Thursday, December 26, 2013

የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የመምራት ዜዴ


የቡድን  መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የመምራት ዜዴ
                          በፓስተር ሳሙኤል ሾንጋ

ክፍል አንድ
2 ጢሞ 316-17፤ዕብራውያን 412፤ሐዋ.1711
መግቢያ፡ የእግዚአብሔርን ቃል በግልም በጋራም ማጥናት ለመንፈሳዊ ህይወት እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በቃሉ በራሱ መመልከት እንችላለን። የእግዚአብሔርን ቃል በሚያጠኑና በማያጠኑ ሰዎችና አገልጋዮች መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩ ግድ ነው። ቃሉን ስናጠና ከሁሉ ይልቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለማድግ ካለን ዓላማ አንጻር መሆን እንዳለበት ነው።
አንድ ሰው በየቀኑ ተገቢውን ምግብ ካላገኘ ለተለያዩ በሽታዎች ከመጋለጡም አልፎ ሕይወቱንም ሊያጣ ይችላል። እንደዚሁም ሁሉ መንፈሳዊ ምግብና ወተት የሆነውን የጌታን ቃል በየዕለቱ የማይመገብ አማኝ በዚህ ዓለም ያሉ የተለያዩ ፈተናዎች ቢመጡበት በቀላሉ ተጠላልፎባቸው ልወድቅ ይችላል።
ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የሚያጠኑብቸው የተለያዩ መንገዶች ያሉ ሲሆን አንደኛው የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዜዴ ሲሆን ሁለተኛው የቡድን ወይም የጋራ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን መንገድ ነው።
የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማለት አንድ ግለሰብ ጊዜ ሰጥቶ ብቻውን በግሉ ቃሉን የሚያጠናበት መንገድ ሲሆን የቡድን ጥናት ግን በዓይነቱ ለየት የሚል ነው።
ሁሉም የክርሰቲና ሕይወት ተሞክሮ የሚመጣው ከግል ሕይወት ነው፡፡ አምልኮ፤ጸሎት፤ንስሐ፤የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ሁሉ የሚመነጨው ከግል ሕይወት ነው፡፡ የግል መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማለት አንድን ሰው ለብቻው አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ወስዶ ወይም መርጦ የሚያጠናበት ሂደት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለአማኙ የመንፈሳዊ ሕይወት ዕድገት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የቡድን የመጽሐፍ ቅዱሰ ጥናት መንገድ፡ ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በጋራ የማጥናት ዘዴ ነው፡፡
በቡድን ማጥናት ስንል በጋራ ማጥናት ማለታችን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በግል ካጠናን አይበቃም ወይ ለምንድነው በጋራ ማጥናት የሚያስፈልገው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል፡፡ ለዚህ ደግሞ መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚያስፈልገው ለእርስ በርስ መማማር ነው፡፡
  • የእግዚአብሔር ቃል በቡድን ማጥናትን ስለሚያበረታታ ነው፡፡ ሐዋ. 241-121711
  • መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና የተለያዩ ደረጃዎች እንደሚኖሩ መገንዘያስፈልጋል፡፡
    ለምሳሌ፡
  1. በብ፡ አሳቡን መመከት
  2. ማጥናት፡ መመልከት መተና መዛመድ
  3. ማሰላሰል፡ ቃሉ እንዳይረሳ በአእምሮ ማላሰና ማሰልሰል
  4. መጫወት፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስላነብብነው ቃ ማውራትና ማካፈ
  • የቡድን የመሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደግል ጥናት በተፈለገው ጊዜና ሁኔታ ሊከናወን አይችልም፡፡ ምክንቱም በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰዎች በአድ ላይ በመሰባብ የሚያደርጉት ስለሆነ ነው፡፡
    በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚታዩ ባሕሪያት
  • ቡድኑ ከ5- 7 ወይም ቢበዛ 9 አባላትን ያቀፈ ነው፡፡ አባላቱ ከ5-9 ሲሆኑ ይህ አነተኛ ቡድን የሚባል ሲሆን ከ9 በላይ ከሆነ ግን መካከለኛ ቡድን ይሆናል፡፡ የባላቱ ቁጥር ከ15 በላይ ከሆነ ደግሞ ከፍተኛ ቡድን ተብሎ ይጠራል፡፡ ስለዚህ የቡድን ጥናቱ አባላት ቁጥር ከ9 መብለጥ የለበትም ምክንያቱም የአባላቱ ቁር በበዛ መጠን አባላቱ አሳባቸውን የማሸራሸር እድል እየቀነሰ ይሄዳል፡፡
  • ሁሉም አባላት የንባብ ክፍሉን በየራሳቸው ይረዱታል፡፡ የተለያዩ አሳቦችንም ፈልቁበል፡፡
  • እያንዳዱ የቡድኑ አባል ለላው ያስተ( ያካፍላል) ከሌላውም ይማራል፡፡
  • የቡድኑ አባላት ተለያየዩ የመረዳት ደረጃዎች የሚኙ ናቸው፡፡
    ሳሌ
    - የቅርብ ጊዜ አማች ሆነው ብዙ የቃሉን መረዳት ያላገኙ ወይም ወደ ከፍተኛ የመረዳት ደረጃ ላይ ያደረሱ፡፡
    - ቃሉን ተግተው የሚያጠኑና በፈጣን እድገት ጎዳና ላይ ያሉ፡፡
    - በሕይወታው ያደጉና ጥልቅ የቃሉ እውቀት ያላቸው፡፡
  • ቡድን የመጽሐ ቅዱስ ጥናት ወደ ጥናቱ የሚመጡ የተለያዩ ባሕሪት ያላቸውን አባላት ያቀፈ ነው፡፡
    ለምሳሌ፡
    - ለመናገር የሚፈጥኑ (መሪውንም ለመቅደም የሚሞክሩ)
    - ረጅም ንግግር የሚወዱ
    - አዋቂ እደሆኑ የሚማቸው
    - በጥናት ወቅት አውደ ጥ የሆኑ
    - ዝምተኞች(የያወቁም ቢሆን ለመናገር የይቸኩሉ
    - ሲሶችና በቀላሉ የሚጎዱ
    - አልፎ አልፎ ብቻ የሚናገሩ
    - ያለዓላማ የሚመጡ(በይሉኝታ)
    - ዓይፋሮችና በሰው ፊት ለመናገር የሚፈሩ፤ የመናገር ልምዱም የሌቸው ሲሆኑ እነዚህን ሁሉ አንድ ላይ አዋዶ በቡድን መምራት የመሪውን ከፍተኛ ጥረትና ትዕግሥት የሚጠይቅ ነው፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከግል ጥናት እንዴት እንደሚለይ
  • በግል ሲጠና በራስ ተነሳሽነት ከየትኛው ታ በነሳት ማጥናት የሚቻ ሲሆን በቡድን ሲጠና ግን የጥናት ክፍሉ ማዕከላዊ በሆነ አካል ይመረጣል፡፡ ለምሳሌ የክርሰቲያናዊ ትምህርት አገልሎት ባለበት ቤተክርሰቲያን ያ የአገልሎት ክፍል የሚመርጠን ካሆነ ደግሞ በመጋቢው በኩ ይመረጥና ይዘጋጃል፡፡
  • በግል የተፈለገው ያህል ምዕራፍ ወይም አንቀጽ ማጥናት የሚቻሲሆን በአንድ ጊዜ የቡድን ጥናት ከአንድ አንቀጽ ይም ቢበዛ ከአንድ ምዕራፍ በላይ ማጥናት አይችልም፡፡ ምክንያቱም በቂ ጊዜ ስለማይኖርና የክፍሉ ጭብጥ አሳብ ሳይያዝ ተንጠልጥሎ ሰለሚቀር ነው፡፡
  • በግል ለሚጠናው ጥናት ሰዓቱን የሚወስነው ግለሰቡ ራሱ ሲሆን በቡድን ለሚጠናው ግን በድኑ ራሱ ይወስናል፡፡
  • የቡድን የመሐፍ ቅዱስ ጥናት በቤስብ ደረጃ፣ በቤተክርስቲያን ደርጃ፣ በአንድ መሥሪያ ቤት የሚሠሩ አማኞች ወዘተ ሰብሰብ ብለው የጌታን ቃል የሚያጠኑበት መንገድ ነው። ብዙ ወገኖች በዚሁ መንገድ በሚደረገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በሕይወታቸው አድገዋል፣ ቃሉን በስተማርም ሆነ በመስበክ ውጤታማ አገልግሎት መስጠት ወደ ሚችሉበት የዕድገት ደረጃ ሊደርሱ ችለዋል።
የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሁለት አቀራረቦች አሉት
  1. ዳይዳክቲቭ (Didactic)አቀራረብ ዜዴ፡ ይህ አቀራረብ ከውስን አሳብ ተነስቶ አጠቃላይ መርሆን የሚዳስስ ሲሆን ወጥ የሆነ የጥናት ክፍል የለውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህ ዓይነቱ አቀራረብ በሰለጠኑት አገሮች ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ ወጥ ለሆነና ተያያዥነት ላለው ጥናት አይረዳም፡፡
  2. ኢንዳክቲቭ (Inductive)አቀራረብ ዜዴ ፡ ይህ አቀራብ ዜዴ ከአጠቃላይ መርህ ተነሰቶ እውነታን በመዳሰስ ውስን ወደ ሆነው አሳብ የሚያደርስ የአቀራብ ዓይነት ነው፡፡ የኢንዳክቲቭ አጠናን ዜዴ ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ተነስቶ ወደ ድምዳሜና የሕይወት ተዛምዶ የሚያደርስ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ጊዜ ጥናቱ የሚጀምረው ከምንባቡ እንጂ ከተወሰኑ ውስን አሳቦች አይደለም፡፡ ውስንና የግል ጉዳዮች የሚዳሰሱት የንባብ ክፍሉ በተገቢው ሁኔታ ከተተነተነ በኃላ ያንን ትንተና መሠረት በማድረግ ነው፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የቡድኑን የውይይት አቅጣጫ ይጠቁማል፡፡ ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ እንዲናገር ለማድረግ ያግዛል፡፡
  • በሁሉም ጊዜ ከሚጠኑ የንባብ ክፍሎች በመነሳት የሚጠየቁ የጥያቄ ዓይነቶች አሉ፡፡
    እነርሱም ፡
  1. የምልከታ ጥያቄዎች፡ ክፍሉ ምን እደሚል ለመናገር የሚያስቸሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ክፍሉ ምን ይላል?ነጥቦችን ዘርዝር፤ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
  2. የትርጉም ጥያቄዎች፡ የክፍሉ አሳብ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የሚያስችሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በራስህ አባባል ገለጽ፤ ይህንን እንዴት ትረዳዋለህ የመሳሰሉት ጥያቄዎች ናቸው፡፡
  3. የትግበራ ወይም የተዛምዶ ጥያቄዎች፡ ተሳታፊዎቹ በንባብ ክፍሉ የተገኘውን አሳብ ከግል ሕይወታቸው ጋር እንዲያዛምዱት የሚረዳ ጥያቄ ነው፡፡ ይህ በሕይወት እንዴት ሊተገበር ይችላል? ሬው ጥናት ያገኘኸውን ለቡድንህ አካፍል፡፡ ይህ አራረብ ... (ምልከታ፤ ትርጉምና ተዛም) ወይም ...(መመልከት፤ መተርጎም ና ማዛመድ ) ሎ ይታወቃል፡፡ መሪው የጥናት ቡድኑን በሚመራበት ወቅት እነዚህን ሦስት ዓይት ጥያቄዎችን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዝግጅቱ የቀረቡት ጥያቄዎች ግልጽ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ መሪው ግን በራሱ አባባል ለቡድኑ አባላት ግልጽ ሊያደርግ ይችላል፡፡
  • የዚህ ዓይነት ጥናት ዋና ዓላማ ፍ ቅዱስ ራሱ እዲናገር ማድግ ነው፡፡

የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በተለይም የኢዳክቲቭ አቀራብ በምን እደሚያተኩር፡፡
  1. ምንባባዊ (Textual Study ) ፡ በምንባብ ክፍል ወይም በአንድ መጽሐፍ ላይ ያተኮረ ጥናት ነው፡፡ይህ ዓይነት አቀራረብ አንድን መጽፍ በሚባ ለማወቅ የሚዳ ነው፡፡ ለምሳሌ፤ የሮሜ መጽፍ፣ የኤፌሶን መጽሐፍ፣ የዘፍጥት መጽሐፍ ወዘተ ናቸው፡፡
  2. ርዕሳዊ ( Topical Study ) በአንድ ርዕስ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ይህኛው ደግሞ አስተምህሮችን ለመዳሰስ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ፡ ፍቅር፤ ቅድስና፤ በቤተ ክርስቲያ፤ ጸሎት፤ መስጠት ወዘተ የመሳሰሉት የጥናት ዝግጅቱ ትኩረት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
  3. ገጸ ባሕሪያዊ ( Character Study)፡ በንድ ሰው ሕይወት ላይ መሠረት ያደረገ ጥናት ሲሆን እግዚብሔር ብሉይ ኪዳም ሆነ በዲስ ኪዳ የተጠቀመባቸውን ሰዎች ሕይወት የሚተነትንና ከምሳሌነታቸው የሚያሰተምር ነው፡፡ ለምሳሌ፡ የዳዊት ሕይወት፤ የአብራሃም ሕይወት፣ የሴ ሕይወት፣ የጳዉሎስ ሕይወት፤ የየሱስ ሕይወት ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡





ክፍል ሁለት
የመሪው ሚና
  • በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት የቡድኑ መሪ ዋና ኤጄንት ስለሆነ ሊኖረው ስለሚገባው ሚና ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  • የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ በመሪው ምክንያት ሊያምርም ሊበላሽም ይችላል፡፡ ሁሉም የሚወሰነው በመሪው ማንነትና አቀራረብ ነው፡፡ ስለዚህ የመሪው ሚና እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
  • የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መሪን ሚና በሦስት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡
  1. የመሪው ሚና ከጥናት በፊት
  • ጥናት ከመካሄዱ በፊት መሪው ግሉ መጋጀት ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ የመሪውን ተሳትፎ ከአማጮቹ የተለየ ያደርገዋል፡፡ የቡድኑ አባላት ወደ ጥናቱ ከመምጣታው በፊት በሚያጠኑበት የምንባብ ከክፍሉ ተዘጋጅተውበት መምጣት ቢችሉ መልካም ነው፡ እነርሱ ቢዘጋጁም ባይዘጋጁም መሪው ግን የመዘጋት ግዴታ አለበት፡፡ መሪው ከጥናት በፊት እዴት ነው የሚዘጋጀው;
  • ስለ አገልሎቱ እዚአብሔርን በማመስገን ተግቶ መጸለይ አለበት፡፡
  • ስለያጠኑ ሰዎች ስለ እያንዳንዳቸው በጌታ ፊት መማለድ አለበት፡፡
  • በተቻ መጠን የቡድኑን አባላት ስለ ዕለቱና ስለ ጥናቱ ማሳሰብ አለበት፡፡
  • ናት ክፍሉን በግሉ አቀድሞ ማጥናት ይኖርበታል፡፡ የጥናት ክፍሉን በግሉ ሲያና በጥናት ዝግጅቱ ለተቀመጠው ጥቄ መልስ ከመስጠት ጠለቅ ለ መልኩ ዘጋጀት አለበት፡፡
  • የንባብ ክፍሉ የሚስተላልፈው መልእክት ምን እደሆነ መረዳትመቻ አለበት፡፡ ለዚህም የሚዱ መርጃዎችና ማጣቀሻዎችን መጠቀም ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ መዝገበ ቃላት(ባይብል ዲክሺኔሪ ) ፤የቃላት ማውጪያ ( ኮንኮርዳንስ)፤የመጽሐፍ ቅዱስ ካርታ ( አትላሰ) እና የማብራሪያ መጻሕፍት ( ኮሜንታሪ) ሲሆን የማራሪያ መጻሕፍት ሲጠቀም መሪው በጣም ከፍኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም በተሳሳተ መንገድ የተተረጎሙ በርካታ ኮሜንታሪዎች ስላሉ ሙሉ በሙሉ በእነርሱ መተማመን አያስፈልግም፡ሩ የሆኑ ኮሜንሪዎች ግን ለመሪው ዝግጅት በጣም ጠቃሚዎች ናቸው፡፡
  1. የመሪው ሚና በጥናት ወቅት
  • ከተሳታፊዎችም ሆነ ከመደበው ሰዓት ቀድሞ መገኘት አለበት፡፡ አንዳድ መሪዎች ቀድመው በመገት መልካም ምሳሌዎች ናው፡፡ ቀድሞ መገኘካታ ጥቅሞች አሉት፡፡ ለምሳሌ፡
  • ቦታው ለማስተካከል የአባላት ወበር አማመጥ ማካከል የሚቻለው ቀድሞ በመገኘት ነው፡፡ የጥናት ቦታን በጥናቱ ጊዜ ለማዘጋጀት ሞከር ዓቱን ያክንና መጨረሻ ለይ ሰውን ሁሉ ለጥድፊያ ያጋልጣል፡፡
  • ቦታው ለጥናት ቡድኑ አባላት ተስማሚና ጸጥታ ያው መሆኑን ማረጋጥ፡፡
  • የአባላት አቀማመጥ ዙሪያ ክብ እን ያስፈልጋል፡፡ መሪውም ሁሉንም አባላት ሊያይ በሚችልበት ቦታ መቀመጥ አለበት፡፡
  • በጥናቱ ቦታ በቂ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ፡፡
  • ጥናቱን ልክ በሰዓቱ መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ማንኛውንም ፕሮግራም በሰዓት አለመጀመር በሰዓት እንዳያልቅ ያደርጋል፡፡ ፕሮግራምን በሰዓት መጀመር ተሳታፊዎቹ በጥናት ፕሮግራሙ ላይ መተማመን እንደዲኖራቸው ከማድረጉም በላይ በሚቀጥለው ፐሮግራም በንቃት እንዲመጡ ያደርጋቸዋል፡፡
  • ጥናቱ በሰዓት ከተጀመረ ደግሞ በሰዓት ለመጨረስ መትጋት ያሰፈልጋል፡፡ ባላቱ ለመምጣት ከሚቸኩሉ ይልቅ ለመሄድ እደሚጣደፉ ምንጊዜም የታወቀ ነው፡፡
  • ጥናቱ ሲጀመር ተገቢውን መግቢያ መስጠት፡፡
  • ፍቅርን የሚገልጽ አጭር ሰላምታ መስ
  • ናቱን በጸሎት መክፈት
  • አጭር ክለሳ መስ(ጥናቱ የተያያዘ ስለሆነ) የባለፈውን ጥናት አሳብ ማሰታ
  • 2 ደቂቃ ላልበለጠ ጊዜ ስዕለቱ ጥናት አጭር መግለጫ መስጠት ምክንያቱም አድማቹ የዕለቱን የጥናት ርዕሰ ጉእምሮአቸው እንዲይዙና እንዲዘጋ ይረዳል፡፡
  • የዕለቱን ጥናት ስትጀምር ክፍሉን በግልጽ ሁኔታ አንብብ ወይም አባላቱ ተከፋፍለው ዲያነቡት ጋዛቸው፡፡
  • ቡድኑን በምትመራበት ወቅት ብዙ እንዳትናገር ጠንቀቅ፡፡ የማጠቃለያ አሳብ መስጠት ካልሆነ በቀር ጥያቄውን ለአባላቱ አቅርብላቸውና አንተም አብረህ ተሳታፊ ለመሆን ሞክር፡፡
  • የቡድኑ አባላት በጥናቱ እንደሚገባ መሳተፋቸውን አረጋግጥ፡፡ ጥት ሰዎች ብቻ የሚሳተፉበትና የቀሩት ደግሞ ሰሚዎች ብቻ እሆኑ ተከታተል፡፡
  • ራስህን እንደ አስተማሪ አቁጠር፡፡
  • ጥያቄዎች ሲነሱ መልስ ከመስጠትህ በፈት ተሳታፊዎች ለቀረበው ጥያቄ መልስ ዲሰጡት አበረታታቸው፡፡ የተሳታዎች መልስ አርኪ ካሆነ አንተ መልስ ስጥበት፡፡ ጥያቄው ከባድ ከሆነ ደግሞ ሌሎችን ለማማከር ተስፋ ስጥ እንጂ ያሆነ ልስ እዳትሰጥ ተጠንቀቅ፡፡ ሉን ጥያቄ የመመለስ ግዴታ ሊኖርብህ ይችም፡፡
  • በጥናት ቅት የቁጣና የተግሣጽ ባሕሪይ እንዳይታይብህ ተጠንቀቅ ይልቁንም ሁሉን በፍቅር ተቀበል፡፡
  • አባላት አሳብ ሲሰጡ ከንባብ ክፍሉ አሳብና ከአውዱ እወጡ ተከታተል ምክንያቱም የአሳብ መልቀቅ ወይም ከርዕስ ውጭ መሆን የጥናን መድሻ ያበላሸዋል፡፡
  • የጥናት ክፍሉን ጥያቄ አባላቱ ፊት እንዳታጠና ተጠንቀ፡ ይልቁንም አስቀድ በአእምሮህ ተዘጋጅተህበት መምጣ ያስፈልጋል
  • በጥናት ጊዜ ክርክር እንዳይኖር ለመቆጣጠር ሞክር፡፡ የሚከራሩ ሰዎች በክርክራቸው ለመቀጠል የሚፈልጉ ከሆነ ጉዳን ትተው ወደ ሌላ ነጥብ እዲሸሩ በጥበብና ዜዴን መጠቀም፡፡
  • እያንዳንዱ ተሳታፊ የሚያቀርበው አሳብ አክብር፡፡ አሳብ አቅራቢውም አበረታታ፤ የሚያቀርበው አሳብ ልክ ካሆነ በፍቅር አስረድተህ መልሰው፡፡
  • በርካታ ጥቅሶችን ከተለያዩ ቦታዎች መጥቀስ ለአሳብ መልቀቅ ( ለአውደ ወጥ) ንስኤ ስለሚሆን ከፍኛ ጥንቃቄ አድርግ፡፡
  • አባላቱ በተቻለ መጠን መጽፍ ቅዱስ ይዘው እንዲመጡ አበረታታ፡፡
  • ጠጥረሩነና መለከካመም የሀሆነ መደመምደመሚየያ አደድረርገግ
  • ከጥናት ክፍሉ የተገኙ አሳቦችንና ዋና አሳቡን ጠቅለል አድርገህ ለአባላቱ አስጨብጥ
  • በጥናቱ ተገኝተው አሳባቸውን ያካፈሉትን ሌሎችንም በአጭር ቃል አመስግናቸው፡፡
  • በሚቀጥለው የጥናት ክፍል ተዘጋጅተውበት እንዲመጡ አሳስባቸው የንባብ ክፍሉንም ንገራቸው፡፡
  • ከቤተ ክርሰቲያን የሚተላለፍ መልእክት ካለ ባጭሩ ተናገር፡፡
  • የፀሎት ርዕስ የሚሰጥ ሰው ካለ ተቀበል፡፡ የይሁን እንጂ እንዳይንዛዛና የሚቸኩሉ አባላት ልብ እንዳያንጠለጥል አድርግ፡፡ ፕሮግራሙን በጸሎት ዝጋው፡፡
  1. የመሪው ሚና ከጥናት በኃላ
የመሪው ሥራ ከጥናቱ በኃላም የሚቀጥል ነው፡፡ ስለዚህ የቡድን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን የመምራት አገልግሎቱን ካጠናቀቀ በኃላ ሊያደርጋቸው የሚገባቸውን ነገሮች በአጭሩ እንመልከት፡፡

  • አባላቱ ጥናቱን በተገቢ ሁኔታ ማጥናት አለማጥናታቸውን ፤በሰዓት መገኘት አለመገኘታቸውን፤መሪው ራሱ በሰዓት ጀምሮ በሰዓት መጨረስ አለመጨረሱን እና ሌሎች ነጥቦችን መሠረት በማድረግ አጠቃላይ የጥናቱን ሁኔታ መገምገም ይኖርበታል፡፡
  • መሪው በጥናት ወቅት የተቸገረባቸው እና መፍትሔ ለመስጠት ያልቻለባቸው ጉዳዮች ካሉ ለቤተክርስቲያን ሪፖርት ማድረግ የጋራ መፍትሔ ሊፈልግ ይችላል፡፡
  • በተቻለ መጠን ረዳት ሊሆን የሚችል ሰው ማዘጋጀት ፡፡ መሪ ተተኪ ሊያፈራ ከቻለ አገልግሎቱ ከሁሉም አንጻር እድገት እያሳየ ሊሄድ ይችላል፡፡
  • ከጥናት ቡድኑ አባላት ጋር በጥሩ ግንኙነትና መቀባበል ቀጥል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለሁሉም በሁሉም የአገልግሎት ወቅት ጸጋውንና ምሕረቱን ያብዛ፡፡ አሜን፡፡ 

No comments:

Post a Comment