Saturday, December 28, 2013

لأنه هكذا أحب الله العالم، انه اعطى ابنه الوحيد، أن كل من يؤمن به لا ينبغي أن يموت، بل تكون له الحياة الأبدية.

  لأنه لم يرسل الله ابنه الى العالم ليدين العالم، بل ان العالم من خلاله يخلصوا.

18 الذي يؤمن به لا يدان ولكن الذي لا يؤمن هو وأدان بالفعل، لأنه لم يؤمن باسم وحيد ابن الله.

19 وهذه هي الدينونة، ويأتي هذا الضوء إلى العالم، وأحب الناس الظلمة أكثر من النور، لأن أعمالهم كانت شريرة....
Gospel of John 3:16-19
Collected by Pastor Samuel Shonga
سوع هو نور العالم، ويمكن أن لا تغلب عليه الظلام. وقال انه يعطي الحياة والنور والصحة والسلطة كونها مدرسية من الله، للذين يؤمنون باسمه

Thursday, December 26, 2013

የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የመምራት ዜዴ


የቡድን  መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የመምራት ዜዴ
                          በፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ

ክፍል አንድ
2 ጢሞ 316-17፤ዕብራውያን 412፤ሐዋ.1711
መግቢያ፡ የእግዚአብሔርን ቃል በግልም በጋራም ማጥናት ለመንፈሳዊ ህይወት እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በቃሉ በራሱ መመልከት እንችላለን። የእግዚአብሔርን ቃል በሚያጠኑና በማያጠኑ ሰዎችና አገልጋዮች መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩ ግድ ነው። ቃሉን ስናጠና ከሁሉ ይልቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለማድግ ካለን ዓላማ አንጻር መሆን እንዳለበት ነው።
አንድ ሰው በየቀኑ ተገቢውን ምግብ ካላገኘ ለተለያዩ በሽታዎች ከመጋለጡም አልፎ ሕይወቱንም ሊያጣ ይችላል። እንደዚሁም ሁሉ መንፈሳዊ ምግብና ወተት የሆነውን የጌታን ቃል በየዕለቱ የማይመገብ አማኝ በዚህ ዓለም ያሉ የተለያዩ ፈተናዎች ቢመጡበት በቀላሉ ተጠላልፎባቸው ልወድቅ ይችላል።
ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የሚያጠኑብቸው የተለያዩ መንገዶች ያሉ ሲሆን አንደኛው የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዜዴ ሲሆን ሁለተኛው የቡድን ወይም የጋራ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን መንገድ ነው።
የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማለት አንድ ግለሰብ ጊዜ ሰጥቶ ብቻውን በግሉ ቃሉን የሚያጠናበት መንገድ ሲሆን የቡድን ጥናት ግን በዓይነቱ ለየት የሚል ነው።
ሁሉም የክርሰቲና ሕይወት ተሞክሮ የሚመጣው ከግል ሕይወት ነው፡፡ አምልኮ፤ጸሎት፤ንስሐ፤የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ሁሉ የሚመነጨው ከግል ሕይወት ነው፡፡ የግል መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማለት አንድን ሰው ለብቻው አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ወስዶ ወይም መርጦ የሚያጠናበት ሂደት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለአማኙ የመንፈሳዊ ሕይወት ዕድገት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የቡድን የመጽሐፍ ቅዱሰ ጥናት መንገድ፡ ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በጋራ የማጥናት ዘዴ ነው፡፡
በቡድን ማጥናት ስንል በጋራ ማጥናት ማለታችን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በግል ካጠናን አይበቃም ወይ ለምንድነው በጋራ ማጥናት የሚያስፈልገው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል፡፡ ለዚህ ደግሞ መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚያስፈልገው ለእርስ በርስ መማማር ነው፡፡
  • የእግዚአብሔር ቃል በቡድን ማጥናትን ስለሚያበረታታ ነው፡፡ ሐዋ. 241-121711
  • መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና የተለያዩ ደረጃዎች እንደሚኖሩ መገንዘያስፈልጋል፡፡
    ለምሳሌ፡
  1. በብ፡ አሳቡን መመከት
  2. ማጥናት፡ መመልከት መተና መዛመድ
  3. ማሰላሰል፡ ቃሉ እንዳይረሳ በአእምሮ ማላሰና ማሰልሰል
  4. መጫወት፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስላነብብነው ቃ ማውራትና ማካፈ
  • የቡድን የመሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደግል ጥናት በተፈለገው ጊዜና ሁኔታ ሊከናወን አይችልም፡፡ ምክንቱም በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰዎች በአድ ላይ በመሰባብ የሚያደርጉት ስለሆነ ነው፡፡
    በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚታዩ ባሕሪያት
  • ቡድኑ ከ5- 7 ወይም ቢበዛ 9 አባላትን ያቀፈ ነው፡፡ አባላቱ ከ5-9 ሲሆኑ ይህ አነተኛ ቡድን የሚባል ሲሆን ከ9 በላይ ከሆነ ግን መካከለኛ ቡድን ይሆናል፡፡ የባላቱ ቁጥር ከ15 በላይ ከሆነ ደግሞ ከፍተኛ ቡድን ተብሎ ይጠራል፡፡ ስለዚህ የቡድን ጥናቱ አባላት ቁጥር ከ9 መብለጥ የለበትም ምክንያቱም የአባላቱ ቁር በበዛ መጠን አባላቱ አሳባቸውን የማሸራሸር እድል እየቀነሰ ይሄዳል፡፡
  • ሁሉም አባላት የንባብ ክፍሉን በየራሳቸው ይረዱታል፡፡ የተለያዩ አሳቦችንም ፈልቁበል፡፡
  • እያንዳዱ የቡድኑ አባል ለላው ያስተ( ያካፍላል) ከሌላውም ይማራል፡፡
  • የቡድኑ አባላት ተለያየዩ የመረዳት ደረጃዎች የሚኙ ናቸው፡፡
    ሳሌ
    - የቅርብ ጊዜ አማች ሆነው ብዙ የቃሉን መረዳት ያላገኙ ወይም ወደ ከፍተኛ የመረዳት ደረጃ ላይ ያደረሱ፡፡
    - ቃሉን ተግተው የሚያጠኑና በፈጣን እድገት ጎዳና ላይ ያሉ፡፡
    - በሕይወታው ያደጉና ጥልቅ የቃሉ እውቀት ያላቸው፡፡
  • ቡድን የመጽሐ ቅዱስ ጥናት ወደ ጥናቱ የሚመጡ የተለያዩ ባሕሪት ያላቸውን አባላት ያቀፈ ነው፡፡
    ለምሳሌ፡
    - ለመናገር የሚፈጥኑ (መሪውንም ለመቅደም የሚሞክሩ)
    - ረጅም ንግግር የሚወዱ
    - አዋቂ እደሆኑ የሚማቸው
    - በጥናት ወቅት አውደ ጥ የሆኑ
    - ዝምተኞች(የያወቁም ቢሆን ለመናገር የይቸኩሉ
    - ሲሶችና በቀላሉ የሚጎዱ
    - አልፎ አልፎ ብቻ የሚናገሩ
    - ያለዓላማ የሚመጡ(በይሉኝታ)
    - ዓይፋሮችና በሰው ፊት ለመናገር የሚፈሩ፤ የመናገር ልምዱም የሌቸው ሲሆኑ እነዚህን ሁሉ አንድ ላይ አዋዶ በቡድን መምራት የመሪውን ከፍተኛ ጥረትና ትዕግሥት የሚጠይቅ ነው፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከግል ጥናት እንዴት እንደሚለይ
  • በግል ሲጠና በራስ ተነሳሽነት ከየትኛው ታ በነሳት ማጥናት የሚቻ ሲሆን በቡድን ሲጠና ግን የጥናት ክፍሉ ማዕከላዊ በሆነ አካል ይመረጣል፡፡ ለምሳሌ የክርሰቲያናዊ ትምህርት አገልሎት ባለበት ቤተክርሰቲያን ያ የአገልሎት ክፍል የሚመርጠን ካሆነ ደግሞ በመጋቢው በኩ ይመረጥና ይዘጋጃል፡፡
  • በግል የተፈለገው ያህል ምዕራፍ ወይም አንቀጽ ማጥናት የሚቻሲሆን በአንድ ጊዜ የቡድን ጥናት ከአንድ አንቀጽ ይም ቢበዛ ከአንድ ምዕራፍ በላይ ማጥናት አይችልም፡፡ ምክንያቱም በቂ ጊዜ ስለማይኖርና የክፍሉ ጭብጥ አሳብ ሳይያዝ ተንጠልጥሎ ሰለሚቀር ነው፡፡
  • በግል ለሚጠናው ጥናት ሰዓቱን የሚወስነው ግለሰቡ ራሱ ሲሆን በቡድን ለሚጠናው ግን በድኑ ራሱ ይወስናል፡፡
  • የቡድን የመሐፍ ቅዱስ ጥናት በቤስብ ደረጃ፣ በቤተክርስቲያን ደርጃ፣ በአንድ መሥሪያ ቤት የሚሠሩ አማኞች ወዘተ ሰብሰብ ብለው የጌታን ቃል የሚያጠኑበት መንገድ ነው። ብዙ ወገኖች በዚሁ መንገድ በሚደረገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በሕይወታቸው አድገዋል፣ ቃሉን በስተማርም ሆነ በመስበክ ውጤታማ አገልግሎት መስጠት ወደ ሚችሉበት የዕድገት ደረጃ ሊደርሱ ችለዋል።
የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሁለት አቀራረቦች አሉት
  1. ዳይዳክቲቭ (Didactic)አቀራረብ ዜዴ፡ ይህ አቀራረብ ከውስን አሳብ ተነስቶ አጠቃላይ መርሆን የሚዳስስ ሲሆን ወጥ የሆነ የጥናት ክፍል የለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህ ዓይነቱ አቀራረብ በሰለጠኑት አገሮች ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ ወጥ ለሆነና ተያያዥነት ላለው ጥናት አይረዳም፡፡
  2. ኢንዳክቲቭ (Inductive)አቀራረብ ዜዴ ፡ ይህ አቀራብ ዜዴ ከአጠቃላይ መርህ ተነሰቶ እውነታን በመዳሰስ ውስን ወደ ሆነው አሳብ የሚያደርስ የአቀራብ ዓይነት ነው፡፡ የኢንዳክቲቭ አጠናን ዜዴ ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ተነስቶ ወደ ድምዳሜና የሕይወት ተዛምዶ የሚያደርስ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ጊዜ ጥናቱ የሚጀምረው ከምንባቡ እንጂ ከተወሰኑ ውስን አሳቦች አይደለም፡፡ ውስንና የግል ጉዳዮች የሚዳሰሱት የንባብ ክፍሉ በተገቢው ሁኔታ ከተተነተነ በኃላ ያንን ትንተና መሠረት በማድረግ ነው፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የቡድኑን የውይይት አቅጣጫ ይጠቁማል፡፡ ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ እንዲናገር ለማድረግ ያግዛል፡፡
  • በሁሉም ጊዜ ከሚጠኑ የንባብ ክፍሎች በመነሳት የሚጠየቁ የጥያቄ ዓይነቶች አሉ፡፡
    እነርሱም ፡
  1. የምልከታ ጥያቄዎች፡ ክፍሉ ምን እደሚል ለመናገር የሚያስቸሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ክፍሉ ምን ይላል?ነጥቦችን ዘርዝር፤ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
  2. የትርጉም ጥያቄዎች፡ የክፍሉ አሳብ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የሚያስችሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በራስህ አባባል ገለጽ፤ ይህንን እንዴት ትረዳዋለህ የመሳሰሉት ጥያቄዎች ናቸው፡፡
  3. የትግበራ ወይም የተዛምዶ ጥያቄዎች፡ ተሳታፊዎቹ በንባብ ክፍሉ የተገኘውን አሳብ ከግል ሕይወታቸው ጋር እንዲያዛምዱት የሚረዳ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ በሕይወት እንዴት ሊተገበር ይችላል? ሬው ጥናት ያገኘኸውን ለቡድንህ አካፍል፡፡ ይህ አራረብ ... (ምልከታ፤ ትርጉምና ተዛም) ወይም ...(መመልከት፤ መተርጎም ና ማዛመድ ) ሎ ይታወቃል፡፡ መሪው የጥናት ቡድኑን በሚመራበት ወቅት እነዚህን ሦስት ዓይት ጥያቄዎችን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዝግጅቱ የቀረቡት ጥያቄዎች ግልጽ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ መሪው ግን በራሱ አባባል ለቡድኑ አባላት ግልጽ ሊያደርግ ይችላል፡፡
  • የዚህ ዓይነት ጥናት ዋና ዓላማ ፍ ቅዱስ ራሱ እዲናገር ማድግ ነው፡፡

የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተለይም የኢዳክቲቭ አቀራብ በምን እደሚያተኩር፡፡
  1. ምንባባዊ (Textual Study ) ፡ በምንባብ ክፍል ወይም በአንድ መጽሐፍ ላይ ያተኮረ ጥናት ነው፡፡ይህ ዓይነት አቀራረብ አንድን መጽፍ በሚባ ለማወቅ የሚዳ ነው፡፡ ለምሳሌ፤ የሮሜ መጽፍ፣ የኤፌሶን መጽሐፍ፣ የዘፍጥት መጽሐፍ ወዘተ ናቸው፡፡
  2. ርዕሳዊ ( Topical Study ) በአንድ ርዕስ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ይህኛው ደግሞ አስተምህሮችን ለመዳሰስ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ፡ ፍቅር፤ ቅድስና፤ በቤተ ክርስቲያ፤ ጸሎት፤ መስጠት ወዘተ የመሳሰሉት የጥናት ዝግጅቱ ትኩረት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
  3. ገጸ ባሕሪያዊ ( Character Study)፡ በንድ ሰው ሕይወት ላይ መሠረት ያደረገ ጥናት ሲሆን እግዚብሔር ብሉይ ኪዳም ሆነ በዲስ ኪዳ የተጠቀመባቸውን ሰዎች ሕይወት የሚተነትንና ከምሳሌነታቸው የሚያሰተምር ነው፡፡ ለምሳሌ፡ የዳዊት ሕይወት፤ የአብራሃም ሕይወት፣ የሴ ሕይወት፣ የጳዉሎስ ሕይወት፤ የየሱስ ሕይወት ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡





ክፍል ሁለት
የመሪው ሚና
  • በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት የቡድኑ መሪ ዋና ኤጄንት ስለሆነ ሊኖረው ስለሚገባው ሚና ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ በመሪው ምክንያት ሊያምርም ሊበላሽም ይችላል፡፡ ሁሉም የሚወሰነው በመሪው ማንነትና አቀራረብ ነው፡፡ ስለዚህ የመሪው ሚና እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
  • የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሪን ሚና በሦስት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡
  1. የመሪው ሚና ከጥናት በፊት
  • ጥናት ከመካሄዱ በፊት መሪው ግሉ መጋጀት ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ የመሪውን ተሳትፎ ከአማጮቹ የተለየ ያደርገዋል፡፡ የቡድኑ አባላት ወደ ጥናቱ ከመምጣታው በፊት በሚያጠኑበት የምንባብ ከክፍሉ ተዘጋጅተውበት መምጣት ቢችሉ መልካም ነው፡ እነርሱ ቢዘጋጁም ባይዘጋጁም መሪው ግን የመዘጋት ግዴታ አለበት፡፡ መሪው ከጥናት በፊት እዴት ነው የሚዘጋጀው;
  • ስለ አገልሎቱ እዚአብሔርን በማመስገን ተግቶ መጸለይ አለበት፡፡
  • ስለያጠኑ ሰዎች ስለ እያንዳንዳቸው በጌታ ፊት መማለድ አለበት፡፡
  • በተቻ መጠን የቡድኑን አባላት ስለ ዕለቱና ስለ ጥናቱ ማሳሰብ አለበት፡፡
  • ናት ክፍሉን በግሉ አቀድሞ ማጥናት ይኖርበታል፡፡ የጥናት ክፍሉን በግሉ ሲያና በጥናት ዝግጅቱ ለተቀመጠው ጥቄ መልስ ከመስጠት ጠለቅ ለ መልኩ ዘጋጀት አለበት፡፡
  • የንባብ ክፍሉ የሚስተላልፈው መልእክት ምን እደሆነ መረዳትመቻ አለበት፡፡ ለዚህም የሚዱ መርጃዎችና ማጣቀሻዎችን መጠቀም ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ መዝገበ ቃላት(ባይብል ዲክሺኔሪ ) ፤የቃላት ማውጪያ ( ኮንኮርዳንስ)፤የመጽሐፍ ቅዱስ ካርታ ( አትላሰ) እና የማብራሪያ መጻሕፍት ( ኮሜንታሪ) ሲሆን የማራሪያ መጻሕፍት ሲጠቀም መሪው በጣም ከፍኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም በተሳሳተ መንገድ የተተረጎሙ በርካታ ኮሜንታሪዎች ስላሉ ሙሉ በሙሉ በእነርሱ መተማመን አያስፈልግም፡ሩ የሆኑ ኮሜንሪዎች ግን ለመሪው ዝግጅት በጣም ጠቃሚዎች ናቸው፡፡
  1. የመሪው ሚና በጥናት ወቅት
  • ከተሳታፊዎችም ሆነ ከመደበው ሰዓት ቀድሞ መገኘት አለበት፡፡ አንዳድ መሪዎች ቀድመው በመገት መልካም ምሳሌዎች ናው፡፡ ቀድሞ መገኘካታ ጥቅሞች አሉት፡፡ ለምሳሌ፡
  • ቦታው ለማስተካከል የአባላት ወበር አማመጥ ማካከል የሚቻለው ቀድሞ በመገኘት ነው፡፡ የጥናት ቦታን በጥናቱ ጊዜ ለማዘጋጀት ሞከር ዓቱን ያክንና መጨረሻ ለይ ሰውን ሁሉ ለጥድፊያ ያጋልጣል፡፡
  • ቦታው ለጥናት ቡድኑ አባላት ተስማሚና ጸጥታ ያው መሆኑን ማረጋጥ፡፡
  • የአባላት አቀማመጥ ዙሪያ ክብ እን ያስፈልጋል፡፡ መሪውም ሁሉንም አባላት ሊያይ በሚችልበት ቦታ መቀመጥ አለበት፡፡
  • በጥናቱ ቦታ በቂ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ፡፡
  • ጥናቱን ልክ በሰዓቱ መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ማንኛውንም ፕሮግራም በሰዓት አለመጀመር በሰዓት እንዳያልቅ ያደርጋል፡፡ ፕሮግራምን በሰዓት መጀመር ተሳታፊዎቹ በጥናት ፕሮግራሙ ላይ መተማመን እንደዲኖራቸው ከማድረጉም በላይ በሚቀጥለው ፐሮግራም በንቃት እንዲመጡ ያደርጋቸዋል፡፡
  • ጥናቱ በሰዓት ከተጀመረ ደግሞ በሰዓት ለመጨረስ መትጋት ያሰፈልጋል፡፡ ባላቱ ለመምጣት ከሚቸኩሉ ይልቅ ለመሄድ እደሚጣደፉ ምንጊዜም የታወቀ ነው፡፡
  • ጥናቱ ሲጀመር ተገቢውን መግቢያ መስጠት፡፡
  • ፍቅርን የሚገልጽ አጭር ሰላምታ መስ
  • ናቱን በጸሎት መክፈት
  • አጭር ክለሳ መስ(ጥናቱ የተያያዘ ስለሆነ) የባለፈውን ጥናት አሳብ ማሰታ
  • 2 ደቂቃ ላልበለጠ ጊዜ ስዕለቱ ጥናት አጭር መግለጫ መስጠት ምክንያቱም አድማቹ የዕለቱን የጥናት ርዕሰ ጉእምሮአቸው እንዲይዙና እንዲዘጋ ይረዳል፡፡
  • የዕለቱን ጥናት ስትጀምር ክፍሉን በግልጽ ሁኔታ አንብብ ወይም አባላቱ ተከፋፍለው ዲያነቡት ጋዛቸው፡፡
  • ቡድኑን በምትመራበት ወቅት ብዙ እንዳትናገር ጠንቀቅ፡፡ የማጠቃለያ አሳብ መስጠት ካልሆነ በቀር ጥያቄውን ለአባላቱ አቅርብላቸውና አንተም አብረህ ተሳታፊ ለመሆን ሞክር፡፡
  • የቡድኑ አባላት በጥናቱ እንደሚገባ መሳተፋቸውን አረጋግጥ፡፡ ጥት ሰዎች ብቻ የሚሳተፉበትና የቀሩት ደግሞ ሰሚዎች ብቻ እሆኑ ተከታተል፡፡
  • ራስህን እንደ አስተማሪ አቁጠር፡፡
  • ጥያቄዎች ሲነሱ መልስ ከመስጠትህ በፈት ተሳታፊዎች ለቀረበው ጥያቄ መልስ ዲሰጡት አበረታታቸው፡፡ የተሳታዎች መልስ አርኪ ካሆነ አንተ መልስ ስጥበት፡፡ ጥያቄው ከባድ ከሆነ ደግሞ ሌሎችን ለማማከር ተስፋ ስጥ እንጂ ያሆነ ልስ እዳትሰጥ ተጠንቀቅ፡፡ ሉን ጥያቄ የመመለስ ግዴታ ሊኖርብህ ይችም፡፡
  • በጥናት ቅት የቁጣና የተግሣጽ ባሕሪይ እንዳይታይብህ ተጠንቀቅ ይልቁንም ሁሉን በፍቅር ተቀበል፡፡
  • አባላት አሳብ ሲሰጡ ከንባብ ክፍሉ አሳብና ከአውዱ እወጡ ተከታተል ምክንያቱም የአሳብ መልቀቅ ወይም ከርዕስ ውጭ መሆን የጥናን መድሻ ያበላሸዋል፡፡
  • የጥናት ክፍሉን ጥያቄ አባላቱ ፊት እንዳታጠና ተጠንቀ፡ ይልቁንም አስቀድ በአእምሮህ ተዘጋጅተህበት መምጣ ያስፈልጋል
  • በጥናት ጊዜ ክርክር እንዳይኖር ለመቆጣጠር ሞክር፡፡ የሚከራሩ ሰዎች በክርክራቸው ለመቀጠል የሚፈልጉ ከሆነ ጉዳን ትተው ወደ ሌላ ነጥብ እዲሸሩ በጥበብና ዜዴን መጠቀም፡፡
  • እያንዳንዱ ተሳታፊ የሚያቀርበው አሳብ አክብር፡፡ አሳብ አቅራቢውም አበረታታ፤ የሚያቀርበው አሳብ ልክ ካሆነ በፍቅር አስረድተህ መልሰው፡፡
  • በርካታ ጥቅሶችን ከተለያዩ ቦታዎች መጥቀስ ለአሳብ መልቀቅ ( ለአውደ ወጥ) ንስኤ ስለሚሆን ከፍኛ ጥንቃቄ አድርግ፡፡
  • አባላቱ በተቻለ መጠን መጽፍ ቅዱስ ይዘው እንዲመጡ አበረታታ፡፡
  • ጠጥረሩነና መለከካመም የሀሆነ መደመምደመሚየያ አደድረርገግ
  • ከጥናት ክፍሉ የተገኙ አሳቦችንና ዋና አሳቡን ጠቅለል አድርገህ ለአባላቱ አስጨብጥ
  • በጥናቱ ተገኝተው አሳባቸውን ያካፈሉትን ሌሎችንም በአጭር ቃል አመስግናቸው፡፡
  • በሚቀጥለው የጥናት ክፍል ተዘጋጅተውበት እንዲመጡ አሳስባቸው የንባብ ክፍሉንም ንገራቸው፡፡
  • ከቤተ ክርሰቲያን የሚተላለፍ መልእክት ካለ ባጭሩ ተናገር፡፡
  • የፀሎት ርዕስ የሚሰጥ ሰው ካለ ተቀበል፡፡ የይሁን እንጂ እንዳይንዛዛና የሚቸኩሉ አባላት ልብ እንዳያንጠለጥል አድርግ፡፡ ፕሮግራሙን በጸሎት ዝጋው፡፡
  1. የመሪው ሚና ከጥናት በኃላ
የመሪው ሥራ ከጥናቱ በኃላም የሚቀጥል ነው፡፡ ስለዚህ የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን የመምራት አገልግሎቱን ካጠናቀቀ በኃላ ሊያደርጋቸው የሚገባቸውን ነገሮች በአጭሩ እንመልከት፡፡

  • አባላቱ ጥናቱን በተገቢ ሁኔታ ማጥናት አለማጥናታቸውን ፤በሰዓት መገኘት አለመገኘታቸውን፤መሪው ራሱ በሰዓት ጀምሮ በሰዓት መጨረስ አለመጨረሱን እና ሌሎች ነጥቦችን መሠረት በማድረግ አጠቃላይ የጥናቱን ሁኔታ መገምገም ይኖርበታል፡፡
  • መሪው በጥናት ወቅት የተቸገረባቸው እና መፍትሔ ለመስጠት ያልቻለባቸው ጉዳዮች ካሉ ለቤተክርስቲያን ሪፖርት ማድረግ የጋራ መፍትሔ ሊፈልግ ይችላል፡፡
  • በተቻለ መጠን ረዳት ሊሆን የሚችል ሰው ማዘጋጀት ፡፡ መሪ ተተኪ ሊያፈራ ከቻለ አገልግሎቱ ከሁሉም አንጻር እድገት እያሳየ ሊሄድ ይችላል፡፡
  • ከጥናት ቡድኑ አባላት ጋር በጥሩ ግንኙነትና መቀባበል ቀጥል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለሁሉም በሁሉም የአገልግሎት ወቅት ጸጋውንና ምሕረቱን ያብዛ፡፡ አሜን፡፡ 

Are Apocrypha authoritative words of God?

አእዋልድ  መጻሕፍት ሥልጣናዊ  የእግዚአብሔር  ቃላት  ወይስ
k°StR ±mƒa_L àN¬
yKRST³ AMnT b¹lM ·lƒ yAMnT aYnÄ{ aNë&³ TLq> s^ÒN yz^U AMnT KFL ytqdsW m:hF «m:hF Që&S» tBÉ Ye™L¥¥ kl_É{ y¾YìÑT m©HFT m:hF Që&SN Ly„ kì@¶dRg&T g:ª¿{ aNë& bKRST³ AMnT CR ¶lƒ Bz& b_t AMnÄ{ m:hÛN y™±[W ìDr¬[W nW¥¥ YU Bê ±YÒN yAMnT KFÉ{ YUNN Që&S yÒnWN yAGz^aBh_RN šL ANdms®[W³ ANdtmê[W yì@rë&T ÒÑ mgit>M kl_É{ yhYìÑT m©HFT Ly„ ¶Rg§L¥¥ lM±l_ yA¼ AMnT KRST³ nW yì@lƒT ÁRÄÌKS¤ ·Äl^K¤ ì…Äë^ST¤ jÒ² MSKÅ{¤ wNg_®W¶N¤ /_Ne_ÖS½W¶N A³ l_É{M Ygi„bªL¥¥ Anz^U uƒlƒM KRSt#¶Ñ{ nN BlW Sl ì@¶Mn& yAMnª[W mcrT m:hF Që&S nW¥¥ YuƒN ANé@ aNëNÌ{ bz^U baNë& m:hF ®Y s^xMÝbT l_É{ dGÀ mcrª§# TRg&mƒN s^¶ºb&T YSt§®lƒ¥¥ s¿{ wYM AMnT KFÉ{ m:hF Që&±{NN ANdms®[W Yrë&T ANé@ wYNM Y^xMÝbT³ bms®[WM mNgD YtRg&mƒT ANé@ yšlƒ AWnt¼nT³ taìn@nT MNg^z_M a¶e™ERM¥¥ kKRST³ WX yÒn&T aNëND AMnÄ{ bms®[W mNgD AytrgmƒT l^¶½ElƒT b^ÀKÝM yAGz^aBh_R šL nW³ aLtlweM¤lz®lMM aYlwEM¥¥
bPÅt†SªNT³ bl_É{ aNëND yKRST³ AMnT KFÉ{ m·kL ymn¬gÞ¶ ajNë ÒÑ lzm³T yÑrW yaA§LD m©HFT g&ëY nW¥¥ aA§LD ìlT ytdbq ìlT s^ÒN aNëND TRg&À{ ANdì@¶±y„N dGÀ AWnt¼nt> lìmN yì@¶e¶YQ wYM yì@¶e™eR ANdìlTM nW¥¥ YU TRg&M km©HFT ¬R lt¶¶z& g&ëÇ{ ytse s^ÒN yPÅt†SªNT b_t KRSt#¶³T aA§LD m©HFTN yì@rë&T bz^uƒ mLK nW¥¥ aC™ aMSt>N yaA§LD m©HFTN xMÅ bBlƒY k^ëN WSE ¾M± a™T ¶UL Që&±T m©HFT Yg¼lƒ yì@lW TMURT lPÅt†SªNÄ{ aL§E BÉa[§L¥¥ Slz^U bAnRs& aåM bqѳ mlk^¶ ¶lÛ ym:hF Që&S Që&±T m©HFT bBlƒY k^ëN 39¤ baë^S k^ëN dGÀ 27 Bê SlÒn& bm:hF Që&S WSE 81 Që&±T m©HFT alƒ yì@lW a±B tq²YnTN a®giM¥¥ aA§LD m©HFT ba^TÇ?¶ Bê ±YÒN bl_É{ y¹lì{N KFÉ{M ASk A.a_.a.1546 DrS bqѳ m©HFT LST WSE ±Y·tt>³ tq²YnTN ±¶gi„ Ñr§L¥¥ A.a_.a. b1546 yt·¾…dW yTrNT g&²a_(·WNs^L ÁF TrNT) kl_É{ yGLet-ml×T³ yqѳ m©HFT ¬R Ak&L CF™³ GMT ANë^^seW aDRÆ ANdnbR bªÞK ANmlkªlN¥¥ yÅì ·Äl^K b_t KRSt#¶NM YUNN mná bìdrG (l^ÒN Y{®L) yaA§LD m©HFTN ANd l_É{ yBlƒY k^ëN m©HFT uƒlƒ CL½³§# šL aDR¬ tqBl§l{¥¥ YuƒN ANé@ yPÅt†SªNT b_t AMnÄ{ kz^U bª{ b_qme& abYT MKN¶Ä{ yTrNT g&²a_N W±n… W±n…¶[W aDRgW aLtqblƒTM¥¥
  1. aYuƒÌ{ baA§LD m©HFT mNf±§# CL½N a®mn&bTM¥¥ bARGE aYuƒÌ{ yAMnT aåMN yì@¶;Dq> wYM yì@}Ý aYdlƒM¥¥ AnRs& ytqblƒT TKKL wYM ¶LtqblƒT uƒlƒ mƒlƒ bmƒlƒ WDQ YÒ³L ìlT aYdlM¥¥ lM±l_ ba^ys&S ms^UnT ±¶Mn& lrJM g^z_¶T yÑݳ ¶NN yHYwT ™S yÒnWN g_ª ysqlƒT AnRs& ANdÒn& S³Y lKRST³ AMnT aåM g&ëY bAnRs& mdgF l^¶±ST Y{®L¥¥ b^ÒNM Sl Që&±T m©HFT s^n± AnRs& mdmE ANël²[W aY·DM¥¥ MKN¶t>M yHG mseT kìNM bÜT lAnRs& SlÒn CL½³§# š®TN bì@g² ¶Wq>ªL¥¥ yBlƒY k^ëNN mLAKT ytqblƒ ymjmÞ¶¿[> aDìÓ{ wYM tq²Ç{ aYuƒÌ{ ³[W¥¥ bmNfS Që&S tnDtW yQë&±T m©HFTN y©ÛT ytl¶y„ d™s^¶N bmƒlƒ kaYuƒD HZB yÒn& nb^¶Ä{ wYM kAnRs& wgN yÒn& Që&±N s¿[ ³[W¥¥ yAGz^aBh_R šL TNb^T bmƒlƒ ytseW aSqDÀ lAnRs& nW¥¥ Slz^U AGz^aBh_R bz^¶N g^z_ lseW šL mªzZ almªzº[W l_® g&ëY YuƒN ANé@ yTÚ[ š®T kAGzaBh_R ANdÒn&³ yTÚ[> ANëLÒn& lYtW lìwQ Bz&M l^[G™[W aY{LM¥¥ ªë^¶ aYuƒD SlÒn Bê ymglEN šL Yly§L ±YÒN AWntÚ[> aìÚ{ yÒn&TN ìlª{N ANdÒN l^smRbT Yg²L¥¥ Slz^U yaA§LD m©HFT yAGz^aBh_R šL aYdlƒM wYM ³[W lìlT KRST¶N aYuƒÌ{ mrët>M aQmƒM a®[W¥¥ btxìÞM yaA§LD m©HFT yt;ÛT bAB™YSE åNå ±YÒN bGÞK åNå nbR¥¥ yåNå g&ëY BêWN w±I nW BlN ²³SBM AGz^aBh_R ls¿{ mLAKt>N ¶St®lfW ysW LÐ{ l^rë&T bìY{lƒT³ bìYªwQ mNgD ±YÒN A¶NëNë& HZB l^G²²W³ l^rëW bì@{L åNå mÒn& yìY·D nW¥¥ bg^z_W ynbÝ td™s^¶NM Òn& d™s^¶N yì@G²b&²[W §N¼ åNå AB™YSE nbR¥¥ yGÞK ²UL³ åNå b½M ytS¨¨W kª®q> al_K±NDR b¸® bmÒn& kz^¶ bÜT bnbÝT g^z_¶Ä{ yGÞK åNå laYuƒD HZÏ{ §N¼ mG²b^¶ aLnbrM¥¥ HZb& åNåWN xRÎ yìYrëW kÒn AGz^aBh_R yì@seW mLAKT We_T l^¶m½ bìY{L uƒn…ª t®lf ìlT nW¥¥ ysìWN ngR ¶Ltrë HZB NSh gBÄ khe^at> l^mlS¤lAGz^aBh_R MC¬³ ™s&N l^¶z¬J aY{LM¥¥ AGz^aBh_R dGÀ ANdz^U ¹YnT DFN ²l TRg&mƒ bìYªwQ uƒn…ª yì@³gR aM®K aYdlM¥¥ bAnz^U MKN¶Ä{ aYuƒÌ{ yaA§LD m©HFT yAGz^aBh_R CL½³§# š®T ³[W BlW a®mn&bTM¥¥ y¶z&TM aåM lPÅt†SªNÄ{³ ll_É{ b_t AMnÄ{ a±ìI nEB ÒÑ ytgi YmS®L¥¥
  2. m©HFt> yt©ÛT yBlƒY këN ymxrá m:hF kÒnW kTNb^t ì@Lk^¶S b¸® nW¥¥ kTNb^t MLk^¶S ASk aë^S k^ëN mjmÞ¶ ¤yBlƒY k^ëN ymxrá³ yaë^S k^ëN ymjmÞ¶ nb^Y ynbrW mEmq> ÇhNS ASKglE DrS b^¶NS 400 ¹mªT aLf§L¥¥ YU wQT yTNb^T mNfS yìYglEbT¤yxlì zmN tBÉ yì@ªwQ g^z_ nbR¥¥ bz^U zmN ytns& d™s^¶N knb^¶T wgN ²lmÒ³[W ymLAKt> taìn@nT E¶q† WSE gB~L¥¥ bBlƒYM Òn baë^S k^ëN yAGz^aBh_RN šL yì@¶me& s¿{ nb^¶T wYM h§Þ¶T ·LÒnM knb^¶T³ kh§Þ¶T ¬R aBrW yAGz^aBh_RN C™ ycÝ lAnRs&M yQRB MSKÅ{ mÒN ANël²[W yqѳ Hg& ¶M³L¥¥ ngR GN yaA§LD m©HFT d™s^¶N bBlƒY k^ëN wQT kAGz^aBh_R CL½N kts½[W nb^¶T m·kL ¶LÒn& wYM kAnRs& ¬R bQRB bAGz^aBh_R mNGCT ¶lcÝ bmÒ³[W aYuƒÌ{N xMÅ bR·ª yPÅt†SªNT b_t AMnÄ{ Anz^UN m©HFT yAGz^aBh_R CL½³§# šL BlW ±Yqblƒ ASkauƒN DrS sNBt§L¥¥
  3. aë^S k^ëN laA§LD m©HFT AWQ³ aLs½[WM¥¥ yQë&±T m©HFT ìOk®§# mLAKT aND s^ÒN ¶WM ms^uƒ KRSÄS nW¥¥ g_ª a^ys&S KRSÄSM s^³gR mƒs_ Sl An… :ÂaL al(Çh.5¥46)¥¥ A³Nt bm©HFT yz®lM HYwT ANë®{uƒ YmS®{çL³ AnRs&N TmrM™®{uƒ.¤ AnRs& Sl An… yì@msKÝ ³[W(Çh.5¥39) BÉaL¥¥ a^ys&S Që&±T m©HFT ²lb_T³ yšlƒ sX nW¥¥ šÉ[† bA³Nt b^ÑÝ (Çh.15¥7)¤šl_N sMÄ(ìt†.5¥24¤lƒšS 6¥47)¤bAn…³ bšl_(lƒšS 9¥26)¤sìY³ MDR ¶L¨lƒ šl_ GN aYLFM (lƒšS 22¥33)s^L ARs& yšlƒ g_ª³ ²lb_T mÒn&N lì±yT ANdÒn MNM a¶e™ERM¥¥ YU ANë^U ÒÑ ±l a^ys&S bMDR ®Y btm®ls²[W³ ²Stìr²[W g^z_¶T kBlƒY k^ëN ·lƒ Që&±T m©HFT Ayeqs aStMÅaL¥¥ kmƒs_ yHG m©HFT¤knb^¶T m©HFT¤kªÞK m;HFT¤kmZmƒR A³ kQn… m©HFT Ayteqs aStMÅaL¤lì@eYq>TM s¿{ tgb^WN M®} sE~L¥¥ ngR GN bTMURt>³ bSBkt> wQT ANë^uƒM fr±W¶N¤së&šW¶N³ l_É{M HZÏ{ lì@eYq>T E¶q†¿{ mLS lmSeT kaA§LD m©HFT yeqsbT CF™ ylM¥¥ h§Þ¶TM bmLAKÄê[W kBlƒY k^ëN m©HFT eQsW b^¶StMݳ lb_t KRSt#¶N mLAKT b^¶St®LÛM kaNDM yaA§LD m©HFT u±B a®·tt>bTM¥¥ YU nW ANGë^U aë^S k^ëN yaA§LD m©HFTN a®wqWM ANDNL ¶SêlN¥¥ m:hF Që&S mƒlƒ yAGz^aBh_RN mLAKT y¶z nW yMNlW yBlƒY³ aë^S k^ë³T aND ¹YnT mLAKT s^¶St®LÛ nW¥¥ bBlƒY k^ëN ytseW yAGz^aBh_R tS¨ mf;mƒN yaë^S k^ëN mLAKT YnGr³L¥¥ kz^U aN©R yaA§LD m©HFT DRá bg&LU S®Lªy auƒN ¶l{WM b_t KRSt#¶N ANd SL½³§# yAGz^aBh_R šL aDR¬ LTqb®[W aLêl{M¥¥
  4. b18¼W KFl zmN yKRSt#¶³§# aStMUÅ MuƒR ynbÝ ÌKtR ÅbRT à ANdt³gÝT Anz^U yaA§LD m©HFT bR·ª SUtT ¶l²[W¤ bkNt> ngR yì@¶Mn&¤ yt±±t a±B ¶l²[W³ yCn MG²R g&DlT yì@N;²rQ²[W s^Òn& ;hÜ¿ê[WM yAGz^aBh_RN ymglE šL yì@³gÝ aLnbÝM¥¥ ìN¼WM ymNf±§# m:hF d™s^ bAGz^aBh_R mNfS ·Ltm™³ yARs&NM am™R ·Ltqbl baNDM Òn bl_® SUtT mFeÝ yìYqR nW¥¥ ynb^¶T TNb^T mNfS ²Lc™bT zmN tnStW m:hF y©Û s¿{ ymLAKª[W MNX AnRs& ™±[W³ bz&Þ¶[W ¶lW uƒn…ª Bê ANé@ ml×T l^ÒN ANdìY{L GL: nW¥¥ baND bk&L yì@¶St®LÛTN ìlܶ a±B bl_®W š®[W ìFrS GD l^ÒN²[W Y{®L¥¥ ARs& Bê b^ÒN ²Lk¨¤GN kml×T ktseW SL½³§# šL ¬R s^®tmƒ ™±[WN l^¶gi„T Y{®lƒ¥¥ ad¬W Az^U ®Y nW¥¥
yANGl^Z aB¶t KRSt#¶³T³ yPÅt†SªNT b_t KRSt#¶³T yaA§LD m©HFTN GLet-ml×T ³[W BlW aYqblƒ ANé@ ym©HFt>N ešìn@T aL]]g&M¥¥ btlYM yANGl^Z b_t KRSt#¶N yaA§LD m©HFTN ANd qѳ ²Tqb®[W³ bAnRs& tmCRª yAMnT TMURÄ{N ²Tgn²²[WM kAnRs&(kaA§LD m©HFT) aNëND KFÉ{N wSë bb_t KRst#¶N ANë^nbB fQël{¥¥ YUNN ¶drg{W mlת§# mglE Sltgi²[W ±YÒN lHYwT M±l_nT³ ln&Å CR¹T YeQìlƒ bì@L A±b_ nW¥¥ aB¶t KRSt#³T m©HFt>M laN²b^¶N wQª§# mré kmSeT aN©R ANdì@eQmƒ ¶Mn&bªL¥¥ ngR GN aA§LD m©HFT yAGz^aBh_R CL½³§# šL aYdlƒM yì@lW AMnT auƒNM y;³ nW¥¥ Slz^U bqѳ mCfRT ¶lÛT yBlƒY³ yhë^S k^ë³T Që&±T m©HFT yAGz^aBh_R CL½³§# šL ³[W yì@lW 15t>N yaA§LD m©HFTN ±YxMR bmÒn& yauƒN§ b_t KRSt#¶NM lwNg_L MSKRnT ¤lìStìR agLGÉT ¤ lKRSt#¶³§# aStMUŤ lb_t KRSt#¶N yAMnT aåM³ mGl´ b66t> m©HFT Bê mmCrT tgb^ nW¥¥ MKN¶t>M k®Y btd¬ì@ ANdtgl;W aA§LD m©HFT ešì@ mÒ³[W yìY·D b^ÒNM yìYlwe&³ yìYáÝ bCL½N ytÀlƒ yAGz^aBh_R š®T S®Ydlƒ nW¥¥ Që&±T m©HFT kAGz^aBh_R ytse& mglÕ{ SlÒn& yAGz^aBh_R šL bmÒ³[W mƒlƒ bmƒlƒ A³MN²[§lN¤ANgº®[§lN¤ANtgB™[§lNM¥¥ YU bANë^U ANël yaA§LD m©HFTN ìNbB ytwgz aYdlM¥¥ yANGl^Z b_t KRSt#¶³T ANëdrg&T M±l_ l^Òn& yì@{lƒ ešì@ a±Ï{N LNwSD²[W AN{®lN¥¥ bENšq† B³n²[W lAWqª{N Yrb&³L ANé@ aNkSR²[WM¥¥ yÒn ÒÑ yaA§LD m©HFT SL½³§# yAGz^aBh_R šL aYdlƒM¥¥



ምድራችሁን እፈውሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር (ክፍል አንድ)

ምድራችሁን እፈውሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
Pastor Samuel Shonga
በአገራችን ሰው ሁሉ የሚሻውና ለወገኑም የሚመኝለት ሙሉ ጤናን ነው። ለወዳጃችን መልካሙን ስንመኝለት አምላክ ጤናን ይስጥህ እንጂ ሁሉም ይደረስበታል እንላለን። “ዋናው ጤና ነው” ማለት አንዳንዴ እንደ ልማድ የሚዘወተር ንግግር ቢመስልም ቂሉ የጤናን አስፈላጊነት አጉልቶ የሚያሳይ ጉልበታም አባባል መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡ የጤንነት ጉዳይ ከፍ ያለ ትኩረት የሚሻና ከብልጥግናም የሚበልጥ ዋጋው የማይታወቅ ሀብት ስለሆነ ብዙዎች ስለ ጤናቸው ስሉ ብዙ ሀብታቸውን ለሕክምና ሲያፈሱት ከሚጠብቁት ጤና ጋር ሲወዳደር ስለ መዋዕለ ንዋያቸው ምንም አይጨነቁበትም። ጤና ቢጎደል የሀብት ክምችት ብቻውን ባለቤቱን የሚያስደስትበት አቅም ሊኖረው አይችልም።
የጤና ችግር ያለበት ሰው ከምንም በላይ ፈውስ ይናፍቃል። ዛሬ በዓለም ላይ በብዙ ሀብትና ባለጠግነት የተጎበኙ፣ የተከማቸ ብርና ወርቅ ያላቸው፣ ዳሩ ግን ከዚያ ገንዘብ እንደ ልባቸው መመገብና መደሰት እንዳይችሉ የጤናቸው ሁኔታ እንቅፋት ስለሆነባቸው አምላክ ሀብት ከሚሰጠኝ ጤናን ቢሰጠኝ ይሻለኝ ነበር የሚሉ ጥቂት አይደሉም። የጤና ማጣት ብዙ ነገርን ሊያቃውስ የሚችል ታላቅ የሕይወት ተግዳሮት ነው። ስለዚህ የታመመ ሁሉ ፈውስ ያስፈልገዋል። የሚያስፈልገን ግን መለኮታዊ ፈውስ ነው። የሥጋ ፈውስ ብቻ ሳይሆን የምድር ፈውስም በሚያስፈልገን ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን።
ይህንን መልዕክት የምታነቡ ወገኖቼ ሁሉ መልዕክቱን በልባችሁ አኑራችሁ በሕያው እግዚአብሔር ፊት እንድትፀልዩ አደራ ለመስጠት እፈልጋለሁ። ማንበብና መፀለይ ብቻ ሳይሆን ለምታዉቁትና የጌታ ነገር ግድ ይለዋል ብላችሁ ለምትታመኑበት ሰው አስተላልፋችሁ አደራ በአምላክህ ፊት ስለ ኢትዮጵያ ፀልይ እንድትሉ በጌታ ፍቅር እማፀናችኃለሁ። መልእክቱን ሳስተላልፍ ማራኪና ደማቅ የአገላለጽ ዘይቤ ለመጠቀም ያልቻልኩት የሥነ ጽሑፍ ሰው ባለመሆኔ ነው። ስለዚሀ አንባቢያኖቼ ደካማ በሆነው አማሪኛዬ ምክንያት የሚተላለፈውን የጌታን ድምፅ ሳታገኙት እንዳትቀሩ አደራ።
ስለ ራሴ ብዙ መናገር የጽሑፍ መልዕክቴ ዋና ዓላማ ባይሆንም መቼም ትውውቅ ሳይደረግ ወደ ንግግር ስለማይገባ ጥቂት ልበላችሁ። ተወልጄ ያደግኩት በክርስቲያን ቤተሰብ ሲሆን የጌታን አገልግሎት የጀመርኩት በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ ሳለሁ የቅዱሳንን እግር በማጠብ ነበር። ቀጥሎም በቤተ ክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ፣ በወንጌላዊነትና በጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና መጋቢነት ለ7 ሙሉ ዓመታት በማገልገል የጌታን ታላቅ እጅ ለማየት ዕድሉን አግኝቻለሁ።
ከወላይታ ጀምሮ በናዝሬትና በአዲስ አባባ በነበረኝ የአገልግሎት ዘመኔ ስለ አገራችን ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ከሚያነቡላት ጋር የማንባት ከሚቆረቆሩላትም ጋር የመቆርቆር ዕድል ጌታ ስለ ሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ። ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ ስለሚነገረው ትንቢትና ስለምድሪቱ ይማለድ ዘንድ ስለተዋቀረው የፀሎት ኔትወርክ ክብሩን ጌታ ሊወስድ ይገባዋል። ከቅዱሳን ወገኖቼ ጋር ባሳለፍኩባቸው ጊዜያት ስለ አገራችን ኢኮኖሚያዊና መንፈሳዊ ሁኔታዎች እንድማልድ በልቤ ውስጥ ትልቅ ሸክም አደረብኝ።
ከአገሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣሁት ሐምሌ 26 ቀን 2003 .. ነበር። በዕለቱ ከባለቤቴና ከሁለት ልጆቻችን ጋር በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 5 ሰዓት ተኩል ከአዲስ አባባ ተነስተን ሊነጋጋ ሲል በፍራንክፈርት ካረፍን በኃላ በማግሥቱ በአሜሪካ ውስጥ በትልቅነትዋ ወደ ምትታወቅዋ ኒው ዮርክ ከተማ ስንደርስ ወደ ግራንድ ራፒዲስ የሚወስደን አውሮፕላን ስላመለጠን እዚያው ኒው ዮርክ ማደር ግዴታችን ሆነ። የአውሮፕላኑ ሁኔታ ቢያሳዝነንም ባለበቴና ልጆቻችን ከመንገዱ ድካም የተነሳ በኒው ዮርክ በማደራችንና እረፍት ማድረግ በመቻላችን ደስ ብሎአቸው ነበር። ለእኔ ግን ያቺ ምሽት ለብቻዬ ከጌታ ጋር ስለ አገሬ በልዩ ሁኔታ ስነጋገር ያሳለፍኩባት የተለየች ምሽት ነበረች። ያረፍነው ራማዳ ፒላዛ ሆቴል በተሰኘው ሥፍራ ሲሆን ወደ ሆቴሉ ዘግይተን ስለ ደረስን ከታች ባሉ ፎቆች ክፍል ስላልነበር ወደ 11ኛ ፎቅ ላይ ለመዉጣት ብንገደድም ሆቴሉ ኤልቬተር የተሰኘ መሣሪያ የተገጠመለት ስለሆነ ወደምንፈለገው ፎቅ ለመድረስ ልፋት አልጠየቀንም። ሁላችንም ወደ ክፍላችን ከግባን በኃላ ሥጋችንን ለመደገፍ ጥቂት የሚበላና የሚጠጣ ነገር ሸምቼ ባመጣም ቤተሰቦቼ ከበድ ያለ ድካም ስለ ጫጫናችውና እንቀልፍ በኃይል ስላሸለባቸው አልተሳካልኝም። ዳሩ ግን እኔ ጥቂት ቀማመስኩና በመስኮት በኩል የኒው ዮርክ ከተማ በከፍል ስለምትታይ ወንበር ሳብ አደረግኩና እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ጥበብ ምንኛ ታላቅ ነው የሚያስኘውን የከተማዋን ውበት ማድነቅ ጀመርኩ፡፡ ከተማው በምሽት ለሚያይ እንግዳ ሰው በእጅ የተሠራ ብሎ ለማመን የሚያደናግር ውበትና ለዓይንም የሚታክት ስፋት ያለው ነው።
በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ እግዚአብሔርን አንድ ጥያቄ የጠየቅሁት። ለመሆኑ ኢትዮጵያም በዚህ ምድር ላይ ትኖራለች ፣ኒው ዮርክም ከእኛ ጋር በዚህ ፕላኔት ላይ እኩል ኑሮ ትጋራለች ማለት ነው? አልኩኝ። በአገሬ ሳለሁ ስለ ኢትዮጵያ ከሚፀልየው ይልቅ በተለየ መልክ መፀለይ የጀመርኩት ከዚያች ሌሊት ጀምሮ ነው።
በጌታ ፊት ከልብ በሆነ መቃተትና ምልጃ እንድቆይ የእግዚአብሔር መንፈስ ይምራኝ ነበር። አዳሩን በዚያ ሁኔታ ምንም እንቀልፍ የሚባል ሳያሸልበኝ አድሬ ወደ ግራንድ ራፒዲስ ከድረስንም በኃላ በምድሪቱ ላይ የሚታየው የልምላሜ ሁኔታ በአገራችን በየትኛውም ክልል፣በደቡብና በምዕራብ ካየሁት በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ነው ብል ቅንጣት ያህል ተጋኖ አይኖርበትም። ይህንን የምነግራችሁ ሌላውን ፈርጀ ብዙ የሕዝቡን ዕድገት ሳልጨምር የከተሞችን ድምቀትና የምድሩን ልምላሜ ብቻ በመጥቀስ ነው። በእነዚህ የፀሎት ጊዜያቶች እግዚአብሔር ግልጽ መልዕክት ሰጠኝ።
እግዚአብሔር አምላክ በፀሎቴ ወቅት የተናገርኝን መልዕክት በጣም ታዋቂ ለሚባሉ ፓስተሮች ሳካፍላቸው ምንም ግምት አለመስጠት ብቻ ሳይሆን እንደቀልድም ጭምር ማየታቸው ከምንም በላይ አስገርሞኛል። ቢሆንም ለአፍሪካ ቀንድ ሸክም ተሰምቶአቸው በጾምና በፀሎት የሚጋደሉ ወገኖችን ጌታ አዘጋጅቶልኝ የውስጤን መልዕክት ለእነርሱ በማካፈሌ ደስታዬ አጥፍ ድርብ ሆነ። የቱንም ያህል ቢዘከዘክ የማያልቅ ቁጥር ሥፍር የሌለው ጉዳይ ስላለ በጣም ሩቅ ሳልሄድ በቀጥታ ወደ መልዕክቴ መግባት ይሻለኛል።
በፀሎቴ “ጌታ ሆይ ኢትዮጵያን ለምን አትጎብኝም?” እያልኩ ሳነባ ከበፊቱ ይልቅ የተለየ መረዳት በአእምሮዬ እንዲፈስ ያደረገው የጌታ መንፈስ ነው ብዬ አመንኩ። ምክንያቱም እንደዚያ ዓይነት መረዳት ከዚያች ጊዜ በፊት በአገሬ በነበርኩበት ጊዜ አልነበረኝም። በአሜሪካ ውስጥና በካናዳ ያሉ የተወሰኑ አካባቢዎችን ባየሁ ቁጥር የፀሎቴ ጥያቄ “ ጌታ ሆይ ኢትዮጵያ መቼ ነው የምትባርከው?” የሚል ነበር። ይህንን የሚለው በረከት ማለት በዓይን የሚታይ በቁሳዊና በምድራዊ ንዋይ መንበሽበሽ እንደሆነ ከነበረንም ልማድና ከልማዳዊ ስብከት ተጽእኖ ሥር ስለወደቅኩ እንደነበር ብዙም አልገባኝም ነበር። የጌታ መንፈስ ፣ መንፈስ ቅዱስ ግን “ምድሪቱ በከት አላነሳትም ይልቁንም ያጣችው ፈውስ ነውአለኝ። ይህ ድምፅ በጣም ግራ አጋባኝ። ምን ማለት ነው በረከት አላነሳትም ፈውስ ነው ያጣችው ማለት? ከዚህ አሳብ በኃላ አስተሳሰቤ ተቀየረ።
በእርግጥም አገራችን የተባረከች ናት። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በብዙ አንጻር ባርኳታል። ``ምድራችን ፍሬውን ከመስጠት አቋርጦ አያውቅም። ወንዞቻችን መፍሰሳቸውን ቀጥለዋል። በምድሪቱ ዉስጥ ስላለው የማዕድን ክምችት ባለሙያዎች የሚነግሩን ዘገባ ለማመን የሚያስቸግር ነው። ይህ አሁን የመጣ ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው። ወርቅና የድንጋይ ከሰል በቅርብ ጊዜ ትግላችን የመጣ ሳይሆን እግዚአብሔር አምላክ ከዘመናት በፊት በምድራችን ውስጥ ያስቀመጠልን ነው። ልዩነቱ ይህ ሁሉ መኖሩ የታወቀው ጊዜው ስለደረሰ አሁን በመሆኑ ነው እንጂ። በፊት ያልነበሩና አሁን የተከሰቱ ደግሞ አሉ። ለምሳሌ የሂዳሴው ግድብ የአገራችንን የቀድሞውን መጥፎ ሥዕል የቀየረ የዘመኑ አስደናቂ የሰው ልጅ ሥራ ነው። ታዲያ አገራችን አልተባረከችም ሳይሆን እግዚአብሔር የሰጣትን በረከት አልተጠቀመችበትም ነው ማለት ያለብን። የጌታ መንፈስ በግልጽ የነገረኝ ይህንን ነው። “እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በሁሉም አንጻር ባርኮአታል ነገር ግን አገሪቱ መባረክዋን ገና አልተረዳችምና ባረከኝ ትላለች። የምድሪቱን ፍሬ ሕዝቦችዋ መብላት አልቻሉም። ፍሬዎች ስል የሰብል ፍሬ ማለቴ ሳይሆን ለማንኛውም ዕድገት ምክንያት የሚሆኑ የአገሪቱ ብርቅ ልጆች፤ ምሁራን፣ህስቶሪያንስ፣ የህክምና ዶክተሮች፣ መሀንዲሶች፣ፕሮፌሰሮች፣የሂሳብ ባለሙያዎች በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በካናዳ እና በስካንዲኒቪያ አገሮች ተበታትነው የሚገኙትን ማለቴ እንደሆነ ልብ ያለው ሁሉ ልብ ይበል። እነዚህ በረከቶቻችን አይደሉም ወይ? በእርግጥ ከእግዚአብሔር የተሰጡን በረከቶቻችን ቢሆኑም አልተጠቀምንባቸውም። እግዚአብሔር ባርኮናል እኮ። በውጭ ዓለም ያሉ ሰዎች ስለ እኛ የነበራቸው ግምት ረሀብተኞች፣ ለማኞች፣ጨካኞችና ጦረኞች እንደሆንን ነው። አንዳንዶቹ እንዲያውም የምናድርበት ቤት፣የምንለብሰው ጨርቅ እንኳን የሌለን ይመስላቸዋአል። ለዚህ ነው ስንተዋወቃቸውና ከኢትዮጵያ ነን ስንላቸው አንዳንዶቹ በአእምሮአቸው ካለው ሥዕል የተነሳ እዝን ትክዝ ብለው ያዩንና እንኳን ደህና መጣህ! እዚህ አገር ስለ መጣህ በጣም ደስ ብሎሃል አይደል? ይላሉ። ሌላ ጊዜ ስንገናኝ ደግሞ ጨዋታውን ከበፊቱ ጨመር ያደርጉና ስለ አኗኗራችን እንድናውራላቸው ይፈልጋሉ። ቤት አላችሁ? ምግብ አብስላችሁ ነው የምትበሉት ? ልብስ መልበስ የጀመርከው መቼ ነው? ይሉናል። ስንነግራቸው እውነት አልመስል ይላቸዋል። ይህንን ሳይ ልቤ ከመጠን በላይ ያዝናል። ለምነድነው ብዬ ሳስብ ለካ አንዳንድ አገር ጎቢኚዎች ወደ እኛ ሲመጡ ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ሕዝቦች፣ቋንቋና ባህል ባለቤት እንደመሆንዋ መጠን በአንዳንድ አካባቢዎች ራቁታቸውን የሚሄዱ ወገኖቻችንን ፎቶ አንስተው ቪዲዮም ቀርጾአችው ይመጡና ሌላውን አካባቢ ሳያሳዩ ኢትዮጵያ ይህን ትመስላለች ብሎአቸው ኖሮአል። አንዳንድ ተንኮለኛ አገር ጎብኚ አይጥፋምና። ስለዚህ ነው ምንኖረው እቤት ውስጥ ሳይሆን እውጭ፣ ሁላችንም ልብስ ሳንልብስ ራቁታችንን የምንሄድ የመሰላቸው እንጂ በርግጥ የተባለውንም ያህል ረሀብተኞች ሆነን አልነበረም። የውጭ አገር ጎብኚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአገራችንም ሰዎች ከሆኑት አንዳንዶች ከፈረንጆች የገንዘብ ድጋፍ ሊያገኙ ሲሉ የሚጠቀሙባቸው ቪዲዮችና ፎቶግራፎች ገጽታችንንና ምሥላችንን ሊያበላሹ እንደቻሉ ምንም አልጠርጥርም። ይህንን ለማረጋገጥ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጀቶች የሚሠሩ ሰዎች ካሜራ ይዘው ወደ አንድ መንደር ሲገቡ ማየት ብቻ በቂ ነው። የእነሱ ካሜራ የሚያውቀው ደሳሳ ቤት፣ ጫማው የተቀዳደደ ሚስኪን ለማኝ፣ጭራሮ የጫነ አህያ የሚነዳ ሽማግሌ ፣ ቁምጣ ሳይኖረው በባዶ እግሩ እየሄደ በጭቃ የመንከባለል ሕፃን ፣በሆነ ህመም ምክንያት ሰውነቱ የገረጣ ሰው ወዘተ እንጂ እንዲያው ሌላ የተሻለ ነገር ካሜራቸው ያየዋል ወይ? ፎቶስ ያነሱታልን? ካልሆነ ደግሞ ፈንዱን ማግኘት ቀላል ላይሆን ይችላልና መፍረድ ቢያስቸግርም አሳዝኙ ነገር ፎቶ የሚያነሷቸውና በቪዲዮ የሚቀርጿቸው ሰዎች ከሚመጣው ገንዘብ ጋር ሳይተያዩ ከቀሩ ነው። እንግዲህ ይህን የሚምስሉ አጥር የጣሱ ነገሮች ገጽታችንን አበላሹት እንጂ አገራችንማ ሀብታም ነች።
የሰው ኃይል የአገሪቱ በረከት ነው። ሰዎችና ሙያቸው ለአገሪቱ ዕድገት ወሳኝ ነበር። ዳሩ ግን የተማሩ ወንድሞቻችን እህቶቻችን በሙያቸ ሌሎች አገራትን እያሳደጉ ናቸው። ታዲያ ለምን አልተጠቀምንባቸውም? መልሱ ግልጽ ነው፣ ምድሪቱ ፈውስ ያስፈልጋታል። አገራቸውን ስላልፈለጉት ነው? በጭራሽ! እነዚሀስ በረከቶቻችን አይደሉምን? ያለ ምንም ጥርጥር በረከቶቻችን ናቸው። በአሜሪካን አገር ታላላቅ ሥራዎችን የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ሳይንትስቶች ለምን በአገራቸው አልሠሩም? ምድሪቱ ገና ስላልተፈወሰች ብቻ ነው። ሁሉም ነገር መልካም ነው ብንልም ልንክድ በማንችልበት ሁኔታ ጭንገፋው በዝቶአል። ጭንገፋና ሞት አለ፣በሽታ አለ፣ ያልተነቀለ ርግማን አለ፣ያልደረቀ ቁስል አለ፣ያልታበሰ እምባ፣ያልተከፈለ የደም ዕዳ በምድሪቱ ላይ አለ። የምድሪቱ ፍሬዎች ጨንግፈዋል። ፍሬው ጨነገፈ ስል ለጊዜው የእርሻ ቡቃያ ማለቴ ሳይሆን ብርቅና ውድ ልጆችዋን ማለቴን ከፍ ብሎ ጠቅሼአለሁ። ኢትዮጵያ ፍሬዎችዋ ለምን ጨነገፉ? መልሱ ግልጽ ነው። ምድሪቱ የተባረከች ሆና ሳለ ፈውስ ስላልፈጠነ ነው። እንጀራቸውን በግፍ ተቀምተው ያለቀሱ፣በዓይናቸው ፊት ልጆቻቸው የተገደለባቸው ወላጆች፣ወላጆቻቸው የተገደለባቸው ልጆች ያለቀሱበት እምባ ገና አልታበሰም ይለኛል የእግዚአብሔር መንፈስ። እግዚአብሔር የነገረኝ ሌላ አስገራሚ ነገር አለ። በምድሪቱ ደም የፈሰሰው ከውጭ በመጣ ወራሪ ጠላት ሳይሆን በወገናቸው ላይ በሚጨክኑ በምድሪቱ ሰዎች ነው። ይህ የበቀለኝነት መንፈስ አሁን በስውር እየሠራ ያለበት ጊዜ ነው። አንድ አስቂኝ የሆነ መፈክር በጣም ትዝ ይለኛል። “ይውደም” የሚል። በወቅቱ አድኃሪ ይውደም፣አቆርቋዥ ይውደም እገለ ይውደም ፤ ጴንጤ ይውደም ሲባል እንደ ነበር በደንብ አስታውሳለሁ። ይውደም የሚለው ማንን ነው? ያው ወገኑን ኢትዮጵያዊ እንጂ ሌላውን ጠላት አልነበረም። ያ ሥርዓት እንዳለውም ብዙ ነገር አውድሞ በመጨረሻም ራሱ ወደመ። ያኔ አሁን የሚታየው ማዕድን አልነበረምን? አባይስ ደርቆ ነበር እንዴ? ምን ነበር ቸግሩ? በማውደም የሚያምን እግዚሔር የለሹ ሥርዓት እግዚአብሔርንም የለም አለ፣እግዚአብሔር የፈጠረውንም ይውደም አለ፣ አስባለ፣በምድሪቱም የእርስ በርስ መራገም አስለመደ ። ያ ውድቀት ተንሰራፍቶ ስለ ቆየ ህዝባችን ከደቀበት ለመነሳት ረዥም ጊዜ ፈጅቶበታል። አሁን በእግዚአብሔር ርዳታ የትንሣኤ ተስፋ ቢታያትም ምድሪቱ ፈውስ ያስፈልጋታል።
አገራችን የምግብ ዋስትና ለማረጋግጥ ከሚሠሩ አገሮች ተርታ ተሰልፋ በዓለም በምሳሌነት መጠቀሷ የሁሉንም ትኩረት ከመሳቡም በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ያኮራ የተወደደም ንግርት ነው። አርሶ አደሩ ከምን ጊዜም በላይ በእርሻ ከፍተኛ ምርት በማግኘቱ ኑሮው ተሻሽሎለታል የሚለውን ዜና መስማት ኢትዮጵያ በበረከት ጎዳና ላይ መገኘቷን የሚያመላክት በመሆኑ እጅግ ደስ ይለናል። የሌላውን አላውቅም በውጭ አገር እንደ መኖሬ መጠን ይህን የመሰለ ዜና ስሰማ የአገሬ ናፍቆት በምን መጠን እንደሚጨምር ማስረዳት ለእኔ በእውነት የከባድ ከባድ ነው። የማቃቸው ትናንሽ የገጠር ወንዞች ሁላ የስፉና የጎለበቱ የሚመስለኝ ጊዜ አለ። ሰው ሁሉ ችግርን ወግድ ያለ፤ የምግብ እጦት ከምድሪቱ ጥርግርግ ብሎ የወጣ የሚመለኝም ጊዜ ጥቂት አይደለም። ዳሩ ግን ይህ ሁሉ እየተነገረ ጉርሻ በገንዘብ እየተሸጠ መሆኑን ማየት ደግሞ በጣም ያሳዝናል። የሚያሳዝነው ጉርሻው መሸጡ ብቻ ሳይሆን ቡፌ እንደሚጠብቅ የሠርግ ቤት እድምተኛ ነፍሱን በጉርሻ ለመታደግ ተራውን በሰልፍ የሚጠብቀው ሰው ብዛት ነው። የብዙዎች ልብ ይህንን ሲያይ እንደሚሰበር አያጠራጥርም። ይህ የሆነው ለምንድነው? በምድሪቱ ፍሬ ለሕዝቦችዋ አንሶ ሳይሆን የበረከት ሁሉ በረከት የሆነው መለኮታዊ ፈውስ ገና ስላልተገለጠ ነው። ኦ! ፈውስ ያስፈልገናልና እግዚአብሔር አምላክ በእውነት ምድራችንን ይፈውሳል!!
እግዚአብሔር የሰጠን በረከቶቻችን የምንላቸው ልጆቻችን ሲሆኑ ለምድራችችን ጌታ የሰጠን ትልቁ በረከት የሰው ኃይል ነው። የአንዲት አገር ልማትም የሚፋጠነው ባለው በሰው ኃይል መሆኑን ማንም ሊክደው አይችልም። የአገራችን የሰው ኃይል ግን በየትኛውም ቀዳዳ ቢሆን ከአገሪቱ መውጣትን ይፈልጋል። እውነት እንነጋገር ካልን ከቄስ እስከ መጋቢ ከኢትዮጵያ ይልቅ በውጭ መኖርን ይፈልጋል ። አንድ ሰው በሆነ አጋጣሚ አንዴ ወደ ውጭ ከወጣ እግዚአብሔር ስለተናገረኝ እዚህ አገር አገለግላለሁ ይልና ይቀራል። ይህንን ልምምድ ያመጡት ታላላቅ መሪዎቻችን ናቸው። በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ቀዳሚ መሪዎች ያልናቸው በምክንያት የአሜሪካን ምድር ይርግጧትና ጌታ ተናገረኝ በሚል መንፈሳዊነት ሰምጠው ይቀራሉ። በእርግጥ ጌታ የሚናገራቸው ቢኖሩም ለአብዛኛዎቹ የሚነግራቸው ልባቸው እንጂ ጌታ አይደለም። ይህ ለምንድነው የሚሆነው የሚል ካለ ቤተ ክርስቲያንም ራሷ ካልተፈወሰች ፈውስ ልታመጣ ስለማትችል ነው። ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከአገልጋይ እስከ ምዕመን ደስ የሚለው ከኢትዮጵያ ይልቅ በአሜሪካ ቢኖር ነው። ይህንን አንድ በሚገርም ገጠመኝ ባስቀምጥ ደስ ይለኛል። የማስተር ዲግሪዬን ለመሥራት ወደ አሜሪካ ስገባ ሌላ ሰው የአፍሪካ አገር ከሆነችው ከማላዊ ከነቤተሰቡ ለተመሳሳይ ፕሮግራም መጥቶ በአንድ ሰሚናሪ ውስጥ መማር ጀመርን። ሁለታችንም የምንሠራው ማስተር በሁለት ዓመት የሚጠናቀቅ ፕሮግራም ቢሆንም እርሱ አስቀድሞ በርቀት ትምህርት ፕሮግራም በርከት ያሉ ኮርሶችን ወስዶ ስለ ነበር ከእኔ ቀድሞ አጠናቀቀና ቶሎ ብዬ ወደ አገሬ ልሂድ ዲግሪውንም ቢሆን በፖስታ ላኩልኝ ብሎ ሄደ። የምረቃው ጊዜ ደረሶ ውጤቱን እስክቀበል ድረስ እንኳ ሊቆይ አልፈለገም። የእሱ ሲገርመኝ ባለቤቱና ልጆቹ ወደ ማላዊ ተመልሰው እንደሚሄዱ ካወቁበት ጊዜ አንስቶ በፊታቸው ይታይ የነበረው ደስታ በቃላት የሚገለጽ አልነበረም። በተቃሪኒው ደግሞ ትምህርቴን ስጨርስ ወደ ኢትዮጵያ እንሄዳለን ስላቸው የእኔ ልጆች ምንም መልስ ሳይሰጡ ቃልም ሳይተነፍሱ ወዲያው ፊታቸው ሲለዋወጥና ዓይናቸው እንባ ሊያፈስ ሲከብድ ሳይ ግራ መጋባት ውስጥ መውደቄን አስታውሳለሁ። በእውነት አሁን ማላዊ ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሆና ነው? ብዬ አልኩ፣ ሰውንም ለመጠየቅ ሞከርኩ። በእውነት እላችኃለሁ የሰማሁት ነገር አገራችን በብዙ እንደምትበልጥ ነው። ታዲያ ለምንድነው ታላላቅ ኢትዮጵያውያንም ጭምር ከአገር መውጣትን እንደ ስኬት የሚቆጥሩት ወይም ከአገር የወጡ ዕለት የግልግል ስሜት የሚሰማቸው? ብዬ ራሴን ጠየቅኩ። በረከት አንሶ ሳይሆን ፈውስ ስላልተገኘ ነው መልሴ። አሜሪካንና እንግሊዝ ፈረንሳይና የዓረቡ ዓለም ተፈውሰዋልና ነው ሕዝባችን ወደ እነዚያ የሚኮብልለውና የሚጎርፈው? የሚል ጥያቄ ቢኖር ግን ለዚህ የሚሆን መልስ የለኝም። ምን ይሁን ምን እግዚአብሔር ምድሪቱን እፈውሳለሁ ብሎኛል።
በለጽገዋል ወደ ተባሉት የምዕራቡ አገሮች ሄዶ መኖር ሌላ ነገር ነው። ወደ አሜሪካና ወደ ካናዳ የሚከደው የበልፀጉና ያደጉ ስለሆኑ በትምህርትም ሆነ በሌላ እንጠቀምበታለን፤ ኑሮአችንም ይሻሻልልናል በሚል ነው እንበል። ዳሩ ግን በአፍሪካ አገሮች ስለ ተበታተኑት ኢትዮጵያውያን ምን እንላለን? ሌላው ቢቀር በኢትዮጵያ ከመኖር ይልቅ በጅቡቲ መኖር የተሻለ እንደሆነ ተቆጥረው ወደዚያ የሚኮበልሉ ወገኖቻችን ጉዳይስ ምን ሊባል ነው? አሁን አሁን እንዴት እንደሆነ አላውቅም ግን ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ሱዳን ለመሄድ ቪዛ ለመጠየቅ ከሜክሲኮ አደባባይ በታች የሚገኘውን የሱዳን ኤምባሲ ሲያጨናንቅ የነበረው የወጣቱ ቁጥር አስደንጋጭ ነበር። ግን እኮ ሱዳንና ግብጽ ዕጣ ፈንታቸው የሚወሰነው በአባይ ወንዝ ነው። የግብጽ ጊዜያዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ በምትገነባው የሂዳሴ ግድብ ምክንያት ለካቢኔው ንግግር ሲያድርግ “ ግብጽ ማለት አባይ ማለት ነው አባይ ከሌለ ግብጽ የለችም፤አባይ ደማችን ነው” ማለታቸው ይታወቃል። አባይ ግን መነሻው ከኢትዮጵያ ምድር ነው ። አሁን አሁን የሂዳሴ ግድብ መገንባቱ የተስፋ ፍንጣቂ ቦግ ብሎ እንዲታይ አደርጓል። ወደ ሱዳን መግቢያ ቪዛ በሕጋዊ መንገድ ማግኘት ባይችሉ በሕገ ወጥ ደላሎች አማካይነት ድንበር አልፈው ሲሄዱ ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከቁጥር በላይ ናቸው ብል እንደማጋነን ሊቆጠርብኝ ስለሚችል ይቅርብኝ። ምን ይሁን ምስጢሩ? እኛ በእጃችን ያለውን በረከት ማየት ያልቻልነው ለምንደነው? መልሱ በጣም ቀላል ነው። እንደ ፖለቲከኛ ለሚያስብ ሰው ብዙ መልስ ይኖረው ይሆናል። እንዲያውም የሕዝቡ ፍላጎትና አቅርቦት ስላልተመጣጠነ ነው ሊባልም ይችል ይሆናል፣ ወይም ዜጋው የአገሩን ሥራ ንቆ ነው የሚል መልስ ይሰጥበት ይሆናል። ይኸው ለዜውጋው የኮብል ስቶን ሥራ ዕድል ተመቻችቶለታል ቢባል ውሸት አይሆንም። እንዲያውም ከዚያ አልፎ ዜጎች በተለይም ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪና በሌሎች ማህበራት እየተደራጁ ሥራ እንዲፈጥሩና ራሳቸውንም አገራቸውንም እንዲያሳድጉ ሁኔታዎች መመቻቸታቸው ሊካድ የሚችል አይደለም፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃንም ጭምር በኮብል ስቶን ሥራ ተሰማርተው ራሳቸውንና ሕዝባቸውን ብሎም ቤተሰባቸውን እያጠቀሙ ነው የሚለውን ዘገባ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲተላለፍ ሳይ ዓይኔን ማመን አቅቶኝ በአጠገቤ የነበረውን ሰው ( ኢትዮጵያዊ ነውና)ይህ ነገር አልገባኝም አንተስ ገብቶሃል? ስለው ፈገግ ብቻ አለ እንጂ ምንም መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም። እኔም ደግሜ አልጠየቅኩትም። የሆነ ሆኖ ሊባል የሚችለው ይህና መሰል ነገር ነው። ከዚህ ውጭ ሊሆንም አይችልም፣ እንዲሆንም መጠበቅ የለብንም። ይህ ሁሉ ቢሆንም የሕዝባችን መሰደድ አላበቃም። ለምን ለሚለው ምላሽ መገኝት ይኖርበታል። በሰው ዘንድ ካለው መልስ ይልቅ የእግዚአብሔር ይለያል። እንደ መንፈሳዊ ሰው ሆነን መንፈስ ቅዱስ የሚለንን ከሰማን ግን ይህ ሁሉ ጭንገፋና ተርምስ እልባት የሚያገኘው ምድራችንና የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፈውስ ሲገናኙ ብቻ ነው። ፈውስ ያስፈልገናል። ኦ!! ለኢትዮጵያ ምድር ፈውስ ያስፈልገዋል። ፈውስ! ፈውስ! ፈውስ! የእግዚአብሔር መሊኮታዊ ፈውስ!!!! እግዚአብሔር ምድሪቱን እፈውሳለሁ ይላል።
እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ወደ ልቤ ሲያመጣ የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ በማገለግላት ቤተ ክርስቲያን የወንጌል ሥርጭት ኮንፍረንስ ሲካሄድ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ወደ ነበርኩበት ቢሮ ያመጡት ወጣት ያጫወተኝና በሕይወቱ የገጠመው አሰቃቂ ምስክርነት ትዝ ብሎኝ ማልቀሰን የሚነግራችሁ ቅንጣት ያህል ይቅር የቅንጣት ሲባሪ ያህል ውሸት ሳልጭምርበት ነው። ወጣቱ ከአገልጋዮቹ ጋር የተገናኘው ከኮንፈራንሱ ስብከት በኃላ ጌታን ለመከተል ለሚሹ ወገኖች ጥሪ ሲደረግላቸው አብሮአቸው ተነስቶ ምክር ወደ ሚሰጥበት ክፍል በመሄዱ ሲያማክሩት ነው። በውስጡ ጌታን የመቀበል ፍላጎት ጨርሶ አልነበረም። ሥራ ፍለጋ ወደ ሱዳን ከተሻገረ በኃላ የገጠመው ሥራ ሳይሆን ከሞት ያልተናነሰ ስቃይ ነበር። ሄዶ የገባበት የመከራ ማጥ የሰው ልጅ እንዴት ቻይ ነው? የሚያሰኝ ነው። ወደ ሱዳን እንደተሻገረ ሕገ ወጥ ደላሎች ተለዩትና የወደቀው በድንበሩ አካባቢ ባሉ ለሰብዓዊነት ምንም ደንታ በሌላቸው በሱዳን ወታደሮች እጅ ነበር። ከአፉ አውጥቶ እንደተናገረኝ ወታደሮቹ ልብሱን ካስወለቁት በኃላ አንድ እግሩን በገመድ ወደ አንድ አቅጣጫ ሌላው እግሩን ደግሞ ወደ ተቃራኒው በኩል ወጥረው ተራ በተራ ሲገናኙት ሲቃዩን መቋቋም አቅቶት ራሱን በሳተበት እግሮቹን ፈትተው በዚያ በረሃ ላይ ጥለውት እንደሄዱና ራሱን ሲያወቅ ግን አንድም ሰው በአጠገቡ እንዳልነበረ ያስረዳኝ ነበር። ይህ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ከእርሱ በፊት የነበሩ ሌሎች ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ስለነበሩና ስላየው እርሱም ቢሆን ከዚህ ሊያመልጥ የሚችልበት ምንም ቀዳዳ ስላልነበረው ሳይወድ የግዱን ራሱን ለአውሬዎቹ አሳልፎ ሰጠ። ነፍሱን ለማዳን ጫካ ለጫካ እየተንፏቀቀ ወደ አንድ ጎዳና ላይ ሲወጣ እግዚአብሔር ያዘጋጀለት አንድ ሩህሩህ ሰው በመኪናው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አሻግሮት ተመለሰ። ከዚያ ወዲያ ገንዘብ ለምኖ ምግቡን እየበላ ፣ ባለ መኪኖችንም እገዛ እየጠየቀ ወደ አንድ የኢትዮጵያ ከተማ ደረሰና በእጁ ባለችው ትንሽ ገንዘብ የማደሪያ ክፍል ተከራይቶ በተኛበት ያኔ የሱዳን ወታደሮች ሲግናኙት የቆሰለው ሰውነቱ ከመጠን በላይ ደምቶ ነበረና የማደሪያ ቤቱ አንሦላ በደም ስለ ተበከለ ማጠብ ነበረበት። ችግሩ ግን ሳሙና መግዣ የሚሆን ገንዘብ አልተረፈውም ነበር። ዳሩ ግን የሆቴሉ አልጋ ቤት ሠራተኞች ችግሩን ሊረዱለት ስላልቻሉ እንዴት እንዳዋከቡትና እንዳመነጫጨቁት ሲያብራራ የሚሰማውን ሰው ከልብ ያስለቅሳል። የሚያሳዝነው ይህ ሰው ሹፌሮችን ለምኖም ቢሆን ወደ መሀል አካባቢ እንዳይመጣ ደም ይፈሰዋል። እንዲህ ዓነቱን ችግር ይዞ በሰው መኪና መሳፈር ከጭንቅም በላይ ጭንቅ ነው። ገና የሕክምና ርዳታ ሊያገኝ ወደ ሚችልበት ሥፍራ ስላልደረሰ የሚያደርገው ሁሉ ጠፍቶት ነበር። ይሁንና እግዚአብሔር ረድቶት ወደ አዲስ አባባ ሲደርስ ወላጅ አባቱ ሲያየው ትምህርቱን አቋርጦ በመሄዱ ምክንያት ተቆጥቶ ስለ ነበር ወደ ቤት እንዳይገባ ከለከለው። ከዚያ በኃላ ዘመዱ ወደ ሚሆን ሰው ሄዶ የደረሰበትን ሁሉ ሲያጫውተው በጣም አዘነና ወደ ሆስፒታል ወስዶት የሕክምና ርዳታ ከተደረገለት በኃላ የጤናው ሁኔታ መሻሻል ቢያሳይም ፊስቱላ ለሚባል ችግር መጋለጡን አጫወተኝ።
ይህ ወጣት ወደ እኔ የመጣበትን ምክንያት ግልጽ ሲያደርግልኝ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የመሆን ፍላጎት ኖሮት ሳይሆን ላለበት ችግር እገዛ እንድናደርገለት ብቻ ነው። እርሱ አንድ ሆኖ አየነው እንጂ በሱዳን በኩል ከአገር ሲወጡ ለከፈተኛ ችግር የተጋለጡ፣የአካል ጉዳት የሚደርስባቸው፣ህይወታቸውንም የሚያጡ ቁጥራቸው ሊገመት ከሚችለው በላይ መሆኑን ሲያጫውተኝ ቆይቶ ከቢሮዬ ከሄደ በኃላ ብቻዬን እንዴት እንዳለቀስኩ ትዝ አለኝ። ልብ እንበል! አንድ ተማሪ ወደ ዪኒቨርሲቲ ሲገባ ራሱንም፣ ወገኑንም፣ አገሩንም የመጥቀም ተስፋ ሰንቆ እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው። ተምሮ የመሻሻል እድል ያላቸውም ጭምር እንደ ምንም ብለው ከዚህች አገር የሚወጡበትን ቀዳዳ መፈለጋቸው እጅጉን የሚያሳሰብም የሚያሳዝንም ጉዳይ ነው።ይህ በሰው ዘንድ መፍትሔ የሌለው ጉዳይ ነው። ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚመጣው ፈውስ ግን መፍትሔ ይሆናል።
ይህ ብቻ አይደለም። በኮንቴይነር ተጭነው ሲውሰዱ በሙቀት ታፍነው ያለቁ 48 ኢትዮጵያውያን እኮ ወደ አሜሪካን ወይንም ወደ ካናዳ ሲሄዱ ነበር ብሎ ሊያሳምነን የሚችል አይኖርም። ወደ አፍሪካ አገር ሲሄዱ እንጂ። ሌሎች ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ዓረብ አገር ሲወሰዱ ተመሳሳይ ዕጣ ገጠሞአቸዋል። ይህንንስ እግዚአብሔር አምላክ ምን ይላል? በየዕለቱ የሚፈሰውን ደም፣በግፍ የሚያልቀውንስ የወንድሞቻችን ሕይወት ተመልክቶ የሚፋረድስ አካል ይገኝ ይሆን? ነገሩስ ራሱ እንዲህ የሆነው ለምንድነው? ሕዝቡስ ለእንደዚህ ዓይነት ሕይወት አልፎ የተሰጠበት ሌላ አገር በምድር ላይ ይኖር ይሁን? በእውነት ጌታ ምድራችንን ሲፈውሰው ይህ ሁሉ ታሪክ ይሆናል።
አንዲት ኢትዮጵያዊት በሊባኖስ አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሊባኖሳውያን ስትደበደብ ኤምባሲያችን ሊከላከላት አለመቻሉ ብዙዎቻችንን አስገርሞናል። ልጂቱ “ወይኔ....ወይኔ...አልገባም” እያለች ወደ መኪና ውስጥ ሊከቷት ከሚታገሉ የዓረብ ጎርምሶች ጋር ብቻዋን ስትጋፈጥ ቤቴ ነው ነፍሴን ያድንልኛል ብላ የመጣችበት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንም ሳይመስለው መቅረቱ ከሁኔታው በላይ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት ነው አሰኘቶናል። በመጨረሻም የልጅቷ ሞት ሲነገረን ምርር ያለ ልቅሶ አልቅሰናል። የልጅቷን ማንነት በፍጹም ባላውቅም ሁኔታው ከልቤ አልወጣ ብሎ ለወራት አሰቃየኝ። መንግሥታችን ለዚህ ጉዳይ የሰጠው ተገቢ ምላሽ ይኖራል ብዬ አምናለሁ። ያቺ ልጅ እንደ ምሳሌ እንጠቀምባት እንጂ በዓረቡ አገራት ሕይወታቸው ተቀጭቶ በከንቱ የቀሩ እጅግ ብዙ ናቸው። ይህ እስከመቼ? ኢትዮጵያ እስክትባረክ? አዎን ነው መልሱ ግን በርከት ብቻውን አይለውጠንም፣ መለኮታው ፈውስ ግን ያስፈልገናል፣እግዚአብሔር አምላክም ይፈውሰናል። ካልተፈወስንማ ሀብቱን በአፉ ብቻ እንደሚቆጥር በሽተኛ ባለጠጋ እንሆናለን። የምሥራቹ ግን እግዚአብሔር አምላክ እፈውሳችኃለሁ ይለኛል።
እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈወሳል ስንል ምን ማለታችን ነው? ይህንን በብዙ አንጻር መመልከት እንችላለን። ከፍ ብሎ እንደጠቀስኩት በፊታችን ስናያቸው የነበረ ታላላቅ መሪዎቻችን ሮል ሞዴሎቻችን ሳይሆኑ ቀሩ። በአራትና አምስት ሺህ የሚቆጠር ጉባኤያቸውን ጥለው ይመጡና አንዱ ያገለግልበት ሥፍራ ይሄዱና በምዕመናን ሲሻሙ ማየት እንዴት እንደሚያሳፍር። በዚያም ላይ ጌታ የአገልግሎት በር ከፍቶልኛል ሲሉ መስማት ተራ ተረት ሆኖአል። ይህ ሲገርም እንደምንም ብለው ወደ ኢትዮጵያ ይሄዱና ሥልጠና ልስጣችሁ፣ስብከት ልስበካችሁ፣ኑ ተስብሰቡ፣ ገንዘብንም አምጡ ሲሉ የዋህ የአገራችን ሕዝብ ይንገላቱታል። ከሚሰጡስ ሥልጠና ምን ታምር ይፈጠር ይሁን ብሎ ቢጠበቅ እውነት እላችሓለሁ በኢትዮጵያ በአንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በመሪዎች ክፍል የሚሰጠው ሥልጠና ትልቅ ቁም ነገር ይገኝበታል። ቄስ እንትና፣ዶር እንትና፣ ፓስተር እንትና ወዘተ መጥተው ሥልጠና ስለሚሰጡ ተጋብዛችኃል እንዳትቀሩ፣ ቦታው ኢምፔርያል ሆቴል፣ሼበሌ ሆቴል፣ገነት ሆቴል ፣ወዘተ ሆቴል ይባልና ሲከድ እነዶክተር እንትና ያምጡት ነገር እዚህ ግባ የማይባል፤ወደ መጣንበት ሥፍራ ተመለሰን ሥራ ላይ ማዋል ይቅርና ውድ የአገልግሎት ጊዜአችንን በከንቱ ያባከንንበት የኪሣራ ጊዜያቶች በርካታ ናቸው። ከመጀመሪያውም ቢሆን እነዚህ ሰዎች መንፈሳዊ ሥልጠና ለመስጠት ጸሎት ቤቶችን ሸሽተው በየሆቴሉ መመሸጋቸውና ሕዝቡንም ማንገላታታቸው ጥያቄ ይፈጥርብን ነበር። እንዲያው ወጣ ማለት ጥሩነው ብለን ነው እያተባለ ተጀመረና አሁን አሁን ያለ ሆቴል መንፈሳዊ ስብሰባ አይካሄድም ወደ ሚባልበት ጀረጃ የደረስን ይመስላል። ይህቺ ናት መነቃቃት! በአገር ቤት እያለሁ ዛሬ ዶር እንትና ምን ነካቸው ትምህርታቸው የተበታተነ፣ጭራው ከጭንቀላቱ የማይለይ፣ውሉ የጠፋበት በዚያ ላይ እንጨት እንጨት የሚል ሆነሳ? ኧረ የእኛ ችግር ይሆናል እየተባባልን የነበረው ለካ ስላልገባን ነው። እኔም እግር ጥሎኝ ወደ አሜሪካ መጣሁና ወደ ኢትዮያ ሲሄዱ በዚያ ምስኪን ሕዝብ ላይ በቃ ከመላእክት መንደር የወረዱ ዓይነት መስለው መንፈሳዊ ነኝ ለማለት ያህል ግዳይ እንደጣል ሰው ወዲያና ወዲህ ሲንጎራደዱ ያየናቸው እነ ጋሽ እንትና ለካ እዚህ አገር ያሰለቹ በጥባጭ ኖረዋል። ይህን በመሰለ ሥጋዊ ጦርነት ውስጥ ኖረው ታዲያ ምን ጠብ የሚል ነገር ሊሰጡን ይችላሉ? በጌታ ፊት በትጋትና በቅንነት በጸሎትና በእምባ ከአምላኩ ጋር ተጣብቆ በኖረው ሕዝብ ላይ ይመጡና ዝም ብለው ያቅራሩበታል እንጂ በጭራሽ ሕዝቡንስ መጥነውት አይደለም። ያም ሳያንስ ጌታ ሊሠራ ተነስቶአልና ያላችሁን ስጡ ሲሉ መቼም ሕዝባችን የእግዚአብሔር ስም ሲጠራና በስሙ አንድ ነገር ሲጠየቅ መግፋት አይሆንለትምና እያመጣ ይሰጣል። ጌታ ለመሥራት ከተነሳ ገንዘቡ ምንድነው? እጅ መንሻ ወይስ ትራንስፖርት? በእውነት እላችኃለሁ እግዚአብሔር ያለ እኛ መሥራት ይችላል። እንዲያውም የሰውን ገንዘብ ተስፋ አድርጎና በሥጋ ለባሹ ተደግፎ የሚሠራ አምላክ አይደለም። ይህንን የሚጠይቅም ስሌለለ በመንፈሳዊነት ስም ምንነቱ የማይታወቅ የገንዘብ አሰባሰብ ያደርጉታል። ከዚያ ጌታ ይባርካችኃል ይሉና እነሱ ይባረኩበታል። ይህንን ያዩ ማንነታቸው የማይታወቅ አንዳንዶች እየተነሱ ጌታ ተናግሮኛልና ኮንፍራንስ አዘጋጅቻለሁና ወደ ስታዲየም ውጡ የሚል ፖስተር በየቦታው ይለጥፍና ይህንን ምስኪን ሕዝብ ይጠራል። ዓላማው ጌታ የተናገረውን መልእክት ማስተላለፍ ሳይሆን ባለፈው እነ ዶ/ር፣ፓስተር፣ቄስ ወዘተ እንዲህ አድርገው ገንዘብ ዝቀው ሄደዋልና እኔም ይህቺ የሃይማኖት ነጻነት የተባለች ነገር እያለች ልዛቅ በሚል ነው። ምክንያቱም ቀዳሚ የቤተ ክርስቲያን መሪ ተብዬዎቹ ያመጡብንና እያስለመዱን ያለው ይኸው ነዋ። ሕዝባችንስ ቢሆን ለስንቱ ይስጥ? ግብሩን ይክፈል የሂዳሴ ግድቡን? ቫቱን ይክፈል ዳቦውን ይግዛ? አሥራትና መባውን ለሚገለገልበት ቤተ ክርስቲያን ይስጥ የተቸገረውን ይርዳ ወይስ በመንፈሳዊነት ስም በሚመጣው ሌባ ይዘረፍ? ይኼ እንግዲህ ፈውስ የሚያስፈልገው ጎናችን ነው።

አደባባይ የወጣው ሕዝብ ምን አተረፈ ቢባል ያው ትባረካላችሁ ይባልላቸዋል ካልሆነም እፍ እያሉበት ሲገፈትሩት ሲገነደስ ውሎ /ለዚያውም ተራ ከደረሰው ነው/ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ተሰበከ ቢባል የደረቁ አጥንቶች፣ አልአዛር፣ደም የፈሰሳት ሴት፣ የኢያሪኮ ግንብ መውደቅ፣ ናቸው። በአንድ ሰሞን ልብህን በአህያ ላይ አትጣል የሚለው ስብከት ከገጠር እስከ ከተማ ብቻውን በየቦታው ይስበከብበት እንደነበር አስታውሳለሁ። አሁን አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ አገራችን የተስፋ ቃል ያላት ነች የሚለው ነው ስብከቱ። እንዲህ ዓይነቱ የተስፋ ቃል ምን ላይ ነው የተጻፈው ተብለው አንዳንዶቹ ሲመልሱ “እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ተብሎ ተጽፎአል ይላሉ። ይህ ነው ተስፋ ቃሉ? ኢትዮጵያ ኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 40 ጊዜ የተጠቀሰች አገር ነችና ቃል ኪዳን አላት ብለውም እርፍ። እንዲህ ዓይነቱ ስብከት የእነ ዶር እንትና ስብከት ነው፡፡ ያሁኖቹም የቀዱት ከዚያ ነው። እነጋሽ ፤ ዶር ፣ቄስ ፣ፓስተር እንትናማ ለኢየሱስ ብቻ የሚሰጠውን ስም ( ሜልከፀዴቅ የተባለውን) ጓደኛቸው ሲያከናንቡት ትንሽም ያላፈሩ፣ተወቅሰውም ተሳስተናል ለማለት ልብ የሌላቸው መሆናቸውን ሥራቸው ሲገልጣቸው ኖረዋል። የአሁኖቹም መንጋ አልባ መጋቢዎችም ከቀደሙት የሰሙትን ደገሙት እንጂ ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 40 ጊዜ ስለ መጠቀስዋ እርግጠኛ ለመሆን አንድ ሁለት ብለው ቆጥረው አይምስለኝም። ዎይ አርባ ጊዜ-----! 40 ጊዜ ይቅርና 40000 ጊዜ ብንጠቀስስ ያ ለመንፈሳዊነታችን ወይም የቃል ኪዳን ሕዝብ ለመሆናችን ማረጋገጫ ሊሆን የቻልበት ምክንያት ምን ይሆን? ኢትዮጵያ በ66ቱ መጻሕፍት ውስጥ 40 ተጠቅሳለች እያሉ ነው። መለኪያው ይህ ከሆነ ግብፅ በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ መጽሐፍ በሆነው በኦሪት ዘፍጥረት ብቻ ከ154 ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች። በተቀሩት 65ቱ ውስጥ ያለውን ብንደምርበት ስንት ሊሆን እንደሚችል እንገምት። ታዲያ መንፈሳዊው ማን ነው? ግብጽ ወይስ ኢትዮጵያ? እግዚአብሔር ካደለን መልሱን ከእነ ዶር፣ቄስ ፣ፓስተር፣ ሰባኪ ወዘተ እንትና እንሰማለን። ሕዝባችን ግን ያሳዝነናል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህንንም ይፈውሰዋል። እርሱ ምድራችሁን እፈውሳለሁ ብሎአልና። ለዛሬ እዚህ ላይ ጌታ እናድርግና ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። እስከ አሁን አንድ ጥቅስ እንኳን አላነበብክልንም እግዚአብሔር በምንድነው የተናገረህ? የምትሉኝ ውዳጆቼ እኔም በምትሉት ሁሉ እስማማለሁ። ሁሉንም እንደርስበታለን። እስከዚያው በቸር ሰንብቱ፣ ጌታም በሰላም ያገናኝን።

Wednesday, December 25, 2013

ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ( 1ኛቆሮ. 12 ፡31)፡ ክፍል አንድ

ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ( 1ኛቆሮ. 12 31)
A more excellent way
ክፍል አንድ
በአንድ ወቅት አንድ የታወቀ ሀብታም ሰው ለሠራተኞቹ ስጦታ ሊሰጥ አሰበና እንደፍላጎታቸውና እንደ ምርጫ ችሎታቸው መሠረት እንዲወስዱ የተለያዩ ማዕድናትን በፊታቸው አቀረበላቸው። ይህ ሰው ፊታቸው ያቀረበላቸው አራት ማዕድናት መዳብ፣ብር፣ወርቅና አልማዝ ሲሆኑ እነዚህንም በተርታ አስቀመጠላቸው። ይህንን ሲያደርግ ሰዎቹ ደስ ያላችውን መርጠው እንዲወስዱ በመፍቀድ ነው። ሀብታሙ ሰው ለሠራተኞቹ ካቀረበላቸው ማዕድናት ውስጥ የማይፈለግ አንድም የለም። ምናልባት ሰጦታው የቀረበላቸው ሰዎች በርከት ያለውንና በዓይናቸው የሞላላቸው መዳብ ቢሆን መዳብን ደስ እያላቸው ሊመርጡ ይችሉ ይሆናል። የሚገርመው ግን አብዛኛዎቹ መዳብን ሲምርጡ ጥቂቶቹ ደግሞ ወርቅ መረጡና አልማዝ የተባለውን ማዕድን ግን ማንም ሳይመርጠው ቀረ። የስጦታው ሰጪ በሁኔታው በጣም ተገረመና ያ የሆነበትን ምክንያት ሲያጠና ሰዎቹ አልማዝ የሚባል ምን እንደሆነ ስለማያውቁትና ማዕድኑ በመጠኑ ከሌሎች ማዕድናት የሚያንስ በመሆኑ ብዙም ዋጋ ላይኖረው ይችላል በሚል ያደረጉት እንደሆነ ተረዳ። ይሁን እንጂ አልማዝ ከሁሉም ማዕድናት የበለጠ ነበር። የስጦታው ተቀባዮቹ የተሳሳቱት ምናልባት በሌሎች ማዕድናት ብልጭልጭነት ተማርከውና ትታልለው እንጂ ማዕድናቱ በሚሰጡት ጥቅምና በጥራት ብልጫቸው ላይ ብዙም ስላላተኮሩበት ይሆናል።
እንደዚሁም ሁሉ በመንፈሳዊ ሕይወታችንም እጅግ የሚበልጠውን መንገድ ሳናውቀው ቀርተን ሳንጠቀምበት የምንቀርባቸው ዘመናትና ወራት ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ከጌታ እጅ ከተቀበልናቸው ስጦታዎች አያስፈልጉንም የምንላቸው በጭራሽ የሉንም ሊኖሩም አይችሉም። ይሁን እንጂ በሕይወታችን እግዚአብሔር ከፍ ያለውን ቦታ እንድንሰጥ የሚፈልግብን ብዙ ቁም ነገሮች አሉ።
ለምሳሌ ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞችን ስለ ጸጋ ስጦታ ሲያስተምራቸው ሁሉንም በዝርዝር አስቀምጦ ሲያበቃ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ እንዳለ ደግሞ ያሳስባቸዋል። አባባሉንም ስንመለክተው ሁሉም የጸጋ ስጦታዎች በጣም የሚያስፈልጉ መሆናችው በቃሉ ውስጥ በማያሻማ ሁኔታ ተቀምጠዋል። እነዚያ የጸጋ ሰጦታዎች እጅግ ሲበዙ ለቤተክርስቲያን (ለአማኞች) መንፈሳዊ ሕይወት ግንባታ በጣም አስፈላጊዎች እንደሆኑ በተለያዩ የመልእክት ክፍሎች መመልከት እንችላለን።
ጳውሎስ ይህንን መልእክት የሚጽፍላቸው የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞች በተለያዩ የመንፈሳዊ ሕይወት ችግር ውስጥ ነበሩ ሲሆን እግዚአብሔር ግን በካከላቸው የተለያዩ የጸጋ ስጦታዎችን አፍስሶ ነበር። የተሰጣቸው የጸጋ ስጦታ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው ዕድገትና ግንባታ ሊሆን ሲገባው በመካከላቸው መለያየትና መከፋፈል ይታይባቸው ነበር። ጳውሎስ የጻፈውን የ1ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ስናጠናው ቀጥሎ የተዘረዘርሩ ችግሮች ተስተውለዋል፡

  • ከምዕራፍ 1-4 በመካክላችው ስለነበረው መከፋፈል
  • ከምዕራፍ 5-6 ክርስቲያን በሐጢአት ላይ ምንም ርምጃ ያለ መውሰድ ችግር
  • ምዕራፍ 7 በጋብቻ ምክንያት አማኞች የሚያነሱት መሠረታዊ ጥያቄዎች
  • ከምዕራፍ 8-10 ለጣዖት ስለተሰዋው ሥጋና አማኞች የሚያነሱት ጥያቄ
  • ከምዕራፍ 11-14 አማኞች በአምልኮ ጊዜ ያሳዪት ስህተት ለምሳሌ በጌታ ራት ጊዜ፣በጸሎት ጊዜና በአምልኮ ጊዜ ማለትም የጸጋ ስጦታዎቻውን በአግባብ ባለመጠቀማቸው በአማኞች መካመታነጽ ይልቅ መለያየትና መከፋፈል በርክ ነበር።
    ይህ ሁሉ በሚሆንበት ወቅት የጸጋ ስጦታ በመካከላቸው ይገለጥ ነበር። ጳውሎስ በምዕራፍ 12 እና በምዕራፍ 14 ላይ ለእነርሱ ስለ ተሰጣቸው የጸጋ ስጦታና ስለ አጠቃቀሙ በግልጽ ያስተምራቸው ነበር። ምዕራፍ 13 ግን በሁለቱ ምዕራፎች መካል ሌላ በጣም አስፈላጊ የሆነ ትምህርት ይዞ የገባ ምዕራፍ ነው። ይህ የሆነው ደግሞ በአጋጣሚ ሳይሆን በጌታ እቅድ ነው።
    ጳውሎስ በምዕራፍ 12 31 ላይ “የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ” ብሎ ይመክራቸዋል። ጋ ስጦታዎች ይበላለጣሉ ወይንም ይተናነሳሉ ማለቱ ግን አይደለም። ነገር ግን ለአማኞች መታነጽን ከማስገኘት አንጻር አብልጠን መሻት ያለብን ስጦታዎች መኖራቸው ደግሞ የሚካድ አይደለም። ለምሳሌ ትንቢትና ልሳን ሁለቱም የጸጋ ስጦታ ሲሆኑ
    ሐዋሪያው በጉባኤ ከሚነገረው ልሳን ይልቅ ትንቢት እንደሚበልጥ በም.14 ላይ በግልጽ ያስረዳል። ምክንያቱም በልሳን የሚናገር ራሱን እንጂ ማህበሩን አያንጽምና። ስዚህ ነው የሚበልጠውን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ የሚለው።
    ዚህመም በተጨማሪ ጳውሎስ “ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ” አሳያችኃለሁ ይላል። የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞች በመንፈሳዊ ስጦታዎቻቸው ለማገልገል ይጥራሉ እንጂ ይህንን ከሁሉ የሚልጠውን መንገድ አላወቁትም አልፈጉትም
    በዛሬው ዘመን ያለንም አማኞችና አገልጋዮች ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉብን ምንም ጥርጥር የለውም። እኛ የተለያዩ የጸጋ ስጦታዎች አገልግሎት በስፋት የሚሰጥበት ግን ከዚህ ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ብዙዎች ቸል ባሉበት ዘመን ላይ እንገኛለን።
    ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ምንድነው? የቱስ ነው? ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ጌታችንና መድኃኒታችንን ኢየሱስን ከሰማይ ክብሩን ትቶ ወደ ምድር የመጣበት ምክንያት ነው። ከሁ የሚበልጠው መንገድ አብ አንዲያ ልጁ ሳይራራ ለሰዎች ኃጢአት አሳልፎ እንዲሰጥ ያስገደደው ነው። ሐሪያው ጳውሎስም ይህ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ነው ይለናል። ሁሉ የሚበልጥ መንገድ ሲል የተለየ ትርጉም ለመስጠት ፈልጎ ነው ምክንያቱም እርሱ ዘመን “መንገድ” የሚለው ቃል ከክርስትና ጋር የተያያዘ ሁኔታ ላለ ነው። የጌታን መንገድ የሚከተሉ ሰዎች በሐዋሪያት ዘመን የመንገድ ሰዎች ተብለው ይጠሩ ነበር (የሐዋ. 92)፡፡ እንዲሁም ክርስትና ራሱ መንገድ ተብሎ ይጠራ ነበር (ሐዋ. 16171825199-23224241422)፡፡ ይህም የተባለው "ኢየሱስ እኔ መንገድ ነኝ" ብሎ በተናገረው መሠረት ሊሆን ይችላል (ዮሐ 146)፡፡ ክርስትና ጉዞ ነው፡፡ ክርስትና ሩጫ ነው ፡፡ ይህም በመሆኑ መንገድ አመልካች የሩጫም መሪ አለው (ዕብ. 121-21ኛ ቆሮ. 9) ይህ መንገድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተራመደበት መንገድ ሲሆን እኛም ደግሞ በዚሁ መንገድ እንድንራመድበት እግዚዚብሔር ይፈልጋል። ከዚህ መንገድ መጣት የክርስትና ሕይወታችንን ርጉም የሌለው ያደርገዋል። ዛሬ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ የሚታየው መተራምስ ይህንን ከሁሉ የሚበልጠውን መንገድ አለማወቀና አውቀውትም ቸል ከማለት የመጣ እንደሆነ ግልጽ ነው
    ሐዋርያው ጳውሎስ በ1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 13 ላይ መጀመሪያዎቹ 13 ቁጥሮች የሚናገረው ከሁሉ ስለሚበልጠው መንገድ ነው።ታዲያ ይህ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ምንድነው? የይይ ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ፍቅር ስለሆኑ የክፍሉ አሳብ በግልጽ ያሳየናል፡፡
    ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ፍቅር ነው( 1ኛ ቆሮንቶስ 131- 10). ስለዚህ በዚህ ትምህርታችን ከሁሉ የሚበልጥ ፍቅር እንመለከታለን፡፡ ሰዎች ሕይወት ተሞክሮ ውስጥ ወደ ምንፈልገው የተለያዩ የፍቅር ዓይነቶች እንመልከት፡፡
  • የውሸት ፍቅር pseudo -love ፡፡ ይህ የውሸት ወይም እውነት ያልሆነ ፍቅር ማለታችን ነው፡፡ ፍቅርን የውሸት ማድረግ እጅግ በጣም አሳዛኝ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ እንደናየው የሰዎችን ትኩረት ከሚስቡ ነገሮች መካከል ዋናዎቹ የማሰመሰል ሥራዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ አንድን ነገር መደበኛ በሆነ መንገድ ለሰው ከማስተማር ይልቅ በድራማ መልክ ቢያደርጉት ቁጥር ሥፍር የሌለው ሕዝብ ተደንቆ ሊማር ይችላል፡፡ እውነተኛ ታሪክ ከሚያነቡት ባልተናነሰ የልበ ወለድ ጽሁፎችን በማንበብ የሚደሰቱ ሰዎች በርካታ ናቸው፡፡ ከእዉነተኛ ነገር ይልቅ የማስመሰል ሥራዎች ብዙዎችን እያስደነቁ ባሉበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡ ሰይጣንና ሥጋም ተባብረው ውሸት ነገር እያመረቱ ያቀርቡልናል፡፡ በዚህም ጊዜ ፍቅርም የውሸት በሆነ መንገድ የሚገለጥባቸውና ብዙዎችን የሚማርክበት መንገድ ብዙ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን ይለናል( ሮሜ 129) እውነትነት የሌለው ፍቅር አደጋ ያለበት ነው፡፡ ለምሳሌ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያት ከሆኑት አንዱ አሰቆሮቱ ይሁዳ ነበረ፡፡ ይህ ሰው ኢየሱስን አቅፎ የሳመበት ታሪክ ያለበትን ሥፍራ በቃሉ እናነባለን፡፡ ይሁዳ ኢየሱስን ሲስመው ያየ ሰው በፍቅር ተንሰፍስፎ ይህንን የሚያያደርገው ሊመስለው ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ፍቅራቸውን የሚገጹልፁት ፈግታ በማሳየት፣ በማቀፍ እና በመሳምም ጭምር ስለሆነ ነው፡፡ አስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን እንደዛው አቅፎ ይሳመው እንጂ እርሱ በፍጹም ውሸታም ነበረ፡፡ እንዲያውም ጻድቁን የእግዚብሔርን ልጅ በ30 ብር በመሸጥ ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ እየሰጠ ነበር የሚስመው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ የውሸት ፍቅር የሚባለው፡፡ በዘመናችንም ቢሆን እንደዚህም ያሉ እግዚአብሔር አምላክ ለሰዎች ልጆች ከሰጠው እና እኛም እንድንተገብረው የሚያስፈልገን ፍቅር የተባለን ትልቅ ጉዳይ ሰዎች የሚያሳዩት የውሸት በሆነ መንገድ ሆኖ ስናየው እጅግ ያሳዝነናል፡፡ ምናልባት ወንድማችንን ለሞት አሳልፈን እየሰጠን አወድሃለሁ እያልን አቅፈነው እንስመው ይሆን፡፡ ወይም ሊፈታ በማይችል መልኩ ከበስተጀርባው ገመድ እየተበተብንበት ከፊቱ በኩል አልፈን እወድሃለሁ እያልን አገላብጠን እንስመው ይሆንን/ የእግዚአብሔር ቃል ግን ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን ይለናል፡፡
  • አሔብ/Aheb/: ( የብልጫ ፍቅር)፡ ይህ ከአንዱ ሌላውን አሰበልጠን ወይንም አንዱን በተለየ መልክ የምንወደበት ፍቅር ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ እግዚአብሔር የሰጠኝን ልጆቼን እወዳቸዋለሁ፣ ባለቤቴን ግን በጣም እወዳታለሁ፡፡ ይህንን ማንም ሊቃወመኝ አይችልም፡፡ ልጆቼም ቢሆኑ እንዴት እናታችንን ከእኛ አስበልጠህ ትወዳታለህ ሊሉኝ አይገባቸውም፡፡ አንድ ሰው ወንድሙን፣ እህቱን ፣ እናትና አባቱን እንደሚወደው በጣም የታወቀ ነገር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሚሰቱን ወይም ባልዋን ከእነዚያ ሁሉ አሰበልጦ መውደድ ይኖርበታል/ ባታል፡፡ አሔብ የተሰኘው ፍቅር ከዚህ አንጻር በጣም ጤናማ ሲሆን አደገኛ የሚሆንበት መንገድም ደግሞ አለ፡፡ ያውም ንብረትንና ንዋይን ከትዳር ጉዋደኞቻችን ወይም ከዘመዶቻችን አስበልጠን የምንወድ ከሆነ አደገኘ ነው ማለት ነው፡፡ በባሎቻችንን ወይንም ሚስቶቻችንን ከሞተልን ጌታ አስበልጠን የምንወደው ከሆነ አጅግ በጣም አጥፊና ጣዖት ይሆንብናል ማለት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ማንም አባቱን ወይም እናቱን ወይም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ከእኔ አብልጦ የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም አለ፡፡ የብልጫ ፍቅር ጥቅምም ጉዳትም እንዳለው ከዚህ እንማራለን፡፡ ልብ ብለን ያየን እንደሆነ ከክርስቶስ የተቀበልነው ፍቅር በቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም ተበርዞ እናየዋለን፡፡ ለምሳሌ የመዘምራን ቡድን እርስ በርሳቸው ያለው ፍቅር በጣም የሚስብና የሚያስቀና ነው፡፡ ይሁን እንጂ የመዘምራን ቡድኑ አባላት ፍቅር ከዚያው ቡድን አልፎ መሄድ የማይችል ነው፡፡ እዚያው እርስ በርሳቸው እንጂ ያንኑን ፍቅር ለሌላው ለማሳየት ብዙም የማይፈልጉባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ የጸሎት አገልግሎት ክፍሎች ከራሳቸው ሰዎች እንጂ ሌላውን በዚያው ሁኔታ መቅረብ ይከብዳቸዋል፡፡ ይህ ፍቅር ነው ግን ክርስቶስ ያስተማረን አይነት ፍቅር አይደለም፡፡ አሁን የምናየው በአብዛኛው ንጹህ የሆነ የጌታ የመስቀሉ ፍቅር ሳይሆን ሰዎች በራሳቸው መንገድ ለማሻሻል እየሞከሩት ለራሳቸውመም በሚመች መንገድ የሚተገብሩት/ Modified / የሆነ ዓይነት ፍቅር ነው፡፡ ዋንኛው/Original / የጌታ ፍቅር ግን እንደዚህ አልነበረም፣ ይልቁንም ሁሉን የሚወድድ ፍቅር ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔርም እኛን ሁላችንን ነው የወደደው እንጂ ከእኛ መካካል የሆነ ሰውን ወደ ጎን ትቶ አልወድህም የሚለው አንድም የለም፡፡ በእርሱ የሚያምን ሁሉ እንዲድን ዓለምን ሁሉ ነው የወደደው፡፡
    አብያተ ክርሰቲያናትም የተቸገርንበት ትልቁ ፈተና ይህ ነው፡፡ በቤተ እምነት ወገንተኝነት ሁሉም ሰው ሲታይ የፍቅር ልዩነት ሲያደርግ ይስተዋላል፡፡ እኔ የዚህ ቤተክርሰቲያን አባል ነኝ ቤተክርሰቲያኔን እወዳታለሁ የሚሉ ብዙ ሰዎችን እንሰማለን፡፡ ይህ ሊበረታታ የሚገባ ነው፡፡ እያንዳንዱ አማኝ የራሱን ቤተክርሰቲያን መውደድ ይኖርበታል፡፡ ግን ታዲያ የሌላውን በቤተ እምነት የሚኮንን ከሆነ አልፎም የሚጠላ ከሆነ የዚህ ሰው ፈቅር ጤናማ ነው ለማለት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ያለን ከሆነ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ በኩል የገለጠልን የመስቀሉ ፍቅር አልገባንም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ወደ እውነተኛው የክርሰቶስ የቄራኒዮ ፍቅር መመለስ ይኖርብናል፡፡
  • ሐባብ/Habab/: በጣም ቅርበትንና የልብ ወዳጅነትን የሚገልጡበት ፍቅር ነው፡፡ ይህ ወደ ደረት የመጠጋትን ሁኔታ የሚያሳይ ሲሆን Bosom friend/ ከተሰኘው የእንግሊዚኛ ቃል ጋር የተቀራረበ ነው፡፡ ዮናታንና ዳዊት ሁለቱ በጣም የሚቀራረቡ ወዳጆች ነበሩ ምክንያቱም የዮናታን ነፍስ በዳዊት ፍቅር የታሰረች ነበረችና፡፡ ይህ ከአንድ ሰው ጋር በሆነ ምክንያት በጣም መዋደድን የሚያመለክት ዓይነት ፍቅር ነው፡፡ በመሠረቱ ይህም ቢሆን ምንም ችግር አይታይበትም ምክንያቱም ማንም ሰው ከወገኑ ጋር መዋደድ ይጠቅማል እንጂ ማንንም የሚጎዳ አይደለም፡፡ ጉዳትና ኃጢአት የሚኖረው በመዋደድ ስም ሌላውን የሚጎዱና የሚያገልሉ ከሆነ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ሐባብ የተሰኘው ይህ ፍቅርም ቢሆን ሐዋሪያው ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ብሎ የሚነግረንን ፍቅር አያሳይም፡፡
  • ኢሮስ /Eros/የጾታ ፍቅር፡፡ ይህንን በተለያየ መልኩ ማየት እንችላለን፡፡ አእምሮአቸው ወደ ጉርምስና የደረሱ ወጣቶች ለተቃራኒ ጾታ መሳሳብ መጋለጣቸው አይቀረ ጉደይ ነው፡፡ እወድሃሁ እወድሻለሁ እንዲባባሉ ይገደዳሉ፡፡ በዚህ ፍቅር ውስጥ አንድ የሩካቤ ሥጋ ፍላጎት የሚባል ድብቅ ኃይል መኖሩ የሚካድ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱን ፍቅር በተገቢው መንገድ መጠቀም ካልተቻለ ከፍተኛ ውድቀትን ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡ የሚፈልጉትን የሥጋ ግንኙነትን አግኝተው ሲያበቁ ከወደዱት መውደድ በበለጠ ጥል የሚጠላሉበት ሁኔታ ይከሰታል፡፡ ለእውነተኛ ጋብቻና ዘላቂነት ላለው የትዳር ትስስር ካልሆነ በእንዲህ ዓይነቱ መቀራረብ ምክንያት የወገኖች ልብ የሚሰብርበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ በበለፀጉት አገሮች የሚታየው ይህን የመሰለ ነገር ነው፡፡ ብዙዎች እወድሃለሁ እወድሻለሁ ሲባባሉ ለሚያይ ሰው እንዴት ዓይነት ጥልቅ ፍቅር ቢኖራቸው ነው እንደዚህ የሚሆኑት ያስብላል፡፡ አንዳንዶች የፍቅር ጉዋደኞቻቸውን በስማቸው እንክዋን ከሚጠሩ ሐኒ መባባል ይቀላቸዋል፡፡ ይህ እንግዲህ ማር ማለት ነው፡፡ በአገራችን አውድ እንጥራው ካልን ደግሞ የኔ ማር ማለታቸው ወይም ደግሞ ማሪዬ እንደ ማለት ነው፡፡ የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን እንደዚህ እንደእሳት የጋለ የሚያስመስሉት ፍቅር ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዳልነበረ ሲሆን ማየት ነው፡፡ ሐኒ ሲባባሉ የኖሩበትን ፍቅር ለማፍረስ ጊዜ አይፈጅባቸውም፡፡ ከዚያ ማይ ኤክስ ዋይፍ ወይም ኤክስ ሃስባንድ የሚለውን ስም ወዲያው ይለጥፉበታል፡፡ የልጆቼ እናት ወይም አባት ለማለትም አይፈልጉም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጾታዊ ፍቅርና ያስከተለውም አደጋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጸፎአል፡፡ የንጉሥ ዳዊት ልጅ ከእህቱ ( ከወንድሙ ልጅ) ከትእማር በጾታዊ ፍቅር በመያዙ ለራሱም ለቤቱም ያሰከተለው መዘዝ ከፍተኛ መሆኑን በእግዚአብሔር ቃል እንመለከታለን( 2ሳሙኤል 13) አምኖን ትእማርን ከመውደዱ የተነሳ እንደ ሕመምተኛ ሆኖ ነበር፡፡ በቃሉ እንደምንመለከተው ከመተከዝም አልፎ የታመሙንም እናነባለን፡፡ እስከ ሕመም የሚያደርሰው ፍቅር ይዞት ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ፍቅር በእውነት ጤናማ ቢሆን ኖሮ ያሳምመው ነበር ወይ የሚል ጥየቄ ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ለምን ቢባል አንድ ወገን ብቻ የሚታመምበት ከሆነና ሌላይኛው ፈጽሞ ለጉዳዮ እንግዳ የሚሆንበት ከሆነ ይህ ፍቅር ሊዘልቅ አይችልም፡፡ አምኖን ትእማርን እርስዋ በማታውቀው መንገድ ወደዳትና ከዚያ ፍቅር የተነሳ እንደ ህመምተኛ ይክሳ እንጂ ትእማር በዚያው መንፈስ እርሱን ለመወውደድ ላለመውደድዋ እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ዛሬም በዘመናችን እገሌን ወደድኩት ወይም እገሊትን ወደድኩአትና ተቃጠልኩ አረርኩ የሚሉት ሰዎች የሚፈጥሩት ተመሳሳይ ስህተት ነው፡፡ አንድ ወገን ብቻ በፍቅር ተያዝኩ ብሎ ብቻውን ቢከንፍ ያ ዓይነት ፍቅር በተቃራኒው ወገንም ላይ የሚያስከትለው ፈጸሜ ጥፋት ነው የሚሆነው፡፡ በቃሉ እንደምንመለከተው አምኖን የብልሁን ሰው የኢዮናዳብን ምክር ተጠቅሞ ትእማርን ካስነወራት በኃላ ወዲያውኑ ፈጽሞ እንደጠላትና እንዲያውም አስቀድሞ ከወደዳት ውድ ይልቅ የጠላት ጥል እንደበለጠ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል(2ሳሙኤል 1315)፡፡ የአምኖን ፍቅር ዕድሜው በተወሰነች ደቂቃ ብቻ የታጠረች ነበረች፡፡ በከባድ የውስጥ ደዌ እንደታመመ ሰው እስክመነምን ድረስ የጎዳው ፍቅር እህቱን ካስነወራት በኃላ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ሊቀጥል አልቻለም፡፡ ትእማርን የጠላበት ጥላቻ ከማየሉ የተነሳ በአገልጋዮቹ አስገድዶ አስወጣትና በሩን ከኃላዋ እንዲዘጉባት አደረገ ምክንያቱም ተመልሳ እንዳትገባ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የአምኖን የፍቅሩ ጅማሬ የሚመስል ፍቅር በባልና በሚስት መካከል ሲሆን እጅግ ያማረ እጅግም የተቀደሰ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ባልና ሚስት አንዳቸው ለሌላው ያላቸውን ፍቅር በተራክቦ ቢገልጹት የተቀደሰና የተባረከ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሐዋሪያው ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ የሚለው ፍቅር እንደዚህ ዓይነቱም አይደለም፡፡
  • ፒሊዮ የቤተሰብ ፍቅር፡ ቤተሰብ ማለት አባት እናት ወንድም እህት ወዘተ ሲሆኑ በአንድ ቤት ውሰጥ የሚኖሩ ማለታችን ነው፡፡ አንዳንድ ወገኖች ፒሊዮ የተሰኘው ፍቅር የቤተሰብ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የምክንያት ወይም የእንካ በእንካ ፍቅርም እንደሆነ ያምኑበታል፡፡ እርግጥ ነው አባቴ ወይም ልጄ ስለሆነ እወደዋለሁ የማለት ግዴታ ይኖርብናል፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ለቤተሰባችን እንድናስብ ይመክረናል፡፡ ቤተሰባችንን ከጌታ አብልጠን መውደድ ነው የተከለከልነው እንጂ የወላጅነትንና የልጅነትን እንዲሁም ደግሞ ወንድምነትና የእህትነት ፍቅራችንን መግለጽ ተገቢ ነው፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዲወድዱአቸው በጣም ይመክራል( ኤፌሶን 5231ጴጥ 3) ባል ሚስቱን እንደራሱ አድርጎ አንዲወድድ የሚያስገድደው የጌታ ትዕዛዝ በሁሉም ዘንድ መከበር አለበት፡፡ ባልና ሚስት አንድ አካል ስለሆኑ ከቤተሰብ ሁሉ መካከል የእነርሱ ፍቅር የተለየ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ፍቅር ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ የሚለውን ፍቅር አይገልጸውም፡፡ ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ከዚህ ቀጥሎ ያለው የፍቅር ዓይነት ነው፡፡
  • አጋፔ ( አጋፔ) የተባለው ፍቅር ነው፡፡ አጋፔ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር ማለት ነው፡፡ ይህ የእዚአብሔር ፍቅር ከላይ ከተለከትናቸው ፍቅር ዓይነቶች ሁሉ የሚለይ ዓይነት ፍቅር ነው፡፡ ይህ ፍር በተለያዩ የጸጋ ስጦታዎች ከማገልል ይበልጣል፡፡ ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኃለሁ የሚለንም መንገድ ይህ ነው፡፡ ይሕ አጋ የተሰኘው የእዚአብሔር ፍቅር በመካላችን ማለትም በቤተክርስቲያን ይገለጥ ዘንድ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር ከሌች የፍቅር ዓይነቶየተለየ ሚያደርጉ ብዙ ባሕሪያቶች አሉ፡፡ እነዚህን በጥቂቱ መመልከት ይኖርብናል፡
  • የእግዚአብሔር ፍር ምንጩ ራሱ እግዚአብር ነው፡፡ እኛ የዚህ ፍቅር ምንጮች ልንሆን አንችልም፡፡
  • እግዚአብሔር ፍር የይወደደውን የሚወድድ ነው፡፡ ሮሜ 56-8
  • ምክንያተ አልባ ወይም በምንም ምክንያት ላይ ያልተመሠረተ የእንዲሁ ፍቅር ነው( unconditional love) የዮሐ 316
  • ራሱን መስዋዕት የመያደርግ ፍቅር ነው( self sacrificial love)
  • ራስን በመካድ የሚገለጥ ፍቅር ነው ( -Self denying)
  • በጊዜ ያልተወሰነ ፍቅር ነው( timeless love) የዮሐ 131
  • አባታዊ ፍቅር ነው Fatherly love፡፡ አባታዊ ፍቅር ስንል በሁለት መልኩ ማየት እንችለን፡፡ ያውም ለልጆቹ የሚራራና የሚቀጣ ፍቅር ነው፡፡ ዕብራዉያን 125-8)፡፡ እንግዲህ ይህ ፍቅር ሰዎች ለራሳቸው ስሜት ሲሉ እንዳሻቸው የሚጠመዝዙት ዓይነት ፍቅር ሳይሆን በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የእግዚአብሔር ፍር ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር አስተምሮአል። የእግዚአብሔርን ፍቅር መከተል ጉዳይ ከጌታ የተሰጠን ተዕዛዝ እንጂ ስንወደው የምናደርገው ሳንወደው ደግሞ የማናደርገው የምርጫ ጉዳይ አይደለም። አጋፔ የተባለው የእግዚአብሔር ፍቅር ለጠላትም ነፍስን አሳልፎ እስከስጠት የበረታና የጸና ነው። ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ የተባለበት ምክንያት ምንድነው? ሐዋሪያው ጳውሎስ በም ዕራፍ 13 ላይ ለዚህ የሚሆን 3 ዋና ዋና ምላሾን ይሰጠናል። በክፍል ሁለት እንመለስበታለን፡፡