Wednesday, December 25, 2013

ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ( 1ኛቆሮ. 12 ፡31)፡ ክፍል አንድ

ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ( 1ኛቆሮ. 12 31)
A more excellent way
ክፍል አንድ
በአንድ ወቅት አንድ የታወቀ ሀብታም ሰው ለሠራተኞቹ ስጦታ ሊሰጥ አሰበና እንደፍላጎታቸውና እንደ ምርጫ ችሎታቸው መሠረት እንዲወስዱ የተለያዩ ማዕድናትን በፊታቸው አቀረበላቸው። ይህ ሰው ፊታቸው ያቀረበላቸው አራት ማዕድናት መዳብ፣ብር፣ወርቅና አልማዝ ሲሆኑ እነዚህንም በተርታ አስቀመጠላቸው። ይህንን ሲያደርግ ሰዎቹ ደስ ያላችውን መርጠው እንዲወስዱ በመፍቀድ ነው። ሀብታሙ ሰው ለሠራተኞቹ ካቀረበላቸው ማዕድናት ውስጥ የማይፈለግ አንድም የለም። ምናልባት ሰጦታው የቀረበላቸው ሰዎች በርከት ያለውንና በዓይናቸው የሞላላቸው መዳብ ቢሆን መዳብን ደስ እያላቸው ሊመርጡ ይችሉ ይሆናል። የሚገርመው ግን አብዛኛዎቹ መዳብን ሲምርጡ ጥቂቶቹ ደግሞ ወርቅ መረጡና አልማዝ የተባለውን ማዕድን ግን ማንም ሳይመርጠው ቀረ። የስጦታው ሰጪ በሁኔታው በጣም ተገረመና ያ የሆነበትን ምክንያት ሲያጠና ሰዎቹ አልማዝ የሚባል ምን እንደሆነ ስለማያውቁትና ማዕድኑ በመጠኑ ከሌሎች ማዕድናት የሚያንስ በመሆኑ ብዙም ዋጋ ላይኖረው ይችላል በሚል ያደረጉት እንደሆነ ተረዳ። ይሁን እንጂ አልማዝ ከሁሉም ማዕድናት የበለጠ ነበር። የስጦታው ተቀባዮቹ የተሳሳቱት ምናልባት በሌሎች ማዕድናት ብልጭልጭነት ተማርከውና ትታልለው እንጂ ማዕድናቱ በሚሰጡት ጥቅምና በጥራት ብልጫቸው ላይ ብዙም ስላላተኮሩበት ይሆናል።
እንደዚሁም ሁሉ በመንፈሳዊ ሕይወታችንም እጅግ የሚበልጠውን መንገድ ሳናውቀው ቀርተን ሳንጠቀምበት የምንቀርባቸው ዘመናትና ወራት ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ከጌታ እጅ ከተቀበልናቸው ስጦታዎች አያስፈልጉንም የምንላቸው በጭራሽ የሉንም ሊኖሩም አይችሉም። ይሁን እንጂ በሕይወታችን እግዚአብሔር ከፍ ያለውን ቦታ እንድንሰጥ የሚፈልግብን ብዙ ቁም ነገሮች አሉ።
ለምሳሌ ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞችን ስለ ጸጋ ስጦታ ሲያስተምራቸው ሁሉንም በዝርዝር አስቀምጦ ሲያበቃ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ እንዳለ ደግሞ ያሳስባቸዋል። አባባሉንም ስንመለክተው ሁሉም የጸጋ ስጦታዎች በጣም የሚያስፈልጉ መሆናችው በቃሉ ውስጥ በማያሻማ ሁኔታ ተቀምጠዋል። እነዚያ የጸጋ ሰጦታዎች እጅግ ሲበዙ ለቤተክርስቲያን (ለአማኞች) መንፈሳዊ ሕይወት ግንባታ በጣም አስፈላጊዎች እንደሆኑ በተለያዩ የመልእክት ክፍሎች መመልከት እንችላለን።
ጳውሎስ ይህንን መልእክት የሚጽፍላቸው የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞች በተለያዩ የመንፈሳዊ ሕይወት ችግር ውስጥ ነበሩ ሲሆን እግዚአብሔር ግን በካከላቸው የተለያዩ የጸጋ ስጦታዎችን አፍስሶ ነበር። የተሰጣቸው የጸጋ ስጦታ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው ዕድገትና ግንባታ ሊሆን ሲገባው በመካከላቸው መለያየትና መከፋፈል ይታይባቸው ነበር። ጳውሎስ የጻፈውን የ1ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ስናጠናው ቀጥሎ የተዘረዘርሩ ችግሮች ተስተውለዋል፡

  • ከምዕራፍ 1-4 በመካክላችው ስለነበረው መከፋፈል
  • ከምዕራፍ 5-6 ክርስቲያን በሐጢአት ላይ ምንም ርምጃ ያለ መውሰድ ችግር
  • ምዕራፍ 7 በጋብቻ ምክንያት አማኞች የሚያነሱት መሠረታዊ ጥያቄዎች
  • ከምዕራፍ 8-10 ለጣዖት ስለተሰዋው ሥጋና አማኞች የሚያነሱት ጥያቄ
  • ከምዕራፍ 11-14 አማኞች በአምልኮ ጊዜ ያሳዪት ስህተት ለምሳሌ በጌታ ራት ጊዜ፣በጸሎት ጊዜና በአምልኮ ጊዜ ማለትም የጸጋ ስጦታዎቻውን በአግባብ ባለመጠቀማቸው በአማኞች መካመታነጽ ይልቅ መለያየትና መከፋፈል በርክ ነበር።
    ይህ ሁሉ በሚሆንበት ወቅት የጸጋ ስጦታ በመካከላቸው ይገለጥ ነበር። ጳውሎስ በምዕራፍ 12 እና በምዕራፍ 14 ላይ ለእነርሱ ስለ ተሰጣቸው የጸጋ ስጦታና ስለ አጠቃቀሙ በግልጽ ያስተምራቸው ነበር። ምዕራፍ 13 ግን በሁለቱ ምዕራፎች መካል ሌላ በጣም አስፈላጊ የሆነ ትምህርት ይዞ የገባ ምዕራፍ ነው። ይህ የሆነው ደግሞ በአጋጣሚ ሳይሆን በጌታ እቅድ ነው።
    ጳውሎስ በምዕራፍ 12 31 ላይ “የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ” ብሎ ይመክራቸዋል። ጋ ስጦታዎች ይበላለጣሉ ወይንም ይተናነሳሉ ማለቱ ግን አይደለም። ነገር ግን ለአማኞች መታነጽን ከማስገኘት አንጻር አብልጠን መሻት ያለብን ስጦታዎች መኖራቸው ደግሞ የሚካድ አይደለም። ለምሳሌ ትንቢትና ልሳን ሁለቱም የጸጋ ስጦታ ሲሆኑ
    ሐዋሪያው በጉባኤ ከሚነገረው ልሳን ይልቅ ትንቢት እንደሚበልጥ በም.14 ላይ በግልጽ ያስረዳል። ምክንያቱም በልሳን የሚናገር ራሱን እንጂ ማህበሩን አያንጽምና። ስዚህ ነው የሚበልጠውን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ የሚለው።
    ዚህመም በተጨማሪ ጳውሎስ “ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ” አሳያችኃለሁ ይላል። የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን አማኞች በመንፈሳዊ ስጦታዎቻቸው ለማገልገል ይጥራሉ እንጂ ይህንን ከሁሉ የሚልጠውን መንገድ አላወቁትም አልፈጉትም
    በዛሬው ዘመን ያለንም አማኞችና አገልጋዮች ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉብን ምንም ጥርጥር የለውም። እኛ የተለያዩ የጸጋ ስጦታዎች አገልግሎት በስፋት የሚሰጥበት ግን ከዚህ ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ብዙዎች ቸል ባሉበት ዘመን ላይ እንገኛለን።
    ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ምንድነው? የቱስ ነው? ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ጌታችንና መድኃኒታችንን ኢየሱስን ከሰማይ ክብሩን ትቶ ወደ ምድር የመጣበት ምክንያት ነው። ከሁ የሚበልጠው መንገድ አብ አንዲያ ልጁ ሳይራራ ለሰዎች ኃጢአት አሳልፎ እንዲሰጥ ያስገደደው ነው። ሐሪያው ጳውሎስም ይህ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ነው ይለናል። ሁሉ የሚበልጥ መንገድ ሲል የተለየ ትርጉም ለመስጠት ፈልጎ ነው ምክንያቱም እርሱ ዘመን “መንገድ” የሚለው ቃል ከክርስትና ጋር የተያያዘ ሁኔታ ላለ ነው። የጌታን መንገድ የሚከተሉ ሰዎች በሐዋሪያት ዘመን የመንገድ ሰዎች ተብለው ይጠሩ ነበር (የሐዋ. 92)፡፡ እንዲሁም ክርስትና ራሱ መንገድ ተብሎ ይጠራ ነበር (ሐዋ. 16171825199-23224241422)፡፡ ይህም የተባለው "ኢየሱስ እኔ መንገድ ነኝ" ብሎ በተናገረው መሠረት ሊሆን ይችላል (ዮሐ 146)፡፡ ክርስትና ጉዞ ነው፡፡ ክርስትና ሩጫ ነው ፡፡ ይህም በመሆኑ መንገድ አመልካች የሩጫም መሪ አለው (ዕብ. 121-21ኛ ቆሮ. 9) ይህ መንገድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተራመደበት መንገድ ሲሆን እኛም ደግሞ በዚሁ መንገድ እንድንራመድበት እግዚዚብሔር ይፈልጋል። ከዚህ መንገድ መጣት የክርስትና ሕይወታችንን ርጉም የሌለው ያደርገዋል። ዛሬ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ የሚታየው መተራምስ ይህንን ከሁሉ የሚበልጠውን መንገድ አለማወቀና አውቀውትም ቸል ከማለት የመጣ እንደሆነ ግልጽ ነው
    ሐዋርያው ጳውሎስ በ1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 13 ላይ መጀመሪያዎቹ 13 ቁጥሮች የሚናገረው ከሁሉ ስለሚበልጠው መንገድ ነው።ታዲያ ይህ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ምንድነው? የይይ ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ፍቅር ስለሆኑ የክፍሉ አሳብ በግልጽ ያሳየናል፡፡
    ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ፍቅር ነው( 1ኛ ቆሮንቶስ 131- 10). ስለዚህ በዚህ ትምህርታችን ከሁሉ የሚበልጥ ፍቅር እንመለከታለን፡፡ ሰዎች ሕይወት ተሞክሮ ውስጥ ወደ ምንፈልገው የተለያዩ የፍቅር ዓይነቶች እንመልከት፡፡
  • የውሸት ፍቅር pseudo -love ፡፡ ይህ የውሸት ወይም እውነት ያልሆነ ፍቅር ማለታችን ነው፡፡ ፍቅርን የውሸት ማድረግ እጅግ በጣም አሳዛኝ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ እንደናየው የሰዎችን ትኩረት ከሚስቡ ነገሮች መካከል ዋናዎቹ የማሰመሰል ሥራዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ አንድን ነገር መደበኛ በሆነ መንገድ ለሰው ከማስተማር ይልቅ በድራማ መልክ ቢያደርጉት ቁጥር ሥፍር የሌለው ሕዝብ ተደንቆ ሊማር ይችላል፡፡ እውነተኛ ታሪክ ከሚያነቡት ባልተናነሰ የልበ ወለድ ጽሁፎችን በማንበብ የሚደሰቱ ሰዎች በርካታ ናቸው፡፡ ከእዉነተኛ ነገር ይልቅ የማስመሰል ሥራዎች ብዙዎችን እያስደነቁ ባሉበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡ ሰይጣንና ሥጋም ተባብረው ውሸት ነገር እያመረቱ ያቀርቡልናል፡፡ በዚህም ጊዜ ፍቅርም የውሸት በሆነ መንገድ የሚገለጥባቸውና ብዙዎችን የሚማርክበት መንገድ ብዙ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን ይለናል( ሮሜ 129) እውነትነት የሌለው ፍቅር አደጋ ያለበት ነው፡፡ ለምሳሌ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያት ከሆኑት አንዱ አሰቆሮቱ ይሁዳ ነበረ፡፡ ይህ ሰው ኢየሱስን አቅፎ የሳመበት ታሪክ ያለበትን ሥፍራ በቃሉ እናነባለን፡፡ ይሁዳ ኢየሱስን ሲስመው ያየ ሰው በፍቅር ተንሰፍስፎ ይህንን የሚያያደርገው ሊመስለው ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ፍቅራቸውን የሚገጹልፁት ፈግታ በማሳየት፣ በማቀፍ እና በመሳምም ጭምር ስለሆነ ነው፡፡ አስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን እንደዛው አቅፎ ይሳመው እንጂ እርሱ በፍጹም ውሸታም ነበረ፡፡ እንዲያውም ጻድቁን የእግዚብሔርን ልጅ በ30 ብር በመሸጥ ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ እየሰጠ ነበር የሚስመው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ የውሸት ፍቅር የሚባለው፡፡ በዘመናችንም ቢሆን እንደዚህም ያሉ እግዚአብሔር አምላክ ለሰዎች ልጆች ከሰጠው እና እኛም እንድንተገብረው የሚያስፈልገን ፍቅር የተባለን ትልቅ ጉዳይ ሰዎች የሚያሳዩት የውሸት በሆነ መንገድ ሆኖ ስናየው እጅግ ያሳዝነናል፡፡ ምናልባት ወንድማችንን ለሞት አሳልፈን እየሰጠን አወድሃለሁ እያልን አቅፈነው እንስመው ይሆን፡፡ ወይም ሊፈታ በማይችል መልኩ ከበስተጀርባው ገመድ እየተበተብንበት ከፊቱ በኩል አልፈን እወድሃለሁ እያልን አገላብጠን እንስመው ይሆንን/ የእግዚአብሔር ቃል ግን ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን ይለናል፡፡
  • አሔብ/Aheb/: ( የብልጫ ፍቅር)፡ ይህ ከአንዱ ሌላውን አሰበልጠን ወይንም አንዱን በተለየ መልክ የምንወደበት ፍቅር ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ እግዚአብሔር የሰጠኝን ልጆቼን እወዳቸዋለሁ፣ ባለቤቴን ግን በጣም እወዳታለሁ፡፡ ይህንን ማንም ሊቃወመኝ አይችልም፡፡ ልጆቼም ቢሆኑ እንዴት እናታችንን ከእኛ አስበልጠህ ትወዳታለህ ሊሉኝ አይገባቸውም፡፡ አንድ ሰው ወንድሙን፣ እህቱን ፣ እናትና አባቱን እንደሚወደው በጣም የታወቀ ነገር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሚሰቱን ወይም ባልዋን ከእነዚያ ሁሉ አሰበልጦ መውደድ ይኖርበታል/ ባታል፡፡ አሔብ የተሰኘው ፍቅር ከዚህ አንጻር በጣም ጤናማ ሲሆን አደገኛ የሚሆንበት መንገድም ደግሞ አለ፡፡ ያውም ንብረትንና ንዋይን ከትዳር ጉዋደኞቻችን ወይም ከዘመዶቻችን አስበልጠን የምንወድ ከሆነ አደገኘ ነው ማለት ነው፡፡ በባሎቻችንን ወይንም ሚስቶቻችንን ከሞተልን ጌታ አስበልጠን የምንወደው ከሆነ አጅግ በጣም አጥፊና ጣዖት ይሆንብናል ማለት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ማንም አባቱን ወይም እናቱን ወይም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ከእኔ አብልጦ የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም አለ፡፡ የብልጫ ፍቅር ጥቅምም ጉዳትም እንዳለው ከዚህ እንማራለን፡፡ ልብ ብለን ያየን እንደሆነ ከክርስቶስ የተቀበልነው ፍቅር በቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም ተበርዞ እናየዋለን፡፡ ለምሳሌ የመዘምራን ቡድን እርስ በርሳቸው ያለው ፍቅር በጣም የሚስብና የሚያስቀና ነው፡፡ ይሁን እንጂ የመዘምራን ቡድኑ አባላት ፍቅር ከዚያው ቡድን አልፎ መሄድ የማይችል ነው፡፡ እዚያው እርስ በርሳቸው እንጂ ያንኑን ፍቅር ለሌላው ለማሳየት ብዙም የማይፈልጉባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ የጸሎት አገልግሎት ክፍሎች ከራሳቸው ሰዎች እንጂ ሌላውን በዚያው ሁኔታ መቅረብ ይከብዳቸዋል፡፡ ይህ ፍቅር ነው ግን ክርስቶስ ያስተማረን አይነት ፍቅር አይደለም፡፡ አሁን የምናየው በአብዛኛው ንጹህ የሆነ የጌታ የመስቀሉ ፍቅር ሳይሆን ሰዎች በራሳቸው መንገድ ለማሻሻል እየሞከሩት ለራሳቸውመም በሚመች መንገድ የሚተገብሩት/ Modified / የሆነ ዓይነት ፍቅር ነው፡፡ ዋንኛው/Original / የጌታ ፍቅር ግን እንደዚህ አልነበረም፣ ይልቁንም ሁሉን የሚወድድ ፍቅር ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔርም እኛን ሁላችንን ነው የወደደው እንጂ ከእኛ መካካል የሆነ ሰውን ወደ ጎን ትቶ አልወድህም የሚለው አንድም የለም፡፡ በእርሱ የሚያምን ሁሉ እንዲድን ዓለምን ሁሉ ነው የወደደው፡፡
    አብያተ ክርሰቲያናትም የተቸገርንበት ትልቁ ፈተና ይህ ነው፡፡ በቤተ እምነት ወገንተኝነት ሁሉም ሰው ሲታይ የፍቅር ልዩነት ሲያደርግ ይስተዋላል፡፡ እኔ የዚህ ቤተክርሰቲያን አባል ነኝ ቤተክርሰቲያኔን እወዳታለሁ የሚሉ ብዙ ሰዎችን እንሰማለን፡፡ ይህ ሊበረታታ የሚገባ ነው፡፡ እያንዳንዱ አማኝ የራሱን ቤተክርሰቲያን መውደድ ይኖርበታል፡፡ ግን ታዲያ የሌላውን በቤተ እምነት የሚኮንን ከሆነ አልፎም የሚጠላ ከሆነ የዚህ ሰው ፈቅር ጤናማ ነው ለማለት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ያለን ከሆነ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ በኩል የገለጠልን የመስቀሉ ፍቅር አልገባንም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ወደ እውነተኛው የክርሰቶስ የቄራኒዮ ፍቅር መመለስ ይኖርብናል፡፡
  • ሐባብ/Habab/: በጣም ቅርበትንና የልብ ወዳጅነትን የሚገልጡበት ፍቅር ነው፡፡ ይህ ወደ ደረት የመጠጋትን ሁኔታ የሚያሳይ ሲሆን Bosom friend/ ከተሰኘው የእንግሊዚኛ ቃል ጋር የተቀራረበ ነው፡፡ ዮናታንና ዳዊት ሁለቱ በጣም የሚቀራረቡ ወዳጆች ነበሩ ምክንያቱም የዮናታን ነፍስ በዳዊት ፍቅር የታሰረች ነበረችና፡፡ ይህ ከአንድ ሰው ጋር በሆነ ምክንያት በጣም መዋደድን የሚያመለክት ዓይነት ፍቅር ነው፡፡ በመሠረቱ ይህም ቢሆን ምንም ችግር አይታይበትም ምክንያቱም ማንም ሰው ከወገኑ ጋር መዋደድ ይጠቅማል እንጂ ማንንም የሚጎዳ አይደለም፡፡ ጉዳትና ኃጢአት የሚኖረው በመዋደድ ስም ሌላውን የሚጎዱና የሚያገልሉ ከሆነ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ሐባብ የተሰኘው ይህ ፍቅርም ቢሆን ሐዋሪያው ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ ብሎ የሚነግረንን ፍቅር አያሳይም፡፡
  • ኢሮስ /Eros/የጾታ ፍቅር፡፡ ይህንን በተለያየ መልኩ ማየት እንችላለን፡፡ አእምሮአቸው ወደ ጉርምስና የደረሱ ወጣቶች ለተቃራኒ ጾታ መሳሳብ መጋለጣቸው አይቀረ ጉደይ ነው፡፡ እወድሃሁ እወድሻለሁ እንዲባባሉ ይገደዳሉ፡፡ በዚህ ፍቅር ውስጥ አንድ የሩካቤ ሥጋ ፍላጎት የሚባል ድብቅ ኃይል መኖሩ የሚካድ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱን ፍቅር በተገቢው መንገድ መጠቀም ካልተቻለ ከፍተኛ ውድቀትን ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡ የሚፈልጉትን የሥጋ ግንኙነትን አግኝተው ሲያበቁ ከወደዱት መውደድ በበለጠ ጥል የሚጠላሉበት ሁኔታ ይከሰታል፡፡ ለእውነተኛ ጋብቻና ዘላቂነት ላለው የትዳር ትስስር ካልሆነ በእንዲህ ዓይነቱ መቀራረብ ምክንያት የወገኖች ልብ የሚሰብርበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ በበለፀጉት አገሮች የሚታየው ይህን የመሰለ ነገር ነው፡፡ ብዙዎች እወድሃለሁ እወድሻለሁ ሲባባሉ ለሚያይ ሰው እንዴት ዓይነት ጥልቅ ፍቅር ቢኖራቸው ነው እንደዚህ የሚሆኑት ያስብላል፡፡ አንዳንዶች የፍቅር ጉዋደኞቻቸውን በስማቸው እንክዋን ከሚጠሩ ሐኒ መባባል ይቀላቸዋል፡፡ ይህ እንግዲህ ማር ማለት ነው፡፡ በአገራችን አውድ እንጥራው ካልን ደግሞ የኔ ማር ማለታቸው ወይም ደግሞ ማሪዬ እንደ ማለት ነው፡፡ የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን እንደዚህ እንደእሳት የጋለ የሚያስመስሉት ፍቅር ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዳልነበረ ሲሆን ማየት ነው፡፡ ሐኒ ሲባባሉ የኖሩበትን ፍቅር ለማፍረስ ጊዜ አይፈጅባቸውም፡፡ ከዚያ ማይ ኤክስ ዋይፍ ወይም ኤክስ ሃስባንድ የሚለውን ስም ወዲያው ይለጥፉበታል፡፡ የልጆቼ እናት ወይም አባት ለማለትም አይፈልጉም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጾታዊ ፍቅርና ያስከተለውም አደጋ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጸፎአል፡፡ የንጉሥ ዳዊት ልጅ ከእህቱ ( ከወንድሙ ልጅ) ከትእማር በጾታዊ ፍቅር በመያዙ ለራሱም ለቤቱም ያሰከተለው መዘዝ ከፍተኛ መሆኑን በእግዚአብሔር ቃል እንመለከታለን( 2ሳሙኤል 13) አምኖን ትእማርን ከመውደዱ የተነሳ እንደ ሕመምተኛ ሆኖ ነበር፡፡ በቃሉ እንደምንመለከተው ከመተከዝም አልፎ የታመሙንም እናነባለን፡፡ እስከ ሕመም የሚያደርሰው ፍቅር ይዞት ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ፍቅር በእውነት ጤናማ ቢሆን ኖሮ ያሳምመው ነበር ወይ የሚል ጥየቄ ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ለምን ቢባል አንድ ወገን ብቻ የሚታመምበት ከሆነና ሌላይኛው ፈጽሞ ለጉዳዮ እንግዳ የሚሆንበት ከሆነ ይህ ፍቅር ሊዘልቅ አይችልም፡፡ አምኖን ትእማርን እርስዋ በማታውቀው መንገድ ወደዳትና ከዚያ ፍቅር የተነሳ እንደ ህመምተኛ ይክሳ እንጂ ትእማር በዚያው መንፈስ እርሱን ለመወውደድ ላለመውደድዋ እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ዛሬም በዘመናችን እገሌን ወደድኩት ወይም እገሊትን ወደድኩአትና ተቃጠልኩ አረርኩ የሚሉት ሰዎች የሚፈጥሩት ተመሳሳይ ስህተት ነው፡፡ አንድ ወገን ብቻ በፍቅር ተያዝኩ ብሎ ብቻውን ቢከንፍ ያ ዓይነት ፍቅር በተቃራኒው ወገንም ላይ የሚያስከትለው ፈጸሜ ጥፋት ነው የሚሆነው፡፡ በቃሉ እንደምንመለከተው አምኖን የብልሁን ሰው የኢዮናዳብን ምክር ተጠቅሞ ትእማርን ካስነወራት በኃላ ወዲያውኑ ፈጽሞ እንደጠላትና እንዲያውም አስቀድሞ ከወደዳት ውድ ይልቅ የጠላት ጥል እንደበለጠ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል(2ሳሙኤል 1315)፡፡ የአምኖን ፍቅር ዕድሜው በተወሰነች ደቂቃ ብቻ የታጠረች ነበረች፡፡ በከባድ የውስጥ ደዌ እንደታመመ ሰው እስክመነምን ድረስ የጎዳው ፍቅር እህቱን ካስነወራት በኃላ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ሊቀጥል አልቻለም፡፡ ትእማርን የጠላበት ጥላቻ ከማየሉ የተነሳ በአገልጋዮቹ አስገድዶ አስወጣትና በሩን ከኃላዋ እንዲዘጉባት አደረገ ምክንያቱም ተመልሳ እንዳትገባ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የአምኖን የፍቅሩ ጅማሬ የሚመስል ፍቅር በባልና በሚስት መካከል ሲሆን እጅግ ያማረ እጅግም የተቀደሰ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ባልና ሚስት አንዳቸው ለሌላው ያላቸውን ፍቅር በተራክቦ ቢገልጹት የተቀደሰና የተባረከ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሐዋሪያው ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ የሚለው ፍቅር እንደዚህ ዓይነቱም አይደለም፡፡
  • ፒሊዮ የቤተሰብ ፍቅር፡ ቤተሰብ ማለት አባት እናት ወንድም እህት ወዘተ ሲሆኑ በአንድ ቤት ውሰጥ የሚኖሩ ማለታችን ነው፡፡ አንዳንድ ወገኖች ፒሊዮ የተሰኘው ፍቅር የቤተሰብ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የምክንያት ወይም የእንካ በእንካ ፍቅርም እንደሆነ ያምኑበታል፡፡ እርግጥ ነው አባቴ ወይም ልጄ ስለሆነ እወደዋለሁ የማለት ግዴታ ይኖርብናል፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ለቤተሰባችን እንድናስብ ይመክረናል፡፡ ቤተሰባችንን ከጌታ አብልጠን መውደድ ነው የተከለከልነው እንጂ የወላጅነትንና የልጅነትን እንዲሁም ደግሞ ወንድምነትና የእህትነት ፍቅራችንን መግለጽ ተገቢ ነው፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዲወድዱአቸው በጣም ይመክራል( ኤፌሶን 5231ጴጥ 3) ባል ሚስቱን እንደራሱ አድርጎ አንዲወድድ የሚያስገድደው የጌታ ትዕዛዝ በሁሉም ዘንድ መከበር አለበት፡፡ ባልና ሚስት አንድ አካል ስለሆኑ ከቤተሰብ ሁሉ መካከል የእነርሱ ፍቅር የተለየ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ፍቅር ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ የሚለውን ፍቅር አይገልጸውም፡፡ ከሁሉ የሚበልጠው መንገድ ከዚህ ቀጥሎ ያለው የፍቅር ዓይነት ነው፡፡
  • አጋፔ ( አጋፔ) የተባለው ፍቅር ነው፡፡ አጋፔ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር ማለት ነው፡፡ ይህ የእዚአብሔር ፍቅር ከላይ ከተለከትናቸው ፍቅር ዓይነቶች ሁሉ የሚለይ ዓይነት ፍቅር ነው፡፡ ይህ ፍር በተለያዩ የጸጋ ስጦታዎች ከማገልል ይበልጣል፡፡ ጳውሎስ ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኃለሁ የሚለንም መንገድ ይህ ነው፡፡ ይሕ አጋ የተሰኘው የእዚአብሔር ፍቅር በመካላችን ማለትም በቤተክርስቲያን ይገለጥ ዘንድ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር ከሌች የፍቅር ዓይነቶየተለየ ሚያደርጉ ብዙ ባሕሪያቶች አሉ፡፡ እነዚህን በጥቂቱ መመልከት ይኖርብናል፡
  • የእግዚአብሔር ፍር ምንጩ ራሱ እግዚአብር ነው፡፡ እኛ የዚህ ፍቅር ምንጮች ልንሆን አንችልም፡፡
  • እግዚአብሔር ፍር የይወደደውን የሚወድድ ነው፡፡ ሮሜ 56-8
  • ምክንያተ አልባ ወይም በምንም ምክንያት ላይ ያልተመሠረተ የእንዲሁ ፍቅር ነው( unconditional love) የዮሐ 316
  • ራሱን መስዋዕት የመያደርግ ፍቅር ነው( self sacrificial love)
  • ራስን በመካድ የሚገለጥ ፍቅር ነው ( -Self denying)
  • በጊዜ ያልተወሰነ ፍቅር ነው( timeless love) የዮሐ 131
  • አባታዊ ፍቅር ነው Fatherly love፡፡ አባታዊ ፍቅር ስንል በሁለት መልኩ ማየት እንችለን፡፡ ያውም ለልጆቹ የሚራራና የሚቀጣ ፍቅር ነው፡፡ ዕብራዉያን 125-8)፡፡ እንግዲህ ይህ ፍቅር ሰዎች ለራሳቸው ስሜት ሲሉ እንዳሻቸው የሚጠመዝዙት ዓይነት ፍቅር ሳይሆን በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የእግዚአብሔር ፍር ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር አስተምሮአል። የእግዚአብሔርን ፍቅር መከተል ጉዳይ ከጌታ የተሰጠን ተዕዛዝ እንጂ ስንወደው የምናደርገው ሳንወደው ደግሞ የማናደርገው የምርጫ ጉዳይ አይደለም። አጋፔ የተባለው የእግዚአብሔር ፍቅር ለጠላትም ነፍስን አሳልፎ እስከስጠት የበረታና የጸና ነው። ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ የተባለበት ምክንያት ምንድነው? ሐዋሪያው ጳውሎስ በም ዕራፍ 13 ላይ ለዚህ የሚሆን 3 ዋና ዋና ምላሾን ይሰጠናል። በክፍል ሁለት እንመለስበታለን፡፡

1 comment: