Thursday, June 11, 2015

የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ወይስ የሙሉ ልብ አገልጋዮች?

      

በቤተክርስቲያን ለምናገልግል አገልጋዮች "የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች" የሚል ስያሜ ወይም ማዕረግ ይሰጠናል፡፡ ወንጌላውያን መጋቢያንና አስተማሪዎች ብሎ ባለን ጸጋና በተሰማራንበት የአገልግሎት ሥፍራ መሠረት መጥራት በቂ አይደለምን እየልኩ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ እኔም በቤተክርስቲያን ሳገለግል ከሌሎች ጋር በአንድ ላይ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እየተባልን ስንጠራ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ይህ አበባል አገልጋዮቹ የትኞቻችንም ቢንሆን ሙሉ ጊዜአችንን ለጌታ አገልግሎት የሰጠን መሆናችንን የሚያመለክት አባባል ነው፡፡ ወንጌላዊም ሆነ መጋቢ ሌላውን ትተው ለጌታ ስራ ሙሉ በሙሉ ጊዜኣቸውን ስለሰው የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ብለን ብንላቸው ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ይሁን እንጂ የአገልጋዮችን አገልግሎት ከጊዜ ጋር ካያያዝነው በአገልጋዮችና በሰራተኞች መካከል ልዩነት መኖር አለመኖሩን መመልከት ይኖርብናል፡፡ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞች የምንላቸው አሉ፡፡ እነዚህ በተሰማሩባቸው የሥራ መስኮች በቀን 8 ሰዓት በሥራ የሚያጠፉ ሲሆኑ ከዚያ በታች የሚሠሩ ከሆነ ደግሞ የግማሽ ጊዜ ሠራተኞች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ሙሉ ጊዜ ወይም የግማሽ ጊዜ ሠራተኝነታቸው የሚወሰነው ሠራተኞቹ በሥራ ላይ የሚያሳልፉት የሰዓት መጠን ነው፡፡የሚያገኙት የገንዘብ መጠንም በዚያው መጠን የተለያየ ይሆናል፡፡ በቀን 5 ሰዓት የሠራ ሠራተኛ የሚያገኘው ደመወዝ በቀን 8 ሰዓት የሚሠራው ሠራተኛ ከሚያገኘው እጅግ ያነሰ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ሠራተኞቹ በሥራ ቦታቸው የሚያስመዘገቡትም ውጤት የዚያውኑ ያህል ልዩነት አለው፡፡
ወደ አገልጋዮች ሁኔታ በምንመለስበት ወቅት የእኛን ሁኔታ ከሠራተኞች ሁኔታ ለይቶ መመልከት ይቻላል፡፡ የአገልጋዮች የአገልግሎት ሁኔታ በሰዓት የሚወሰን ሳይሆን ከጌታ ዘንድ በተቀበልነው ጥሪና በውስጣችን ባለው፣ በእኛም በሚገለጠው ጸጋ መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ ወንጌላዊን ወንጌላዊ የሚያሰኘው እርሱ በቤተ ክርሰቲያን ያሳለፈው ሰዓት መብዛት ወይም ማነስ ሳይሆን ጥሪውንና ጸጋውን የገለጠበት መንገድና ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ ነው የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ከምንባል ወንጌላውያን ፣ መጋቢያን፣ ወይም መምህራን ብንባል ይሻላል ያልኩት፡፡
አገልጋዮች ራሳቸን ስለ ራሳችን ስንናገር የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ነን ስንል እንደመጣለን፡፡ እኛ ካልነው ደግሞ በግልጽ መታየት ያለበት ነገር አለ፡፡ አገልግሎትም ቢሆን ከጊዜ ጋር የሚሄድ እንጂ ከተሰጠን ጊዜ ውጭ የሚሰራ ነገር አይደለም፡፡ ጊዜዬን ሙሉ በሙሉ ለጌታ ሰጠሁ የሚል ከሆነ ከእኛ አንድ አገልጋይ በቀን ስንት ሰዓት በጌታ ሥራ ላይ ያሳልፋል? ወይስ እኛ ቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊ ብላ ስለተቀበለችን ሌላ ሥራ ሳንሠራ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ስለምናሳልፍ ብቻ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ተባልን? በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ካለን አገልጋዮች መካከል በቀን 8 ሰዓት ይቅርና በታማኝነት 4 ሰዓት የምንሠራ ስንቶቸችን ይሁን?ይህንን ለመመዘን የሚያስችል ሥርዓት በቤተ ክርሰቲያን ውስጥ ስለሌለ እንዲሁ በደፈናው የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እየተባልን አገልግሎቱ ይጓተታል፡፡ በሌላም በኩል አገልጋዮቹ ትክክለኛ የጌታ ጥሪ የደረሳቸው ሲሆኑ ቀስቃሽና ጎትጓች ሳይፈልጉ የኃላፊነት ስሜት እየተሰማቸው አገልግሎታቸውን በትጋት ይወጡታል፡፡ በውስጣቸው ያለው የአገልግሎት ሸክም በአጥንታቸው ውስጥ እንደሚሄድና እንደሚነድድ እሳት ሲሆንባቸው ጊዜ እንቅልፍ እንኳ ሳይተኙ ለጌታ ሥራ ሌት ቀን ይሮጣሉ፡፡ ምንደኝነትና የአገልጋይነት ስም የቀላቀለባቸው አገልጋዮች ግን ከሥራ ይልቅ ስለሚሰጣቸው ስም ሲሟገቱ የአገልግሎት ጊዜአቸው ከፊታቸው ሮጦ ያልቅባቸዋል፡፡ እኔና አንባቢ ከየትኞቹ ነን?
በትጋት የሚያገልገሉ አገልጋዮች ከሚገባው ሰዓት በላይ ሰርተው ነገ ለሚጠብቃቸው አገልገሎት ጉልበት እንዳያጡ፣የዛሬው ዉጤታቸውም እንዳያንስ ቤተ ክርስቲያን ተገቢ እንክብካቤና ጥበቃ ታደርጋለች ወይ የሚለው ደግሞ ሌላ ጥያቄ ነው፡፡ እንዲያውም አንዱ ሲሰራ ቆመን ጸሐይ ከምንሞቅ አገልጋዮች ይልቅ በሥራ በሚጠመዱ ላይ ተጨማሪ ሥራ በላይ በላዩ እየተሰጣቸው ከጫና ብዛት የተነሳ እንዲገዳገዱ ይደረጋል፡፡ ቆመን የሚናወራውና የሚንተቸው ግን የሥራ ኃላፊነት መሸከም የማንፈልግ ደግሞ ተደማጭነት ያለን እኛው መሆናችን የበለጠ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ሠራተኞች እያሉ ተናጋሪዎችን ፊት ለፊት እያቆሙን ሰዎች ምሥጋናውን ሁሉ ለእኛ ይሰጡናል፡፡ ምክንያቱም እኛ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እያልን ስለሚያወራና ስለሚናስወራ ለሰዎች የተሸለ መንፈሳዊ እንመስላቸዋለን፡፡ አሁን አሁን በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ትኩረት የሚሰጠው ለሚሰሩ ሳይሆን ብዙ ለሚያወሩ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያን በአፋቸው ለሚኖሩ የተሸለ መሸሸጊያ ሆናለችና፡፡ ሥራ ካጣሁ ካጣሁ ወንጌላዊነት እንኳ ቢሆን አገኛለሁ እንጂ አልወድቅም ያለም ወንጌላዊ እገሌ ፣ፓሰተር እገሌ እየተባለ ነው፡፡ አንባቢ አጋነንክ አይበለኝ እንጂ አሁን አሁንማ ያሉን ምዕመናን የግማሽ ያህሉ ፓስተር ሊሆን ነው፡፡ ፓስተርነት ግብር የማይከፈልበት የገቢ ማሰገኛ መንገድ ስለሆነ ሰዎች የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ሃይ በል የሚሉት ከፓስተርነት ነው፡፡ ስለዚህ የምዕመናንም ሕይወት ጥራት የዚያኑ ያህል ነው፡፡
እዉነተኞች አገልጋዮች ለእግዚአብሔር ቤት እድገትና ለወንጌል መሥፋፋት በጣም የሚጠቅሙ ናቸው፡፡ እነርሱ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የምንላቸው ሳይሆን የሙሉ ልብ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጉት የሙሉ ጊዜ ሳይሆን የሙሉ ልብ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ጌታ ከማንም ቢሆን ጊዜውን ሳይሆን ልቡን ይፈልጋልና፡፡ ሙሉ ጊዜውን ሰጠ የምንለው ሙሉ ልቡን የሰጠው ሰው ነው፡፡ የሙሉ ልብ አገልጋዮች እንሁን ፣ የሙሉ ልብ አገልጋዮችንም እናፍራ ፣ ላሉትም እንጠንቀቅላቸው፡፡

ሥልጠና በኢትዮጵያ ላሉ ለወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያናት

      ሥልጠና በኢትዮጵያ ላሉ ለወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያናት

በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የኤች አይ ቪን ሥርጭት ለመከላከል የተለያዩ ሥልጠናዎች ይሰጡ ነበር፡፡ በየቤተ ክርስቲያናት ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች በበጎ ፈቃደኝነት መንፈስ ተነሳስተው በሙያቸው በእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ አገልጋዮችንና አባላትን በማሰልጠን አመረቂ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ በአንጻሩም ደግሞ በየአጥቢያው ብዙ የተማሩና በሙያው የተካኑ ሰዎች እያሉ አንዳንድ ከሙያው ጋር ብዙም ቅርበት የሌላቸው ሰዎች ስለ ኤች አይ ቪ ሥልጠና አዘጋጅቻለሁና ሰልጥነው ሊያሰለጥኑ የሚችሉ 5 ሰው፣ 6 ሰው፣ 4 ሰው ወዘተ ከነመመዝገቢያ ብር ጋር ላኩልን እየተባለ በየጊዜ ጥሪ ይደረግ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ የተባለው ሥልጠና የሕክምና ባለሙያዎች በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ከሚሰጡት ጋር ሲነጻጸር ግን እንዲያው የማላከፍ ያህል እንጂ ቀረብኝ የሚያሰኝ አልነበረም፡፡ አልጠቀመንም ማለቴ ግን አይደለም፡፡ ሌላም ጊዜ ለተመሳሳይ ሥልጠና እነዚያውኑ ሰዎች ይጠሩና አሁንም ሰዎች ተዋጥተው ይሄዱና የተባለውን ሥልሥተና ይካፈሉና ይመጣሉ፡፡ መጥተው እንዳያሰለጥኑ በሕክምና ሙያ እውቀታቸው አጥናፍ ያለፈ ፣ በማስተማር ሙያቸውም እኔ ነኝ ያሉ ሐኪሞች እዚያው እያሉ ደፍረው ላድርግ ማለት ይሳናቸዋል፡፡ ሌላም ጊዜ ሌላው ወገን ደግሞ በኤች አይ ቪ ኤዲስ በዓይነቱ ልዩ ሥልጠና ልሰጥ ተነስቻለሁ ይልና አሁንም ለየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ጥሪ ይበትንና ይህን ያህል ሰው ከመመዝገቢያ ጋር ላኩልን፣ እንዳያመልጣችሁ! ሲል አሁንም ሰዎች ይላኩና ሰልጥነው ይመጣሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደተባለው ሁሉ የሚሄድ አንድ ወንጌላዊ ነበርና አሁንም በሌላ ጊዜ ለተመሳሳይ ሥልጠና ሰው ይመረጥ ሲባል ያ ወንጌላዊ ተጠቆመ፡፡ ይህን ጊዜ አንድ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ እንዲህ አሉ፡፡ ይህ ወንጌላዊ እገሌ ኤች አይ ቪ በአገራችን ከተሰማበት ጊዜ አንሥቶ የሚሰጠውን ሥልጠና አንድም ሳይቀር ሁሉን ተካፍሏል ፣ ታዲያ የዶክተር ዲግሪ ቢሰጠውስ ምን አለበት እንዳሉ አስታውሳለሁ፡፡ እውነት ለመናገር ያ ወንጌላዊ ሥልጠና ወዳለበት ሁሉ ይሄዳል፣ ይካፈላል እንጂ የሰለጠነውን ግን ለሌላው አያስተላልፍም ነበር፡፡ ለሕዝብ ሥልጠና ይሰጥ ሲባል እርሱም ሆነ ሌሎች ከሌላ ቦታ ሌላ ሰው ይጋብዛሉ እንጂ አይ ብዙ ሰልጥኛለሁና አሁን እኔ ላሰልጥን ሲል አይታይም ፣ አይደመጥምም ነበር፡፡
ስለ ኤች አይ ቪ እንደ ምሳሌ አነሳሁ እንጂ ብዙ ተደጋጋሚ ሥልጠናዎች ይሰጡ ነበር፡፡ ለሕዝብ የሚዘጋጁ የሥልጠና ፕሮግራሞችን በሚመለከት በጣም የሚታወቁት፣ የጸረ ኤች አይ ቪ ሥልጠና ፣ የወንጌል ሥርጭት ሥልጠና፣ የመሪዎች ሥልጠና፣ ሲሆኑ አልፎ አልፎ የጸሎት ሥልጠና ይሰጣል፡፡ በተደጋጋሚ የሚሰጠው ሥልጠናዎች በይዘታቸው አንድ ዓይነት እንጂ ምን ልዩነት አይታይባቸውም፡፡ ይህ መሆኑ እየታወቀ ሰዎች በተደጋጋሚ እየሄዱ ይካፈላሉ፡፡ ከዚህ ጋር አንድ ላይ ማየት የሚገባው ሌላው ነገር ሥልጠና አዘጋጆቹ ዓላማ ነው፡፡ በየትኛውም ዘርፍ ቢሆን ሥልጠና የሚያዘጋጁ ሰዎች ከዚያ ሥልጠና ምን ጠብቀው ነው ቢባል ብዙዉን ጊዜ ያላቸው ዓላማ የቤተ ክርስቲያን ዓላማ ሳይሆን የአዘጋጆቹ የራሳቸው ዓላማ ነው፡፡ ይህን ለማወቅ ሥልጠናው ያዘጋጁ ሚኒስቲሪዎች የሥልጠናቸውን ሪፖርት የሚያቀርቡት ሰልጣኞችን ለላኩት ቤተ ክርስቲያናት ሳይሆን በገንዘብ ለሚደግፉአቸው ድርጅቶች መሆኑን መረዳት በቂ ነው፡፡ የተቀረጸው ምስል፣ የተደረገው እንቅስቃሴ ሁሉ የሚነገረው ለውጭ ድርጅቶች ብቻ ነው፡፡ በአገልገሎት መስኩ አብረው ስለተሰለፉ ለእነርሱ ሪፖርት መቅረቡ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ለአነርሱ ብቻ ምንጭር ቆራጭ ከመሆን ባለፈ ለአብያተ ክርስቲያናት ምንም አለማለት ደግሞ ሌላው ድክመት ነው፡፡ ሥልጠናው በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ያመጣው በጎ ተጽእኖስ ምንድነው የሚለውን ለማወቅ መጣር እኮ አንድ ነገር ነው ግን በሚኒሰቲሪዎችችን በኩል ይህ ብዙም አይታይም፡፡
በአብዛኛው የተለቀቀው በጀት ዝም ብሎ እንዳይመለስ ቶሎ ቶሎ ብለን ሥልጠና እናዘጋጅ በሚል የሚሰጥ ሥልጠና በጣም በርክቷል፡፡ የሚሰጠው ሥልጠና የቤተ ክርስቲያናትን ዓላማ ለማስፈጸም ምን ያህል ይረዳል የሚለውን በአጥቢያ ቤተ ከርስቲያን ማየት ብዙም አይታሰብም፡፡ ሥልጠና ሰጪዎቹስ ለምን ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ጋር አብረው ተመካክረው የሥልጠና መርሀ ግብር አይዘረጉም? ቢባል መጀመሪያውም ገንድሰው የወጡት እነርሱ ስለሆኑ፣ አሁን አብረው ለመሥራት አይችሉም፡፡ እንዲያውም የአንዳንዶች ልብ በራስ የግል ዓላማ በእልክ ተጨብጦ ስላስቸገራቸው ፣ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የሌላትን እኔ አምጥቻለሁ ስለሚሉ ሩቅ ሆነው ወደራሳቸው ይጠራሉ እንጂ አብረው መሥራት ይፈሩታል፡፡ ወይ ሥልጠና………
በአንድ ወቅት አንድ ሚኒሰትሪ እኔ ልዩ ነገር ታይቶኛልና የልጆች ሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ሥልጠና ልሰጥ ነው ብሎ ጠራና በጣም ጠቃሚና ቁም ነገር ያለበትን ነገር ለአገልጋች ያስጨበጠበት ጊዜ ደግሞ ነበር፡፡ ያንን አይተው ይመስለኛል ሌሎች ደግሞ ለሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ሥልጠና አዘጋጅቻለሁና ሁላችሁም ኑ ብሎ የሰጠውን ስልጠና ስናየው ከመጠነኛ ለውጦች በቀር የዛኛውን አሠራር እንደነበር ገልብጠው የመጣበት ነበር፡፡ የሚገርመው ግን ያዘጋጀሁትም ሥርዓተ ትምህርት አለና እንኩ፣ ከዛሬ ጀምሮ እርሱን ለልጆቻችሁ አስተምሩ ሲል ቤተ ክርሰትያንም ተቀብላ ማስተማር ጀመረች፡፡ ይሁን እንጂ ራዕይው ከመጀመሪያውም የቤተ ክርሰቲያንና የአገልጋዮቿ ስላነበር ብዙ የተደነጋገሩ ነገሮችና ብዥታዎች አንደነበሩ ትዝ ይለኛል፡፡ ወይ ሥልጠና››››››››
በአገር ውስጥ ያሉ ሰዎች ከሞላ ጎደል እዚያው ስለሆኑ ቤተ ክርስቲያናት ስላሉበት ተጨባጭ ሁኔታ መቃኘት ብዙም አያቸግራቸውም፡፡ ስለዚህ ቢያንስ ቤተ ክርስቲያን ካለችበት ሁኔታ ጋር የተቀራረበ የሥልጠና ፕሮግራም ማቀድ ይችላሉ፡፡ የሚያስገርመው ከባህር ማዶ የሚመጡ አሰልጣኖች ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም በአሜሪካን አገር ሰንብትበት ያሉ አገልጋዮች ወደ አገር ቤት ሲሄዱ ስልጠና ልሰጣችሁ ጌታ በልቤ አስቀምጧልና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ ካሉ ሁሉ ነገር አለቀ፡፡ ምን ዓይነት ሥልጠና ነው የምትሰጠን? በምን ርዕስ ነው የምታሰለጥነን? የሥልጠናህስ ዓላማ ምንድነው? የሚለው ጥያቄ ምንም አይጠየቅም፡፡ ለነገሩ ከዚያ በዘለለ መልኩ አንተ ባለህበት የምትኖረው አንዴት ነው? ለመሆኑ ያለህበትን ቤተ ክርስቲያን አማኞች ምን ያህል አሰልጥነህ አዘጋጅተሃል? በምትሰጠውስ ሥልጠና ምን ያህል ቀደ መዛሙርትን አፍርተሃል? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ የአገር ቤት ቤተክርስቲያንም ደግሞ ይህ ሥልጠና ካለንበት ሁኔታ፣ ካነገብው ዓላማ፣ እና ከራዕያችን ጋር ምን ያህል ይሄዳል የሚለውን በሰከነ አኳኃን አይገመግሙትም፡፡ ብቻ ከአሜሪካ ነው የሚመጣው ሲባል ከሰሙ ሣር ቅጠሉን ሁሉ ያሯሩጡታል፡፡ በተለይም አንድ ፈረንጅ አስከትሎ የሚሄድ ከሆነ አገልጋዩም ምድር ደህና ሁኚ ይላል፣ የአገር ቤት ሰዎችም እንዲያው ታይቶ የማይታወቅ ነገር እንደሆነ አድርገው ይራቆቱበታል፡፡ እነዚያ አገልጋዮች በአሜሪካን አገር እንዴት እንደሚኖሩ ቀርበው ቢያዩ ማ ኖሮ ሥልጠናው ቀርቶ አንተ በሰላም ወደ መጣህበት በተመለስክልን ባሉ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ ከአሜሪካን ወደ ኢትዮጰያ የሚሄዱ ሰዎች ብልጥ መሆን እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡ ከረጅም ዘመን የውጭ ቆይታ በኋላ ቤተ ሰባቸውን ለመጠየቅ ሲሄዱ የትኬት ገንዘብ ብዙ ነው፡፡ አንድ ፈረንጅ ቢያባብሉት እንደበረከት ይቆጥርና አብሮ ለመሄድ ከተስማማ የአየር ትኬቱን ዋጋ የሚሸፍነው ያ ፈረንጅ ነው፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ፈረንጅ ከተገኘ ማ በቃ የአየር ትኬት ብቻ አይደለም ሌላው ወጪ ሁሉ ይሸፈናል፡፡ ይህንን የኢትዮጵያ አገልጋዮች በጭራሽ አያውቁትም፡፡ ስለዚህ አንድ ያንን ፕሮግራም ማስተባበር የሚችል አዳማቂ ሰው በአገር ቤት ማዘጋጀት አንዱ ስልት ነው፡፡ እርሱ ሁሉንም ነገር ያሰናዳል፡፡ የአሜሪካው ሰዎች አስክመጡ ድረስ ሁሉንም ቀምሞ ይጠብቃቸዋል፡፡ ከዚያ የተፈለገው ነገር ተሳካ ማለት ነው፡፡ እኔም ይህ ነገር የገባኝ አሜሪካን አገር ከመጣሁና ስለ አንዳንድ የሰው ልጆች ብልሃቶችና በእግዚአብሔር አገልግሎት ስም የሚደረጉ ቅጥፈቶችን ካየሁ በኋላ ነው፡፡ በእውነት ሕዝባችንን በደረቁ እየላጥነው ነው ያልኩት አሁን ነው፡፡ ሰዎቹ እንደማናችንም ትምህርት ቃርመው ሊሆን ይችላል፡፡ ያ ብቻውን ግን በቂ አይደለም፡፡ እውነተኛና ትሁት ልብ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ መዝናናት ኃጢአት እንዳይመስላቸው ህልናቸው ስለታመመባቸው ግድ የላቸውም፣ ቀጥሎ ስለሚሆነው ነገር ደንታ ቢሶች ናቸው፡፡ ይህን ነው እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መንቃት ያልቻሉት! ለምን ቢባል ከአገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ስለ ሰጡት ሥልጠና እዚሁ እንደ ጉድ ያስወራሉ እንጂ ያ ሥልጠና በምን ሥራ ላይ ዋለ ብለው አይጠይቁም፡፡ ሥራ ላይ የሚውል አለመሆኑን ገና ከዚህ ሲነሱ በደንብ ያውቁታል፡፡ ሥራውም ሲታይ ከቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታና አገልግሎት ጋር የማይዋሄድ ብትን ሥራ እንደሆነ የሁሉም ሆድ ያውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምን ዓይነት ሥልጠና እንደሚያስፈልጋት የሚያውቅ በአሜሪካን ያለ አንድ አገልጋይ ወይም ኢትዮጵያን በእግሩ ረግጦ የማያውቅ ፈረንጅ ሳይሆን የኢትዮጵያ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እረኛ ነው፡፡ ካስፈለገም አቅም አንሳቸው ይሆናል እንጂ በኢትዮጵያ ያሉ እረኞች ለአሜሪካን አገልጋዮችም የሚሆን ስልጠና መስጠት ይችሉ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በጸጋ ስጦታው ባርኮአቸዋል እያልኩ ነኝ፡፡ በፈረንጅና በኢትዮጵያውያን መካከል ያለው የቆዳና የቋንቋ ልዩነት እንጂ የእግዚአብሔር ጸጋ አይበልጥም አያነስምም፡፡ ማንም ይሁን ማን በአንድ ቀን ሥልጠና የሚያመጣው ታአምር የለም፡፡
አውነተኞች የተከበሩ ኢትዮጵያውያን አገልጋዮች በአሜሪካን አገር አሉ፡፡ ይህም የሚያስገርም ነገር ነው፡፡ወደ ኢትዮጵያም በመመላለስ ከሥልጠናም ባለፈ ትላልቅ ሥራዎችን የሠሩና ለቤተ ክርስቲያን በብዙ እየተረፉ እንዳሉ የታመነ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ ከመጀመሪያውም ከኢትዮጵያ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጋር አብረው ስለ ነበሩ የሚያደርጉትን ያውቁበታል ፣ እኔ ይሁንልኝ፣ ደህናም አድርጌ ልቀርቅብ እንጂ ሌላው የራሱ ጉዳይ የሚሉ አይደሉም፡፡ እንደነዚህ ያሉት ምንም እንኳን ነዋሪነታቸው በአሜሪካን ቢሆን ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልሎት የሚጠቅም ሞልቶ የተረፈ ነገር አላቸው፡፡ ሥልጠናና ትምህርት ለምን እንደሚሰጡ ያውቃሉ ፣ ከቤተ ክርስቲያንም ጋር እጅና ጓንት ስለሆኑ እነርሱ ባሉበት ሻሞ ሆይ አይባልም፡፡ የሥልጠናቸው ይዘት እንደነዚኛዎቹ ሥር የሌለው ቁርበተ- ነክ አይደለም፡፡ ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባል፡፡
ስለዚህ፣ እኔ ያለኝ መልእክት ቢኖር ሥልጠና፣ ሥልጠና፣ ሥልጠና እየተባለ እንደ አዝማች ከመደጋገም በሥልጠናው አስፈላጊነት ላይ አስቀድሞ መወሰን ጥሩ ነው፡፡ ደግሞ በአሜሪካን ያሉ ኢትዮጵያውያን አገልጋዮች ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሲያስቡ ያለ ሥልጠና የማይታያቸው ምን ነክቶአቸው ነው? ሥልጠና መስጠት ከፍ ብለን አንደተመለከትነው የአጭር ጊዜ ስለሆነችና የአገር ቤቱን ወጭ ለመሸፈን ስለሚትረዳ ወይስ ሌሎች አባቶችና ወንድሞች ሲያደርጉ ሲሳካላቸውም እንዲሁም ከመልካም ሥራቸው የተነሳ ዝናቸው ሲወጣ ሰላየን እኛም ለምን በዚህ ስማችንን አናስጠራም በሚል ይሆን? ዝና እኮ መልካሙን ሥራ ስንተገብር ያዩ ሰዎች ሰብሰብ ብለው የሚያስተጋቡት የሠፈር ወሬ ነው፡፡ እኛ መልካሙን ከሠራን ሰዎች አንዱ ለሌላው እያሰማ ሳናውቀው ዝናችን ሊወጣ ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እግዚአብሔርን ይወዳል፣ ይፈራልም፡፡ ግን እንዲያው ምንም የማይገባው ድፍን ቅል አኮ አይደለም፡፡ እንግዳ ይወዳል ያቀበላል ግን በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ሌባ ሁሉ ሲመዠርጠው አይሰማውም ማለት እንዳይደለ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በመሆኑም ለወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን ሥልጠና አዘጋጅቻለሁ የሚሉ ወንድሞች ምን አስበው እንደሚያደርጉት አስቀድሞ ይታወቅ፡፡ በሥልጠና ብቻ ቤተ ክርስቲያንን ማሳደግ፣ መደገፍ፣ የወደፊት ራዕይዋንም መሳካት አይቻለልም፡፡ ሥልጠና የሚያስፈልግባቸው ሁኔታዎች የትኞቹ አንደሆኑ የአጥቢያ እረኞች ያስቡበት እንጂ ሩቅ ሆነን እኛ እናውቅላችኋለን ማለት ከልክ ያለፈ ቀልድም በደልም ነውና ሁላችንም እናስብበት፡፡

Tuesday, April 14, 2015

የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት አገልግሎት

የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት አገልግሎት
በአንድ ወቅት በአሜሪካን አገር ግራንድ ራፒዲስ በሚባለው ከተማ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የእግዚአብሔርን ፊት በጾምና በጸሎት እየፈለግን ባለበት ሰዓት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያካፍል የተመረጠው ሰው ለመልእክቱ መግቢያ ያደረገውን የማይረሳ ምሳሌ ሁል ጊዜ አስታውሳለሁ፡፡ እንዲሀ ነው ነገሩ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2009 የተባበሩት መንግታት የኢኮኖሚ ፎረም ባደረገው ዓመታዊ ስብሰባ የተለያዩ የመንግሥታቱ አባል አገሮች ተወካዮች የየአገራቸውን የሥራ ሪፖርት ይዘው ቀረቡ፡፡ ከየአገሩ የመጡ ወካዮች ምን ለሥራት ታሰቦ ምን አንደተከናወነና እንዴት ያለ ለውጥ እየታየበት እንደሆነ እያካፈሉ አንዳቸው ከሌላው ልምድም እየቀሰሙ ባለበት ወቀት የአንድ አገር ሪፖርት ግን የብዙዎችን ልብ የነካና የተደነቀ ሆነ፡፡ ያቺ አገር በሩቅ ምሥራቅ የምትገኝ ባርማ በመባል የምትተወቅ አገር  ናት ፡፡ ባርማ በ2009 .ም ልትሠራ ያቀደችውና ያከናወነችው ሌሎች አገሮች ካቀረቡት ጋር በፍፁም የይገናኝ ነገር ግን ሁሉንም ያስደነቀ አቀራረብ ነበር፡፡ ሌሎች  ስለ ልማት፣ ስለ አኮኖሚያዊ እድገት፣ ስለ ውጭ ግንኙነትና ስለ ወታደራዊ ዝግጅቶቻቸው ሆኖ ካቀዱት ምን ያህል እንደተሳካላቸው ነበር ያቀረቡት፡፡  ባርማ ግን በ2009 መግቢያ ላይ የያዘቺው እቅድ በአገሪቱ ውስጥ ያለ እያንዳንዱን ዜጋ በነፍሰ ወከፍ ደስተኛ እንዲሆን ስለማድረግ ነበር፡፡ ከልማት ሥራዎች ሁሉ የሚቀድመው የዜጋው ረክቶና ተደስቶ የመኖር ጉዳይ ስለሆነ ከዚህ አንፃር አቅዳ 90 በመቶ እደተሳካለት ያቀረበቺው ሪፖርት ሁሉንም የጉባኤ ተሳታፊዎችን ሊያስደንቅ ችሏል፡፡
ይህ ለእኛ የእግዚአብርን ሕዝብ ምናገለግል ሰዎች እጅግ በጣም አስገራሚ ትምህርት ያለበት ምሳሌያዊ መልእክት ነው፡፡ እኛ ከባርማ መንግሥት ይልቅ የምናገለግላቸውን ቅዱሳን ልባቸው እንዲያርፍ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብርም እኛን በዚህ ምድር ይ ያስቀመጠን የእርሱን አሳብ እያገለገልን በስሙ የተጠሩትን ሁሉ እንድናንፃቸው ነው፡፡ የአገልጋዮች አገልግሎት የምዕመናንን ልብ የሚያሳፈርፍ እዲሆን ደግሞ የእግዚዘአብር ቃል ይመክረናል፡፡ አገልግሎታችን የቅዱሳንን ልብ እንዴት ማሳረፍ እንደሚቻል ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልሞና ጻፈውን መልእክት ከቁጥር 1-7 መመልከት እንችላለን፡፡ ወደ ዋናው አሳባችን ከመግባታችን በፊት ስለ ፊልሞና መጽሐፍ ሁለት ወይም ሦስት መሰረታዊ በሕሪያቶችን እንመልከት፡፡ የፊልሞና መጽሐፍ ዋሪያው ጳውሎስ እሥር ቤት ሆኖ ከጸፋቸው የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ጳውሎስ ይህንን መፅሐፍ በሚጽፍበት ወቅት በሮም እሥር ቤት ሊሆን ይችላል፣ ወይም በሌላ ቦታ ሊሆን ይችላል ብቻ መልእክቱን ያስተላፈው ከእሥር ቤት ነው፡፡ የፊልሞናን መጽሐፍ በጣም ተናፋቂ ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይህ ነው፡፡ ከየትና እንዴት በማንስ ተጻፈ የሚለው አሳብ የሚተላለፈው መልእክት ተሰሚነት እንዲኖረውና አቅምም አንዲያገኝ ያደርገዋል( .9)፡፡ ሁለተኛው የፊልሞና በጣም አጠር ካሉ ወይም ምዕራፍ ከሌላቸው መጻሕፍት ይመደባል፡፡ በጠቅላላው በመጽሐፍ ቅዱ ውስጥ ወደ አራት ያህል መጻሕፍት በምዕራፍ ያተከፈሉ ሲሆን እነርሱም ብዲዩ፣2ኛ ዮሐንስ፣ 3ኛ ዮሐንስ ና ፊልሞና ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በምዕራፍ አይከፋፈሉ እንጂ ትልቅ ቁም ነገር ያዘሉ ናቸው፡፡ በምዕራፍ ያልተከፈሉበት ምክንያት አጠር ባለ መልክ ስለቀረቡ ብቻ እንጂ መልእክቱ ከእግዚአብሔር ስላልሆነ አይደለም፡፡ ሦስተኛ የፊልሞናን መጽሐፍ ልዩ የሚያደርገው የመልእክታቴ ምጋቤ አካል ከሆኑት መጸሕፍት የሚመደብ መሆኑ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ለቡድን ወይም ከቤተ ክርስቲያን ወይም ለአንድ አገልግሎት ክፍል የተላከ ሳይሆን የሕዝብ እረኛና አገልጋይ ለሆነ ሰው በግሉ የተላከ የመጋቢያዊ መልእክት ያዘለ ነው፡፡ ለአንድ ግለሰብ የተላኩ ሌሎችም ጻሕፍት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሲሆን ሁላቸውም የየራሳቸው ባሕሪያት ያሉአቸው ናቸው፡፡
በዚህ አጭር ትምህርት ውስጥ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለፊልሞ የሚያቀበውን መልእክት ሁሉንም ማየት እችልም ፣ ነገር ግን ከቁ 1-7 ያለውን ብቻ እንመለከታን፡፡ ይንን መልእክት የሚያስተላልፈው የእግዚአብሔር ሰው ጳውሎስ የጌታ አገልጋይ ከሆነው ከፊልሞና ጋር ትልቅ የአልግሎት መተሣሠር ነበራቸው፡፡ ጳውሎስ በእሥር ቤት ሆኖ ስለ ፊልሞና አገልግሎት የሰማው ነገር በእርሱ ላይ የፈጠረው አዎንታዊ ተጽእኖ በዚህ የንባብ ክፍል ውሰጥ ይገኛል፣ ምክንያቱም ጳውሎስ በፊልሞና አገልግሎት ምክንያት መጽናናቱንና መደሰቱን ይናራል( . 7)፡፡ በፊልሞና አገልግሎት በቤተ ክርሰቲን ያሉ ቅዱሳን ልብ በማረፉ ምክንያት ጳውሎስ ተደስቷል፣ በብዙ መጽናናት ተጽናንቷል፡፡ እንዲህ ያለ አገልግሎት ማገልገል እንዴት ዓይነት መታደል ነው!
ፊልሞና የሚያገለግለው አገልግሎትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያደርገው ሥራና ተግባር ሁሉ የሕዝቡን ልብ ከመረበሽና መንፈሳቸውን ከማናወጥ ይልቅ ልባቸውን የሚያሳርፍ ነበር፡፡ ስለዚህ እኛ ዛሬ በዚህ ዘመን የምንገኝ አማኞች የቅዱሳንን ልብ ከማሳረፍ አንፃር እንዴት አይነት አገልግሎት እየሰጠን እንደሆነ ራሳችንን መመልከት ይኖርብናል፡፡ እስቲ የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ ሕይወትና አገልግሎት ምን እንደሚመስል ሐዋሪያው ጳውሎስ ለፊልሞና ከጻፈው መልእክት እንመልከት፡፡
1. አገልገሎቱ የቅዱሳንን ልብ ሚያሳርፈው አገልይ የይቅርታ ልብ ያለው ነው፡፡
ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለፊልሞና የሚልክበት ተቀዳሚ ምክንያት በፊልሞናና በአናሲሞስ መካከል ክርስትያናዊ ይቅርታን ለማስፈን ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ሙሉውን የሚገረው ስለ ይቅርታ ነው፡፡ ፊልሞና በፍቅርና ሌሎች መልካም ሥራዎች የቅዱሳንን ልብ ያሳረፈ ምርጥ አገልጋይ ቢሆንም ጳውሎስ በድጋሚ ስለ አናሲሞስ ይጠይቀዋል፡፡ አናሲሞስ የፈልሞና አገልጋይ (በጥንት አባባል ባሪያው) ሆኖ ከፊልሞናም ጋር አብሮ ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን በአንድ ወቅት ፊልሞናን ዘርፎ በመኮብለሉ የፊልሞና ልብ በአናሲሞስ አዘነ፡፡ ይሁን እንጂ አናሲሞስ ኮብልሎ በሄደበት ጳውሎስ አገኘውና ወንጌል ሰበከለት፣ አናሲሞስም  በጌታ በኢየሱስ አመነ፡፡ ጳውሎስ በእሥር ቤት በነበረበት ወቅት በወንጌል ንዲያምን ምክንያት ስለሆነው አናሲሞስ ይረዳና ያግዘው ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ የአናሲሞስ ለጳውሎስ አስፈላጊ ሰው ቢሆንም ያለ ፊልሞና ፈቃድ ለራሱ ሊያስቀረው ስላልፈለገና በሁለቱ መካከል የይቅር መንፈስ እንዲሰፍን ስለፈለገ ወደ ፊልሞና ይልከዋል፡፡ እንዲያውም ፊልሞና አናሲሞስን እንደ ወንድሙ እንዲቀበለው ይማጸነዋል፡፡ ያ ብቻ ሳይሆን የተደበለውንም ሁሉ በእርሱ ላይ እንዲቆጥርበት ይጠይቀዋል፡፡ እንግዲህ ከዚህ የምናየው እርቅና ሰላም በሌለበት ሥፍራ ሁሉ ጭንቀትና መረበሽ እንዲሁም አለመረጋጋት መኖሩን ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሐዋሪያው እባክህ ልቤን አሳርፍልኝ የሚለው! ይህ የጌታ አገልጋይ ባደረጋቸው ሥራዎች ሁሉ የቅዱሳንን ልብ በማሳረፍ የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ደግሞ ለአናሲሞስ ይቅርታ በማድረግ የበለጠ የጳውሎስንና የሌሎችን ልብ እንዲያሳርፍ ተጠይቋል፡፡ ይቅርታ ሲደረግ የቅዱሳን ልብ ያርፋል ማለት ነው፡፡ ሁለት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሲጫቃጨቁና ሲቃረኑ እንቅልፉን የሚያጣው ምዕመኑ ነው፡፡ ሁለት መጋቢዎች ባለመግባባት እርስ በእርሳቸው ሲገፋፉ የሚያዝነውና የሚረበሸው ጉባኤው ነው፡፡ መሪዎች እርስ በእርሳቸው የሰላምና የፍቅርን አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በምዕመናን መካከል ያለው ደስታና ፍንደቃ ትልቅ ይሆናል፡፡
የብሉይ ኪዳን መጸሕፍትን በምንመለከትበት ወቅት የእሥራኤል ሕዝብ ለጦርነት ከተጋለጠባቸው ምክንያች አንዱ የመሪዎች ሁኔታ ነው፡፡ በአናጸሩ ደግሞ አገርን ከሚመሩ ነገሥታት የተነሳ ምድርት አርፋ እንደምትቀመጥ የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ጊዜ ምድሪቱ በሰላም አርፋ ተቀመጠች እያለ ይናገራል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በቤተ ክርስቲያንም የሚያገልግሉ መሪዎች እርስ በርሳቸው በፍቅር ሲቀባበሉና ሲዋደዱ በመላ ቤተ ክርስቲያን የሚታየው ደስታ እጅግ የላቀ ይሆናል፡፡  ጳውሎስም ፊልሞናን ልቤን አሳርፍልኝ  ማለትም ይቅርታ በማድረግ ልብ የሚያሳርፍ ሥራህን ቀጥል የሚለው ለዚህ ነው፡፡
ዛሬም እኛ የሚያስፈልገን የአገልግሎት ብዛት አይደለም፡፡ ብዙ መስበክም አይደለም፡፡ ነገር ግን የቅዱሳንን ሁሉ ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ሆነን መገኘት ነው፡፡ እኛ ይቅርታን የማይቀበል በቀለኛ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ያደግን ሰዎች ነን፡፡ አብዛኛው ባህላችን ቁጣና በቀል የተሞላ ነው፡፡ ብድር በምድር የሚለው አስተሳሰብ አብሮት ከማደጉ የተነሳ  ትውልዳችን ይቅርታን መጠየቅን እንደ ሽንፈት፣ ይቅርታን ማድረግን እንደ ሞኝነት የሚቆጥር ነው፡፡  ጌታን ተቀብለን አገልጋዮችና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከሆንንም በኃላ እንኳ ያ አብሮን ያደገው ልማዳችን ከውስጣችን አልወጣ ብሎ ጊዜ ይወስድብናል፡፡ ስለዚህ ብዙዎቻችን በእግዚአብሔር ቤት እንበቃቀላለን፣ አንዳችን ሌሎችን እናሳድዳለን፡፡ በተለያየ የአገልግሎት ዘርፎች ብናገለግልም በእግዚአብሔር መድረክ ላይ እያለንም በቀለኝነት ያጠቃናል፡፡ ይህ ከመሆኑ የተነሳ የእግዚአብሄርም ልብ አልተደሰተም የቅዱሳንም ልብ አላረፈም፡፡ እኛ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እያሳረፍን ነው ወይስ እያሳዘንን; እያራወጥነው ወይስ እያረጋጋነው፣ እያጽናናነው ወይስ እያስጨነቅነው ነው የሚለውን ጠይቀን መልስ ማግኘት ይኖርብናል፡፡ የእግዚብሄርን ቃል በማስተማርና የተያዩ ቅዱሳት መጻሕፍትን መበጻፍ በዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ትልቅ አክብሮት ያላቸው ዶር ጆን ማካርተር ይቅርታ አለማድረግ እንዴት ያለ ክፉ ነገር እንደሆነ እንደሚከተለው ገልተዋል፡፡
ይቅርታን አለማድረግ ባለፈው የመራርነት ሕይወት እሥረኞች አንድንሆን የሚያደርገን ነው፡፡ ይቅርታን አለማድረግ ለሰይጣን አሠራር የተከፈተ በር የሚሰጥ ሲሆን እኛም አጋንንትን በዚያው እንኳን ደህና መጣህ እያልነው ነው፡፡ ይቅርታ አለማድረግ በእኛና በእግዚአብሔር መካካል ላለን ሕብረት እንቅፋት ነው፡፡ ምከንያቱም ጌታ ኢየሱስ ሲያስተምር ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማዩ አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም፡፡ ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ካላልን ደስታችንና ሰላማችን ይወሰድብናል፡፡ ጳውሎስ በፊልሞናና በአናሲሞስ መካካል ሆኖ ሁለቱን የሚሸ መግላቸው ይመስላል፡፡ አናሲሞስ ፊልሞናን በጣም አድርጎ በድሎታል፡፡ ጳውሎስና ፊልሞና በነበሩበት ዘመን አናሲሞስ ያደረገውን ዓይነት በደል የፈጸመ በባህላቸው መሠረት ይወገዛል ፣ ይወገራል፣ ይሰደዳል እንዲያውም ገደላልም፡፡ እርሱ የፈጸመው ወንጀል በማንኛውም ማኅበራዊና ሕዝባዊ ጉዳዮች ሥፍራ እንዳይኖረው የሚያደርግ ነው፡፡ምክንያቱም አናሲሞስ ለፊልሞና ባሪያው ሆኖ እያለ ያንን በአሠሪዎች ዘንድ ከባድ ወንጀል ሆኖ የሚታወቀውን ጥፋት ሠራ፡፡ ምናልባት አናሲሞስ ከአካባቢው የሸሸው የሚደርስበትን ቅጣት ፈርቶም ሊሆን ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ሕግ ግን ይህንን በደለኛውን ሰው አንደ ወንድምህ ቁጠረው ይላል፡፡ ይህ ቀላል ሊሆን የማይችልበት ምክንያት አለ፡፡ አንደኛ ባሪያና ጌታ ሁለቱ እኩል በማዕድ መቀመጥ የሚችሉበት ባህላዊ አግባብ በጊዜው አልነበረም፡፡ ዘራፊና ቀመኛ ምንም ቢሆን ከተቀማው ሰው ጋረ ሕብረት እንዲያደርግና ከዚያም አልፎ እንደ ወንድም ሊቀበል የሚችል ሥርዓትም ሆነ ልማድ አልነበረም፡፡ የእግዚአብሔር ህግ ግን ከዚህ ሁሉ ይለያል፡፡ እንደ ወንድምህ ቁጠረው ፣ ባሪያ ከነበረበት እንደ ወንድምህ አድርገው የሚል ነው፡፡ ጥፋት አድርሶ የኮበለለውን የጠገበ ሠራተኛ ወደ ሥራው አንዲመለስ አሠሪውን እንማፀነው ይሆናል ፣ ወንድም አድርገው ለማለት ምንም የማይታሰብ ነው፣ ማለት የሚፈልግም ካለ ደግሞ ሆን ብሎ ሽምግልናውን ለማደፍረስ እንደሚፈልግ ሰው ለፈረጅበት ሁል ይችላል፡፡ ጳውሎስ ለፍልሞና የሚናረው መልእክት ግን ወደ ሥራው እንዲመለስ ከሚለው የዘለለና እንደ ወንድም ቁጠረው የሚለው ነው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ክርስትና ሲገባን ብቻ ነው፡፡ ስለ ይቅርታ ሰብከው ሲመለሱ ወንድማቸውን ይቅር አልልም ብለው ሳምንት ሙሉ ሽማግሌ የሚያመላልሱ አገልጋዮች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ስብከት ችለዋል እንጂ ክርሰትናው ገና አልገባቸውም አሊያም ክርስትና የሚያሰከፍለውን ዋጋ ገና አላወቁትም፡፡ ምክንያቱም ክርስትና የዘረፈህን ጥጋበኛና ጎረምሳ አገልጋይን ወደ አንተ ሲመጣ እንደ ወንድምህ አድርገው እንጂ እንደ ሠራተኛህ አትየው የሚል ነው፡፡
ጳውሎስ ስለ ፊልሞና የተረዳው ሁሉ አዎንታዊ ነው፡፡ የሚያርምበት አንድም ነገር እስከማይኖርበት ድረስ ሕይወቱ የተመሰከረለት ሰው ነው፡፡ ምን አይነት ባሕሪያ ነው! አሁን ግን ለአናሲሞስ ይቅርታ በማድረግ የበለጠ ይምሰገናል ክርሰቲያናዊ ጀግና ይባላል ወይም ብዙ የሆነው መልካም ነገሩ በአንድ ነገር ምክንያ ብቻ ዋጋው ሊረክሲበት ይችላል፣ ያውም ይቅርታ በማድረግ ወይም ባለማድረግ፡፡ ብዙ የመድረክ ጀግኖች ተፈትነው በቀላሉ ክብደታቸው ታወቀ፡፡ እኔ እኮ ጌታን ካገኘውና በመንፈስ ቅዱስ ከተሞላው ይህን ያህል ሰዓት ሆኖኛል፣ እነ እገሌም በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት እኔ እጅ ጭኜ ስጸልይ ነው ብለው የሰውን ሁሉ እትኩሮት ሲስቡ የኖሩ ቱባዎቻችን ክርስትናቸው ከወጣበት በአንዴ ሲወርድ ያየነው ለባልንጀራቸው ይቅርታ እንዲያደርጉ ሲጠየቁ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ያየን ቀን ነው፡፡
2. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ስለ ሰዎች ሕይወት የሚጨነቅ ነው( .4)፡፡
ፊልሞና ለሰዎች ግድ የሚለው ለእርሱ የሚጨነቅበቅዱሳን ሁሉ ዘንድ ፍቅር ያለው ሰው ነበር፡፡ እር ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በፍቅር የተሳሰረ ፣ ከተቀሩት ጋር ደግሞ አኩራፊ ዓይነት ሰው ሳይሆን ከቅዱሳን ሁሉ ጋር በፍቅር የሚኖር ሰው ነው፡፡ ይህ ፍቅር ደግሞ ለሰዎች ሁሉ ሸክም እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ ጳውሎስ ለፍልሞና ፍቅር እንደነበረው ከቁ.11-14 ያሳየናል፡፡ አናሲሞስ በእሥር ቤት ላለው ለጳውበጣም ስለሚያስፈልገው ከራሱ ጋር ቢያቆየው የማይወቀስበት ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛው፣ አናሲሞስ ገና ጌታን ሳያገኝ ከፊልሞና ኮብልሎ ሄዷል፡፡ ሁለተኛ ወንጌል መስክሮ  እንዲለወጥ ምክንያት ስለሆነው አሁን የወንጌል ልጁ ሆኖታል፡፡ ስለዚህ ቢያስቀረው ፊልሞናም ቢሆን ቅር ሊሰኝበት አይችልም፡፡ ይንጂ ጳውሎስ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የፍሞናን በመስቀደም አናሲሞስን ወደ ፊልሞና ላከው፡፡ ለእኔ ይልቅ የአንተ ይሻላል የሚል አቅም ያለው ክርስትና ያለው ሰው ነው፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔም ደስ የሚሰኝበትና የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት ሕይወት እንዲህ ዓይነቱ ነው፡
3. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ስለ እግዚአብሔር የሚያስብ ነው(4-5)፡፡
የእግዚአብሔር ክብርና ከእርሱ ጋር ያለን ሕብረት ግድ የሚለን ስንሆን የቅዱሳን ልብ ያርፋል፡፡ ጳውሎስ በዚህ ክፍል ስለ ፍልሞና እምነት ሰምቶ እግዚእብሔርን ያመሰግናል፡፡እምነት ሙ በሙሉ ለእግዚአብሔር ያንን መሰጠት መተማመን እንዲሁም በጌታችን በፍጹም ማረፋችንን የሚያመለክት ሲሆን እኛን ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኘናል፡፡ ፍቅር ደግ ከሰዎች ጋር ያገናኘናል፡፡ ፡ ፈልምና እነተኛ የሆነ እምነት የነበርውነና በእውነትም የተመሰከረለትም አማኝ ነው፡፡ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ጋር ያላቸውን ነገር የሚያላሹት ከእግዚአብሔር ጋራ ያላቸው ነገር መበላሸት ሲጀምር ነው፡፡ ብዙዎች ከእግዚአብሔርና ከወንድሞቻቸው ጋር ካላቸው ህብረት ይልቅ ለመድረካቸውና ለአገልጋይነት ስማቸው ትኩረት ይሰጣ፡፡ ከአሥር ዓመት በፊት ከአዲስ አባባ 400 ኪሎ ሜትር አካባቢ የምትገኝ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጀቺው ኮንፍራንስ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ሄድኩ፡፡ ጉባኤው በጣም ትልቅ በመሆኑ ጸሎት ቤቱ ስላልቻለ ፕሮግርሙ የተካሄደው በሜዳ ላይ ነበር፡፡ በዚያ ኮንፍራንስ መልእክት ካቀረብኩ በኋላ የንሰሐ ጥሪ ሳቀርብ አንድ ወጣት ሚስቱን እንደበደላትና ይቅርታ ሊጠይቃት እንደሚፈልግ ተናገረ፡፡ ስለዚህ ከቤተ ክርስቲያን መጋቢ ጋር በመሆን ሚስቱን አስጠራናትና ይቅርታ እንድታደርግለት ስንጠይቃት አባቴ ይህንን መስማት አለበት አለች፡፡ አባቷ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ስለሆነ ከሰዎች ጋር የነገውን ፕሮግራም በሚመለከት አንዳንድ ሥራዎችን እየሠራ ካለበት አስጠራነውና ጉዳዩን ሁሉ አጫወትነው፡፡ ልጅቷ ይቅርታ አድርጋ ወደ ትዳሯ የመመለስ ልብ ቢኖትም የአባቷ አቋም ግን ከጠበቅነው በላይ አስቸጋሪ ሆኖ ተገኘ፡፡ ልጅቱ ከባሏ ጋር በተፈጠረው ጊዜየያዊ አለመግባባት ምክንያ ካለችበት ትዳር ወጥታ ወደ አባቷ ቤት መታ እዛው ናት፡፡ ጉዳዩን ለማስተካካል በጣም ሰፊ ጊዜ ወሰደብን፡፡ ልጁን የበደለውን ሰው ይቅር እንዲል ደጋመን ብንለምነውና ብማጸነው አባትዬው በጭራሽ እምቢ አለ፡፡ በመጨረሻም ላይ እንዲህ ኣይነት ክርስቲና ይዘህ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ትሆን ስለማትችል አግደንሃል ሲሉት እንደዚህ ከሆነ እሺ እንዳላችሁት ይሁን አለ፡፡ ወጣቱ ባለትዳር ሚስቱን የዞ ቤቱ ቢገባም ይህ ሽማግሌ ስለ ክርስቲናውና እግዚአብሔር ስለሚጠብቅበት ኑሮ ሳይሆን የተጨነቀው ስለ ሽምግልናው መሆኑ የሁላቸንንም ልብ እንዳሳዘነ አስታውሳሁ፡፡
ዛሬም በእኛ ዘመን ስለ ስማቸውና ስለ መድረካቸው እንዲሁም በሰው ፊት ስለሚታየው አገልግሎታቸው እንጂ ስለማይታየው መንፈሳዊ ሕይወታቸውና የጌታ መንፈስ ከእነርሱ ስለሚፈልግባቸው ሕይወታቸው ግድ የማይላቸው ብዙ አገልጋዮችና መሪዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ፊልሞና ግን እንዲህ ዓይነት ሰው አይደለም፡፡ የሰሙትን ሁሉ የሚያስመሰግን እምነት ያለው ሰው ነው፡፡ አንዲህ ዓይነቱ ሕይወት እግዚአብሔርን ያስደስዋል ፣ የቅዱሳንንም ልብ ያሳርፋል፡፡
4. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፈው ስለ እውነተኛ ሕብረት የሚያሳስበው ነው፡( 6)፡፡
በጌታ ያለን አማኞች ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር እውነተኛ እምነትን የቅዱሳን ሕብረት እንደሚከተለው ነው፡፡ አንድነት፣የወንድማዊ ፍቅርና ሰላም የክርስትያንነታችን ምልክትና የሕይወታችን ክፍል ነው፡፡ ከሌሎች ጋር በምናሳልፍበት ወቅት ከሌሎች እንማራለን፣ እንታነጽባቸዋለንም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምንሄደው ስብከት ሰምተንና ተነቃቅትን ለመመለስ ብቻ ከሆነ ያ ሁኔታ እኛን ራስ ወዳዶች ያደርገናል፡፡ ይልቁንም ለሌሎች በረከት ለመሆን፣ ከእርሱም ጋር ለመተያየትና እርስ በእርሳችንም ለመልካም ሥራ እንድነነቃቃ ነው፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቤት የምንሄደው ለጋራ በረከት ነው፡፡ የወንድማችንን ሐዘን ሀዘናችን ደስታውንም ደስታችን ልናደርግ ነው ፡፡ የእኛንም ሸክም እነርሱ እንዲጋሩ ለማድረግ ጭምር እንጂ ተሰብከን፣ ወይም ሰብከን ወይም ዘምረን ወይም ለራሳችን በረከቱን አፍሰን ልንመጣ ብቻ አይደለም፡፡ ቅዱሳን ልብ የሚያርፈው ግን አንዳችን ከሌላው ጋር በሕብረት ስንተሳሰር ነው፡፡ በርካታ አገልጋዮች ሰዎች ሲጣሉ ደስ ይላቸዋል፡፡ እንዲያው ሰው ምን ይለናል ብለው እንጂ ዱላ ቢያቀብሉ የማይጠሉ አናካሾች አይጠፉም፡፡አንዲት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እርስ በርሳቸው ሲጨቃጨቁ አሁን ወደ እኛ ይመጣሉ ብለው የሚደሰቱ ቤተ ክርስያን አገልጋዮች ጥቂት አይደሉም፡፡ እነ ፊልሞና ግን ይህ አይነከካቸውም፡፡ ስለ ሕብረትና አንድነት የሚያስቡና የሚጨነቁ፣ የሚጠበቡም ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደዚህ ባሉት አገልጋዮች ሕይወትና አገልግሎት የቅዱሳን ልብ ያርፋል፡፡
5. የቅዱሳን ልብ የሚያርፍበት አገልጋይ ስለ መንፈሳዊ እውቀት የሚያሳስበው ነው( 6)፡፡ እውቀት ስንል ተራ መረጃ ሳይሆን ስለ እግዚአብሔር ያን ጥልቅ መረዳት ማለታችን ነው፡፡ የእግዚአብሐሔርን ነገር በጽንሰ አሳብ ደረጃ ማወቅናTheoretical knowledge በሕይወት ልምምድ ውስጥ ገብተን ማወቅ /experiential knowledge/ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ፅንሰ አሳብ በሆነው እውቀት ወደ ንስሐ አምልኮ፣ እንዲሁም ወደ ይቅርታ ሕይወት መድረስ አይቻልም፡፡ በአገራችን ሳለሁ በአውሮጳና በአሜሪካ እንዲሁም በሌሎች የምዕራብ አገሮች በየክረምቱ ስለሚወርደው በረዶ ከሚሰማው ነገር ተነስቼ ለሌሎችም ሰዎች አስረዳቸው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የተቆረቆሩ የፕሮቴስታንት አማኞች ቤተ ክርስቲያን ሕንጸዎች ጣሪያቸው ከመሀል ከፍ ያለና ዳርና ዳሩ ዝቅ ያለ ሲሆን ይህ አሠራር ምዕራባውያን በረዶው ሲወርድ ጣሪያው ላይ ተከምሮ እንዳይጎዳው እየተንሸራተተ እንዲወርድ አድርገው ስለሚሠሩት ሚሲዮናውያኑ ወደ አገራችን ሲመጡ ያንን የለመዱትን ዓይነት ቤት ስለሚሠሩ ነው የጸሎት ቤቶቸችን ሕንጻዎች ከሌላው የተለዩ የሚሆኑት ሲባል ስለ ሰማሁ እኔም ለብዙዎች የሰማሁትን ያንኑን አስረዳ ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ የማስረዳው በረዶውን በዓይኔ እንኳን ሳላየው ነበር፡፡ ከብዙ ጊዜያት በኋላ ወደ ሚቺጋን መጥቼ በረዶ ሲወርድ፣ ከተማውን ሁሉ ሲሸፍን፣ መንገዱን ሁሉ ሲዘጋ በቤቶች ሁሉ ጣሪያ ላይ ተከምሮ ከዚያ እየተንሸራተተ ሲወድቅ፣ መንገዱን ሁሉ ሸፍኖ ለመንዳት ሲያስቸግርና እያንዳንዱ የሚቺጋን ነዋሪ በወፋፈፍራም ልብሶች ተጀቡኖ ሲሄድ ሳይ ለበረዶ ያለኝ እውቀት የተለየ ሆነ፡፡ እንዲያውም እኔ በበረዶ ላይ ሲነዳና መኪናዬ መንገድ ስታ የወጣችበትን አጋጣሚ ሁሉ ሳስበው ሰው በመረጃ ብቻ የሚያውቀው እውቀት በሕይወት ልምድ ከሚያውቀው ምን ያህ የተለየ እንደሆነ በለጠ ተገነዘብኩ፡፡ ጳውሎስም ይህ የሕይወት ልምድ እውቀት እንዲበዛለት ለልሞና እንደሚጸልይለት ቃል ይገባለታል፡፡ ይህ ጥልቅ እውቀትና መረዳት አፓጎኒሲስ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ስለ እግዚአብሔርና በእኛ ውስጥ ስላለው መንፈሳዊ ነገር ጥልቅ የሆነ መረዳት a deep understanding about God and about what in us/ ማለታችን ነው፡፡ በእኛ ዘንድ እግዚአብሐየር ያቀመጠው በጣም ብዙ የሆነ መልካ ነገር አለ፡፡ ጌታ ኢየሱስን ካመንንበት ጊዜ ጀምሮ ከእርሱ በጣም ብዙ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ተቀብለናል፡፡ ይህንን እግዚአብሔርን አውቆ መከተልና አውቆም ማገልገል ሕይወታችንን ያሳድገዋል፤ በእግዚአብሔርም ላይ ያለን መተማመን ይጨምራል፡፡ በእኛ ዘንድ ያው ሁሉ በማወቅ የሚው አሳብ ል ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ እግዚአብሔር በእኛ ብዙ መልካም ነገሮችን አስቀምጧል፡፡ ከጌታ ያገናቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች ክርስቶስን ወደ ወቅ እንድንደርስ የሚያደርጉን ናቸው፡፡ ስለዚህ የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ በክርስቶስ ስላው እውቀት ግድ የሚለው ነው፡፡
6. የቅዱሳንን ልብ የሚያሳርፍ አገልጋይ ለክርስቶስ ክብር ግድ የሚለው ነው፡፡
ፍልሞና ሁሉንም ነገር ያደረገው ለክርስቶስ ነው፡፡ መንፈሳዊ ፍሬንም የሚያፈራው ለክርስቶስ ነው፡፡ ጳውሎስ በአንተ ያለው ነገር ለክርስቶስ ፍሬን እንዲያፈራ እለምናለሁ በማለት ለፍልሞና የሚጸልየውን የጸሎት ይዘት ይገጻል፡፡ በአገልግሎታችን ፍሬን ብናፈራ ያ ፍሬ ክርስቶስን ለማክበር መሆን አለበት፡፡ ሰዎችንም በአገልግሎታችን የምናዘጋጀው ለክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ በእኛ ሕይወትና ኑሮ በሚከብርብት ወቅት የምናገልግላቸውና አብረውን ጌታን የሚያመልኩ ሰዎች ልባቸው ያረፈ ይሆናሉ፡፡
ስለዚህ ጳውሎስ ይንን አንቀጽ ሲደመድም ልቤን አሳርፍልኝ ይላል፡፡ ዛሬም ሰዎች ተንቀዋል፣ ፈርተዋ፣ተረብሸዋል፣ ግራም ተጋብቷል፣ምእናንም በአገልጋችና በመሪዎች መካከል ካለው አላስፈላጊ ሽኩቻ የተነሳ ተንገላትተዋል፣ ከቦታ ወደ ቦታ ተንከራተዋል፣ ከአንዱ አበባ ተነስታ በሌላው ላይ እንደምትቀመጥ ከዚያም ተነስታ ወደሌላው አበባ እንደምትበር ንብ ተጉላልተዋል ፡፡  በንፈሳዊ ሕይወታቸው መጠንከር አልቻሉም፡፡ አማኞች ሥር መስደድ ሲጀምሩ መሪዎችና መድረክ ናፋቂ ሰባኪዎች ካሉበት ሥፍራ ያፈናቅሉአቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ በመንፈሳዊ ሕይወት መጭብርብር ውስጥ ገብተዋል ፣አያሌዎችም ለአውሬ ተጋልጠዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እኛ አገልጋዮች ስለ እነርሱ ግድ አላለንም፡፡ ስለዚህ ቆም ብለን በማሰብ የምዕመናኖቻችን ልብ ልናሳርፍ ይገባናል፡፡ ጳውሎስ ለፍልሞና የሚልከው ይህ መልእክት ለአገልጋች ሁል ማነቂያ ደወል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የቅዱሳንን ልብ ሚያሳርፈውን ማንነት እግዚአብሔር ይስጠን፡፡ አሜን፡፡








Thursday, April 9, 2015

የኢየሱስ ማኅተም
( የማንነታችን ምልክት )
                                                                                                                                     በፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1992 ..ገዳማ በምዕራቡ በአገራችን ክፍል አንድ በዓይነቱ የተለየ ወፍ ተገኘና መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት ንደተንከባከበው ይታወቃል፡፡ ይህንን ወፍ ልዩ የሚያደርገው ነገር መልኩ ብቻ ሳይሆን በአንገቱ ላይ ንጠለጠለው ታግ ወይም ምንነቱን የሚያሳይ ጽሑፍና ቁጥር ያለበት ካርድ መኖሩ ነው፡፡ የካከቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማሩት ሰዎች ይህንን በያዩበት ወቅት ይህ ወፍ ከየት አካባቢ እንደመንዴትስ እንደመ ጥናት ድረግ ነበረባቸውና ሲጠና በታጉ ላይ የተቀመጠው ጽሑፍ በዴች ቋንቋ የተጻፈ በመሆኑ ወፉ ከሆላንድ አገር መምጣቱ ታወቀና የኢትዮጵያ መንግሥት ከሆላንድ መንግሥት ጋር ግንኙነት በማድረግ ያንን ወፍ በአውሮፕላን አሳፍሮ ወደ አገሩ መመለሱ በኢትዮጵያ ዜና መነገሩን እናስውሳለን፡፡ ይህ ወፍ በአገራችን ካሉ በብዙ ሚሊዮን ከሚቆጠሩ ወፎች እንዲያውም በሌሎች በአገሮች የማይገኙ ከተባለትና አገራችንን የቱሪም መገኛ እንትባል ካደረጉ ብርቅዬ ወፎች ሁሉ ተለይቶ የሁሉን ትኩረት የሳበበት ምክንያት ምንድነው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ይህ ወፍ በአንገቱ ላይ የተንጠለጠለው ታግ ባይኖረውስ ኖሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ግምት ሰጥቶ ወደ ሆላንድ አገር ይመልሰዋል ማለት እንችል ይሆን፣ ምናልባት በዓይነቱ የተለየ ወፍ በአገራችን ተገኘ ተብሎ ከመወራት ያለፈ ነገር ሊደረግለት ባልቻለ ነበር፡፡ በተሸከመው ምልክት ምክንያት ያ ሁሉ እንክብካቤ ተደርጎለት ክብርም አግኝቶ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡
ይህ ለእኛ ለጌታ አገልጋዮችና ምዕመናን ሁሉ ልዩ ትምህርት ሊሰጥ የሚችል ምሳሌ ነው፡፡ የማንነታችን ማረጋገጫ ፣ ከሌላው የዓለም ሕዝብ የምንለይበት መለያ ምልክት ምንድነው፡፡ የጌታ የሱስ መሆናችን ተለይቶ የሚታወቀው በምንድነው፡፡ የሚያዩ ሁሉ የሚማረኩበት ኢየሱስን በእኛ የሚያዩት ስለ እኛ የሚመሰክሩበት ምልክታችን ምንድነው? ስብከታችን ወይስ ወደ ቤተክርስቲያን አውትረ መሄዳችን? በጉባኤ መገኘታችን ወይስ ብዙ መማራችን? ይህ ሁሉ አስፈላጊና መልካም ነው፡፡ ሰዎች ማን እንደሆኑና ከየት እንደሆኑ በምን ዓይነት ልምምድ ውስጥ እንዳሉ በሰውነታቸው የሚታዩና የሚለጠፉ ነገሮች፣ የተለበሱ ልብሶች ለይተው ያሳዩአቸዋል፡፡ ካህናት በሚብሱት ልብስ፣ ናዝራውያን በጸጉራቸው፣ ዜማውያን በልብሳቸው፣ የመንግስት ታማኝ ታደሮች በትከሻቸው ላይ ባለው የማዕሬግ ምልክቶቻቸው፣ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ ህንጸዎችም እንደዚሁ፣ ለምሳሌ ትምርት ቤቶች፣ መስጊዶች፣ ቤተክርስቲያናት ፣ የጦር ካምፖች፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ኬላዎች፣ ሆቴሎች በላያቸው በተተከለው ምልክት ምክንያት ምንነታቸውና ባለቤትነታቸው ተለይቶ ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛ የኢየሱስ ክርስቶስና ለእርሱ አልግሎት ራሳችንን የሰጠን መሆናችን የሚታወቅበት ምልክታችን ምንድነው?
ሓዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ በሥጋችን ስለ ምንሸከመውና ተለይተን ስለምንታወቅበት መለያችን በገላትያ 617፣ ሐዋ 9 10 -16፣ እና 2ቆሮ 411-16 ባሉ ክፍሎች እንዲህ ይላል፡፡ አነባለሁ የጌታችንን ቃል፡፡ ከጳውሎስ አጠቃላይ ትምህርቶች በአጭሩ የተወሰኑ ነጥችን እንመለከታለን፡፡
1. በሥጋችን የምንሸከመው የኢየሱስ ማህተም ነው፡፡
እኔ የኢሱስን ማህተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ፡፡
ይህ አንድ ዓረፍተ ነገር ነው ፣ ነገር ግን ትልቅ መንፈሳዊ ምሥጥር ያዘለ መልእክት ነው፡፡ አጭር አሳብ ነው ግን የጳውሎስን ሕይወት ከደህንነቱ እሰከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ያለውን ዓላማ ሁሉ ተቅልሎ በውስጡ የያዘ አሳብ ነው፡፡ የጳውሎስ ብቻ ሳይሆን የእኛን የሁላችንንም ሕይወት፣ አገልግሎት፣ ትምህርት ፣ ስብከት ፣ በምድር ላይ የምንኖርበትን የኑሮ ዓላማ ሁሉ የሚያሳየን አሳብ ነው፡፡ ያውም በሰውነታችን የምንሸከመው የማንነታችን መለያ ፡፡
ሐዋሪያው ጳውሎስ በገላትያ አውራጃዎች የጌታን ወንጌል ሰብኮ ቤተ ክርስቲያናትን ከተከለ በኋላ ሌሎች ሌላ ወንጌል የሚሰብኩ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ተነስተው ጳውሎስ እውነተኛ ሐዋሪያ ስላይደለ የሚሰብከው ስብከት ትክክል አልነበረም ብለው አስተማሩ:: ደህንነት የሚገኘው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በጸጋው ብቻ መሆኑን ያስተማረውን የጳውሎስን ስብከት በማጣጣል ደህንንት የሚገኘው ሕግን በመጠበቅ፣ በመገረዝና በመልካም ሥራ ነው በማለት ምዕመናንን ከእውነተኛው ትምህርት ዘውር አድርገዋል፡፡ ይህንን የነፋቄ ትምህርት ሲሞግት ከቆየ በኋላ የገላትያን መጽሐፍ ሲያጠቃልል እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያድክመኝ በማለት ይናገራል፡፡
ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ሓዋሪያ የመሆን፣ እውነተኛ ለመሆኔ ምንም ጥርጥር የሌለው በሥጋዬ የተሽከምኩት ምልክት አለኝ፡፡ ይህ ምልክት ሌሎች የኑፋቄ አስተማሪዎች የሌላቸው ምልክት ነው፡፡ ይህን ምልክት ጳውሎስ ማኀተም ብሎታል፡፡ ጳውሎስ ይህ ምልክት የኖረበት ምክንያት ምንድነው ለሚለው የተለያዩ ምክንያች ይኖራሉ፡፡ አንደኛው በልስጥራና በደርቤ ወንጌልን በሰበከበት ወቅት ተቃዋሚዎቹ ክፉኛ ከደበደቡት በኋላ ከከተማው ውጭ ጎትተው እንደጣሉት የገላትያ ሰዎቸ ራሳቸው ያውቃሉ፡፡ ጳውሎስ እንደዚያ የተደበደበው የወንጌል ስብከት ሥራውን በተቃውሞ ውስጥ በመስበክ ለኢየሱስ ያለውን ታማኝነት በመግለጹ ምክንያት የተደረሰበት ስለሆነ በድብደባው ምክንያት በሰውነቱ ላይ የተፈጠረውን ጠባሳ ማኅተም ብሏል፡፡ እንዲያውም እርሱ አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ ( 2 ቆሮ 12 ) እንዳለው ይህ ድርጊት በተፈጸመበት ወቅት በሰውነቱ ላይ ከግርፋቱ የተነሳ የከሰተው ጠባሳ ለሁሉም ሰው የሚታይ ሲሆን ያ ደግሞ ለጌታ ኢየሱስና ለወንጌል አገልግሎት ባለው መሰጠት ምክንያ የመጣበት ነው፡፡ ይህንን በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ማንም አያድክመኝ ይላል፡፡ እኛ የጌታ ታማኝ መሆናችንን ሰዎች ሁሉ እንዲያቁልን በዚህ ዘመን የግድ የግርፋትን ጠባሳና ገጣባ ለሰው ሁሉ በሚታይ የሰውነት ክፍላችን መኖር አይኖርብንም፡፡ ነገር ግን ማኅተም የሚለው ሌላ ቁልፍ አሳብ አለ፡፡ እርሱም ከማንም ጋር ድርድር የማናደርግበት የድንነታችን ጉዳይ ነው፡፡ በጌታ ያለንን ደህነንትና ሕይወት ማንም ይሁን የማንም ትምህርት እንዲያጎድፍብን አንፈቅድለትም፡፡ ይህ ማሕተም የጌታ የመሆናችን ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህንን በኤፌሶን 113-14 እንመለከታለን፡፡ ከምንም በላይ የደህንንታችንና ስደህንነታችን የሚሰጠው ትምህርት ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በምንም የሚለና ከምንም ጋር የምናወዳድረው አይደለም፡፡ ስለዚ ነው ጳውሎስ የጌታ የኢየሱስን ማኅተም ሥጋዬ ተሸክምአለሁና ማንም አያድክመኝ የሚለው፡፡ ማተም የባቤትነት ማረጋገጫ ነው፡፡ የማን እንደሆንን እና ለየትኛው ዜጋ እንደሆንን የማያን ሰዎች የሚለዩን በያዝው መታወቂያ ወይም በታታመበት ማሕተም ነው፡፡ የበግ ነጋዴዎች በጅላ ካጫኑቸው በጎች ውስጥ የየራሳቸውን በጎች ለይተው የሚያውቁት በበጎቹ ጀርባ ላይ በቀቡት የቀለም ማሕተም ነው፡፡ ለእኛ ደግሞ ለእግዚአብሔርና ለመንግሥቱ የተለየን መሆናችን የሚታወቅበት ትልቁ ማኅተማችን በሥጋችን የተሸከምነው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው፡፡
2.     የጌታችን የኢየሱስን ስም ነው(ሐዋ 910-16)
በደማስቆ ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀመዝሙር ነበር፣ ጌታም በራዕይ ሓናኒያ ሆይ አለው፡፡ እርሱም ጌታ ሆይ እነሆኝ አለ፡፡ ጌታም ተነስተህ ቅን ወደሚባለው መንገድ ሂድ በይሁዳም ቤት ሳውል የሚባል አንድ የጤርሴስ ሰው ፈልግ፡፡ እነሆ እርሱ ይጸልያልና ሓናንያ የሚሉት ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቷል አለው፡፡ ሐናንያ መልሶ ፣ ጌታ ሆይ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቻለሁ ፣ በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው አለ፡፡ ጌታም ይህ በአሕዛብም ፣ በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፣ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁ አለው፡፡
ጌታ ኢየሱስ ከጳውሎስ ምን ፈልጎ እንደጠራው ይህ አሳብ ይነግረናል፡፡ ጳውሎስ በአህዛብ አገሮች ቤተ ክርስቲያናትን ተክሏል፡፡ ብዙ ሰዎችን የጌታን ቃል አስተምሯል፡፡ እደነ ጢሞቴዎስ ያሉት ደመዛሙርትና የቤተ ክርስቲያን መጋቢያንን አፍርቷል፡፡ እንደምናየው ዛሬም ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት የሚሆኑ 13 የሚያህሉ መልእክቶችን ጽፎ አል፡፡ በተዘዋወረባቸው አገሮችና መንደሮች ሉ ተአምራቶችን ሁሉ አድርጓል፡፡ እነዚህ ሁሉ ሥራዎቹ የተጠቃለሉት በአህዛብም በነገሥታም፣ በእሥራኤልም ልጆች ፊት የጌታን ስም በመሸከም ውስጥ ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ልናደርጋቸው የተገባን ቢሆንም ከሁሉም በላይ የጌታን ስም የምንሸከምለት ዕቃው ንድንሆን ይፈለግብናል፡፡ ዛሬ አማኞች በምንኖርበት የክርስትና ሕይወታችን የጌታ የኢየሱስ ስም ከፍ ብሎ ይውለበለባል ወይስ ይሰደባል? መቅረዝ የሚባል ዕቃ አለ፡፡ ይህ መረዝ የሚባው ዕቃ በአድ ቤት ውስጥ መብራትን ከፍ አድርጎ የሚሻከም ነው፡፡ መቅረዙ መብራቱን ከፍ አድርጎ ሲሸከም መብራቱ ሲታ እርሱም አብሮ ይታያል፡፡ መብራቱ ካታየ ግን መረዙ ምንም ክብር ሊኖረው እንደማይች ሁሉ እኛም የኢየሱስን ስም ካተሸከምን ከክርስቶስ የሚጣውን ክብር ልናይ አንችልም፡፡ ወገኖቼ ሆይ ዛሬ ራሳችንን የጌታ ዕቃ አድርገን አቅርበናል ወይ? ክቡር ስሙን ለመሸከም የተመረጥን ዕቃዎች መሆናችንን አውቀን ስሙን እተሸከምን ነው ወይስ ራሳችንን እያወጅን ነው? በየቤተ ክርስቲያናችን መድረክ ኢየሱስ ይሰበካል? መድረክ ስንወርሰድ ሰዎች ኢየሱስን እንዲመለከቱ ስሙን እንዲጠሩ ፣ በስሙ እንዲታመኑ ፣ የኢየሱስ ብቻ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ ስሙን ከፍ እያወጅን ነው ወይስ የእኛ ስም እያወጅን ነው? ተሸካሚ ዕቃ ለራሱ አይኖርንም ለተሸከመለት ጉዳይ ይኖራል ምክንያቱም ዕቃ ነውና፡፡ የሚታየው እርሱ አይደለም ያ የተሸከመው እንጂ፡፡ ተሸካሚው ምንዜም ከታች እንጂ ከላይ ሊሆን አይችልም፡፡ እኛ ከታች ሆነን የጌታ ስም በእኛ ላይ ሆኖ ሰዎች ሁሉ ይህንን ስም በሰውነታችን፣ በሕይወታችን ፣ በአካሄዳችን አኗኗራችን ያዩታል ወይ?
3. የክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ነው( 2 ቆሮ. 4 7-16)
የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፡፡፡ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፣ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፣ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፣ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፡፡የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁል ጊዜ የኢየሱስን ሞት በሥጋችን ተሸክምን እንዞራለን፡
ይህን አሳብ ለመግለጸው ሐዋሪያው ጳውሎስ ከቀጥር 7 ጀምሮ በጣም አስደናቂ ነገር ይናገራል፡፡ በእኛ እግዚአብሔር የሚሠራው ሥራ የሚያስገርም መሆኑን ሲያመለክት  እንዲሁም ደግሞ አንድንም ነገር በራሳችን ብርታት እንዳላደረግነው እንድናውቅ ያሳስበናል፡፡ የኃይሉ ታላቅነት ከእኛ እንዳይደለ እንድናውቅ ያሳስበናል፡፡ በዓለም ላይ ብርቱዎች የተባሉ ብዙዎቸ እያሉ እግዚአብሔር አምላክ የክብር መዝገቡን ሸክላ በሆንንው በእኛ ውስጥ እንዳስቀመጠ ይናገራል፡፡ ሸክላ ምንም ክብር የሌለው ነገር ነው፡፡ በጣም ደካማ ነገር ነው፡፡ አንዴ ወድቆ ከተሰበረ መልሶ መጠገን የማይችል በጣም አሳዛኝ የሆነ ዕቃ ነው፡፡ ሸክላ ከአር የሚሠራ ነው፡፡ ሸክላ ደካማና አቅመ ብስ ነው፡፡ ሸክላ ብዙ ክብርም የሚሰጠው ነገር አይደለም እንዲም የሸክላ ዕቃ የሚሠሩ ሰዎችም ጭምር በሌሎች ዘንድ ክብር የማያገኙባቸው ብዙ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ግን የሚገርመው ነር ቢኖር ይህ ደካማ የሆነ ተሰባሪ ዕቃ ውድ የሆነውን ነገር ለመሸከምና በውስጡ ለመጠበቅ መመረጡ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በሸክላ ዕቃ ውስጥ ወርቃቸውን ይኖሩታል፣ ብራቸውን ያስቀምጡበታል፣ ጌጣቸውንም ይደብቁበታል፡፡ ሽካላ ዕቃ ተሰባሪና የተናቀ ደካማ ነው ግን በጣም ውድ ለሆነ አገልግሎት ይውላል፡፡ በጥንት ጊዜ የእግዚአብሔር ሰዎች በጣም አስፈላጊ የሆነ የብራና ጽሑፋቸውን መሸሸግ ባስፈለጋቸው ወቅት በእንሥራ ( በሸክላ ዕቃ) ውስጥ አድርገው በዋሻ ስለሸሸጉት ሰነዱ ሳይጠፋ ለዘመናት እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ዕቃው ሸክላ ነው ግን ለክቡር አገልግሎት ተፈለገ፡፡ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በኩል ባለው በረሀማ አካባቢ የኖሩ ኩምራን ሶሳይቲስ የተባሉ በሚኖሩበት ኩምራን  ዋሻ ውስጥ የተገኘው የሙት ባህር ጥቅል የተባለው ብራና የተገኘው በዋሻ ውስጥ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ታሽጎ ነበር፡፡ ይህ የሙት ባህር ጥቅል የተሰኘው ብራና ትክክለኛ የሆኑ ብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በውስጡ የያዘ የጥንት  ጽሑፍ ሲሆን ለበርካታ ዘመናት ተደብቆ የቆየውና ከመቃጠልና ከመውደም የተረፈው በሽክላ ዕቃ ውስጥ ነበር፡፡ በጊዜው የነበሩ ሰዎች ያንን ስክሮል ለመሸሸግ ለምን የሸክላ ዕቃ እንደመረጡት ባይገባኝም ግን ታሪኩ በጣም ያስደንቀኛል፡፡ ወገኖቼ ሆይ እግዚአብሔር አሁንም እያደረገ ያለው ይህን ነው፡፡ የእርሱን ታላቅ ሥራ በሚያምኑትና በማያምኑት ሁሉ ዘንድ ለማስፈጸም እኛን ደካሞችን፣ ሸክላዎችን፣ ተሰባሪዎችን መረጠና ክቡር መዝገቡን በእኛ ውስጥ አኖረው፡፡ ለምን? የእርሱ ሥራ በሰው ኃይል እንደማይከናወን ንዲወቅ ነው፡፡ ኃይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ እንዳይደለ እንዲታወቅ ነው፡፡ በዓለም ስንኖር ይህ የክብር መዝገብ እያለ በሁሉ እንገፋን፣ እናመነታለን፣ እንሰደዳለን፣ እንወድቃለን ይላል፡፡ ይን እንጂ አንጨነቅም፣ ተስፋ አንቆርጥም፣ አንጠፋም ይለናል፡፡ ምክንያቱም ጌታ በውስጣችን ላስቀመጠው መዝገቡ ስለሚጠነቀቅ ነው፡፡
ጳውሎስ ይህንን አስደናቂ ነገር ከተነናገረ በኋላ አሁንም በሥጋችን ስለምንሸከመው ጉዳይ ይናገራል፡፡ እንዲያው በሥጋችን የኢሱስን ሞትና ሕይወት ተሸክምን ንዞራለን፡፡ የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን ይላል፡፡ ወንጌልን በመስበካችን ምክንያት የተለያዩ መከራዎች ቢደርሱብንም እንደሚደርሱብን መከራዎች ብዛት መጠን አንጠፋም ምክንያቱም ለደካማው የሸክላ ዕቃ የእግዚአብሔር ርዳታ ስለማይለየው ነው፡፡ ከዚህም በላይ በመገፋት ፣ በማመንታት፣ እና በስደት ውስጥ በምናልፍበት ጊዜ ሁሉ እኛን በሚያዩን ሁሉ ፊት የኢየሱስ ሞት በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን፡፡ ይህንን የምናደርገው የኢየሱስ ትንሣኤ በሰዎች ሁ ዘንድ እንዲታወቅ ነው፡፡ በወንጌል አገልግሎታችን ምክንያት ለሞት አልፈን የምንሰጥ ቢመስለንም ግን የኢየሱስን ሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን ይላል፡፡ እንዞራለን ማለት ምን ማለት ነው በሚያዩን ሁሉ ዘንድ ፣ የምንመላሰው የኢሱስን ሞትና ትንሣኤ እያጅን ነው፡፡ የቤተ ክርሰቲያን በምድር የመኖሯ ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ለሁሉም ማወጅ ነው፡፡ እኛ ይህንን እድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
የቤተ ክርስቲያን ትልቁ ጥሪ የጌታችንን የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤ በዓለም ላይ ከፍ አድርጋ መሸከም ነው፡፡ የክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ መስበክ ከጳውሎስ በፊት ሆነ ከእርሱ በኋላ የነበሩ ነቢያትና ሐዋሪያት ቁልፍ ተግባርና የተልዕኮአቸው ማእከል እንደሆነ  ቅዱሳት መጸሕፍትን በምናነብበት ጊዜ የምናገኘው ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነቢይ የነበረው መጥመቁ ዮሐንስ ከኢየሱሰስ በፊት የመጣ ነበር፡፡ እርሱ መንግሥተ ሰማይ ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ እያለ ለንስሐ በውሃ እያጠመቀ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ በሰበከበት ወቅት አንድ ምቹ አጋጣሚ አግኝቶ ነበር፡፡ ያውም ሰዎች አንተ ማነህ ፣ መሲሁ ነህን? ኤልያስ ነህን፣ ኤርምያስ ነህን፣ ነቢዩ ነህ እያሉ ሲጠይቁት ሁሉንም አይደለሁም ነው ያላቸው፡፡ ስለራሳችን ዝና፣ ክብርና ሞገስ እንደምንኖረው የዛሬው ዘመን አገልጋዮች ቢሆን ኖሮ ስለ ራሱ ብዙ መናገርና ብዙ ክብር ማግኘት ይችል ነበር፡፡ ግን አይለደለሁም አለ፡፡ ታዲያ ማን ነህ ሲሉት እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፣ ከእኔ በኋላ የሚመጣው አጎንብሼ የእግሩን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔም የሚበረታ መንፈስ ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቃችሁ ነው አለ፡፡ ኢየሱስ ሲመጣ ኣይቶ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያወግድ የእግዚአብሔር በግ ብሎ ወደ ኢየሱስ አመለከተ፣ እንዲያውን እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባኛል ብሎ ክብርን ለኢየሱስ ሰጠ እንጂ ከራሱ ባገኘው አጋጣሚ ክብርን ሙገሳን አልወሰደም፡፡ ስለዚህ ከሴቶች ከሚወለዱት መጥመቁ ዮሀንስን የሚበልጥ የለም ተባለለት፡፡ ጌታ ሲከብር እርሱም አብሮ ከበረ፡፡
ሐዋሪያው ጳውሎስም አንደዚሁ ነው፡፡
የኢየሱስን መኅጸም በሥጋዬ ተሸክሜአሁ፣
ግሪኮች ጥበብን ይሻሉ፣አይሁዶች ምልክትን ይፈልጋለሉ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እሰብካለን፡፡
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነው
ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቆጥሬዋለሁ …. እርሱንና የትንሳኤውን ኃይል አውቅ ዘንድ ቢሆንልኝ በሞቱ እንኳ እመስለው ዘንድ እነፍቃለሁ
ከጌታችን ከኢየሱስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ራቅ አለ፡:
እኔ ክርስቶስን እንደሚመስል እናንተ ደግሞ እኔን ምሰሉ
በቆላስይስ መልእክት ብቻ ከ18ጊዜ በላይ ክርስቶስን የበላይነት ጠቅሷል፡፡
አንዳንድ ይወታቸው ለጌታ ያልታመኑ ሰችን ሲገልጽ ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉ የክርስቶስ ኢየሱስን ግን አይደለም፡፡ ፊል 221
18ኛው ክፍለ ዘመን የፑሪታን አባት ተብለው ሚጠሩ ዊሊያም ፔርክስ የተባሉ የሥነ መለኮት ሰው ትምህራቸውና የሕይወታቸው መፈክር ለክርስቶስ፣ በክርስቶሰ፣ ስለ ክርሰቶስ የሚል ነበር፡፡ በቅርቡ ከሁለት ዓመት በፊት ገዳማ ወደ ጌ የተጠሩት የእግዚአብሔር ሰው ጆን ሰቶትም ክርስቶስ ካተሰበከ ስብከቱ አልተሰበከም፡፡ ክርቶስ ካልዘመረ ዘማሪው መዝሙሩን አልዘመረውም፣ ክርስቶስና ስሙ ካታከሉበት ሎቱም አልተጸለየም ብለዋል፡፡
4. የጌታ የኢየሱስን መስቀል መሸከም፡፡ ማቴ. 1624-28፣ ሉቃስ 9 23-24
ሰዎች ጌታን እንደተቀበሉ መጀመሪያ የሚሰጣቸው ትምህርት የደቀመዝሙርነት ትምህርት ነው፡፡ ጌታ ማንም እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር መስቀሌን ይሸከም ያለውን ትምህርት አማኞች የው ጥምቅ እስክ ወስዱ ድረስ ብቻ ብቻ እናስተምራቸዋለን፡፡ ከዚያ በኋላ ላለው የክርስትን ሕይወት ዕድገት ደረጃዎች ውስጥ እንደማያስፈልገን አድርገን እንመለከተዋለን፡፡
ይሀን እንጂ የጌታን መስቀል መሸከም እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ የምንተገብረውና የማናቋርጠው ጉዳይ ነው፡፡ ክርስትና ደስ የሚል የሕይወት ጉዞ ቢሆን መስቀል የመሸከም ግዴታ ያለበት መሆኑ ደግሞ ሌላው ገጽታው ነው፡፡ በክርስትና ሕይወት ጦርነት ድል፣ ያለ መስዋዕትነት ክብር ፣ ያለመሰጠት በረከት የለበትም፡፡ ስለዚህ ክርስትና እንዴት ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚፈልግ እንደሆነ እንመለከታለን፡፡ ኢየሱስ  በዚህ ሥፍራ ምንም እኔን ለመከተል የሚወድ የሚወድ ቢኖር  የሚል ቃል ተጠቅሞአል፡፡ በሌላ ሥፍራ ደግሞ ከኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር አለ፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው; ማንም ክርስቲያን ሊሆን የሚፈልግ ማለቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ክርስትና የጥንት ስሙ መከተል ወይም መንገድ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በአንጾኪያ ክርስትና ከመባለቸወው በፊት ክርስትና መንገድ በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አማኞችም ደግሞ የመንገዱ ሰዎች ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ እኔን መከተል የሚወድ ወይን ከኋላዬ ሊመጣ የሚወድሲል ክርስትያን መሆን የሚወድ ወይም የሚፈልግ ማለቱ ነው፡፡ ክርስትና መሆን ደግሞ የአንድ ጊዜ ሞቅታ የሚያመጣው ሳይሆን ሁል ጊዜ የምንተገብረው ነው፡፡ የኢየሱስ ተከታይ መሆን ፣ የእርሱ ተማሪ መሆን  የክትትል ትምህርት ጨርሰን ወደ አገልግሎት መሥመር እስክንገባ ድረስ ብቻ የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ኢየሱስን የምንከተው ፣ በመንገዱም የምንራመደው በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ነው፡፡
እህግዲህ ይህ አሰብና እውነት ዛሬ ተረስቷል፡፡ አንዳንድ ጊዜ  ወደ አገልግሎት ደረጃ ከደረስን ምንም ከክርስትና አኗኗር እንደተመረቅን ይሰማናል፡፡ ግን የእግዚአብሔር ቃል መስቀሉን መሸከም ያለብን በየዕለቱ እንደሆነ ይነገረናል፡፡ በየዕለቱ እንምንዘምረውና እንደምናገልግለው ሁሉ በየዕለቱ የጌታን መስቀል እንሽከማለን ማለት ነው፡፡ መስቀሉን ሳይሸከሙ በኢየሱሰስም ንገድ ሳይሄዱበት የሚያገልገልሉት አገልግሎት ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም ለምዕመናንም አይጠቅምም፡፡ በኢየሱስ መንገድ ሳይሄዱበት የሚደረገው አገልግት፣ ዘማሪነት፣ ሰባኪነት፣ አስተማሪነት፣ መሪነት ሁሉ  ለቤተከርስቲን እጅግ በጣም ጠንቅ ነው፡፡ የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ትለቁ ችግር የአገልጋዮችና የመሪዎች ችግር ሳሆን በሕይወታቸው ጌታን የማይከተሉ አገልጋዮችና መሪዎች የተበራከቱ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ለመሆኑ በሕይወታቸው ኢየሱስን የማይተሉ መሪዎችና አገልጋዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እናውቃለንን;
የኢየሱስ መሆናችንና በመንገዱ የመሄዳችን ትልቁ መሥፈርት አንዱ ራስን መካድ ነው፡፡ ራሳችን ካልካድን የእርሱን መንገድ መምረጥ እንችልም፡፡ ሰው ወደ ጌታ ሲመጣ ራሱን ሲክድ ብቻ ነው ኢየሱስ በልቡ የሚነግሰው፡፡ ሰዎች ክርስትያኖች አንዲሆኑ እናስተምራቸውና ራሳቸውን እንዲክዱ ስላላገዝናቸው ማነታቸውና እነርሱነታቸው በውስጣቸው ይኖራል ፣ ሲያድጉም ያ እኔነታቸው አብሮ እያደገ እየጎመሰ ይሄድና የክርስቶስን ቦታ ይይዝባቸዋል፡ ከዚህ የተነሳ በሕይወታቸው ጌታን ሌለሎች ማሳየት ያቅታዋል፡፡ ምክንያቱም በልባቸው ዙፋን ላይ ፣ በሕይወታቸው የውስጠኛው ክፍ ላይ ቦታውን የያዘውና የሞላው ጌታ ኢየሱስ ሳይሆን እኔነቻው ነው፡፡ እኔን አወድሱኝ የሚሉ መጋቢዎች ገጥሞአችሁ አያውቁም; እኔ ነኝና ባለመፍትሔው እኔን ብቻ የሚሉ አገልጋዮች ገጥሞአችሁ አያውቁምእነዚህ ራስን ያለመካድ  ችግር ተጠቂዎች ናቸው ማለት ነው፡፡ ራሳችንን በካድን ጊዜ እኛ ሳንሆን እገዚአብሔር ብቻ ሕይወታችንን ሊያድን እንደሚችል አውቀን ራሳችንን በእርሱ እጅ ላይ ወደምንጥልበት የአቅም ደረጃ እናድጋለን ማለት ነው፡፡ ስላራችንን ያለንን የተሳሳተ ግምት ትተን ፣ ሰይጣንም የሚሰጠንን ፍቅር ሁሉ ወደ ጎን በመተው በክርስቶስ ፍቅር ወደምንታሰርበት ካፓሲቲ እያደግን እንሄዳን ማለት ነው፡፡ በአንጸሩመ ደግሞ ራሳችንን ወደ ማገሱና መሸሙ ደረጃ በደረሽን ቁጥር ጌታን ከልባችን ዙፋንና የክብር ሥፍራ ወደ ማውረዱ ደረጃ እየተሸጋርን እሄዳለን ማለት ነው፡፡ ሰዎች የእግዚአብሔር ነገር እንደተወሰደባቸው ከሚታወቅበት መንገድ አንዱ እኔ እኔ እኔ ሲሉ ነው፡፡ በእኔነት የተሞላው ሰው ጌታ ኢየሱስን ለሌሎች ማሳየት አይችልም ምክንያቱም ሰው በውስጡ ከሞላው ነገር ያፈሳልና፡፡
ሁለተኛው መሥፈርት ፈቃደኝነት ነው፡፡ የሚወድ ቢኖር ( የሚፈልግ ቢኖር) የሚለው አሳብ በጣም አስፈላጊ ቃል ነው፡፡ ሁሉም ነገር በራስ ውሳኔ በፈቀደኝነትና በፍቅር ነው፡፡ ይህ ማኛውንም ነገርለማድረግ የሚያስችለን ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔርም ሆነ ሰይጣንም የራሳቸውን መንገድ እንድንከተለ የሚያደርጉን በፍቅር ነው፡፡ ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ የእርሱ ተለታች የሚየደርገን በፍቅር ነው፡፡ ሰጣን ደግሞ የራሱ ተከታዮች የሚያደርገን ፍቅርን በማሳየት ነው፡፡ ሰይጣን ፍቅርን የገለጠበት መንገድ ኢየሱሰስ ፍቅርን ከገለጠበት መንገድ ይለያል፡፡ ይህንን ነው አማኞች መለየትና መንቃት ያቃተን፡፡ ኢየሱስ ምክንያታዊ ባልሆነ ፍጹም ፍቅር ወደደን፡፡ እኛን አብልጦ ከመውደዱ የተነሳ ክቡር ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ክቡር ደሙንም ስለ እኛ አፈሰሰልን፡፡ ሰይጣን ደግሞ ፍቅር የገለጠው  ሰዎች ብቻ አፍቃሪዎች እንዲሆኑ በማድረግ ነው፡፡ የገንዘብ አፍቃሪዎች፣ የክብር አፍቃሪዎች፣ የዝሙት አፍቃሪዎች፣ የዚህ ዓለም አፍቃሪዎች ፣ የዘር የወገን አፍቃሪዎች፣ የመጠጥ የሲጋራ የጫት ፣ ተድላ ወዘተ አፍቃሪዎች እንዲሆን ያደርግና ጌታ የሚያፈቅሩበትን አቅም ይወስድባቸዋል፡፡ እዚያ ውስጥ ግን ሳይታወቅ እየተወደደ ያለው እርሱ እንደሆነ ማንም ላያስተውል ይችላል፡፡ ለሰዎች ደግሞ የሚያምራቸው መንገድ ሰይጣን የገለጠው መንገድ ነው፡፡ ስዚህ መከራን ፣ ችግርን፣ ስዴትን ልፋትንና መንፈሳዊ ጦርነትን እንዲሁም መስዋዕትነትን የሚጠይቀውን የኢሱስን መንገድ ለጊዜውም ዞር አድርገው ይሕንን በጣም ማራኪና ናፋቂ የሆነ ልፈትና እንግልት የሌለበትን የፍቅረር መንገድ መከተል ይላቸዋል፡፡
ሌላው እንግዲህ መስቀሉን መሸከም ነው፡፡ ምንድነው መስቀሉ;  መስቀል የመሸከም ጉዳይ ብዙ ጊዜ የማይገባን ምስጥር ይሆንብናል፡፡ ሌላው ቀርቶ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትም ቢሆኑ ግር ሳይላቸው አልቀረም ምክንያቱም ኢየሱስ መስቀሉን ማይሰከም ለእኔ ሊሆን አይችልም ሲል ገና በመስቀል አልተሰቀለም ነበርና፡፡ ይሁን እንጂ በጊዜው ከኢየሱስ በፊት በመስቀል ላይ የተሰቀሉ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ ለመምጣቱ ምናልባት 120 ዓመታት በፊት ኢንተርተስታሜንት ፒሬድ ተብሎ በሚታወቅው ጊዜ አንቲክዮስ ኤፒፓኔስ በግሪክ መንግሥት ሥልጣን ጊዜ በርካታ አይሁዶችን  በእንጨት ላይ ሰቅሎ ገድሎአቸዋል፡፡ ደግሞ  የሮማውያን ንጉሥ ታላቁ  ሄሮዲስ 2000 አይሁዶችን ሰቅሎአቸዋል፡፡ በኢየሱስ የምድር አገልግሎት  ጊዜ  ሥቅላት በግሪክ፣ በሮማውያን፣ በመካካላኛው ምሥራቅ በግብጾችም ዘንድ በጣ የተለመደ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች 30.000 አይሁድ በስቅላት ተገድለል የሚል ግምት አላቸው፡፡ ይህንን ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ያውቃሉ፡፡ ቢሆንም ኢየሱስ የሚለው ከባድ ሊሆንባቸዋል፡፡ እንዲህ ኢየሱስን መከተል እና የክርስትና ሕይወት መኖር ምን ዓይነት ከባድ እንደ ነበረ የሚያሳይ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ብዙ ሰዎች የመስቀልን ከቁሳዊ ገጽታ በላይ ባለፈ ማየት የሚሳነን ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ ግን መስቀልን መሸከም ስንል ምን ማለታችን ነው› የክርስትናችን ምልክት ነው አይደለም;፡፡ በደረት ኪሳችን ላይ የምናስቀምጠው፣ በቤተክርስትያናችን ሕንጻ ላይ የምንተክለው፣ በአንገት ብላችን ላይ የምናሳትመው፣ ሌላ ሌላም፡፡ አዎን ውነት ነው ግን በልባችን የሚሳውም እርሱ ሊሆን ይገባዋል፡፡ መስቀሉ ለእኛ ምን ያሳየናል;  ጌታ ኢየሱስ በሄደባቸው መንገዶች ሁሉ ለመሄድ ራችንን የሰጠንበት ሕይወት ተሞክሮ አይደለምን ; ክርስትና እኮ ኢየሱስ የኖረበትን ሕይወት ለመኖር በመወሰን ራሳችንን የምንሰጥበት መርህ ነው፡፡ ይህ መርህ ማቴ 1024 ላይ እንደተቀመጠው ባሪያው እንደ ጌታው ደቀመዝሙሩ እንደ መምህሩ የሚሆኑበት የሕይወት መርህ ነው፡፡ እኛ ኢየሱስስን ለመከተል ስንል ሕይወታችንንና እኛነታችንን ለእርሱ የምንሰጥበት የሕይወት መርህ ነው፡፡
ከዚህም በላይ ጌታ ኢየሱስ ስለ እኛ መከራን የተቀበለበትን፣ የተዋረደበትን፣ የተንገላታበትን የሚያሳይን ነው፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ተወረዶ እኔን ያስከበረበትን፣ የእኔን ነፍስ ሊያረካት ተጠማሁ ያለበትን፣ የእኔን እጅና እግር ለክብሩ ለመማረክ እጅና እግሩን የተቸነከረበትን፣ እኔን ከአብ ጋር ሊያስታርቀኝ እርሱ በአባቱ የተራሳበትንና አባቴ አባቴ ሰልምን ተውከኝ ያለበትን ፣ የእኔን ቁስል ለመፈወስ እርሱ ጀርባው በሮማውያን መጥፎ ጅራፍ አለንገጋ የተተለተከበትን ፣ እኔን የእግዚአብሔር፣ የሰውና የራሴ ጠላት የሆንኩትን ሰው የእርቅና የሰላም ሰው ለማድረግ የሚያደርጉትን አየውቅምና ይቅር በላቸው ብሎ የተማጠነበትንና ያማለደበትን ያንን የክርስቶስን መስቀል በሥጋዬና በነፍሴ ተሸክሜአለሁ፡፡ እንግዲህ ይህንን በሕይወታችን በምንተግብርበት ጊዜ የማነታትችን መለያለሁሉም ያወቃል ማለት ነው፡፡
5. የጌታ የኢየሱስ ቀንበር መሸከም( ማቴ 1129-31)
እኛ የኢየሱስ መሆናችን ከሚታወቅበት መንፈሳዊ ገጽታዎቻችን አንዱ ቀንበር መሸከም ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ብዙ ሰው በክርስትና ሕይወቱ መስቀል ስለመሸከም ይሰማል ቀንበር መሸከም የሚባል ነገር እንዳለ አያውቅም፡፡ ብዙዎቻችን የመስቀል ምልክት አለን ግን የቀንበር ምልክት የለንምምክንያቱም ቀንበርን ስለመሸከም ብዙም ትኩረት ስላለሰጠን ነው፡፡ መስቀልምን መሸከም ያልቻለ ነው ቀንበርንም መሸከም ሊከብድበት ይችላልና፡፡ ምክንያቱም መስቀል ወደ ክርስትና ሕየወታችን ከገባንበት ቀን ጀምሮ የምለማደው ስለሆነ ቀንበር ወደምንሸከምበት ሁኔታ ስንደርስ ቀላል ይሆናል፡፡ መስቀልን መሸከም ያልተለማመደ ሰው ቀንቡም የዚያሀውኑ ያህል ሊከብደው ይችላል፡፡ ግን መሸከም ማን ማለት ነው፡፡ አይሁዶች ቀንበር የሚለውን ቃል የሚወስዱት በአንድ ነገር ውስጥ ለመግባት ራስን ከመስጠት ጋር በማያያዝ ነው( ሳሚሺን) ፡፡ በሐዋሪት ዘመን መሪዎቻቸው ሕዝቡ ሊሸከሙ የማይወዱትን ቀንበር ( ግዴታ) በትከሻው ላይ ይጭኑባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም የሮማውያን አገዛዝና ሥልጣን በሕዝቡ የተወደደ ሳይሆን በግድ ተብሎ የተጫነ ቀንበርና እሥራት ነበር፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ ለሕዝቡ ቀንበሩን እሰብራሁ እያለ ተስፋ ይሰጣቸው የነበረው፡፡ መጥፎ ቀንበር፣ የባርነት ቀንበር፣ የጭቆና ቀንበር  ተጭኖባቸው ስለነበር ሕዘቡ ወደ እግዚአብሄር በጮኹ ጊዜ እገዚአብሔር ቀንበሩን  ከትከሻቸው እንሚሰብር ተናረ፣ ያም ቀንበር ደግሞ በጌታ በኢየሱስ ስም ተሰብሮልናል፡፡
ኢሱስ በማጣ ጊዜ ወደ እርሱ የሚመጡትን ቀንበር እንዲሸከሙ ጥሪ አድርጎላቸዋል፡፡ ይህንን ያደረገው ግን በሕይወታቸው ያለውን ከባዱን ቀንበር ሁሉ ከሰበረ በኋላ ነው፡፡ በነፍሳቸውም ያለውን ቀንበርና ሸክም ሁሉ ካወረደላቸው በኋላ ነው፡፡ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ ብሎ ነው፡፡ የእናንተን መጥፎ ሸክም እኔ አነሳለሁ እናንተ ግን የኔን ቀላልና እረፍት የሚሰጠውን ሸክም የሆነውን ቀንበር በላያችሁ ተሸከሙ ይለናል፡፡  ልክ እንደመስቀሉም ሁሉ ቀንርም ከእንጨት የሚሠራ መሣሪያ ነው፡፡
ቀንበር ለኃላፊነት የምንሰጥበት መንገድ ነው፡፡ ቀንበር የሚሠራውም በሰለጠኑ አናጢዎች እንስሳውን በማይጎዳ መልክ ተለክቶ የሚሠራ ነው፡፡ ከዚያ ቀንበር ሥር የሚሆነው በሬ ሞፈሩን ለመጎተት፣ በገበሬውም ትልም ለመመራት፣ ትልሙንም የመቅደድ ኃላፊነቱን ለመቀበል አቅመ ቢስ ከሆነው ገበሬ እጅ ሥር ራሱን አስገዝቶ በቀንበሩ ላይ ባለው ማነቆ ይተሰራል፡፡  እንደዚሁም ሁሉ የጌታን ሥራ ለመስራት የአገልግሎትንም ኃላፊነት ለመቀበል በፈቃዳችን ራሳችንና ሁለንተናችንን ለጌታ ለኢየሱስ መስጠታችንን የሚያመላት ነው፡፡ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ የሚለው ቃል፡፡
በኢሱስ ጊዜ ለቀንበር የሚሰጠው ሌላው ምሥል ደግሞ መማር ነው፡፡ ተማሪው ሁሉ ጊዜ በራሱ ውዴታ ከመምህሩ ለመማር ይመጣል እንጂ ተማሪ አስገድዶ የሚያስተምር አስተማሪ በፍጹም የለም፣ አይኖርምም፡፡ ስለዚህ አይዶች ቀንበርን ምን ይሉታል የህግ ቀንበር፣ ቶራህ ቀንበር፣የትዕዛዝ ( ኮማድሜንት)ቀንበር፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የእግዚአብሔር ቀንበር ብለው ይጠሩታል፡፡  ጌታ ኢየሱሰስም ያኑትን የሚጠይቃቸው አንዱ ጥያቄ ይህ ነው፡፡ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ( ከእኔ ተማሩ ) ይላቸዋል፡፡ የእርሱን ቀንበር መሸከምና ከእርሱ መማር ለት ምን ማለት ነው፡፡ ለእርሱ አመራር፣ ትምህርት ሥልጣን ራሳችንን መስጠት ማለት ነው፡፡  ይህ መታዘዝን የሚያሳይ ቀንበር ነው፡፡ ይህ ቀንበር በክርስትና ሕይወታችን ስንኖር ይንጨነቅበትና የምንጠበብበት ሳይን እፎይ የምንልበት ነው፡፡ ለጌታ ታዘዝና ራሳችንን ለእርሱ መስጠት እረፍትን የሚሰጥ ነው፡፡ ሸክማችሁን ወደ እኔ አምጡ እኔ አሳርፋችኀዋለሁ ብሎ እዳሳረፈ ሁሉ ቀንበሩንም ስንከም ነፍሳችንን ያሳርፋታ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ለነፍሳችሁ እረፍትን ታችሁ የሚለን::
ኢየሱስን ቀንበር የመሸከም ሌላው ምስጥር ደግሞ ትብብር ነው፡፡ ከእንዱ ከሌላው ጋር በሕብረት መዋሄድን የሚያመለክት ነው፡፡ ቀንበር በአንድ በሬ ትከሻ ብቻ አይጫንም፡፡ ሁለት በሬዎች ናቸው የሚገትቱት፡፡ የበሬዎቹ ትክለ ቁና፣ እድመሜ ፣ ጉልበት፣ ልምድ፣ ባሕሪያ ወዘተ የተለያየ ሊሆን ይችላ፡፡ እነዚህ የተለያዩ በሬዎችን በአንድ ሥራ ላይ የሚያሰማረው ቀንበሩ ነው፡፡ሁለቱ በቀንበር ሥራ ሆነው አንዳቸው ለሌላው ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሲሰጡ በእነርሱ ላይ ጌታ የሆነው የገነሬው ሥራ ወይም እርሻው በተሳካ ሁኔታ ይታረሳል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከሁለቱ በሬዎች አንዱ እምቢ ያለ እንደሆነ እርሻው ሳይታረስ ሊከርም ይችላል ከቀንበር ምስጥር ይንማረው አንዱ ይህን ነው፡፡ ጌታ ቀንበሬን በላይችሁ ተሸከሙ ሲለን በእግዚአሔር እርሻ ላይ ለመሰማራት አንዳችን ለሌላችን ራሳችን ዝቅ ማድረግን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ከባድ ሆኖብናል፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አሁንም ይህንን እንድናደርግ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ወንድሞችና እህቶች ሆይ ይህ ታላቅ ምስጥር ነው፡፡ ትልቅ በረከት ያለበት ነው፡፡ ለወንጌላውያን አብያተክርስትያና አገልጋዮች ዘንድ ትልቅ ፈተና የሆነብን ይህ ነው፡፡ ሸክማችንን በኢየሱስ አጠገብ ላመስቀመጥና ለማረፍ በጣ እንመኛለን ግን የእርሱን ቀንበር በሸከም የሚገኘው የነፍስ እረፍት ለማወቅ አልቻልንም፡፡ ሐዋሪው ጳውሎስ ማን ባልንጀራው ከእርሱ እንዲሻል ይቁጠር የሚለው ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስም እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ ብሏል፡፡ ሰዎች እኛ የኢሱስ መሆናችንን የሚያቁብ መንገድ ወይም መለያ ምልክታችን የእርስ በርስ ፍቅር ነው
6. የቅዱሳንን ሸክም መሸከም ( ገላትያ 625)
የቅዱሳንን  ሸክም መሸከም ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ይህ እንዲገባን ዕብራውያን 131-3 ፣ እና ሮሜ 129-16 ያለውን  ማበቡ የተሸለ ነው፡፡ የታሠሩ ሰዎች ሲኖሩ እናንተም ከእነርሱ ጋር በእሥር ቤት እንዳላችሁ አድርጋችሁ ራሳችሁን ተመልከቱ፡፡ ከጌታ ከኢየሱስ ትምህርትና ከመጀመሪያዋ የኢየሩሳሌም ቤከርስቲያን ተግባራዊ አኗኗር የምንማረው አስደናቂ ነገር ቢኖር አንዱ የከመንፈስ ቅዱስ ሌላውን ሸክም መሸከም ነው፡፡ የሐዋሪያትን ስራ 4ን በምመለከትበት ወቅት በበዓለ ሃምሳ ቀን የተከሰተውን የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ተከትሎ በሕይወታቸወ ከታየው አስደናቂ ነገር አንዱ የእርስ በርስ ሸክም መሸካካም ነበር፡፡ አንድም ደሀ በመካላቸው አንዳይኖር ያላቸውን ሁሉ እያመጡ በሐዋሪያት እግር ሥር ያስቀምጡ ነበር፡፡ ለሁሉም እንሚያስፈልጋቸው ያካፍሉ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የአይሁድ እምነት ወይም የሀይኖት መሪዎች የነበሩ ፈሪሳውያ ደሀዎችን ቤት ፣ የመበለቶችን ቤቶስ ሲበዘብዙ ኣና ሲበሉአቸው ደቀመዛሙርቱና የኢየሩሳኬም ቤተክርስቲያን አማኞች ደግሞ ያቻውን ንብረትን ጥሪት በመሸጥና ወደ ሐዋሪያት በማምጣት ደሀዎችንኛ የተቸገሩትን ይደግፉአቸው ነበር፡፡ ይንን በማደረጋቸው በፈሪሳውያንኛ በመንደፍስ ቅዱስ አማካይነት በሚደረገው እወውነተኛ ርስትና መካካል የሚኖረውን ልዩነት በግልጽ ለማሳየት ችለዋል፡፡ በመከራና በችግር ውስጥ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ገንዘብ አዋጥተው ይሰጡ ነበር፡፡ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ስለ ተረፋቸው ሳይሆን ከድህነታቸው ጥልቀት ሁሉ የኢየሱሰስን ቸር ላጋስነት በተግባራቸው ይገልጡት ነበር፡፡ ይህ ዓይነት ሕይወተወ ለሁላችንም የሚያስፈልግ ነው፡፡፡
ከዕብራውያ ትምህርት እንደምንመለከተው  በክርስቶስ የሆነው ወንድማችን ቢታሠር ያ እሥራት የእኛም ነው ማለት ይኖርባቸዋል፡ የታመመውን ሲያይ ያንን ሕመም አብራችሁ ልትታመሙ ይገባቸዋል፡፡ ይህ የክርስቶስ የመሆናችን መለያ ነው፡፡ የጥንታቤተ ክርስቲያን የምትታወቀው በዚህ ነው፡፡
በወንገጌው ያን አብያተ ክርስቲናት ዘንድ ይህ እነደቀድሞዎቹ ሕዝቦች መሆን እጅግ የተሳነን ጊዜ ቢሆን አሁን ነው፡፡ ዛሬ አንገታቸው እየተቀላባቸው ወገኖች ጉዳይ ፣ የቤተሰባቸው ልቅሶና ሰቆቃ እኛን ለየገነበግብ ይገባናል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በየሰምንቱና በየቀኑ የሚቃጠሉ ቤተ ክርስቲያናት የእኛ ናቸው ፣ እኔ የማመልክባት ቤተ ክርስቲያን ነው የተቃጠለው ማለት ወደምንችልበት የአቅም ደረጃ ከፍ ማለት ይኖርብናል፡፡ ስግብግብነት በጣም አደገኛ እሥራት ነው፡፡ በመካከላችሁ የተቸገሩትን ገልጋዮቻችሁን፣ እህቶቸችሁን ፣ የቤተከርስቲያን አባቶች ፣ የተራቡ በእሥራት ያሉትን በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ ሰዎች አንገታቸው በክርስትና ምክንያት እየተቀላ ነው፡፡ እነዚያን ከብባችን ልናስብ ይገባናል፡፡ ብዙ ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ ነው፡፡ የእኔ ቤተ ክርስትያን እደተቃተለ በማሰብ በእግብሔር ፊት አብረን ልናለቅስ ይገባናለ ይህ ሁሉ የክርስቶስ የመሆናችን ምልክት ስለሆን በዚህ ልንተጋ ይገባናል፡፡
የክርስቶስ የመሆናችን ምልክት. የማነታችንና  የምነታችን መለያ ፡፡







Wednesday, March 25, 2015

የፓስተሩ በወሲብ መፈተንና የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ እወጃ

የአደጋውን መንስኤ ካወቅን ጉዳተኞችን እናድናቸው
የምንኖርባት ምድር በርካታ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎችን እንደምታስተናግድ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ በየብስ የሚሽከረከሩ፣በባሕር ላይ የሚጓዙና በአየር የሚበሩ መጓጓዣዎች አንዴ በሚከሰትባቸው አደጋ ከፍተኛ የሕይወትና የንብረት ውድመት ይደርስባቸዋል፡፡ አንድ አደጋ ሲከሰት ኃላፊነት የሚመለከታቸው አካላት አደጋው የተከሰበትን ጊዜ፣ ቦታ፣ የደረሰውን አካላዊና ቁሳዊ ጉዳት፣ የአደጋውን መንስኤዎችና ወዘተ ይመረምራሉ፡፡ በሥራ ላይም ሆነ በሰው ሆን ተብሎ በሚደረጉ ወንጀሎች ምክንያት በተከሰተው አደጋ የጠፋውን ንብረት ፣ የአደጋውን ሁኔታ፣ ወዘተ ከመተንተን ይልቅ ቢቻል አደጋው እንዳይከሰት ማድረግ ለሁሉም ዋስትና ሊሰጥ እንደሚችል የሚታመን ነው፡፡ ግን እንዲህ አይነቱ በራሱ የሚቻል አይደለም፡፡ ለምሳሌ የመኪና አደጋ መከላከያ የለውም፡፡ አውሮፕላን እንዳይከሰከስ የሚያደርግ መከላከያ የለም፡፡ ከአዳገው የተረፉትንና የተጎዱትን መርዳት ግን ከምንም ይልቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው፡፡
ይህንን አሳብ ያነሳሁት ስለ ሰው ሠራሽና ተፍሮአዊ አደጋ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ሳይሆን ቤተክርስቲያናችን እየደረሰባት ስላለው መንፈሳዊ አደጋ ትንሽ ለማውጋት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተከርስቲያን በትልቅ አደጋ እየተመታች መሆኑዋን አላወቅሁም የሚል ካለ ከባድ እንቅልፍ አሽልቦታል፣ ወይም ከነአካተው በሞት ጣር ውስጥ ነው ያለው፡፡ እኛ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ቤተ ክርስቲያናችንን አደጋ እያጠቃት እንደሆነ ካላወቅን በአደጋው ምክንያት ሁሉም ነገር ወደ ፈርስራሽ እስክለውጥ ሊገባን አይችልም፡፡ ዋና ትኩረቴ ይህ ሁሉም ሳይሆን በቅርቡ በራሳቸውና በሰው ትዳር ላይ መማገጣቸው በአሜሪካን ድምፅ ራዲዮ ከተነገረ በኋላ የኢትዮጵያውያን ልብ የሰበረ ወገኖቻችን ጉዳይ መነሻ በማድረግ የተደቀነብንን የውድቀት አደጋ ለመጠቆም ነው፡፡ የማናውቀውን አዲስ ነገረ- ጉዳይ ማውሳቴ አይደለም ግን እንደገና እንድናስብበት ብዬ ነው፡፡ ይህንን አደጋ ያልኩበት ምክንያት ከዚህ በፊት ሆኖ የማያውቅ እንግዳ ነገር በድንገት ስለ ወደቀብን ሳይሆን በየጓዳው እግዚአብሔር የመጠቀምባቸው አገልጋዮችን እየጠለፈ የሚጥል የኃጢአት ገመድ መጠኑን እየጨመረና ባሕሪዩን እየለዋወጠ ስለሚሄድ ነው፡፡ ሰዎች በኃጢአት ሲወድቁ ያለ ልክ የሚኮንኑና ያለገደብም የሚያበረታቱ የጽንፈኞች ተግባር የባሰ ሌላ አደጋ የሚጨምርብን ሆኖ ስለታየኝም ነው፡፡
ፓስተር ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ቢያንስ ሁለት ሀይማኖታዊ ማዕረጎችን የደረበ፣ ከኢትዮጵያ ተነስቶ በዓለም ዙሪያ ባሉ አህጉራት ባልሳሳት ደቡብ አፍሪካ ፣በአውሮጳና አሜሪካ አገሮች ተዘዋውሮ በዝማሬ ኢትዮጵውያንን ያገለገለ ታዋቂ አገልጋይ ነው፡፡ ይህ አገልጋይ አንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያንን በተሰጠው የዝማሬ አገልግሎት እየጠቀመ ይገኛል፡፡ ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ አንዳንዶቻችን የእዚህን አገልጋይ በዝሙት ኃጢአት መውደቅ ከአሜሪካን ራዲዮ የሰማነው እየጎመዘዘንና እየተናነቀን ነው፡፡ እውነት ለመናገር የራዲዮ እወጃውን ከሰማን በኋላ የምንለውም የምናደርገውም ጠፍቶን ምድር የዞረችብንም ጥቂቶች አይደለንም፡፡ ጆሮአችንን ማመን አቅቶን ጭራሽ ሰውነታችን ተሟገተብን፡፡ “ይህ የጌታ ባሪያ ይህን አያደርግም ፣ እሬ ምን ቆረጠውና እንዲህ ያለ ነገር….. በኢየሱስ ስም የጠላት ወሬ ነው”፣ብለን ራሳችንን ለማሳመን ብንሞክርም ነገሩ እኛ ወደ ምንጎትተው አቅጣጫ ሊጎተትልን ሳይችል ቀረ፡፡
አንዳንድ “ምን አለበት ታዲያ የማይወድቅ ሰው አለ እንድዬ? ዳዊት ወድቆ የለም ወይ? የገለሞታ መንፈስ የደሊላ መንፈስ ተዋጋው እግዚአብሔር ይገስጸው” የሚሉ በርካታዎች መኖራቸውም ታይቷል፡፡ እነዚህን አደጋ ሲከሰት አስፈላጊው ርዳታ መደረግ የለበትም፣ የተጎዱትም ባወጣቸው ይውጡ፣ሌላም አስፈለጊ ጥንቃቄ ማድረግ አይገባም የሚሉ ዓይነት አድርጌ አወስዳቸዋለሁ፡፡ አገልጋይ በኃጢአት ሊወድቅ እንደሚችል የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል፡፡ ስለዚህ ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ ፓስተር ጢሞቴዎስን ከኃጢአት እንዲሸሽ የመከረው(1ጢሞ.6፡11)፡፡ ካልሸሸ ተጠልፎ እንደማይወድቅ ምንም ዋስትና የለውምና፡፡ አገልጋዮች ተሠርተን ያለቅን አይደለንም( ፓስተር ኃይሉ ቸርነት)፡፡ ዳዊትም የወደቀውና የእግዚአብሔርን ቅጣት የተቀበለው ስላልሸሸ ነው፡፡ ቃሉም የሚነግረን ከዳዊት ውድቀትና መቀጣት ተምረን እንድንጠነቀቅ እንጂ ኃጢአትን እንድንለማመደው አይደለም፡፡ የገለሞታና የደሊላ መንፈስ የሚባለውም ቢሆን ተመዝኖ የቀለለ አጉል ቃላተ- ቋጥኝ(jargon) ነው፡፡ ተከስተን ስለወደድነው የደሊላ መንፈስ ወይም የጋለሞታ መንፈስ ተዋጋው ካልን ከእርሱ ጋር ያመነዘረቺውን ሴትና ትዳሩዋን የሚወዱ ደግሞ ምን ሊሉ ነው? ”እህታችንን የአመንዝራ መንፈስ ተዋጋት እግዚአብሔር የምታው” ብሉ ተሳሳቱ እንል ይሆን? ሁለቱም የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው ሳለ በትዳራቸው ላይ ያማገጡ ደፋሮች አይደሉምን? ስለዚህ ታዋቂ ዘማሪና ፓሰተር የሆነውን ወንድማችንን አይዞህ ካልን በቃል ኪዳን ያገባት ሚስቱ ምን ትሁን? ስለ እርሷስ ምን ተሰምቶናል ወይስ የትዳር ጉዳይ ከመድረክ አገልግሎት የበለጠ ዋጋ እንደሚሰጠው ጠፍቶብን ነው?
እግዚአብሔር ምሕረትና ጥንቃቄውን ያድርግ እንጂ ዘማሪ ፓሰተር ተከስተ በፈጸመው ድርጊት የአቶ መላኩ የሺዳኛ ቤት እንዳይፈርስ ምን መተማመኛ አለን? ያንን ቤትና ትዳር ከተከስተ አገልገሎት እኩል ማየት ከተሳነን የአንድ ወገን ቲፎዞዎች ብቻ ያስመስለናል፡፡ እኛስ እንዲያው ስለዚያ ቤተሰብ አስበን ካልጸለይንና ተከስተ በመዝሙር ስላስደሰተን ብቻ አይዞህ የምንል ከሆነ ፍቅራችን እውነተኛው የክርስቶስ የመስቀሉ ፍቅር ለመሆኑ እንዴት እርግጠኛ እንሆናለን? ወንድማችንን አሰናከለቺው ማለትስ ተገቢ ነው? እርሱስ አላሰናከላትምን? ቢያንስ እኮ እንደ ፓስተርነቱ ለሕይወቷ መጠንቀቅና ሊያስተምራት በተገባው ነበር፡፡ ከዋሽንግተ ዲሲ ወደ ሜኒሶታ የሄደው፣ እርሱ በራሱም ምኞት ተስቦ ወይስ ሴትዮዋ አሰናክላው ነው? በሜኒሶታ ሆና በዲሲ አገልግሎት ላይ ያለውን የእግዚአብሔር ሰው ልታሰናክል እንደምትችል የሚታሰበው በምን መለኪያ ነው? ከዚህ ሁሉ ይልቅ የወደቀውን የሚያነሳ የምሕረት አምላክ የሆነውን እግዚአብሔርን ስለ ሁሉም ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አገልጋያችን የበደውን ትዳርና የትዳር አጋሮችን፣ የሚያገለግውን ሕዝብ ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቅና እንዲታደስ ማድረግ የእውነተኞች ወዳጆች ተግባር እንደሆነ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ዘማሪ ፓስተር ተከስተ ያደረገው ይህንን በመሆኑ ከአድናቂዎቹ ይልቅ እግዚአብሔር ይባርክህ መባል ያለበት እርሱ ነው፡፡ ምክንያቱም “ከአገልግሎት ሪቄ ራሴን እያሰታመምኩ ነኝ፣ለሆነው ነገር ሁሉ አቶ መላኩን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ፣ በሁኔታዎች ራሴን መግታት ነበረብኛና ያ ባለመሆኑ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን በድለናል ቀጥሎም አቶ መላኩን፣ጥፋት ጥፋት ነውና እኔ ጥፋቱን እቀበለላሁ ይቅርታ ልጠይቀው እፈልጋለሁ” ማለቱን የቮኦኤ ጋዜጤኛ ራሱ መስከሮአል፡፡ አቶ መላኩ ራሳቸውም ቢሆኑ ተከስተ ድርጊቱን እንደፈጸመው ማመኑንና ይቅርታም መጠየቁን በይፋ መስክረውለታል፡፡ ይህ ከአንድ እውነተኛ የንስሐ ልብ ካለው አገልጋይ የሚጠበቅ ተግባር ነውና ምንም እንኳ የንስሐውን ፍሬ ፈጥነን ባናየውም ቢያንስ ጎሽ እደግ እንድንለው ይህ በቂ ይመስለኛል፡፡ እግዚአብሔርም እንደገና በገናውን አንስቶ ቅኔውን የሚቀኝበትና በአዲስ ጉልበት የሚቆሚበትን አቅም ይሰጠዋል ብለን እናምናለን፡፡ የጸጋ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ሽማገሌ ለቪኦኤ የሰጠው ምስክርነት ወንድማችን ተከስተ አውነተኛ የንስሀ ልብ እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ በራሱ ተነሳሽነት የትዳር ጓደኛውን፣ የሚያገልግልበትን ማህበረ ምዕመናንንና እንዲሁም ሌሎች በዚህ የተጎዱትን ሁሉ ይቅርታ መጠየቁንና ራሱን በራሱ ከአገልግሎት አግልሎ በእግዚአብሔር ፊት ራሱን የሚያይበትን ጊዜ እየወሰደ መሆኑን ስንሰማ በእውነት ልባችን አርፏል፡፡
ሌሎች ደግሞ አይዞህ ተኬ እንወድለን ወዘተ የሚል በፌስ ቡክና በሌሎች ማበራዊ ገጾች ፎቶ በመለጠፍ ስሜታቸውን የገለጡም አልታጡም፡፡ እነዚህ ደግሞ ምንም ብታደርግ ከጎንህ ነንና አታስብ የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ይህ ፍቅር ይሉት ጥፋት፣እልህ ይሁን ሌላ አይታወቅም፡፡ ታዲያ ይህን ወንድም አይዞህ ብለን ብቻ ማለፍ ፍቅር ነው? ካልንም ስለ ወንድማዊ ፍቅር ገና እንግዶች ያስብለናል፡፡ እነዚህ ወገኖች ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና ዶር ቶሎሳ ጉዲና በአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ አሳብ እንዲሰጡ የተደረገው ዓይነት እድል ቢያገኙ ምላሻቸው ምን ይሆን ነበር? ተከስተን እንወደዋለን ምንም ችግር የለበትም ብለው ሁሉንም ነገር ሊያበላሹብንና ገደል ሊከቱብን እንደሚችሉ አያያዛቸው ይመሰክራል፡፡ ፍቅራቸው መሬት ያልረገጠና ቅዱስ ቃሉና መንፈሱ የማያውቁት መሆኑን ድርጊተ- ሥራቸው ያሳያል፡፡ አንደኛ ነገር ፣ ይህ ሰው ንስሐ እንዲገባና ከመንገዱ እንዲመለስ አንድም የወንድማዊ ምክር ቃል አልሰጡትም፡፡ ሁለተኛ ፣የሰውን ሚስት ያማገጠ ፓስተር ፎቶ ከራሳቸው ፎቶ ጋር አድርገው እየለጠፉ የጅላጅል ጨዋታቸውን ሲንቦጫረቁበት አልከለከላቸውምና ፌስ ቡክ የሥራውን ይስጠው፡፡
የእግዚአብሔር የትዕግሥቱ ጽዋ ሞልቶ ወይዘሮ ሆሳዕና አዳዳ ለአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ አሳወቀችና ጉዳዩ የማይሸሸግና የማይታፈን ሆነ እንጂ ሌሎችም የተደበቁ ነገሮች አይኖሩም ማለት እንችላለን? ድርጊቱ እኮ የለመደ ሰው ሥራ ይመስላል፡፡ ሥር የሰደደ ልምምድስ ያለው ባይሆን ከሴትዮዋ ጋር በተኛባቸው ቀናት የጠጣው መጠጥ በአገሩ እያለ የሚያውቀው ነበር እንዴ? በእንዲህ ዓይነቱ አነቃቂና አስካሪ አልኮል መራጨት ከጀመረ ምን ያህል ጊዜው ይሆን? የቆሎ ተማሪ፣ ደበሎ ለባሽ ሲባል የነበረ በጌታ ምክንያት ክብር ቢያገኝና በቅዱሳን መባና አሥራት የሚሰፈርለትን ቀለብ ለዝሙት ተግባሩ አልቤርጎ ይከራይበታል፣ የወሲብ ማነሳሻ መጠጥ ይሸምትበታል፡፡ ተሳሳተ፣ ሰይጣንም ተዋጋው ከምንለው ያለፈ መሆኑን ሳንዘነጋ ከጎንህ ነን ማለቱን ትንሽ ቀዝቀዝ እናድርገው፡፡ ይልቁንም የተጀመረው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሽምግልና ወንድማችን እንዲታደስ ይረዳዋልና ብዙም አንፍረድበት እንጸልይለት እንጂ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰይጣን ሲያሰናክልንም ሆነ እኛው በምኞታችን ተስበን ስንወድቅ ሳይቀጣን አያልፍም፣ እንደ ተከስተ በእውነት ስንመለስ ግን ወሰን በሌለው ምሕረቱ ይምረናልና በእርሱ ብቻ እንታመን፡፡
ተከስተ በዚህ ኃጢአት ስለወደቀ ብቻ አብቅቶለታል፣የክርስትናውና የአገልግሎቱ ነገር በአራት ነጥብ ተደምድሟል ብንል ትልቅ ስህተት ይሆንብናል፡፡ እግዚአብሔር የምህረት አምላክ በልጁ በኢየሱስ ክርሰቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ሊያነጻ የታመነ፣ የወደቁትንም የሚያነሳ ሩህሩህ አምላክ ነውና፡፡ በዝሙት ኃጢአት አገልጋዮች ማለትም ፓስተር፣ ዘማሪ ፣ ወንጌላዊ ፣ቄስ ሲወድቅ ተከስተ ጌትነት በዚህ ምድር የመጀመሪያው ሰው አይደለም፡፡ ብዙዎች ወድቀው ከወደቁበትም በእግዚአብሔር ምሕረት ምክንያት ተነስተው ፣ እንደገና የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀብለው የሕይወትና የአገልግሎት ሩጫቸውን እየሮጡ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡ ግን ታዲያ ይህን የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲቀበሉ በእውነተና ንስሐ ወደፊቱ እንዲቀርቡ ከማበረታታት ይልቅ በየፌስ ቡኩ አይዞህ እንወድሃለን መባባል ምን የሚሉት ነው?
የወንድማችንን የተከስተ ጌትነትን ስህተት የመላው ፕሮቴስታንት አማኞች ውድቀት አድርገው ሁሉን በገፍና በጅምላ የሚያብጠለጥሉም አሉ፡፡ እነዚህ ደግሞ የአንድ ወይም የሁለት ሰው ውድቀት የመላው ቤተ እምነት እንዳይደለ ወይም ተከስተ ጌትነት ከዲሲ በአይሮፕላን ተሳፍሮ ሜኒሶታ የሄደው የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ለማስፈፃም ሳይሆን ከወይዘሮ ሆሳዕና ጋር የዝሙት ፍላጎቱን እውን ለማድረግ እንደሆነ አላሰቡበትም፡፡ የኃጢአት ፈተና ማንንም የማይለይ እንዲያውም ሰይጣን በአገልግሎት የሚታወቁትን እየጠለፈ በመጣል ምዕመናንን የሚያሳቅቅበት መሣሪያው ዝሙት እንደሆነ ማወቅ ለምን እንደተሳናቸው ግልጽ አይደለም፡፡ የሰውን ትዳር አበላሸ፣ ይኼው አስነወራአት በማለት በወደቀ ዛፍ የምሳር ብዛት እንደሚሉት በወንድማችን ላይ የስድብ ሩምታ የሚያዘንቡ የአሸዋ ያህል ናቸው፡፡ በቤታቸው እንግዳ ሲጋብዙ በተለይም በእንግዶች መካከል የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ከተገኘበትማ ሆን ብለው የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ያደረገውን ቃለ ምልልስ የሚከፍቱ ይኼውና ጴንጤዎች እንደዚህ ናቸው በሚል ጥቂት አይደሉም፡፡
በዚህ ውድቀት ምክንያት አንጀቱ የራሰው ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር አዝኗል፣ ቅዱሳን ደንግጠዋል፣ በቃል ኪዳን የቆመው ትዳር ተጎድቷል፣ በኃጢአት የወደቁ ወገኖቻችንም ልብ በመንፈስ ቅዱስ ወቀሳና በህሊና ክስ መሰቃየቱና አንገታቸው መሰበሩ አልቀረም፡፡ ተከስተ ጌትነት ጌታ ኢየሱስን ለመከተል ሲወስን ዘማሪ እሆናለሁ ብሎ ሳይሆን የዘላለምን ሕይወት አገኛለሁ በሚል ነው፡፡ የመረጠው ጌታ ጨምሮ የወንጌሉ አገልጋይ አድርጎ በመቀባት በሕዝቡ ፊት ገለጠው እንጂ፡፡ አገልጋዮቻችን በሕይወትና በኑሮአቸው ከምዕመናን በልጠውና ተሽለው መገኘት ስላለባቸው የወቀሳውና የሀይማታዊ ቅጣቱ ደረጃ ጠንከር ይል ይሆናል እንጂ በተከሰተው ነገር የጥፋተኛነቱን ክብደት የምናሸክመው ሁሉንም ነው፡፡ ዘማሪውን ብቻ መግቢያ መድረሻውን አሳጥተን የምናበቃው አይደለም፡፡
እውነት ለመናገር እህታችን ሆሳዕና አደዳም ብትሆን እንዲያው እሾክ አይውጋሽ የምንላት አይደለችም፡፡ እርሷም ለዚህ ውድቀት የተጫወተችው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ እርሰዋ ብቻ እንደተደፈረች አድርገው የሚናገሩ ወገኖች ምነው ቆም ብሉና ቢያስቡስ ? የስልክ ጥሪውን ከተቀበለች በኋላ ባለቤቷ በሌለበት ምሽት ወንድ ወደተከራየው አልቤርጎ መሄዷ ምን ቢያምራት ነው ብለው ለምን አይጠየቁም? እሺ የመጀመሪያውን ቀን ምናልባት ስላልተጠራጠረች ሄደች እንበል፡፡ ሁለተኛ ቀን ወንድን ለወስብ በሚያነሳሳ መልኩ ልብሷን ቀይራ ያውም የትላንትናውን ያላማረ አቀራራቡን ካስተዋለች በኋላ ተመልሳ መሄዷ ከወቀሳ ነጻ የሚያስለቅቃት በየትኛው ፍርድ ይሆን? ለሰው ሁሉ የማይታይና ማንም እንደፈለገው የማይነካካው የሰውነታችን ክፍሎች አሉ፡፡ ጡት፣ ዳሌ፣ ደረት፣ ከንፈር ወዘተ በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው የሰውነት ክፍሎች ሲሆኑ በተለይም ላገቡት ከትዳር ጓደኛቸው በስተቀር ሌላ እንደዚህ ያሉ የአካል ክፍሎችን እንዲያየቸውም እንዲነካቸውም አይፈቀድም፡፡ ለላጤዎች የተፈቀደ ነው ማለቴ እንዳይደለም ያዙልኝ፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ጡቷን ፎቶ ላንሳ ሲል ደረቷን ገልጣ ማሳየቷና መፍቀደዋ ምትሆነውን ብያሳጣት ነው አያስብልምን? በዚያው ላይ ደግሞ የጓደኛዬ ባል ስለሆነ ልጠይቀው ብዬ ነው አለች፡፡ በዚህ ምክንያት ጠያቂ አያሳጣሽ ብትባልም የጓደኛዋን ባል ነድፋ በመጣልዋ ግን አላበጀሽም ለማለት ምነው የማይደረስ የወንጭፍ ያልህ ሩቅ የሆነባቸው? ደግሞ በጉዳዩ ጨርሶ የሌለበትን ዘማሪ ሳሙኤል ተክለማርያምን በመላው ክርስቲያን አፍ እንዲገባ መድረጓስ በእግዚአብሔርም በሰውም የተጠላ ተግባር አይደለም ወይ? ለአሜሪካ ድምዕ ራዲዮ ያለቺውን እነሆ፡
“ሳሚ የሚባል ጓደኛ አለውና ለእርሱ ከእኔ ጋር ስላለው ግንኙነት ሲነግረው እርሱም መልሱ እንኳን እኔ እግዚአብሔርም ደስ ይለዋል… አለው እና እርሱም የሚያሳየው መጠጥ አለ አለኝ፣ ገዝቶ ይዞ ገባ፡፡ መጠጡ ጠንካራ መጠጥ ነው … ለእኔ ግን ሻፓኝ ገዛልኝ፡፡ ሆቴል ውስጥ እንደገባን መጠጦቹን ደረደረና ፎቶ አነሳ፡፡ መጀመሪያ ለእኔ ሻፓኙን ሰጠና ለራሱ ያኛውን መጠጥ አንስቶ መጠጣት ጀመረ ማለት ነው፡፡፡ ያንን ፎቶ ለጓደኛው ለሳሚ ላከለት፡፡ ደግሞ ጡቴን ፕክቼር ነገር ብድግ አደረገና ላከለት ቴክስት አደረገለት፡፡ ከዚያ ይህንንማ ለብቻህ አትችለውም አጋዥ ያስፈልግሃል አለኝ አለ፡፡ እስቲ አናግሪው ብሎ ወዲያው ሰጠኝ፡፡ ከዚያ እመጣለሁና አብሬን መገናኘት እንችላን ብሎ ወሬ ማውራት ጀመረ፡፡ …. ከእኔ ጋር ለሁለት ሊወጡ አሳብ እንዳላቸው ማውራት ጀመሩ ማለት ነው፡፡”
የጸጋ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ሸማግሌ ከሌሎች ጋር ሆነው ባደረጉት ማጣራት ዘማሪ ሳሙኤል ተክለማርያም ስለዚህ ጉዳይ ምንም እንደማያውቅ መናገሩን ተከስተም ሳሙኤል በነገሩ ውስጥ ጨርሶ እንደለሌበት መመስከሩን ይፋ አድርጓል፡፡ መቼም በጌታ ስም ካላቸውም የአገልግሎት ኃላፊነት የተነሳ በጉዳዩ የገቡ የተከበሩ መሪዎቻችን የሚዋሹበት ምንም ምክንያት አይኖራቸውም፡፡ ግን ለመሆኑ እህታችን ሆሳዕና ከላይ የተመለከተውን አሳብ ተናግራ የእግዚአብሔርን አገልጋይ ስብዕና ያጠላሸቺው ለምን ይሆን? ሁሉንም ገደል ልክተታቸው ካልሆነ እንዲያው ምን ሊባል ይችላል? በሰጠችው ቃል ያሳሳተቺው ሰው ጥቂት አይደሉም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ዘማሪ ሳሙኤል ተክለማሪያምን እንደ አገር አጥፊ ቦዜኔም ሳይይቆጥሩት የቀሩ አይመስለኝም፡፡ መደበቅ ምን ያረጋል እኔ ራሴ ልቤ በሳሙኤል ላይ ክብዶብኝ ነበር፡፡ ባለቤቷ መላኩም ተከስተ ይቅርታ እንደጠየቀና ንስሐ መግባቱን እየመሰከረ ለቪኦኤ የደውለው ሳሙኤል ንስሐ እንዲገባ ብሎ መሆኑን ተናገረ፡፡ እህት ሆሳዕና ከቤቷ ከጀምራ እስከ አገር ድረስ ያለነውን ሁሉ ፈራጆች አደረገቺን፡፡ ለምን ይህንን እንዳደረገቺው ለእርሷ መተው ይሻላል፡፡ ተከስተን የምንወቅሰው አቅዶና አልሞ ለዚህ ተግባር ራሱን በመስጠቱ ነው እንጂ ከፍ ብሎ እንዳየነው ሰው ነውና ወደቀ ከሚሉ ወገኖች ጋር እኔም እስማማለሁ፡፡ ሰው ምንጊዜም ደካማ ነውና ሊሰናከል እንደሚችል አለማሰባችን ለምንድነው? ዘማሪና ፓስተር ቢሆንም ልታሰናክለው እንደምትችል እርጠኛነቱ ስለነበራት እንጂ ልብስ ቀይራ በምሽት ወደ በርጎ የሄደችው ለየትኛው ድግስ ስለተጋበዘች ነው? ያውም ባሏ ወደ ሥራ የሚሄድበትን ሰዓት ጠብቃ! ደጋግሞ ስልክ ቢደውልም እቤቷ ቁጭ ብትል ጎትቶ የሚያወጣት በምን ይሆናል ብላ ነው? ስለዚህ በሁለቱም ትዳሮችና በቅዱሳን ላይ ለደረሰው አደጋ መንስኤ ሁሉም ናቸው፡፡ ምንም ይሁን ምን እርሷም ሰው ናትና መሳሳቷን ባንክድም እንዲያው እጅና እግሯ ታሥሮና ተገድዳ አልተደፈረችም ብንል ጨካኞች ያደርገናል ብዬ አላስብም፡፡ የምናምነው አንድ እውነት ግን አለ፡፡ ያውም በእውነተኛ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር ፊት ከቀረበች እግዚአብሔር ለእርሷም ምሕረት እንደሚያደርግላት የሚያጠራጥረን ነጥብ የለንም፡፡
የጓዳችን ነገር ግድቡን አፍርሶ ወደ አደባባይ ወጣና ዓለም ሁሉ እንዲሰማው በመደረጉ የሐይማኖት መሪዎችም አስተያየት እንዲሰጡበት ከጋዜጠኞቹ ግብዣ ቀረበላቸው፡፡ ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት በኩል በራዲዮ ጣቢያው ምርጫ የተጋበዙ ስመ ጥሩ ሰው የተናሩት አሳብ ያልተያያዘ ብትን ሥራ መስሎ ታየኝ፡፡ እንዲህ ነው ያሉት፡
"በአገልጋዮቻችን መካከል እየሆነ ያለው አስነዋሪና አሳፋሪ ነገር አንድ ወሳኝ የሆነ ክፍተት እንዳለ የሚጠቁም ነው፡፡ በባህላችን መንፈሳዊ ሰዎች ይታመናሉ ይወደዳሉ፡፡ ስለሆነም መናገር ከቻሉ ይሰብካሉ፡፡ ድምፅ ካላቸው ይዘምራሉ፣ ይቀድሳሉ፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ስምና መድረክ ይሰጣቸዋል፡፡ እነርሱም የሚችሉትን መስጠት እንጂ ከአገልግሎት ጋር የሚመጣውን በረከት ተወዳጅነት ዝና ታዋቂነት እንዲሁም ተጠያቂነት ለማስተናገድ በቂ ትምህርት ላይኖራቸው ይችላል፡፡ እንግዲህ ለወደፊት ይህንን ክፍተት ለመሙላት የሞራል ጉዳይ ሆነ የአገልግሎት ብቃት የሚያስመሰክር ስልጠናና ብስለት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እንደዚሁም ሲያጠፉ የሚመልሳቸው ሲወድቁ የሚያነሳቸው መንፈሳዊ መሪ ሥር መሆን የግድ ነው፡፡"
ይህ የምንወዳቸው አባታችን የዶር ቶሎሳ ጉዲና አስተያየት ነው፡፡ ዶክተር ብዙም ሳያስቡ የተናሩት ወይም የተከስተን ቤተ ክርስትያን መሪዎችን ሳያማክሩ ያስተላፉት አሳብ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ እረኛ ስላለውማ በቤተ ክርስቲያን የሥነ ሥርዓት ርምጃ ሥር መሆኑ እየተነገረ እረኛ ሥር መሆን እንዳለባቸው ግድ ነው ማለት ዶክተሩ ካለው የቤተ ክርስቲያናትና የአገልጋዮች ተጨባጭ ሁኔታ ርቀው ያሉ እንዳያስመስላቸው ፈራሁ፡፡ ደግሞ ሥልጠና ከፈተናና ከመሰናከል እንደሚያድን የሚናገረው የትኛው የወንጌል ክፍል ነው ብዬ ባስብ መልስ አጣሁ፣ ይህም በጣም ከማከብራቸው ከዶር ቶሎሳ ስለተነገረ ልክ አይደለም ለማለትም አቅም ከዳኝ፡፡ ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ሕግን በመጠበቅ የሚለውን የዳዊትን ቅኔ ሊያሳዩን ይሆናል ብዬ ራሴን በራሴ ሰበክሁ፡፡ አገልጋዮችስ መናገር ስለቻሉ የሚሰብኩበት፣ ድምጽም ስላላቸው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ስምና መድረክ ተሰጥቶአቸው የሚዘምሩበትና የሚቀድሱበት ባህል ያላት የትኛዋ ቤተክርስቲያን ነች? አንድ ሰባኪ ከመስበኩ በፊት የስብከት የጸጋ ስጦታ እንዳለውና ለዘማሪም መድረክ የሚሰጠው ስጦታው ታይቶ መሆኑ እንዴት ሊረሳ ቻለ? ዶር የሰጡት አስተያያት ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወይስ ስለ ሌላ ነው ለማለት ተገደድኩኝ፡፡ ያለ ስጦታቸው የሚሰብኩ መኖራቸውን ባንክድም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የመናገር ችሎታ እና ድምፅ ላለው ብቻ መድረክ የሚሰጥ ቤተ ክርሰቲያን እንዳለ አድርገው በዓለም መድረክ መናገራቸው ያስመስግናቸዋል ለማለት አልችልም፡፡ መቼም የዶክተርን ያህል በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የቆየን ባንሆንም ትክክለኛ የአመራር መዋቅር ያላት እውነተኛዋ ቤተ ክርሰቲያን አገልጋዮችን በአገልግሎት ከማሰማራቷ በፊት እንዴት እንደምትፈትናቸው እያየን ነው፡፡ የዶክተሩ አባባል ግን ከእውነታው ጋር ተጋጨብኝ፡፡ ሲወድቅ የሚያነሳ እረኛ ሲሳሳቱ የሚመልስ እረኛ ያስፈልጋል ማለታቸው እውነት ነው፡፡ ግን እረኛው ሲሳሳትስ የሚመልሰው ማነው? ሲወድቅስ የሚያነሳው ማን ነው? ዶር ቶሎሳ የሚናገሩት ስለ የትኛው እረኛ ነው? ከማንም በላይ እኔ ነኝ ስለሚለው ፈላጭና ቆራጭ እረኛ ነው ወይስ በቤተ ክርስቲያን የጋራ አመራር በሚያምንና ሲሳሳት የሚመልሱት ሲወድቅ የሚያነሱት አካላት ስላለው ሎሌያዊ አገልጋይ ነው የሚናሩት? ፓሰተር ተከስተስ እረኛ ቢሆንም ከእረኞች ሥር ስለሆነ ምክር የሚቀበልበት እድል አግኝቷል፡፡ ይህን የማይፈልጉ እረኞችስ ካሉ ችግሮች የሚፈቱት እንዴት ነው? ለምሳሌ በአትላንታ ኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን እረኛና መጋቢ ዶክተር ራሳቸው ናቸው፡፡፡ እርሳቸው ቢያጠፉና ቢሳሳቱ የሚገስጻቸው ከእርሳቸው በላይ ሆኖ መመሪያ የሚሰጣቸው አካል ካለ ጥሩ ምሳሌያችን ናቸው፡፡ ካልሆነስ እርሳቸው የማይነኩ እንደሆኑ የሚያስቡ ወጣት አገልጋዮችም በጋራ አመራር አያምኑምና ፈልጠውና ቆርጠው መኖር የሚያዋጣ ቢመስላቸውና ቢሳሳቱ ችግርም ቢገጥማቸው ዶክተር ቶሎሳ በምን ሥልጣን ሊወቅሱአቸው ነው፡፡ ወጣት መጋቢያን የሚማሩት እንደነዶር ካሉት ነዋ? ስለዚህ የሚሉትን ክፍተት የፈጠረው ማን ነው? የሚለውን ዶር ቢመልሱልን እድለኞች ነን፡፡
ከላይ ያየናቸው አሳቦች እንዳሉ ሆነው ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሁኔታ ከቃኘን በኋላ ሊመሰገኑ የተገባቸውን ሳናመሰግን ማለፍ ተወቃሽ ያደርገናል ብዬ አስባለሁ፡፡ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ካወቅን የአደጋው ተጠቂዎችን ከፍርስራሹ ውስጥ ለማውጣት በምንችለው ሁሉ መትጋት ይገባናል ባይ ነኝ፡፡ ወይዘሮ ሆሳዕና በመንፈሳዊ ህይወቷ ምን ያህል የበሰለች እንደሆነች አላውቅም ግን ልትመሰገንበት የሚገባት ጉዳይ አለ፡፡ ውድቀቷን ከትዳር አጋሯ ደብቃ፣ ለስሟ ተጠንቅቃ የቻለቺውን ያህል ዓመት መኖር አላስፈለጋትም፡፡ አስፈሪ ቢሆንም ደፍራ ራሷን ገለጠች፡፡ ይህን ለማድረግ ኃይል እንዴት እንዳገኘች ቢያስደንቀንም ከዚህ በላይ መንፈሳዊነት አለ ብዬ ማመን ይቸግረኛል፡፡ እግዚአብሔር እኮ በኃጢአት በሚወድቁት እንደሚያዝባቸው ሁሉ በሚናዘዙ ደግሞ የበለጠ ደስ ይለዋል፣ እነርሱንም ያለመልማቸዋል፡፡ ዓለም አቀፋዊ ታዋቂነት ያለው ዘማሪያችን ሳሙኤል ተክለማሪያም እንዳለው እኔ ይህንን አላደረግኩም ብላ በመሸምጠጥ እግዚአብሔር ነገሮችን ወደ ፀሐይ እስክያመጣው ድረስ መቀጠል አልፈለገችም፡፡ ታዲያ አይዞሽ እግዚአብሔር ይቅር ይልሻልና ብልንስ?
እስቲ ሁላችንም ራሳችንን በአቶ መላኩ የሺዳኛ ጫማ እናቁምና ህመሙን እናዳምጠው፡፡ በፍቅር የተሳሰሩ የልጆቹ እናት የሆነቺው አካሉ ከሌላ ወንድ ጋራ ለመተኛት ራሷን ገላልጣ መስጠቷን ሰምቶ በሰላም ለመኖር መወሰኑ እውነተኛ የእግዚአብሔር ሰው አያሰኘውምን? በዝሙት ምክንያት ካልሆነ ሚስቱን የሚፈታ አመንዝራ ያደርጋታል የሚለውን ጥቅስ ተመርኩዘው ሰው አንዴ በዝሙት ከወደቀ ትዳሩን መፍታት አለበት በሚል ትዳሩን ለመፍረስ የሚጣደፍ ሰው በበዛበት በዚህ ክፉ ዘመን ሁሉንም ዋጥ አድርጎ አብሮአት ለመቀጠል መወሰኑ በሳልና ለባሎች ሁሉ ምሳሌ ሊሆን የሚችል አያደርገውምን? የቃል ኪዳን አሳቢነት ለልጆቹ ተቆርቋሪነት፣የእግዚአብሔር ፍርሃት፣የባለቤቱም ኃላፊነት ሁሉ የተሰማው ሰው ነውና ቢቻል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ካልሆነም ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ተባረክ ተመንደግ በማለት ትዳሩም ዳግም ልዩ ጣዕም እንዲኖረው እግዚአብሔርን መለመን ይገባል ባይ ነኝ፡፡
አደጋው መከሰቱን በመስማት የተጎዱትን አካላት ሁሉ ለመታደግ የእረኝነትና የካህንነት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የተንቀሳቀሱ የወንጌላውያን አማኞች ቤተ ክርስቲያናት መሪዎች በእውነት ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ ያሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች ወንድማችንን ተከስተ ጌትነትን ከአገልግሎት በማገድ ራሱን እንዲያይ በማድረጋቸው እርሱ ለቤተክርስቲያን ሥልጣን ራሱን በማስገዛቱ እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ በተለይ በአሁኑ ዘመን ይህ ውድ ነገር ነው፡፡ ይህን በመስማቴ እየተጽናናሁ ዶር ቶሎሳ ለአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ከተናገሩት አሳብ ጋር መስማማት ያቃተኝ ለዚህ ነው፡፡ የሐይማኖት መሪዎች አስተያየት ጉዳይ ከተነሳማ የፕሮፌሴር ጌታቸው ኃይሌ አስተያየት ሚዛኑን የጠበቀ ነው፡፡ እንዲህ ነው ያሉት፡
"ይህ ችግር የዛሬ አይደለም፡ ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ በሰው ልጅ መካከል ያለ ነው፡ እንዲውም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቁ ኃጢአት የወሲብ ጉዳይ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ በሰው ላይ ያለ ነው፡……፡፡ ይኼ በተለይም መንፈሳውያን የሆኑትን በበለጠ ያስቸግራል፡፡ በየመጻሕፍቱ ሁሉ ላይ ስናየው፣ በየገድሉ ሁሉ ላይ ሲናየው፣ በተለይ በካህናቱ ላይ ይጠነክራል ይኼ ደግሞ፡፡ ለእኛ አዲስ የሚሆንብን…… በካህናት ላይ ሲመጣ ነው፡፡ ያን ጊዜ ነው የሚያስደነግጠን፡፡ ነገር ግን ታስታውሱ እንደሆነ ዳዊት ሰለሞንን የወለደው በኃጢአት ነው የዳዊት ልጅ እህቱን የደፈረው በኃጢአት ነው፣ እና ይህ ትላልቆቹን መንፈሳውያንን በበለጠ ይጎዳቸዋል፡፡…….ይኼ በተለይም መንፈሳውያን የሆኑትን በበለጠ ያስቸግራል፡፡ በየመጻሕፍቱ ሁሉ ላይ ስናየው፣ በየገድሉ ሁሉ ላይ ሲናየው፣ በተለይ በካህናቱ ላይ ይጠነክራል ይኼ ደግሞ፡፡ ለእኛ አዲስ የሚሆንብን…… በካህናት ላይ ሲመጣ ነው፡፡ ያን ጊዜ ነው የሚያስደነግጠን፡፡ ነገር ግን ታስታውሱ እንደሆነ ዳዊት ሰለሞንን የወለደው በኃጢአት ነው የዳዊት ልጅ እቱን የደፈረው በኃቲአት ነው፣ እና ይህ ትላልቆቹን መንፈሳውያንን በበለጠ ይጎዳቸዋል፡፡……አባቶች ከእግዚብሔር ቀጥሎ እሰከ መመለክ የሚደርሱ ናቸው፡፡ እና ያ ነው እንግዲህ የሚያስደነግጠን፡፡ በዚያ ደግሞ በአንድ በኩል ሕዝበ ክርስትያኑ መነገር አለበት ማወቅ አለበት፡፡ እንደዚህ ያለ ነገር ከሕብ ክርስቲኑም መጠበቅ አለበት፡ … ካህናቱም ወጥተው ሲያስተምሩ እኛ ሁላችንም ደካሞች ነን፡፡ እርዱን ማለት አለባቸው፡፡ ይህናው ሕዝበ ክርስቲያኑም መርዳት አለበት ለማለት ነው፡፡"
ስለዚህ እኒህን ሰው እግዚአብሔር ይባራካቸው ማለት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ የእምነት አባቶቻችን በማሕበራዊ ገጾች ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በሚጋበዙበት ጊዜ ከብዙ አንጸር በጥንቃቄ መናገር እንዳለባቸው መምከር ያለብን አይመስለኝም፣ለዚያ የሚሆን አቅም ገና የለኝምና፡፡
ልትረሳ የማይገባት ሰው የዘማሪ ፓስተር ጌትነት ባለቤት ነች፡፡ ምንም እንኳን ባሌ ለትዳሩ ታማኝ አይደለም እና ልለየው እፈልጋለሁ ብትል ማንም ቢሆን ለትዳሩ መፍፈረስ ምክንያት የሚያደርገው ተከስተን እንጂ እርስዋን አይደለም፡፡ እርሷ ግን ከመብቷ ይልቅ በቃል ኪዳን በታሠረችበት ባሏና በፍቅሩ ተረታች፡፡ ማህበረ ምዕናኑን ይቅርታ ሲጠይቅ አብራው ሆና ከጎኑ እንደቆመችና ይቅርታ እንደለመነች ተመስክሮላታልና እግዚአብሔር ይባርካት፡፡ ሰይጣንን ማሳፈር ከተባለ እንዲህ ዓይነቱ ቀዳሚ ይመስለኛል፡፡
በመጨረሻም፡ በተፈጠረው አደጋ የተጎዱትን ሁሉ ለማዳን የፍቅርና የርሕራሄ ልብ ያስፈልገናል፡፡ በምሕረት ዓይኖች እንድናያቸውም ያሻናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በጸጋ ዘመን ብንሆንና እኛው በጸጋው የዳንን ጸጋው የበዛልን ብንሆንም በኃጢአት ጸንተን እንድንኖር ቃሉ አይፈቅድምና ለኃጢአት ከሚያጋልጡ ሁኔታዎችና ቦታዎች ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባናል፡፡ ሰዎች በተለይም አገልጋዮች ተፈትነው ሲወድቁ ከውድቀታቸው የሚነሱበትን መንገድ እንፈልግላቸው የጌታንም ታላቅ ምሕረት እናሳየቸው እንጂ ያለርህራሔ አንውገራቸው፡፡ እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ቢሆንም የሚባላ እሳትም መሆኑን ሳንረሳ በኃጢአት የወደቀውን ሰው በጭፍኑ ምንም አትሁን የሚል ተስፋ በመስጠት የንስሐ ዕድል እንዳንከለክለውና በጣም ወደ ጥግ ከተለጠጠው ቲፎዞነት መቖጠብ ይኖርብናል፡፡ ማናችንም ፈጥነን ከምንፈርድ ይልቅ የቅጣቱንም ሆነ በነጻ የመልቀቁን ኃላፊነት እግዚአብሄር መንፈሳዊ ሥልጣን ለሰጣት ቤተ ክርሰቲያን እንተውላትና ከእርሷ ድምጽ በመስማት የምናድረጋቸውን ሁሉ እናድርግ፡፡ ራሳችንንም በፍርድ ወንበር ላይ ፈጥነን እንዳናወጣ ጌታ ይጠብቀን፡፡ በሆነው ነገር ያዘኑትን፣ የተጎዱትን ሁሉ እግዚአብሔር በምሕረቱ ያስባቸው!! አሜን