ገንዘብን
በአግባብ የመጠቀም ሕይወት
ከመጋቢ
ሳሙኤል ሾንጋ
የገንዘብ
ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባ ነው፡፡
በጥንቃቄም ሊታይ የሚያስፈልገው ነው፡፡
ምክንያቱም የሰው ሕይወት ከገንዘብ ጋር
በተያያዘ ሊሰናከልበትም ሊቀናም ይችላል፡፡
ስለገንዘብ ስንነጋገር ከምንነቱ ብንጀምር
የተሻለ ይሆናል፡፡
ገንዘብ
ምንድነው?
በመጽሐፍ
ቅዱስ ገንዘብ በተለያዩ ቃላት ተገልጿል፡፡
በጣም የሚታወቁት ዕብራውያንና ግሪኮች
የሚጠቀሙባቸው ቃላት በእጅጉ የተለመዱ ናቸው፡፡
ዕብራውያን ከሰፍ/keceph/
ሲሉ
ግሪኮች ደግሞ አርጉሪዩን/argurion/
እንደሚሉ
ተንታኞችና አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ የሁለቱም
ትርጉም አንድ ሲሆን ያውም ብር/silver/
ማለት
ነው፡፡ ሰብቱአጂንት በመባል የሚታወቅና
በ250
ዓ.
ዓ.
አካባቢ
ብሉይ ኪዳንን ወደ ግሪክ ቋንቋ የተረጎመው
የሰባ ሊቃውንት ጉባኤ ገንዘብን ሲተረጉመው
ላምብ /Lamb/
የሚል
ስያሜ ሰጥቶታል፡፡ ይህ አባባል የበግ ጠቦት
ከሚለው ጋር ተቀራራቢነት ያለው ነው፡፡ ዳግማዊ
አግሪጳ
የተባለው
ንጉሥ
ገንዘብን
ሳንቲም(
coin) ብሎ
ስም
ሰጥቶአል፡፡
ገንዘብ የተሰጠው ሌላው ስያሜ ደግሞ ፍራንክ
(coin)
የተባለው
ነው፡፡ ቀዳማዊ ዳርዮስ በራሱ ዘመን ፍራንክ
የተባለውን ገንዘብ ለፔርሺያውያን አስተዋውቋል፡፡
በማቴዎስ
ወንጌል 10፡9
ማር.
6፡8
12፡
41ላይ
የተጠቀሱት እንደነ መሐልቅ፣ በትር፣ እንጀራ፣
ከረጢት፣ ሳንቲም፣ ናስ፣ እጀጠባብ፣ ጫማ
የመሳሰሉት ሁሉ በጊዜው ገንዘብን የሚወክሉ
ነበሩ፡፡
ያኔም
ይሁን
ዛሬ
ገንዘብ
በሰዎች
ልጆች
ሕይወት
በዕለታዊ
እንቅስቃሴዎቻቸው፣
በአኗኗር
ዜዴዎቻቸውና
በማህበራዊ
ግንኙነታቸው
ውስጥ
ወሳኝና
ጠቃሚ
ሚና
ሊጫወት
የሚችል
አገልጋይ
መሆኑ
ሊታወቅበት
ይገባል፡፡
ታሪክም
እንደሚያስረዳው
በቀድሞ
ዘመን
ወርቅና
ብር
በሶሪያና
በፓለስታይን
ታዋቂ
የመገበያያ
መሣሪያዎች
ነበሩ፡፡
ግብፅና
ባቢሎን
የውጭ
ምንዛሪያቸውን
ለንግድ
ሥራ
ተጠቅመውበታል፡፡
በእርግጥ
በዘፍጥረት
13፡1
እደምንመለከተው
እንደነአብርሃም ያሉ
የእምነት
አባቶች
በኖሩበት
ዘመን
የአንድ
ሰው
የሀብቱ
መጠን
የሚለካው
በከብቶች፣
በእህል፣በብርና
በወርቅ
ብዛት
ነው፡፡
አብርሃም
በከብት፣
በብርና
በወርቅ
እጅግ
በለፀገ
ይላል፡፡
በዚያን
ዘመን
የነበረው
ሁኔታና
አሁን
ያለን
የሀብትን
መጠን
የምንለካበት
ሁኔታ
በጣም
የተለያዩ
ናቸው፡፡
ያኔ
ሀብት የሚባለው
በጎተራ የሚከተት
እህል
በሜዳ
የሚሰማራ
ከብት
በከረጢት
የሚቋጠር
ብርና
ወርቅ
ሲሆን
በእኛ ዘመን
ደግሞ በቀላሉ ተጣጥፎ በኪስ በሚገባ የወረቀት
ኖቶች በባንክ በሚቀመጥ ወይም በብዙ ሚሊዮን
የሚቆጠር ሀብት በአንድ ብጣሽ ወረቀት ከቦታ
ወደ ቦታ ሊንቀሳቀስ በሚችል ሁኔታ ነው፡፡
በጥንት
ባቢሎናውያን ዘመን የገንዘብ ልውውጡ በብረት
ዘንግና ሽብልቅ (ሻውል)
እንደነበር
ይታወቃል፡፡ በመፅሐፈ ኢያሱ 7፡21
አካን
የወሰደው ካባና ወርቅ እንዲሁም ብር ለገንዘብ
ልውውጥ ሊረዱ እንደሚችሉ ይታመናል፡፡ እነዚህ
ከላይ የተመለከትናቸው በጣም ትላልቆችና
ሰፋፊዎች ለሆኑ ልውውጦች የሚያገለግሉ ሲሆኑ
በጣም አነስተኛ ለሆኑም የሚያገለግሉ አሉ፡፡
ለመገበያያ ልውውጥ ብቻ ሳይሆን ለወዳጅም
የሚሰጠው ስጦታ ዓይነቱ ተመሳሳይነት ያለው
ነው፡፡ የአብርሃም ሎሌ ለርብቃ የሰጠው
የወርቅ፣ የቀለበትና የአምባር ስጦታ ነበር፡፡
በዘፍጥረት 24፡22
ላይ
ይህንን መመልከት ይቻላል፡፡
ብርና
ወርቅ ገንዘብን የሚወክል ቢሆንም የጊዜው
ልውውጥና ግብይይት በቁጥር ሳይሆን በመጠን
ወይም በሚዛን እየተመዘነ ነበር፡፡ ስለዚህ
ነው የአብርሃም ሎሌ ለርብቃ የሰጠው የስጦታ
ብርና ወርቅ ሲለካ ግማሽ ሰቅልና አሥር ሰቅል
ተብሎ የተገለፀው፡፡ የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ
ቃላት (ዲክሽኔሪ)
እንደሚገልፀው
ሰቅል በጥንት ዘመን የነበሩ ሕዝቦችና መንግሥታት
የአንድን ነገር ክብደት የሚያውቁበት መለኪያ
ነው (1ሳሙ.
17፡5
2ሳሙ
14፡26
2ነገሥ.
15፡19)
፡፡የዮሴፍ
ወንድሞች እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ በወረዱ
ጊዜ የያዙት ገንዘብ አንድ ሁለት ተብሎ የሚቆጠር
ሳይሆን በከረጢት እንደተቋጠረ ተደርጎ
የተገለፀው ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ነው
(ዘፍ.42፡
35)
፡፡
ለእነርሱ
ብቻ ሳይሆ ለአይሁዶችም እንዳስተዋወቀ ግልፅ
ነው፡፡ የይሁዳ ልጆች የፍራንክን ግብብይት
ያስፋፉት ከባቢሎን ምርኮ በኃላ ነበር፡፡
በተለይም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ7ኛው
ክፍለ ዘመን ይገለገልበት የነበረው ፍራንክ
(ሳንቲም)
እንደእንቁላል
ዓይነት ቅርፅ ያለው ሞላላ ነበር፡፡ ኤች ፖርት
የተባሉ የሥነ መለኮት ምሁር The
International Standard Bible Encyclopedia በተባለው
ፅሑፋቸው ስለ እነዚህ ፍራንኮች ወይም ሳንቲሞች
ሲገልጹ ባቢሎናውያን ሳንቲሞቹን ለንግድ
ግልጋሎት እንደሚያውሉአቸውና በመካከለኛው
ምሥራቅ በተይም በፓለስቲና ምድር እስከ ድህረ-
ምርኮ
/post
exile/ ድረስ
የፍራንክ ገንዘብ እንዳልነበረ ይናገራሉ፡፡
ከዚያ ዘመን በኃላ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰው
ብቸኛው ፍራንክ ወይም ሳንቲም ዳሪክ የተሰኘው
ነበር፡፡ ዕዝ.2፡69
8፡27
ነህ.7፡70-72፡፡
አይሁዶች ይህንን ገንዘብ የተጠቀሙበት ምክንያት
መቃቢያን እስከተነሱበት ዘመን ድረስ የራሳቸው
ገንዘብ ሳላልነበራቸው ነው፡፡ መቃቢያን
ከክርስቶስ ልደት በፊት 143-
141ዓ.ዓ.
ራሳቸውን
ችለው መተዳደር ስለጀመሩ የራሳቸውን ፍራንክ
(ሳንቲም)
አዘጋጁ፡፡
ይህ ደግሞ ጥንካሬአቸው ከሚለካባቸው መንገዶች
አንዱ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አንድ አቅመ ደካማ የሆነ
መንግሥት ገንዘብ ማሳተምና መቅረጽ ሳይችል
ቢቀር የሌሎች ጡንቸኞች መንግሥታትን ገንዘብ
ይጠቀምበታል፡፡ ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት
የኢጣሊያንን እና የእንግሊዚን ገንዘብ
ትጠቀምበት እንደነበረ ሁሉ አይሁዶችም
አስቀድመው ተመሳሳይ ሁኔታዎችን አሳልፈዋል፡፡
እንዲሁ
ለመንደርደሪያነት ይህን ያህል ካልን ከፍ
ብሎ እንደተገለፀው ገንዘብ በልዩ ልዩ መልክ
የሚተረጎም ነው፡፡ መጠኑ በመለኪያ የሚመዘን
ብርና ወርቅ ይሁን ሌላው በከረጢት የሚቋጠር
አሊያም የከብትና የጎተራ ቁጥር ይሁን እንደየዘመኑ
አውድ መሠረት በሰዎች ሕይወትና ማንነት ላይ
አዎንታዊም አሉታዊም ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል
ከፍተኛ ኃይል ያለው ነገር ቢኖር አንዱና
የመጀመሪያው ገንዘብ ነው፡፡ ስማቸው ገንኖ
የወጣ የምድር ነገሥታት ታሪክ በአንድም ይሁን
በሌላ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነገር አለው፡፡
ርቀን ሳንሄድ አሁን ያለንበትን ሁኔታ ከገንዘብ
ጋር አያይዘን ብናየው ስሙ የማይጠራበት
መድረክና አደባባይ የለም፡፡ ሰው ማን ነው
ሲባል ወዲያውኑ ያለው የገንዘቡ መጠን ከፍ
ወይም ዝቅ ሊያደርገው ይጀምራል፡፡ እግዚአብሔር
በፈጠራት ምድር የሚኖሩ ሰዎች ዘንድ በስብዕናቸው
የቅንጣት ያህል እንኳ አይበላለጡም አይተናነሱምም፡፡
ይሁን እንጂ በሰዎች ያላቸው ተሰሚነትና ከበሬታ
ይለያያል፡፡ ይህንን ልዩነት ያመጣው በዋናነት
ገንዘብ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር የእግዚአብሔር
ቤት በሆነው በቤተክርስትያን እንኳ ገንዘብ
ላላቸው ሰዎች የሚሰጠው ከበሬታና ለምስኪኖች
ያለው ግምት በእጅጉ የተለያየ ነው፡፡ ለሰዎች
የምንሰጠው የቅጽል ስም እንኳ አንዳንዴ
ከገንዘብ ጋር ትሥሥር ያለው ነው፡፡ ለምሳሌ
አንዳንዶችን እንጥቀስ፡፡
አቶ
ከንጃሎ በጣም የተረፋቸው ናቸው ቢባል ምን
ማለት ነው?
የተረፋቸው
ምንድነው?
የተረፋቸው
ንግድ ነው?
የተረፋቸው
ቤት ነው?
የተረፋቸው
ምግብ ነው?
ምንድነው
የተረፋቸው?
መልሱ
አጭር ነው ፡፡ ያው ገንዘብ አላቸው ማለት
ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ እንይ፡፡ አቶ
ከንጃሎ አቅም ያላቸው ሰው ናቸው ሲባል ብንሰማ
ሰውዬውን ባናውቃቸውም ወዲያው አንድ ነገር
እንረዳለን፡፡ አቅም አላቸው የሚለው አባባል
ወደ አእምሮአችን የሚያመጣው ብረት ስለሚያነሱ
ጡንቻ ያላቸውና መቶ ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ናቸው
ተፈጥሮም የለገሳቸው ጉልበትና ጥንካሬ አላቸው
የሚለውን ትርጉም ሳይሆን ገንዘብ ያላቸው
ሀብታም ናቸው የሚለውን ነው፡፡ በተቃራኒው
ደግሞ አንድን ሰው እርሱ እኮ አቅም የለውም
ሲባል ብንሰማ ደካማ ኮሳሳ እድሜው 40
ዓመት
ሆኖት እያለ ገና 25
ኪሎ
የሚመዝን ሚስኪን ሰው ማለታችን ብቻ እንዳይደለ
ልቦናችን በደንብ ያውቃል፡፡ አባባሉ በአጭሩ
ገንዘብ የሌለው እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡
ገንዘብ
የራሱ ኃይል ያለው ነገር እንደሆነ መታወቅ
እንዳለበት ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡ ኃይል
የሚኖረውም ሰዎች ለገንዘብ ከለን አመለካከት
የተነሳ እንደሆነም ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ይህንን ሃሳብ የሚያረጋግጡልንን ተጨማሪ
ማስረጃዎችን እንመልከት፡፡
- ገንዘብ እንደጌታ ሆኖ ሰዎችን የመግዛት ኃይል አለው፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም በማለት ያስተማረው፡፡ማቴ 6፡24
- ገንዘብ እውነትን የማስለወጥና ውሸትን የማስከበር ኃይል አለው፡፡ ማቴ.28፡11-15
- ሰዎችን የማስታበይና ልበ ደንዳና የማድረግ ኃይል አለው፡፡
- እግዚአብሔርን የማስካድና ከፊቱ የማስኮብለል ኃይል አለው፡፡ማቴ 26፡14-16
- የእግዚአብሔርን ሥራና አገልግሎት የማስጣል ኃይል አለው፡፡
- በወንድማማቾች መካከል ጠብ የመጫር አቅም አለው፡፡
- ክፋትን ሁሉ የማፍራትና የማፅናት ኃይል አለው፡፡
- የሰዎችን ስብዕና የማዋረድ አቅም አለው፡፡
- የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የማቁሸሽ አቅም አለው፡፡
እነዚህ
ከላይ ያየናቸው የገንዘብን ክፋት የሚጠቁሙ
ቢሆኑም መልካምነቱንም እንደሚከተለው የተሻለ
ነው፡፡ ገንዘብ እንደ መጥፎ ነገር እንዲታይና
ከዙሪያችን ርቆ እንዲቀመጥ የሚያስፈልግበት
ምክንያት የለም፡፡ ገንዘብን ተከትለው የሚመጡ
ነገሮች ጉዳትም ይሁን ጥቅሙ የሚወሰነው በሰው
አያያዝ መሠረት ነው፡፡ አያያዙ ጥንቃቄ
የጎደለውና ፈርሃ እግዚአብሔርም ፈፅሞ የጠፋበት
ከሆነ ከላይ እንደተቀመጠው ትልቅ ጥፋት
ሊያስከትል ይችላል፡፡ ነገር ግን ሚዛናዊ
አመለካከት ኖሮን ገንዘብ የተሰሰጠበትንም
ዓላማ ጠንቅቀን አውቀን የምንመራውና
የምንሰለጥንበት ከሆነ ገንዘብ ትርፍና ጥቅም
ያለው ነው፡፡ ወደ አንዳንድ ክርስትያናዊና
መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎች ከመግባታችን በፊት
ቀጥለ የተቀመጡ ጠቃሚ ሀሳቦችን እንመልከት፡፡
- ገንዘብ የእግዚአብሔር ነው፡፡ ሐጌ 2፡8
ገንዘብ
የማንም ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ
ብሩና ወርቁ የእኔ ነው ብሏልና፡፡ ብዙ ሰዎች
ያላቸው ገንዘብ በእነርሱ ብርታትና ድካም
እንዲሁም በጥረታቸው ብቻ እንደተገኘ አድርገው
ያስባል፡፡ ለወደፊቱም ቢሆን ገንዘብን በማግኘት
ረገድ ይህ ነው የማይባል ሚና መጫወትና ታሪክ
መሥራት እንደሚችሉ በልባቸው የሚሰማቸው
በርካታ ናቸው፡፡ የሚገርመው ግን እንደዚህ
ብለው ብዙም ፎክረው ሲያበቁ ሳይሳካላቸው
ቀርቶ ሰው ጥገኛ የሆኑም ይኖራሉ፡፡ የሰው
ልጅ ትልቁ ስህተት እዚህ ላይ ነው፡፡ ያውም
ይህ ያለኝ ገንዘብ የእኔ ነው በብርታቴ ያገኘሁት
ነው ማለት ሲጀምር የእግዚአብሔርን ባለቤትነት
ከአጀንዳው ውጪ አድርጎታል ማለት ነው፡፡
እውነትን እንነጋገር ካልን ብርና ወርቅ የእኛ
ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው፡፡ ይሁን እንጂ
እግዚአብሔር በአደራ ለእኛ ሰጥቶናል፡፡ እኛ
ባለአደራዎች ነን ማለት ነው፡፡ በምድር ላይ
ያለ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፡፡በሺህ ተራሮች
ላይ ያሉ አራዊትና እንስሶች ሁሉ የእርሱ
ናቸው፡፡ እኛም ራሳችን የእርሱ ነን፡፡
እስትንፋሳችንም፣ቤታንና ኑሮአችን ጭምር
ሁሉ ከእርሱ የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡ ስለዚህ
አማኞች ሁላችን ይህንን በመገንዘብ ይህ
የሚኖረው ኑሮ፣የማርፍበት ሥፍራ፣ የሚለብሰው
ልብስ፣ የማረገው ጫማ፣የተወለዱልኝ ልጆች፣በዙሪያዬ
ያለ በረከት የምለው ሁሉ ከእኔ ሳይሆን
በእግዚአብሔር ቸርነት ያገኘሁት ነው ማለት
ይገባናል፡፡
- ገንዘብ በረከት ነው፡፡ (የበረከት ሥጦታ)
ዘዳግም
28፡እግዚአብሔር
ሰውን በገንዘብ ይባርካል፡፡ እርሱ ካልፈቀደ
የሚበላና የሚጠግብ የሚጠጣም የሚረካ ማንም
የለም፡፡ በጥበቡ የሚታወቅ ሰው ንጉሡ ሰለሞን
በመክብብ 2፡24-26
ላይ
እንዲህ ሲል አስቀምጧል፡፡ “ሰው
ከሚበላና ከሚጠጣ በድካሙም ደስ ከሚለው በቀር
የሚሻለው ነገር የለውም፡፡ ይህም ደግሞ
ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደተሰጠ አየሁ፡፡
ያለእርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን
የቀመሰ ማን ነው?
እርሱ
ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንም እውቀትንም
ደስታንም ያሰጠዋል፡፡”
እንግዲህ እዚህጋ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ
ነገር አለ፡፡ የእግዚአብሔር በረከት በተለያዩ
መንገዶች ሊመጣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር
ሲባርክ በምድራዊ ብልፅግና ማለትም በቁሳቁስ
ይባርካል፡፡ ነገር ግን የምድራዊ ቁሰቁስ
ብቻ የእግዚአብሔር በረከት ማስረጃዎች ሆነው
መታየት የማይታይባቸው እውነታዎች አሉ፡፡
በተጭበረበረ መንገድ ብዙ ንዋይ እያግበሰበሰ
በቤቱ የቆለለውን ሰው እግዚአብሔር ባርኮታል
ማለት አንችልም፡፡ በመተትና በጥንቆላ ኃይል
ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ ባለቤት የሆነውን
ሰው እግዚአብሔር ባርኮታል ብንል እንሳሳታለን፡፡
ከዚህ ሁሉ ይልቅ የእግዚአብሔር ባርኮት ነው
የምንለው በትክክለኛና በፅድቅ መንገድ
የሰበሰበውን ሰው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን
እግዚአብሔር ባርኮታል ብለን መደነቅ አግባብ
ነው፡፡ የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ
ታደርጋለችና፡
- ገንዘብ መገልገያ ነው፡፡
ገንዘብ
አገልጋይ
ከመሆን ባለፈ መልኩ የሚሰለጥንብን ከሆነ
የሚገዛን ጌታ ነው ማለት ነው፡፡ በአገልጋይነቱ
እንጂ በጌትነቱ ልንረዳው አይገባንም፡፡
በመጨረሻው ዘመን ያሉ ሰዎች ትልቁ ችግር
የገንዘብ ፍቅር ነው፡፡ ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ
በ1ጢሞ
3፡
ሲናገር በዘመኑ ያሉ ሰዎች ስለሚያሳዩአቸው
ባህሪያት ሲገልፅ ገንዘብን የሚወዱ ከእግዚአብሔር
ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ ብሏል፡፡ ተድላ
ለገንዘብና ከሀብት ጋር የተያያዘ ነገር
አለው፡፡ እግዚአብሔርን እያመሰገንን በአግባቡና
በጥንቃቄ እንዲሁም ማንኛውንም ንብረታችንን
ወይም ስጦታችንን እንደምናከብረው ልንይዘውና
ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ሰውን የሚገዛው
የተሰጠለት ነገር ነው፡፡ ለገንዘብ የተሰጠውን
ሰው ገንዘብ ይገዛዋል፡፡ ለእግዚአብሔር
የተሰጠውን ደግሞ እግዚአብሔር ይገዛዋል፡፡ለገንዘብ
የሚሰጥሰው የገንዘብ ባሪያ ሲሆን ለእግዚአብሄር
የሚሰጥ ሰው ደግሞ የእርሱ አገልጋይ ይሆናል፡፡
ከምንም በላይ ለእግዚአብሔር መገዛት እጅግ
የተሻለ ነው፡፡ሕይወቱን በመልካም የሚመራ
ክርስትያን ወንድም ከገንዘብ ይልቅ ለእግዚአብሔር
ለመገዛት ሊተጋ ያስፈልገዋል፡፡ ገንዘብ
በራሱ ጥሩም መጥፎም አይደለም፡፡ የሚወስነው
የሰው አያያዝ ነው፡፡ ጥሩና መልካም እንደሆነ
ተረድቶ ለሚይዝ ሰው ጥሩ ሲሆን መልካም ላልሆነና
ለክፉ ተግባር ለሚያውል ደግሞ የክፋትና
የወንጀል ማስፈፀሚያ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህም
በላይ ያለው እውነት ግን ገንዘብ መገልገያ
ነው፡፡
- ገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡
አንዳንድ
ጊዜ በጣም መንፈሳዊ ለመሆን ስንንጠራራ
ገንዘብን በፍጹም እንደማንፈልግ ሆነን
እንገኛለን፡፡ ይህ ግን ካለው እውነታ በጣም
የራቀ ነው፡፡ ገንዘብ አያስፈልገኝም የሚል
ሰው ቢኖር በምድር ላይ ካሉት ከማናቸውም የሰው
ዘሮች የተለየ መሆን አለበት፡፡ ገንዘብ በግልም
በጋራም ለሕብረተሰብም ለቤተክርስትያንም
በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ
ለመሥራት ለቤቱም አገልግሎት ገንዘብ
ያስፈልገናል፡፡ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ
ለመገንባት የይሁዳ ነገሥታትና መሪዎች ከሕዝቡ
ገንዘብን ፈልገዋል፡፡ ሕዝቡ በየዓመቱ
በሚያከብሩዋቸው እንደነ ፋሲካ፣የቂጣና
የጴንጤቆስጤ ዓይነት በዓላት ወቅት ያላቸውን
ስጦታ ለእግዚአብሔር ቤት ይዘው ይመጡ ነበር፡፡
ምክንያቱም በእግዚአብሔር ቤት ለሚሠራው ሥራ
ገንዘብ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሐርም
ዕድል ፈንታ ሕዝቡ ስለሆነ የሕዝቡ ልግስና
ለሥራው በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡ ጌታ
እግዚአብሔር የእሥራኤልን ሕዝብ በቤቴ መብል
ይሆን ዘንድ አሥራቱን ወደ ጎተራው አስገቡ
ያለው ሀሳብ በራሱ በየትኛውም ሁኔታ የምጣኔ-
ሀብትን
አስፈላጊነት ያሳያል፡፡ (ሚል.3፡10)
በጌታ
ኢየሱስም የምድር አገልግሎት ሴቶች በገንዘባቸው
አገልግለውት እንደነበር ሉቃስ በወንጌሉ
ውስጥ ይናገራል፡፡ (ሉቃ.8፡1-4)
በምንኖርበት
በ21ኛው
ክ/
ዘመን
ሁሉም ነገር ፈጣን ምላሽ ይፈልጋል፡፡
የቴክኖሎጂውም ዕድገት የዓለም አቀፉን
መንፈሳዊና ቁሳዊ ገጽታዎችን ከተለመደው ውጭ
እያሰቸኮለው ይገኛል፡፡ በአንድ ነገር ጅማሬና
ፍፃሜ መካከል ምንም ክፍተት ያለ እስከማይመስል
ድረስ ሁኔታዎች እየተፋጠኑ ይገኛሉ፡፡ ታዲያ
በዚህ ሁሉ ውስጥ የገንዘብ አስፈላጊነት በጣም
ከፍተኛ ነው፡፡ በወንጌል አገልግሎትም ውስጥ
የገንዘብ አስተዋፅዖ ሰፊ ሥፍራ አለው፡፡
በቂ ገንዘብ ካለ በጣም ለየት ባለና በተፋጠነ
መልኩ ወንጌልን ማዳረስ ይቻላል ማለት ነው፡፡
- ገንዘብ ክቡር ነው
ገንዘብን
መናቅ አግባብ አይደለም፡፡ ያለ ቦታውም
መበተንም አስፈላጊ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር
ቃል ማባከንን ይቃወማል፡፡ መንፈስ ይሙላባችሁ
እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና
ኤፌ 5፡18.
እግዚአብሔር
የሰጠንን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ማዋል እርሱን
ጌታን የሚያስከብር ሲሆን ለእኛም ጥቅምና
ክብር ያለው ነው፡፡ ሰዎች ገንዘብን በአንዳንድ
አጉዋጉል በሆኑ ቦታዎች የሚያውሉት የገንዘብን
ክቡርነት ስላልተረዱት ነው፡፡ አማኝ ግን
አደራ አለበት፡፡ በአንድ ባንክ ቤት ገንዘብ
ከፋይ የሆኑ ትልቅ ሰው የመቶ ብር ኖት ሊዘረዝር
ከመጣው ወጣት ጋር ተጣሉ፡፡ የጥላቸው መንስኤ
ወጣቱ የመቶ ብር ኖቱን በአራት ቦታዎች አጣጥፎ
ስለሰጣቸው ገንዘብ ክቡር ሆኖ ሳለ እንዲህ
የሚታጎሳቁለው ለምንድነው ብለው ነው፡፡
ያሉት ቃል አስደንቆኛል፡፡ አንተ እንደዚህ
ያማረብህ የምትኮራውና የምትዝናናው በገንዘብ
ምክንያት ነው፡፡ ግን ይህንን ገንዘብ
አላከበርከውም አሉ፡፡ መቼም ገንዘብን
እንደአምላክ የማናመልክ ብንሆንም የሚገባውን
ጥንቃቄ ማድረግና የአያያዝ ሥነ-ምግባራችንን
ማስተካከል የሚጠበቅብን ጉዳይ ነው፡፡
- መንፈሳዊነት በገንዘብ አይለካም፡፡
ደጋግመን
እንደተነጋገርነው የሰው ልጅ ሕይወት ከገንዘብ
ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ “
ገንዘብ
ካለ
በሰማይ መንገድ አለ”
“ገንዘብ
ያለው መብት አለው”
የመሳሰሉት አባባሎች በጣም የተለመዱ ናቸው፡፡
ከዚህ በዘለለ አንዳንዶች ገንዘብን የደህንነትና
የመንፈሳዊነት መለኪያ አድርገው ያዩታል፡፡
በዚህ አንፃር ሁለት የተለያዩ ፅንፎችን
የሚከተሉ ሰዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል የብህትውና
አመለካከት ያላቸው መንፈሳዊነትን ከድህነትና
ከጉስቁልና ጋር ያያይዙታል፡፡ የሚበላውንና
የሚጠጣውን ሁሉ እስክገድብ ድረስ ከአለም
ጉዳዮችና ለሰው ልጆች ከሚያስፈልጉ መሠረታዊ
ፍላጎቶች ሁሉ ተለይቶና ርቆ መኖር መንፈሳዊነት
ነው ይላሉ፡፡ ጎላ ብሎ አይውጣ እንጂ ይህ
አመለካከት መልኩን ቀይሮ በአንዳንድ ወንጌላውያን
አብያተ ክርስትያናትም ውስጥ አለ፡፡ አገልጋዮቻቸው
መከራን ተቀብለው ተጎሳቁለው ቁልቁዋል በልተው
ማገልገል እንዳለባቸው የሚያስቡ የቤተክርስትያን
መሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ የጠራቸው
ጊዜአቸውንና ጉልበታቸውን ለጌታ አገልግሎት
የሰጡ አገልጋዮች ወንጌላውያን መጋቢያንና
ሌሎችም ኑሮአቸው በጉስቁልና ተወርረው
የምናየው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የገንዘብ ክብርና
ሞገስ ጥቂት በሆነበት በ21ኛው
ክ/ዘመን
እየኖሩም እንኳን እንደድሮ ለምን በ10
ብር
በግ አንገዛም የሚሉ ይመስላሉ፡፡
አንዳንዶች
ደግሞ በጭራሽ ለየት ያለ ጫፍ ይዘው እናገኛቸዋለን፡፡
እነዚህ ደግሞ ሰው ከዳነ መበልፀግ አለበት
ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ በዘመኑ አጠራር የብልፅግና
ወንጌል ተብሎ የሚጠራው ነው፡፡ በእነርሱ
ዘንድ ቁሳዊነት በጣም አይሎ ከድነት ጋር
የተያያያዘ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ
ድነትን ከጉስቁልናም ሆነ ከብልፀግና ጋር
ፈፅሞ አያገናኝም፡፡ ስለዚህ በምድራዊ ቁሳቁስ
መበልጠግ ዋንኛው የመዳናችን ምልክት ሰለሆነ
መበልፀግ አለብን በሚሉና የለም ሰው የፅድቅን
መንገድ መከተሉን በጉስቁልናው ማሳየት
ይኖርበታል በሚሉ አመለካከቶች መካከል የመጽሐፍ
ቅዱሳዊ እይታና ሚዛናዊ አቋም ሊታይ ይገባል፡፡
ይህ ካልሆነ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ በሌለበት
ቦታ ልንወድቅ እንችላለን፡፡ የሀብት ክምችትም
ሆነ ድህነት ከአምላካችን ጋር ላለን የፅድቅ
መንገድ እንቅፋት እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ስለሰጠም መንፈሳዊ ነው
ማለት አንችልም፡፡ይልቁንስ ከስጦታው በስተጀርባ
ያለው ዓለማ መንፈሳዊነትን የሚወስን መሆኑ
መረሳት የለበትም፡፡
መጽሐፍ ቅዱሳዊ
መርሆዎች
ቀደም
ሲል እንደተነጋገርነው ገንዘብ የሚለው ቃል
በእያንዳንዱ ቀን ባለን ንግግር ውስጥ ሳይገባ
አይቀርም፡፡ ገንዘብ ያለው ሰው በማንኛውም
ቦታና ሥፍራ ኃይል ያለው መሆኑንም ተነጋግረንበታል፡፡
ገንዘብን ከአጠቃላዩ የምጣኔ -
ሀብት
ለይተን ለብቻው መመልከት ያስቸግራል፡፡
ምክንያቱም ከእያንዳንዱ የምጣኔ -
ሀብት
ክስተትና ሥርዓት ጋር ገንዘብ የተያያዘ በመሆኑ
ነው፡፡ ይህም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ምክር
ይሰጠናል?
የእግዚአብሔር
ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን የሚያየው
ዛሬ ስግብግበነትና ስስት በነገሠበት ዘመን
የሚኖር አንድ ሰው ከሚያይበት በጣም በተለየ
መልኩ ነው፡፡ የሰዎች ሥነ ምግባርና መልካም
ስማቸው በገንዘብ ምክንያት ጎድፎ እንዳይበላሽ
ያስተምራል ያስጠነቅቃልም፡፡ የእግዚአብሔር
ቃል ስለትምህርተ ሃይማኖት ስለሰው ልጅ ምድራዊ
አኗኗር ትክክለኛ ትምህርት ይሰጠናል፡፡
እንዲያውም የሰው ልጅ ለምጣኔ-ሀብት
ከድርጅቶች በምድር ካሉ ሥርዓቶች ከኢኮኖሚያዊና
ከፖለቲካ ኃይላት ጋር ሊኖር ስለሚገባው ዝምድና
ጭምር ያስረዳል፡፡ ስለገንዘብ የሚያስተምረንን
ቀጥለን እንመልከት፡፡
- ገንዘብን በፅድቅ ማግኘት ( ምሳሌ 10፡2 )
የገንዘብ
ማግኛ መንገዶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዳንዱ ገንዘብ
የሚያገኘው በኃጢአት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ
ጉዳይ ከጠንቋይ ቤት ወደ ጠንቋይ ቤት የሚዞር
ሰው ቁጥር ብዙ ነው፡፡ በውሸትና በማጭበርበር
ሀብት የሚያገኝ ሰው ጥቂት አይደለም፡፡ በዚህ
መንገድ ገንዘብ ቢገኝና ብዙዎችም ብበለጽጉም
እንኳ ዉጤቱ ሰላም ማጣትና ሁከት ነው፡፡በፅድቅ
የሚገኘው ገንዘብ ግን ለባለቤቱ ደስታና ተድላ
ይሆናል፡፡ እግዚአብሔርን
ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት
ብዙ መዝገብ ይሻላል፡፡ምሳሌ 15፡16፡፡
በጽድቅ የሚገኝ
ጥቂት ሀብት በሀሰት ከሚግበሰበስ ብዙ ብልጥግና
ይሻላል፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ ከመጎምጀት
ተጠበቁ ያለው፡፡ (ሉቃስ
12፡)
ብዙ
ክርስትያኖች በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡
አንዳንዶች በመንግሥት ኃለፊነት ቦታዎች
ተቀምጠው ሊሆን ይችላል፡፡ ገንዘብን ማግኘት
በእግዚአብሔር ቃል የተፈቀደ ሲሆን በአንድም
ሆነ በሌላ እያንዳንዱ ሰው ገንዘብ የሚያገኝበት
የራሱ መንገድ አለው፡፡ ለሠራተኛው ደመወዙ
ይገባዋል፡፡ በውትድርና የተሰማራ ሰው የአገርን
ደህንነት ሲያስጠብቅ ለእርሱ የሚገባውን
ክበር ወይም ደመወዝ ማግኘት ይኖበታል፡፡
እንደዚሁም ደግሞ ሁሉም ሠራተኛ ተገቢውን
ድጋፍ ማግኘት እንዳለበት የእግዚአብሔርም
ቃል ይነግረናል፡፡ 1ጢሞ.5፡
17
2ጢሞ
2፡5-7
1ቆሮ.9፡3-12.
የተፈቀደለትን
መብት ማግኘት በሰውም በእግዚአብሔርም
አያስወቅስም፡፡ ከታዘዘለት አብልጦ የሚወስድ
ያልተፈቀደለትን መንገድ ተጠቅሞ ሀብትን
ወይም ጥቅምን ለራሱ የሚያደርግ አማኝ አምላኩንም
ሰውንም ይበድላል፡፡ በንግድ ሥራ ተሰማርቶ
የተሸቃቀጠ ምርትን ለሸማቹ የሚያቀርብ
ክርስትያን ነጋዴ ቢኖር እግዚአብሔር
የማይከብርበትን ነገር እያደረገ ነው ማለት
ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ አሳዛኝ የንግድ
ልምምድ አለ፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ የሚመጡ
አንዳንድ የቅቤ ነጋዴዎች አሉ፡፡ በላተኛው
ቅቤ ነው ብሎ ያገዛቸዋል፡፡ ነገር ግን ቅቤ
ሳይሆን ከቅቤ ጋር የተቀላቀለ ሞራና ሙዝ
ካልሆነም ሰው ሰራሽ ቅቤ ነው፡፡ ሌሎች ማር
የሚሸጡ ደግሞ አሉ፡፡ እነርሱ ደግሞ ማሩን
ስኳር ጨምረውበት ያመጣሉ፡፡ ይህ ተጠቃሚዎችን
ለተለያዩ በሽታዎች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
ያልታወቀ ሌብነት ያካሄዳል ማለት ነው፡፡
የሚገርመው ግን እንዲህ ዓይነት ድርጊት
የሚፈጽሙ ሰዎች አብዛኛዎቹ ዓለማዊያን ቢሆኑም
ዳግመኛ ተውልደናል የሚሉ ክርስትያኖችም
በጉዳዩ ተሳታፊዎች መሆናቸው ነው፡፡
ፅድቅ
የሌለበት ሌላው የገንዘብ ማግኛ መንገድ ጉቦ
ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ጉቦን አጥብቆ
ይቃወማል፡፡ በጉቦ የሚገኘው የገንዘብ መጠን
በደመወዝ ከሚገኘው በጣም የበለጠና ከፍተኛ
ነው፡፡ አማኞች ጉቦን ይቀበሉም ይሰጡም
ይሆናል፡፡ በሁሉም አንፃር ጉቦ የራስን ጥቅም
ለማስከበር ሲባል የሚደረግ ኃጢአት ነው፡፡
ጉቦ ምን እንደሆነና ኃጢአትነቱን ላልተረዳ
ሰው ምንም ላይመስል ይችላል፡፡ ከገንዘብ
ጋር በተያያዘ ሰዎች የሚፈጽሙት ትልቅ ኃጢአት
ቢኖር ጉቦ መቀበልና መስጠት ነው፡፡ ጉቦ
ምንድነው ብሎ መጠየቅና ለዚህ ተገቢውን ምላሽ
መስጠት አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ በዕብራውያን
ዘንድ ጉቦ ኮፐር(koper)
ሾሃድ(shohad)
በተባሉ
ቃላቶች እንደሚገለፅ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡
ብራይብ(
Bribe) የምንለው
የእንግሊዝኛው ቃልም Brib-er-I
ከሚለው
የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የእነዚህን
ትርጉም በጥቅሉ ስንመለከተው ስጦታ ማለት
ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስጦታነቱ ከሌላው ጤናማ
ስጦታ የተለየ ነው፡፡ ትክክለኛ ባለሆነና
ንፅህና በሌለው መንገድ የሚሰጥ ስጦታ(
Gift in corrupted sense) ነው፡፡
ፍርድንና ፅድቅን ለማጣመም የሚደረግ የገንዘብ
አሰጣጥና አቀባበል ሥርዓት ነው፡፡ 1
ሳሙኤል
8፡3፣መዝ.26፡10
ኢሳ1፡23፣33፡15፣ሕዝቅ.22፡16፡፡
በተጨማሪም የመንግሥትን ፍርድ ለማስቀረት
ወይም ለማስለወጥ የሚያደርግ ስጦታ ነው፡፡
በጉቦ ምክንያት ብዙዎች ሕግን ተላልፈው ሳለ
እንደ ሕጋዊ ሰው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነትን
አግኝተው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ
ቅዱስ ጉቦን መስጠትንም መቀበልንም በግልጽ
ይኮንናል፡፡ አሞጽ.5፡12
ፍርድን
ለማጣመም ፍትህን ለማዛነፍ የሚደረገውን
የጉቦ ሂደት መጽሐፍ ቅዱስ ይጠላዋል፡፡ ዘዳግም
23፡
8-
እግዚአብሔርም
ጉቦን የሚለማመዱትን ይቀጣቸዋል ኢዮብ
15፡34.፡፡
ስለዚህ አማኝ ክርስትያን ራሱን ይህን ከሚመስል
ነገር ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ፈተና ይመጣል፡፡ ተቀበል ወይም ስጥ የሚል
ከባድ ፈተና ይደቀንበት ይሆናል፡፡ ይህንን
ፈተና ለማሸነፍ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል፡፡
የቱንም ያህል ፈተና ቢኖር ክርስትያን ምስክርነቱን
መጠበቅና አምላኩን ማስከበር መቻል ይኖርበታል፡፡
- በቃኝታ (እርካታ) ሉቃ.3፡10-14
ለክርስትያን
እውነተኛ እርካታው በገንዘብ ሳይሆን በአምላኩ
ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠኝ ኑሮዬ ይበቃኛል
ማለትና በስጦታው እግዚአብሔርን ማመስገን
ይገባናል፡፡ ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ
ጉዳይ በጥልቀት ሲያስተምር ስንወለድ ምንም
ይዘን አልመጣንም ስንሞትም ምንም ይዘን
አንሄድም ይላል፡፡(1ጢሞ.6፡6-8)
ለሰው
ልጆች የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ፍላጎቶች
እንደምግብ ልብስና መጠለያ ካገኘን ይበቃናል
ይላል ፡፡ እግዚአብሔርን ለሚመስል ሰው ኑሮዬ
ይበቃኛል ማለት ትርፍ ያለው ነገር ነው፡፡
በኑሮ ከማማረርና ከማጉረምረም ይልቅ እርሱ
በሰጠኝ ኑሮዬ ረክቻለሁ ማለት እግዚአብሔር
የሚፈልግበትን ሕይወት የሚኖር ሰው ምሳሌ
ነው፡፡ የምበላው እንጀራ፣ የማገኘው ደመወዝ፣
የማርፍበት ቤት በቂዬ ስለሆነ እግዚአብሔር
ይመስገን ማለት ስንችል ረክተናል ማለት ነው፡፡
“ያላችሁ
ይብቃችሁ” ባላችሁ ርኩ፡፡ በተሰጣችሁ ደስ
ይበላችሁ፡፡ ከበቂ በላይ ኑሮ እየኖረ
እግዚአብሔርን ማመስገን አቅቶት የሚያጉረመርም
ሰው በቀን አንዴ መብላት የተሳነውንና የደስታ
ሕይወት የሚመራውን ቢያይ ራሱን ሊታዝብ
እንደሚችል አስባለሁ፡፡ ከዚያ ባለፈ ግን
የረካ ሰው ብዙ ኖረውም ጥቂት የረካ ነው፡፡
ያልረካ ሰው ግን የቱንም ያህል ቢያገኝ አይረካም
አይጠግብምም፡፡ አንድ ጊዜ አንዱ ሰው ጫማው
ስላረጀበት በእግዚአብሔር እያጉረመረመ
እንዲያውም ጸሎቱንም ሁሉ ትቶ ከቆየ በኃላ
ሌላ ሁለት እግሮች የሌሉት አንድ ሰው እግዚአብሔርን
ሲያመሰግንና ሲዘምር አገኘው፡፡ በዚህን ጊዜ
ወደ ልቡ ተመለሰና ይህ ሰው ጫማ የሚያደርግበት
እግር እንኳ ሳይኖረው እግዚአብሔርን ያመሰግናል፣
እኔ ግን ሁለት ጤናማ እግሮች ተሰጥቶኝ ጌታዬን
ማመስገን አቅቶኝ በማጉረምረም የተሞላሁ
በደለኛና ኃጢአተኛ ሰው ነኝ ብሎ ንስሐ ገባ
ዛሬ
ብዙዎች እግዚአብሔር በሰጠን ኑሮ ከማመስገን
ይልቅ እናጉረመርማለን፡፡ ካልሆነም ኑሮን
ለመገንባት የማይገባውን የገንዘብ ማግኛ
መንገድ እንጠቀማለን፡፡ እግዚአብሔር ግን
በቃሉ በኑሮአችሁ እርኩ፣ ያላችሁም ይብቃችሁ
ያለናል፡፡ ዕብ.13፡5
ይህ
ብቻ አይደለም እርሱ ዝም ብሎ በድፍኑ እርኩ
አይለንም፡፡ ነገር ግን ከቶ አልተዋችሁም
አልጥላችሁም የሚለንና እንደቃሉም የማይተወን
ጌታና አምላክ ነው፡፡
3.
መጠንቀቅ
(1ጢሞ
6፡9
– 11)
የገንዘብ
ጉዳይ ትልቅ ጥንቃቄ የሚጠይቅ እንደሆነ
በተደጋጋሚ ተመልክተናል፡፡ ለዚህም ሐዋሪያው
ጳውሎስ የተለያዩ ምክንያቶች አሉት፡፡
ያለአግባብ ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ወድቀዋል፡፡
ውድቀቱም መንፈሳዊ ውድቀት ነው፡፡ በፈተናም
ወድቀዋል፡፡ ይህ ፈተና ደግሞ የገንዘብ ፍቅርን
ተከትሎ የሚመጣ ፈተና ነው፡፡ የአወዳደቁንም
አሳዛኝ ሁኔታ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡፡
በጥፋት፣በሚያፈርስ፣ በሚጎዳ፣ በሚያሰምጥ
በብዙ ምኞት ብሎ ይነግረናል፡፡ በመቀጠልም
ደግሞ በወጥመድ ወድቀዋል ይላል፡፡ ወጥመድ
ሊላቀቁት የማይችሉበት ትልቅ የከፋ እሥራት
ነው፡፡ ወጥመድ አኗኗርንም መንፈሳዊ አካሄድንም
የሚገታ ነው፡፡ በቀላሉ ሊያዙ የማይችሉትን
እንደነወፍ ሚዳቋና እንደነብር የመሳሰሉትን
ፈጣን እንስሳትን ለመያዝ ወጥመድ ይዘጋጃል፡፡
እንደዚሁም ሁሉ አንድ ጠንካራና መንፈሳዊ
ሩጫውን በትጋትና በታማኝነት እየሮጠ ያለውን
አማኝ ወደ ኃላ ለማስቀረት የሚችል ወጥመድ
ቢኖር ገንዘብ ነው፡፡ እኛ ባለንበት ዘመን
በትልቅ የአገልግሎት ሥፍራ ላይ ያሉ ሰዎች
ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ምስክርነታቸው
የተበላሸበት ብዙ ታሪክ ሊኖር ይችላል፡፡
እነጳውሎስ በነበሩበት ዘመን ይህ ዓይነቱ
ጉዳይ በግልፅ የሚታይ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር
ፈቃድ ላይ ያልተመሠረተ የገንዘብ ፍቅር ወጥመድ
ይሆናል ማለት ነው፡፡
የዓለም
ተቃውሞ፣ስደት፣መከራ፣ረሀብ፣በክርስቶስ
ምክንያት የሚደርስ ማንኛውም ነቀፋና ስድብ
ያላሸነፋቸውን ጀግናዎችን የገንዘብ ወጥመድ
ጥሎአቸዋል፡፡ ኢየሱስ ስለአራቱ የዘር ምሳሌዎች
ባስተማረበት ወቅት አንድ በእሾህ መካከል
ስለወደቀች ዘር ሲተረጉም እንዲህ አለ፡፡
ቃሉን የሚሰማ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሀብትና
የባለጠግነት መታለል የሚያንቀው ሕይወት
እንደሆነ አስተማረ፡፡ (ማቴ.13፡22-23)
ስለዚህ
መንፈሳዊ ሕይወታችን እንዳይታነቅ ፍሬም
የማያፈራ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባናል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ከመጎምጀት ተጠበቁ
ይለናል፡፡ “የሰው ሕይወቱ በገንዘቡ ብዛት
አይደለምና ከመጎምጀት ተጠበቁ፡፡ሉቃስ
12፡6
ጳውሎስ
በዚህ ሥፍራ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ
ሥር ነው ብሎ ያስተምራል፡፡ ነገሩ ያለው
ከገንዘቡ ሳይሆን ገንዘብን ያለአግባብ ከመውደድ
ጋር ነው፡፡ ከፍ ብሎ እንደተመለከትነው ግን
ገንዘብ መገልገያ ስለሆነ ያስፈልገናል፡፡
ከልክ ባለፈ የገዘንብ ፍቅር ለተለከፈ ሰው
ግን ችግር ሊፈጥርበት እንደሚችል ለማሳየት
ነው፡፡
4. ማካፈል
(1ጢሞ.6፡18-19፣ዕብ.13፡16፣13፡3
)
እግዚአብሔር
ለሌሎች በጎነትን እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡
ቃሉ ስለማካፈል ልዩ ልዩ አገላለፆችን
ይጠቀምበታል፡፡ በሚመጣውም ዘመን መልካም
መሠረት እንዲኖረን ከገንዘብ ይልቅ በመልካም
ነገር ባለጠጋዎች እንድንሆን ያበረታታናል፡፡
ምክንያቱም የዚህ ዓለም ብልፅግና የሚጠፋ
ስለሆነ ነው፡፡ ሰው ያለውን ገንዘብ ብቻውን
በልቶ አይጨርስም፡፡ ካካፈለ ግን በእግዚአብሔር
ዘንድ መዝገብን ይሰበስባል፡፡ ወንድሙ
የሚቀምሰውን አጥቶና በጉስቁልና እየተገረፈ
ሲንደፋደፍ እያየ ገንዘብን ጨብጦ ይዞ አይዞህ
ጌታ ይረዳሃል ከማለት ጥቂትም ቢሆን የማካፈል
ልምድ ሊኖር ይገባል፡፡ የወንድማቸውን ርዳታ
የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፡፡ እነዚህን በሁለት
ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ እነርሱም ፦
አንደኛ፦
የሚረዱ ሲሆኑ የተራቡ፣የታመሙ፣መበለቶች፣እሥረኞች፣ወላጅ
አልባ ሕፃናት ዕብ.13፡
3፣16፣ያዕቆብ
1፡
26-
27 እውነተኛ
አምልኮም ይህ ነው፡፡
ሁለተኛ፦
የምናካፍላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ
እንግዶች፣አገልጋዮች፣ለቤተክርስትያን
የበጎ ሥራ ወዘተ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ
እግዚአብሔር ባበለፀገን መጠን ለእነዚህ
እጆቻችንን መዘርጋት ተገቢ ነው፡፡ ይህ
የእውነተኛ አገልጋየነትና የመንፈሳዊ ሕይወት
አኗኗር ነፀበራቅ ነው፡፡
5. በፅድቅ
ማውጣት
ከፍ
ብሎ እንደተመለከትነው ገንዘብ በፅድቅ ሊገባ
ያስፈልጋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በፅድቅም
ሊወጣ ይገባል፡፡ ክርስትያን የእግዚአብሔር
ባለአደራ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡
ነቢዩ ሐጌ እንደተናገረው ምጣነ ሀብት ሁሉ
የእግዚአብሔር ነው እንጂ የሰው አይደለም፡፡
ያለንን ገንዘብ ያገኘነው በእርሱ ፈቃድ ነው፡
በእርሱ ርዳታ ላይ ተመስርተን ባለጠጋዎች
ልንሆን ችለናልና ገንዘብን ስናስተዳድም
በእርሱ ፈቃድ ላይ ተመስርተን እንድናስተዳድረው
ይገባናል፡፡ ስለጉቦ የተወያየነውን ሀሳብ
እንደገና መመልከቱ ጥሩ ነው፡፡ ገንዘብን
ለርኩስ ዓላማ ማዋል አይገባም፡፡ ለጥፋት
ተልዕኮ ማስፈፀሚያ፣ ለመጠጥ፣ ለጉቦ፣የሚያወጣ
ሰው ከእግዚአብሔር ፅድቅ ለራቀ ዓላማ እያዋለው
ነው፡፡ ግን አሥራቱን ፣መባውን ፣ልዩ ልዩ
የፍቅር ስጦታዎችን ለሚመለከት ጉዳዮች የሚየወጣ
ሲሆን በጽድቅ ወጣ የምንለው ይህንን ነው፡፡
ክርስትያን ገንዘቡን አካሉንም ሆነ ሌላ
ባልንጀራውን ለሚጎዳ ጉዳይ ማፍሰስ የለበትም፡፡
እንደአማኝ ግን ጌታ የሰጠንን ገንዘብ ለሚጠቅም
ጉዳይ ማዋላችንን በእርግጠኝነት የመናገር
አቅማችንን ልናጠናክር ይገባናል፡፡ የክርስትያን
አኗኗር በገንዘብ አጠቃቀሙ አንፃር ሲመዘን
ምን ይመስላል?
ደመወዙንስ
ወስዶ እቤቱ ሳያደርስ በመጠጥ ቤት ፈጅቶ ባዶ
እጁን ወደ ቤቱ እንደሚመጣ፣ ቤተሰቡን
እንደሚያስርብና እንደሚያጎሳቁል እንደ
ዓለማዊ ሰው ገንዘባችንን አላስፈላጊ በሆኑ
ቦታዎች ላይ እናውለውን?
ወይስ
ገንዘቡ የእግዚአብሔር ሆኖ ሳለ በአደራ
እንደተሰጠን ዘንግተን ለጋለሞታዎች እንስጥን?
ወይስ
በዜማውያንና በሴትኛ አዳሪዎች ደጅ እንበትንን?
እንደክርስትያን
እንነጋገር ካልን ይህ በፍፁም ሊሆን አይገባም፡፡
ተገቢዉን መንገድ ትተን በአቋራጭ ለመክበር
ስንል ይህንን ክቡር የእግዚአብሔርን ስጦታ
ለጉቦ በላተኞች እንደጉምን?
ይህ
እንዲሆን የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ
አይደለም፡፡ ስለዚህ ገንዘብ በፅድቅ መውጣት
እንዳለበት ልብ ይሏል፡፡ በጽድቅ እናውጣ
ስንል ምን ማለታችን ነው?
የሂሳብ
ሰው ባልሆንም ትክክለኛና አግባብነት ያለው
የገንዘብ አወጣጥ እንደሚከተለው መሆን
እንዳለበት አምናለሁ፡፡
- የመጀመሪያው ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ መስጠት ነው፡፡ ይህ አሥራትን ፣በኩራትን፣መባንና ሌሎች የፍቅር ስጦታዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡
- ለቤት ወጭ ማውጣት፡፡ ይህ ደግሞ የቤት ኪራይን ፣ቀለብን፣የህክምና ወጪ፣ለተቀማጭ፣ለቤተሰብ መዝናኛ፣ለመብራት ለውሃና ለልዩ ልዩ ጉዳዮች የሚሆን ነው፡፡
- ለመንግሥት ጉዳዮች የሚወጣ ወጭ ነው፡፡ እንዲህ ደግሞ ለግብር፣ለመዋጮ፣ለአገር ግንባታ የሚውል ነው፡፡
- ለማህበራዊ ጉዳዮች የሚወጣ ወጭ፣ ዕድርን፣ዕቁብን፣እገዛን፣ለጉርብትናና ለመሳሰሉት የሚወጡ ናቸው፡፡
- ዕዳ ያለበት ሰው ምስክርነቱ እንዳይበላሽበት በወቅቱ መክፈል አለበት፡፡
- እንደማንኛውም ሰው ክርስትያንም ገንዘብን በዓላማ የመቆጠብ ልማድ ማዳበር ይኖርበታል፡፡
እንዚህንና
የሚመስሉአቸውን ጉዳዮች ላማከናወንና ለማስፈፀም
የሚወጣ ወጪ ኃጢአት የሌለበት ነው፡፡
6. አለመታበይ
(ኤር.9፡23-24፣1ጢሞ.6፡17-19)
በእግዚአብሔር
እንጂ በሀብቱ የሚመካ እርሱ ሞኝ ነው፡፡
በገንዘብ የተባረኩ ሰዎች ባለጠጎች ስለሆኑ
በብልጠግናቸው ምክንያት የትዕቢትን ነገር
እንዳያስቡ መጽሐፍ ቅዱስ ይመክራል፡፡
በእግዚአብሔር መመካት ከምንም በላይ ያዋጣል፡፡
ክብርና ሀብት ውበትና ደምግባት ሁሉ ቀሪና
አላፊ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር
ዘላለማዊና የማያልፍ በመሆኑ ልዩነቱን
የሚያመጣው ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን
ደስ እንዲለን ሁሉን አትረፍርፎ የሚሰጥ፣ሕያው
የሆነ አምላክ ነው፡፡ ገንዘብ ግን ከእግዚአብሔር
የሚሰጥ ስጦታ ብቻ እንጂ እስከወዲያኛው
የምንመካበት አይደለም፡፡ የተራቡ የሚጠግቡበት
ዘመን ምግብ የተረፋቸውም እንጀራ የሚናፍቃቸው
ቀን ሊመጣ ይችላል፡፡ ስለዚህ አማኞች ከመመካትና
በገንዘብ ከመታመን ይልቅ እግዚአብሔር
በባረካቸው ቁጥር ራሳቸውን በሕዝቡና በእግዚአብሔር
ፊት ትሁት ሊያደርጉ ያገባቸዋል፡፡ ብዙ ገንዘብ
ስላላቸው ብቻ እንዲደመጡ የሚፈልጉ ሰዎች
አሉ፡፡ ለቤተክርስትያንም ብዙ ስጦታዎችን
ስላበረከቱ እኔ የምለውን ምንም ይሁን ምን
ተቀበሉ እያሉ እግዚአብሔር ከሾማቸው መሪዎችም
አልፈው ወሳኝ ሊሆኑ የሚቃጣቸው ሰዎች አሉ፡፡
የእግዚአብሔር ቤት አገልጋዮች እነርሱ በሚሰጡት
ገንዘብ እንደሚኖሩ እየተሰማቸው አንተ እኮ
ደመወዝ የምትበላው እኔ በምሰጠው አስራትና
መባ እንዲሁም ስጦታ ነው ብለው መፎከር
የሚከጅላቸው ሰዎች አይታጡም፡፡ ይህ እንግዲህ
ለክርስትና አኗኗር ጠንቅ ነው፡፡ በእግዚአብሔር
መመካት ለምን እንደሆነ ከ1ኛ
ጢሞቴዎስ 6፡15-17
እንይ፡፡
- እርሱ ( እግዚአብሔር ) አትረፍርፎ የሚሰጥ አምላክ ስለሆነ፡፡ቁ.17 ስጦታው ከእጅ ወደ አፍ ብቻ ሳይሆን የተትረፈረፈና ሞልቶ የሚፈስ ፣ከተቀባዩም አልፎ ለሌላውም የሚበቃ ነው፡፡ እርሱ የማያልቅበት ምንጩም የማይደርቅ ነው፡፡
- የእግዚአብሔር ስጦታ አስደሳች ነው፡፡ቁ 17 እግዚአብሔር የሚሰጠን የእኛን ደስታ ለማብዛት ነው፡፡ እንግዲህ ልዩነቱ ያለው እዚህጋ ነው፡፡ በውንብድናና በውስልትና የሚግበሰበስ ገንዘብ ደስታንና እርካታን አይሰጥም፡፡ ደስታን ተድላንና ሐሴትን የሚያመጣው ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ንፁህ ስጦታና ልግስና ነው፡፡
- ገንዘብ አላፊ ነው፡፡ቁ 18 ቃሉ በሚያልፍ ባለጠግነት ተስፋ አታድርጉ ይለናል፡፡ ሕያውና ለዘላለም የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ አማኞች በሰጪው እንጂ በስጦታው ተስፋ ማድረግና መመካት ሞኝነት መሆኑን አንዘንጋ፡፡
ማጠቃለያ፡
እንግዲህ ከላይ ስለገንዘብ የተመለከትናቸው
ሀሳቦች በጥልቀትና በጥንቃቄ ልናስብባቸው
የሚገቡ ናቸው፡፡ አልፎም እንደክርስትያንም
ተግባራዊ ርምጃ መውሰድ በሚኖርብን ጉዳዮች
ባለማመንታት ልንንቀሳቀስ ይገባናል፡፡
የገንዘብ ጉዳይ እንዲያስመሰግነን እንጂ
እንዲያስወቅሰን በእኛ ላይ የተጠራውን ቅዱሱን
የጌታን ስም ሊያስድብብን አይገባም፡፡
እግዚአብሔርም በነገር ሁሉ ይርዳን፡፡
ልጨምርበት የምፈልገው ነጥብ ደግሞ እኔ ጥቂቱን
ነገር ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡ ከዚህ በላይ
አስፍተው ሊገልፁ የሚችሉ በእግዚአብሔር ቃል
እውቀትና በምድራዊም ትምህርት ጌታ የባረካቸው
ብዙ የጌታዬ ልጆች እንዳሉ አምናለሁ፡፡ ለሕዝቡ
ጥቅምና ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆን እኔ
ያላየሁትን እነርሱ ግን የሚያዩትን እንዲጨምሩበትና
እንድንታነፅበት ይሁን እላለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment