Wednesday, July 18, 2018
እኛ ስንደመር ፍትሕ ይጨምር
ጠቅላይ ሚኒስትራችን ክቡር ዶር አቢይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ በአገራችን እየታየ ያለው ፈጣን ለውጥ የሚያስገርም፣ የሚያስደምምና ለማመን ሁሉ የሚያስቸግር ሆኗል፡፡ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ዲሞክራሲን ፣ ይቅርታንና መደመርን በመስበክ ከአገር አልፎ የጎረቤት አገሮችንም ትኩረት የሳበው መሪያችን በዚህ ፕላኔት ላይ የዚህ ትውልድ የመጀመሪያው ሰው ናቸው ብል እንደሚበዛባቸው አላስብም፡፡ በአሳቤ ከዚህም ያለፈ አድናቆት ልቸራቸው ብከጅልም አድናቆትም ከልኩ ካለፈ አምልኮት ይሆናል ብሎ ልቤ ስለነገረኝ ገታ አደረግኩት እንጂ የምለው ብዙ ነገር ነበረኝ፡፡ ሰውን ማክበር፣ የሚገባውን አድናቆት መስጠትና በጸሎትም መደገፍ በጎ ነው፣ ያማረም የተወደደም ነው፡፡
ወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን 27 ዓመት ሙሉ ሲፈርስና ሲፈራርስ የኖረውን አገር በ3 ወራት ውስጥ መልሶ ለማቆም በሄዱባቸውም መንገዶች ሁሉ ስኬትን በማግኘታቸው ከሠፈር እስከ አገር፣ ከልጅ እስከ አዋቂ፣ሁሉ ከአፉ የማያወርዳቸው፣ በለበሰው ጨርቅም የሳላቸው ሰው መሆናቸውን ሳይ በአንድ በኩል በደስታ እየቧረቅኩ በሌላ በኩል ደግሞ ከሰው የተወለዱ ሥጋ ለባሽ ሰው እንጂ መልአክ አለመሆናቸውን እንዳልረሳ ልቤ ስለወተወተኝ በሁለቱ መካከል ታመምኩ እላችኋለሁ፡፡
እኛ የምናውቀው እስከአሁን ድረስ የነበሩ የቀደሞዎቹ የአገራችን መሪዎች የስላም ኃይል ፖሊስና የጠብ መንጃ አፈሙዝ መሆኑን ያምኑ እንደነበር ነው እንጂ ፍቅር የሚለው ቃል ከመሪ አፍ ወጥቶ ሲሰበክ የሰማነው በዘመነ አቢይ ነው፡፡ እነዚያዎቹ ስለአገሩ እንኳን ሲናገሩ " ለአገሬ እሞታለሁ፣ እንሙትላት" እንጂ እንውደዳት፣ እርስ በርሳችንም እንዋደድ የሚል አሳብ እንደ ኃጢአት ወይም እንደ ሽንፈት ወስደውት ሲመሩን እዚህ ላይ ደርሰናል፡፡ እንዲያው የጠብመንጃ አፈሙዝ እንጂ ፍቅር የሚባል አያውቁም ነበር፡፡ ለአፈሙዛቸውም የሰጡት የቁልምጫ ስም " ፍቱን መድኃኒት" የሚለው ነው፡፡ መቼም ሰው እግዚአብሔር የወሰነለትን ዘመን ሲጨርስ ወደ ዘላለሙ ቤት ይሄዳል፡፡ የአንዳንዶቹ መሄድ ለአገር ጉዳት ሲሆን የአንዳንዶቹ መሄድ ደግሞ ለህዝብ እፎይታና ግልግል የመሆኑ ነገር ልባችን የሚያውቀው ሆኖ የቀድሞው የሕወሓት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሲያስፈራሩ " ፍቱን መድሓኒት ተዘጋጅቷል" ይሉ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ፍቱኑ መድኃኒት ለእርሳቸውም የማይሆንበት ዘመን መጥቶ አየነው፡፡ ቅዱስ ቃሉ " ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንምና" እንዳለው ሆነ ነገሩ፡፡ እግዚአብሔር እድሜአቸውን ያርዝመውና ወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶር አቢይ አህመድ ሕዝብን የሚያቃልሉበትና የሚንቁበት እንደዚያ ያለ ንግግር በአፋቸው የለም፡፡ ንግግራቸውም ሕልማቸውም ከነዚያዎቹ ይለያል፡፡ ይቅርታና ፍቅር ነው ዜማቸው፡፡ ሰውዬ ካህን እንጂ የፖለቲካ መሪም አይመስሉም፡፡ በእውነት!
ሰላም ፣ ፍቅር ፣ ይቅርታ መደመር ፣ አንድነት የሚሉ የዶር አቢይ መርሆዎችና ንግግሮች አንጀቴን ሲያርሱት በመሳጭና ጥዑም አንደበታቸው ብሎም በሚወስዷቸው ፈጣን እርምጃዎች ሁሉ ውስጥ "ፍትሕ" የምትለዋን ቃል ፈልጌ ፣ ፈልጌ እንደምፈልጋት ያህል አለማግኘቴ አየር ላይ የተንሳፈፈው ሞራሌ በመጠኑም ቢሆን ዝቅ ሊል ታገለኝ፡፡ ይህ ስሜት የሚፈጠርባቸው ሌሎችም ይኖሩ እንደሆነ ገና አላወቅሁም፡፡ ዶር አብይ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ ባሰናዱት የቡፌ ግብዣ ፍቅር ፣ ሰላም፣ ይቅርታ፣ መደመር፣ወዘተ የሚሉ በየዓይነቱ በርክተው ቢቀርቡም "ፍትሕ " የምትባለዋ ቃል ከተግባር ጋር ባለመታየቷ በተሟላ ድግስ ውስጥ አንድ ወሳኝ ነገር እንደተረሳ ያህል ተሰምቶኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት እጅ ለእጅ፣ እግርም ለእግር፣ ወይም ዓይን ለዐይን፣ ጥርስም ለጥርስ እንዲከፈል፣ የእሥረኛውን ሁለት እግር የቆረጠ እንደዚያው ይደረግበት፣ ባይሆን አንደኛውም ቢሆን ብቻ ይቆረጥበት ካልሆነም ዕድሜ ልክ እሥራት ይወሰንበት፣ ብልት ያኮላሸም ብልቱ ይኮላሽ፣ የእጅና የእግር ጣቶችን ጥፍር የነቀለም ጥፍሩ ይነቀል ወዘተ የሚል ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ብቀላ Talionic Justice ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በአማሪኛ አቻ ቃሉ ምን እንደሆነ ገና አልደረስኩበትምና ይቅርታ ይደረግልኝ፡፡
ይሁንና በዜጎች ላይ ያንን የመሰለ ዘግናኝ ወንጀል የፈጸሙ ወይም ያስፈጸሙ አካላት ታውቀው የኢትዮጵያን ሕዝብ ግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ያለዚያ የተያዘው መደመር ፍትሕ የጎደለበትን በደልም የደረሰበትን ዜጋ የሚያገልል ይሆናልና፡፡ የአገርንም ሀብት የዘረፈ፣ቢያንስ መስረቁንና አገሪቱ አጥንት እስክቀራት ድረስ የጋጠው የምድሩን ሕዝብ ይቅርታንና ምሕረት መጠየቅ ይኖርበታል፡፡
በቅርቡ በደቡብ ክልል በወላይታ ተወላጆች ላይ የተሰነዘረ ዘርንና ብሔርን ኢላማ ያደረገውን ግዲያና ጭፍጨፋ ያየው ሰብዓዊ ማንነትና የሰው ሕሊና ያለው ሁሉ ተጸይፎታል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ የወላይታ ብሔር ተወላጆች በሜዳ ላይ ተበትነው ይገኛሉ፡፡ ዕድሜአቸው ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ፣የሚያጠቡ እናቶች ፣ነፍሰ ጡራን፣ አዛውንቶችና አረጋውያን ከመኖሪያ ሥፍራቸው ተፈናቅለው መግቢያ ስላጡ በሜዳ ላይ ናቸው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች የመብት ጥያቄ የሚመልስ አካል እስከአሁን አለመገኘቱ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ ወደ ቀድሞው ኑሮአቸው እንደሚመለሱም የተሰጠ ምንም ተስፋ የለም፡፡
መንግሥት ፍቅርን ሲሰብክ ሳለ የወንጌል ሰባኪነት አደራ ከተሰጣቸው የአዳዲስ እምነት እንቅስቃሴ ቤተ እምነቶች አንዳንዶቹ በጭፍጨፋው ጊዜ ነፍሳቸውን ለማዳን ወደ እነርሱ ለሄዱ ወገኖች በራቸው በመጠርቀም ለገዳዮች ጦርና ለአራጆች ካራ አሳልፈው የመስጠታቸውን ዜና መስማት ይበልጡኑ ልብን የጎዳ ክስተት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ መመስገን የሚገባቸውን አመስግነን ብናልፍ የነገራችን ሚዛን ይጠበቃል ብዬ አምናለሁ፡፡ ጭፍጨፋው ሲበረታ ነፍስ የያዛውን ተጠቂዎች እህልና ውሃ ይዘው በማስጠጋት ነፍሳቸውን ያዳኑትን የሐዋሳ አካባቢ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እግዚአብሔር ይባርክ ካላልን በጎ ሥራን አለማሰብ ይሆናል፡፡ በአካባቢ አቸው ያሉ የሲዳማ ተወላጆችን ሰዎች እንዳያጠቁ በጥብቅ የገሰጹ የወላይታ አገር ሽማግሌዎች በእርጅናቸው ይለምልሙ፡፡ ቤታቸውንም ከፍተው በመስጠት የቻሉትን ያህል ደብቀው ያቆዩልን በሐዋሳ ከተማ ያሉ ጥቂት ሰዎች እግዚአብሔር ብድራታቸውን በመልካም ይመልስላቸው ፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሐዋሳ ዙሪያ ከ80 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በሜዳ ላይ ናቸው፡፡ ለዘመናት ጥረው ግረው ያገኙት ንብረትና አለን የሚሏቸው ሁሉ በብሔር ተኮር ጥቃት አራማጆች የተባበረ ክንድ ወድሞባቸው ባዶ እጃቸውን ቀርተዋል፡፡ ተጠቂዎች እምባ እየረጩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ ሌሎች የዘር ማጥፋቱን ዘመቻ የቀሰቀሱትን የመንግሥት ባለሥልጣናትን ባለመሸማቀቅ አጋልጠዋል፡፡ እነዚህ ባለሥልጣናት ተጠያቂነትን እንዲወስዱ በመንግሥት ተወካዮች ፊት አቤቱታ ካሰሙ በኋል ያፈሰሱት እምባ እንደ ከንቱ ተቆጥሮ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሹመት ላይ ሹመት ማግኘታቸው የተጥቂዎችን እና የቤተስቦቻቸውን ልብ ክፉኛ ጎድቶታል፡፡ ሥልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ሕዝብን ያሳረደ ወንጀለኛ ና ፀረ፟ ሕዝብ አጀንዳ አቀንቃኝ ሹመትና ሽልማት ከተሰጠው የፍትሕ ጥማት የሚያቃጥለው ሕዝባችን እስከ አሁን ከተጎዳው በላይ ጉዳት በጉዳት ይጨመርበታል፡፡ ይህንን ያዩ ተጎጂዎቹና ፍትሕ ናፋቂዎች ሁሉ "መደመር" የሚለው አሳብ ቢተናነቃቸው አንፍረድባቸው፡፡ በሐዋሳና በዙሪያዋ ተበታትነው የመከራን እንጀራ እየበሉና የመከራን ውሃ እየጠጡ ያሉ ሚስኪን ኢትዮጵያውያን የዶር አቢይን የመደመር መርህ እንዴት ይቀበሉታል፣ ከማንስ ጋር ይደመራሉ የሚለው ጥያቄ ከእሳት የጋለ ነው፡፡
መንግሥት በደለኛውን ይጠይቅልን እያሉ በእምባ ለጠየቁበት ምላሹ ለገዳያቸው የላቀ ሹመት ሰጥቶ ማሳየት ቁስላቸው ላይ እንጨት መክተት ሆኖባቸዋል፡፡ ለወደፊቱም በዚያ አካባቢ የመኖር ተስፋቸውን ጭምር አጨልሞባቸዋል፡፡ ፍቅርና መደምር የሚለው ቃል የአዋሳ ዙሪያውን ጨምሮ፣ በጌዴኦ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሌ ፣ በአማራና በትግራይ አካባቢ ወዘተ በሕዝብ ደም የሚረኩ ወገኖች በሚቀሰቅሱት የርስ በርስ ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ያለ ፍትሕ ሊገባቸው አይችልም፡፡ ያለ ፍትሕ የፍቅር፣የይቅርታና የመደመር ውበት ለማንም የሚታይበት አግባብ የለም፡፡
ከቡድን አሳልጣኞቹ የተማረውን ዘረኝነትና የጅምላ ጭፍጨፋ ሠርቶና ለፍቶ በሚኖረው ሕዝብ ላይ በመለማመድ ጎዳናውን በዜጎች ደም ያጨቀየ፣ የወገኖቻችንን ሬሳ በእሳት የሚያቃጥሉ አሬመኔያዊ አስተሳሰብ ያላቸውን መልምሎ ያሰማራና ከሰይፉ የተርፉትንም ንብረታቸው እንዲዘረፍና ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ ያደረጋቸው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አገርን ወክሎ አምባሳደር እንዲሆን መሾሙን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ ይህ ሰው የቡድን ካቦ ለመሆን የሚያበቃ የሞራል ብቃት እንኳ የለውም፡፡ የመንግሥትን አሰላለፍ ማበላሸቱ እየታየ በሌሎች እናካክሳለን ካልተባለ በቀር የዜጎችን መብትና ሰብአዊ ማንነታቸውን በማርከሱ ሂስ ሊወስድ እየተገባው ለኢትዮጵያ እንደራሴ እንዲሆን መሾሙ የኢትዮጵያን ክብር ዝቅ ያደርገዋል፡፡ ጎማው የሚደመረው መኪናው በወጉ እንዲሽከረከር ስለሆነ የተበላሸው ጎማ በመኪናው ከመደመሩ በፊት ተገቢው ፍተሻና ጥገና ያልተደረገ እንደሆነ በመኪናው መላ ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ የመኪናውን ጤና ከሚነሳ ፣ አንዴ ተበላሽቷልና የሚመጥነው ሥራ ሊሰጠው ይገባዋል እንጂ ክብ ቅርጽ ስላለው ብቻ ጎማ ነው ተብሎ በመኪና እንደማይደመር የእኔ ምክር የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ እውነት ለመናገር ይህንን አስጽያፊ ድርጊት የፈጸመው የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ አምባሳደርነት ይቅርብና እርሱ በደም የተበከለው እጁን ቢታጠብ፣ በዘረኝነት ሰክሮ በሕዝብ ላይ የሚያፈጥበትን ዓይኑን ቢሰበስብ፣ የጎረሰውን ሕወሃታዊ መርዝ ቢተፋና ቢጸዳ ትልቅ ሥራ እንደሠራ ልንቆጥር እንችላለን፡፡ እንደ ሽፈራው ሽጉጤ ያሉት ዶር አቢይ የሚያራምዱትን በሳል ዴሞክራሲያዊና ሕዝብን ያሳታፈ ፖለቲካ ስለማይመጥኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ራሳቸው ሰውዬን ከላይ አማስለውም ይሁን ከሥር አንድደው ወደ ብስለት ያምጡት እንጂ ሹመት አይስጧቸው፡፡ ያለዚያ እንደ አቶ ሽፈራው ያሉ ሰዎች ጠቅላይ ሚንስትራችንንም ሆነ እኛን ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አንገት ያስደፉናል፡፡
የእነሽፈራው ሽጉጤ ድርጊት የጠቅላይ ሚኒስትራችንን ሕዝባዊና ኢትዮጵያ፟ መር አመራርን እንዲያጠላሸው አንሻም፡፡ ሌቦችና ዘራፊዎች ፣ ነፍሰ ገዳዮችና ጨፍጫፊዎች በሕግ የሚጠየቁበት አግባብ ችላ ከተባለ ህገ፟ወጥነትና ፍትሕ አልባነት ማንሰራራቱ አይቀርም፡፡ መደመር ፣ ፍቅር፣ ሰላም ፣አንድነትና ይቅርታ በሚለው መርህ ውስጥ " ፍትሕ በተግባር" የሚለው እንዲካተትበትና እንዲያነቡትም አቶ ሽፈራውና ግብረ አባሮቹ ተጽፎእ ቢሰጣቸው እኛ ፍትሕ የተጠማን ሁላችንም አቢይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እየዋለ ካለው ውለታ ጋር እንደምረዋለን፡፡ እኛ ስንደመር ፍትሕ ይጨምር እንጂ አይረሳ፡፡
በመጨረሻም ፍትሕን የተጠማና ሰባዊነት ያለው ሁሉ ሰለተጎዱ ወኞቻችን ደምፁን እንዲያሰማ አቤት እንላለን፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሐዋሳ ከተማ ዘጠኝ እናቶች በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ልጅ ወልደው ከነሕጻናቶቻቸው ጋር እዚያው ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ከመቶ የሚበልጡ እናቶችና ሕጻናት በአንድ ክፍል በጅምላ ታፍነው ይኖራሉ፡፡ ዘመድና ቤተሰብ የሞተባቸው ሰዎች ከወላይታ መጥተው የወገኖቻቸው ሬሳ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ በጅብ ተበልቷል የሚል ምላሽ ተሰጥቶአቸው መመለሳቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ አሁን ደግሞ ተፈናቃዮቹ በአስቸኳይ አካባቢውን ለቅቀው እንዲሄዱ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑ ያንን አካባቢ የጥፋት መንደር አድርጎታል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይና የእኤርትራው ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሐዋሳን ሲጎበኙና ሕዝቡም በደስታ ሲሰክር እነዚህ ተፈናቃዮች ፍትሕ ርቆአቸው በሰቆቃ ውስጥ ነበሩ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እውነታው እንዳይታወቅ ምንም ዓይነት የመገናኛ ብዙኃን ግብቶ ሁኔታውን እንዳይዘግብ መንገዶች የተዘጉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩ የብዙዎችን ልብ የሰበረና የብዙዎችን ድምፅ የሚፈልግ ስለሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለእነዚህ ድምፅ አልባ ሰዎች ድምፅ እንዲሆኑላቸው ና ከዚህ የመከራ ሕይወት የሚወጡበት መንገድ እንዲገኝ በያላችሁበት ችጩኼታችሁን እንዲታሰሙ እንማጸናለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ ጠቅላይ ሚኒስትራችንንም ከቀን ጅቦቹ ቀስት ይጠብቅልን፡፡ አሜን
ሳሙኤል ሾንጋ ነኝ
Tuesday, July 3, 2018
ሕልም የሚመስሉ እውነቶች
በዓለም ካሉ ጎጂ ፍልስፍናዎች አንዱ በእግዚአብሔር መኖር የማያምን / ኤቲይዝም/ የሚባለው ነው። የዚህ ፍልስፍና አራማጆች በእግዚአብሔር መኖር ባለማመናቸው ሳይገቱ ሌሎችም ፈለጋቸውን እንዲከተሉ ከብረት ጠንክረው መሟገታቸው የፍልስፍናውን ጎጂነት ይበልጥ ያጎላዋል። እንደ እነርሱ ትጋት ቢሆን የአዳም ዘር ሁሉ ፊቱን ከፈጣሪው መልሶ ተስፋ ቢስ ሆኖ በቀረ ነበር። ገና ጨቅላ ወጣት በነበርኩበት ወቅት የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና መዝሙር መዘመር ከልቤ ስወድ ሳለ “እግዚአብሔር የለም” የሚለውን መርዘኛ የክህደት መለከት ሲነፉ የነበሩ ወገኖች እንዴት እንዳስጨነቁን ከቶም አይረሳም። በወቅቱ የኮሚዩኒዝም ፖለቲካ ሥርዓት በየቀበሌው ያለን ለጋ ወጣቶች “ከሁሉ በላይ አብዮቱ” የሚለውን መፈክር እንዲናስተጋባ ያስገድደን ነበር። ጉዳዩ “ከሁሉ በላይ አብዮቱ” በሚለው ሳያበቃ “ከአብዮታችንና ከአንድነታችን በላይ ምንም ኃይል የለም” የሚለው ደግሞ እጅግ የከፋው ነበር። እኔና ሌሎች ጓደኞቼ በዚህኛው መፈክርና አብሮት ተያይዞ በመጡ ጣጣዎች ምክንያት መጐዳት ብቻ ሳይሆን አሳራችንን ቆጥረናል ብል እንኳ ያለፍንበትን ጨለማና አስከፊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ አይገልጸውም። ወደ ጌታ ከተሰበሰቡት ወንድም እህቶቻችን እና አባቶቻችን በቀር በጊዜው የነበራችሁ ወንድሞቼ ጋሽ ወልዴ መኩሪያ፣ ቡታቆ ቡናሮ፣ ያዕቆብ ቦጃጐ፣ በለጠ በላቸው፣ ሳሙኤል ታንጋ፣ ሚልክያስ ወኖ ፣ አቦታ አንዳቦ፣ ባልቻ ባራታ፣ እህቶቼ አዲስ ወጋሶ፣ ንግሥት ጋሞ፣ አልማዝ ዳና ፣ አባቶቼ ጋሼ ወጋሶ ሄሊሶ፣ ወጋሶ ሻማና፣ እንድሪያስ ታንቱ እና ሌሎችም ያ የጨለማ ዘመን ያልፋል ብላችሁ አስባችሁ ነበር? በፍጹም እንዳላሰባችሁና ሥርዓቱ ሲወድቅ ወንጌል በአደባባይ ሲሰበክ ሲታዩ ሕልም እንደመሰላችሁ እርግጠኛ ነኝ። እኔ በበኩሌ ከዚያው ዘመን ጋራ ሳነጻጽረው አሁን የሚታየው ሁሉ ሕልም እስክመስለኝ ድረስ እገረማለሁ። በሁላችሁም ላይ ጠባሳው አለና ይህች ጽሑፍ ለእናንተ ማስታውሻነት ትሁን። ። በተለይም በኦፋ ወረዳ በኦኮቶ ሴሬ ቀበሌ ያሳለፍንባቸውን የጭንቅ ዓመታት ከቶውንም እንደማትረሱ ዛሬ ላይ ቆማችሁ ለእግዚአብሔር የልባችሁን ምሥጋና እንደምታቀርቡ አልጠራጠርም። የዘመኑ ሁኔታ ጠባሳ ሳይጥልበት ያለፈ አማኝ ማን ነውና! በተለይም ለመስከረም 2 የአብዮት በዓል ኪነት እንዲጨፈር ጴንጤዎች ድምጻቸው ጥሩ ነው ተብሎ በኦኮቶ ሴሬ ቀበሌ ሲያከማቹን አንጨፍርም ማለታችን ምን እንዳስከተለብን ወደ ጌታ ከተሰበሰቡት ወንድማችን አማኑኤል ጐአ፣ እህታችን ኤልሳበጥ ጐአ፣ ወንደማችን መስዋዕት ማሞ በቀር ሌሎች በሕይወት ያለነው ሁላችን በደንብ እናስታውሰዋለን። እኔ በበኩሌ በአሁኑ ጊዜ መዘምራኖቻችን መድረክ ላይ የሚያደርጉት ውዝዋዜ ከደርግ ጊዜው የኪነት ጭፈራ ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ በመሆኑ አብሬአቸው ለማምለክ እስክቸገር ድረስ ጠባሳ ጥሎብኝ አልፏል። ቃላት የማይገልጹት የጨለማ ዘመን! እናንተ ያ ዘመን አለፈ ሲባል ስትሰሙና በዓይናችሁም ሲታዩ ሕልም የምታዩ አልመሰላችሁም? ያን ጊዜ የመሠረተ ትምህርት ዘማች ሆናችሁ ወደ ኦኮቶ ሴሬ ቀበሌ የተመደባችሁና እኛን ክርስቲያን ወጣቶችን በድብቅ የእግዚአብሔርን ቃል በማስጠናትና በስደቱም ምክንያት እንዳንፈራና እንዳንንሸራተት ያበረታታችሁን ታላላቆቻችን በአዲስ አባባ ኮምፓሺን ቢሮ ያለኸው ወንድም ኢሳይያስ ኦምቦሌና በወላይታ የምትገኘው ወንድም ያሲን ሾንዴ የተባረካችሁ ሁኑ።
በቀበሌአችን እሥር ቤት እያለሁ አንድ በቤተክርስቲያን ያገለግል የነበረ ግን ጌታን መከተሉን ትቶ ከካድሬዎች ጋር የተቀላቀለ መቶ አለቃ የሆነ ሰው የጠየቀኝ ጥያቄ አይረሳኝም። ያለኝ እንዲህ ነበር ፡ “እንደዚህ እየሆንክ ኖረህ በኋላ እግዚአብሔርን ባታገኘው ምን ትሆናለህ?”። ይህ ጥያቄ በጊዜው ከእኔ አቅም በላይ ሆኖ መልስ ለመስጠት ቢያስቸግረኝም ከሰነፍ ልብ የመነጨ ፣ ከሰነፍም አፍ የፈለቀ መሆኑን የተረዳሁት በአስተሳሰብም በአካልም ጎላ ካልኩ በኋላ ነው። ያነ ገና ምርቁን ከፍትፍቱ ወደምለይበት የአስተሳሰብ ደረጃ ስላልደረስኩ ነገሮቹን መገናዝብም ሆነ ጥያቄዎቹን እንደአመጣጣቸው መመለስ ሳልችል ቀረሁ። ፈተናዬ እዛጋ ሳያበቃ ሌሎች ጥያቄዎችንም ተጠይቄአለሁ። በተለይም ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ከተዘጋች በኋላ እኔና ጥቂት የአካባቢ ወጣቶች አሁንም በአቋማችን የጸናን መሆናችንን ያዩ አንዳንዶች “ አሁን ሁሉም ነገር የለም ታዲያ እምነታችሁ ምን ይጠቅማችኋል ? ብለውናል። በውስጣችን የነበረው የጌታ ፍቅር ከእርሱ ጋር አጣብቆን እንጂ የተጋፈጥናቸው ፈታኝ ጥያቄዎች ከአቅማችን በላይ በመሆናቸው ለመመለስ አቅቶን ከሕይወት መንገድ ተንሸራትተን በወደቅን ነበር። ሰውን ሁሉ የሚረዳ እግዚአብሔር እኛንም ረድቶንና ደግፎን አለፍናቸው እንጂ ጊዜያቶቹ ቀላል የሚባሉ አልነበሩም። በጊዜው በወላይታ አውራጃ በኦፋ ወረዳ ያ ሁሉ እንግልት ለደረሰባቸው አሁን በህይወት ላሉም ሆነ ወደ ጌታ ለተሰበሰቡም ሁሉ ከልቤ የሆነ አድናቆት አለኝ።
በአሁኑ ጊዜ በአገራችን አማኞች እምነታቸውን እንዲተው የሚያነቃ ካልሆነም የፍጥኝ አስሮ የሚገርፍ ወግና ሥርዓት የለም። ፈጣሪን ክዶ በራሱ ማንነት የተጠቀጠቀ፣ ለሰሚው የማይገባ እንግዳ ቋንቋ ለዜጋው ያስተማረ፣ ሰይፍ ይዞ ቤተ እምነቶችን ያሳደደ፣ አማኒያንንም በባትሪ እየፈለገ ካሉበት ጎትቶ እያወጣ በአደባባይ ያሸማቀቀ እንደ ኮሚዩኒዝም ያለ ጉደኛ ሥርዓት አንድ ቀን መታሰቢያው ተረስቶ ፣ ድብዛውም ይጠፋል ብለን አስበን አናውቅም። በተቃራኒው ለምድሪቱ በረከት የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ መሪ መታየቱ አቤቱ እግዚአብሔር “ሆላ ላንተ” አሰኝቶናል። ጊዜያቱን ለማንጻጸር ዕድል ያገኘ፣ ዕድሜም የተቸረው ሁሉ የምለው ይገባዋል። በ1972-79 ባሉት ጊዜያቶች አንድን ክርስቲያን መንገድ ላይ አቁሞ ለማዋከብ ባለሥልጣን መሆን ሳያስፈልግ ማንም ተራ ሰው እንደፈለገው ሊስፈራራው የሚችልበት፣ ደስ ካሰኘው የሚደበድብበት ሁኔታዎች ነበሩ። ጴንጤ በሰፈራችሁ ካለ አውግዙ እያለ ጓደኛን ከጓደኛ፣ ወላጅን ከልጅ የሚያለያይ የአቴና ወጊ፣ የደብተራ፣ የጥላወጊና የአስማተኛ ቅልቅል እምነት የሚወረውርብን ቀስት አንዴም ኢላማውን ስስት አንዴም በመንገድ ላይ ሲክሽፍ ኖረን አሁን ወንጌል በአደባባይ ሲሰበክ ለማየት በቃን።
መስከረም 28 ቀን 1978 ዓ.ም በጌታ ታላቄ ከሆነው ወልዴ መኩሪያ ከተባለ ወንድሜ ጋር ተይዘን ወላይታ ሶዶ ፖሊስ ጣቢያ ታሥረን ሳለ የአሥር አለቃ አማን የተባለ የጣቢያው ፖሊስ ያደረገብኝን አስታውሳለሁ። ይህን ይህል ዘመን ቆይተን ጉዳዩን አሁንም የማስታውሰው በአሥር አለቃው ላይ ቂም ቢጤ ቋጥሬበት ሳይሆን የሁኔታዎች አስከፊነት የማይረሳ ስለነበረ፣ የጨለማው ብርታት ከአእምሮ ሊፍቁ ከሚችሉት በላይ እንዲያውም ከሁለት ቀን በፊት እንደተደረገ ያህል ስለሚሰማኝ ብቻ ነው። በትክለ ቁመናው ሞላ ያለና መካከለኛ ቁመት ያለው የአሥር አለቃ አማን በጐርናና ድምጹ ጧት ጧት በስሜ እየጠራ ወደ ውጪ ያወጣኛል፣ ሁለት እጆቼን ወደ ኋላ አድርጌ ጐንበስ ብዬ እጆቼን ከሁለት እግሮቼ መካከል ወደፊት ካሾለክኩ በኋላ ዝቅ ብዬ በሁለት እጆቼ ሁለቱን ጆሮዎቼን ይዤ በዚያው ሁኔታ ጆሮቼን ሳልለቅ የፖሊስ ጣቢያውን ግቢ እንዲዞር ያደርግኝ ነበር። ሲያሰኘው ደግሞ ያለ ምንም ምክንያት በያዘው አጭር በትር በመቀመጫዬ በኩል ያላሽቀኝ ነበር። ደስ ሲለው ደግሞ ለ3 እና ለ 4 ሰዓታት ቁጥጥ ብዬ እንዲቀመጥ ያዘኝ ነበር። ቁጥጥ ማለቱ ለመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ምንም ባይሉ ደቂቃዎች በጨመሩ ቁጥር ወገብ፣ ጉልበት ፣ የውስጥ እግር፣ ባትና ታፋ የተቆራረጠ ያህል ይታመም ይጀምራል። ቅጣቱ ሲያልቅ ቆሞ መሄድ ሌላ ፈተና ነው። ይህ ከተያዝንበት ቀን ጀምሮ በየዕለቱ ከቁርስ በፊት ለሁለት ሰዓታት ያህል ከሌሎች ስፖርት ዓይነቶች ጋር የሚሰጠኝ ቅጣት ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ጓደኛዬ ወልዴ ውስጥ ሆኖ ይቃትት ነበር። ወንጀል ሆኖ ለዚህ ሁሉ ቅጣት የዳረገን “ የመካከለኛው ዘመን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” የሚል በኤስ አይ ኤም የታተመ መጽሐፍ እኔና ወንደሜ ወልዴ በእጃችን ይዘን መገኘታችን ብቻ ነው።
ዛሬ ግን በቤተክርስቲያን ላይ እንደዚያ ዓይነት ሁሉን የሚያሸማቅቅ ስደት የለም። እምነትንም የሚቃወም የለም። ሁሉም ነገር ተቀይሮ ወንጌል በየቦታው ይሰበካል፣ መዝሙራችን በሕዝብ መመላለሻ ተሽከርካሪዎች ውስጥ ሁሉ ሳይቀር እየተከፈቱ ናቸው። የሚያሳዝን ቢሆንም ጫት ቃሚዎችም ጭምር ከዘፈን ይልቅ የመዝሙር ካሴቶቻችንን እየተከፈቱ ነው። ማን ያውቃል እነርሱ ለምርቃና ብለው ቢያደርጉትም ጌታ የወንጌል ድምጹን በዚያ በኩል እያስተላለፈላቸው ይሆናል ብለን እናምናለን። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ልንገምተው በማንችለው ፍጥነት ስለቀየረው በክርስትና ምክንያት መሸማቀቅ የለም፣ አይታሰብምም። እግዚአብሔር የት አለ? አሳየኝ እያለ የሚያፈጥ ካድሬ፣ የትምህርት ቤት መምህርም አይታይም። በመንገድ ማዕዘን ላይ ቆሞ ንብረት እየቀማና አጓጉል የአካል ክፍሎቻችንን ሲመታ ታይቶ ጴንጤዎችን አዋረደ ተብሎ የሚጨበጨብለት፣ በድርጊቱም አንጀቱ ምርስለት ያበጠ ጐረምሳም የለም። ሕልም የሚመስል ግን በዓይን የሚታይ እግዚአብሔር የሠራው ታሪክ ይሏል ይህ ነው ።
ከብዙ ዓመታት ቆይታ በኋላ ቤተሰቦቼን ለመጐብኘት ወደ ወላይታ ሄጄ ባየሁትና ለማመን በሚያስቸግር ነገር ምክንያት ወደ ማረፊያ ቦታዬ ገብቼ በሩን ከኋላዬ ዘግቼ በአምላኬ ፊት ተንበርክኬ ለእርሱ ያለኝን ምሥጋና በእምባ አቀርብኩ። ምክንያቱም ያቺ የአሥር አለቃ አማን ሲያሰቃየኝ የነበረበት ፖሊስ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ ፈርሳ በቦታዋ ትልቅ የገበያ አዳራሽ ተሠርቶ፣ በላይኛው ፎቅ ላይ ባለው የካፊቴሪያ በረንዳ ተቀምጥው ሻይ እየጠጡ ስለ መንፈሳዊ ነገር የሚመካከሩ ሰዎችን ሳይ ስሜቴን መቆጣጠር ስላቃተኝ ነው። በእውነት ሕልም የማይ መሰለኝ እንጂ እውነት አልመሰለኝም ነበር። የእናት አባቶቻችን እንባ መክኖ ሳይቀር ዘመን ቆጥሮ እግዚአብሔር በምድራችን ስለመንገሡ ያነ የነበርን ሁላችንም አሁን አውራ ምስክሮች ነን።

እግዚአብሔር ዛሬም ሕልም የሚመስሉ እውነተኛ ታሪኮችን እየሠራ በዙፋኑ ላይ ነው። በክርስትና ሕይወታችንም ሆነ በአገራችን በኢትዮጵያ የሚሆነውን ስናይ ሕልም የማየት ያህል ነው። ክቡር የሰው ልጅ ደሙ በከንቱ ሲፈስ የነበረው ታሪክ በቅጽበት ተቀይሮ የአገራችን ዜጐች የሰላም አየር መተንፈስ ፣ የሰላምን ወሬ ማውራትና መስማት መቻል፣ ያውም የአምባገነኖች አምባገነን መሪዎች ሥልጣን ተቆናጥጠው ሕዝብን እርስ በርሱ በሚያጫርሱበትና በሕዝብ ደም እንጀራቸውን በሚጋግሩበት አገር አሁን የሚታየውን የሰላምና የእኩልነት ጅማሬ ማን አስቦ ነበር? እንዲያው እውነት ነው ሕልም? ብቻውን ተአምር የሚሠራው እግዚአብሔር ብቻውን ክብር ይገባዋል።
ዲያብሎሱ ይሁዳና ሰይጣኑ ጴጥሮስ ( ሁለቱ የጌታ ደቀመዝሙሮች)
የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ መንፈሳዊ ሕይወትን ያሳድጋል፣ የሚያስገኛቸውም ቁም ነገሮች ከቁጥር ያለፉ ናቸው። የዚያኑ ያክል ደግሞ ለመተርጐም የሚያስቸግሩ የምንባብ ክፍሎችና አረፍተ ነገሮችም አሉ። አስደንጋጭና ግራ መጋባት ውስጥ የሚከቱን መኖራቸውም ግልጽ ነው። ለምሳሌ ጌታ ሲናገር፦ “ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” ያለው አሳብ አስደንጋጭ ነው። ጥያቄ ከሚፈጥሩብን መካከል “አስቆሮንቱ ይሁዳ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነው እንዴት ነው?’ ኢየሱስ ደቀመዝሙሮችን ሲመርጣቸው ዲያብሎስ የሆነውን ይሁዳን ለምን አካተተው? (ዮሐ 6:70)። ለሚለው መልስ መፈለግ በራሱ ከባድ የቤት ሥራ ነው። ከደቀ መዝሙሮች መካከል “ዲያብሎስ” መሆኑ የተነገረለት ይሁዳ ነበር። አገልጋይ የሆነው በኢየሱስ ምርጫ ነው። ጌታም ማንነቱን እያወቀ መርጦታል ግን ለምን? ለመመለስ ያስቸግራል።
ይሁዳ ራሱ ወደ ኢየሱስ የቀረበ ለማስመስል ብዙ ተፍ ተፍ ይበል እንጂ የተለወጠ አገልጋይ አልነበረም። ከሌሎች ጋር ሐዋሪያ ተብሎ የወንጌል ምስክርነት ሲሰጥ ለካ እርሱ “ዲያብሎስ” ነበር። ጌታ ተአምራትን ሲያደርግ፣ በሁለት ዓሣና በአምስት እንጀራ በሺዎች የሚቆጠሩትን አጥግቦ አሥራ ሁለት መሶብ ሲስያተርፍ፣ ደቀመዛሙርትም ሰዎችን በሜዳው ላይ ባለው ሣር በሃምሳ ሃምሳ እያደረጉ አስቀምጠው ሲያገልግሉ አስቆሮቱ ይሁዳ አብሮአቸው ያገለግል ነበር። ይሁን እንጂ ሰውየው “ዲያብሎስ” ነበር። ዲያብሎስ መሆኑን ከኢየሱስና ከራሱ ከይሁዳ በቀር የሚያውቅ አልነበረም። እነዮሐንስ ያዕቆብና ጴጥሮስ ወዘተ ሌሎች ሐዋሪያት ይሁዳን በሐዋሪያነቱ እንጂ በዲያብሎስነቱ አላወቁትም። አብሮአቸው ብዙ ተጉዞአል፣ አገልግሏል፣ ምናልባትም አብሮአቸው ጸልዮም ይሆናል። እርሱ ግን ውጭው ሐዋሪያው ይሁዳ ውስጡ ግን አደገኛው ዲያብሎስ ሆኖ ኖሯል። እንደ ደቀመዛሙርት ቢያገለግልም ልቡን የገዛው ከጌታ ፍቅር ይልቅ የገንዘብ መጎምጀት ነው። ከኢየሱስ ይልቅ ገንዘብን አብልጦ በመውደዱ ለዲያብሎስ ቀኝ እጁ፣ የዓይኑም ብለን ሆኖ አገልግሏል። ኢየሱስን ለመሸጥ፣ ለጠላቶቹም አሳልፎ ለመስጠት ዋጋውን ሲተምን ሰንብቷል። ግን የሚባለው የኢየሱስ ደቀመዝሙር ነው። የተመረጠ ሐዋሪያ ነው። ፈረንጆች የመጽሐፉን ሽፋን አይተህ አትፍረድ የሚሉት ለዚህ አይደል?
ይህ አሳብ ሰው ስለ ደህንነቱ ቆም ብሎ እንዲያስብ የሚያደርግ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጅምላ ከማህበረ ምዕመናን ጋር የተቀላቀሉ ያልዳኑ ሰዎች ዛሬም ሊኖሩ እንደሚችሉ መጠርጠር ይኖርብናል ወይ ቢባል “በሚገባ እንጂ” የሚል ነው መልሱ። ያልዳነ ሐዋሪያ፣ ያልዳነ ወንጌላዊ፣ ያልዳነ ነቢይ ወይም መጋቢ ይኖራል ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል? የሚሉ ብዙ ናቸው። ሰዎች የሚከራከሩት ስለ አገልጋይነት ጉዳይ ነው። አገልጋይ መሆን ለደህንነታችን ዋስትና አይሰጥም፣ ሊሰጥም አይችልም። አስተማሪ፣ ዘማሪ ፣ መስካሪ መሆን ዳግም መወለዳችንን አያረጋግጥም። ይህ አስደንጋጭና አስደማሚ ነው። ያለጥርጥር ለመቀበል የሚከብድ ነው። ግን ደግሞ የማይታበል ሐቅ የማይጠረጠር እውነታ ነው።
የይሁዳ ገርሞን ሳንጨርስ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ሰይጣን” ማለቱ አያስደነግጥም? ጴጥሮስ በሐዋሪያት መካክል ዋናና አእማድ ተባለው ነበር። ሁሉን ትቶ ኢየሱስን የተከተለ ቆራጥና ተወዳጅ ሐዋሪያ! ለጌታ የሚቀናና ስለጌታ ሲል ራሱን ለሞት ለመስጠት የወሰነ ሐዋሪያ! ታዲያ አንድ ቀን ጌታ “ሰይጣን” ብሎ አረፈው። ታዲያ ማን ነው ሰው? ማነው አገልጋይ?
ይሁዳና ጴጥሮስ ሁለቱ የማይመሳሰል ማንነት አላቸው ። ይሁዳ ምኞቱና የልቡ ጩኼት ኢየሱስን ሽጦ ገንዘብ መቀበል ነበር። ጌታ እስክገልጠው ድረስ የዲያብሎስን አጀንዳ ለማስፈጸም የኖረ ነው። እንክርዳዱ ከስንዴው፣ እሾክም ከወይን ጋራ በአንድ ማሳ እንደሚኖሩ ከእውነተኞቹ ሐዋሪያት ጋር አብሮአቸው ኖሯል። ጴጥሮስ ሰይጣን የተባለበት ምክንያት ለኢየሱስ ያለውን ፍቅር በቃላት ለመግለጽ በሞከረበት ወቅት የተከሰተ ጉዳይ ነው። “ እርሱ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን ፣ ወድ ኋላዬ ሂድ ፣ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል አለው(ማቴ 16:23)። ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች እንዲሁም ከጸሐፍት ብዙ መከራ እንደሚደርስበት፣ እንደሚገድልና እንዲሁም በሦስተኛ ቀን እንደሚነሳ ይገልጥ ዘንድ ሲጅምር ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ አይሁንብህ ፣ ይህ አይድረስብህ ብሎ ኢየሱስን ገሰጸው። ይህንን ያለው ኢየሱስን ከማፍቀሩ የተነሳ ነበር። ቅንነቱንና ለጌታ ያለውን ፍቅር የገለጠበት መንገድ ይህ ቢሆንም አሳቡ ለካ ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ጋር ይጣረስ ኖሯል። ብዙዎቻችን እንደምናምነው ሰይጣን የጴጥሮስን ቅናአትና ለጌታም ያለው የሚቀጣጠል ፍቅር ለራሱ ዓላማ ተጠቅሞ በኢየሱስ በኩል ዓለምን ሁሉ ለማዳን የተዘረጋውን የእግዚአብሔርን ዕቅድ ለማሰናከል በጴጥሮስ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ሞከረ። ጌታ የገሰጸው ያንን የሰይጣንን ዓላማ ነው። እውነተኞችም አገልጋዮች ጸጋቸውንና መንፈሳዊ ቅንአታቸውን በእውቀትና በብስለት እንዲሆም በጥበብና በማስተዋል ካላላደረጉት መንፈሳዊ በሚመስሉ ሁኔታዎች በኩል ሰይጣን ጫና ሊፈጥርባቸው እንደሚችል ከዚህ እንማራለን።
ይሁዳ ዲያብሎስ የገባበት፣ የሰለጠነበት ልቡንም ለመንግሥቱ ያስወረሰ የዲያብሎስ መኖሪያ ለመሆን ራሱን የሰጠ possessed ሲሆን (ሉቃስ 22:3፣ዮሓ 13:27) ጴጥሮስ ግን ሰይጣን ተጽዕኖ ሊያሳድር ሙከራ ደረገበት Influenced አገልጋይ ነበረ። አማኞች ከሁለቱም የሰይጣን ተንኮሎች ራሳችንን መጠብቅ ይኖርብናል። እንደ ይሁዳ በአገልጋይነት፣ በነቢይነት፣ በሐዋሪያነት፣ በመጋቢነት፣ በወንጌላዊነት ወዘተ ስም ሕዝብን እያተራመሱ የእግዚአብሄርን ክቡር ዓላማ የሚያበላሹ ራሳቸውን ስለሚያውቁ ፈጥነው መመለስ ካልቻሉ የሰበሰቡትን ሳይበሉ ገመድ ያንቃቸዋል። እንደ ጴጥሮስም በመንፈሳዊ ቋንቋ የተለወሰውን የሰይጣንን ምክር እየሰሙ ከጠራቸው ጌታ ጋር የሚጣሉ ወደ ቃሉ መመለስ ያስፈልጋቸዋል። መልካም የሚመስሉን ልምምዶችና በውስጣችን የሚሰሙን ስሜቶች ሁሉ በሕያው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ከልታሹና ካልተገሩ አደገኛነታቸው ከፍ ያለ መሆኑን ልብ ይሏል። ይሁዳ በመታነቅ ሕይወቱ ተደመደመች፣ እርሱም ወደ መረጣት የገዛ ራሱ ሥፍራ ሄደ(ሐዋ 1:25)። ጌታ ግን ጴጥሮስን በመገሰጽ ሕይወቱን አዳነው። መንፈስ ቅዱስም ሲሞላው ስለ ጌታው ትንሣኤ በድፍረት በመስበክ በሺዎች የሚቆጠሩትን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ማረከ። ሰለ ኢየሱስ ሲል እጁን ለሰንሰለት ሰጠ። ከብዙ ተግባራትም መካከል ዘመን ተሻጋሪ ቃል ከጌታ ተቀብሎ ሁለት መጸህፍትን ጽፎ በአዲስ ኪዳን ቀኖና ውስጥ ከተተው። ባለማወቅ ያደረገው ሳይታሰብ የጌታን ማዳን ሰብኮና ጽፎ መለኮታዊ ሰነድ ትቶልን ሄደ። ፍጻሜአችን እንደ ይሁዳ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በመልካም ይሁንልን። አምንእ!

Subscribe to:
Posts (Atom)