንዲት  ሕጻን ሴት ልጅ ያውም በምርኮ የመጣት ገረድ የምትለውን ይስማ;  ይህ ሰዎች ራሳቸው የፈጠሩት ነገር እንጂ  እግዚአብርን ለመናገር አይከለክለውም፡፡ ስለዚህ በየትኛውም መንገድ እግዚአብሔር ቢናገር አርሱን መስማት ለችግራችን መፍትሔ ለማጣት ብቸናው መንገድ ነው፡፡ንዕማን ግን ካለበት ሥፍራ ዝቅ ብሎ  እግዚአብሔር አምላክ በብላተናይቱ በኩል የሚናገረውን ድምጽ ሰማ፡፡ እኛም ለእግአብሔር አምላ ድምጽ ምላሽ ልንሰጥ ይገባናል፡፡

2.     እግዚአብሔርን መታዘዝ ነው( ቁ7-14) ፡፡ ንዕማን የብላተናይቱን ቃለ ሰምቶ ከንጉሡም እጅ መንሻ ይዞ በሰማሪያ ወዳለው ነቢይ ድረስ ሄደ ፡፡ ነገር ግን በራሱ መንገድ መፍትሔው እንዲመጣለት ፈለገ፡፡ ነቢዩ እንዳለው መሆን ከበደው፡፡ በዮራዳኖስ ወንዝ አንዲታጠብ ሲነገረው መታዘዝ አቃተው፡፡  ኤክሰፐክቴሺን የሚባለው ነገር እኛን ከእግዚአብሔር ኣስብ ጋር እንድንተላፍ ያደርገን ይሆናል፡፡ በእርግጥም በሥጋ ዓይን ሲታይ የሶሪያ ወንዞች ከእሥራኤል ወንዞች ሊበልጡ ይችላሉ፡፡ የገላ የመታጠብ  መታጠብ ከሆነ ለምን በአገሬ ወንች አልታጠብም የሚል ነገር ተፈጠረበት፡፡ አንዲያውም ተቆጣ፡፡ ልንምድነው ቢባል ነቢዩ በፊቱ እንዲቆም፣ የአምላን ስም እየጠራ የለምጹን ስፍራ በእጁ እየዳሰሰ እንዲጸልይለት እክስፐክት ስላደረገ ያ ባለሆኑ ተቆጣ፡፡ ነገር ግን ሰዎች በመከሩት ጊዜ ተመልሶ መጣና በዮርዳኖስ ወንዝ 7 ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፡፡ ተቆጥቶ ቢሄድም ከዮርዳኖስ ይሻላል ብሎ በተማመነባቸው በአገሩ ወንዞች ደግሞ አልታጠበም፡፡ ምክንያቱም ለዚያ የሚያበቃ ምሪት ገና አላገኘም ነበርና፡፡ ስለዚህ ተመልሶ መጥቶ በወንዙ ሰባት እጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፡፡ ሰውነቱም ተፈወሰ አንዲያው እን ሕጻን ልጅ ገላ መስሎ ወጣ፡፡ መታዘዝ ታላቅ በረከትና ሕይወት ለውጥ ያመጣል፡ ንዕማን ባይታዝ ኖሮ እንደተቆጣ ቢያው ቢሄድ ኖሮ ከለምጹ ባልተፈወሰ ነበር፡፡  የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ያደረጉት ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ በመጣ ጊዜ በከተማይቱ ያለውን ችግር ሲነገሩት አዲስ ማሰሮ አምጡና ጨው ጭምሩበት አለ፡፡ ይህ በሥጋ የሚያየውንኛ የሚያስበውን ሰው ሊያስቆጣ ይችላል፡፡ ማሰሮና ጨው ሁል ጊዜ እነርሱ አጠገብ ነው ያለው፡፡ እኛ ጨው እየበጠበጥን መጨመር ያቅተናልን አላሉሉም ነገር ግን ታዘው አመጡለት፡፡ አርሱም ያንን ጨው በውሃው ላይ ጨመረ ምድሪቱ ከጭንገፋ ተፈወሰች፡፡ መታዘዝ ሲባል በማይመስሉ ሁኔታዎች ውስጥ እግዚአብሔር ለሚናገረው ነገር ምላሽ መስጠት ማለት ነው፡፡ የራሳችንን ፒሪሳፖዚሺንን እውቀት ፣ ልምድ ሁሉ ጌታ ለሚለው አሳብ ማስገዛት ስንችል እግዚአብሔርን ታዘዝን ማለት ነው፡፡ ያነ ከጌታ ዘንድ መፍትሔ ይመጣልናል፡፡

3.     በእግዚአብሔር ፊት መጽናት ፡ መታዘዝ ብቻ ሳይን የመጽናት ሕይወት ያስፈልገናል፡፡ ንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፡፡ ይህ በአንድ ቀን የተደገ ትዕይንት ይመስላል፡፡ ግን ኤልሳዕ ካለው አሳብ ስንነሳ ብቅ ጥልቅ በል ሳይሆን ሰባት ጊዜ ታጠብ፡፡ ይህንን አንዳንዶች ሰባት ጊዜ ተመላልሶ ታጠበ ይሉታል፡፡ እኔም ይህ አሳብ ይመቸኛል፡፡  ሰባት ጊዜ ታጠብ ሲል ደጋግመህ ታጠብ ማለቱ ነው፡፡ ሰባት የፍጹም ቁጥር ነው፡፡  refer the Biblical meaning) ለምሳሌ መጽኸፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ከሥራው አረፈ ይላል፡፡ እሥራኤላውያ ወደ ተስፋይቱ ምድር በሚጓዙበት ወቅት የኢያርኮን ግምብ ሰባት ጊዜ ከዞሩ በኋላ ግቡ በሰባተኛው ዙር ጊዜ ላይ ወደቀ፡፡ ኤልያስ ከ3ዓመት ተኩል ረሀብ ጊዜ በኋላ በቄርሜሎስ ተራራ አጠገብ እግዚአብሔርን ይለምን ነበርና ዝናብ መምጣቱን ለማረጋገጥ ብለቴናው ሰባት ጊዜ እንዲመላለስ አደረገውና በሰባተኛው ግን የእጅ መዳፍ የምታክል ደመና ከባሕር እንደወጣች አየ፡፡ ያንን እስክያይ ድረስ ብላቴናው መመላለስ ነበረበት ማለት ነው፡፡ ንዕማንም ያደረገው ይ ነው፡፡ ሰባት ጊዜ ተመላልሶ ታጠበ፡፡ እግዚአብሔር የተናገረውን እስክጽም ድረስ  በፊቱ መጽናት ፡፡ ነገሮች ወደ  ፍጻሜቸው እስክመጡ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት በጽናት.  The illustration of PUSH
4.     ይህንን ቃል የምትሰሙ ወገኖቼ! እግዚአብሔር በሁሉም በኩል ባርኮአችሁ ሳለ በሕይታችሁ ጎደሎ ሆኖባችሁ የሚያቆዝማችሁ ነገር ምን ይሁን; የአንዳቸን ተግዳሮት ከአንዳችን ይለያል፡፡ የአንደችን የአገልግሎት፣ የሌሎቻችን ደግሞ ጤና ይሆናል፡፡ የሌሎቻችን ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ በልጆቻችን ወይም በትዳር ጓኞቻችን ላይ የምናየው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ በዚሕ ሄሉ ውስጥ ግን እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ደንቃራ ፣ መራረነ አንከሳ የሆነውን ሁሉ ለመለወጥ የራሱ የሆነ መንገድ አለው፡፡ ነገረችን ይዘን ወደ ፊቱ እንቅረብና እንማጸነው.፡፡
እንስማው
እንታዘዘው

እንጽና  እግዚአብሔር ፈውስ ይሰጠናል፡፡ አሜን፡፡ 

No comments:

Post a Comment