Sunday, December 13, 2015

ለኢየሱስ ሥፍራ ይኑረን

ለኢየሱስ ሥፍራ ይኑረን
በአንድ ወቅት በአዲስ ከተማ ውስጥ የተከሰተውን የአንድ አስገራሚ ሰርግ ሁኔታ በእንድ መጽሔት ላይ ተጽፎ አነበብን፡፡ ሰርጉን የደገሱ ሰዎች በሀብት የተባረኩ ስለነበረ የልጃቸውን በተለየ ሁኔታ ደግሰው ነበር፡፡ለሠርጉ ከፍተኛ ዝግጅት አድርነው ነበር፡፡ በጊዜው ከ1500 በላይ ሰዎች ወደ ሠርጉ ተጋብው ነበር፡ አራት ትላልቅ ድንኳኖችን ተክለዋል  ሰናጋዎችን አርደዋል ፣ ምግብ በየዓይነቱ  አሰናድተዋል፡፡ የታደሙትም ሰዎች ወደ ሰርግ ቤቱ ከየአቅጣጫው ተምመዋል፡፡ ዘፈኑ ጭፈራው እልልታው ሲቀልጥ ግን የማታ ማታ አንድ ግራ የሚገባ ነገር ተከሰተ፡፡ ያውም በዚያ ሁሉ ሁካታና ግርግ በፈጠረ ሠርግ ውስጥ ሙሽራው አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉን ያስደነደጠና ግራ ያጋባ  ደስታውንና ጭፈራውን ሁሉ ወደ ድንጋጤ የለወጠ ነገር ነበር፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ያንን ሙሽራ መፈለግ ነበረባቸውና ፍለጋውን ተያያዙት፡፡ በመጨረሻም ሙሽራው ተፈልጎ ተገኘና ለምን እንደጠፋባቸው ሲጠየቅ እኔን አልፈለጋችሁኝም፣ ለራሳችሁ ብቻ ነው የምትጭፍሩት ፣ የምትደሰቱት፣ የምትበሉና የምትጠጡ እናንተ እኔን ዞር ብሎ ያየኝ ከእናንተ ማንው;፡ ወጥቼ ሲሄድ እንኳ ወዴየት ነው አላላችሁኝም፡፡ ይህን ያህል ጊዜ ከመካካለችሁ ሳልኖር ሲቀር እንኳ አላስተዋላችሁም፡፡ እና ታዲያ ሠርጎ እናንተ ወይስ  የእኔ ;አላቸው፡፡  ሙሽራው ሰይኖር ሰርግ ና ድግስ፣ ጭፈራና ስካር ያሳዝናል፡፡ ሙሽራ የሌለበት ሠርግ!  በመሠረቱ ደስታው ሙሽራውን ለማስደሰት እንጂ ሰዎች ለረሳቸው ብቻ እንዲደሰቱበት መሆን አልበረበትም፡፡ የሙሽራውን ደስታ ለራሳቸው ስለወሰዱበት ሙሽራ በዚ ሥፍራ አላገኙትም፡፡  
ይህ እኛ ያለንትን ዘመን እና ሁኔታ ግል አድርጎ የሚገልጽ ምሳሌ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ ባለንበት በዚህ ዘመን በየዓመቱ የሚከበሩ አለም አቀፍ የሆኑ በዓላት አሉ ፡፡ ከእነዚህ በዓላት አንዱ ጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ነው፡፡ በዓለም ዙሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይህንን በዓልን ያከብሩታል፡፡ ይህ በዓል በክርስተትና እምነት  ብቻ ሳይሆን ክርስቲያን ባልሆኑትም ዘንድ  በድምቀት ይከበራል ምክንያቱም ለብዙዎች እንደ ብሔራዊ በዓል ስለሚታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ በሮማ ውስጥ የኢየሱስ ልደት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በ354 ዓመት ነበር፡፡ እስከዚህ ዓመት ድረስ ቀድሞ በነበሩ ጊዜያቶቸ የጥበብ ሰዎች ነበሩ ታስበው የሚውሉት፡፡ ይኸው ሁኔታ  ዕለት የኋላ ኋላ ወደ ጥር 6 ቀን መዛወሩ እንዳልቀረ ታሪኮች ይናገራሉ ፡፡ አንዳንድ የታሪክ ሰዎች በሮማ ቤተ-ክርስቲያን ይህንን ዕለት ሆነ ብለው የመረጡት ድርጊት በ274ኛው ዓመት መከበር የጀመረውን በሀገሪቱ የማይሸነፍ ይባል የነበረውን የሮማውያን የፀሐይ ንጉስ ልደት ቀን ለማጉላት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባህላዊ የበኣል አከባሮችና የጌታ ልደት የሚከበርበት በዓል በአንድ ወቅት እንዲውም በአንድ ቀን ስለሚደረግ የልደት በዓል አከባበሩ ለባህላዊ በዓል ጋር መቀላቀሉ ልማድ እየሆነ መጣ ማለት ነው፡፡  
በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት የተለያዩ የቀን መቁጠሪያዎችን ካሌንደርስ  በመጠቀም ገና በዓልን ያከብራሉ፡፡ ለምሳሌ የኢየሩሳሌም፣ የሩሲያ፣ የሰርቢያ፣ የፖላንድ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ የሶሎቫኪያ፣ የጆርጅያ፣ የኡክሪንያና አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም የኮኘቲክ ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያናትና አርሜኒያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የጁሊያንን የቀን መቁጠሪያ በመጠቀም የገናን በዓል ጥር 6 ቀን ያከብራሉ፡፡ የግሪክ፣ የኮንስቶትንኦኘል፣ የአሌክሳንደሪያ፣ የሩማኒያ፣ የቡልጋሪያ ፣ የሶሪያ አብያተክርስቲያናት በአንፃራቸው የጎርጎሳዊያንን ካላንደር ይጠቀማሉ ፡፡  እነዚህ አገሮች ሁሉ የክርስቶስ ልደት በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ  የበዓል አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ ድምቀቱን እየጨመረ በመምጣቱ በየአመቱ በታላቅ ናፍቆት የሚጠበቅ በዓል ነው፡፡ ብዙ ግርግሮች የሚታዩበት፣ ብዙዎች ስጦታ የሚለዋወጡበት፣ ቤተሰቦቻችውንና ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ከፍተኛ ወጪ አውጥተው ከቦታ ወደ ቦታ የሚጓዙበት በዓል ነው፡፡ በኣሉ የሚከበረው ገና ዲሴምበር 25 ቢሆንም ከአሁኑኑ ከተማዎች መሸብረቅ ጀምረዋል፡፡  በዓሉ በእንዲህ ዓይነቱ በድምቀት ይከበር እንጂ የጌታ መገኘት የዚኑ ያህል ትኩረት የመሰጠቱ ጉደይ ብም አይታይም፡፡ ጌታችን መወለዱን በተመለከተ በዓሉን እናከብራለን ግን በዓል ከማክበር ባለፈ ፣ ከመጠጣት፣ ከመብላት፣ እና ከመደሰት ባለፈ ጌታ ኢየሱስን እንደ ጌተነቱ የሚከብር ስንቱ ነው; ኢየሱስ የተወለደበትን ዓላማ በግልጠጽ ተረድቶ ለዚህ ምላሽ የሚንሰጠው ስንቶቻችን ነን›
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም በተወለደባት እለት የቤተ ልሄም ከተማ ልክ እንደ አሁኑ ያለወትሮዋ በሰዎች ብዛት የተጨናነቀችበት ጊዜ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ወደ ቤተልሔም የመጡበት ጊዜ ነበር፡፡ ምክንያቱም በንጉሡ አዋጅ ምክንያት ለመመዝገብ( ለመቆጠር)  ብዙዎች ወደ ክተማይቱ ስለመጡ ነው፡፡

በዚያን ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጸፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትዕዛዝ ወጣች፡፡ ቄሬኔዎስ በሶሪያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ ፡፡ ሁሉም እያንዳንዱ እንዲጸፍ ወደ ከተማው ሄደ( ሉቃስ 2፡2-3)፡፡

ንጉሡ እያንዳንዱ ሰው እንዲመዘገብ ወይም እንዲቆጠር በንጉሡ ስለታዘዙ ነው፡፡ የሕዝብ ቆጠራ በጥንት ሰዎች ዘንድ በጣም ይታወቃል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናያቸው ታላላቅ የሕዝብ ቆጠራዎች አንዱ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለት ላይ የምናየው ነው፡፡ ከዚያም በፊት በብሉ ኪዳን የተለያዩ ታላላቅ የሕብ ቆጠራዎች ተከናውነዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን በኦሪት ዘኁልቁ  1-4 እና ምዕራፍ 26 ላይ የተደረጉ ታላላቅ የሕዝብ ቆጠራዎች ነበሩ፡፡ ከዚያ ጊዜ አንስቶ የተለያቱ የሕብ ቆጠራዎች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡   መንግሥታት ሕዝባቸው እንዲቆጠሩ ከሚያደርጉባቸው ምክንያቶች አራት ዋና ዋናዎቹ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ አንደኛው ለአገር ለአገር መከላከያ ( ለጦርነት የሚሆነው የሰው ኃይል ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ነው፡፡ ሁለተኛ ለግብር ማለትም ታክስ ለመከፈል የሚችለውን የሕዝብ መጠን ለይቶ ለማወቅ ነው፡፡ ሶስተኛ ፍታዊ ሀብትና የመሬት ክፍፍል እንዲኖር  ነው፡፡ አራተኛው በአገሪቱ ግዛት ውስጥ ያለው የሰው  ቁጥር በውል ምን ያህል እንደሆነ ለመረዳት ነው፡፡ አውግስጦስ ቄሳርም ዓልም ሁሉ እንዲጸፍ የሚውን አዋጅ ያወጣው በዚህ ዓላማ ምክንያ ሊሆን ይችላል፡፡  ስለዚህ  ሁሉም ሰው ወደዚያ ከተማው ሲሄድ ከዳዊት ወገን የሆኑት ሁሉ የዳዊት ከተማ ወደሆነችው ወደ ቤቴልሔም ተጓዙ፡፡ ስለዚህ ከተማይቱ በከፍተኛ ሁኔታ በእግዶች ተጨናንቃች ማለት ይቻላል፡፡ እንግዲህ እንግዶች በሚገቡባቸው ጊዜ ከተሞች ላይ የሚታየው ደምቀት፣ ሽርጉድ፣ የአቀባበል ዝግጅት፣ ሁሉ የተለየ መሆኑ ግድ ነው፡፡ ቤተልሄምም እንግዶችን በማስተናግድ በጣም የተጨናናቀችበት ጊዜ ነው፡፡
በወቅቱ ለመመዝገብ ወደ ቤተልሔም ከተጓዙት ታላላቅ እንግዶች ውስጥ ዮሴፍና ማርያም ይገኙበታል፡፡ እነርሱ ወደዚያ ከተማ ሲደርሱ ማርያም የማውለጀ ጊዜ ደርሶ ነበር፡፡ ምናልባት ዮሴፍና ማሪያም ወደዚያ ሥፍራ የመጡት እግዚአብሔር አስቀድሞ በነቢያት አፍ ጌታ በቤተልሔም ከተማ እንደሚወለድ የተናረውን የትንቢት ቃል እያስተዋሉና ቀኑም መድረሱን አውቀው እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ አናውቅም፡፡ የሆነ ሆኖ ማርያም  ልክ ወደ ከተማዋ እንደገባች የበኩር ልጇን ጌታችንን ኢየሱስን ወለደች፡፡ የዓለም መድኃኒት የሆነውን፣ የዳዊት ዘር የተባለውን ንጉሥ፣ የነግሥታት ንጉስ የሆነውን፣ ልዑል ጌታችን፣ የእስራኤል ተስፋ የሆነውን መሲህ ወለደች፡፡ ከወለደችም በኋላ በጨርቅ ጠቅልላ በግርግም ላይ አስተናችው ይላል የእግዚአብሔር ቃል፡፡ ለምን;  ለምንድነው በግርግም አስተናችው፡ ምክንያቱ አንድ ነው ያውም በእንግዶች ማረፊያ ለማርያምና ለየሴፍ በተለይም ደግሞ ለተወለደው ጌታ ለኢየሱስ ሥፍራ ስላልነበራቸው ነው፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፡፡ በእግዶችም ማደሪያ ሥፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው ይላል፡፡ በቤተልሔም ከተማ ያሉ ሰዎች ሁሉ እንግዶችን ይቀበላሉ ያስተናግዳሉ፣ ምናልባት የበሉና ይጠጡም ይሆናል፣ ይጨፍሩም ይሆናል፡፡ ይደሰቱበትም ይሆናል፡፡ ለመመዝገብ መጥተው ስለ ታሪካቸው ፣ ስለ ዘራቸው፣ ስለትውልዳቸው ይዘክሩ ይሆናል ይህም ሊሆን ግድ ነውና፡፡ ሕዝብ ቆጠራውና ምዝገባው በባሕሪዩ ይህ እንዲሆን ያስገድዳልና፡፡ ይሁን እንጂ ለኢየሱስ ሥፍራ አልበራቸውም፡፡ ቦታ አልነበራቸውም፡፡  ይህም በመሆኑ ማርያምና ዮሴፍ የከብቶች በረት ውስጥ ገብተው ሕጻን ልጃቸውን ከብቶች ምግብ በሚበሉበትና ውሃ በሚጠቱበት ገንዳ ላይ አስተኙት፡፡ እንግዲህ ማርያም ከዮሴፍ ጋር  ወደ ቤተልሔም የመጣችሁ ገሊላ ከተባለው ከሌላ ቦታ ተጉዛ ነው፡፡ ማርያም ወደ ቤተልሔም ስትመጣ ልትወለድ የደረሰች ነፍሰ ጡር ነበረች፡፡ እንደዚያ  ሆና ወደ ቤተ ልሔም መጣች፡፡ ምናልባት በእግር ተጉዛ ይሁን ጋማ ከብት ላይ ተቀምጣ ይሁን ስለ አመጣጣቸው አናውቅም ግን  ነፍሰጡራን እንኳን ሳይቀሩ ለመቆጠር እንዲመጡ ያደረገው የንጊሡ አዋጅ ምን ያህል ከውሃ የቀጠነ እንደሆነ ለመገመት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ሌላው ቢቀር ለነፍሰ ጡርነቷን እንኳ አይተው ሊራሩላት ይገባቸው ነበር፡፡ ግን ያንን ያደረገ አንድም ሰው በቤተ ልሔም ከተማ ውስጥ አልነበረም፡፡ ሕጻን ከተወለደስ በኃላ አዲስ ለተወለደው ሕጻን ሲሉ ያያዙትን ቦታ እንኳን መልቀቅ ነበረባቸው ግን እንዲያ አይነት ልብ ያለው ሰው በቤተልሔም ከተማ አልነበረም፡፡ ማርያምና ዮሴፍ ለጌታችን ለኢየሱስ የሚሆን ሥፍራፋ በእንግዶች ማረፊያ ውስጥ አላገኙም፡፡ ስለዚህ የዚህን ታሪክ መንፈስ ስንረዳ ሰዎች በሚያድሩበትና በሚያርፉበት በእንግዶች ማረፊያ ሥፍራ ቦታ ስላጡ ወደ ከብቶች በረት የሄዱ ይመስላል፡፡ ማርያም ኢየሱስን ስትወልድ ለኢየሱስም ሆነ ለዚያ ቤተሰብ የነበራቸው ብቸኛ ሥፍራ በከብቶች የመመገቢያ ገንዳዎች የተሞላ በረት ብቻ ነበረ ፡፡ አንዳንድ የሥነ-ጥበብና ተመራማሪዎችም የሥነ-መለኮት ምሁራንም እንደሚተነትኑት ያ ሥፍራ እንደዋሻ አይነት ሊሆን ይችላል ፡፡ ወይንም ደግሞ በአንድ ግቢ ውስጥ ለብቻዋ የቀረች ትንሽ  ኦና ክፍል ልትሆን ትችላለች ፡፡ ምን ዓይነት አሳዛኝ ነገር እንደሆነ መመልከት ቀላል ነው፡፡
ወገኖቼ ሆይ እሰቲ ልብ ብለን እንመልከት! እንደዚሁም  በተልሔም ለሕዝብ ቆጠራ ታዘው በመጡ ዜጎች እንደተሞላችና ከተማዋ በከፍተኛ ድምቀት ወስጥ ብትሆንም ጌታችንን  ሊታስተናደው የምትችልበት የመረዳት ብልጭታ እንኳን እልዳነበራት ሁሉ  ዛሬ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመወለዱ መታሰቢያ የሆነው የልደት በዓል ወይም የገና በዓል በከፍተና ድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ አብየተ ክርስቲያናትም ሆነ ሌሎች ሕዝቦች በዓሉን ለማክበር እየተጣደፉ ናቸው፡፡ የስጦታ ልውውጦች እየተደረጉ ናቸው፡፡ ምብብና የመጠቱ ዝግጅት ተጀምሮአል፡፡ የገና ዛፎች በየቦታው እየተተከሉ፣ የክርስትማስ መብራቶች በየዛፎች ላይ አያሸበረቁ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ጊዜው የክርስትማስ ጊዜ ነው፡፡ የመብላት የመጠጣት፣ የመደሰት ጊዜ ነው፡፡ ሳንታ ክላውስ ከተባለው ጋር ፎግራፍ የመነሳት ጊዜ ነው፡፡ ታዲያ በብዙ ቦታ የዚህ ሁሉ ደስታ ምክንያት የሆነው ጌታ ኢየሱስ ሥፍራ ሲሰጠው አይታይም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሚያደርጉት ዝግጅት ሁሉ ውስጥ ለኢየሱስ ስፍራ የሌላቸው የእምነት ቤቶች በርካታ ናቸው፡፡ ይህም የምንነርበትን ዘመን ልክ ሙሽራ በሌለበት ሠርግ እንደሚጨፍሩ ሰዎች ሕይወት እጅግ አሳዛኝ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡ የተወደዳቸወሁ ወገኖች ሆይ እኔና እናንተ ዛሬ በዚህ ዓለም ውስጥ ስንኖር ፣ አብረንም ይህን በዓል ስናከብር ለእየሱስ ያለን ሥፈራ ምን ይመስላል፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፣ ማንም ድምፄን ቢሰማ በሩን ቢፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር ራት እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል( ራዕያ 3፡10)፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከቤተ ክርቲያናችን ውጭ ወጥቶ ከሆነ፣ በትዳራችንም ቢሆን እርሱ ማእከላዊ መሆን ሲገባው እርሱን አግልለነው ከፍተነው ወደ ውጭ አስወጥተነው ከሆነ፣ በመድረካችንም እርሱ ሥፍራ አጥቶ ከሆነ ፣ ከሁሉም በቅድሚያ ደግሞ በልባችን ውስጥ እርሱ ሥፍራ አጥቶ ከሆነ እኛም ክልክለነው  እንደሆነ  ዛሬ መልእክቱ እንዲህ ነው እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፣ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢጀፍትል ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱ ጋር ራት እበላላሁ እርሱም ከእኔ ጋር እይበላል ይላል ጌታ፤፤
ሰዎች ዛሬ ለኢየሱስ ሥፍራ የማይኖራቸው ለምንድነው ብለን እንጠይቅ እስቲ፡፡ ካነበብነው የሉቃስ ወንጌል ተነስተን ብንመለከት እነዚያ በቤተልሔም ከተማ የነበሩ ሰዎች  ከዚያ በፊት ስለ መሲሁ፣ ሊመጣ ስለነበረው ስለ ኢየሱስ የተነገረላቸውን የተስፋ ቃል ስለዘነጉት ይሆናል፡፡ ከእነርሱ በፊት በነበሩ በሕግና በነቢያት ስለ መሲሁ ስለ ክስርቶስ ተነገሮአቸዋል፡፡ አባቶቻቸውም ይህንን ተስፋ ተቀብለው ነበር፡፡ የሙሴና የነቢያት መልእክት ማእከላዊ አሳብ፣ የህጋቸውና የትንቢታቸውም ጭብጥ ሊገለጥ ስላለው መሲህ ስለ ክርስቶስ ነበር፡፡ በሙሴ በኩል እግዚአብሔር ከእነርሱ መካከል እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ  እንደሚያስነሳለቸውና ሕዝቡም እርሱን እንደሚያዳምጡት  በዘዳግም 18፡15-16 ላይ ተነገሮአቸዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ጌታ ነቢዩ በኩል በትንቢተ ሚክያስ ምዕራፍ 5፡ 2 ላይ አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ ከይሁዳ አእላፍ መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፡፡ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ለዘላለም የሆነ በእስራኤል ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፡፡  ይህ ትንቢት ኢየሱስ ከመወደሉ ከ700 ዓመት በፊት የተነገረ ትንቢት ነው፡፡ ይህ ትንቢት ቤተልሔምን በተለየ ሁኔታ የሚመለከታት ስለሆነ  ይህቺ ከተማ ይህ ትንቢት የሚፈጸምበትን ጊዜና ሁኔታ በንቃት መጠበቅ ነበረባት፡፡ ቤተልሔም ማለት የዳቦ ቤት ማለት ሲሆን ቤተልሑም  ኤፍራታ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ መካከል በጣም የመጨረሻዋና ደካማዋ ከተማ ነበረች፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እሥራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ መሲህ ከእርሷ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር፡፡ ደካማና የናቀች ገረድና እግር አጣቢ የሆነች ይህች ከተማ ከውስጧ የእሥራኤል መድኃኒት እንደሚወጣ የተነገረላትን ተስፋ በትጋትና በንቃት መጠበቅ ባለመቻሏ መሲሁ ኢየሱስ በመካከሏ ተወልዶ እንኳን ልታውቀው አልቻለችም፡፡ ምናልባት በጊዜ የነበረው ግርግር፣ የንጉሡ አዋጅና እንግዶችን ለመቀበል የምታደርገው ሩጫ ለሚወለደው መሲህ ልትሰጠው የሚገባትን ስፍራ ወስዶባት ይሆናል፡፡  በእኛም ዘመን አንዲሁ ወገኖቼ! ምናልባትም በእያንዳንዳችንም ሕይወት እንደዚህ ይሆን ይሆናል፡፡ ጌታ የነገረንን የተስፋ ቃል  ተግተን ባለመጠበቃችን የተነሳ ልባችን በሌላ ጉዳይ ተይዞ  ለእርሱ ሥራ አልሰጠነውም ይሆናል፡፡ የዛሬ የተለያዩ አብተክርስቲያናት እግጅ በጣም ማራኪ ሆኑ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃሉ፣ ስብሰባዎችን ያስተናግዳሉ፣ ነገር ግን ለጌታ ለኢየሱስ ሥፍራ አይኖራቸውም ይሆናል፡፡ ኮንፍራንሶች  ይዘጋጃሉ፣ የነቢያትና ፣ የሐዋሪያት፣ የመጋቢያን እና የመዘምራን ቁጥር እጅግ እየጨመረ ነው፡፡ ይህንን ስናይ የሁላችንም ልባችንም ልብ ይደነቃል፡፡ ነገር ግን ቆም ብለን መጠየቅ የሚኖርብን አንድ መሠራታዊ ጥያቄ አለን ያውም ለኢየሱስ ሥፍራ አለን ወይ የሚለውን ነው፡፡ ለጌታ ስፋ አለን ወይ; መድረኩን የሞላው ኢየሱስና የእርሱ ክር ነው ወይ ; ቤታችንን ትዳራችንን የሚስተዳድረው ኢየሱስና የእርሱ ቃል ነው ወይ; ወይስ እርሱ ገለል ብሎ ሥፍራውንም ሁሉ ለእና ለቆ ሄዶ እኛ ባቻ የእታየን ነው የሚለውን መጠየቅና መልስ መስጠት ይኖርብባል፡፡ ብዙዎቻችን በምድሪቱ ካለው ድህነት ጋር እየታገልን ነው ያንን የኑሮ ውጣ ውረድ ለማሸነፍ ስንል ብዙ እንደክማለን እንጂ የተሰጠንን የተስፋ ቃል አናስበውም፡፡. በበለጸጉና በአደጉ አገሮች ያለን ደግሞ ከቴክኖሎጂው ጋር ስንታገል ፣ ሲስተሙንም ለማሸነፍ ስነገላበጥ ለጌታ ያለንን ሥፍራ ተወስዶብ ይሆን;  ምናልባት  ለአገራችን ያለን ፍቅር፣ ለምንታገልለት የፖለቲካ አቋም ያለን ፍቅር ለጌታ ሥፍራ እንዳይረው አድርጎብ ይሁን› ለዘራችን ፣ ለቋንቋችን የምንለው ሁሉ ዘላማዊ የሆነው ጌታችን በእኛ ውስጥ ስፍራ እንዳገኝ አድርብን ይሁን; ወስታችን በዙሪችን ያሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችን እንጂ ጌታ ለእኛ የተጠንን የተስፋ ቃል ለማሰብ ጊዜ እስከማያገኝ ድረስ ውስጣችን ወደቆ ይሆንን;
ይህን አሳብ አንስተን በምንወያይበት ጊዜ ስለአንድ ነገር ልብ እንበል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከማርያም የተወለደበት ጊዜ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ባለንበት ዘመን  መቼ እንደ ሆነ በማናውቀው ሰዓት ከመላእክቱ ጋራ ዳግመኛ የሚመጣበት (ድግም ምዕአት) ጊዜ ከፍታችን አለ፡፡ እነዚህ ሁለት ክስተቶች ማለትም የኢየሱስ ልደትና ዳግም ምጽአቱ ተመሳሳይ ባሕሪይ አሉአቸው፡፡ ያውም ሁለቱም በመጨረሻው ዘመን ክስተቶቸ መሆናቸው ነው፡፡ ጌታችን የተወለደው በመጨረሻ ዘመን ጅማሬ ላይ ሲሆን ተመልሶ የሚመጣው ደግሞ በመጨረሻው ዘመን ፍጻሜ ላይ ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት ዘመናት ውስጥ ያሉ ሰዎች የአኗኗር ሁናቴ ተመሳሳይ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በሥጋ የተወለደው በመጨረሻው ዘመን ጅማሬ ላይ መሆኑን ለማሳየት ሐዋሪው ጳውሎስ በገላትያ 4፡4 እንዲህ አለ፡፡ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፣ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፣ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ እንዲህ አለ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን( ዕብ 1፡1-2)፡፡
እንግዲሕ የጌታችን በሥጋ በተወለደበትም ሆነ ዳግመኛ በሚመጣበት ዘመን ያሉ ሰዎች የአኗኗር ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ በሉቃስ ወንጌል እንዳነበብነው  የኢየሱስ የመወለዱ ጊዜ ምንም እንኳ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር  የተናገረው ተስፋ የተፈጸመበት አስደናቂ ክስተት ቢሆንም ሰዎች ለኢየሱስ ሥፍራ እስከማሰይጡ ድረስ በግል አጀንዳቸው የተያዙበት  ጊዜ ነበር፡፡
እኛ በአሁኑ ጊዜ ኡየሱስ ክርስቶስ ይወለዳል ብለን አንጠብቅም ፣ ልደቱን እናከብራለን እንጂ፡፡ የእርሱን ዳግም መምጣት ግን እንጠብቃለን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ልክ እንደ በፊቱ ስለሚመጣው ጌታ የማያስቡ በራሳቸው አጀንዳና መርሀ ግብር የታጠሩ መሆናቸውን የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል፡፡ በኖህ ዘመን እንደነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናል፡፡ በዚያች ወራት ከጥፋት ውሃ በፊት ፣ ኖህ ወደ መርከብ እስክገባበት ድረስ ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡ እንደነበሩ፣ የጥፋት ውሃም መጥቶ ሁሉን እስከወሰደ ድረስ እንዳላወቁ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናል(ማቴ 24፡38-39)፡፡ እንዲሁ  በሉቃስ ወንጌል  21፡33-35 ላይ  ደግሞ  ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር ስለ ትዳርም በማሰብ  እንዳይክብድ ፣ ያም ቀን በድንገት እንዳይ መጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስጠንቅቋል፡፡ በዚህ ክፍል ትዳር ማለት የእያንዳዱን የሰው ልጅ የኑሮ ሂደት የሚመለክት ነው፡፡ ስለ ምግብና ስለ መጠጥ ማሰብ የመሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይህንን የማያስብ የለም ነገር ግን ከመሠርታዊ ፍልጎት ባለፈ በመጠጣትና በመስከር  እጅግም የመቀናጣትን ሕይወት እያሳደዱ ልባቸው በዚያ ብቻ ተይዞ የጌታን ቀን ሳያስቡ እንዳይቀሩ ያስጠነቅቃቸዋል፡፡   
እንግዲህ ከላይ ያየናቸው በቤተልሔም ከተማ የሚኖሩ ሕዝቦች በመካከላቸው ለተወለደው ጌታ ሥፍራ ያልነበራቸው ስለሚመጣው መሲህ ተነገራቸውን የተስፋ ቃል ስለዘነጉ ነው፡፡
ሁለተኛ በቤተልሔምና ከቤተልሔም ውጭ የተገለጠውን የጌታ ክብር ለማየትና የሚነገረውን የመላእክት መልእክት መስማት አለመቻላቸው ነው፡፡ የንጉሡን አዋጅ ሰምተው የመጡ ሕዝቦች በቤተልሔም ከተማ ሳሉ  እንግዶች ሲቀበሉና ሲስናግዱ ሳለ የሚበላ ሲበላ የሚጠጣው ሲጠጣ ሳለ በከተማይቱ ዳርቻ ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ሁሉም ሊሰማው የተገባውን አስደናቂ አዋጅ ያውጅ ነበረ፡፡ በክፍሉ እንደምንመለከተው ኢየሱስ በቤተልሔም ከተማ በተወለደበት ሰዓት የጌታ መልእክት  በከተማይቱ ዳርቻ ላይ ለእረኞች ሰማያዊ አዋጅ ተናገረ፡፡  ቃሉ በሉቃስ ወንጌል 2፡11 ላይ እንዲህ ላል፡፡ በዚያ ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ፡፡ እነሆ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ፡፡ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፡፡ በታላቅ ፍርሃትም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው፡ እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፡፡ ዛሬ በዳዊት ከተማ   መድኃኒት እርሱም ክርስቶሰ  ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡  እንግዲህ የቤተልሔም ከተማ ይህን ታላቅ መልእክት መገንዘብ ነበረባት፡፡ እነርሱ ብቻም ሳይሆን ከዚያም በኋላ የነበሩ አብተ ክርስቲናትም ይህንን የመላእክት ስብከት ማስተዋል ነበረባቸው፡፡ በአሁኑም ዘመን በተለያዩ ኣለም ማዕዘናት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል የሚያከብሩ ሁሉ ዛሬ ይህንን መልእክት የምነሰማው እኛም ጭምር ይህን መልክት በጥልቀት በመረዳት ሌሎችም ልንመሰከር ይገባናል፡፡ መልእክቱ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፡፡ እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ በማለት ይጀምራል፡፡ ይህ መልእክት የተነገረው ለእረኞች ነው፡፡ በዚያን ጊዜ እረኞቹ ሜዳ አዳሪዎች ነበሩ፡፡ እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ በቤተ ልሔም ከተማ ባለው የሕዝብ ምዝገባና ቖጠራ ሲደረግ እንደሌሎቹ እነርሱ ሊመዘገቡ አልሄዱም፡፡ በሜዳ ነበር ያደሩት፡፡ ይህን ጊዜ አንድ አስደናቂ ነገር ሆነ፡፤ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ፣ ከዚያም የተነሳ የጌታ ብርሃን በዙሪያቸው አበራ ይላል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ነገር ግን የቤተልሔም ከተማ አስቀድሞ የተነገረላትን የተስፋ ቃል አለማሰብ ብቻ ሳይሆን አሁን ደግሞ የሚነገራትን መሠራታዊ መልእክት ልትሰማ የምትችልበት ጆሮና አቅም አልነበራትም፡፡ ስለዚህ ይመስለኛል የጌታ መልአክ ከተማውን ትቶ ከዚያ ውጭ በሜዳ ላደሩ እረኞች የተገለጠው፡፡ ስለዚህ መላእከቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩበትን መልእክት ለእረኞቹ አስተላላፉ ይህንን መልእክት እንመለከታለን፡፡ ከሰማይ የመጡት የጌታ  መላእክት ያስተላለፉት መልእክት የራሱ በህሪያት( character) አሉት፣ ሽፋንም(scope ) አለው‹ እንደገና ይዘትም(content) አለው፡፡
የመልእክቱን  ባሕሪይ content  ስናየው ይህ መልእከት የምሥራች ነው፡፡ የምሥራች ማለት መልካም ዜና የምንለው ነው፡፡ በአንድ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ላለ ሰው ያ ጉዳይ መፍትሔ እንደተገኘለት ሲነገር የምሥራች ወይም መልካም ዜና  ይሆናል ነው፡፡ ዌም ደግሞአንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነበር በመዘግየቱ ምክንያት ልብ ወደቆ ባለበት ሰዓት የዚያን ጉዳይ መከናወን በድንገት ሲነገር የምስራች ይናል ማለት ነው፡፡ ይህን ለመረዳት እንዲህ አድርገን እናስብ እስቲ! ልጃዋ ወደ ጦር ሜዳ ሄዶ በውጊያ ላይ እያለ በጠላት ወገን ጦር በወታደራዊ የበላይነት ተማርኮ የመወሰዱን ዜና የሰማች እናት የልጇን መሞት ወይ በሕይወት መኖር ዜና መስማት በቀንና በሌሊት በልቧ ውስጥ ሳለ ምንም ሳትሰማ ዘመናት ስላለፉባት ተስፋ ቆርጣ አልቅሳ አንብታ ወገቧን በጨርቅ ጥፍንግ አድርጋ አሥራ የእተከዘች ሳለ አንድ ሰው ወደ እርሷ ቀርቦ ስሟን ጠርቶ ያ  በጠላት ወገን ተማርኮ የወሰደው ልጅሽ ፣ ገና በሕይወት አለ፣ እንዲያውም ወደ አንቺ እየመጣ ነው ፣ እኔም አይቼዋለሁና ደስ ይበለስሽ ብላት ይህ ለዚች ሴት የምሥራች ወይም መልካም ዜና ነው ማለት ነው፡፡ እንዲያውም ለማን የሚስቸግር አስደሳች ዜና ይሆንላታል ማለት ነው፡፡  ልክ እንዲዚሁ የመላእክ የተናገሩት አሳብ  በሮማውያን የአገዛዝ  ቀንበር ሥር ሆነው ለተጨነቁ ሕዝቦች ፣ በጨለማ ለኖሩ ለዓለም ሕዝቦች ብርሃን መምጣቱና ያ ጨለማ በብርሃን ኃይል የሚለወጥበት አንድ ተአምር ስለ መፈጠሩ ሲሆን ይህም ለሰው ሁሉ መነገር ያለበት ታላቅ ደስታ የምሥራች ነው፡፡ መልካም ዜናዎች ሁሉ አውራ  ነው፡፡
የመልእክቱን ሽፋን ስናየው ለሰው ሁሉ የሚሆን ነው፡፡ (It is global )ኣለም አቀፋዊ ነው::  ምንም እንኳን መልእክቱን የተቀበሉት በሜዳ ላይ ያሉ እረኞች ቢሆኑም ይህ የምሥራች ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ነው፡፡ ምክንያቱም በኃጢአት ቀንበር ውስጥ ያለው  ሰው ሁሉ ስለሆነ ነው፡፡ ሁሉም ኃጢአትን ስለሠራ የእግዚአብሔር ክብር በሁሉም ላይ ስለጎደለ ሁሉ የሞት እዳ አለበት፡፡ እዳ ደግሞ አስጨናቂ ነው፡፡ እዳ ያለበት ሰው አርፎ አያድርም እንቅልፍም አይወስደውም፡፡ ኃጢአተኛው ሕዝብ ደግሞ ተራ እዳ ሳይሆን የሞት እዳ ያለበት ነው፡፡ ስለዚህ ኑሮው ሁሉ የጭንቅ ኑሮ  ነው፡፡  ነቢዩ ኢሳያስ በኢየሱስ መምጣት ምክንያት ሊገለጥ ስለለው ፍትሔ       ( Resolution) ሲናገር እንዲህ አለ፡፡ ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም…..በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፣ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ይላል (ኢሳ 9፡1-3)፡፡ ከዚህ በላይ የምሥራች የለም፡፡ በጨለማ ውስጥ ለምንደፋደፉና የሕይወት ተስፋ ለማይታያቸው የሚደነቅ ብርሃን ስለመውጣቱ ከመናገር በላይ የተሻለ የምሥራች የለም፡፡ ይህ ምሥራች ነው( This is the good news that must be told to all people, in every  corner of the World)፡፡ የምሥራችነቱ ለእረኞቹ ብቻ አይደልም ፣ በቤተልሔም ከተማ ላሉ እንግዶችም ሁሉ ነው፡፡ ከዚያም በኃላ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ፣ ነገሥታት ሁሉ፣ ለአብያክርስቲያናት ሁሉ፣ በእኛም ዘመን ላላነው ሁሉ ለሀያላን ሁሉ፣ ለመኳንንት ሁሉ ፣ ለጥቁሩ ለነጩ፣ ለሴት ለወንዱ ለሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች ነው፡፡ ወገኖቼ ሖይ የኢየሱስ መወለድ የምሥራች ( The good tiding, wonderful hearald) ነው፡፡ ይህ እንግዲህ መላአኩ የሰበከው ስብከት ባሕሪይ ይህንን የሚመስል ነው፡፡
የመልእክቱ ይዘት (content) ምንድነው ብለን እንጠይቅ፡ አንዳንዴ ምንም ይዘት ይሌላቸውን ሰማይዊ ቁም ነገር ያላዘሉ ስብከቶችን ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? በዚህ ሥፍራ የእግዚአብሔር መልአክ የሰበከው ስብከት አስደናቂ የሆነ ሰማያዊ ቁም ነገር ያለበት ነው፡ ፡የጌታ መላእክት የተናገሩት መልእክት ይዘት እንዲህ የሚል ነው፡፡ ያ ሲጠበቅ የነበረው ወንድ ልጅ ተወልዶላችኋልና አትፍሩ፣ ብርሃን ተወልዶላችኋልና አትፍሩ ይላቸዋል ይህ የተወለደውን እንደሚከተለው   ይገልጸዋል፡፡
መድኃኒት ተወልዶላችኋል የሚል ነው፡፡ የተወለደው ጌታ ኢየሱስ መድኃኒት ነው፡፡ ይህ የነገር ሁሉ መቋጫ ነው፡፡ በእኛና በጌታ መካከል ላለው ግንኙነት እና ዝምድና ማዕከል ነው፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያስፈለገበት ምክንያቱም ይህ ነው፡፡ በኃጢአት የተበከለው የሰው ልጅ ሁሉ ፣ ዓለም ሕዝብ መድኃኒት( አዳኝ) የሚሆነውን ይፈልግ ነበር፡፡  መላእክት ያሉትን ይህ አሳብ ልብ ብለን ያየን እንደሆነ ከብሉይ ኪዳን መዳን ( Salvation)  ከሚለው አሳብ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ እግዚአብሔርም መልኣክ ለማርያም በተናገራት እንደምትጸንስና ወንድ ልጅንም እንደምትወልድ ስሙንም ኢየሱስ እንደምትለው ከተናገር በኋላ እርሱም ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል አላት፡፡ ኢየሱስ ሲል አዳኝ ጌታ ማለት ነው፡፡ በዚም ክፍል እንደምናየው ጌታችን ኢየሱስ መድኃኒት ነው፡፡ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ለኢየሱስ ከተሰጣቸው አስደናቂ ስሞች አንዱ መዳን ወይም መድኃኒት (Savior ) የሚል ነው፡፡
አንዳንድ ለዘብተኛ ሰዎች ይህ አሳብ የአዲስ ኪዳን አሳብ እንጂ ከብሉይ ኪዳን ጋር ግንኙነት የለውም ምክንያም እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን ጨካኝ፣ የሚቀጣ፣ በእሳት የተመሰለ በቀለኛ  ብቻ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክችን በብሉይ ኪዳንም ቢሆን ለህዝቡ አዳኛቸው ነበረ፡፡ ረዳታቸው ነበረ፡፡ ከአንበሳው አፍ ሕዝቡን ያዳነው፣ ከእሳትና ከውሃ ያስመለጣቸው ፣ ባሕሩንም ከፍሎ ሕዝቡን ካሸገረ በኋላ ከፈርዖን ሰይፍና ጦር ያዳነው እርሱ እግዚአብሔር ነበር፡፡ እንዲያው እግዚአብሔር አዳኝ ሴልቪሺን በሚለው ቃል ከ180 ጊዜ በላይ በብሉይ ኪዳን ተጠቅሷል ፡፡ የእግዚአብሔርን አዳኝነት ትዕብተኞች የሆኑ የአህዛብ ነገሥታትም  ጭምር እስክመሰክሩ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናቸው ነበር፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 3፡28-29 እንደምናበው ናቡካድናጾርም መልሶ መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፎ የሰጡትን የንጉሡን ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ የስድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ…. እንደዚህ የሚያድን አምላክ የለምና (ዳን. 3፡28-28)፡፡ እንደ ቤልና ናባው ያሉ የተፈሩ የባቢሎናውያን አማልት ነበሩ፡፡ ቤል ( በአል) ማለት ሎርድ ወይም ጌታ ማለት) ነው፡፡ ቤል ጌታ ይባል እንጂ ሕዝቡን  አያድንም፣ እግዚአብሔር ያህዌ ግን ያድናል፡፡ ቤል ጸሎት አይሰማም ፣ አምላዎቹ ሰውነታቸውን በጭሬ እየቧጨሩና እያደሙ ከጠዋት አስከ ቀትር ድረስ ወደ እርሱ ቢጮኹም እርሱ አይሰማቸውም፡፡ የእሥራኤል አምላክ ያህዌ የተባለው ግን ጸሎትን ሰምቶ በእሳት ይመልሳል፡፡ ቤልና ናባው በደካማ እንስሶች ጭነት ይሆናሉ እግዚአብሄር አዳኙ ግን ሕዝቡን እስከ ሽበት እስከ ሽምግልና ይሸከማል፣ እርሱ ያድናል፡፡ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ዘመን እርሱ ለሕዝቡ የሚያደርገው አስደናቂ ሥራውና ሆነ እርሱ ራሱ ደግሞ መድኃኒት ተብሏል፡፡ 
ይህ ስም በአዲስ ኪዳን ኃጢአተኖችን ሁሉ ሊያድን ለተገለጠው ለጌታ ለአየሱስ ተሰጥቶታል፡፡ ለምሳሌ ማርያም ስትዘመር  ነፍሴ አምላኬን መድኃኒቴን ታከብረዋለች( ሉቃስ 1፡47) አለች፡፡ ካህኑ ዘካሪያስም መጥመቁ ዮሐንስ በተወለደና ቤተሰቦቹም ወደ ቤተመቅደስ ባመጡበት ወቅት ስለ ኢየሱስ ትንቢት ሲናገር እንዲህ አለ፡ ከጥንት ጀምሮ በነበሩት ቅዱሳት ነቢያት አፍ እንደተናገረ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳንን ቀንድ አስነስቶአልና፣ ማዳኑም ከወረደረኞቻችንና ከሚጠሉን እጅ ነው(ሉቃሰ 1፡68-71)፡፡ የዮሐንስ ወንጌል 4፡42 እንደሚነግረን የሰማሪያ ሰዎች ኢየሱስ ያስተማረውን ሁሉ ሰምተው በእርሱ ካመኑ በኋላ ለሰማሪያዊቲቱ ሴት ሲናገሩ እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን አሉ ፡፡ ልክ መላእክት ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እንዳሉ ሁሉ የሰማሪያም ሰዎች ኢየሱስ የዓለም መድኃኒት ነው አሉ፡፡
በአዲስ ኪዳን የመጠልን የተወለደለን ጌታ ኢየሱስ ነው፣ እርሱ መድኃኒት ነው፡፡ መድኃኒት ሰጭ አይደለም፡፡ ራሱ መድኃኒት ነው፡፡ No expairation date ኤክፓየር የማያደርግ መድኃኒት ነው፡፡፣ ለዘመናት የኖር ግን በየእለቱ አዲስ የሆነ መድኃኒት ነው፡፡ እርሱ ብቻ ስለሚያድን መዳን በሌላ በማንም የለም ተባለ፡፡ በኢየሱስ ዘመን ብዙ ባለ መድኃኒቶች ስለነበሩ ሕመምተኞቸ ወደ እነርሱ ይሄደ ነበር፡፡ ነገር ግን ያላቸውን ከስረው ሕመማቸውም ይብሰባቸውና ጉዳም በላያቸው ጨምረው ወደ ቤታቸው  ይመለሱ ነበር፡፡ የባለመድኃኒቶች መድኃኒት ለሕመምተኖች ሌላ ሕመም ይሆንባቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን የታመሙት ከሕመማቸው ይፈውሳቸው ነበር ይህም ብቻ ሳይሆን  ፈውሱ በነጻ ያለ ዋጋ ነበረ፡፡ ያ ጌታ አየሱስ ዛሬም በጨለማ፣ በህመም በእንቆቅልሽ ውስጥ ላሉት ሁሉ መድኃኒታቸው ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር የተሰጠው መድኃኒት ወይም አዳኝ የተለው ስም በኢየሱሰስ በኩል ነው የተገለጠው፡፡ ኢየሱስ መድኃኒት ነነው፡፡ ስለዚህ ይህን የገታ የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ብናከብርበት ጊዜ ኣመት በዓል አይደለም እያከበርን ያለነው፡፡ ወይም አውደ ዓመት እያሳለፍን አይደለም ያለነው፡፡ ለእና ይህ የመብላት፣ ወይም የመጠጣት ወይም በዓል ማድመቅ አይደለም፡፡ ከምንላውና ከምንጠጣው ሁሉ ባለፈ እጅግ በጣም የሚስደስተን ነገር የነፍሳችን መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ መምጣቱ ነው፡፡  መድኃኒት ተፈልጣል፣ መዳን በሌላ በማንም አልተገኘም የለምም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከሰማይ በታች የኢየሱሰስ ስም ብቻ ሆነ፡፡ ሃሌሉያ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት  ያድናል፣ ከመከራ ሁሉ ያድናል፣ በዓለም ካለው ጭንቅ ሁሉ ያድናል‹ ከጨለማ ያወጣል፣  እርሱ መድሃኒት ነው፡፡ መድኀኒትነቱ ለሥጋ በሽታ ብቻ አይደለም፡፡ እርሱ ለምድር ፓለቲካ፣ ለሃማኖት ሁ ለምድር ምጣኔ ሀብት ሁሉ፣ ለዚህ ምድር ለአየሯ ፣ ለነፋሳት ሁሉ መድኃኒት ኢየሱስ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ኢየሱሰስ የት ናው ያለው; የዓለም መንግሠታት ኢየሱሰስን ከፖፐቲካቸው አስወጥተውታል፣ አብያክርስቲያናትም ይህንን መድኃነኒት ከቤታቸው አስወጥተው መድረኩን ብቻቸውን ሞልተውታል፡፡ ኢየሱስ በበርካታ ቦታዎቸ ላይ ዛሬ የለም፡፡ ነገርግን ኢየሱሰስን ወደ ውስጣቸው ቢገብዙት፣ እንዲሰጥንባቸው ቢብዙት ኖር፣ ባለትዳሮች ከቤታቸው ያስወጡትን ጌታ ልሰው በቤታቸው ከመሾሙት አስደናቂ ፈውስ ይሆን ነበር፡፡ ለአሜሪካና ሌሌሎች የበለጸጉ አገሮች እድገትና ለልዕለ ኀያልነታቸው ምክንቱ የጥንት አባቶቻቸው ከእግዚአብሔር የነበራቸው መሰጠጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህች ምድር ሀታዋንና አምላኳን የሚገፋ ትውለድ ስለበዛ፣ ስለኢየሱስ ማሰብ ሞንነት ወይም ከዚያ አልፎ ወንጀል እስከሚሆንበት ድረስ የሚየያስበ ትውልድና የፖለቲካ መሮዎች ስተበራከቱ ምድሪቱ የከፍተኛ የሞራልና መንፈሳዊ ውድቀት ውስጥ እተፈቀች ትገኛለች፡፡ መድሃኒቱን ስለጣለት እርሷም አብራ እየወደቀች ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ይህንን መድኀኒት በሕይወታቸው ቢሾሙት ኖሮ ያድናቸው ነበር ምድራቸውን ይፈውስላቸው ነበር፣ ትዳራቸውን ይፈውስላቸው ነበር፡፡ እነርሱ በአል ያደምቃሉ፡፡ የበኣሉን ጌታ ፣ በበአሉ ጊዜ የደሰሱበሰት የደስታ ምክንያ ሖነውን ጌታ ከፍተው ዳር አስወጥተውታል፡፡ በአፋቸው ጌታን የሚያመልኩ ይመስላሉ ግን በልባቸው በፍጹም ክደውታል እናዲያው ጦር ስለው ሳያሳድዱትም አይቀሩም፡፡ ሠይጣም የዚህ ዓለም ፈውስ ያለው በኢየሱስ እንደሆነ ስለሚውቅ የዓም መንግሥታት ኢየሱስን እነዳያስጠጉት እና ፈውስም እንዳይኖራቸው ያለመታከት እየተዋጋ ነው፡፡ ትዳር ኢየሱስ ኖሮ ባልና ሚስት የተፈወሰ የትዳርን ሕይወት እነዳጣታሙት መድኀኒት የሆነውን ጌታ ከትዳራቸው ከፍትረው እንዲያስጡ ያለው ዓላማው እየተሳካለት ነው፡፡  የዛሬ ዓለም  ሙሽራ በሌለበት ሠርግ ቤት እንደሚጨፍሩ ሰዎች ኢየሱስን ከሕይታቸው አውጥተው በዓል የሚደያምቁና የሚያከብሩ ሰዎች የበዛበት ሀኗል፡፡ ወገኖች ሆይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታታ እንዳየነው እኛ ባለንባት በዚህ በአሜሪካን አገር ብዙ አብያተክርሰቲናት የክርስተማስ በዓል በድንቅ ሁኔታ ያከበሩታል፡፡ ድራማው፣ ግጥም ንባቡ፣ እንዲያውም በአንዳንድ ቤተክርቲያናት የሚለኮሰው የገና መብራት የጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ በአምና በአንድ ቤተክርሲያን አዳራሽ ብቻ 25000 መንራቶች ተለኩሰው ነበር፡፡ እንደዚህ የሚደርጉ ብዙ ጸሎት ቤቶች ቢኖሩም ዪያኑ ህል የጌታ አዳኝነት ሲመሰከር አይታይም፡፡ ይህ አስደናቂ መልእክት  በቤተ ልሔ ከተማ ዳርቻ ይሰበክ ነበር ያውም እግዚአብሔር ከሰማይ በላከው መልአክ በኩል የተሰበከ ሲሆን ቤተልሔም ከተማ ግን ይህን መልእክት አልሰሙም ፡፡  የተወደዳችሁ ወገኖች ሆይ ፣ እህቶቼና ወንድሞቼ ዛሬ የጌታን ልደት ስናከብር ደስ ይለናል፡፡ የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመን ደስ በሚያሰኙ ሁኔታዎች ሁሉ ይህንን ልደት በደማቅ ሁኔታ ልናከብረው እንችላለን ግን ቁም ነገሩ ጌታ ኢየሱስ የተናገረውን ስለ እርሱን የተነገረንን እውነት እንሰማለንን; ለኣለምስ እንሰብካለንን፡ እርሱ መድኃኒታችን እንደሆነ አውቀን ደስ ይልናልን፡ እግዚአብሔር የሰጠንን የተስፋ ቃል እየጠበቅነው ነው? ኢየሱሰስ በልባችን ሥፍራ ያለው ጌታ ነውን? የቤልሔም ከተማ እንደፈለገችው ሆና አልፋለች፡፡ ቢህ ምድር ያሉው የጊው ሁኔታ እንምናየው ይሁን፡፡ እኔና እናንተስ ለእኛ ኢየሱስ ማን ነው? በየትኛው ሥፍራ አስቀምጠነዋል? የእኛ ከሆኑት ነገሮቻችን ሁሉ አስወጥተነው እደጅ ነው ወይ እቤታችን በጓዳችን የነገሠ የሰለጠነ ንጉሳችን ነው? እርሱ እንዲ ይላል እኔሆ በደጅ ቆሜ እንኳኳለሁ ምንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትል ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር ራት እበላለሁ፣ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፡፡
ከመላእክቱ ትምህርት ውስጥ እጅግ በጣም አስደናቂው  ነገር በመልእክቱ ውስጥ እረኞችን ያደረታቱበት መንገድ ያስደንቀኛልና እርሱን ተናግሬ እንጨርስ፡፡ የምስራች አምጥቼላችኋለሁና አትፍሩ የሚል መልእክት ሰጣቸው፡፡ አትፍሩ ምክንያምቱም አሁን ተወለደው መድኃኒት ስለሆነ ፣ አዳኝ ነውና ፣ ኢየሱስ ነውና አትፍሩ፡፡  በተለይም ደግሞ እረኞች የሚኖሩበትን ዓይነት ሕይወት ለሚኖሩት ሰዎች እንደዚህ ዓይነት የማጽናናት መልእክት ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ የሚያስፈራ ዘመን ነበረ፡፡ ምክንያቱም እረኝነት የከበረ ሥራ አልበረምና:: በኢየሱስ ዘመን በሮማውያን ዘንድ እረኝነት ዝቅ ተደርጎ የሚታይ ማንነት ከመሆኑም በላይ ሙያውም ያልከበረና ንጹህ እንደሆነም የማይተሰብ ነበር፡፡ ስለዚህም ሊሆን ይችላል እነዚያ እረኞች ሕዝብ ወደሚቆጠርበት ሥፍራ ከመሄድ ይልቅ በሜዳ መንጋዎቻቸውን ሲጠብቁ ማደርን የመረጡት፡፡ ይሁን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሆነው መልእክት ሲል በመጀመሪያ እነርሱን በማጽናናት ጀመረ፡፡ ስለዚህ እረኞችን መልአኩ እንዲህ አላቸው፡፡ አትፍሩ! የምትፈሩ አትፍሩ መድኃኒት ተገኝቶላችኋልና፡፡  ኢየሱስ ተወልዶአልና፡፡ አትፍሩ! አትፍሩ፡፡ የተነገረው መልእክት አስገራሚ የሆነው ደግሞ ጌታ የተወለደው ለእናንተ ነው፡፡ ይህንን በሁለት ቃላት ይገልጻል፡፡ የምስራች እነግራችኋለሁ፣ ተወልዶላችኋልና፡፡  ይህ በደንብ የሚገባን በእንግሊዝኛ ስናነበው ነው፡፡
And the angel said unto them, Fear not: for, behold, I bring you good tidings of great joy, which shall be to all people. For unto you is born this day in the city of David a Saviour, which is Christ the Lord.

በሕብረተሱ ውስጥ የክብር ሥፍራ ያላገኙ እረኞች፣ ሜዳ አዳሪ የነበሩ፣ ዝምድናቸውና ዉሎአቸው ከከብት ጋር የነበረ እነዚህ ሰዎች  አስደናቂ በሆነው የእግዚአብሔር ክብር ሲጎበኙ እጅግ ያስደንቃል፡፡ እረኞቹ ለማመን ተቸግረው ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይም ደግሞ ይህ መድኃኒት የተወለደው ለእናንተ ነው ሲባሉ ያቺን ቀን እንዴት ባርከው ይሁን፡፡ በእግዚአብሔር የተጎበኙባት ያቺ ሌሊት እንዴት አስደናቂ ናት፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈልግሃል ሲሉን ለማመን  እንቸገራለን፡፡ እኔን ፣ እኔን ደካማውን ደካማዋን፣ እኔን ሞኙን እኔን ኃጢአተኛውን እንዴት ብሎ ነው ያልንባቸው ቀናት አሉ፡፡ እኔም ራሴ እገረማለሁ ኢየሱስ ለእኔ መምጣቱ፣ የእኔን ታሪክ መቀየሩ፣ ያስገርመኛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኔን እግዚአብሔር ያየኛልን ብለን የምጠይቅበት ጊዜ እንዲያውም ብዙ ነው፡፡ አሁን ይህንን ፕሮግራም ለመካፈል ስትመጡ እንኳን እግዚአብሔር እንደሚያያችሁና ጸሎታችሁን እንደሚሰማ ሳይመስላችሁ የምትቸገሩ ሁሉ አላችሁ፡፡ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ ሆኜ እንግራችኋለሁ፣ ይህ መልእክት ለእናንተ ነው፡፡ የአንቺ ነው አትፈሪ፣ ወንድሜ ሆይ ይህ መልእክት የአንተ ነው አትፍራ ምክንያቱም ኢየሱስ መድኃኒት ሆኖ የተወለደው ለንተ ነው፡፡ ተወለወዶልሃል ፣ እርሱ መድሃኒት ተገኝቶልሻል፡፡ ወገኖቼ ሆይ እባካችሁ ጌታን የራሳችሁ አድርጉት፡፡ ሌሎች ሰዎች አምላክ አታድርጉት እነዚያ እርሱን የሚያመልኩና እናንተ ግን አጃቢዎች አድርጋችሁ አትውሰዱ፡፡ እርሱ የናንተም ጌታ ነው፡ ለእናንተም መድሃኒት ነው፡፡ ኢየሱስ የበሽታ መድኃኒት ፣ የትዳርህ የትዳርሽ መድኃኒት የልጆቻችሁ መድሃኒት የእርሻችሁ የሥራችሁ የጓዳችሁ መድኃኒት ነው፡፡  ስለዚህ አይአችሁ አትፍሩ፡፡ ይህ ለሕዝቦች ሁሉ ሊነገር የሚገባው ታላቅ የምሥራች ነው ሃሌሉያ፡፡
የምሥራች ዛሬ መድሐኒት ክርስቶስ እርሱ ጌታ የሆነው የተወለደው ለእኛ ነው፡፡ ለእረኞች የታወጀው መልካም ዜና መድሐኒት ተወልዷል ብቻ ሳይሆን ተወልዶላችኋል የሚል ነው፡፡ የኢየሱስ መወለድ የምሥራቹ በመጀመሪያ ለግላችን ነው ፡፡ ለእኔ ነው ብለን የምንቀበለው ነው ፡፡ ለእኔ ለኃጢያተኛው ተወለደ ፡፡ እኔን ከጥፋት ፈልጎ ሊያገኘኝ እርሱ ተወለደ፡፡ ለእናንተ ተወልዶለችኋል፡፡ ይህ የተወለደው መድኃኒት የእኛ ነው፡፡  የእኛ ጌታ ኢየሱስ የተወለደበት ቀን ያቺ ሌሊት ከቀኖች ሁሉ ልዩ ቀን ናት፡፡ በየእምነት ቤቱና ሥርዓቱ በተለያዩ ቀናት ቢታሰቡም ያቺ ልናያት ያልቻልናት ግን ሁልጊዜ የምናስባት ቀን የከበረች ቀን ናት፡፡ እግዚአብሔር እኛን የጎበኘበት ቀን ያቺ ቀን ያቺ ሌሊት የተባረከች ትሁን ፡፡ የምሥራቹን ቃል የሰማሁባት ቀን /ሌሊት መድኃኒቱ ኢየሱስ የተወለደልን ያቺ ቀን ያቺ የደስታ ምሽት ከቀኖች መካከል የተባረከች ትሁን፡፡ እግዚአብሔር የሠራት በእርሷም ደስ የምንሰኝባት ያቺ ትታሰብ በጨለማ ለምንሄድ ታላቅ ብርሃን የበራልን ያቺ ቀን ትወደስ ትባረክ፡፡ በቀኖች ሁሉ መካከል ከፍ ትበል ያቺ ቀን ኢየሱስ ሥጋ ለብሶ በበረት በግርግም ተኝቶ የተገኘባት ሌሊት ያቺ ሌሊት ውድናት ዋጋዋ በብዙ አልማዝና እንቁም አይመዘንም የተባረከች ትሁን ስትታሰብ ትኑር ፡፡ አትረሳ ያቺ ቀን የምሥራቹን የሰማንበት ቀን አብረን ደስ የምንሰኝባት ምሽት መልአኩ  ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፡፡ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ” አለን ፡፡  ዛሬ ለዓለም ሁሉ የምሥራች የምሥራች የምሥራች!!  


Thursday, June 11, 2015

የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ወይስ የሙሉ ልብ አገልጋዮች?

      

በቤተክርስቲያን ለምናገልግል አገልጋዮች "የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች" የሚል ስያሜ ወይም ማዕረግ ይሰጠናል፡፡ ወንጌላውያን መጋቢያንና አስተማሪዎች ብሎ ባለን ጸጋና በተሰማራንበት የአገልግሎት ሥፍራ መሠረት መጥራት በቂ አይደለምን እየልኩ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ እኔም በቤተክርስቲያን ሳገለግል ከሌሎች ጋር በአንድ ላይ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እየተባልን ስንጠራ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ይህ አበባል አገልጋዮቹ የትኞቻችንም ቢንሆን ሙሉ ጊዜአችንን ለጌታ አገልግሎት የሰጠን መሆናችንን የሚያመለክት አባባል ነው፡፡ ወንጌላዊም ሆነ መጋቢ ሌላውን ትተው ለጌታ ስራ ሙሉ በሙሉ ጊዜኣቸውን ስለሰው የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ብለን ብንላቸው ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ይሁን እንጂ የአገልጋዮችን አገልግሎት ከጊዜ ጋር ካያያዝነው በአገልጋዮችና በሰራተኞች መካከል ልዩነት መኖር አለመኖሩን መመልከት ይኖርብናል፡፡ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞች የምንላቸው አሉ፡፡ እነዚህ በተሰማሩባቸው የሥራ መስኮች በቀን 8 ሰዓት በሥራ የሚያጠፉ ሲሆኑ ከዚያ በታች የሚሠሩ ከሆነ ደግሞ የግማሽ ጊዜ ሠራተኞች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ሙሉ ጊዜ ወይም የግማሽ ጊዜ ሠራተኝነታቸው የሚወሰነው ሠራተኞቹ በሥራ ላይ የሚያሳልፉት የሰዓት መጠን ነው፡፡የሚያገኙት የገንዘብ መጠንም በዚያው መጠን የተለያየ ይሆናል፡፡ በቀን 5 ሰዓት የሠራ ሠራተኛ የሚያገኘው ደመወዝ በቀን 8 ሰዓት የሚሠራው ሠራተኛ ከሚያገኘው እጅግ ያነሰ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ሠራተኞቹ በሥራ ቦታቸው የሚያስመዘገቡትም ውጤት የዚያውኑ ያህል ልዩነት አለው፡፡
ወደ አገልጋዮች ሁኔታ በምንመለስበት ወቅት የእኛን ሁኔታ ከሠራተኞች ሁኔታ ለይቶ መመልከት ይቻላል፡፡ የአገልጋዮች የአገልግሎት ሁኔታ በሰዓት የሚወሰን ሳይሆን ከጌታ ዘንድ በተቀበልነው ጥሪና በውስጣችን ባለው፣ በእኛም በሚገለጠው ጸጋ መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ ወንጌላዊን ወንጌላዊ የሚያሰኘው እርሱ በቤተ ክርሰቲያን ያሳለፈው ሰዓት መብዛት ወይም ማነስ ሳይሆን ጥሪውንና ጸጋውን የገለጠበት መንገድና ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ ነው የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ከምንባል ወንጌላውያን ፣ መጋቢያን፣ ወይም መምህራን ብንባል ይሻላል ያልኩት፡፡
አገልጋዮች ራሳቸን ስለ ራሳችን ስንናገር የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ነን ስንል እንደመጣለን፡፡ እኛ ካልነው ደግሞ በግልጽ መታየት ያለበት ነገር አለ፡፡ አገልግሎትም ቢሆን ከጊዜ ጋር የሚሄድ እንጂ ከተሰጠን ጊዜ ውጭ የሚሰራ ነገር አይደለም፡፡ ጊዜዬን ሙሉ በሙሉ ለጌታ ሰጠሁ የሚል ከሆነ ከእኛ አንድ አገልጋይ በቀን ስንት ሰዓት በጌታ ሥራ ላይ ያሳልፋል? ወይስ እኛ ቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊ ብላ ስለተቀበለችን ሌላ ሥራ ሳንሠራ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ስለምናሳልፍ ብቻ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ተባልን? በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ካለን አገልጋዮች መካከል በቀን 8 ሰዓት ይቅርና በታማኝነት 4 ሰዓት የምንሠራ ስንቶቸችን ይሁን?ይህንን ለመመዘን የሚያስችል ሥርዓት በቤተ ክርሰቲያን ውስጥ ስለሌለ እንዲሁ በደፈናው የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እየተባልን አገልግሎቱ ይጓተታል፡፡ በሌላም በኩል አገልጋዮቹ ትክክለኛ የጌታ ጥሪ የደረሳቸው ሲሆኑ ቀስቃሽና ጎትጓች ሳይፈልጉ የኃላፊነት ስሜት እየተሰማቸው አገልግሎታቸውን በትጋት ይወጡታል፡፡ በውስጣቸው ያለው የአገልግሎት ሸክም በአጥንታቸው ውስጥ እንደሚሄድና እንደሚነድድ እሳት ሲሆንባቸው ጊዜ እንቅልፍ እንኳ ሳይተኙ ለጌታ ሥራ ሌት ቀን ይሮጣሉ፡፡ ምንደኝነትና የአገልጋይነት ስም የቀላቀለባቸው አገልጋዮች ግን ከሥራ ይልቅ ስለሚሰጣቸው ስም ሲሟገቱ የአገልግሎት ጊዜአቸው ከፊታቸው ሮጦ ያልቅባቸዋል፡፡ እኔና አንባቢ ከየትኞቹ ነን?
በትጋት የሚያገልገሉ አገልጋዮች ከሚገባው ሰዓት በላይ ሰርተው ነገ ለሚጠብቃቸው አገልገሎት ጉልበት እንዳያጡ፣የዛሬው ዉጤታቸውም እንዳያንስ ቤተ ክርስቲያን ተገቢ እንክብካቤና ጥበቃ ታደርጋለች ወይ የሚለው ደግሞ ሌላ ጥያቄ ነው፡፡ እንዲያውም አንዱ ሲሰራ ቆመን ጸሐይ ከምንሞቅ አገልጋዮች ይልቅ በሥራ በሚጠመዱ ላይ ተጨማሪ ሥራ በላይ በላዩ እየተሰጣቸው ከጫና ብዛት የተነሳ እንዲገዳገዱ ይደረጋል፡፡ ቆመን የሚናወራውና የሚንተቸው ግን የሥራ ኃላፊነት መሸከም የማንፈልግ ደግሞ ተደማጭነት ያለን እኛው መሆናችን የበለጠ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ሠራተኞች እያሉ ተናጋሪዎችን ፊት ለፊት እያቆሙን ሰዎች ምሥጋናውን ሁሉ ለእኛ ይሰጡናል፡፡ ምክንያቱም እኛ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እያልን ስለሚያወራና ስለሚናስወራ ለሰዎች የተሸለ መንፈሳዊ እንመስላቸዋለን፡፡ አሁን አሁን በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ትኩረት የሚሰጠው ለሚሰሩ ሳይሆን ብዙ ለሚያወሩ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያን በአፋቸው ለሚኖሩ የተሸለ መሸሸጊያ ሆናለችና፡፡ ሥራ ካጣሁ ካጣሁ ወንጌላዊነት እንኳ ቢሆን አገኛለሁ እንጂ አልወድቅም ያለም ወንጌላዊ እገሌ ፣ፓሰተር እገሌ እየተባለ ነው፡፡ አንባቢ አጋነንክ አይበለኝ እንጂ አሁን አሁንማ ያሉን ምዕመናን የግማሽ ያህሉ ፓስተር ሊሆን ነው፡፡ ፓስተርነት ግብር የማይከፈልበት የገቢ ማሰገኛ መንገድ ስለሆነ ሰዎች የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ሃይ በል የሚሉት ከፓስተርነት ነው፡፡ ስለዚህ የምዕመናንም ሕይወት ጥራት የዚያኑ ያህል ነው፡፡
እዉነተኞች አገልጋዮች ለእግዚአብሔር ቤት እድገትና ለወንጌል መሥፋፋት በጣም የሚጠቅሙ ናቸው፡፡ እነርሱ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የምንላቸው ሳይሆን የሙሉ ልብ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጉት የሙሉ ጊዜ ሳይሆን የሙሉ ልብ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ጌታ ከማንም ቢሆን ጊዜውን ሳይሆን ልቡን ይፈልጋልና፡፡ ሙሉ ጊዜውን ሰጠ የምንለው ሙሉ ልቡን የሰጠው ሰው ነው፡፡ የሙሉ ልብ አገልጋዮች እንሁን ፣ የሙሉ ልብ አገልጋዮችንም እናፍራ ፣ ላሉትም እንጠንቀቅላቸው፡፡

ሥልጠና በኢትዮጵያ ላሉ ለወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያናት

      ሥልጠና በኢትዮጵያ ላሉ ለወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያናት

በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የኤች አይ ቪን ሥርጭት ለመከላከል የተለያዩ ሥልጠናዎች ይሰጡ ነበር፡፡ በየቤተ ክርስቲያናት ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች በበጎ ፈቃደኝነት መንፈስ ተነሳስተው በሙያቸው በእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ አገልጋዮችንና አባላትን በማሰልጠን አመረቂ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ በአንጻሩም ደግሞ በየአጥቢያው ብዙ የተማሩና በሙያው የተካኑ ሰዎች እያሉ አንዳንድ ከሙያው ጋር ብዙም ቅርበት የሌላቸው ሰዎች ስለ ኤች አይ ቪ ሥልጠና አዘጋጅቻለሁና ሰልጥነው ሊያሰለጥኑ የሚችሉ 5 ሰው፣ 6 ሰው፣ 4 ሰው ወዘተ ከነመመዝገቢያ ብር ጋር ላኩልን እየተባለ በየጊዜ ጥሪ ይደረግ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ የተባለው ሥልጠና የሕክምና ባለሙያዎች በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ከሚሰጡት ጋር ሲነጻጸር ግን እንዲያው የማላከፍ ያህል እንጂ ቀረብኝ የሚያሰኝ አልነበረም፡፡ አልጠቀመንም ማለቴ ግን አይደለም፡፡ ሌላም ጊዜ ለተመሳሳይ ሥልጠና እነዚያውኑ ሰዎች ይጠሩና አሁንም ሰዎች ተዋጥተው ይሄዱና የተባለውን ሥልሥተና ይካፈሉና ይመጣሉ፡፡ መጥተው እንዳያሰለጥኑ በሕክምና ሙያ እውቀታቸው አጥናፍ ያለፈ ፣ በማስተማር ሙያቸውም እኔ ነኝ ያሉ ሐኪሞች እዚያው እያሉ ደፍረው ላድርግ ማለት ይሳናቸዋል፡፡ ሌላም ጊዜ ሌላው ወገን ደግሞ በኤች አይ ቪ ኤዲስ በዓይነቱ ልዩ ሥልጠና ልሰጥ ተነስቻለሁ ይልና አሁንም ለየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ጥሪ ይበትንና ይህን ያህል ሰው ከመመዝገቢያ ጋር ላኩልን፣ እንዳያመልጣችሁ! ሲል አሁንም ሰዎች ይላኩና ሰልጥነው ይመጣሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደተባለው ሁሉ የሚሄድ አንድ ወንጌላዊ ነበርና አሁንም በሌላ ጊዜ ለተመሳሳይ ሥልጠና ሰው ይመረጥ ሲባል ያ ወንጌላዊ ተጠቆመ፡፡ ይህን ጊዜ አንድ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ እንዲህ አሉ፡፡ ይህ ወንጌላዊ እገሌ ኤች አይ ቪ በአገራችን ከተሰማበት ጊዜ አንሥቶ የሚሰጠውን ሥልጠና አንድም ሳይቀር ሁሉን ተካፍሏል ፣ ታዲያ የዶክተር ዲግሪ ቢሰጠውስ ምን አለበት እንዳሉ አስታውሳለሁ፡፡ እውነት ለመናገር ያ ወንጌላዊ ሥልጠና ወዳለበት ሁሉ ይሄዳል፣ ይካፈላል እንጂ የሰለጠነውን ግን ለሌላው አያስተላልፍም ነበር፡፡ ለሕዝብ ሥልጠና ይሰጥ ሲባል እርሱም ሆነ ሌሎች ከሌላ ቦታ ሌላ ሰው ይጋብዛሉ እንጂ አይ ብዙ ሰልጥኛለሁና አሁን እኔ ላሰልጥን ሲል አይታይም ፣ አይደመጥምም ነበር፡፡
ስለ ኤች አይ ቪ እንደ ምሳሌ አነሳሁ እንጂ ብዙ ተደጋጋሚ ሥልጠናዎች ይሰጡ ነበር፡፡ ለሕዝብ የሚዘጋጁ የሥልጠና ፕሮግራሞችን በሚመለከት በጣም የሚታወቁት፣ የጸረ ኤች አይ ቪ ሥልጠና ፣ የወንጌል ሥርጭት ሥልጠና፣ የመሪዎች ሥልጠና፣ ሲሆኑ አልፎ አልፎ የጸሎት ሥልጠና ይሰጣል፡፡ በተደጋጋሚ የሚሰጠው ሥልጠናዎች በይዘታቸው አንድ ዓይነት እንጂ ምን ልዩነት አይታይባቸውም፡፡ ይህ መሆኑ እየታወቀ ሰዎች በተደጋጋሚ እየሄዱ ይካፈላሉ፡፡ ከዚህ ጋር አንድ ላይ ማየት የሚገባው ሌላው ነገር ሥልጠና አዘጋጆቹ ዓላማ ነው፡፡ በየትኛውም ዘርፍ ቢሆን ሥልጠና የሚያዘጋጁ ሰዎች ከዚያ ሥልጠና ምን ጠብቀው ነው ቢባል ብዙዉን ጊዜ ያላቸው ዓላማ የቤተ ክርስቲያን ዓላማ ሳይሆን የአዘጋጆቹ የራሳቸው ዓላማ ነው፡፡ ይህን ለማወቅ ሥልጠናው ያዘጋጁ ሚኒስቲሪዎች የሥልጠናቸውን ሪፖርት የሚያቀርቡት ሰልጣኞችን ለላኩት ቤተ ክርስቲያናት ሳይሆን በገንዘብ ለሚደግፉአቸው ድርጅቶች መሆኑን መረዳት በቂ ነው፡፡ የተቀረጸው ምስል፣ የተደረገው እንቅስቃሴ ሁሉ የሚነገረው ለውጭ ድርጅቶች ብቻ ነው፡፡ በአገልገሎት መስኩ አብረው ስለተሰለፉ ለእነርሱ ሪፖርት መቅረቡ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ለአነርሱ ብቻ ምንጭር ቆራጭ ከመሆን ባለፈ ለአብያተ ክርስቲያናት ምንም አለማለት ደግሞ ሌላው ድክመት ነው፡፡ ሥልጠናው በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ያመጣው በጎ ተጽእኖስ ምንድነው የሚለውን ለማወቅ መጣር እኮ አንድ ነገር ነው ግን በሚኒሰቲሪዎችችን በኩል ይህ ብዙም አይታይም፡፡
በአብዛኛው የተለቀቀው በጀት ዝም ብሎ እንዳይመለስ ቶሎ ቶሎ ብለን ሥልጠና እናዘጋጅ በሚል የሚሰጥ ሥልጠና በጣም በርክቷል፡፡ የሚሰጠው ሥልጠና የቤተ ክርስቲያናትን ዓላማ ለማስፈጸም ምን ያህል ይረዳል የሚለውን በአጥቢያ ቤተ ከርስቲያን ማየት ብዙም አይታሰብም፡፡ ሥልጠና ሰጪዎቹስ ለምን ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ጋር አብረው ተመካክረው የሥልጠና መርሀ ግብር አይዘረጉም? ቢባል መጀመሪያውም ገንድሰው የወጡት እነርሱ ስለሆኑ፣ አሁን አብረው ለመሥራት አይችሉም፡፡ እንዲያውም የአንዳንዶች ልብ በራስ የግል ዓላማ በእልክ ተጨብጦ ስላስቸገራቸው ፣ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የሌላትን እኔ አምጥቻለሁ ስለሚሉ ሩቅ ሆነው ወደራሳቸው ይጠራሉ እንጂ አብረው መሥራት ይፈሩታል፡፡ ወይ ሥልጠና………
በአንድ ወቅት አንድ ሚኒሰትሪ እኔ ልዩ ነገር ታይቶኛልና የልጆች ሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ሥልጠና ልሰጥ ነው ብሎ ጠራና በጣም ጠቃሚና ቁም ነገር ያለበትን ነገር ለአገልጋች ያስጨበጠበት ጊዜ ደግሞ ነበር፡፡ ያንን አይተው ይመስለኛል ሌሎች ደግሞ ለሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ሥልጠና አዘጋጅቻለሁና ሁላችሁም ኑ ብሎ የሰጠውን ስልጠና ስናየው ከመጠነኛ ለውጦች በቀር የዛኛውን አሠራር እንደነበር ገልብጠው የመጣበት ነበር፡፡ የሚገርመው ግን ያዘጋጀሁትም ሥርዓተ ትምህርት አለና እንኩ፣ ከዛሬ ጀምሮ እርሱን ለልጆቻችሁ አስተምሩ ሲል ቤተ ክርሰትያንም ተቀብላ ማስተማር ጀመረች፡፡ ይሁን እንጂ ራዕይው ከመጀመሪያውም የቤተ ክርሰቲያንና የአገልጋዮቿ ስላነበር ብዙ የተደነጋገሩ ነገሮችና ብዥታዎች አንደነበሩ ትዝ ይለኛል፡፡ ወይ ሥልጠና››››››››
በአገር ውስጥ ያሉ ሰዎች ከሞላ ጎደል እዚያው ስለሆኑ ቤተ ክርስቲያናት ስላሉበት ተጨባጭ ሁኔታ መቃኘት ብዙም አያቸግራቸውም፡፡ ስለዚህ ቢያንስ ቤተ ክርስቲያን ካለችበት ሁኔታ ጋር የተቀራረበ የሥልጠና ፕሮግራም ማቀድ ይችላሉ፡፡ የሚያስገርመው ከባህር ማዶ የሚመጡ አሰልጣኖች ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም በአሜሪካን አገር ሰንብትበት ያሉ አገልጋዮች ወደ አገር ቤት ሲሄዱ ስልጠና ልሰጣችሁ ጌታ በልቤ አስቀምጧልና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ ካሉ ሁሉ ነገር አለቀ፡፡ ምን ዓይነት ሥልጠና ነው የምትሰጠን? በምን ርዕስ ነው የምታሰለጥነን? የሥልጠናህስ ዓላማ ምንድነው? የሚለው ጥያቄ ምንም አይጠየቅም፡፡ ለነገሩ ከዚያ በዘለለ መልኩ አንተ ባለህበት የምትኖረው አንዴት ነው? ለመሆኑ ያለህበትን ቤተ ክርስቲያን አማኞች ምን ያህል አሰልጥነህ አዘጋጅተሃል? በምትሰጠውስ ሥልጠና ምን ያህል ቀደ መዛሙርትን አፍርተሃል? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ የአገር ቤት ቤተክርስቲያንም ደግሞ ይህ ሥልጠና ካለንበት ሁኔታ፣ ካነገብው ዓላማ፣ እና ከራዕያችን ጋር ምን ያህል ይሄዳል የሚለውን በሰከነ አኳኃን አይገመግሙትም፡፡ ብቻ ከአሜሪካ ነው የሚመጣው ሲባል ከሰሙ ሣር ቅጠሉን ሁሉ ያሯሩጡታል፡፡ በተለይም አንድ ፈረንጅ አስከትሎ የሚሄድ ከሆነ አገልጋዩም ምድር ደህና ሁኚ ይላል፣ የአገር ቤት ሰዎችም እንዲያው ታይቶ የማይታወቅ ነገር እንደሆነ አድርገው ይራቆቱበታል፡፡ እነዚያ አገልጋዮች በአሜሪካን አገር እንዴት እንደሚኖሩ ቀርበው ቢያዩ ማ ኖሮ ሥልጠናው ቀርቶ አንተ በሰላም ወደ መጣህበት በተመለስክልን ባሉ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ ከአሜሪካን ወደ ኢትዮጰያ የሚሄዱ ሰዎች ብልጥ መሆን እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡ ከረጅም ዘመን የውጭ ቆይታ በኋላ ቤተ ሰባቸውን ለመጠየቅ ሲሄዱ የትኬት ገንዘብ ብዙ ነው፡፡ አንድ ፈረንጅ ቢያባብሉት እንደበረከት ይቆጥርና አብሮ ለመሄድ ከተስማማ የአየር ትኬቱን ዋጋ የሚሸፍነው ያ ፈረንጅ ነው፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ፈረንጅ ከተገኘ ማ በቃ የአየር ትኬት ብቻ አይደለም ሌላው ወጪ ሁሉ ይሸፈናል፡፡ ይህንን የኢትዮጵያ አገልጋዮች በጭራሽ አያውቁትም፡፡ ስለዚህ አንድ ያንን ፕሮግራም ማስተባበር የሚችል አዳማቂ ሰው በአገር ቤት ማዘጋጀት አንዱ ስልት ነው፡፡ እርሱ ሁሉንም ነገር ያሰናዳል፡፡ የአሜሪካው ሰዎች አስክመጡ ድረስ ሁሉንም ቀምሞ ይጠብቃቸዋል፡፡ ከዚያ የተፈለገው ነገር ተሳካ ማለት ነው፡፡ እኔም ይህ ነገር የገባኝ አሜሪካን አገር ከመጣሁና ስለ አንዳንድ የሰው ልጆች ብልሃቶችና በእግዚአብሔር አገልግሎት ስም የሚደረጉ ቅጥፈቶችን ካየሁ በኋላ ነው፡፡ በእውነት ሕዝባችንን በደረቁ እየላጥነው ነው ያልኩት አሁን ነው፡፡ ሰዎቹ እንደማናችንም ትምህርት ቃርመው ሊሆን ይችላል፡፡ ያ ብቻውን ግን በቂ አይደለም፡፡ እውነተኛና ትሁት ልብ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ መዝናናት ኃጢአት እንዳይመስላቸው ህልናቸው ስለታመመባቸው ግድ የላቸውም፣ ቀጥሎ ስለሚሆነው ነገር ደንታ ቢሶች ናቸው፡፡ ይህን ነው እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መንቃት ያልቻሉት! ለምን ቢባል ከአገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ስለ ሰጡት ሥልጠና እዚሁ እንደ ጉድ ያስወራሉ እንጂ ያ ሥልጠና በምን ሥራ ላይ ዋለ ብለው አይጠይቁም፡፡ ሥራ ላይ የሚውል አለመሆኑን ገና ከዚህ ሲነሱ በደንብ ያውቁታል፡፡ ሥራውም ሲታይ ከቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታና አገልግሎት ጋር የማይዋሄድ ብትን ሥራ እንደሆነ የሁሉም ሆድ ያውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምን ዓይነት ሥልጠና እንደሚያስፈልጋት የሚያውቅ በአሜሪካን ያለ አንድ አገልጋይ ወይም ኢትዮጵያን በእግሩ ረግጦ የማያውቅ ፈረንጅ ሳይሆን የኢትዮጵያ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እረኛ ነው፡፡ ካስፈለገም አቅም አንሳቸው ይሆናል እንጂ በኢትዮጵያ ያሉ እረኞች ለአሜሪካን አገልጋዮችም የሚሆን ስልጠና መስጠት ይችሉ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በጸጋ ስጦታው ባርኮአቸዋል እያልኩ ነኝ፡፡ በፈረንጅና በኢትዮጵያውያን መካከል ያለው የቆዳና የቋንቋ ልዩነት እንጂ የእግዚአብሔር ጸጋ አይበልጥም አያነስምም፡፡ ማንም ይሁን ማን በአንድ ቀን ሥልጠና የሚያመጣው ታአምር የለም፡፡
አውነተኞች የተከበሩ ኢትዮጵያውያን አገልጋዮች በአሜሪካን አገር አሉ፡፡ ይህም የሚያስገርም ነገር ነው፡፡ወደ ኢትዮጵያም በመመላለስ ከሥልጠናም ባለፈ ትላልቅ ሥራዎችን የሠሩና ለቤተ ክርስቲያን በብዙ እየተረፉ እንዳሉ የታመነ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ ከመጀመሪያውም ከኢትዮጵያ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጋር አብረው ስለ ነበሩ የሚያደርጉትን ያውቁበታል ፣ እኔ ይሁንልኝ፣ ደህናም አድርጌ ልቀርቅብ እንጂ ሌላው የራሱ ጉዳይ የሚሉ አይደሉም፡፡ እንደነዚህ ያሉት ምንም እንኳን ነዋሪነታቸው በአሜሪካን ቢሆን ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልሎት የሚጠቅም ሞልቶ የተረፈ ነገር አላቸው፡፡ ሥልጠናና ትምህርት ለምን እንደሚሰጡ ያውቃሉ ፣ ከቤተ ክርስቲያንም ጋር እጅና ጓንት ስለሆኑ እነርሱ ባሉበት ሻሞ ሆይ አይባልም፡፡ የሥልጠናቸው ይዘት እንደነዚኛዎቹ ሥር የሌለው ቁርበተ- ነክ አይደለም፡፡ ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባል፡፡
ስለዚህ፣ እኔ ያለኝ መልእክት ቢኖር ሥልጠና፣ ሥልጠና፣ ሥልጠና እየተባለ እንደ አዝማች ከመደጋገም በሥልጠናው አስፈላጊነት ላይ አስቀድሞ መወሰን ጥሩ ነው፡፡ ደግሞ በአሜሪካን ያሉ ኢትዮጵያውያን አገልጋዮች ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሲያስቡ ያለ ሥልጠና የማይታያቸው ምን ነክቶአቸው ነው? ሥልጠና መስጠት ከፍ ብለን አንደተመለከትነው የአጭር ጊዜ ስለሆነችና የአገር ቤቱን ወጭ ለመሸፈን ስለሚትረዳ ወይስ ሌሎች አባቶችና ወንድሞች ሲያደርጉ ሲሳካላቸውም እንዲሁም ከመልካም ሥራቸው የተነሳ ዝናቸው ሲወጣ ሰላየን እኛም ለምን በዚህ ስማችንን አናስጠራም በሚል ይሆን? ዝና እኮ መልካሙን ሥራ ስንተገብር ያዩ ሰዎች ሰብሰብ ብለው የሚያስተጋቡት የሠፈር ወሬ ነው፡፡ እኛ መልካሙን ከሠራን ሰዎች አንዱ ለሌላው እያሰማ ሳናውቀው ዝናችን ሊወጣ ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እግዚአብሔርን ይወዳል፣ ይፈራልም፡፡ ግን እንዲያው ምንም የማይገባው ድፍን ቅል አኮ አይደለም፡፡ እንግዳ ይወዳል ያቀበላል ግን በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ሌባ ሁሉ ሲመዠርጠው አይሰማውም ማለት እንዳይደለ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በመሆኑም ለወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን ሥልጠና አዘጋጅቻለሁ የሚሉ ወንድሞች ምን አስበው እንደሚያደርጉት አስቀድሞ ይታወቅ፡፡ በሥልጠና ብቻ ቤተ ክርስቲያንን ማሳደግ፣ መደገፍ፣ የወደፊት ራዕይዋንም መሳካት አይቻለልም፡፡ ሥልጠና የሚያስፈልግባቸው ሁኔታዎች የትኞቹ አንደሆኑ የአጥቢያ እረኞች ያስቡበት እንጂ ሩቅ ሆነን እኛ እናውቅላችኋለን ማለት ከልክ ያለፈ ቀልድም በደልም ነውና ሁላችንም እናስብበት፡፡

Tuesday, April 14, 2015

የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት አገልግሎት

የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት አገልግሎት
በአንድ ወቅት በአሜሪካን አገር ግራንድ ራፒዲስ በሚባለው ከተማ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የእግዚአብሔርን ፊት በጾምና በጸሎት እየፈለግን ባለበት ሰዓት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያካፍል የተመረጠው ሰው ለመልእክቱ መግቢያ ያደረገውን የማይረሳ ምሳሌ ሁል ጊዜ አስታውሳለሁ፡፡ እንዲሀ ነው ነገሩ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2009 የተባበሩት መንግታት የኢኮኖሚ ፎረም ባደረገው ዓመታዊ ስብሰባ የተለያዩ የመንግሥታቱ አባል አገሮች ተወካዮች የየአገራቸውን የሥራ ሪፖርት ይዘው ቀረቡ፡፡ ከየአገሩ የመጡ ወካዮች ምን ለሥራት ታሰቦ ምን አንደተከናወነና እንዴት ያለ ለውጥ እየታየበት እንደሆነ እያካፈሉ አንዳቸው ከሌላው ልምድም እየቀሰሙ ባለበት ወቀት የአንድ አገር ሪፖርት ግን የብዙዎችን ልብ የነካና የተደነቀ ሆነ፡፡ ያቺ አገር በሩቅ ምሥራቅ የምትገኝ ባርማ በመባል የምትተወቅ አገር  ናት ፡፡ ባርማ በ2009 .ም ልትሠራ ያቀደችውና ያከናወነችው ሌሎች አገሮች ካቀረቡት ጋር በፍፁም የይገናኝ ነገር ግን ሁሉንም ያስደነቀ አቀራረብ ነበር፡፡ ሌሎች  ስለ ልማት፣ ስለ አኮኖሚያዊ እድገት፣ ስለ ውጭ ግንኙነትና ስለ ወታደራዊ ዝግጅቶቻቸው ሆኖ ካቀዱት ምን ያህል እንደተሳካላቸው ነበር ያቀረቡት፡፡  ባርማ ግን በ2009 መግቢያ ላይ የያዘቺው እቅድ በአገሪቱ ውስጥ ያለ እያንዳንዱን ዜጋ በነፍሰ ወከፍ ደስተኛ እንዲሆን ስለማድረግ ነበር፡፡ ከልማት ሥራዎች ሁሉ የሚቀድመው የዜጋው ረክቶና ተደስቶ የመኖር ጉዳይ ስለሆነ ከዚህ አንፃር አቅዳ 90 በመቶ እደተሳካለት ያቀረበቺው ሪፖርት ሁሉንም የጉባኤ ተሳታፊዎችን ሊያስደንቅ ችሏል፡፡
ይህ ለእኛ የእግዚአብርን ሕዝብ ምናገለግል ሰዎች እጅግ በጣም አስገራሚ ትምህርት ያለበት ምሳሌያዊ መልእክት ነው፡፡ እኛ ከባርማ መንግሥት ይልቅ የምናገለግላቸውን ቅዱሳን ልባቸው እንዲያርፍ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብርም እኛን በዚህ ምድር ይ ያስቀመጠን የእርሱን አሳብ እያገለገልን በስሙ የተጠሩትን ሁሉ እንድናንፃቸው ነው፡፡ የአገልጋዮች አገልግሎት የምዕመናንን ልብ የሚያሳፈርፍ እዲሆን ደግሞ የእግዚዘአብር ቃል ይመክረናል፡፡ አገልግሎታችን የቅዱሳንን ልብ እንዴት ማሳረፍ እንደሚቻል ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልሞና ጻፈውን መልእክት ከቁጥር 1-7 መመልከት እንችላለን፡፡ ወደ ዋናው አሳባችን ከመግባታችን በፊት ስለ ፊልሞና መጽሐፍ ሁለት ወይም ሦስት መሰረታዊ በሕሪያቶችን እንመልከት፡፡ የፊልሞና መጽሐፍ ዋሪያው ጳውሎስ እሥር ቤት ሆኖ ከጸፋቸው የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ጳውሎስ ይህንን መፅሐፍ በሚጽፍበት ወቅት በሮም እሥር ቤት ሊሆን ይችላል፣ ወይም በሌላ ቦታ ሊሆን ይችላል ብቻ መልእክቱን ያስተላፈው ከእሥር ቤት ነው፡፡ የፊልሞናን መጽሐፍ በጣም ተናፋቂ ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይህ ነው፡፡ ከየትና እንዴት በማንስ ተጻፈ የሚለው አሳብ የሚተላለፈው መልእክት ተሰሚነት እንዲኖረውና አቅምም አንዲያገኝ ያደርገዋል( .9)፡፡ ሁለተኛው የፊልሞና በጣም አጠር ካሉ ወይም ምዕራፍ ከሌላቸው መጻሕፍት ይመደባል፡፡ በጠቅላላው በመጽሐፍ ቅዱ ውስጥ ወደ አራት ያህል መጻሕፍት በምዕራፍ ያተከፈሉ ሲሆን እነርሱም ብዲዩ፣2ኛ ዮሐንስ፣ 3ኛ ዮሐንስ ና ፊልሞና ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በምዕራፍ አይከፋፈሉ እንጂ ትልቅ ቁም ነገር ያዘሉ ናቸው፡፡ በምዕራፍ ያልተከፈሉበት ምክንያት አጠር ባለ መልክ ስለቀረቡ ብቻ እንጂ መልእክቱ ከእግዚአብሔር ስላልሆነ አይደለም፡፡ ሦስተኛ የፊልሞናን መጽሐፍ ልዩ የሚያደርገው የመልእክታቴ ምጋቤ አካል ከሆኑት መጸሕፍት የሚመደብ መሆኑ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ለቡድን ወይም ከቤተ ክርስቲያን ወይም ለአንድ አገልግሎት ክፍል የተላከ ሳይሆን የሕዝብ እረኛና አገልጋይ ለሆነ ሰው በግሉ የተላከ የመጋቢያዊ መልእክት ያዘለ ነው፡፡ ለአንድ ግለሰብ የተላኩ ሌሎችም ጻሕፍት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሲሆን ሁላቸውም የየራሳቸው ባሕሪያት ያሉአቸው ናቸው፡፡
በዚህ አጭር ትምህርት ውስጥ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለፊልሞ የሚያቀበውን መልእክት ሁሉንም ማየት እችልም ፣ ነገር ግን ከቁ 1-7 ያለውን ብቻ እንመለከታን፡፡ ይንን መልእክት የሚያስተላልፈው የእግዚአብሔር ሰው ጳውሎስ የጌታ አገልጋይ ከሆነው ከፊልሞና ጋር ትልቅ የአልግሎት መተሣሠር ነበራቸው፡፡ ጳውሎስ በእሥር ቤት ሆኖ ስለ ፊልሞና አገልግሎት የሰማው ነገር በእርሱ ላይ የፈጠረው አዎንታዊ ተጽእኖ በዚህ የንባብ ክፍል ውሰጥ ይገኛል፣ ምክንያቱም ጳውሎስ በፊልሞና አገልግሎት ምክንያት መጽናናቱንና መደሰቱን ይናራል( . 7)፡፡ በፊልሞና አገልግሎት በቤተ ክርሰቲን ያሉ ቅዱሳን ልብ በማረፉ ምክንያት ጳውሎስ ተደስቷል፣ በብዙ መጽናናት ተጽናንቷል፡፡ እንዲህ ያለ አገልግሎት ማገልገል እንዴት ዓይነት መታደል ነው!
ፊልሞና የሚያገለግለው አገልግሎትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያደርገው ሥራና ተግባር ሁሉ የሕዝቡን ልብ ከመረበሽና መንፈሳቸውን ከማናወጥ ይልቅ ልባቸውን የሚያሳርፍ ነበር፡፡ ስለዚህ እኛ ዛሬ በዚህ ዘመን የምንገኝ አማኞች የቅዱሳንን ልብ ከማሳረፍ አንፃር እንዴት አይነት አገልግሎት እየሰጠን እንደሆነ ራሳችንን መመልከት ይኖርብናል፡፡ እስቲ የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ ሕይወትና አገልግሎት ምን እንደሚመስል ሐዋሪያው ጳውሎስ ለፊልሞና ከጻፈው መልእክት እንመልከት፡፡
1. አገልገሎቱ የቅዱሳንን ልብ ሚያሳርፈው አገልይ የይቅርታ ልብ ያለው ነው፡፡
ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለፊልሞና የሚልክበት ተቀዳሚ ምክንያት በፊልሞናና በአናሲሞስ መካከል ክርስትያናዊ ይቅርታን ለማስፈን ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ሙሉውን የሚገረው ስለ ይቅርታ ነው፡፡ ፊልሞና በፍቅርና ሌሎች መልካም ሥራዎች የቅዱሳንን ልብ ያሳረፈ ምርጥ አገልጋይ ቢሆንም ጳውሎስ በድጋሚ ስለ አናሲሞስ ይጠይቀዋል፡፡ አናሲሞስ የፈልሞና አገልጋይ (በጥንት አባባል ባሪያው) ሆኖ ከፊልሞናም ጋር አብሮ ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን በአንድ ወቅት ፊልሞናን ዘርፎ በመኮብለሉ የፊልሞና ልብ በአናሲሞስ አዘነ፡፡ ይሁን እንጂ አናሲሞስ ኮብልሎ በሄደበት ጳውሎስ አገኘውና ወንጌል ሰበከለት፣ አናሲሞስም  በጌታ በኢየሱስ አመነ፡፡ ጳውሎስ በእሥር ቤት በነበረበት ወቅት በወንጌል ንዲያምን ምክንያት ስለሆነው አናሲሞስ ይረዳና ያግዘው ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ የአናሲሞስ ለጳውሎስ አስፈላጊ ሰው ቢሆንም ያለ ፊልሞና ፈቃድ ለራሱ ሊያስቀረው ስላልፈለገና በሁለቱ መካከል የይቅር መንፈስ እንዲሰፍን ስለፈለገ ወደ ፊልሞና ይልከዋል፡፡ እንዲያውም ፊልሞና አናሲሞስን እንደ ወንድሙ እንዲቀበለው ይማጸነዋል፡፡ ያ ብቻ ሳይሆን የተደበለውንም ሁሉ በእርሱ ላይ እንዲቆጥርበት ይጠይቀዋል፡፡ እንግዲህ ከዚህ የምናየው እርቅና ሰላም በሌለበት ሥፍራ ሁሉ ጭንቀትና መረበሽ እንዲሁም አለመረጋጋት መኖሩን ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሐዋሪያው እባክህ ልቤን አሳርፍልኝ የሚለው! ይህ የጌታ አገልጋይ ባደረጋቸው ሥራዎች ሁሉ የቅዱሳንን ልብ በማሳረፍ የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ደግሞ ለአናሲሞስ ይቅርታ በማድረግ የበለጠ የጳውሎስንና የሌሎችን ልብ እንዲያሳርፍ ተጠይቋል፡፡ ይቅርታ ሲደረግ የቅዱሳን ልብ ያርፋል ማለት ነው፡፡ ሁለት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሲጫቃጨቁና ሲቃረኑ እንቅልፉን የሚያጣው ምዕመኑ ነው፡፡ ሁለት መጋቢዎች ባለመግባባት እርስ በእርሳቸው ሲገፋፉ የሚያዝነውና የሚረበሸው ጉባኤው ነው፡፡ መሪዎች እርስ በእርሳቸው የሰላምና የፍቅርን አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በምዕመናን መካከል ያለው ደስታና ፍንደቃ ትልቅ ይሆናል፡፡
የብሉይ ኪዳን መጸሕፍትን በምንመለከትበት ወቅት የእሥራኤል ሕዝብ ለጦርነት ከተጋለጠባቸው ምክንያች አንዱ የመሪዎች ሁኔታ ነው፡፡ በአናጸሩ ደግሞ አገርን ከሚመሩ ነገሥታት የተነሳ ምድርት አርፋ እንደምትቀመጥ የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ጊዜ ምድሪቱ በሰላም አርፋ ተቀመጠች እያለ ይናገራል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በቤተ ክርስቲያንም የሚያገልግሉ መሪዎች እርስ በርሳቸው በፍቅር ሲቀባበሉና ሲዋደዱ በመላ ቤተ ክርስቲያን የሚታየው ደስታ እጅግ የላቀ ይሆናል፡፡  ጳውሎስም ፊልሞናን ልቤን አሳርፍልኝ  ማለትም ይቅርታ በማድረግ ልብ የሚያሳርፍ ሥራህን ቀጥል የሚለው ለዚህ ነው፡፡
ዛሬም እኛ የሚያስፈልገን የአገልግሎት ብዛት አይደለም፡፡ ብዙ መስበክም አይደለም፡፡ ነገር ግን የቅዱሳንን ሁሉ ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ሆነን መገኘት ነው፡፡ እኛ ይቅርታን የማይቀበል በቀለኛ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ያደግን ሰዎች ነን፡፡ አብዛኛው ባህላችን ቁጣና በቀል የተሞላ ነው፡፡ ብድር በምድር የሚለው አስተሳሰብ አብሮት ከማደጉ የተነሳ  ትውልዳችን ይቅርታን መጠየቅን እንደ ሽንፈት፣ ይቅርታን ማድረግን እንደ ሞኝነት የሚቆጥር ነው፡፡  ጌታን ተቀብለን አገልጋዮችና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከሆንንም በኃላ እንኳ ያ አብሮን ያደገው ልማዳችን ከውስጣችን አልወጣ ብሎ ጊዜ ይወስድብናል፡፡ ስለዚህ ብዙዎቻችን በእግዚአብሔር ቤት እንበቃቀላለን፣ አንዳችን ሌሎችን እናሳድዳለን፡፡ በተለያየ የአገልግሎት ዘርፎች ብናገለግልም በእግዚአብሔር መድረክ ላይ እያለንም በቀለኝነት ያጠቃናል፡፡ ይህ ከመሆኑ የተነሳ የእግዚአብሄርም ልብ አልተደሰተም የቅዱሳንም ልብ አላረፈም፡፡ እኛ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እያሳረፍን ነው ወይስ እያሳዘንን; እያራወጥነው ወይስ እያረጋጋነው፣ እያጽናናነው ወይስ እያስጨነቅነው ነው የሚለውን ጠይቀን መልስ ማግኘት ይኖርብናል፡፡ የእግዚብሄርን ቃል በማስተማርና የተያዩ ቅዱሳት መጻሕፍትን መበጻፍ በዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ትልቅ አክብሮት ያላቸው ዶር ጆን ማካርተር ይቅርታ አለማድረግ እንዴት ያለ ክፉ ነገር እንደሆነ እንደሚከተለው ገልተዋል፡፡
ይቅርታን አለማድረግ ባለፈው የመራርነት ሕይወት እሥረኞች አንድንሆን የሚያደርገን ነው፡፡ ይቅርታን አለማድረግ ለሰይጣን አሠራር የተከፈተ በር የሚሰጥ ሲሆን እኛም አጋንንትን በዚያው እንኳን ደህና መጣህ እያልነው ነው፡፡ ይቅርታ አለማድረግ በእኛና በእግዚአብሔር መካካል ላለን ሕብረት እንቅፋት ነው፡፡ ምከንያቱም ጌታ ኢየሱስ ሲያስተምር ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማዩ አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም፡፡ ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ካላልን ደስታችንና ሰላማችን ይወሰድብናል፡፡ ጳውሎስ በፊልሞናና በአናሲሞስ መካካል ሆኖ ሁለቱን የሚሸ መግላቸው ይመስላል፡፡ አናሲሞስ ፊልሞናን በጣም አድርጎ በድሎታል፡፡ ጳውሎስና ፊልሞና በነበሩበት ዘመን አናሲሞስ ያደረገውን ዓይነት በደል የፈጸመ በባህላቸው መሠረት ይወገዛል ፣ ይወገራል፣ ይሰደዳል እንዲያውም ገደላልም፡፡ እርሱ የፈጸመው ወንጀል በማንኛውም ማኅበራዊና ሕዝባዊ ጉዳዮች ሥፍራ እንዳይኖረው የሚያደርግ ነው፡፡ምክንያቱም አናሲሞስ ለፊልሞና ባሪያው ሆኖ እያለ ያንን በአሠሪዎች ዘንድ ከባድ ወንጀል ሆኖ የሚታወቀውን ጥፋት ሠራ፡፡ ምናልባት አናሲሞስ ከአካባቢው የሸሸው የሚደርስበትን ቅጣት ፈርቶም ሊሆን ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ሕግ ግን ይህንን በደለኛውን ሰው አንደ ወንድምህ ቁጠረው ይላል፡፡ ይህ ቀላል ሊሆን የማይችልበት ምክንያት አለ፡፡ አንደኛ ባሪያና ጌታ ሁለቱ እኩል በማዕድ መቀመጥ የሚችሉበት ባህላዊ አግባብ በጊዜው አልነበረም፡፡ ዘራፊና ቀመኛ ምንም ቢሆን ከተቀማው ሰው ጋረ ሕብረት እንዲያደርግና ከዚያም አልፎ እንደ ወንድም ሊቀበል የሚችል ሥርዓትም ሆነ ልማድ አልነበረም፡፡ የእግዚአብሔር ህግ ግን ከዚህ ሁሉ ይለያል፡፡ እንደ ወንድምህ ቁጠረው ፣ ባሪያ ከነበረበት እንደ ወንድምህ አድርገው የሚል ነው፡፡ ጥፋት አድርሶ የኮበለለውን የጠገበ ሠራተኛ ወደ ሥራው አንዲመለስ አሠሪውን እንማፀነው ይሆናል ፣ ወንድም አድርገው ለማለት ምንም የማይታሰብ ነው፣ ማለት የሚፈልግም ካለ ደግሞ ሆን ብሎ ሽምግልናውን ለማደፍረስ እንደሚፈልግ ሰው ለፈረጅበት ሁል ይችላል፡፡ ጳውሎስ ለፍልሞና የሚናረው መልእክት ግን ወደ ሥራው እንዲመለስ ከሚለው የዘለለና እንደ ወንድም ቁጠረው የሚለው ነው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ክርስትና ሲገባን ብቻ ነው፡፡ ስለ ይቅርታ ሰብከው ሲመለሱ ወንድማቸውን ይቅር አልልም ብለው ሳምንት ሙሉ ሽማግሌ የሚያመላልሱ አገልጋዮች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ስብከት ችለዋል እንጂ ክርሰትናው ገና አልገባቸውም አሊያም ክርስትና የሚያሰከፍለውን ዋጋ ገና አላወቁትም፡፡ ምክንያቱም ክርስትና የዘረፈህን ጥጋበኛና ጎረምሳ አገልጋይን ወደ አንተ ሲመጣ እንደ ወንድምህ አድርገው እንጂ እንደ ሠራተኛህ አትየው የሚል ነው፡፡
ጳውሎስ ስለ ፊልሞና የተረዳው ሁሉ አዎንታዊ ነው፡፡ የሚያርምበት አንድም ነገር እስከማይኖርበት ድረስ ሕይወቱ የተመሰከረለት ሰው ነው፡፡ ምን አይነት ባሕሪያ ነው! አሁን ግን ለአናሲሞስ ይቅርታ በማድረግ የበለጠ ይምሰገናል ክርሰቲያናዊ ጀግና ይባላል ወይም ብዙ የሆነው መልካም ነገሩ በአንድ ነገር ምክንያ ብቻ ዋጋው ሊረክሲበት ይችላል፣ ያውም ይቅርታ በማድረግ ወይም ባለማድረግ፡፡ ብዙ የመድረክ ጀግኖች ተፈትነው በቀላሉ ክብደታቸው ታወቀ፡፡ እኔ እኮ ጌታን ካገኘውና በመንፈስ ቅዱስ ከተሞላው ይህን ያህል ሰዓት ሆኖኛል፣ እነ እገሌም በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት እኔ እጅ ጭኜ ስጸልይ ነው ብለው የሰውን ሁሉ እትኩሮት ሲስቡ የኖሩ ቱባዎቻችን ክርስትናቸው ከወጣበት በአንዴ ሲወርድ ያየነው ለባልንጀራቸው ይቅርታ እንዲያደርጉ ሲጠየቁ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ያየን ቀን ነው፡፡
2. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ስለ ሰዎች ሕይወት የሚጨነቅ ነው( .4)፡፡
ፊልሞና ለሰዎች ግድ የሚለው ለእርሱ የሚጨነቅበቅዱሳን ሁሉ ዘንድ ፍቅር ያለው ሰው ነበር፡፡ እር ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በፍቅር የተሳሰረ ፣ ከተቀሩት ጋር ደግሞ አኩራፊ ዓይነት ሰው ሳይሆን ከቅዱሳን ሁሉ ጋር በፍቅር የሚኖር ሰው ነው፡፡ ይህ ፍቅር ደግሞ ለሰዎች ሁሉ ሸክም እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ ጳውሎስ ለፍልሞና ፍቅር እንደነበረው ከቁ.11-14 ያሳየናል፡፡ አናሲሞስ በእሥር ቤት ላለው ለጳውበጣም ስለሚያስፈልገው ከራሱ ጋር ቢያቆየው የማይወቀስበት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛው፣ አናሲሞስ ገና ጌታን ሳያገኝ ከፊልሞና ኮብልሎ ሄዷል፡፡ ሁለተኛ ወንጌል መስክሮ  እንዲለወጥ ምክንያት ስለሆነው አሁን የወንጌል ልጁ ሆኖታል፡፡ ስለዚህ ቢያስቀረው ፊልሞናም ቢሆን ቅር ሊሰኝበት አይችልም፡፡ ይንጂ ጳውሎስ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የፍሞናን በመስቀደም አናሲሞስን ወደ ፊልሞና ላከው፡፡ ለእኔ ይልቅ የአንተ ይሻላል የሚል አቅም ያለው ክርስትና ያለው ሰው ነው፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔም ደስ የሚሰኝበትና የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት ሕይወት እንዲህ ዓይነቱ ነው፡
3. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ስለ እግዚአብሔር የሚያስብ ነው(4-5)፡፡
የእግዚአብሔር ክብርና ከእርሱ ጋር ያለን ሕብረት ግድ የሚለን ስንሆን የቅዱሳን ልብ ያርፋል፡፡ ጳውሎስ በዚህ ክፍል ስለ ፍልሞና እምነት ሰምቶ እግዚእብሔርን ያመሰግናል፡፡እምነት ሙ በሙሉ ለእግዚአብሔር ያንን መሰጠት መተማመን እንዲሁም በጌታችን በፍጹም ማረፋችንን የሚያመለክት ሲሆን እኛን ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኘናል፡፡ ፍቅር ደግ ከሰዎች ጋር ያገናኘናል፡፡ ፡ ፈልምና እነተኛ የሆነ እምነት የነበርውነና በእውነትም የተመሰከረለትም አማኝ ነው፡፡ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ጋር ያላቸውን ነገር የሚያላሹት ከእግዚአብሔር ጋራ ያላቸው ነገር መበላሸት ሲጀምር ነው፡፡ ብዙዎች ከእግዚአብሔርና ከወንድሞቻቸው ጋር ካላቸው ህብረት ይልቅ ለመድረካቸውና ለአገልጋይነት ስማቸው ትኩረት ይሰጣ፡፡ ከአሥር ዓመት በፊት ከአዲስ አባባ 400 ኪሎ ሜትር አካባቢ የምትገኝ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጀቺው ኮንፍራንስ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ሄድኩ፡፡ ጉባኤው በጣም ትልቅ በመሆኑ ጸሎት ቤቱ ስላልቻለ ፕሮግርሙ የተካሄደው በሜዳ ላይ ነበር፡፡ በዚያ ኮንፍራንስ መልእክት ካቀረብኩ በኋላ የንሰሐ ጥሪ ሳቀርብ አንድ ወጣት ሚስቱን እንደበደላትና ይቅርታ ሊጠይቃት እንደሚፈልግ ተናገረ፡፡ ስለዚህ ከቤተ ክርስቲያን መጋቢ ጋር በመሆን ሚስቱን አስጠራናትና ይቅርታ እንድታደርግለት ስንጠይቃት አባቴ ይህንን መስማት አለበት አለች፡፡ አባቷ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ስለሆነ ከሰዎች ጋር የነገውን ፕሮግራም በሚመለከት አንዳንድ ሥራዎችን እየሠራ ካለበት አስጠራነውና ጉዳዩን ሁሉ አጫወትነው፡፡ ልጅቷ ይቅርታ አድርጋ ወደ ትዳሯ የመመለስ ልብ ቢኖትም የአባቷ አቋም ግን ከጠበቅነው በላይ አስቸጋሪ ሆኖ ተገኘ፡፡ ልጅቱ ከባሏ ጋር በተፈጠረው ጊዜየያዊ አለመግባባት ምክንያ ካለችበት ትዳር ወጥታ ወደ አባቷ ቤት መታ እዛው ናት፡፡ ጉዳዩን ለማስተካካል በጣም ሰፊ ጊዜ ወሰደብን፡፡ ልጁን የበደለውን ሰው ይቅር እንዲል ደጋመን ብንለምነውና ብማጸነው አባትዬው በጭራሽ እምቢ አለ፡፡ በመጨረሻም ላይ እንዲህ ኣይነት ክርስቲና ይዘህ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ትሆን ስለማትችል አግደንሃል ሲሉት እንደዚህ ከሆነ እሺ እንዳላችሁት ይሁን አለ፡፡ ወጣቱ ባለትዳር ሚስቱን የዞ ቤቱ ቢገባም ይህ ሽማግሌ ስለ ክርስቲናውና እግዚአብሔር ስለሚጠብቅበት ኑሮ ሳይሆን የተጨነቀው ስለ ሽምግልናው መሆኑ የሁላቸንንም ልብ እንዳሳዘነ አስታውሳሁ፡፡
ዛሬም በእኛ ዘመን ስለ ስማቸውና ስለ መድረካቸው እንዲሁም በሰው ፊት ስለሚታየው አገልግሎታቸው እንጂ ስለማይታየው መንፈሳዊ ሕይወታቸውና የጌታ መንፈስ ከእነርሱ ስለሚፈልግባቸው ሕይወታቸው ግድ የማይላቸው ብዙ አገልጋዮችና መሪዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ፊልሞና ግን እንዲህ ዓይነት ሰው አይደለም፡፡ የሰሙትን ሁሉ የሚያስመሰግን እምነት ያለው ሰው ነው፡፡ አንዲህ ዓይነቱ ሕይወት እግዚአብሔርን ያስደስዋል ፣ የቅዱሳንንም ልብ ያሳርፋል፡፡
4. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፈው ስለ እውነተኛ ሕብረት የሚያሳስበው ነው፡( 6)፡፡
በጌታ ያለን አማኞች ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር እውነተኛ እምነትን የቅዱሳን ሕብረት እንደሚከተለው ነው፡፡ አንድነት፣የወንድማዊ ፍቅርና ሰላም የክርስትያንነታችን ምልክትና የሕይወታችን ክፍል ነው፡፡ ከሌሎች ጋር በምናሳልፍበት ወቅት ከሌሎች እንማራለን፣ እንታነጽባቸዋለንም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምንሄደው ስብከት ሰምተንና ተነቃቅትን ለመመለስ ብቻ ከሆነ ያ ሁኔታ እኛን ራስ ወዳዶች ያደርገናል፡፡ ይልቁንም ለሌሎች በረከት ለመሆን፣ ከእርሱም ጋር ለመተያየትና እርስ በእርሳችንም ለመልካም ሥራ እንድነነቃቃ ነው፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቤት የምንሄደው ለጋራ በረከት ነው፡፡ የወንድማችንን ሐዘን ሀዘናችን ደስታውንም ደስታችን ልናደርግ ነው ፡፡ የእኛንም ሸክም እነርሱ እንዲጋሩ ለማድረግ ጭምር እንጂ ተሰብከን፣ ወይም ሰብከን ወይም ዘምረን ወይም ለራሳችን በረከቱን አፍሰን ልንመጣ ብቻ አይደለም፡፡ ቅዱሳን ልብ የሚያርፈው ግን አንዳችን ከሌላው ጋር በሕብረት ስንተሳሰር ነው፡፡ በርካታ አገልጋዮች ሰዎች ሲጣሉ ደስ ይላቸዋል፡፡ እንዲያው ሰው ምን ይለናል ብለው እንጂ ዱላ ቢያቀብሉ የማይጠሉ አናካሾች አይጠፉም፡፡አንዲት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እርስ በርሳቸው ሲጨቃጨቁ አሁን ወደ እኛ ይመጣሉ ብለው የሚደሰቱ ቤተ ክርስያን አገልጋዮች ጥቂት አይደሉም፡፡ እነ ፊልሞና ግን ይህ አይነከካቸውም፡፡ ስለ ሕብረትና አንድነት የሚያስቡና የሚጨነቁ፣ የሚጠበቡም ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደዚህ ባሉት አገልጋዮች ሕይወትና አገልግሎት የቅዱሳን ልብ ያርፋል፡፡
5. የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት አገልጋይ ስለ መንፈሳዊ እውቀት የሚያሳስበው ነው( 6)፡፡ እውቀት ስንል ተራ መረጃ ሳይሆን ስለ እግዚአብሔር ያን ጥልቅ መረዳት ማለታችን ነው፡፡ የእግዚአብሐሔርን ነገር በጽንሰ አሳብ ደረጃ ማወቅናTheoretical knowledge በሕይወት ልምምድ ውስጥ ገብተን ማወቅ /experiential knowledge/ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ፅንሰ አሳብ በሆነው እውቀት ወደ ንስሐ አምልኮ፣ እንዲሁም ወደ ይቅርታ ሕይወት መድረስ አይቻልም፡፡ በአገራችን ሳለሁ በአውሮጳና በአሜሪካ እንዲሁም በሌሎች የምዕራብ አገሮች በየክረምቱ ስለሚወርደው በረዶ ከሚሰማው ነገር ተነስቼ ለሌሎችም ሰዎች አስረዳቸው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የተቆረቆሩ የፕሮቴስታንት አማኞች ቤተ ክርስቲያን ሕንጸዎች ጣሪያቸው ከመሀል ከፍ ያለና ዳርና ዳሩ ዝቅ ያለ ሲሆን ይህ አሠራር ምዕራባውያን በረዶው ሲወርድ ጣሪያው ላይ ተከምሮ እንዳይጎዳው እየተንሸራተተ እንዲወርድ አድርገው ስለሚሠሩት ሚሲዮናውያኑ ወደ አገራችን ሲመጡ ያንን የለመዱትን ዓይነት ቤት ስለሚሠሩ ነው የጸሎት ቤቶቸችን ሕንጻዎች ከሌላው የተለዩ የሚሆኑት ሲባል ስለ ሰማሁ እኔም ለብዙዎች የሰማሁትን ያንኑን አስረዳ ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ የማስረዳው በረዶውን በዓይኔ እንኳን ሳላየው ነበር፡፡ ከብዙ ጊዜያት በኋላ ወደ ሚቺጋን መጥቼ በረዶ ሲወርድ፣ ከተማውን ሁሉ ሲሸፍን፣ መንገዱን ሁሉ ሲዘጋ በቤቶች ሁሉ ጣሪያ ላይ ተከምሮ ከዚያ እየተንሸራተተ ሲወድቅ፣ መንገዱን ሁሉ ሸፍኖ ለመንዳት ሲያስቸግርና እያንዳንዱ የሚቺጋን ነዋሪ በወፋፈፍራም ልብሶች ተጀቡኖ ሲሄድ ሳይ ለበረዶ ያለኝ እውቀት የተለየ ሆነ፡፡ እንዲያውም እኔ በበረዶ ላይ ሲነዳና መኪናዬ መንገድ ስታ የወጣችበትን አጋጣሚ ሁሉ ሳስበው ሰው በመረጃ ብቻ የሚያውቀው እውቀት በሕይወት ልምድ ከሚያውቀው ምን ያህ የተለየ እንደሆነ በለጠ ተገነዘብኩ፡፡ ጳውሎስም ይህ የሕይወት ልምድ እውቀት እንዲበዛለት ለልሞና እንደሚጸልይለት ቃል ይገባለታል፡፡ ይህ ጥልቅ እውቀትና መረዳት አፓጎኒሲስ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ስለ እግዚአብሔርና በእኛ ውስጥ ስላለው መንፈሳዊ ነገር ጥልቅ የሆነ መረዳት a deep understanding about God and about what in us/ ማለታችን ነው፡፡ በእኛ ዘንድ እግዚአብሐየር ያቀመጠው በጣም ብዙ የሆነ መልካ ነገር አለ፡፡ ጌታ ኢየሱስን ካመንንበት ጊዜ ጀምሮ ከእርሱ በጣም ብዙ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ተቀብለናል፡፡ ይህንን እግዚአብሔርን አውቆ መከተልና አውቆም ማገልገል ሕይወታችንን ያሳድገዋል፤ በእግዚአብሔርም ላይ ያለን መተማመን ይጨምራል፡፡ በእኛ ዘንድ ያው ሁሉ በማወቅ የሚው አሳብ ል ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ እግዚአብሔር በእኛ ብዙ መልካም ነገሮችን አስቀምጧል፡፡ ከጌታ ያገናቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች ክርስቶስን ወደ ወቅ እንድንደርስ የሚያደርጉን ናቸው፡፡ ስለዚህ የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ በክርስቶስ ስላው እውቀት ግድ የሚለው ነው፡፡
6. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ለክርስቶስ ክብር ግድ የሚለው ነው፡፡
ፍልሞና ሁሉንም ነገር ያደረገው ለክርስቶስ ነው፡፡ መንፈሳዊ ፍሬንም የሚያፈራው ለክርስቶስ ነው፡፡ ጳውሎስ በአንተ ያለው ነገር ለክርስቶስ ፍሬን እንዲያፈራ እለምናለሁ በማለት ለፍልሞና የሚጸልየውን የጸሎት ይዘት ይገጻል፡፡ በአገልግሎታችን ፍሬን ብናፈራ ያ ፍሬ ክርስቶስን ለማክበር መሆን አለበት፡፡ ሰዎችንም በአገልግሎታችን የምናዘጋጀው ለክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ በእኛ ሕይወትና ኑሮ በሚከብርብት ወቅት የምናገልግላቸውና አብረውን ጌታን የሚያመልኩ ሰዎች ልባቸው ያረፈ ይሆናሉ፡፡
ስለዚህ ጳውሎስ ይንን አንቀጽ ሲደመድም ልቤን አሳርፍልኝ ይላል፡፡ ዛሬም ሰዎች ተንቀዋል፣ ፈርተዋ፣ተረብሸዋል፣ ግራም ተጋብቷል፣ምእናንም በአገልጋችና በመሪዎች መካከል ካለው አላስፈላጊ ሽኩቻ የተነሳ ተንገላትተዋል፣ ከቦታ ወደ ቦታ ተንከራተዋል፣ ከአንዱ አበባ ተነስታ በሌላው ላይ እንደምትቀመጥ ከዚያም ተነስታ ወደሌላው አበባ እንደምትበር ንብ ተጉላልተዋል ፡፡  በንፈሳዊ ሕይወታቸው መጠንከር አልቻሉም፡፡ አማኞች ሥር መስደድ ሲጀምሩ መሪዎችና መድረክ ናፋቂ ሰባኪዎች ካሉበት ሥፍራ ያፈናቅሉአቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ በመንፈሳዊ ሕይወት መጭብርብር ውስጥ ገብተዋል ፣አያሌዎችም ለአውሬ ተጋልጠዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እኛ አገልጋዮች ስለ እነርሱ ግድ አላለንም፡፡ ስለዚህ ቆም ብለን በማሰብ የምዕመናኖቻችን ልብ ልናሳርፍ ይገባናል፡፡ ጳውሎስ ለፍልሞና የሚልከው ይህ መልእክት ለአገልጋች ሁል ማነቂያ ደወል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የቅዱሳንን ልብ ሚያሳርፈውን ማንነት እግዚአብሔር ይስጠን፡፡ አሜን፡፡








Thursday, April 9, 2015

የኢየሱስ ማኅተም
( የማንነታችን ምልክት )
                                                                                                                                     በፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1992 ..ገዳማ በምዕራቡ በአገራችን ክፍል አንድ በዓይነቱ የተለየ ወፍ ተገኘና መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት ንደተንከባከበው ይታወቃል፡፡ ይህንን ወፍ ልዩ የሚያደርገው ነገር መልኩ ብቻ ሳይሆን በአንገቱ ላይ ንጠለጠለው ታግ ወይም ምንነቱን የሚያሳይ ጽሑፍና ቁጥር ያለበት ካርድ መኖሩ ነው፡፡ የካከቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማሩት ሰዎች ይህንን በያዩበት ወቅት ይህ ወፍ ከየት አካባቢ እንደመንዴትስ እንደመ ጥናት ድረግ ነበረባቸውና ሲጠና በታጉ ላይ የተቀመጠው ጽሑፍ በዴች ቋንቋ የተጻፈ በመሆኑ ወፉ ከሆላንድ አገር መምጣቱ ታወቀና የኢትዮጵያ መንግሥት ከሆላንድ መንግሥት ጋር ግንኙነት በማድረግ ያንን ወፍ በአውሮፕላን አሳፍሮ ወደ አገሩ መመለሱ በኢትዮጵያ ዜና መነገሩን እናስውሳለን፡፡ ይህ ወፍ በአገራችን ካሉ በብዙ ሚሊዮን ከሚቆጠሩ ወፎች እንዲያውም በሌሎች በአገሮች የማይገኙ ከተባለትና አገራችንን የቱሪም መገኛ እንትባል ካደረጉ ብርቅዬ ወፎች ሁሉ ተለይቶ የሁሉን ትኩረት የሳበበት ምክንያት ምንድነው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ይህ ወፍ በአንገቱ ላይ የተንጠለጠለው ታግ ባይኖረውስ ኖሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ግምት ሰጥቶ ወደ ሆላንድ አገር ይመልሰዋል ማለት እንችል ይሆን፣ ምናልባት በዓይነቱ የተለየ ወፍ በአገራችን ተገኘ ተብሎ ከመወራት ያለፈ ነገር ሊደረግለት ባልቻለ ነበር፡፡ በተሸከመው ምልክት ምክንያት ያ ሁሉ እንክብካቤ ተደርጎለት ክብርም አግኝቶ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡
ይህ ለእኛ ለጌታ አገልጋዮችና ምዕመናን ሁሉ ልዩ ትምህርት ሊሰጥ የሚችል ምሳሌ ነው፡፡ የማንነታችን ማረጋገጫ ፣ ከሌላው የዓለም ሕዝብ የምንለይበት መለያ ምልክት ምንድነው፡፡ የጌታ የሱስ መሆናችን ተለይቶ የሚታወቀው በምንድነው፡፡ የሚያዩ ሁሉ የሚማረኩበት ኢየሱስን በእኛ የሚያዩት ስለ እኛ የሚመሰክሩበት ምልክታችን ምንድነው? ስብከታችን ወይስ ወደ ቤተክርስቲያን አውትረ መሄዳችን? በጉባኤ መገኘታችን ወይስ ብዙ መማራችን? ይህ ሁሉ አስፈላጊና መልካም ነው፡፡ ሰዎች ማን እንደሆኑና ከየት እንደሆኑ በምን ዓይነት ልምምድ ውስጥ እንዳሉ በሰውነታቸው የሚታዩና የሚለጠፉ ነገሮች፣ የተለበሱ ልብሶች ለይተው ያሳዩአቸዋል፡፡ ካህናት በሚብሱት ልብስ፣ ናዝራውያን በጸጉራቸው፣ ዜማውያን በልብሳቸው፣ የመንግስት ታማኝ ታደሮች በትከሻቸው ላይ ባለው የማዕሬግ ምልክቶቻቸው፣ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ ህንጸዎችም እንደዚሁ፣ ለምሳሌ ትምርት ቤቶች፣ መስጊዶች፣ ቤተክርስቲያናት ፣ የጦር ካምፖች፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ኬላዎች፣ ሆቴሎች በላያቸው በተተከለው ምልክት ምክንያት ምንነታቸውና ባለቤትነታቸው ተለይቶ ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛ የኢየሱስ ክርስቶስና ለእርሱ አልግሎት ራሳችንን የሰጠን መሆናችን የሚታወቅበት ምልክታችን ምንድነው?
ሓዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ በሥጋችን ስለ ምንሸከመውና ተለይተን ስለምንታወቅበት መለያችን በገላትያ 617፣ ሐዋ 9 10 -16፣ እና 2ቆሮ 411-16 ባሉ ክፍሎች እንዲህ ይላል፡፡ አነባለሁ የጌታችንን ቃል፡፡ ከጳውሎስ አጠቃላይ ትምህርቶች በአጭሩ የተወሰኑ ነጥችን እንመለከታለን፡፡
1. በሥጋችን የምንሸከመው የኢየሱስ ማህተም ነው፡፡
እኔ የኢሱስን ማህተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ፡፡
ይህ አንድ ዓረፍተ ነገር ነው ፣ ነገር ግን ትልቅ መንፈሳዊ ምሥጥር ያዘለ መልእክት ነው፡፡ አጭር አሳብ ነው ግን የጳውሎስን ሕይወት ከደህንነቱ እሰከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ያለውን ዓላማ ሁሉ ተቅልሎ በውስጡ የያዘ አሳብ ነው፡፡ የጳውሎስ ብቻ ሳይሆን የእኛን የሁላችንንም ሕይወት፣ አገልግሎት፣ ትምህርት ፣ ስብከት ፣ በምድር ላይ የምንኖርበትን የኑሮ ዓላማ ሁሉ የሚያሳየን አሳብ ነው፡፡ ያውም በሰውነታችን የምንሸከመው የማንነታችን መለያ ፡፡
ሐዋሪያው ጳውሎስ በገላትያ አውራጃዎች የጌታን ወንጌል ሰብኮ ቤተ ክርስቲያናትን ከተከለ በኋላ ሌሎች ሌላ ወንጌል የሚሰብኩ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ተነስተው ጳውሎስ እውነተኛ ሐዋሪያ ስላይደለ የሚሰብከው ስብከት ትክክል አልነበረም ብለው አስተማሩ:: ደህንነት የሚገኘው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በጸጋው ብቻ መሆኑን ያስተማረውን የጳውሎስን ስብከት በማጣጣል ደህንንት የሚገኘው ሕግን በመጠበቅ፣ በመገረዝና በመልካም ሥራ ነው በማለት ምዕመናንን ከእውነተኛው ትምህርት ዘውር አድርገዋል፡፡ ይህንን የነፋቄ ትምህርት ሲሞግት ከቆየ በኋላ የገላትያን መጽሐፍ ሲያጠቃልል እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያድክመኝ በማለት ይናገራል፡፡
ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ሓዋሪያ የመሆን፣ እውነተኛ ለመሆኔ ምንም ጥርጥር የሌለው በሥጋዬ የተሽከምኩት ምልክት አለኝ፡፡ ይህ ምልክት ሌሎች የኑፋቄ አስተማሪዎች የሌላቸው ምልክት ነው፡፡ ይህን ምልክት ጳውሎስ ማኀተም ብሎታል፡፡ ጳውሎስ ይህ ምልክት የኖረበት ምክንያት ምንድነው ለሚለው የተለያዩ ምክንያች ይኖራሉ፡፡ አንደኛው በልስጥራና በደርቤ ወንጌልን በሰበከበት ወቅት ተቃዋሚዎቹ ክፉኛ ከደበደቡት በኋላ ከከተማው ውጭ ጎትተው እንደጣሉት የገላትያ ሰዎቸ ራሳቸው ያውቃሉ፡፡ ጳውሎስ እንደዚያ የተደበደበው የወንጌል ስብከት ሥራውን በተቃውሞ ውስጥ በመስበክ ለኢየሱስ ያለውን ታማኝነት በመግለጹ ምክንያት የተደረሰበት ስለሆነ በድብደባው ምክንያት በሰውነቱ ላይ የተፈጠረውን ጠባሳ ማኅተም ብሏል፡፡ እንዲያውም እርሱ አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ ( 2 ቆሮ 12 ) እንዳለው ይህ ድርጊት በተፈጸመበት ወቅት በሰውነቱ ላይ ከግርፋቱ የተነሳ የከሰተው ጠባሳ ለሁሉም ሰው የሚታይ ሲሆን ያ ደግሞ ለጌታ ኢየሱስና ለወንጌል አገልግሎት ባለው መሰጠት ምክንያ የመጣበት ነው፡፡ ይህንን በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ማንም አያድክመኝ ይላል፡፡ እኛ የጌታ ታማኝ መሆናችንን ሰዎች ሁሉ እንዲያቁልን በዚህ ዘመን የግድ የግርፋትን ጠባሳና ገጣባ ለሰው ሁሉ በሚታይ የሰውነት ክፍላችን መኖር አይኖርብንም፡፡ ነገር ግን ማኅተም የሚለው ሌላ ቁልፍ አሳብ አለ፡፡ እርሱም ከማንም ጋር ድርድር የማናደርግበት የድንነታችን ጉዳይ ነው፡፡ በጌታ ያለንን ደህነንትና ሕይወት ማንም ይሁን የማንም ትምህርት እንዲያጎድፍብን አንፈቅድለትም፡፡ ይህ ማሕተም የጌታ የመሆናችን ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህንን በኤፌሶን 113-14 እንመለከታለን፡፡ ከምንም በላይ የደህንንታችንና ስደህንነታችን የሚሰጠው ትምህርት ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በምንም የሚለና ከምንም ጋር የምናወዳድረው አይደለም፡፡ ስለዚ ነው ጳውሎስ የጌታ የኢየሱስን ማኅተም ሥጋዬ ተሸክምአለሁና ማንም አያድክመኝ የሚለው፡፡ ማተም የባቤትነት ማረጋገጫ ነው፡፡ የማን እንደሆንን እና ለየትኛው ዜጋ እንደሆንን የማያን ሰዎች የሚለዩን በያዝው መታወቂያ ወይም በታታመበት ማሕተም ነው፡፡ የበግ ነጋዴዎች በጅላ ካጫኑቸው በጎች ውስጥ የየራሳቸውን በጎች ለይተው የሚያውቁት በበጎቹ ጀርባ ላይ በቀቡት የቀለም ማሕተም ነው፡፡ ለእኛ ደግሞ ለእግዚአብሔርና ለመንግሥቱ የተለየን መሆናችን የሚታወቅበት ትልቁ ማኅተማችን በሥጋችን የተሸከምነው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው፡፡
2.     የጌታችን የኢየሱስን ስም ነው(ሐዋ 910-16)
በደማስቆ ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀመዝሙር ነበር፣ ጌታም በራዕይ ሓናኒያ ሆይ አለው፡፡ እርሱም ጌታ ሆይ እነሆኝ አለ፡፡ ጌታም ተነስተህ ቅን ወደሚባለው መንገድ ሂድ በይሁዳም ቤት ሳውል የሚባል አንድ የጤርሴስ ሰው ፈልግ፡፡ እነሆ እርሱ ይጸልያልና ሓናንያ የሚሉት ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቷል አለው፡፡ ሐናንያ መልሶ ፣ ጌታ ሆይ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቻለሁ ፣ በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው አለ፡፡ ጌታም ይህ በአሕዛብም ፣ በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፣ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁ አለው፡፡
ጌታ ኢየሱስ ከጳውሎስ ምን ፈልጎ እንደጠራው ይህ አሳብ ይነግረናል፡፡ ጳውሎስ በአህዛብ አገሮች ቤተ ክርስቲያናትን ተክሏል፡፡ ብዙ ሰዎችን የጌታን ቃል አስተምሯል፡፡ እደነ ጢሞቴዎስ ያሉት ደመዛሙርትና የቤተ ክርስቲያን መጋቢያንን አፍርቷል፡፡ እንደምናየው ዛሬም ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት የሚሆኑ 13 የሚያህሉ መልእክቶችን ጽፎ አል፡፡ በተዘዋወረባቸው አገሮችና መንደሮች ሉ ተአምራቶችን ሁሉ አድርጓል፡፡ እነዚህ ሁሉ ሥራዎቹ የተጠቃለሉት በአህዛብም በነገሥታም፣ በእሥራኤልም ልጆች ፊት የጌታን ስም በመሸከም ውስጥ ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ልናደርጋቸው የተገባን ቢሆንም ከሁሉም በላይ የጌታን ስም የምንሸከምለት ዕቃው ንድንሆን ይፈለግብናል፡፡ ዛሬ አማኞች በምንኖርበት የክርስትና ሕይወታችን የጌታ የኢየሱስ ስም ከፍ ብሎ ይውለበለባል ወይስ ይሰደባል? መቅረዝ የሚባል ዕቃ አለ፡፡ ይህ መረዝ የሚባው ዕቃ በአድ ቤት ውስጥ መብራትን ከፍ አድርጎ የሚሻከም ነው፡፡ መቅረዙ መብራቱን ከፍ አድርጎ ሲሸከም መብራቱ ሲታ እርሱም አብሮ ይታያል፡፡ መብራቱ ካታየ ግን መረዙ ምንም ክብር ሊኖረው እንደማይች ሁሉ እኛም የኢየሱስን ስም ካተሸከምን ከክርስቶስ የሚጣውን ክብር ልናይ አንችልም፡፡ ወገኖቼ ሆይ ዛሬ ራሳችንን የጌታ ዕቃ አድርገን አቅርበናል ወይ? ክቡር ስሙን ለመሸከም የተመረጥን ዕቃዎች መሆናችንን አውቀን ስሙን እተሸከምን ነው ወይስ ራሳችንን እያወጅን ነው? በየቤተ ክርስቲያናችን መድረክ ኢየሱስ ይሰበካል? መድረክ ስንወርሰድ ሰዎች ኢየሱስን እንዲመለከቱ ስሙን እንዲጠሩ ፣ በስሙ እንዲታመኑ ፣ የኢየሱስ ብቻ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ ስሙን ከፍ እያወጅን ነው ወይስ የእኛ ስም እያወጅን ነው? ተሸካሚ ዕቃ ለራሱ አይኖርንም ለተሸከመለት ጉዳይ ይኖራል ምክንያቱም ዕቃ ነውና፡፡ የሚታየው እርሱ አይደለም ያ የተሸከመው እንጂ፡፡ ተሸካሚው ምንዜም ከታች እንጂ ከላይ ሊሆን አይችልም፡፡ እኛ ከታች ሆነን የጌታ ስም በእኛ ላይ ሆኖ ሰዎች ሁሉ ይህንን ስም በሰውነታችን፣ በሕይወታችን ፣ በአካሄዳችን አኗኗራችን ያዩታል ወይ?
3. የክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ነው( 2 ቆሮ. 4 7-16)
የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፡፡፡ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፣ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፣ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፣ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፡፡የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁል ጊዜ የኢየሱስን ሞት በሥጋችን ተሸክምን እንዞራለን፡
ይህን አሳብ ለመግለጸው ሐዋሪያው ጳውሎስ ከቀጥር 7 ጀምሮ በጣም አስደናቂ ነገር ይናገራል፡፡ በእኛ እግዚአብሔር የሚሠራው ሥራ የሚያስገርም መሆኑን ሲያመለክት  እንዲሁም ደግሞ አንድንም ነገር በራሳችን ብርታት እንዳላደረግነው እንድናውቅ ያሳስበናል፡፡ የኃይሉ ታላቅነት ከእኛ እንዳይደለ እንድናውቅ ያሳስበናል፡፡ በዓለም ላይ ብርቱዎች የተባሉ ብዙዎቸ እያሉ እግዚአብሔር አምላክ የክብር መዝገቡን ሸክላ በሆንንው በእኛ ውስጥ እንዳስቀመጠ ይናገራል፡፡ ሸክላ ምንም ክብር የሌለው ነገር ነው፡፡ በጣም ደካማ ነገር ነው፡፡ አንዴ ወድቆ ከተሰበረ መልሶ መጠገን የማይችል በጣም አሳዛኝ የሆነ ዕቃ ነው፡፡ ሸክላ ከአር የሚሠራ ነው፡፡ ሸክላ ደካማና አቅመ ብስ ነው፡፡ ሸክላ ብዙ ክብርም የሚሰጠው ነገር አይደለም እንዲም የሸክላ ዕቃ የሚሠሩ ሰዎችም ጭምር በሌሎች ዘንድ ክብር የማያገኙባቸው ብዙ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ግን የሚገርመው ነር ቢኖር ይህ ደካማ የሆነ ተሰባሪ ዕቃ ውድ የሆነውን ነገር ለመሸከምና በውስጡ ለመጠበቅ መመረጡ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በሸክላ ዕቃ ውስጥ ወርቃቸውን ይኖሩታል፣ ብራቸውን ያስቀምጡበታል፣ ጌጣቸውንም ይደብቁበታል፡፡ ሽካላ ዕቃ ተሰባሪና የተናቀ ደካማ ነው ግን በጣም ውድ ለሆነ አገልግሎት ይውላል፡፡ በጥንት ጊዜ የእግዚአብሔር ሰዎች በጣም አስፈላጊ የሆነ የብራና ጽሑፋቸውን መሸሸግ ባስፈለጋቸው ወቅት በእንሥራ ( በሸክላ ዕቃ) ውስጥ አድርገው በዋሻ ስለሸሸጉት ሰነዱ ሳይጠፋ ለዘመናት እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ዕቃው ሸክላ ነው ግን ለክቡር አገልግሎት ተፈለገ፡፡ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በኩል ባለው በረሀማ አካባቢ የኖሩ ኩምራን ሶሳይቲስ የተባሉ በሚኖሩበት ኩምራን  ዋሻ ውስጥ የተገኘው የሙት ባህር ጥቅል የተባለው ብራና የተገኘው በዋሻ ውስጥ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ታሽጎ ነበር፡፡ ይህ የሙት ባህር ጥቅል የተሰኘው ብራና ትክክለኛ የሆኑ ብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በውስጡ የያዘ የጥንት  ጽሑፍ ሲሆን ለበርካታ ዘመናት ተደብቆ የቆየውና ከመቃጠልና ከመውደም የተረፈው በሽክላ ዕቃ ውስጥ ነበር፡፡ በጊዜው የነበሩ ሰዎች ያንን ስክሮል ለመሸሸግ ለምን የሸክላ ዕቃ እንደመረጡት ባይገባኝም ግን ታሪኩ በጣም ያስደንቀኛል፡፡ ወገኖቼ ሆይ እግዚአብሔር አሁንም እያደረገ ያለው ይህን ነው፡፡ የእርሱን ታላቅ ሥራ በሚያምኑትና በማያምኑት ሁሉ ዘንድ ለማስፈጸም እኛን ደካሞችን፣ ሸክላዎችን፣ ተሰባሪዎችን መረጠና ክቡር መዝገቡን በእኛ ውስጥ አኖረው፡፡ ለምን? የእርሱ ሥራ በሰው ኃይል እንደማይከናወን ንዲወቅ ነው፡፡ ኃይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ እንዳይደለ እንዲታወቅ ነው፡፡ በዓለም ስንኖር ይህ የክብር መዝገብ እያለ በሁሉ እንገፋን፣ እናመነታለን፣ እንሰደዳለን፣ እንወድቃለን ይላል፡፡ ይን እንጂ አንጨነቅም፣ ተስፋ አንቆርጥም፣ አንጠፋም ይለናል፡፡ ምክንያቱም ጌታ በውስጣችን ላስቀመጠው መዝገቡ ስለሚጠነቀቅ ነው፡፡
ጳውሎስ ይህንን አስደናቂ ነገር ከተነናገረ በኋላ አሁንም በሥጋችን ስለምንሸከመው ጉዳይ ይናገራል፡፡ እንዲያው በሥጋችን የኢሱስን ሞትና ሕይወት ተሸክምን ንዞራለን፡፡ የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን ይላል፡፡ ወንጌልን በመስበካችን ምክንያት የተለያዩ መከራዎች ቢደርሱብንም እንደሚደርሱብን መከራዎች ብዛት መጠን አንጠፋም ምክንያቱም ለደካማው የሸክላ ዕቃ የእግዚአብሔር ርዳታ ስለማይለየው ነው፡፡ ከዚህም በላይ በመገፋት ፣ በማመንታት፣ እና በስደት ውስጥ በምናልፍበት ጊዜ ሁሉ እኛን በሚያዩን ሁሉ ፊት የኢየሱስ ሞት በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን፡፡ ይህንን የምናደርገው የኢየሱስ ትንሣኤ በሰዎች ሁ ዘንድ እንዲታወቅ ነው፡፡ በወንጌል አገልግሎታችን ምክንያት ለሞት አልፈን የምንሰጥ ቢመስለንም ግን የኢየሱስን ሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን ይላል፡፡ እንዞራለን ማለት ምን ማለት ነው በሚያዩን ሁሉ ዘንድ ፣ የምንመላሰው የኢሱስን ሞትና ትንሣኤ እያጅን ነው፡፡ የቤተ ክርሰቲያን በምድር የመኖሯ ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ለሁሉም ማወጅ ነው፡፡ እኛ ይህንን እድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
የቤተ ክርስቲያን ትልቁ ጥሪ የጌታችንን የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤ በዓለም ላይ ከፍ አድርጋ መሸከም ነው፡፡ የክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ መስበክ ከጳውሎስ በፊት ሆነ ከእርሱ በኋላ የነበሩ ነቢያትና ሐዋሪያት ቁልፍ ተግባርና የተልዕኮአቸው ማእከል እንደሆነ  ቅዱሳት መጸሕፍትን በምናነብበት ጊዜ የምናገኘው ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነቢይ የነበረው መጥመቁ ዮሐንስ ከኢየሱሰስ በፊት የመጣ ነበር፡፡ እርሱ መንግሥተ ሰማይ ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ እያለ ለንስሐ በውሃ እያጠመቀ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ በሰበከበት ወቅት አንድ ምቹ አጋጣሚ አግኝቶ ነበር፡፡ ያውም ሰዎች አንተ ማነህ ፣ መሲሁ ነህን? ኤልያስ ነህን፣ ኤርምያስ ነህን፣ ነቢዩ ነህ እያሉ ሲጠይቁት ሁሉንም አይደለሁም ነው ያላቸው፡፡ ስለራሳችን ዝና፣ ክብርና ሞገስ እንደምንኖረው የዛሬው ዘመን አገልጋዮች ቢሆን ኖሮ ስለ ራሱ ብዙ መናገርና ብዙ ክብር ማግኘት ይችል ነበር፡፡ ግን አይለደለሁም አለ፡፡ ታዲያ ማን ነህ ሲሉት እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፣ ከእኔ በኋላ የሚመጣው አጎንብሼ የእግሩን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔም የሚበረታ መንፈስ ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቃችሁ ነው አለ፡፡ ኢየሱስ ሲመጣ ኣይቶ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያወግድ የእግዚአብሔር በግ ብሎ ወደ ኢየሱስ አመለከተ፣ እንዲያውን እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባኛል ብሎ ክብርን ለኢየሱስ ሰጠ እንጂ ከራሱ ባገኘው አጋጣሚ ክብርን ሙገሳን አልወሰደም፡፡ ስለዚህ ከሴቶች ከሚወለዱት መጥመቁ ዮሀንስን የሚበልጥ የለም ተባለለት፡፡ ጌታ ሲከብር እርሱም አብሮ ከበረ፡፡
ሐዋሪያው ጳውሎስም አንደዚሁ ነው፡፡
የኢየሱስን መኅጸም በሥጋዬ ተሸክሜአሁ፣
ግሪኮች ጥበብን ይሻሉ፣አይሁዶች ምልክትን ይፈልጋለሉ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እሰብካለን፡፡
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነው
ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቆጥሬዋለሁ …. እርሱንና የትንሳኤውን ኃይል አውቅ ዘንድ ቢሆንልኝ በሞቱ እንኳ እመስለው ዘንድ እነፍቃለሁ
ከጌታችን ከኢየሱስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ራቅ አለ፡:
እኔ ክርስቶስን እንደሚመስል እናንተ ደግሞ እኔን ምሰሉ
በቆላስይስ መልእክት ብቻ ከ18ጊዜ በላይ ክርስቶስን የበላይነት ጠቅሷል፡፡
አንዳንድ ይወታቸው ለጌታ ያልታመኑ ሰችን ሲገልጽ ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉ የክርስቶስ ኢየሱስን ግን አይደለም፡፡ ፊል 221
18ኛው ክፍለ ዘመን የፑሪታን አባት ተብለው ሚጠሩ ዊሊያም ፔርክስ የተባሉ የሥነ መለኮት ሰው ትምህራቸውና የሕይወታቸው መፈክር ለክርስቶስ፣ በክርስቶሰ፣ ስለ ክርሰቶስ የሚል ነበር፡፡ በቅርቡ ከሁለት ዓመት በፊት ገዳማ ወደ ጌ የተጠሩት የእግዚአብሔር ሰው ጆን ሰቶትም ክርስቶስ ካተሰበከ ስብከቱ አልተሰበከም፡፡ ክርቶስ ካልዘመረ ዘማሪው መዝሙሩን አልዘመረውም፣ ክርስቶስና ስሙ ካታከሉበት ሎቱም አልተጸለየም ብለዋል፡፡
4. የጌታ የኢየሱስን መስቀል መሸከም፡፡ ማቴ. 1624-28፣ ሉቃስ 9 23-24
ሰዎች ጌታን እንደተቀበሉ መጀመሪያ የሚሰጣቸው ትምህርት የደቀመዝሙርነት ትምህርት ነው፡፡ ጌታ ማንም እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር መስቀሌን ይሸከም ያለውን ትምህርት አማኞች የው ጥምቅ እስክ ወስዱ ድረስ ብቻ ብቻ እናስተምራቸዋለን፡፡ ከዚያ በኋላ ላለው የክርስትን ሕይወት ዕድገት ደረጃዎች ውስጥ እንደማያስፈልገን አድርገን እንመለከተዋለን፡፡
ይሀን እንጂ የጌታን መስቀል መሸከም እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ የምንተገብረውና የማናቋርጠው ጉዳይ ነው፡፡ ክርስትና ደስ የሚል የሕይወት ጉዞ ቢሆን መስቀል የመሸከም ግዴታ ያለበት መሆኑ ደግሞ ሌላው ገጽታው ነው፡፡ በክርስትና ሕይወት ጦርነት ድል፣ ያለ መስዋዕትነት ክብር ፣ ያለመሰጠት በረከት የለበትም፡፡ ስለዚህ ክርስትና እንዴት ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚፈልግ እንደሆነ እንመለከታለን፡፡ ኢየሱስ  በዚህ ሥፍራ ምንም እኔን ለመከተል የሚወድ የሚወድ ቢኖር  የሚል ቃል ተጠቅሞአል፡፡ በሌላ ሥፍራ ደግሞ ከኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር አለ፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው; ማንም ክርስቲያን ሊሆን የሚፈልግ ማለቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ክርስትና የጥንት ስሙ መከተል ወይም መንገድ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በአንጾኪያ ክርስትና ከመባለቸወው በፊት ክርስትና መንገድ በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አማኞችም ደግሞ የመንገዱ ሰዎች ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ እኔን መከተል የሚወድ ወይን ከኋላዬ ሊመጣ የሚወድሲል ክርስትያን መሆን የሚወድ ወይም የሚፈልግ ማለቱ ነው፡፡ ክርስትና መሆን ደግሞ የአንድ ጊዜ ሞቅታ የሚያመጣው ሳይሆን ሁል ጊዜ የምንተገብረው ነው፡፡ የኢየሱስ ተከታይ መሆን ፣ የእርሱ ተማሪ መሆን  የክትትል ትምህርት ጨርሰን ወደ አገልግሎት መሥመር እስክንገባ ድረስ ብቻ የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ኢየሱስን የምንከተው ፣ በመንገዱም የምንራመደው በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ነው፡፡
እህግዲህ ይህ አሰብና እውነት ዛሬ ተረስቷል፡፡ አንዳንድ ጊዜ  ወደ አገልግሎት ደረጃ ከደረስን ምንም ከክርስትና አኗኗር እንደተመረቅን ይሰማናል፡፡ ግን የእግዚአብሔር ቃል መስቀሉን መሸከም ያለብን በየዕለቱ እንደሆነ ይነገረናል፡፡ በየዕለቱ እንምንዘምረውና እንደምናገልግለው ሁሉ በየዕለቱ የጌታን መስቀል እንሽከማለን ማለት ነው፡፡ መስቀሉን ሳይሸከሙ በኢየሱሰስም ንገድ ሳይሄዱበት የሚያገልገልሉት አገልግሎት ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም ለምዕመናንም አይጠቅምም፡፡ በኢየሱስ መንገድ ሳይሄዱበት የሚደረገው አገልግት፣ ዘማሪነት፣ ሰባኪነት፣ አስተማሪነት፣ መሪነት ሁሉ  ለቤተከርስቲን እጅግ በጣም ጠንቅ ነው፡፡ የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ትለቁ ችግር የአገልጋዮችና የመሪዎች ችግር ሳሆን በሕይወታቸው ጌታን የማይከተሉ አገልጋዮችና መሪዎች የተበራከቱ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ለመሆኑ በሕይወታቸው ኢየሱስን የማይተሉ መሪዎችና አገልጋዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እናውቃለንን;
የኢየሱስ መሆናችንና በመንገዱ የመሄዳችን ትልቁ መሥፈርት አንዱ ራስን መካድ ነው፡፡ ራሳችን ካልካድን የእርሱን መንገድ መምረጥ እንችልም፡፡ ሰው ወደ ጌታ ሲመጣ ራሱን ሲክድ ብቻ ነው ኢየሱስ በልቡ የሚነግሰው፡፡ ሰዎች ክርስትያኖች አንዲሆኑ እናስተምራቸውና ራሳቸውን እንዲክዱ ስላላገዝናቸው ማነታቸውና እነርሱነታቸው በውስጣቸው ይኖራል ፣ ሲያድጉም ያ እኔነታቸው አብሮ እያደገ እየጎመሰ ይሄድና የክርስቶስን ቦታ ይይዝባቸዋል፡ ከዚህ የተነሳ በሕይወታቸው ጌታን ሌለሎች ማሳየት ያቅታዋል፡፡ ምክንያቱም በልባቸው ዙፋን ላይ ፣ በሕይወታቸው የውስጠኛው ክፍ ላይ ቦታውን የያዘውና የሞላው ጌታ ኢየሱስ ሳይሆን እኔነቻው ነው፡፡ እኔን አወድሱኝ የሚሉ መጋቢዎች ገጥሞአችሁ አያውቁም; እኔ ነኝና ባለመፍትሔው እኔን ብቻ የሚሉ አገልጋዮች ገጥሞአችሁ አያውቁምእነዚህ ራስን ያለመካድ  ችግር ተጠቂዎች ናቸው ማለት ነው፡፡ ራሳችንን በካድን ጊዜ እኛ ሳንሆን እገዚአብሔር ብቻ ሕይወታችንን ሊያድን እንደሚችል አውቀን ራሳችንን በእርሱ እጅ ላይ ወደምንጥልበት የአቅም ደረጃ እናድጋለን ማለት ነው፡፡ ስላራችንን ያለንን የተሳሳተ ግምት ትተን ፣ ሰይጣንም የሚሰጠንን ፍቅር ሁሉ ወደ ጎን በመተው በክርስቶስ ፍቅር ወደምንታሰርበት ካፓሲቲ እያደግን እንሄዳን ማለት ነው፡፡ በአንጸሩመ ደግሞ ራሳችንን ወደ ማገሱና መሸሙ ደረጃ በደረሽን ቁጥር ጌታን ከልባችን ዙፋንና የክብር ሥፍራ ወደ ማውረዱ ደረጃ እየተሸጋርን እሄዳለን ማለት ነው፡፡ ሰዎች የእግዚአብሔር ነገር እንደተወሰደባቸው ከሚታወቅበት መንገድ አንዱ እኔ እኔ እኔ ሲሉ ነው፡፡ በእኔነት የተሞላው ሰው ጌታ ኢየሱስን ለሌሎች ማሳየት አይችልም ምክንያቱም ሰው በውስጡ ከሞላው ነገር ያፈሳልና፡፡
ሁለተኛው መሥፈርት ፈቃደኝነት ነው፡፡ የሚወድ ቢኖር ( የሚፈልግ ቢኖር) የሚለው አሳብ በጣም አስፈላጊ ቃል ነው፡፡ ሁሉም ነገር በራስ ውሳኔ በፈቀደኝነትና በፍቅር ነው፡፡ ይህ ማኛውንም ነገርለማድረግ የሚያስችለን ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔርም ሆነ ሰይጣንም የራሳቸውን መንገድ እንድንከተለ የሚያደርጉን በፍቅር ነው፡፡ ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ የእርሱ ተለታች የሚየደርገን በፍቅር ነው፡፡ ሰጣን ደግሞ የራሱ ተከታዮች የሚያደርገን ፍቅርን በማሳየት ነው፡፡ ሰይጣን ፍቅርን የገለጠበት መንገድ ኢየሱሰስ ፍቅርን ከገለጠበት መንገድ ይለያል፡፡ ይህንን ነው አማኞች መለየትና መንቃት ያቃተን፡፡ ኢየሱስ ምክንያታዊ ባልሆነ ፍጹም ፍቅር ወደደን፡፡ እኛን አብልጦ ከመውደዱ የተነሳ ክቡር ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ክቡር ደሙንም ስለ እኛ አፈሰሰልን፡፡ ሰይጣን ደግሞ ፍቅር የገለጠው  ሰዎች ብቻ አፍቃሪዎች እንዲሆኑ በማድረግ ነው፡፡ የገንዘብ አፍቃሪዎች፣ የክብር አፍቃሪዎች፣ የዝሙት አፍቃሪዎች፣ የዚህ ዓለም አፍቃሪዎች ፣ የዘር የወገን አፍቃሪዎች፣ የመጠጥ የሲጋራ የጫት ፣ ተድላ ወዘተ አፍቃሪዎች እንዲሆን ያደርግና ጌታ የሚያፈቅሩበትን አቅም ይወስድባቸዋል፡፡ እዚያ ውስጥ ግን ሳይታወቅ እየተወደደ ያለው እርሱ እንደሆነ ማንም ላያስተውል ይችላል፡፡ ለሰዎች ደግሞ የሚያምራቸው መንገድ ሰይጣን የገለጠው መንገድ ነው፡፡ ስዚህ መከራን ፣ ችግርን፣ ስዴትን ልፋትንና መንፈሳዊ ጦርነትን እንዲሁም መስዋዕትነትን የሚጠይቀውን የኢሱስን መንገድ ለጊዜውም ዞር አድርገው ይሕንን በጣም ማራኪና ናፋቂ የሆነ ልፈትና እንግልት የሌለበትን የፍቅረር መንገድ መከተል ይላቸዋል፡፡
ሌላው እንግዲህ መስቀሉን መሸከም ነው፡፡ ምንድነው መስቀሉ;  መስቀል የመሸከም ጉዳይ ብዙ ጊዜ የማይገባን ምስጥር ይሆንብናል፡፡ ሌላው ቀርቶ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትም ቢሆኑ ግር ሳይላቸው አልቀረም ምክንያቱም ኢየሱስ መስቀሉን ማይሰከም ለእኔ ሊሆን አይችልም ሲል ገና በመስቀል አልተሰቀለም ነበርና፡፡ ይሁን እንጂ በጊዜው ከኢየሱስ በፊት በመስቀል ላይ የተሰቀሉ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ ለመምጣቱ ምናልባት 120 ዓመታት በፊት ኢንተርተስታሜንት ፒሬድ ተብሎ በሚታወቅው ጊዜ አንቲክዮስ ኤፒፓኔስ በግሪክ መንግሥት ሥልጣን ጊዜ በርካታ አይሁዶችን  በእንጨት ላይ ሰቅሎ ገድሎአቸዋል፡፡ ደግሞ  የሮማውያን ንጉሥ ታላቁ  ሄሮዲስ 2000 አይሁዶችን ሰቅሎአቸዋል፡፡ በኢየሱስ የምድር አገልግሎት  ጊዜ  ሥቅላት በግሪክ፣ በሮማውያን፣ በመካካላኛው ምሥራቅ በግብጾችም ዘንድ በጣ የተለመደ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች 30.000 አይሁድ በስቅላት ተገድለል የሚል ግምት አላቸው፡፡ ይህንን ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ያውቃሉ፡፡ ቢሆንም ኢየሱስ የሚለው ከባድ ሊሆንባቸዋል፡፡ እንዲህ ኢየሱስን መከተል እና የክርስትና ሕይወት መኖር ምን ዓይነት ከባድ እንደ ነበረ የሚያሳይ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ብዙ ሰዎች የመስቀልን ከቁሳዊ ገጽታ በላይ ባለፈ ማየት የሚሳነን ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ ግን መስቀልን መሸከም ስንል ምን ማለታችን ነው› የክርስትናችን ምልክት ነው አይደለም;፡፡ በደረት ኪሳችን ላይ የምናስቀምጠው፣ በቤተክርስትያናችን ሕንጻ ላይ የምንተክለው፣ በአንገት ብላችን ላይ የምናሳትመው፣ ሌላ ሌላም፡፡ አዎን ውነት ነው ግን በልባችን የሚሳውም እርሱ ሊሆን ይገባዋል፡፡ መስቀሉ ለእኛ ምን ያሳየናል;  ጌታ ኢየሱስ በሄደባቸው መንገዶች ሁሉ ለመሄድ ራችንን የሰጠንበት ሕይወት ተሞክሮ አይደለምን ; ክርስትና እኮ ኢየሱስ የኖረበትን ሕይወት ለመኖር በመወሰን ራሳችንን የምንሰጥበት መርህ ነው፡፡ ይህ መርህ ማቴ 1024 ላይ እንደተቀመጠው ባሪያው እንደ ጌታው ደቀመዝሙሩ እንደ መምህሩ የሚሆኑበት የሕይወት መርህ ነው፡፡ እኛ ኢየሱስስን ለመከተል ስንል ሕይወታችንንና እኛነታችንን ለእርሱ የምንሰጥበት የሕይወት መርህ ነው፡፡
ከዚህም በላይ ጌታ ኢየሱስ ስለ እኛ መከራን የተቀበለበትን፣ የተዋረደበትን፣ የተንገላታበትን የሚያሳይን ነው፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ተወረዶ እኔን ያስከበረበትን፣ የእኔን ነፍስ ሊያረካት ተጠማሁ ያለበትን፣ የእኔን እጅና እግር ለክብሩ ለመማረክ እጅና እግሩን የተቸነከረበትን፣ እኔን ከአብ ጋር ሊያስታርቀኝ እርሱ በአባቱ የተራሳበትንና አባቴ አባቴ ሰልምን ተውከኝ ያለበትን ፣ የእኔን ቁስል ለመፈወስ እርሱ ጀርባው በሮማውያን መጥፎ ጅራፍ አለንገጋ የተተለተከበትን ፣ እኔን የእግዚአብሔር፣ የሰውና የራሴ ጠላት የሆንኩትን ሰው የእርቅና የሰላም ሰው ለማድረግ የሚያደርጉትን አየውቅምና ይቅር በላቸው ብሎ የተማጠነበትንና ያማለደበትን ያንን የክርስቶስን መስቀል በሥጋዬና በነፍሴ ተሸክሜአለሁ፡፡ እንግዲህ ይህንን በሕይወታችን በምንተግብርበት ጊዜ የማነታትችን መለያለሁሉም ያወቃል ማለት ነው፡፡
5. የጌታ የኢየሱስ ቀንበር መሸከም( ማቴ 1129-31)
እኛ የኢየሱስ መሆናችን ከሚታወቅበት መንፈሳዊ ገጽታዎቻችን አንዱ ቀንበር መሸከም ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ብዙ ሰው በክርስትና ሕይወቱ መስቀል ስለመሸከም ይሰማል ቀንበር መሸከም የሚባል ነገር እንዳለ አያውቅም፡፡ ብዙዎቻችን የመስቀል ምልክት አለን ግን የቀንበር ምልክት የለንምምክንያቱም ቀንበርን ስለመሸከም ብዙም ትኩረት ስላለሰጠን ነው፡፡ መስቀልምን መሸከም ያልቻለ ነው ቀንበርንም መሸከም ሊከብድበት ይችላልና፡፡ ምክንያቱም መስቀል ወደ ክርስትና ሕየወታችን ከገባንበት ቀን ጀምሮ የምለማደው ስለሆነ ቀንበር ወደምንሸከምበት ሁኔታ ስንደርስ ቀላል ይሆናል፡፡ መስቀልን መሸከም ያልተለማመደ ሰው ቀንቡም የዚያሀውኑ ያህል ሊከብደው ይችላል፡፡ ግን መሸከም ማን ማለት ነው፡፡ አይሁዶች ቀንበር የሚለውን ቃል የሚወስዱት በአንድ ነገር ውስጥ ለመግባት ራስን ከመስጠት ጋር በማያያዝ ነው( ሳሚሺን) ፡፡ በሐዋሪት ዘመን መሪዎቻቸው ሕዝቡ ሊሸከሙ የማይወዱትን ቀንበር ( ግዴታ) በትከሻው ላይ ይጭኑባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም የሮማውያን አገዛዝና ሥልጣን በሕዝቡ የተወደደ ሳይሆን በግድ ተብሎ የተጫነ ቀንበርና እሥራት ነበር፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ ለሕዝቡ ቀንበሩን እሰብራሁ እያለ ተስፋ ይሰጣቸው የነበረው፡፡ መጥፎ ቀንበር፣ የባርነት ቀንበር፣ የጭቆና ቀንበር  ተጭኖባቸው ስለነበር ሕዘቡ ወደ እግዚአብሄር በጮኹ ጊዜ እገዚአብሔር ቀንበሩን  ከትከሻቸው እንሚሰብር ተናረ፣ ያም ቀንበር ደግሞ በጌታ በኢየሱስ ስም ተሰብሮልናል፡፡
ኢሱስ በማጣ ጊዜ ወደ እርሱ የሚመጡትን ቀንበር እንዲሸከሙ ጥሪ አድርጎላቸዋል፡፡ ይህንን ያደረገው ግን በሕይወታቸው ያለውን ከባዱን ቀንበር ሁሉ ከሰበረ በኋላ ነው፡፡ በነፍሳቸውም ያለውን ቀንበርና ሸክም ሁሉ ካወረደላቸው በኋላ ነው፡፡ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ ብሎ ነው፡፡ የእናንተን መጥፎ ሸክም እኔ አነሳለሁ እናንተ ግን የኔን ቀላልና እረፍት የሚሰጠውን ሸክም የሆነውን ቀንበር በላያችሁ ተሸከሙ ይለናል፡፡  ልክ እንደመስቀሉም ሁሉ ቀንርም ከእንጨት የሚሠራ መሣሪያ ነው፡፡
ቀንበር ለኃላፊነት የምንሰጥበት መንገድ ነው፡፡ ቀንበር የሚሠራውም በሰለጠኑ አናጢዎች እንስሳውን በማይጎዳ መልክ ተለክቶ የሚሠራ ነው፡፡ ከዚያ ቀንበር ሥር የሚሆነው በሬ ሞፈሩን ለመጎተት፣ በገበሬውም ትልም ለመመራት፣ ትልሙንም የመቅደድ ኃላፊነቱን ለመቀበል አቅመ ቢስ ከሆነው ገበሬ እጅ ሥር ራሱን አስገዝቶ በቀንበሩ ላይ ባለው ማነቆ ይተሰራል፡፡  እንደዚሁም ሁሉ የጌታን ሥራ ለመስራት የአገልግሎትንም ኃላፊነት ለመቀበል በፈቃዳችን ራሳችንና ሁለንተናችንን ለጌታ ለኢየሱስ መስጠታችንን የሚያመላት ነው፡፡ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ የሚለው ቃል፡፡
በኢሱስ ጊዜ ለቀንበር የሚሰጠው ሌላው ምሥል ደግሞ መማር ነው፡፡ ተማሪው ሁሉ ጊዜ በራሱ ውዴታ ከመምህሩ ለመማር ይመጣል እንጂ ተማሪ አስገድዶ የሚያስተምር አስተማሪ በፍጹም የለም፣ አይኖርምም፡፡ ስለዚህ አይዶች ቀንበርን ምን ይሉታል የህግ ቀንበር፣ ቶራህ ቀንበር፣የትዕዛዝ ( ኮማድሜንት)ቀንበር፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የእግዚአብሔር ቀንበር ብለው ይጠሩታል፡፡  ጌታ ኢየሱሰስም ያኑትን የሚጠይቃቸው አንዱ ጥያቄ ይህ ነው፡፡ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ( ከእኔ ተማሩ ) ይላቸዋል፡፡ የእርሱን ቀንበር መሸከምና ከእርሱ መማር ለት ምን ማለት ነው፡፡ ለእርሱ አመራር፣ ትምህርት ሥልጣን ራሳችንን መስጠት ማለት ነው፡፡  ይህ መታዘዝን የሚያሳይ ቀንበር ነው፡፡ ይህ ቀንበር በክርስትና ሕይወታችን ስንኖር ይንጨነቅበትና የምንጠበብበት ሳይን እፎይ የምንልበት ነው፡፡ ለጌታ ታዘዝና ራሳችንን ለእርሱ መስጠት እረፍትን የሚሰጥ ነው፡፡ ሸክማችሁን ወደ እኔ አምጡ እኔ አሳርፋችኀዋለሁ ብሎ እዳሳረፈ ሁሉ ቀንበሩንም ስንከም ነፍሳችንን ያሳርፋታ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ለነፍሳችሁ እረፍትን ታችሁ የሚለን::
ኢየሱስን ቀንበር የመሸከም ሌላው ምስጥር ደግሞ ትብብር ነው፡፡ ከእንዱ ከሌላው ጋር በሕብረት መዋሄድን የሚያመለክት ነው፡፡ ቀንበር በአንድ በሬ ትከሻ ብቻ አይጫንም፡፡ ሁለት በሬዎች ናቸው የሚገትቱት፡፡ የበሬዎቹ ትክለ ቁና፣ እድመሜ ፣ ጉልበት፣ ልምድ፣ ባሕሪያ ወዘተ የተለያየ ሊሆን ይችላ፡፡ እነዚህ የተለያዩ በሬዎችን በአንድ ሥራ ላይ የሚያሰማረው ቀንበሩ ነው፡፡ሁለቱ በቀንበር ሥራ ሆነው አንዳቸው ለሌላው ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሲሰጡ በእነርሱ ላይ ጌታ የሆነው የገነሬው ሥራ ወይም እርሻው በተሳካ ሁኔታ ይታረሳል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከሁለቱ በሬዎች አንዱ እምቢ ያለ እንደሆነ እርሻው ሳይታረስ ሊከርም ይችላል ከቀንበር ምስጥር ይንማረው አንዱ ይህን ነው፡፡ ጌታ ቀንበሬን በላይችሁ ተሸከሙ ሲለን በእግዚአሔር እርሻ ላይ ለመሰማራት አንዳችን ለሌላችን ራሳችን ዝቅ ማድረግን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ከባድ ሆኖብናል፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አሁንም ይህንን እንድናደርግ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ወንድሞችና እህቶች ሆይ ይህ ታላቅ ምስጥር ነው፡፡ ትልቅ በረከት ያለበት ነው፡፡ ለወንጌላውያን አብያተክርስትያና አገልጋዮች ዘንድ ትልቅ ፈተና የሆነብን ይህ ነው፡፡ ሸክማችንን በኢየሱስ አጠገብ ላመስቀመጥና ለማረፍ በጣ እንመኛለን ግን የእርሱን ቀንበር በሸከም የሚገኘው የነፍስ እረፍት ለማወቅ አልቻልንም፡፡ ሐዋሪው ጳውሎስ ማን ባልንጀራው ከእርሱ እንዲሻል ይቁጠር የሚለው ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስም እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ ብሏል፡፡ ሰዎች እኛ የኢሱስ መሆናችንን የሚያቁብ መንገድ ወይም መለያ ምልክታችን የእርስ በርስ ፍቅር ነው
6. የቅዱሳንን ሸክም መሸከም ( ገላትያ 625)
የቅዱሳንን  ሸክም መሸከም ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ይህ እንዲገባን ዕብራውያን 131-3 ፣ እና ሮሜ 129-16 ያለውን  ማበቡ የተሸለ ነው፡፡ የታሠሩ ሰዎች ሲኖሩ እናንተም ከእነርሱ ጋር በእሥር ቤት እንዳላችሁ አድርጋችሁ ራሳችሁን ተመልከቱ፡፡ ከጌታ ከኢየሱስ ትምህርትና ከመጀመሪያዋ የኢየሩሳሌም ቤከርስቲያን ተግባራዊ አኗኗር የምንማረው አስደናቂ ነገር ቢኖር አንዱ የከመንፈስ ቅዱስ ሌላውን ሸክም መሸከም ነው፡፡ የሐዋሪያትን ስራ 4ን በምመለከትበት ወቅት በበዓለ ሃምሳ ቀን የተከሰተውን የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ተከትሎ በሕይወታቸወ ከታየው አስደናቂ ነገር አንዱ የእርስ በርስ ሸክም መሸካካም ነበር፡፡ አንድም ደሀ በመካላቸው አንዳይኖር ያላቸውን ሁሉ እያመጡ በሐዋሪያት እግር ሥር ያስቀምጡ ነበር፡፡ ለሁሉም እንሚያስፈልጋቸው ያካፍሉ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የአይሁድ እምነት ወይም የሀይኖት መሪዎች የነበሩ ፈሪሳውያ ደሀዎችን ቤት ፣ የመበለቶችን ቤቶስ ሲበዘብዙ ኣና ሲበሉአቸው ደቀመዛሙርቱና የኢየሩሳኬም ቤተክርስቲያን አማኞች ደግሞ ያቻውን ንብረትን ጥሪት በመሸጥና ወደ ሐዋሪያት በማምጣት ደሀዎችንኛ የተቸገሩትን ይደግፉአቸው ነበር፡፡ ይንን በማደረጋቸው በፈሪሳውያንኛ በመንደፍስ ቅዱስ አማካይነት በሚደረገው እወውነተኛ ርስትና መካካል የሚኖረውን ልዩነት በግልጽ ለማሳየት ችለዋል፡፡ በመከራና በችግር ውስጥ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ገንዘብ አዋጥተው ይሰጡ ነበር፡፡ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ስለ ተረፋቸው ሳይሆን ከድህነታቸው ጥልቀት ሁሉ የኢየሱሰስን ቸር ላጋስነት በተግባራቸው ይገልጡት ነበር፡፡ ይህ ዓይነት ሕይወተወ ለሁላችንም የሚያስፈልግ ነው፡፡፡
ከዕብራውያ ትምህርት እንደምንመለከተው  በክርስቶስ የሆነው ወንድማችን ቢታሠር ያ እሥራት የእኛም ነው ማለት ይኖርባቸዋል፡ የታመመውን ሲያይ ያንን ሕመም አብራችሁ ልትታመሙ ይገባቸዋል፡፡ ይህ የክርስቶስ የመሆናችን መለያ ነው፡፡ የጥንታቤተ ክርስቲያን የምትታወቀው በዚህ ነው፡፡
በወንገጌው ያን አብያተ ክርስቲናት ዘንድ ይህ እነደቀድሞዎቹ ሕዝቦች መሆን እጅግ የተሳነን ጊዜ ቢሆን አሁን ነው፡፡ ዛሬ አንገታቸው እየተቀላባቸው ወገኖች ጉዳይ ፣ የቤተሰባቸው ልቅሶና ሰቆቃ እኛን ለየገነበግብ ይገባናል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በየሰምንቱና በየቀኑ የሚቃጠሉ ቤተ ክርስቲያናት የእኛ ናቸው ፣ እኔ የማመልክባት ቤተ ክርስቲያን ነው የተቃጠለው ማለት ወደምንችልበት የአቅም ደረጃ ከፍ ማለት ይኖርብናል፡፡ ስግብግብነት በጣም አደገኛ እሥራት ነው፡፡ በመካከላችሁ የተቸገሩትን ገልጋዮቻችሁን፣ እህቶቸችሁን ፣ የቤተከርስቲያን አባቶች ፣ የተራቡ በእሥራት ያሉትን በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ ሰዎች አንገታቸው በክርስትና ምክንያት እየተቀላ ነው፡፡ እነዚያን ከብባችን ልናስብ ይገባናል፡፡ ብዙ ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ ነው፡፡ የእኔ ቤተ ክርስትያን እደተቃተለ በማሰብ በእግብሔር ፊት አብረን ልናለቅስ ይገባናለ ይህ ሁሉ የክርስቶስ የመሆናችን ምልክት ስለሆን በዚህ ልንተጋ ይገባናል፡፡
የክርስቶስ የመሆናችን ምልክት. የማነታችንና  የምነታችን መለያ ፡፡